قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Відкрити в Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
914
Підписники
-324 години
-177 днів
+5330 днів
Архів дописів
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
ፖለቲከኞች የባሩድ እና የደም ሽታ ይወዳሉ፣ ለዚህ ፍላጎታቸው አዕላፍ ነፍሶችን ይቀጥፋሉ። videoን እዩትና ትምህርት ውሰዱበት !!
ሀገራችንን ጀሊሉ ሰላም ያድርግልን።
Repost from رعــايــة الــقـلــوب
⇨እማ‼
≣አንቺን መንከባከብ አለብኝ ግዴታ
ችዬም ባልከፍለው የእናትነት ውለታ
አልጣሽ ከጎኔ ትንሽም ለአፍታ
እንዲህ ባረግላት ብዬ በሀሳብ ብነዳ
ህሊናም ነበረኝ ችግርሽን ሚ'ረዳ
ዱኒያ እደሆን የሆነች ቀዳዳ
እጅ አጠረኝ አንቺን የሚረዳ
እንዲሁ እኖራለሁ ውስጤ እያነባ
መርዳትስ አልቻልኩም ወዴት ሆኜ ልግባ
ልቤ ጭንቅ አለው አንቺን እያሰበ
ምንም ማረግ አልችል ወዴትም አልገባ
ዱአ አርጊ እማ እጆችሽን ዘርጊ
አማክሪልኝ እስቲ ወደ አላህ ተጠጊ
ሰላምሽን ያብዛው እምዬ እናቴ
አንገት ቢያስደፋኝ አሁን ላይ ማጣቴ
በጣም እወድሻለሁ ከውስጤ ከአንጀቴ
ሰላም! ብዬሻለሁ በስንኝ ቤቴ፡፡
በአላህ ተስፋ አረጋለሁ አስደስትሻለሁ እማ
ስላልቻልኩ አኮ ነው ትንሽ ቆይኝማ
ያንቺን ደስታ እንጂ ክፉሽን አልስማ፡፡
---------------------//---------------------
رب ارحمهما كما ربياني صغيرا
Repost from SadatKemal Abu Meryem
ተውሒድ የነብያት ሁሉ ጥሪ ነው። ተውሒድ ማለት አላህን በብቸኝነት፣ ያለ ምንም ተጋሪ ማምለክ ነው። ተውሒድን ከነምታስፈርዳቸው ነገሮች ይዘው የሞቱ ሰዎች ጀነት መኖሪያቸው ናት። አላህ ሙስሊሞች ሆናችሁ ቢሆን እንጂ እንዳትሞቱ ብሎናል። አላህ ሙስሊሞች ሆነው ከሚሞቱት ያድርገን።
ታሞ ነበረ ዳነ፤ አጥቶ ነበረ አገኘ፤ አዝኖ ነበረ ሳቀ! ለመባል አላህ ያብቃችሁ፤ ያብቃን።
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
ለማንም አይበጅም ክፉ ነው ጦርነት
የሰው ደም ያፈሳል ያስዘርፋል ንብረት
ህይወት ያበላሻል ያስከትላል ፀፀት
ሀገርን ያወድማል ይጎትታል ክስረት
እንኳን ተጨምሮ በዚህ ላይ ጦርነት
በጣም አስፈርቷል የኑሮው ውድነት
ሰላም ይሁንልን ለሁሉም በአንድነት
= t.me/Abu_lmran_Alaseriy
ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ።
የጀነት በር ጠባቂ መላዒካ ረድዋን ይባላል፡፡
Repost from ተውሒድ እና ሱና (በጭረቻ)
⬇️ ፈተናዉ በዛሳ??⬇️
▪️ፈተናዉ በዛሳ ምድነዉ ችግሩ?
▪️ምንስ አጥፍተን ነዉ ምድነዉ ሚስጥሩ?
▪️ ለምን በሙስሊም ላይ ይህ ሁላ ፈተና?
▪️ የሚደራረበዉ ምን አጠፋንና?
▪️ ብሎ ይጠይቃል ምንም ያልተረዳዉ
▪️ ለኒህ ጥያቄዉች መልሱማ ግልፅ ነዉ
▪️ መከራ ሚመጣዉ በራሳችን ጥፋት
▪️ መሆኑን ነግሮናል የአርሹ ባለቤት
▪️ከባባድ ወጀሎች በሀገራችን ስፍቶ
▪️ማህበረሰቡ ሽርክ ላይ ተዘፍቆ
▪️ተዉሂድን እረስቶ እርግፍ አርጎ ትቶ
▪️ቀንና ሌሊቱን ሽርክ እየፈፀመ
▪️ የአሏህን መብት ለሰዉ እየሰጠ
▪️ ለጅኑ ለቆሌዉ እጁን እየሰጠ
▪️ችግር ስመጣብን ጠቋይ ስር እየሄድን
▪️ በደል የሆነዉን ሽርክ እየፈፀምን
▪️እዴትስ ይገኛል የአሏህ እርዳታ
▪️በሱላይ አጋርተን በአለማቱ ጌታ
▪️ ደግሞ በዚህ በኩል ቢድዓን አምጥተን
▪️ሱና ያልሆነዉን አዲስ ነገር ፈጥረን
▪️ቀደምቶች ሰለፎች መፅሞ የማያዉቁት
▪️ በዚህኛዉ በኩል በዘር ፖለቲካ እየተበላላን
▪️ባስቀያሚ ቃላይ እየተወጋጋን
▪️ እዴትስ ይገኛ የጌታችን ነስር
▪️ አመፀኞች ሆነን እዝነት እርቆብን
▪️ እናም የአሏህ ነስር ዝም ቡሎ አይገኝም
▪️የአሏህን ነስር የምንሻ ከሆነ
▪️ ወደሱ እንመለስ እንራቅ ከጥፋት
▪️ በሀቅ እናምልከዉ በብቸኝነት
▪️ እሱን እንገዛ ካላንድ ጣወት
▪️ ሽርክን አሽቀጥረን ወዲያ እንወርዉረዉ
▪️ በተዉሂድ አብበን በሱና እናድምቀዉ
▪️ ልክ ሱና መስሎ ከመጣዉ ብድዓ
▪️ኢስላም ከማያዉቀዉ ካዲስ መጤ ነገር
▪️ አምጥተን ሱና ነዉ ብለን ከመናገር
▪️ መላቀቅ አለብን ከንዲህ አይነት ነገር
▪️የዛኔ ይመጣል የአሏህ እርዳታ
▪️እሱ ይረዳናል የአለማት ጌታ
▪️ የበላይ አድርጎ ነስር የሰጠናል
▪️ የኢስላም ጥላትን ይበቀልልናል
▪️ ጌታችን ቃል ገብቷል ቃሉን አያፈርስም
▪️የጌታችን ነስር ይመጣል አይቀርም
~~
▪️ያረቢ ያአሏህ አተ በቃ በለን
▪️ለሙስሊም ባሮችህ ሰላምን አምጣልን
▪️አማኝ ባሮችህን ከኒያ ካሀዲወች አተ ጠብቅልን
▪️የኢስላም ጥላት እኒያ ካሀዲወች
▪️ሙስሊሙን ለመጉዳት ለሚሰሩ ሰወች
▪️የንፁሀኑን ደም ለሚያፈሱ ሰወች
▪️ያረቢ ተበቀል እኒያን ከሀዲወች
▪️ያረብ ያአሏህ ድልን አጉናፅፍን
▪️በኒያ ካሀዲያን ላይ የበላይ አድርገን
እሙ አይመን
Repost from 🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
አንዲት እህት እንዲህ ትላለች፦
«ባሌ ከእኔ ውጪ ሶስት ሴቶችን እንዲያገባ እመኛለሁ፤ ምክንያቱም አንድ ቀን ለባሌ፡ ሶስቱን ቀን ደግሞ ጌታዬን በማምለክ አሳልፋለሁ።»
ዓይኖች የሚያነቡበት ንግግር...(እኔ አላልኩም¿)
https://t.me/https_Asselfya
Repost from አቡ ዓብደሏህ(أبو عبد الله الولوي)🇸🇦
🌿 بِسْمِ اللهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ 🌿
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
🎙️✨ አስደሳች ኸበር ለእውቀት ፈላጊዎች! ✨🎙️📚 ለወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና በአካባቢው ላሉ የእውቀት ፈላጊዎች የተዘጋጀ አዲስ የደርስ ፕሮግራም! ━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🎙️① አንደኛ የደርስ ማስታወቂያ📚 ኪታብ፦ العقيدة الواسطية አቂደቱል ዋሲጢያህ 📚 የኪታቡ አዘጋጅ፦ شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ 🎙️ ትምህርቱን የሚሰጡት፦ فضيلة الشيخ محمد آمين حفظه الله 👉 የተከበሩ ሸይኽ ሙሐመድ አሚን ደበቅ ሀፊዘሁሏህ 📅 የትምህርቱ ቀናት፦ ከማክሰኞ እስከ ሐሙስ ዘወትር ━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🎙️ ② ሁለተኛ የደርስ ማስታወቂያ📖 ኪታብ፦ الأربعون النووية (አርበዒን አል-ነወዊ) ✍️ የኪታቡ አዘጋጅ፦ الإمام يحيى بن شرف النووي رحمه الله ኢማም አል-ነወዊ ረሒመሁሏህ 🎙️ ትምህርቱን የሚሰጡት፦ أبو فواز حفظه الله 👉 አቡ ፈዋዝ(ጁሐር)ሀፊዘሁሏህ 📅 የትምህርቱ ቀናት፦ ከቅዳሜ እስከ ሰኞ ዘወትር ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📍 የትምህርቱ ቦታ፦ 🕌 ወሎ ዩኒቨርሲቲ ሰለፊያ ተማሪዎች መስጅድ — መስጅደል አዝር
⏰ ሰዓት፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻ━━━━━━━━━━━━━━━━━━
⚠️📢 ተንቢህ! ተንቢህ! ተንቢህ! 📢⚠️🔔 ይህንን የእውቀት እድል እንዳታሳልፉ! 📖 ﴿وَقُلْ رَبِّ زِدْنِي عِلْمًا﴾ 🌸 «ጌታዬ ሆይ! እውቀቴን ጨምርልኝ» 📖 [ጣሃ፡ 114] 📚 የእውቀት ፈላጊ ሆይ! እውቀት የሚጨመረው በመፈለግ ነው፤ ይህን ዕድል አታምልጥ! 🔥 📢❤️ ይህንን የዒልም መልእክት ለሌሎች የእውቀት ፈላጊዎችም SHARE አድርጉ! 🤲 አላህ ከእውቀት የሚጠቅመን ያድርገን። بارك الله فيكم ونفع بكم 🌿 📲🔥 የTelegram ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ 👉 https://t.me/abuabdelah123 👈 📢 JOIN • SHARE • ለሌሎችም አስተላልፉ! 🌿
✅ አንድ ግለሰብ (በተናጥል) ለማክፈር ቅድመ መስፈርቶች ከተሟላ እና ለማክፈር የሚከለክሉ ነገሮች ከተወገዱ በኋላ ነው።እነሱም 4 ናቸው፦
1⃣ ለማክፈር መስፈርት በምርጫው ወይም በፍላጎት ማድረግ(الختيار)፤ከማክፈር የሚከለክለው መገደድ(الإكراه)።
2⃣ ለማክፈር መስፈርት ድርጊቱ አስቦ (تقصد)መፈፀም፤ከማክፈር የሚከለክለው ሳያስበው በስህተት (عدم تقصد)መፈፀም።
3⃣ ለማክፈር መስፈርት ተግባሩ በእውቀት (العلم)መተግበር፤ከማክፈር የሚከለክለው አለማወቅ(ጅህልና)(الجهل)
4⃣ ለማክፈር ቦታ የማይሰጠው የተሳሳተ ትርጓሜ(التأويل غير الساءغ)፤ ለማክፈር የሚከለክለው ቦታ የሚሰጠው (የሚመች) የተሳሳተ ትርጓሜ(التأويل الساءغ)።
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
እነዚህን 7ት ሴቶች እንዳታገባ
1. አል-አናናህ (الأنانة) - "ሁልጊዜ አማሪሪዋ"
ይህች ሴት በማንኛውም አጋጣሚ ማማረር እና ማጉረምረም የምታበዛ ናት። ያላት ነገር አያስደስታትም፤ ሁልጊዜም ያልተሟላላት ነገር እንዳለ ይሰማታል። በትንሽ በትልቁ ራሷን እንደታመመች በማስመሰል (በማቃሰት) የባሏን ሀሳብ እና ጉልበት ትጨርሳለች።
2. አል-መናናህ (المنانة) - "ውለታ ቆጣሪዋ"
ለባሏ ወይም ለቤተሰቡ ያደረገችውን ማንኛውንም ጥሩ ነገር ሁልጊዜ የምታነሳ እና የምትመፃደቅ ናት። "እኔ እንዲህ አድርጌልህ፣ የኔ ቤተሰቦች እንዲህ ረድተውህ..." እያለች በተፈጠረችው ክፍተት ሁሉ ባሏን በውለታዋ ልታሸማቅቀው ትሞክራለች። በእስልምና ውለታ መቁጠር (መን) መልካም ስራን ከሚያበላሹ ነገሮች አንዱ ነው።
3. አል-ሐናናህ (الحنانة) - "ወደ ኋላ ናፋቂዋ"
ይህች ሴት አሁን ካለችበት ትዳር ይልቅ ትኩረቷ እና ልቧ ያለው ያለፈ ህይወቷ ላይ ነው። ከዚህ ቀደም አግብታ ከነበረ የቀድሞ ባሏን፣ ወይም ደግሞ የቤተሰቦቿን ቤት ሁልጊዜ በናፍቆት እያነሳች አሁን ያለችበትን የትዳር ህይወት እና ባሏን ዝቅ የምታደርግ ናት።
4. አል-ሐዳቃህ (الحدّاقة) - "አይኗ ያረፈበትን ሁሉ ፈላጊዋ"
በአጭሩ ቁሳቁስ ወዳድ (Materialistic) የሆነች ሴት ናት። አይኗ ያረፈበትን እና ያየችውን እቃ ሁሉ እንዲገዛላት ትፈልጋለች። የባሏን አቅም እና የኪስ ሁኔታ ከግምት ሳታስገባ፣ "ይሄ ካልተገዛልኝ፣ ያንን ካላመጣህልኝ" በማለት ባሏን በፋይናንስ እጅግ ታስጨንቀዋለች።
5. አል-በራቃህ (البرّاقة) - "ለውጫዊ ውበቷ ብቻ ተጨናቂዋ"
ሁለት ትርጉሞች አሏት፦ አንደኛው፣ አብዛኛውን ጊዜዋን በመስተዋት ፊት በማሳለፍ ለውጫዊ ገፅታዋ (ለሜካፕ እና ለመዋቢያ) ብቻ ከልክ በላይ የምትጨነቅ እና የቤት ውስጥ ሀላፊነቷን የምትዘነጋ ናት። ሁለተኛው ትርጉም ደግሞ፣ ምግብ ሲቀርብላት ሁልጊዜ የምትነቅፍ እና በምንም ነገር የማትረካ ማለት ነው።
6. አል-ሸዳቃህ (الشدّاقة) - "ለፍላፊዋ"
በጣም ብዙ የምትናገር፣ ዝምታን የማታውቅ ችግር ሲፈጠር ጎረቤት እስኪሰማ የምትጮህ እና በየሰዉ ጉዳይ የምትገባ ናት። በንግግሯ የሰውን ሚስጥር የምታወጣ፣ ሐሜት የምታበዛ እና ምላሷ ባሏን የሚጎዳ (የማይገታ) ነው።
7. አል-ሙኽተሊዓህ (المختلعة) - "ሁሌም ፍቺ ጠያቂዋ"
በጣም ቀላል እና መፍትሄ ሊያገኙ በሚችሉ የትዳር ውስጥ አለመግባባቶች ሁሉ ትዕግስት አጥታ "ፍታኝ! ካልፈታኸኝ..." እያለች ቃለ-ፍቺን (ጦላቅን) እንደ ማስፈራሪያ እና የዘወትር ዛቻ የምትጠቀም ናት። ነብዩ (ሰለሏህ ወአለይሂ ወሰላም ) ያለ በቂ የሸሪዓ ምክንያት ፍቺን የምትጠይቅ ሴት የጀነትን ሽታ አታገኝም ብለዋል።
እነዚህን 7ት ሴቶች እንዳታገባ
1. አል-አናናህ (الأنانة) - "ሁልጊዜ አማሪሪዋ"
ይህች ሴት በማንኛውም አጋጣሚ ማማረር እና ማጉረምረም የምታበዛ ናት። ያላት ነገር አያስደስታትም፤ ሁልጊዜም ያልተሟላላት ነገር እንዳለ ይሰማታል። በትንሽ በትልቁ ራሷን እንደታመመች በማስመሰል (በማቃሰት) የባሏን ሀሳብ እና ጉልበት ትጨርሳለች።
2. አል-መናናህ (المنانة) - "ውለታ ቆጣሪዋ"
ለባሏ ወይም ለቤተሰቡ ያደረገችውን ማንኛውንም ጥሩ ነገር ሁልጊዜ የምታነሳ እና የምትመፃደቅ ናት። "እኔ እንዲህ አድርጌልህ፣ የኔ ቤተሰቦች እንዲህ ረድተውህ..." እያለች በተፈጠረችው ክፍተት ሁሉ ባሏን በውለታዋ ልታሸማቅቀው ትሞክራለች። በእስልምና ውለታ መቁጠር (መን) መልካም ስራን ከሚያበላሹ ነገሮች አንዱ ነው።
3. አል-ሐናናህ (الحنانة) - "ወደ ኋላ ናፋቂዋ"
ይህች ሴት አሁን ካለችበት ትዳር ይልቅ ትኩረቷ እና ልቧ ያለው ያለፈ ህይወቷ ላይ ነው። ከዚህ ቀደም አግብታ ከነበረ የቀድሞ ባሏን፣ ወይም ደግሞ የቤተሰቦቿን ቤት ሁልጊዜ በናፍቆት እያነሳች አሁን ያለችበትን የትዳር ህይወት እና ባሏን ዝቅ የምታደርግ ናት።
4. አል-ሐዳቃህ (الحدّاقة) - "አይኗ ያረፈበትን ሁሉ ፈላጊዋ"
በአጭሩ ቁሳቁስ ወዳድ (Materialistic) የሆነች ሴት ናት። አይኗ ያረፈበትን እና ያየችውን እቃ ሁሉ እንዲገዛላት ትፈልጋለች። የባሏን አቅም እና የኪስ ሁኔታ ከግምት ሳታስገባ፣ "ይሄ ካልተገዛልኝ፣ ያንን ካላመጣህልኝ" በማለት ባሏን በፋይናንስ እጅግ ታስጨንቀዋለች።
5. አል-በራቃህ (البرّاقة) - "ለውጫዊ ውበቷ ብቻ ተጨናቂዋ"
ሁለት ትርጉሞች አሏት፦ አንደኛው፣ አብዛኛውን ጊዜዋን በመስተዋት ፊት በማሳለፍ ለውጫዊ ገፅታዋ (ለሜካፕ እና ለመዋቢያ) ብቻ ከልክ በላይ የምትጨነቅ እና የቤት ውስጥ ሀላፊነቷን የምትዘነጋ ናት። ሁለተኛው ትርጉም ደግሞ፣ ምግብ ሲቀርብላት ሁልጊዜ የምትነቅፍ እና በምንም ነገር የማትረካ ማለት ነው።
6. አል-ሸዳቃህ (الشدّاقة) - "ለፍላፊዋ"
በጣም ብዙ የምትናገር፣ ዝምታን የማታውቅ ችግር ሲፈጠር ጎረቤት እስኪሰማ የምትጮህ እና በየሰዉ ጉዳይ የምትገባ ናት። በንግግሯ የሰውን ሚስጥር የምታወጣ፣ ሐሜት የምታበዛ እና ምላሷ ባሏን የሚጎዳ (የማይገታ) ነው።
7. አል-ሙኽተሊዓህ (المختلعة) - "ሁሌም ፍቺ ጠያቂዋ"
በጣም ቀላል እና መፍትሄ ሊያገኙ በሚችሉ የትዳር ውስጥ አለመግባባቶች ሁሉ ትዕግስት አጥታ "ፍታኝ! ካልፈታኸኝ..." እያለች ቃለ-ፍቺን (ጦላቅን) እንደ ማስፈራሪያ እና የዘወትር ዛቻ የምትጠቀም ናት። ነብዩ (ሰለሏህ ወአለይሂ ወሰላም ) ያለ በቂ የሸሪዓ ምክንያት ፍቺን የምትጠይቅ ሴት የጀነትን ሽታ አታገኝም ብለዋል።
https://t.me/Sobabilalmesjid
https://t.me/Sobabilalmesjid
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የጁሙዐ የመጀመሪያው አዛን ጉዳይ
~
የጁሙዐ አዛን መሰረቱ አንድ ነው። እሱም ኸጢቡ ሚንበር ላይ ሲወጣ የሚደረገው ነው። በነብዩ ﷺ ዘመን፣ በአቡበክርና በዑመር ዘመን በዚሁ ሁኔታ ነበር የቀጠለው። ቀደም ብሎ የሚፈፀመው ሌላኛው አዛን የተጨመረው በዑሥማን ነው። ተጨማሪ አዛን ያዘዙት የመዲና ህዝብ ቁጥር በመጨመሩና ከተማዋ በመስፋቷ የተነሳ አዛኑ ስለማይደርሳቸው ነው። ይሄኛው አዛን የሚደረገው መስጂድ ውስጥ አልነበረም። ይልቁንም ዘውራእ በተባለ የገበያ ቦታ ነበር።
ዛሬ ይህንን አዛን ለመፈፀም #አንዳንዴ ካልሆነ በስተቀር በቂ ምክንያት የለም። ምክንያቱም :-
* መዲና ያኔ ጁሙዐ የሚሰገድበት አንድ መስጂድ ብቻ ነበር የነበረው። ህዝብ ቁጥር ሲጨምርና ቤታቸው እየራቀ ሲሄድ ጊዜ በመስጂዱ በር ላይ የሚደረገው አዛን አይሰማቸውም ነበር። ዛሬ ላይ በአንድ ከተማ ውስጥ በርካታ ጅሙ0 የሚሰገድባቸው መስጂዶች ሲኖሩ ሁኔታው ከዚያን ዘመኑ ይለያል።
* እንደገና ዛሬ ላይ ከፊሎቹ ወይም ብዙዎቹ መስጂዶች ድምፅ ማጉያ ስለተገጠመላቸው ድምፃቸው ከርቀት ይደርሳል። ይህም ዑሥማን ሁለተኛ አዛን የጀመሩበት ምክንያት በድምፅ ማጉያው ተሳካ ማለት ነው።
እውነታው ይህ ከሆነ በነብዩ ﷺ አዛን ላይ መብቃቃት ይገባል። በዑሥማን የተጨመረውን አዛን ለመፈፀም ዑሥማን የጀመሩበት ሰበብ መኖር አለበት። ይሄ መነሻ በሌለበት የሚጨመረው አዛን የዑሥማን አዛን አይደለም።
.
ከሸይኹል አልባኒይ ረሒመሁላህ አልአጅዊበቱ ናፊ0ህ ኪታብ ተጨምቆ የቀረበ
ከገፅ 13 ጀምሮ ይመልከቱ። ሃሳብ ያለው ነጥቡን ጠብቆ በአደብ መሰንዘር ይቻላል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 18/2015 )
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
اللهم إنا نسألك خير هذا اليوم فتحه ونصره ونوره وبركته وهُداه، ونعوذ بك من شرِّ ما فيه و شرِّ ما بعده.
يا حي يا قيوم برحمتك نستغيث أصلح لنا شأننا كله ولا تكلنا لأنفسنا طرفة عين.
ربنا آتنا من لدنك رحمة وهيئ لنا من أمرنا رشدا.
"أعوذ بكلمات الله التامات التي لا يجاوزهن بر، ولا فاجر من شر ما خلق، وذرأ وبرأ ،
ومن شر ما ينزل من السماء، ومن شر ما يعرج فيها،
ومن شر ما ذرأ في الأرض، ومن شر ما يخرج منها،
ومن شر فتن الليل والنهار،
ومن شر كل طارق إلا طارقا يطرق بخير، يا رحمن "،
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
እጅህ ላይ ምን አለ?
በጣም የሚገርመኝ አሏህ ሙሳን የጠየቀው ጥያቄ ነው። “ሙሳ ሆይ! ይህች በቀኝ እጅህ ያለችው ምንድናት?” ከሌለህ ነገር መነሳት አትችልም። ከህልም ዓለምህ ወደ ስራው ዓለምህ የሚያሸጋግርህ ነገር አሁን ያለህ ነገር ነው። ሙሳ እጅ ላይ የነበረው ብትር ነበር። የሚደገፍበት፣ ለፍየሎቹ ቅጠል የሚያረግፍበትና ሌሎች ጉዳዮችን የሚፈፅምበት። አንዳንድ የተፍሲር ሊቃውንት ምን እንደሚሉ ታውቃላችሁ? “አንዳንዴ አላህ ህይወትህ ውስጥ ተዓምር የሚሰራው እጅህ ላይ ባለው ነገር ነው። ለሙሳ በብትሩ ተዓምር እንዳሳየው ሁሉ።”
ባለህ ነገር ተንቀሳቀስ፣ ወደፊት ተራመድ !!
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
