قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Open in Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
908
Subscribers
-324 hours
-157 days
+4830 days
Posts Archive
ከአገር መፍረስ ባሻገር
~
አገር እንድትፈርስ የሚመኙ፣ አገር ለማፍረስ የሚጥሩ፣ ለአገር አፍራሾች ድጋፍ የሚሰጡ ብዙ ሰዎች አሉ። ወንድሜ ሆይ! እውነት በሃገር መፍረስ የምታተርፍ መስሎህ ነው? ለመሆኑ አገር ሲፈርስ ምን ምን ሊከሰት እንደሚችል አሻግረህ ተመልክተሃል? ወይስ በሆኑ አካላት ላይ ያለህ ጥላቻና ቁጭት በሩቅ እንዳትመለከት ሸፍኖብሃል? ወንድሜ አገር ዳቦ አይደለም ፤ እንደዋዛ ቆራርሰህ በመካፈል አትገላገልም።
* ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ይፈናቀላሉ። እንኳን አገር ፈርሶ በብሄር ግጭትና ጥቃት ብቻ የሚሊዮኖች ህይወት ተመሰቃቅሏል። ምናልባት አንተ ከሚፈናቀሉት ባትሆን እንኳ ራስህን በነሱ ጫማ ላይ አድርገህ ተመልከት።
* ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ትዳር ይፈርሳል። ከሌላ ብሄር ጋር የተጋቡ ወገኖቻችን እጅግ ብዙ ናቸው። ይሄ ዘር እየለየ የሚገድል ትውልድ የሚተዋቸው እንዳይመስልህ። ስንት ቤተሰብ እንደሚበተን ተመልከት።
* ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ንብረት ይወረሳል። እንኳን አገር ፈርሶ ሰላም በመጥፋቱ ብቻ የስንቱ ምስኪን ንብረት በተለያዩ ክልሎች በጉልበተኛ ተነጥቋል!
* ሃገር ሲፈርስ እዚያም እዚህም መቋጫ የሌለው የድንበር ግጭት ይነሳል። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው በሶማሊና በኦሮሞ የድንበር ግጭት ከሚሊየን በላይ ህዝብ የተፈናቀለው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው አፋርና ዒሳ በየጊዜው የሚጋደለው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው ዘጠኝ መቶ ሺ አካባቢ የጌዲዎ ህዝብ የተፈናቀለው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው የወሎ ኦሮሞና የሸዋ አማራ የሚጋጨው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው በደቡብ ክልል የተለያዩ ህዝቦች መካከል ግጭት የሚቀሰቀሰው። በአንድ መንግስት ስር ሆነን ነው "ወሎ ኦሮሞ ነው"፣ "ወልቃይት፣ ደራ፣ በረራ፣ መተከል አማራ ነው" የሚል ጩኸት የምንሰማው፡፡ ሃገር ከፈረሰ እነዚህ ጩኸቶች ዛሬ ከምናየው በላይ ሚሊዮኖችን የሚበላ እሳት ይቀሰቅሳሉ።
* ሃገር ሲፈርስ እልፍ አእላፍ ነፍስ ይጠፋል። ከላይ የተጠቀሱት በሙሉ መጨረሻቸው እልቂት ነው።
* ምናልባት መልኩ ይቀየር ካልሆነ በስተቀር በሃገር መፍረስ ጭቆና የሚቀር፣ ለድሃ ቀን የሚወጣ እንዳይመስልህ። ወላሂ! ዘር እየለየ፣ ሃይማኖት እየመረጠ በሚገድል ቡድን፣ ከርሱን በሚያስቀድም ፖለቲከኛ መቼም ፍትህና ነፃነት አታገኝም።
የሚሻለው በጋራ ለሰላምና ለፍትህ መጣር ነው። መፍትሄው እንደ ህዝብ ከገጠመን የስነ ምግባር ዝቅጠት ለመውጣት ተባብሮ መሥራት ነው። ችግራችን ስር የሰደደ ነው። ችግራችን በማህበረሰብ ደረጃ የተንሰራፋ ነው። ስለ መንግስት ችግር ጧት ማታ ማውራቱን እንደ ንቃት ቆጥረን እራሳችንን እየሸወድን እንጂ እንደ ህዝብ መተዛዘናችን ሳስቶ መጨካከን ነግሶብናልኮ።
~ በየገበያው የሚያጭበረብረው፣ በየተቋሙ ህዝብ የሚያጉላላው፣ ... ሁሉ ምንም ስቅ ሳይለው ስለ ፍትህ እየወሸከተ ነው።
~ ለብዙዎች ከትምህርት ገበታ መራቅ ሰበብ የሚሆነው፣ ዘርና ሃይማኖት እየለየ ተማሪዎቹን የሚያከላፍተው አስተማሪ ምንም ሳያፍር ስለ ፍትህና ርትእ እየጮኸ ነው።
~ ታካሚዎቹን ፊቱን አጨፍግጎ የሚያስተናግደው፣ በግዴለሽነት የሰው ነፍስ ላይ የሚቀልደው፣ ለርካሽ ጥቅም ሲል የማይገናኝ ምርመራ እያዘዘ ደካማ ወገኑ ላይ ጭካኔ የሚፈፅመው ሃኪም እኮ ነው ስለ ፍትህ የሚጮኸው!
~ የተበላሸ ምግብ፣ ጊዜው ያለፈበት መድሃኒት፣ ፎርጂድ እቃ፣ የተጭበረበረ ምርት፣ ... የሚሸጠው ነጋዴ እኮ ነው "መስራት አቃተን" እያለ የሚያለቅሰው።
~ ፍትህ በገንዘብ የሚሸጠው፣ ከሌባ ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራው፣ እምነትና ብሄር እየመረጠ ፍትህ የሚቀብረው ዳኛና ፖሊስ እኮ ነው ስለ ፍትህ የሚዘፍነው።
~ ሚሊዮኖች የወጡበትን መሬት ሶስት አራት ካርታ ሰርቶ የሚቸበችበው ሰራተኛ፣ የሚሊዮኖችን ውሃና መብራት እየቆረጠ ሺ ጊዜ ብር እየተቀበለ የሚቀጥለው ሌባ እኮ ነው ስለ ፍትህና ስለ ነፃነት የሚለፍፈው።
~ መንገዶችንና ህዝባዊ ተቋማትን ከደረጃ በታች እየሰራ በሀገር በወገኑ ላይ የሚቆምረው እኮ ነው ለሀገር ለወገኑ ተቆርቋሪ መስሎ የሚፈተፈተው።
~ መኪናና ሞተር ሳይክል አዘጋጃቶ፣ አንድ ላምስት ተደራጅቶ የሚዘርፈው፣ ህፃናት እያፈነ የሚወስደውኮ ነው እኩል ስለ ፍትህ የሚያወራው!
~ የሁለት ቀን ጨቅላ፣ የ70 አመት አዛውንት፣ አቅመ ደካማ ሴቶችን ሳይቀር የሚገድለው እኮ ነው የነፃነት ታጋይ የሚባለው።
እስኪ በየትኛው ዘርፍ ነው የሚነሳ ጥሩ ነገር ያለን? ፖለቲከኞቹ የኛው ነፀብራቆች ናቸው። እኛኑ ነው የሚመስሉት። ከኛው የወጡ እንጂ ከሌላ ፕላኔት የመጡ አይደሉም። ክፋታቸው ክፍታችን፣ ንቅዘታቸው ንቅዘታችን ነው።
እንደ ህዝብ በዚህ ደረጃ መልካሞች የመነመኑ ከሆኑ እንዴት ነው ፍትህና እፎይታ የምናገኘው? በቅድሚያ በራሳችን ላይ ሰፊ ስራ መስራት ይጠበቅብናል። ወደተነሳሁበት ስመለስ፣ ስግብግብ ስሜታችን እየጋረደን፣ ቁንፅል አመልካከታችን እየሸወደን እንጂ በርግጠኝነት በሃገር መፍረስ እንደ ህዝብ ከሳሪዎች እንጂ አትራፊዎች አይደለንም። ስለዚህ ደግመን ደጋግመን ልንመለከት፣ ከጥፋት ልንርቅ፣ ለአጥፊዎች ጉልበት ከመሆንም ልንጠነቀቅ ይገባል። ጥፋትን ማስቆም ባንችል እንኳ ቢያንስ ተጋሪ ባለመሆን የራሳችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል።
=
https://t.me/IbnuMunewor
🌿 የእርጉዝ ሴት አምሮት በባህሪዋ ላይ ያለው ተፅዕኖ 🌸
📌 የሞሮኮ ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዐሊ ፈርኩስ حفظه الله ተጠየቁ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌸 ጥያቄ፦
የሴት አምሮት (الوَحَم) በሴቶች ላይ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰተው እውነተኛ ነገር ነውን? ወይስ ተራ ምናብና ቅዠት ብቻ ነው?
አላህ መልካም ዋጋ ይክፈልዎትና።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌿 መልስ፦
الحمد لله رب العالمين، والصلاة والسلام على من أرسله الله رحمة للعالمين، وعلى آله وصحبه وإخوانه إلى يوم الدين، أما بعد:
የእርጉዝ አምሮት (الوَحَم) በአረብኛ ቋንቋ የታወቀ ቃል ሲሆን፣ እርጉዝ ሴት የምትመኘውንና በዚያ ወቅት የምትፈልገውን ነገር ያመለክታል። ይህም በታዋቂ የአረብኛ መዝገበ ቃላት የተጠቀሰ ትርጉም ነው።
🌿 ነገር ግን ዛሬ ሰዎች ስለ «አምሮት» የሚናገሩት ሌላ ነገር አለ።
እሱም እርጉዝ ሴት አንድን ነገር በጣም ከፈለገች፣ ያ ፍላጎቷ ካልተሟላላት፣ በሆዷ ያለው ልጅም እርሷ የፈለገችውን ነገር የሚመስል ምልክት ወይም ጥቁር ምስል በሰውነቱ ላይ ይዞ ይወለዳል ይጠቁራል የሚለው እምነት ነው።
ይህንን ግን በሸሪዓ ውስጥ መሠረት የሌለው ነገር ነው። እንዲሁም ይህ እምነት በሚታመን የሸሪዓ ማስረጃ የተደገፈ መሆኑን አላውቅም።
🌿 ይህ ነገር በተለይ በሴቶች አንደበት የሚዘወተር እምነት ነው።
እንደዚህ ያለው ነገር በሸሪዓ ውስጥ የታወቀና አስፈላጊ ቢሆን ኖሮ፣ በዲን ውስጥ የታወቀ ይሆን ነበር፤ ነቢዩ ﷺም ለሰዎች በግልጽና በበቂ ሁኔታ ያስረዱት ነበር። ምክንያቱም ሰዎች ይህንን ጉዳይ በጣም ይፈልጉት ነበር፤ ለሁሉምም የሚመለከት ጉዳይ ነውና።
🌿 ነቢዩ ﷺ የተላኩትን መልዕክት በሙሉ አድርሰዋል፣ አደራውንም በትክክል ተወጥተዋል።
አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ብሏል፦
﴿ٱلۡيَوۡمَ أَكۡمَلۡتُ لَكُمۡ دِينَكُمۡ وَأَتۡمَمۡتُ عَلَيۡكُمۡ نِعۡمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلۡإِسۡلَٰمَ دِينٗاۚ﴾
“ዛሬ ዲናችሁን ለእናንተ ሞልቼላችኋለሁ፤ ጸጋዬንም በእናንተ ላይ ሞላሁ፤ እስልምናንም ለእናንተ ዲን አድርጌ ወደድኩላችሁ።”
📖 [ሱረቱል ማኢዳህ፡ 3]
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌿 ነቢዩ ﷺ መልዕክቱን በሙሉ ማድረሳቸውን እንዲህ ብለው ለሰሐቦቻቸው አረጋግጠዋል፦
«أَلَا هَلْ بَلَّغْتُ؟»
“እኔ መልዕክቱን አድርሻለሁን?”
እነርሱም፦ “አዎን!” አሉ።
እንደገና፦ «أَلَا هَلْ بَلَّغْتُ؟»
“እኔ መልዕክቱን አድርሻለሁን?”
እነርሱም፦ “አዎን!” አሉ።
ከዚያም ነቢዩ ﷺ እንዲህ አሉ፦
«اللَّهُمَّ اشْهَدْ، فَلْيُبَلِّغِ الشَّاهِدُ الْغَائِبَ»
“አላህ ሆይ! መስክር! እዚህ ያለው ለሌለው ያድርስ።”
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌸 ነገር ግን እርጉዝ ሴት በዚያ ወቅት ልዩ እንክብካቤ አያስፈልጋትምን?
በእርግጥ ያስፈልጋታል። 🌷
ሸይኹ رحمه الله እንደሚገልጹት፣ ሴቷ በዚያ ወቅት ተጨማሪ እንክብካቤ፣ ፍቅር፣ ርኅራኄና ትኩረት ልትፈልግ ትችላለች።
ስለዚህ ባል የባለቤቱን ሁኔታ ሊያስተውል፣ በርኅራኄ ሊያስተናግዳት፣ በተቻለውም መጠን የምትመኘውን ነገር ሊያሟላላት ይገባል። ብለዋል።
🌿 በዚህ ጊዜ እሷን ማስጨነቅ ማለት በእርግዝናዋ ላይ ተጨማሪ ጫና ማስገባት ነው።
ስለዚህ ባል ከባለቤቱ ጋር በመልካም ሁኔታ ይኑር፤ ሁኔታዋንም ያስተውል፤ የሚያስፈልጋትንም ነገር በቻለው መጠን ያሟላላት።
💎 ይህንን ሲያደርግም ከአላህ ዘንድ ምንዳን በመፈለግ ያድርገው።
አላህ سبحانه وتعالى ምንዳን የሚሰጥ ከሁሉ የተሻለ ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌿 ለጀግና ለባሎች የሚሆን ማስታወሻ
ሚስትህ እርጉዝ ስትሆን በሰውነቷ ውስጥ አንድ ሕይወት እየተሸከመች ነው።
ስለዚህ በዚያ ወቅት የምትፈልገውን በማድረግ ደስ ብሎህ አግዛት፤ ድካሟን በርኅራኄ ተመልከት፤ በቃልህም አጽናናት።
🌷 እርግዝናዋ የሚያልፍ ወቅት ነው፤ ነገር ግን በዚያ ወቅት ያሳየኸው ርኅራኄ በልቧ ውስጥ ረጅም ጊዜ ሊቀር ይችላል።
🌿 ትዳር የሚያምረው በደስታ ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ አንዱ ሲደክም ሌላው እጁን ሲይዘው ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
اللَّهُمَّ احْفَظْ نِسَاءَ الْمُسْلِمِينَ وَأَجِنَّتَهُنَّ وَارْزُقْهُنَّ الصِّحَّةَ وَالْعَافِيَةَ، وَأَصْلِحْ بُيُوتَهُنَّ، وَاجْعَلْ بَيْنَ الْأَزْوَاجِ مَوَدَّةً وَرَحْمَةً وَسَكِينَةً.
“አላህ ሆይ! የሙስሊም ሴቶችንና በማህፀናቸው ያሉትን ልጆቻቸውን ጠብቅልነረ፤ ጤናና ደህንነትን ስጣቸው፤ ቤቶቻቸውንም አስተካክልላቸው፤ በባሎችና በሚስቶች መካከልም ፍቅር፣ ምሕረትና ሰላም አድርግላቸው።” 🌸
📌 ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዐሊ ፈርኩስ حفظه الله
🇩🇿 አልጀሪያ — 22 ረጀብ 1426ሂ / 17 ኦገስት 2005
🌿 العِلْمُ عِنْدَ اللهِ تَعَالَى 🌿
الحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የማለዳ መልእክት (50)
~
በሞት የተለዩ ወላጆቻችሁን በዱዓችሁ አትርሱ። ከቻላችሁ በሶደቃ አስታውሷቸው፤ በተለይም አገልግሎቱ የሚቆይ የሆነ ሶደቃ ቢሆን ተመራጭ ነው። ለምሳሌ አጅሩን ለነሱ በማሰብ የመስጂድ ግንባታ ላይ መሳተፍ፣ ውሃ ማውጣት፣ የደዕዋ ስራን ማገዝ፣ የወቅፍ አገልግሎት፣ ወዘተ.
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 20/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የሉምዐቱል ኢዕቲቃድ ደርስ ተጠናቋል፣ አልሐምዱሊላህ።
~
የኪታቡ ፒዲኤፍ ፋይል፦
https://t.me/IbnuMunewor/9934
ክፍል 1↓↓
https://t.me/IbnuMunewor/9938
ክፍል 2↓↓↓
https://t.me/IbnuMunewor/9943
ክፍል 3↓↓↓
https://t.me/IbnuMunewor/9954
ክፍል 4 ↓↓↓
https://t.me/IbnuMunewor/9991
ክፍል 5↓↓↓
https://t.me/IbnuMunewor/10000
ክፍል 6↓↓↓
https://t.me/IbnuMunewor/10005
ክፍል 7 ↓↓↓
https://t.me/IbnuMunewor/10033
ክፍል 8↓↓↓
https://t.me/IbnuMunewor/10041
ክፍል 9 ↓↓↓
https://t.me/IbnuMunewor/10051
ክፍል 10↓↓↓
https://t.me/IbnuMunewor/10124
ክፍል 11↓↓↓
https://t.me/IbnuMunewor/10134
ክፍል 12
https://t.me/IbnuMunewor/10164
ክፍል 13
https://t.me/IbnuMunewor/10176
ክፍል 14
https://t.me/IbnuMunewor/10177
ክፍል 15
https://t.me/IbnuMunewor/10181
ክፍል 16
https://t.me/IbnuMunewor/10217
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
~ከሳዳት ተማሩ
የሀበሻው ንጉስ ኡስታዝ ሳዳት ከማል
መርሁ ወጥ ነው እውነት ያስቀድማል
በዲን መዋሸትን በጥብቅ ይቃወማል
ወቀሳን ሳይፈራ፣ ለዲን ዘብ ይቆማል
የሽርክን ወረርሽኝ፣ በጥበብ ያክማል
የቢድዓን ተውሳክ፣ በድፍረት ያርማል
ውለታህ ብዙ ነው የተውሒዱ ጀግና
የሱናው ነፀብራቅ፣ ስምህ ነው ገናና
ድምፅህ ያስተጋባል በሁሉም ቀጠና
ጠላት ያ ደ ን ቅ ሃ ል ወዳጅ ይቅርና
የኛ ቆራጥ ጀግና፣ ግልፅ ነው ቀመሩ
እውነት አትደብቁ ውሸት አትቀባጥሩ
በዲን ስም አትዋሹ ያለዒልም አታውሩ
ሰዎች መንገድ ለቀው ውሸትን ካወሩ
መልስ ይሰጣቸዋል ሳዳት መምህሩ
አ ያ ስ ጨ ን ቀ ው ም ሀገር እና ዘሩ
ለ "ፍ ት ህ" መቆምን ከሳዳት ተማሩ
= t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በለሆሳስ ውስጥ ያለ አደብ
~
አንዳንዶች ዱዓአቸው ልክ እንደ መፈክር በሃይለ ቃል የታጀበ ነው። ሰው ፊት ለልመና ቢቆም የማያደርገውን ጌታውን ሲማፀን ግን አደብ ያጣል። ዱዓአችን መተናነስ፣ ዝቅ ማለት የጎላበት ሊሆን ይገባል። ድምፃችን ሰበር ሁኔታችን ዝቅ ሲል ይበልጥ ለላቀ ለአደብ የቀረበ ይሆናል። ከፍ ያለው አላህ ስለ ነብዩ ዘከሪያ ሲያወሳ እንዲህ ይላል፦
{ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥ نِدَاۤءً خَفِیࣰّا (3) قَالَ رَبِّ إِنِّی وَهَنَ ٱلۡعَظۡمُ مِنِّی وَٱشۡتَعَلَ ٱلرَّأۡسُ شَیۡبࣰا وَلَمۡ أَكُنۢ بِدُعَاۤىِٕكَ رَبِّ شَقِیࣰّا (4) }
{ጌታውን የምስጢርን ጥሪ በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)። አለ "ጌታዬ ሆይ! እኔ አጥንቴ ደከመ፤ ራሴም በሺበት ተንቀለቀለ፤ አንተም በመለመኔ ጌታዬ ሆይ! (ምንጊዜም) ዕድለ ቢስ አልሆንኩም፡፡"} [መርየም፡ 3-4]
ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"ዝቅ ባለ ድምፅ የሚደረግ ጥሪ በውስጡ ጥልቅ ኣደብ አለበት። ከንጉሳን ዘንድ ድምፅ ከፍ አይደረግምና።" [ መጅሙዑል ፈታዋ፡ 15/15]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ።
የጀሀነም በር ጠባቂ መላዒካ ማሊክ ይባላል፡፡
Repost from Mohammed Siraj Al kemissie
የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ልጆች
~
የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ስድስት ወንዶችና አንዲት ሴት፣ በድምሩ ሰባት ልጆች ነበሯቸው።
[ሀ] የ"ኣሉ ሸይኽ" (የሸይኽ ቤተሰብ) ዝርያ የቀጠለባቸው አራት ልጆች ናቸው።
ዛሬ ድረስ በሳዑዲ ዐረቢያ ውስጥ "እከሌ ኣሉ ሸይኽ" እየተባሉ የሚጠሩት የእሳቸው ዝርያዎች ናቸው። ይሄ የእሳቸው ዝርያ የቀጠለው በአራቱ ልጆቻቸው በኩል ሲሆን፣ ሁሉም ታላላቅ ዐሊሞችና ዳኞች ነበሩ። እነሱም፦
1. ሸይኽ ሑሰይን ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1224 ሂ.)፦
ከአባታቸው በኋላ በዲርዒያህ ከተማ ውስጥ ዳኛ (ቃዲ) ሆነው አገልግለዋል። ታላቅ ዐሊም እና የዲርዒያህ መስጂድ ኢማም ነበሩ።
* ከእሳቸው የ"ኣሉ ሑሰይን" (የሑሰይን ቤተሰብ) ቅርንጫፍ ተዘርግቷል።
2. ሸይኽ ዐብዱላህ ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1224 ሂ.)፦
ከታላላቅ ዐሊሞችና ፀሐፊዎች አንዱ ነበሩ። ዲርዒያህ ውስጥ ቃዲ የነበሩ ሲሆን፣ ዲርዒያህ ከግብፅ በተነሳው የኦቶማን ቱርክ ጦር ስር ስትወድቅ ወደ ግብፅ ተወስደው እዚያው ሞተዋል።
* ከእሳቸው በኩል የ "ኣሉ ዐብዲላህ" (የሑሰይን ቤተሰብ) ቅርንጫፍ የተገኘ ሲሆን፣ "ተይሲሩል ዐዚዝል ሐሚድ" የተሰኘውን ታዋቂው የኪታቡ ተውሒድ ሸርሕ ያዘጋጁት ልጃቸው ሱለይማን ብኑ ዐብዲላህ ናቸው።
3. ሸይኽ ዐሊይ ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1245 ሂ.)፦
ታላቅ የፊቅህ ዐሊምና አላህን ፈሪ ሰው ነበሩ። የዳኝነት ሹመት ቢቀርብላቸውም አልተቀበሉም።
* ሙሐመድ ከተሰኘው የእሳቸው ልጅ የ "ኣሉ ዐሊይ" ወይም "ኣሉ ሙሐመድ" ቅርንጫፍ ተገኝቷል።
4. ሸይኽ ሐሰን ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ፦
አባታቸው በሕይወት እያሉ ነው የሞቱት። ነገር ግን "ፈትሑል መጂድ" የተሰኘውን ታዋቂ የኪታቡ ተውሒድ ሸርሕ ያዘጋጁትን ልጃቸውን ዐብዱረሕማን ብኑ ሐሰንን ተክተው አልፈዋል። ከእሳቸው የ"ኣሉ ሐሰን" ቅርንጫፍ ተዘርግቷል።
[ለ] ሌሎች ልጆች (ዝርያ ያልቀጠለባቸው)
1. ሸይኽ ኢብራሂም ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1250 ሂ.)፦
እውቀት ያላቸው ዐሊም ነበሩ። በዲርዒያህ የማስተማሪያ ሐለቃህ ነበራቸው። በኋላም ወደ ግብፅ ሄደው እዚያ ነው የሞቱት።
2. ዐብዱልዐዚዝ ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ፦
በልጅነታቸው በአባታቸው የሕይወት ዘመን ነው የሞቱት።
3. ፋጢማ ቢንት ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ፦ የተከበረች ዐሊማ (የእውቀት ባለቤት) የነበረች ሲሆን ተማሪዎችን ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ያስተምሩ ነበር። ዲርዒያህ በኦቶማን ጦርነት በወደቀች ጊዜ ተሰዳ ቆይታ በመጨረሻም በሪያድ ከተማ ሞታለች።
አስተውሉ! ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ከአንድኛው በስተቀር ልጆቻቸውን በሙሉ በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤተሰቦች ስም ነው የሰየሟቸው። ዐብዱላህ፣ ኢብራሂም እና ፋጢማ በቀጥታ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ልጆች ስም ሲሆን ሐሰን እና ሑሰይን ደግሞ የልጅ ልጆቻቸው ስም ነው። ዐሊይ ደግሞ የነብዩ ዐለይሂ ወሰለም የአጎት ልጅ እና አማቻቸው የሆነው የታላቁ ሶሐቢይ ስም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Mohammed Siraj Al kemissie
عَلِمْتُ أَنَّ رِزْقِي لَنْ يَأْخُذَهُ غَيْرِي، فَاطْمَأَنَّ قَلْبِي.
وَعَلِمْتُ أَنَّ قَدَرِي لَنْ يُغَيِّرَهُ قَلَقِي، فَهَدَأَتْ نَفْسِي.
وَعَلِمْتُ أَنَّ رَاحَتِي فِي ذِكْرِ اللهِ وَحْدَهُ، فَذَكَرْتُهُ.
وَعَلِمْتُ أَنَّ عُمْرِي مَحْدُودٌ، فَلَنْ أَعِيشَ بَعْدَهُ، فَزَهِدْتُ فِي الدُّنْيَا.
وَعَلِمْتُ أَنَّ الصَّبْرَ يُدْخِلُنِي جَنَّةَ رَبِّي، فَشَكَرْتُ رَبِّي.
أَرَادَ إِخْوَةُ يُوسُفَ عَلَيْهِ السَّلَامُ أَنْ يَقْتُلُوهُ، فَلَمْ يَقْتُلُوهُ.
ثُمَّ أَرَادُوا أَنْ يَمْحُوا أَثَرَهُ، فَارْتَفَعَ شَأْنُهُ.
ثُمَّ بَاعُوهُ بِثَمَنٍ بَخْسٍ لِيَكُونَ مَمْلُوكًا، فَأَصْبَحَ عَزِيزًا فِي مِصْرَ.
ثُمَّ أَرَادُوا أَنْ يَمْحُوا حُبَّهُ مِنْ قَلْبِ أَبِيهِ، فَازْدَادَ حُبُّ أَبِيهِ لَهُ.
فَلَا تَقْلَقْ مِنْ تَدَابِيرِ النَّاسِ، فَإِنَّ تَدْبِيرَ اللهِ فَوْقَ كُلِّ تَدْبِيرٍ، وَاللهُ فَعَّالٌ لِمَا يُرِيدُ.
يَقُولُ لِلشَّيْءِ: كُنْ، فَيَكُونُ.
فَالْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ.
https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie
Repost from Abu Hayder Aliy
🕊️ ስለ መገዳደልና ሰላም ትንሽ ልበል :-
የሰው ልጅ ሕይወት በአላህ ዘንድ የተከበረ ነው። አንዱ ሰው በሌላው ላይ ጥቃት ማድረስ፣ ደም ማፍሰስና መገዳደል እጅግ ከባድ ጉዳይ ነው።
📖 አላህ ﷻ እንዲህ ይላል፦
﴿وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ﴾
«አላህ የከለከለውን ነፍስ በሕጋዊ ምክንያት ካልሆነበስተቀር አትግደሉ።»
📖 አል-ኢስራእ፡ 33
እንዲሁም አላህ ﷻ ይላል፦
﴿وَمَنْ يَقْتُلْ مُؤْمِنًا مُتَعَمِّدًا فَجَزَاؤُهُ جَهَنَّمُ خَالِدًا فِيهَا﴾
«አንድን ሙእሚን ሆን ብሎ የገደለ ሰው ቅጣቱ ገሀነም ነው።»
📖 አን-ኒሳእ 4፥93
ነቢዩ ﷺም እንዲህ ብለዋል፦
«سِبَابُ الْمُسْلِمِ فُسُوقٌ، وَقِتَالُهُ كُفْرٌ»
«ሙስሊምን መስደብ ፉሱቅ ነው፤ ከእርሱ ጋር መዋጋት ደግሞ ኩፍር ነው።»
📚 ቡኻሪና ሙስሊም
እንዲሁም
አላህ ﷻ ይላል፦
﴿وَالصُّلْحُ خَيْرٌ﴾
«እርቅ የተሻለ ነው።»
📖 አን-ኒሳእ፡ 128
🌿ስለዚህ የሚያስፈልገን ጥላቻ ሳይሆን ሰላም፣ መገዳደል ሳይሆን እርቅ፣ መበቀል ሳይሆን ይቅርታ ነው።
🌿እያንዳንዳችን ከራሳችን እንጀምር፤ ቃላችን ግጭትን እንዳያባብስ፣ እጃችን ጉዳትን እንዳያመጣ፣ ልባችንም ለወንድማችን ምሕረትን እንዲይዝ።
🤲 አላህ ሆይ! በኢትዮጵያ እና በሁሉም የሙስሊሞች አገሮች ሰላምን አውርድልን። ደም መፋሰስንና መገዳደልን አስወግድልን። ልቦቻችንን አስታርቅልን፣ በመካከላችንም ፍቅርንና ወንድማማችነትን አጠናክርልን። አሚን🤲።
🕊️ السَّلَامُ خَيْرٌ لِلْجَمِيعِ
https://t.me/abu_hayder_aliy
https://t.me/abu_hayder_aliy
Repost from Abu Zekeriya #1
أين أنتم يا إخوتي؟
👉የት ገቡ እነዛ ዘብ ጠንካራ ወንድሞች ምን ዋጣቸው ??
👉ተማሪ ሳለን በ አሚርነት እንዲሁም የጀማዓ ስራ ላይ ሲሳተፉ የነበሩ እና የተሾሙ ጀማዓዎን በሚገርም ጥበብ ሲመሩ የነበሩ ??
👉በየ ዩኒቨርሲቲው የጀማዓው ቀኝ እጅ የነበሩ ??
👉 ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ደካማ ወንድም እህቶችን በማገዝ ሲተጉ የነበሩ ??
👉በየ ሰፈሩ የጀማዓው ልብ የነበሩ ??
👉በየ መድረሳው እና መሳጂዶች ላይ ለሱና ሲተጉ የነበሩ የት ናቹህ በአላህ ??
:- ديوان أبي تمام
إِذَا ما انقَضَى يومٌ بِشَوْقٍ مُبَرِّحٍ
أتى باشتياقٍ فادحٍ بعدَهُ غَدُ
فلم يبقَ مني طولُ شوقي إليهم
سوى حسراتٍ في الحَشا تتردّدُ
አንድ ቀን በከባድ ናፍቆት ከተጠናቀቀ
ከእርሱ በኋላ የሚመጣው ነገር ግን የበለጠ ከባድ ናፍቆት ይዞ ይመጣል።
ለእነርሱ ባለኝ ረጅም ናፍቆትም፣
በውስጤ የሚመላለሱ የልብ ቁጭቶች ብቻ ቀርተውኛል።
أين أين أين ,,,,؟؟؟
ወንድም / አቡ ዘከሪያ
https://t.me/Abuzekeriya01
Repost from Abu_Oubeida~channel
ጥንካሬ ከስንፍና ጋር የሚደረግ የፍልሚያ ውጤት ነው!
በህይወት ውስጥ ትልልቅ ስኬቶችን ያስመዘገቡ፣ የሚታይ ለውጥ ያመጡ ሰዎች ስንፍናን አያውቁም ማለት አይደለም። ልዩነታቸው ስንፍና ሲፈታተናቸው በዝምታ ተቀምጠው አልተሸነፉም፤ ይልቅስ የዕለት ተዕለት የትግል ማዕበል ውስጥ ገብተው ድል አነሱ እንጂ።
እያንዳንዱ ቀን የራሱ ፈተና አለው። ጠዋት ከምንጣፍ መነሳት፣ ሰነፍ ልብን "ዛሬም መስራት አለብኝ" ብሎ ማሳመን ከባድ ፍልሚያ ነው። ጥንካሬ ማለት ፈተና የሌለበት ህይወት መኖር አይደለም፤ ስንፍና እጅ እንድንሰጥ በሚጎትተን ሰዓት ጀርባችንን ሰጥተን ፊት ለፊት መጋፈጥ ነው።
ስንፍና ዛሬን አፍኖ ነገ ላይ ይጥለናል።
ጥንካሬ ግን ዛሬን ሰንጥቆ የነገን ድል ያበስራል።
የሚገርመው ነገር፣ ጥንካሬ በአንድ ቀን የሚመጣ አይደለም። ልክ በጂም ውስጥ ጡንቻን ለመገንባት ከብደት ማንሳት እንደሚያስፈልግ ሁሉ፣ የአዕምሮ እና የስራ ጥንካሬም በየቀኑ ከስንፍና ጋር ከሚደረግ ትግል የሚገኝ ውጤት ነው። ዛሬ ያሸነፍከው አነስተኛ ስንፍና፣ ነገ ትልቅ ስኬት ሆኖ ይመለስልሃል። መልካም ትግል።
አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida
ለአስተውሎት
~
ፉዶይል ብኑ ዒያድ አንዱን ሰው “እድሜህ ስንት ነው” ብለው ጠየቁት።
* "ስልሳ አመት" አለ።
- "ስልሳ አመት ሙሉ ወደ ጌታህ እየተጓዝክ ነው፡፡ መድረሻህ ሳይቃረብ አይቀርም።"
* "ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!" (እኛ ለአላህ ነን፡፡ ወደሱም ተመላሾች ነን)
- “ 'ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን' የሚለውን ተፍሲሩን ታውቃለህ? ለአላህ ባሪያ እንደሆነ ወደሱም ተመላሽ እንደሆነ የሚያውቅ እንደሚቆም ይወቅ፡፡ እንደሚቆም ያወቀ እንደሚጠየቅ ይወቅ፡፡ እንደሚጠየቅ ያወቀ መልስ ያዘጋጅ፡፡”
* "ምንድን ነው መፍትሄው?"
- "ቀላል ነው!"
* "ምንድን ነው እሱ?"
- "በቀረህ እድሜ መልካም ስራ፡፡ ያለፈው ይማርልሃል፡፡ ቀሪው እድሜህን ካጠፋህ ግን ባለፈውም በቀሪውም ትያዛለህ፡፡"
ምንጭ፦ [ሒልየቱል አውሊያህ፡ 8/113]
አስተውል። ስልሳ ዓመት ከደረስክም አስተውል። ስልሳ ካልደረስክም ገና ነኝ ብለህ አትዘናጋ ነቃ በል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 20/2005)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from قَناةُ وفَوا ئِد أبي فَوزان الْحَبَشِيِّ
........"ታሳዝነኛለች".......
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
በኑሮ ስንክ ሳር በህይወት አዙሪት፡
በንጋት በምሽት ምድረ-ሽክርክሪት፡
በይሆናል ተስፋ ስትነድ እንደ ክብሪት፡
መልካም ጥሩ አሳቧ ሲወልድባት እብሪት፡
ፅኑና ብርቱዋ ዝንጉ ትሆናለች፡
ይህች አይነት እህቴ ታሳዝነኛለች፡
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
ትዳርን ስታስብ ኑሮን ለመጋራት፡
ከቢጤዋ ጋራ አብራ ለመዳራት፡
ሀሳብ ስትመገብ ህይወትን ለመምራት፡
ጧት ቁርስ ሳትበላ ማታ ሳትቀምስ እራት፡
የምታማክረው የምታወያየው ሰው እየቸገራት፡
ወስና እንዳትገባ አቋሙ እያስፈራት፡
ለሷ እንደማይሆናት ውስጧ እየነገራት፡
አለች እስከ ዛሬ በውዝግብ ስሜት፡
በለቅሶና በሳቅ በስላቅ በሀሜት፡
ውዝግብግብ ብላ ዛሬም ድረስ አለች፡
ምንም ባላግዛት ታሳዝነኛለች፡
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
ወስና እንዳቶወው ፍቅር ይይዛታል፡
በወደደች ቁጥር ደስታ ይሰማታል፡
ስትጠጋው ደግም በጣም ይጎዳታል፡
ፕላንና እቅዱ ያደናግራታል፡
ብቸኛ እንዳትሆን ልጅ መውለድ ያምራታል፡
ደግሞ ባንድ በኩል እድሜዋን ስታስብ፡
እየቆጠረ ነው ሞትን ለሷ ሊስብ፡
በቁጭት በንዴት ትላለች እንግብግብ፡
የህይወቷ ጣዕም ሲጠፋት የርሷ ግብ፡
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
ልቧ እየዋለለ በመሄድ በመቅረት፡
ሀዘን ያሳብቃል የልቧ ላይ ንዝረት፡
ትርጉሙ ጠፍቶባት የመንጋት የመምሸት፡
ሰላም ነኝ እያለች አለች በውሻሸት፡
ከደስታ ተኳርፋ ህይወት ትገፋለች፡
ይቺ አይነቷ እህቴ ታሳዝነኛለች፡
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
.......በኑረዲን_አልአረቢ....2015
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
ታዋቂ የነበሩ የጃሒልያ ዘመን ገጣሚያን
❶ ➛♦️ኢምሩዑል-ቀይስ
❷➛ጦርፈቱ ኢብኑ አብድ
❸➛ዘህረቱ ኢብኑ አቢ ሱለሚ
❹➛ለቢድ ኢብኑ ረቢዓህ(ሙኸድረም)
❺➛♦️አንተራ ኢብኑ ሸዳድ
❻➛ዓምር ኢብኑል ኩልሱም
❼➛ሐሪስ ሒ'ሊዘህ
❽➛ናቢዘቱ ዙብያንይ
❾➛አዕሸል አክበር
❿➛አብድ ኢብኑል አብረስ
⓫➛ሙሐልሐል ኢብኑ ረቢዓህ
⓬➛አውስ ኢብኑ ሐጀር
⓭➛አልቀመቱል ፈህል
⓮➛አዲይ ኢብኑ ዘይድ አል-ዒባድ
⓯➛አ'ሸንፈሪይ
⓰ ➛ተአ'በ'ጦ ሸ'ራ
⓱➛ዑርወት ኢብኑ ወርድ
⓲➛ሰመውአት ኢብኑ ዓዲያዕ
⓳➛ሐሪስ ኢብኑ ዑባድ
⓴➛♦️ሐቲም አጧዒይ
ከሞላ ጎደል ታዋቂወቹ የጃሒልያ ዘመን ገጣሚዎች እነዚህን ይመስላሉ...ግጥሞቻቸው በታሪክ ተሰንደው በአረቡ አለም ብሎም በአለም ላይ ተፅኖ ፈጣሪ ናቸው አንዳንዶቹ በቋንቋ መፀሀፎች ላይ የሰፈሩ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ በሸሪዓ ኪታቦች ላይም እንደ ምሳሌ ይቀርባሉ።
በተለይ ሶስቱ
❶♦️አንተራ ኢብኑ ሸዳድ
❷♦️ሐቲም አጧዒና
❸♦️ኢምሩዑል ቀይስ በሙስሊሙ ዘንድም እጂግ ታዋቂዎች ናቸው።
✅......በቀጣይ የሙስሊም ኢምፓየር ገጣሚወችን እንጠቅሳለን ኢንሻ አሏህ።
...በኑረዲን አል-አረብ
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from አቡ ዓብደሏህ(أبو عبد الله الولوي)🇸🇦
🔥 የዒልም ሲልሲላ | አዲስ ደርስ 📚
🌟 ኡስታዝ ሙሐመድ አሕመድ حفظه الله
ከየመን መርከዝ የመጡ፣ በዒልም አቅማቸውና በሱና ላይ ባላቸው ሂማ የሚገለጹ ኡስታዝ። 💎
📖 القواعد الأربع | ቀዋዒዱል አርበዓ
ከእንዲህ ያለ ኡስታዝ ጋር መማር፣ የአቂዳን መሠረቶች በጥልቀት ለመረዳትና የተማርነውን በትክክል ለመተግበር ውድ እድል ነው። 🌱📚
🚨 ነገ ጧት ይጀምራል! ⏰
🔥 የዒልም ፍላጎት ካለህ — እድሉን አታሳልፍ!
📌 መስፈርቶች:
❤️ የዒልም ፍላጎት
⏰ በሰዓቱ መገኘት
📝 ፈተና መፈተን
📍 መስጅደል አዝሀር | ወሎ ዩኒቨርሲቲ
📚 የዒልም ጉዞ… በሲልሲላ
ይቀጥላል! 🌿
📢❤️ ይህንን የዒልም መልእክት ለሌሎች የእውቀት ፈላጊዎችም SHARE አድርጉ!
🤲 አላህ ከእውቀት የሚጠቅመን ያድርገን።
بارك الله فيكم ونفع بكم 🌿
📲🔥 የTelegram ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
👉 https://t.me/abuabdelah123 👈
📢 JOIN • SHARE • ለሌሎችም አስተላልፉ! 🌿
ድካምህ ምንም ያህል ቢበዛና ቢበረታብህም፤ በዚች በዱንያ እረፍትን መፈለግ የማይቻል ነገር መሆኑን አስታውስ። የዚህም ማስረጃ የፍጥረታት ሁሉ ሁኔታ በመሆኑ ተጨማሪ ንግግር አያስፈልገውም። በሕይወት ታሪክ ውስጥ፣ አእምሮ ከሌለው «እብድ» ሰው በቀር አንድም እረፍት ያገኘ ሰውን ማግኘት ከባድ ነው። ስለዚህ ችግሩና መከራው ምንም ያህል ቢጠናብህ ታገስ፣ ተጋደል፤ የስሜትህና የምኞትህ ባሪያ እንዳትሆን! በትዕግስት የሚገኝ ሕይወት ፍሬው ያማረ፣ ስሩም የጸና የበረታነውና።
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
~ ወሰን አትለፍ!
ሸይኽ ረስላን -ሐፊዘሁላህ- እንዲህ ይላሉ፦
"የዘመኑ ሰዎች ስነ-ምግባር ብልሹነት ተፅዕኖ ፈጥሮብህ እንደነሱ ከመበላሸት አስጠነቅቅሃለሁ። የነሱ ስነ-ምግባር ፈር ቢለቅም አንተ በራስህ ትክክለኛ ባህሪ ላይ ፅና። ቢሰድቡህ አትስደባቸው። ቢከዱህም አትክዳቸው። ረሱልﷺ እንዳሉት "የከዳህን ሰው አትክዳው"። አንዳንዴ አንድ አካል የተከራካሪውን ወይም የባላንጣውን ብልግና እና ወንጀል እንደዚሁም ነውሮቹን ጠንቅቆ ሊያውቅ ይችላል። ነገር ግን ዲኑ ስለማይፈቅድለት በምንም አይነት መልኩ የዚያን ሰው ነውር አይናገርበትም። ይህን ማድረጉ ደካማ ሊያስመስለው ይችላል። ነገር ግን ይህ የትክክለኛ ስብዕና ባለቤት እምቅ ሃይል የሚረጋገጥበት ቦታ ነው። ይህም ልክ ረሱልﷺ ባልደረቦቻቸውን በዚህ እንደኮተኮቱት ሁሉ ማንኛውም ሙስሊም ሊላበሰው የሚገባ ስብዕና ነው።"
ከዚህ በመነሳት አንድን የጥመት ተጣሪ በተለያዩ ጥፋቶች ላይ ልታየውና ብዙ ጉዳጉዶችንና እጅ በአፍ የሚያስጭኑ ከእርሱ የማይጠበቁ ብልግናወችን ልታውቅ ትችላለህ። ነገር ግን ይህን ነውሩን እንድትሰትርለት ዲንህ ያዛል። ነውሩን ከማጋለጥ ሸሪዓ ይከለክልሃል። ይህን ብታደርግ ወንጀል ፈፀምክ እንጅ ዲንን ረዳህ አይደለም የሚባለው። የጥመት ተጣሪ ላይ መልስ ሲሰጥ በግልፅ የተሳሳተበትን ነጥብ አንስተህ በማስረጃ ረድ ታደርጋለህ እንጅ ገና መንሃጁ ልክ አይደለም በሚል የግል ሚስጥርና ነውሮችን መበተን ነውር ነው። ይልቁንም ልትደብቅለት ነው የሚገባህ።
አላህ እንዲህ ይላል፦
{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ كُونُوا۟ قَوَّ ٰمِینَ لِلَّهِ شُهَدَاۤءَ بِٱلۡقِسۡطِۖ وَلَا یَجۡرِمَنَّكُمۡ شَنَـَٔانُ قَوۡمٍ عَلَىٰۤ أَلَّا تَعۡدِلُوا۟ۚ ٱعۡدِلُوا۟ هُوَ أَقۡرَبُ لِلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِیرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ } [سُورَةُ المَائـِدَةِ: ٨]
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡"
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
