ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
Відкрити в Telegram
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
323
Підписники
+124 години
-77 днів
+5830 днів
Архів дописів
Repost from N/a
አንተ የሰው ልጅ ሆይ! በደንብ አድርገህ ስማኝ ልብህን ሰተህ አድምጠኝ!
👉በጎዳህ ሰው አትዘን
👉ጥሎህ በሄደም ሰው አትከፋ
👉በሰበረህም ቂም አትያዝ
👉ባሳዘነህም አትዘንበት
👉ባሳመመህ ሰውም አትበሳጭ
ምክንያቱም እንደነሱ #የወደደህ፣_ ያሰበልህ፣_ያስደሰተህ፣_ያጠነከረህ የለምና።ለምን መሰለህ እነሱ ባያስከፉህ፣ ባይሰብሩህ ፣ባያስደብሩህ ፣ባያሳምሙህ፣ ባያሳዝኑህ መች ትጠነክር ነበር?! መች ይቆርጥልህ ነበር? ስለ ራስህ መኖር ማሰብ እራስህን ማዳመጥ መች ትጀምር ነበር? ነፃነትህን መች ይፋ ታወጣ ነበር?ስለዚህ የጎዱህን ለመጉዳት ከማሰብ አስበህላቸው እንዳጠነከሩህ ሰብረውህ ሊሄዱ አስበው እንደ ተጠገንክ አንዳስከፉክ ሲያስቡ ደስተኛ እንድትሆን እንዳደረጉ አሳያቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/AbulBuhari46
https://t.me/AbulBuhari46.
አስገዳጅ ሁኔታ ሲገጥም ፊትን ለወንድ መግለጥ
~
አንዳንዴ ፊታቸውን ከባዳ ወንዶች የሚሸፍኑ እህቶቻችን እንዲገልጡ የሚገፋ ጫና ይገጥማቸዋል። ለምሳሌ ጥጋበኛ እጅ ላይ ወድቀው ካልገለጡ ለከባድ ጥቃት ሊጋለጡ ይችላሉ። በመሰል ሁኔታዎች ላይ መግለጥ ይችላሉ? ወይስ ችግሩ የፈለገ ቢከፋ እምቢ ማለት አለባቸው?
አስገዳጅ ሁኔታ ሲገጥም የማይፈቀድ ነገር ይፈቀዳል። الضرورات تبيح المحظورات የሚለው የፊቅህ መርህ ጠንካራ መነሻ ያለውና የታወቀ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦
{ لَا یُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۚ }
አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም።" [አልበቀረህ: 286]
በአስገዳጅ ሁኔታ ህይወትን ለማትረፍ በክት መብላት ይቻላል። ተጨባጭ የሆነ አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠመ የክህደት ንግግር በመናገርም ራስን ማትረፍ ይቻላል።
{ مَن كَ.فَرَ بِٱللَّهِ مِنۢ بَعۡدِ إِیمَـٰنِهِۦۤ إِلَّا مَنۡ أُكۡرِهَ وَقَلۡبُهُۥ مُطۡمَىِٕنُّۢ بِٱلۡإِیمَـٰنِ }
"ከእምነቱ በኋላ በአላህ የካደ ሰው (ብርቱ ቅጣት አልለው)፡፡ ልቡ በእምነት የረጋ ሁኖ (በክህደት ቃል በመናገር) የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር።" [አነሕል: 106]
ሌሎችም ጉዳዮች እንዲሁ ይታያሉ። የሙስሊሟ ለባዳ ወንዶች ፊቷን መግለጥም በዚሁ አግባብ የሚታይ ይሆናል። ይህንን መርህ በመንተራስ አስገዳጅ ጉዳይ ሲገጥም ጊዜ ሴት ልጅ ፊቷን መግለጥ እንደምትችል ዓሊሞች ይገልፃሉ። በዚህ ላይ በምሳሌነት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ውስጥ የሚከተሉትን ማንሳት ይቻላል:-
1ኛ፦ በማጨት ጊዜ :- ይሄ ሐዲሦች የመጡበት እንዲሁም ኢጅማዕ ያለበት በመሆኑ ለብዙ ሰውም የሚሰወር ስላልመሰለኝ ለማሳጠር ያክል በዚሁ ልለፈው።
2ኛ፦ ለህክምና፦ ጉዳቱ ያለበት ክፍል ፊትም ሆነ ሌላ ክፍል መግለጥ ይቻላል። ከተቻለ ባል ወይም ሌላ መሕረም (ቅርብ ቤተሰብ) አብሮ መኖር አለበት። ባይሆን ሴት ሃኪም ካለ ወደ ወንድ፣ ሙስሊም ካለ ወደ ሌላ መሄድ አይገባም ይላሉ ዓሊሞች። ለህክምና በሚያስፈልገው መጠን ሃኪሙ አካሏን መመልከት ይችላል ይላሉ ኢብኑ ቁዳማ። [አልሙግኒ፡ 7/459]
በነገራችን ላይ ጦር ሜዳ ላይ ሴቶች ሶሐቢያት ወንዶችን ያክሙ ነበር። ኡሙ ዐጢያህ - ረዲየሏሁ ዐንሃ - እንዲህ ትላለች፦
غَزَوْتُ مَعَ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ سَبْعَ غَزَوَاتٍ أَخْلُفُهُمْ فِي رِحَالِهِمْ، فَأَصْنَعُ لَهُمُ الطَّعَامَ، وَأُدَاوِي الْجَرْحَى وَأَقُومُ عَلَى الْمَرْضَى
"ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ጋር ሰባት ዘመቻዎችን ዘምቻለሁ። እቃዎቻቸውን እጠብቅ፣ ምግባቸውን አዘጋጅ፣ ቁስለኞችን አክም እንዲሁም ህመምተኞችን እንከባከብ ነበር።" [ሙስሊም፡ 1812] የቡኻሪን باب هل يداوي الرجل المرأة، والمرأة الرجل እንዲሁም ዘርዘር ያለ ነገር የፈለገ ፈትሑል ባሪን መመልከትም ይቻላል።
3ኛ፦ ችሎት ላይ፦ በፍርድ ችሎት ላይ ፍርድ ለመስጠት ዳኛው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ፊቷን ይመለከታል። ካልሆነ ሐቅን ማስከበር አስቸጋሪ ሊሆንበት ይችላል። ምስክር ሆና ስትቀርብ ወይም በሷ ላይ ምስክርነት ለመስጠትም እንዲሁ መገለጥ ግዴታ ሊሆን ይቻላል። ኢብኑ ቁዳማ እንዲህ ይላሉ፦
وللشاهد النظر إلى وجه المشهود عليها لتكون الشهادة واقعة على عينها، قال أحمد: لا يشهد على امرأة إلا أن يكون قد عرفها بعينها
"መስካሪ ሰው ምስክርነቱ ቦታው ላይ ያረፈ ይሆን ዘንድ የሚመሰከርባትን ሴት ሊመለከት ይችላል። (ኢማሙ) አሕመድ 'በትክክል ለይቶ እስካላወቃት ድረስ አንዲት ሴት ላይ አይመሰክርም' ብለዋል።" [አልሙግኒ፡ 7/459]
ይሄ የሳቸው ሃሳብ ብቻ አይደለም። ሌሎችም "ኒቃብ በለበሰች ሴት ላይ ፊቷን ሳትገለጥ መመስከር አይቻልም" ይላሉ። [አሸርሑል ከቢር፣ ደርዲር፡ 4194]
4ኛ፦ በግብይት ላይም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ሻጭ ወንድ ገዢዋን ሴት ሊመለከት እንደሚችል ዑለማኦች ይገልፃሉ። [አልሙግኒ፡ 7/459] ያለበለዚያ በግብይቱ ላይ ለተፈጠረ ክፍተት ማስተካከያ ለማድረግ ሊቸገር ይችላል። ለምሳሌ እቃ ሽጦላት ፊቷን ካላየ ኋላ ላይ እቃው ችግር ኖሮበት መመለስ ቢያስፈልግ በትክክል እሷ መሆኗን መለየት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።
5ኛ፦ አስገዳጅ ህግ ባለበት ሁኔታ፦ በአንዳንድ ሃገራት ህግ ወይም ኤርፖርት አካባቢ ወይም ሌላ አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠመም ፊቷን መግለጥ ትችላለች። ለምሳሌ በመጥፎ ሰዎች እጅ ላይ ወድቃ ራሷን አደጋ ላይ ከምትጥል ፊቷን በመግለጥ ራሷን ማትረፍ ትችላለች። "አስገዳጅ ሁኔታዎች የተከለከለን ነገር ያስፈቅዳሉ።" ስለዚህ ማንነቷን ለመለየት የሚጠይቅ አስገዳጅ ሁኔታ ቢገጥም ወይም ሌላ ተጨባጭ ምክንያት ከኖረ ፊቷን መግለጥ ትችላለች ማለት ነው።
ይሄ እንግዲህ ከዑለማኦች አቋም ውስጥ ለደረሰች ሴት ልጅ ፊትን መሸፈን ግዴታ ነው የሚለውን ስንወስድ ነው። የሆነ ሆኖ ጫን ያለ ሁኔታ ካልገጠማት በስተቀር ለትንሽ ለትልቁ እጅ ልትሰጥ አይገባም። ፍተሻና መሰል ቦታዎች ላይ ሴቶችን መጠቀም የሚቻልበት ሁኔታ ካለ ወይም ደግሞ ጉዳዩ አንገብጋቢ ካልሆነ ባዳ ለሆኑ ወንዶች ፊትን መግለጥ አይገባም። አስገዳጅ ችግር ሲገጥም ደግሞ ጉዳዩን በችግሩ መጠን ብቻ ማስተናገድ ይገባል። "አስገዳጅ ሁኔታዎች በልካቸው ነው የሚስተናገዱት።" እንጂ ችግሩን ማመሀኛ አድርጎ አጉል መዘናጋት ውስጥ መግባት አይገባም። #ወላሁ_አዕለም።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 01/2017)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
(12) ከደባል ሱሶች ራቅ። አላማ ያለው ሰው ከሱስ ጋር አይነካካም። ለነፃነቱ ዋጋ የሚሰጥ ሰው በተልካሻ ነገሮች አይታሰርም። ደግሞም ውለታ ቢስ አትሁን። አንተ አክብረህ ያማረ ቪላ፣ ወይም ቆንጆ መኪና፣ ወይም ሚሊየን ገንዘብ ቆጥረህ የሰጠኸው ሰው አይንህ እያየ ከፊትህ በእሳት ቢያጋየው ምን ይሰማሀል? ሰውስ ምን ይላል? አላህ በክብር የሰጠህን ህይወት በጫትና በሲጋራ መግደል ማለት ከዚህ የከፋ ውለታቢስነት ነው። ራስህን በሱስ የምትገድለው ከቤተሰብ በተቆነጠረ ሳንቲም ከሆነ ግን አንተ ዘመን ተሻጋሪ ገልቱ ነህ። እንስሳ ነህ ብየ የእንስሳን ክብር ዝቅ ማድረግ አልፈልግም።
"ራስን በሱስ በመጉዳትና ራስን በማጥፋት መካከል ያለው ልዩነት የጊዜ ርዝማኔ ነው።"
(13) ለወላጆችህ በጎ ሁን። አቅምህ የሚችለውን ሁሉ ሁንላቸው። የሚረኩብህ እንጂ የሚሸማቀቁብህ፤ የሚዘኑብህ እንጂ የሚሳቀቁብህ፤ የምታሳርፋቸው እንጂ የምታሳፍራቸው አትሁን። ቤተሰብህ ላይ ጥገኛ ሆነህ ሳለ አልፈህ የምትፏልልባቸው ከሆነ ግን በርግጠኝነት መጥፊያህን ይዘሀል። "የማያድግ ልጅ ታዝሎ ያፏጫል" ይባላል።
"የቤት ቀጋ፣ የውጭ አልጋ አትሁን።"
(14) አላማ ይኑርህ። ለአላማህ ትጋ። ወደ አላማህ ተጓዝ። ወዴት ነው የምትሄደው? ታውቀዋለህ? ምንድነው የምትፈልገው? ይገባሃል? ምን ሰበብ እያደረስክ ነው? መቼስ ሰሜን ለመድረስ ወደ ደቡብ አይኬድም። ጤፍ ዘርቶ ባቄላ አይጠበቅም። ባጭሩ አላማህንም፣ አቅጣጫህንም፣ ሚናህንም እወቅ።
"የሚሄድበትን የማያውቅ የትኛውም መንገድ ይወስደዋል።"
(15) የኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ ቁርጠኛ ሁን። የሶላትና የጥናት ጊዜህን የሚበላ፣ አሰተሳሰብህን የሚበክል፣ መጥፎ ምስሎችን ከመመልከት ሱስ የሚያጣብቅ እንዳይሆን ደጋግሞ ማሰብ ይገባል። ማህበራዊ መገናኛዎችም ሱስ እንዳይሆኑብህ ተጠንቀቅ። ብትችል ቲክቶክ ከሚሉት ጥሩ ያልሆነ ሰፈር ከነጭራሹ ብትርቅ መልካም ነው። አጠቃላይ ከኢንተርኔት ጋር ያለህ ትስስር የሚያንፅህ እንጂ የሚያጠፋህ እንዳይሆን ደጋግመህ አስብበት።
ሰላም!
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 21/2011)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ጥቂት ምክሮች ለሙስሊም ተማሪዎች
~
ትምህርት እየተጀመረ ነው። ፈተና ሲደርስ መደናበር ወይም የአመቱ መጨረሻ ላይ ውጤትን ጭንቅ ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ምንም ፋይዳ የለውም። ይልቁንም በየትኛውም ደረጃ ላይ ያሉ ተማሪዎች ከቀን አንድ ጀምረው በቁም ነገር መዘጋጀት ነው የሚያዋጣው። ከልቡ የተዘጋጀ ሰው በአላህ ፈቃድ የልፋቱን አያጣም። ጥሮ ግሮ ውጤት ባይመጣ እንኳ ሰበብ ያደረሰ ሰው የሚጠበቅበትን ተወጥቷል።
ይህን እንደ መግቢያ ካልኩኝ ለተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የተሻለ ስብእና እንዲኖራቸው ያግዛሉ ያልኳቸውን የተወሰኑ ነጥቦት እንደሚከተለው አስፍሬያለሁና በማሰራጨት ብታግዙኝ ደስ ይለኛል።
① መምህርህን አክብር። አስተማሪህ ለደሞዝ ቢሰራም ላንተ ውለታ እየዋለ ነው። ኋላ ከሚፀፅትህ ዛሬ ለአስተማሪህ ትሁት ሁን። እድሜውንም አክብር። የሚያስተምርህን መናቅ የሚያጎርስህን መንከስ ነው። እንዲያዝንብህ፣ "ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ" እንዲል አታድርገው። ውለታ ይግባህ። የወጣትነት ስሜት ድፍን ቅል አያድርግህ።
"አስተማሪን መናቅ እውቀትን መናቅ ነው።"
"ለእውቀት ያለህ ክብር መጠኑ ለአስተማሪህ ባለህ ክብር ልክ ነው።"
② ተባባሪ ሁን። እንዳቅምህ የምታግዛቸው በርካታ ደካማ ተማሪዎች በዙሪያህ አሉ። የእለት ጉርስ የሚጎድላቸው፤ የደንብ ልብስ አቀበት የሆነባቸው፤ የሳሙና፣ የኮፒ፣ የታክሲ፣ የቤት ኪራይ፣ የህክምና፣ የደብተር፣ … የሚቸግራቸው፤ ብዙ ናቸው። ቢቻል አስተባብራችሁ የተቀናጀ ስራ ስሩ። ካልሆነ የራስህን ሐላፊነት ተወጣ። ደካማ ተማሪዎችን አስጠና፣ አግዝ። በዱንያ እርካታን ታገኝበታለህ። ልምድን ትቀስምበታለህ። ህይወትን ትማርበታለህ። በኣኺራ እጥፍ ድርብ ትሸለምበታለህ።
③ ከመንደሬነት ራቅ። የሰፈር፣ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የአካባቢ ብሽሽቅ ውስጥ አትግባ። ዘረኝነትን በየትኛውም መልኩ ተፀየፍ። ዘረኞችንም ከቻልክ ምከር። ካልሆነ አፍንጫህን ይዘህ ሽሻቸው። በዘርህ ከማንም በላይም፣ ከማንም በታችም አይደለህም። ለዘር ተኮር ቀልዶች ጥርስህን አታሳይ። ሌሎችን በዘር አትውጋ። በዘር ለሚተነኩስህም ንቀህ እለፍ እንጂ እሳት ጎርሰህ አትነሳ። የማንም ሙገሳ ከፍ እንደማያደርግህ ሁሉ የማንም ትችትም ዝቅ አያደግህም። ትእግስት ፍርሃት እንዳልሆነ ለራስህ ሹክ በለው።
"ዘረኝነት ጥንብ ሲሆን ዘረኛ ደግሞ ጥንብ አንሳ ነው።"
④ ለዲንህ ጊዜ ስጥ። አንተ ያለ ዲንህ ባዶ ነህ። ያለ ዲን ስኬትም ስኬት፣ ህይወትም ህይወት አይደለም። ስለ ዲንህ ስትማር ክፍል ውስጥ ዲንህን አታስነካም። የተሳሳተ ቲዎሪ አያነቃንቅህም። ውሎህ በፕሮግራም ይሆናል። ሕይወትህ ጣእም ይኖረዋል። ስለዚህ ቁርኣን ቅራ። አስቀራ። ኪታብ ተማር። አስተምር። ደዕዋ ሞክር። ሶላት ስገድ። ስታልፍ ስታገድም ዚክርህን አድርግ። ዲንህን በራስህ ላይ አንፀባርቅ። ዲንህ የሚወራ ሳይሆን የሚንኖር ነው።
"ዲንህ ህይወትህ ነው። ዲንህ ከሌለ አንተ እራስህ የለህም።"
⑤ በትምህርትህ ላይ ሃላፊነት ይሰማህ። ቤተሰብ የላከህ ለዋዛ አይደለም። ገንዘቡም፣ ጊዜውም፣ ድካሙም ዋጋ አይጣ። ስለዚህ በወጉ ተማር። ክፍል ውስጥ በሚገባ ተከታተል። ንቁ ተሳትፎ ይኑርህ። በሚገባ አጥና ። ስንፍናን አትቀበል። "አልችልምን" አርቅ ። ኩረጃን፣ ጥገኝነትን ተፀየፍ። በጥረትህ የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ወኔ ይኑርህ። አትጠራጠር! ስትጥር ዛሬ ካለህበት የተሻለ ትሆናለህ። ባለ መጣሩ እንደ ሰነፍ የሚታይ፣ ራሱን የማያውቅ ስንት ባለ ብሩህ አእምሮ አለ?! መማርህ ካንተ አልፎ ለወገን የሚተርፍ ዋጋ ሊኖረው እንደሚችል ተረዳ።
"Education is a better safeguard of liberty than a standing army."
⑥ ራስህን ሁን። የመጣውን ፋሺን ሁሉ ካልሞከርኩ አትበል። ለራስህ ክብር ስጥ። አንተ የማስታወቂያ አሻንጉሊት አይደለህም። አርአያህን ለይ። መልካም ስብእና ያላቸውን እንጂ፣ ያለ ቁም ነገር ስማቸው የገነነ ሰዎችን ለመምሰል አትፍሰስ። አንተ ህሊና የተሰጠህ ክቡር ፍጡር እንጂ በቀደዱለት የሚፈስ የቦይ ውሃ አይደለህም።
"ራሱን ያላገኘ ሌሎችን ሲከተል ይኖራል።"
⑦ ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም። አንተ ዘንድ አላህ ከሰጠህ ሃብት ሁሉ ርካሹ ጊዜህ የሆነ'ለት ያለ ጥርጥር ከስረሀል። ወደ ጨለማ ጥግ ከሚያደርስ የድንግዝግዝ ባቡር ላይ ተሳፍረሀል።
እባክህን ሕይወትህ ላይ አንዳች እሴት በማይጨምሩ ነገሮች ዳግም የማታገኘው ውድ ጊዜህን አታባክን። የምልህ እየገባህ ከሆነ በሙዚቃ ከመመሰጥ፣ ፊልም ጋር ከመርመጥመጥ፣ የፈረንጅ እርግጫ ከማሳደድና መሰል አልባሌ ነገሮችን ራቅ እያልኩህ ነው። እነዚህ ነገሮች ከእለት መዝናኛነት ባለፈ ተሻጋሪ ሱስ የሚሆኑ ወጥመዶች ናቸው።
"ጊዜ ሰይፍ ነው። ካልቆረጥከው ይቆርጥሀል።"
"አንተ የጊዜያት ድምር እንጂ ሌላ አይደለህም። እያንዳንዷ የጊዜ ክፍልፋይ ስታልፍ አንተ ራስህ እያለፍክ ነው።"
⑧ ጓደኞችህን ለይ። ጓደኛህ ወይ የምትጠቅመው ወይ የሚጠቅምህ መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ የሆነ ጓደኛ የፋንዲያ ያክል ዋጋ የለውም። እንዲያውም ያጠፋሀል። በዱንያ ቁም ነገር ላይ ከመድረስ ያሰናክልሀል። አልፎም ኣኺራህን ያጨልመዋል። ኧረ ለመሆኑ አንተ ራስህ ምን አይነት ጓደኛ ነህ? አልሚ ወይስ አጥፍቶ ጠፊ? በል ከዛሬ ጀምሮ ከጓደኛህ ጋር ቁጭ ብላችሁ የአብሮነታችሁን ሂሳብ አወራርዱ። ጓደኝነታችሁ የምትጠቀሙበት እንጂ የምትጎዱበት እንዳይሆን በስርኣት ተመካከሩ።
"ሰው በወዳጁ እምነት ላይ ነው። ስለሆነም አንዳችሁ ማንን እንደሚወዳጅ ይመልከት።"
⑨ መልካም ስነ ምግባርን ተላበስ። አትሸማቀቅ፤ ግን አትኮፈስ። ትሁት ሁን፤ ግን አትልፈስፈስ። ሰከን በል፤ ግን አትፍዘዝ። ረጋ በል፤ አትንጣጣ። ከአንደበትህ ክፉ አይውጣ።
ፊትህ ሁሌ በፈገግታ ይታጀብ። ተግባቢና ለሰዎች ቀላል ሁን። የደረስክበትን ሁሉ በሰላምታ አውደው። በትህትና አጊጥ። በቅንነት አሸብርቅ። "መጣብን" ሳይሆን "መጣልን" የምትባል ሁን። አታጣላ። አታባላ። ሃሜትና ውሸትን ክላ።
"ህዝብ ማለት ስነ ምግባር ነው። ስነ ምግባር የሌለው ህዝብ ካለ አይቆጠርም።"
(10) በትምህርት ሕይወትህ ላይ ሳለህ መዝናኛህን ቁም ነገር መጨበጫ አድርገው። ቁም ነገር አዘል መፃህፍትን አንብብ። ከቻልክ እንደ የመጀመሪያ እርዳታ /first aid/ አሰጣጥ፣ ቴኳንዶ፣ የእጅ ሙያዎች፣ የችግኝ ወይም የጓሮ አትክልት አተካከል፣ እና መሰል ጠቃሚ ስልጠናዎችን ሰልጥን፣ አሰልጥን። አካባቢህን አስተባብረህ አፅዳ።
"ራስን ብቁ ዜጋ ማድረግ ለሀገርም ለወገንም እሴት መጨመር ነው።"
(11) ከህገ ወጥ ፆታዊ ግንኙነት አጥብቀህ ራቅ። ህጋዊ በሆነ መልኩ ተረጋግተህ ለምትደርስበት ነገር በህገ ወጥ መልኩ ለማግኘት እየቸኮልክ ስብእናህን አታቆሽሽ። የሌላን ህይወትም አታበላሽ። ከአላማህም አትሰናከል። ክፉ ምሳሌም አትሁን።
"ስድ ግንኙነት ለህሊና ጠባሳ፣ ለቤተሰብ ጦስ፣ ለህዝብ መቅሰፍት ያስከትላል።"
"ከጓደኞቿ የወጣች ማሽላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ ትሆናለች።"
👉#በዘርህ ከማንም በላይ ከማንም በታች አይደለህም።
ኡስታዝ ሙሐመድ አህመድ ሙነወር(ኢብኑ ሙነወር) አላህ ይጠብቀው
=
የቴሌግራም ቻናል፦
@IbnuMunewor
https://t.me/DeewaSeleffya1448
https://t.me/DeewaSeleffya1448.
የባልን የሞት ዜና ለሚስት በብልሃት የማድረስ ምርጥ ዘዴ
በአንዲት መንደር ውስጥ "ሙቅቢል" የሚባል ሰው ነበር
የአላህ ውሳኔ ሆነና በድገት ሞተ። ጎረቤቶቹ መሞቱን ሲያረጋግጡ
አጠቡት ከፈኑት ከዚያም
ሬሳውን በሳጥን ተሸክመው ወደ ቤቱ ወሰዱት፤
ግን በሩ ላይ ቆመው እየፈሩና እየተጨነቁ፡ "የባሏን መሞት ለሚስቱ ሳናስደነግጣት እንዴት ብለን እንንገራት?" ተባባሉ።
ድንገት ነው የሞተው እንደት ሳናስደነግጥ እናስረዳት በማለት ግራ ገብቷቸው እያለ
አንዱ ቀረብ ብሎ በሙሉ እምነት፡ "ነገሩን ለእኔ ተዉልኝ፤ እኔ ከሴቶች ጋር እንዴት እንደሚወራ አውቃለሁ" አለ።
ከዚያ "ሳጥኑን ይዛችሁ ከቤት በስተጀርባ ተሸሸጉ፤ እኔ ስጠራችሁ ወዲያው አምጡት" አላቸው።
ሰውዬው ሄዶ በሩን አንኳኳ፤ ሚስቲቱም ማነው ብላ
በሩን ከፈተች፡ "ሰላም ነው?
ሰውየውም አንች የሙቅቢል ሚስት ነሽ ብሎ ጠየቃት ?
እሷም አወ ምነው በባሌ ላይ የተፈጠረ ነገር አለእንዴ?" አለችው።
ሰውዬው በተረጋጋ መንፈስ፡ "አይዞሽ፣ ምንም መጥፎ ነገር አልሆነም.. ግን ባልሽ ሙቅቢል ባንች ላይ ሌላ ሚስት አገባ!" አላት።
ሚስቲቱም በቁጣ አብዳ መርገም ጀመረች፡
"በእኔ ላይ ሌላ አገባ?!⁉️
1️⃣አምላክ ይበቀለው!
2️⃣እልም አላህ ያርገው
3️⃣በጁሱ መርዝ እምታጠጣ ይስጠው
እያለች ተራገመች
ከዚያም ሰውዬው ዞር ብሎ
"እልል በይ! አላህ ዱአሽን ተቀብሎሻል ሰምቶሻል!..
አምጡት ወጣቶች!" ብሎ ጮኸ።
ወጣቶቹ ሳጥኑን አምጥተው ፊቷ አስቀመጡት።
ሚስቲቱም ሳጥኑን አይታ ረጋ ባለ ድምፅ፡
"አላህ ይማረው፣ ይህ የአላህ ውሳኔና ፍቃድ ነው..
ዋናው ነገር በእኔ ላይ ሌላ አለማግባቱ ነው!" አለች።
ክክክ
copy
Repost from ተቀርተው ያለቁ ደርሶች
የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ደርሶች
1) ሹሩጡ ሶላት
2) ሪያዱ ሷሊሒን
3) ኪታቡ ተውሒድ
4) ኪታቡ ተውሒድ
5) ሒስኑል ሙስሊም
6) ላሚየቱ ብኒ ተይሚያ
7) ላሚየቱ ኢብኒ ተይሚያ
8) አልአርበዑነ ነወዊያህ
9) አልቀዋዒዱል አርበዕ
10) ሓኢየቱ ብኒ አቢ ዳውድ
11) ዶላሉ ጀመዐቲል አሕባሽ
12) ሸርሑ ሱንና ሊል በርበሃሪ
13) ሠላሠቱል ኡሱል
14) አልቀዋዒዱል አርበዕ
15) ሹሩጡ ሶላት
16) አልዐቂደቱል ዋሲጢያ
17) ዑምደቱል አሕካም
18) አልኢማም ፊ አሕካሚ ሲያም
19) ሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም
20) ሉምዓቱል ኢዕቲቃድ
21) መንሃጁ ሳሊኪን
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የማለዳ መልእክት (51)
~
ቢድዐዎች መጠናቸው ይለያያል።
1. አንዳንዶቹ በመሰረታዊ ኢዕቲቃድ ላይ የተከሰቱ ከባባድ ቢድዐዎች (بدع اعتقادية كبرى) ናቸው። ለምሳሌ የጀህሚያ፣ የሙዕተዚላ፣ የአሻዒራ እና መሰል ቢድዐዎች።
2. ሌሎች ደግሞ በዒባዳዎች ውስጥ የሚከሰቱ (بدع عملية) ናቸው።
ይሄ እንዲሁ በግርድፉ ሲታይ ነው። እንጂ መሀል ላይ ብዙ የተራራቁ የቢድዐ መጠኖች አሉ። በአንድ ምድብ ውስጥ ያሉ ቢድዐዎች ራሱ መጠናቸው በጣም ይራራቃል። ለምሳሌ የጀህሚያ ቢድዐ ከአሽዐሪያ በጣም የከፋ ነው። "አላህ ከፍጡሩ ጋር ተዋህዷል" ወይም "ሰፍሯል" የሚለው እንደነ ሐላጅ፣ ኢብኑ ዐረቢ፣ ኢብኑል ፋሪድ፣ ዐፊፉ ቲልሚሳኒይ፣ ኢብኑ ሰብዒን፣ ... ያሉ ሱፍዮች ቢድዐ ክብደቱ እንግዳ ዒባዳዎችን ወይም የዒባዳ አፈፃፀሞችን ካመጡ አካላት ቢድዐ በጣም የከፋ ነው። የሁለተኞቹ ክፍሎች ቢድዐ ከመጀመሪያዎቹ በንፅፅር በጣም ያነሰ ነው። የመጀመሪያዎቹ ከኢስላም ጠርጎ የሚያስወጣ ነው።
ይህንን መለየታችን
1ኛ፦ ጥፋቶችን የክብደታቸውን መጠን እንድንለይ ያግዘናል።
2ኛ፦ በዚሁ መሰረትም ለአጥፊዎቹ የሚኖረን አቋምና አያያዛችንም ይለያያል። መቼስ በሁሉም ላይ ያለን አቋም እንደ ሳሙና አንድ ቁርጥ ሊሆን አይችልም።
2 ኛ፦ ቢድዐ ከወንጀል የከፋ እንደሆነ የሚጠቁሙ የቀደምት ዑለማኦችን ንግግሮች ያላግባብ እንዳንረዳም ያግዘናል። እንደ ዝሙት፣ ነፍስ ማጥፋት፣ ወለድ (አራጣ) መብላት፣ ... ያሉ ከባባድ ወንጀሎች (کبائر الذنوب) ከተወሰኑት የቢድዐ አይነቶች (بدع عملية) ያነሱ አይደሉም፣ የከበዱ እንጂ። በመሰረታዊ ዐቂዳ ላይ የመጡ ከባባድ ቢድዐዎች ደግሞ ከተዘረዘሩት ከባባድ ወንጀሎች (کبائر الذنوب) በጣም የከፉ እንጂ ያነሱ ጥፋቶች አይደሉም። እና የቢድዐን አደጋ ለማጉላት የምናደርገው "ቢድዐ ከወንጀል የከፋ ነው" የሚለው ገለፃ ባላሰብነው አቅጣጫ እነዚህን ወንጀሎች አቅልሎ እንዳያሳይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
ወላሁ አዕለም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 24/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from الّدَاء و الّدَوَاء 📖
• قَال ابْـنُ القَيِّـمُ رَحِمَـهُ الله : -
«المؤمن المخلص لله من أطيب الناس عيشًا، وأنعمهم بالًا، وأشرحهم صدرًا، وأسرّهم قلبًا، وهذه جنة عاجلة قبل الجنة الآجلة.
قال النبي ﷺ : " إذا مررتم برياض الجنة فارتعوا، قالوا: وما رياض الجنة؟ قال «حِلَق الذكر»".»
- الداء و الدواء (٤٥٩).📚
Repost from አህመድ ፈንታቢል
💡እውቀት የሌለው አካል ያለ እውቀት ሺርክ ቢሰራ ስራው ሽርክ ነው ሰውየው ግን በጅህልናው ዑዝር ይሰጠዋል ይላሉ ሸይኽ ፈውዛን
Repost from تَحْتَ ظِلِّ الْعَرْش
➡️ 1 የአሜሪካ ዶላር በ 2,700,000 የኢራን ሪያል እየተገበየ ይገኛል።
ጉድ በል👌 ምንዛሬ ይህ መረጃ እንዴት ነው ❗️
መሳሳት ተፈጥሮአዊ ነው፤ ማረም ግን የብቃት መለኪያ ነው! 📖✨
➲
መሳሳት የሰው ልጅ ባህሪ ነው። ዋናው ቁምነገር አለመሳሳታችን ሳይሆን ስህተታችንን አይቶ የሚነግረንን አዳምጠን ለማስተካከል ፈቃደኛ መሆናችን ነው።
በተለይ ከቅዱስ ቁርዓን ትምህርትና ሂፍዝ ጋር በተያያዘ፦
🔹 ስህተትሽን/ህን የሚነግርሽን/ህን አመስግኚ/ን፡ በሂፍዝሽ/ህ ወቅት ስህተትሽን/ህን እየሰማ ዝም የሚልሽ/ህ አይጠቅምሽም/ህም። ጉድለትሽን/ህን አርሞ የሚያስተካክልሽ/ህ አካል ነው ትክክለኛው ውለታው የሚገባው። «الَّذِي يَقْرَأُ القُرْآنَ وَهُوَ مَاهِرٌ بِهِ مَعَ السَّفَرَةِ الكِرَامِ البَرَرَةِ، وَالَّذِي يَقْرَأُ القُرْآنَ وَيَتَتَعْتَعُ فِيهِ وَهُوَ عَلَيْهِ شَاقٌّ لَهُ أَجْرَانِ» (رواه البخاري ومسلم) 🔹 ከመጀመሪያው አስተካክለሽ/ህ ቅሪ/ቅራ፡ ገና ከጀማሪነትሽ/ህ ጀምረሽ/ህ በትክክለኛው መንገድ ቅሪ/ቅራ። ከነስህተቱ ከተሀፈዘ በኋላ በኋላ ላይ ለማስተካከል መሞከር እጅግ አስቸጋሪ ይሆንብሻል/ሃል። 🔹 የዛሬው ጥብቅነት የነገው ስኬት ነው፡ ስህተትን በዋዛ የማያልፉ ጥብቅ አስተማሪዎች መኖር፣ ነገ ውጤቱን አይታችሁ እንድታመሰግኑ ይሆናል።http://t.me/eqrai_jemea
Repost from ስለ ቀልባችን
📢 ታላቅ የምስራች ለመላው የ«ስለ ቀልባችን» ቤተሰቦች!
🌍 «ስለ ቀልባችን» ለዓለም ተደራሽ ሊሆን የራሱን ዓለም አቀፍ ዌብሳይት አዘጋጅቶ ጨርሷል!
🌐በየትኛውም የዓለም ጥግ ለሚገኙ ሙስሊሞች ተደራሽ የሆነ፣ ዘመኑን የዋጀ ሁሉን አቀፍ ኢስላማዊ ዲጂታል መድረክ ይዘንላችሁ ብቅ ብለናል!
🌐 በድረ-ገጻችን ምን ምን ያገኛሉ?
🇪🇹በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የምስጢር አገልግሎት፦ ማንነትዎ ሳይገለጽ ማንኛውንም ጥያቄ በድረ-ገጹ ለኡስታዝ ጠይቀው፣ አስተማማኝ መልሱን በኢሜይልዎ ብቻ በምስጢር የሚቀበሉበት ልዩ ሲስተም!
⚜️ውብ የቁርኣን ቲላዋዎች፦ ቀልብን የሚያረጥቡ የዓለም አቀፍ ቃሪኦች ቲላዋ።
📚 ዘመናዊ ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት፦ ጠቃሚና ድንቅ ኪታቦች (PDF) ከአውዲዮ ማብራሪያዎቻቸው ጋር በአንድ ላይ ተቀናጅተው የቀረቡበት።
🎥 አስተማሪ ዳዕዋዎችና ቪዲዮዎች፦ ከ1 ደቂቃ አጫጭር መልእክቶች እስከ ጥልቅ ሙሉ የቪዲዮ እና አውዲዮ ትምህርቶች።
📖 የወጣቶች፣ የፍቅርና የትዳር መመሪያዎች፦ በወጣቶች ህይወት፣ በፍቅር፣ በትዳር ፣በሱስ እና በቀልብ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮሩ መፍትሔ አዘል ምክሮች።
❓የጥያቄና መልስ ማህደር፦ ከዚህ ቀደም ምላሽ የተሰጠባቸው በርካታ አስተማሪ ጥያቄዎችና ምክሮችን በቀላሉ የሚገኙበት።
✈️የድረ-ገጻችን ልዩ ገጽታዎች፦
🖥 በ3 ቋንቋዎች የቀረበ፦አማርኛ | እንግሊዘኛ | ዐረብኛ-(በዓለም ዙሪያ ላሉ ሙስሊሞች ምቹ እንዲሆን)
📲 ለሁሉም ምቹ፦ በስልክም ሆነ በኮምፒውተር እጅግ ፈጣንና ለመጠቀም ቀላል
🇷🇺አሁኑኑ ድረ-ገጻችንን ይጎብኙ፤ ለወዳጅ ዘመድዎም በማጋራት የበጎ ነገር ተካፋይ ይሁኑ!
🔗 አሁኑኑ ይጎብኙን፦
👉 www.sileqelbachin1.com
👉 www.sileqelbachin1.com
ስለ ሽርክ የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት ማዳመጥ ይችላሉ ➍❹አከባቢ ሙሓደራወች❶ሽርክ ታላቁ በደል ❷ከሽርክ ለመውጣት ❸የቀብር አምልኮ ❹ሽርክ ሲፈርስ ❺ሽርክ ላይ መዳረሻ ምክናያቶች ❻ለምን ሽርክ ይፈፀማል ❼ሸይኽ ኑሩ ሁሴን እና ሽርክ ➑በዱአ ስም የሚሰራ ሽርክ ❾ የሽርክአስከፊነት ➓ትንሹ ሽርክ ❶❶ሽርክ እና ተያያዥ ነገሮች ❶❷ሽርክ ምንድነው ❶❸የአብሬት ሽርክ ❶❹መጠበቅ በአላህ ብቻ ነው ❶❺የሽርክ አደገኛነት ❶❻ወሎ ላይ ሽርክ በየአይነቱ ❶❼ስለሽርክ ❶➑ሽርክ ❶❾ሽርክ ከወንጀለኞች ሁሉ የከፋ ነው ❷0የሽርክ አደጋ ❷❶ከሽርክ ነፃ መውጫ መንገዱ ❷❷አብሬት እና ሽርክ ❷❸ሽርክ ሸይኽ አወል ❷❹ሽርክ እና ማህበረሰባችን ❷❺ከአላህ ውጭ ማረድ ሽርክ ነው ❷❻በገድ ማመን ሽርክ ነው ❷❼ሽርክ ሲኮታኮት ❷➑ትንሹ ሽርክ ዩዩልኝ እና ይስሙልኝ ❷❾አላህ ሽርክን አይምርም ❸0የሽርክ ሰወች ቅጥፈት ❸❶ርዕሱ አይቀርም ❸❷ደገር እና ሽርክ ❸❸የሽርክ አስከፊነት ❸❹ስለ ሽርክ እና ንፍቅና ❸❺ሽርክ ማለት ምን ማለት ነው ❸❻ሽርክ እና ውደታ ❸❼በመታዘዝ የሚመጣ ሽርክ ❸➑ግጥም ስለ ሽርክ ❸❾ሽርክን ኑዛዜ ❹0የሽርክ ተግባር ❹❶የሽርክ ጠበቃ አትሁን ❹❷መጠንቆል ሽርክ ነው ❹❸የአህባሽ ቲቪ እና ሽርክ ❹❹ሽርክን ተጠንቀቁ
Repost from قناة د. عيسى السعدي
رأى سعيد بن المسيب رجلا يعبث في صلاته ؛ فقال : لو خشع قلب هذا خشعت جوارحه .
شرح السنة
٣ / ٢٦١
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኣደማዊ እንጂ ኢብሊሳዊ አትሁን!
~~~~~~~
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል:–
·
"ኣደም በወነጀሉ ጊዜ ተመልሰዋል። በዚያኔ ጌታቸው መረጣቸው። አቀናቸውም።
·
ኢብሊስ በወንጀሉ በፀናና በተሟገተ ጊዜ አላህ ረገመው። አራቀው።
·
ስለዚህ ከወንጀሉ የተመለሰ ሰው አደማዊ ሲሆን በጥፋቱ የፀናና በቀደር የተሟገተ ኢብሊሳዊ ሆኗል።
·
ስለዚህ እድለኞች አባታቸውን ሲከተሉ እድለ ቢሶች ደግሞ ጠላታቸውን ኢብሊስን ነው የሚከተሉት።
አላህ ቀጥተኛውን ጎዳና እንዲመራን እንማፀነዋለን። የነዚያ አላህ ያጣቀማቸው የሆኑት የነብያት፣ የሲዲቆች፣ የሸሂዶችና የደጋጎቹን መንገድ።
·
[መጅሙዑል ፈታዋ: 8/64]
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from N/a
«ሕመምህን ሰው እንዲረዳህ ማስረዳት አለብህ፤ አላህ ግን ሳይነገረው የልብህን ሕመም እና የውስጥህን ጭንቀት ያውቃል።»
አንዳንዴ በሕይወታችን ውስጥ በቃላት ልንገልጸው የማንችለው፣ ለሰው አውርተንም ቀላል የማይሆን ከባድ የውስጥ ሕመም ያጋጥመናል።
ለቅርብ ሰው እንኳን ለማስረዳት ቃላት ያጥሩናል፤ አሊያም ደግሞ "ሰው አይረደኝም" በሚል እጣፋንታ ዝምታን እንመርጣለን።
ሰው ሕመምህን እንዲረዳህ በረጅም አብራርተህ ማስረዳት አለበት፤ ያን ያህል ደክመህ አብራርተህ እንኳን አንዳንዴ ሙሉ በሙሉ ሊረዳህ አይችልም።
አላህ ግን እንዲህ አይደለም!
እሱ የልብህን ትርታ፣ የዓይንህን ዕንባ፣ እና በውስጥህ የሚመላሰውን ጭንቀት ሁሉ ሳይነገረው ያውቃል።
በልብህ ውስጥ የተቀበረውን ስቃይ ለመግለጽ ቃላትን ማደራጀት አይጠበቅብህም።
ዝም ብለህ በዓይንህ ዕንባና በልብህ ስብራት ወደ እሱ ስታዞር፣ እሱ የውስጥህን ስቃይ ሰምቶ መልስ ይሰጣል።
የሰው ረዳትነት ወሰን አለው ሰው ሊያዝንልህ ይችላል፣ ሊያዳምጥህ ይችላል፤ ነገር ግን የልብህን ክብደት ከውስጥህ አውጥቶ ሊቀንስልህ አይችልም።
የአላህ እውቀትና እዝነት ግን ወሰን የለውም ያልተናገርከውን ያውቃል፣ ያላወጣኸውን የውስጥ ቁስል ያክማል፣ የልብህንም ስብራት ይጠግናል።
ስለዚህ፣ ሰው አልተረዳኝም ብለህ አትጨነቅ። የልብህን ጭንቀትና ሕመም የሚያውቅ፣ ሳይናገሩ የሚያዳምጥ፣ ሲለምኑት ደግሞ የማይሰለች ጌታ አለህ።
ውስጣችሁን በእሱ ላይ ጣሉ፤ በዝምታችሁ ውስጥ ያለውን ድምፅ እሱ ብቻ በትክክል ይሰማዋል!
@BerhanFelega
@BerhanFelega
Repost from አል ኢርሻድ የሠለፍዮች ስቱድዮ
➥ኡዝር ቢል ጀህልን የተመለከቱ ወይይቶች እና ሙሓዶራዎች ለማግኘት በዚህ በኩል ይግቡ
🎙በኡስታዝ ኸድር አህመድ ያደረገውን ውይይት
🎙ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ስለ ዑዝር ሙሓዶራ
🎙በኡስታዝ አቡ ዒምራን ተከታታይ በያን ስለዚህ መስዓላ
ወደ ድምፆች ለማግኘት 👇👇
https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin/4774
https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin/4774
