ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше4 387
Подписчики
-424 часа
+2487 дней
+1 44230 дней
Архив постов
በወለጋ የአማራ ንጹሐን ጭፍጨፋ በተባባሰበት ወቅት የአፋብን አንሻ ሰይድ 4ኛ ዕዝ ለተከታታይ አራት ወራት ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ ማስመረቁን የይበልጣል መኮነን አዲስ ዓለም ክፍለ ጦር አስታወቀ
ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ለዘመናት የዘለቀውን የሕዝብ አብሮነትና አገራዊ አንድነት በመሸርሸር ላይ የሚገኘውና በንጹሐን ዜጎች ደም ሥልጣኑን ለማስቀጠል የሚታገለው የብልጽግና አገዛዝ፣ በወለጋ ምድር የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን ኢላማ ያደረገ ስልታዊና መዋቅራዊ ጭፍጨፋውን አጠናክሮ ቀጥሎበታል።
በሁለቱ የወለጋ ዞኖች ማለትም በምስራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ የንጹሐን አማራዎች ግድያ፣ ማፈናቀል፣ የቤትና ንብረት ውድመት፣ እንዲሁም ጅምላ እስራት በፀረ-አማራውና ፀረ-ኢትዮጵያዊ በሆነው የብልጽግና ሥርዓት አሁንም አጠናክሮ መቀጠሉንና በተለይም በኪረሙ እና ጊዳ ወረዳዎች ውጥረቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የአፋብን አንሻ ሰይድ 4ኛ ዕዝ የይበልጣል መኮነን አዲስ ዓለም ክፍለ ጦር አስታውቋል።
ይህ አረመኔያዊ ወረራና የሕዝብ እልቂት በስፋት በገፋበት በአሁኑ ወቅት፣ የሕዝቡን ህልውና ለመታደግና የአገዛዙን ግፍ በጽናት ለመመከት የሚደረገው ሕዝባዊ ትግል በአዲስ ወታደራዊ አቅም እየጎለበተ ይገኛል።
በዚህም መሠረት የአፋብን አንሻ ሰይድ 4ኛ ዕዝ ስር የሚገኘው ለጠላት አይበገሬው የይበልጣል መኮነን አዲስ ዓለም ክፍለ ጦር ለተከታታይ አራት ወራት ያሰለጠናቸውን አዳዲስ ተዋጊ ፋኖዎች በቀን 08/02/2019 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ማስመረቁን አስታውቋል።
በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የእዝ አመራሮች እንዲሁም የአንሻ ሰይድ 4ኛ ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ሻለቃ ሀብታም ጥላሁን ተገኝተው ለተመራቂዎች የትግል መመሪያና የሥራ አቅጣጫ አስተላልፈዋል።
አዛዡ በመልእክታቸውም ተመራቂዎች ይህንን ዘራፊና ወራሪ ሥርዓት በልበ ሙሉነት፣ በቁርጠኝነትና በታማኝነት ታግለው የተጣለባቸውን የታሪክና የሕዝብ አደራ በአስተማማኝ ሁኔታ እንደሚወጡ ያላቸውን ሙሉ እምነት ገልጸዋል። አክለውም ይህ ነፍሰ-በላ ሥርዓት፣ የአገዛዙ ሠራዊትና የክልሉ ጥምር ኃይል የሆነው ገዳ ኮማንዶ በቅርብ ሰዓት ግብዓተ-መሬቱ እንዲፈጸምበትና የማስወገድ እርምጃው እንዲፋጠንም ጥሪ ማቅረባቸውን ክፍለ ጦሩ አብራርቷል።
የፋኖን ድልና የሕዝቡን የህልውና ተጋድሎ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በተደረገው በዚህ የምረቃ መድረክ ላይ ሌሎች የክፍለ ጦሩ አመራሮችም የውጊያ ዝግጁነታቸውንና የቁርጠኝነት መልእክታቸውን ማስተላለፋቸውን ክፍለ ጦሩ አስታውቋል።
ጥቅምት 12/2019
አፋብን አንሻ ሰይድ 4ኛ ዕዝ የይበልጣል መኮነን አዲስ ዓለም ክፍለ ጦር
የዘረፈጁን ብልፅግና አገዛዝ የሚያወግዝ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ በሬማ ከተማ ተካሔደ!
ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም
ከአገዛዙ የጭቆና ቀንበር በጀግናው ሰራዊታችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ነፃ የወጣችው በመርሀቤቴ አውራጀ የሚዳ ሬማ ወረዳ የሬማ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም የዘረፈጁን የብልፅግና አገዛዝ የሚያወግዝ ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ በማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ ማካሔዳቸውን የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ከስፍራው አስታውቋል።
በሬማ ከተማ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ አገዛዙ በአንድ አንድ የወረዳና የዞን ከተሞች ህዝቡ በገዛ ፍቃዱ "የድጋፍ ሰልፍ አደረገልኝ" በሚል የተደረገውን አስገዳጅ ሰልፍ ያጋለጡ ሲሆን በሰልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮችም ተሰምተዋል።
ድምፃቸው ከፍ ብለው ከተሰሙ መፈክሮች ውስጥ ዋነኛው አገዛዙ "በሴይፍ ያላሳካውን ፖለቲካ በሰልፍ አያሳካውም!" በሚል የተወገዘ ሲሆን፣ "የእኛ አጀንዳ ህልውናችን እንጅ የብልፅግና የጦርነት ማስፈፀሚያ የወደብ አጀንዳ አይደለም!" ፣ "የኛ ወደብ በህይዎት የመኖር ጥያቄ ነው!"፣ "ብልፅግና የኤምሬት የውክልና ጦርነት አስፈፃሚ! ተላላኪ! ድርጅት ነው!" ፣ "የአማራ ግድብም ወደብም በህይዎት የመኖር ዋስትናው ሲቀድም ነው!" የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል።
ዘረፈጁ የብልፅግና አገዛዝ በነቂስ ለሰልፍ የወጣውን ህዝብ ለመበተን የድሮን ቅኝት ቢያደርግም አይበገሬው የሬማ ከተማ ህዝብ በንቂስ ወጥቶ ድምፁን አሰምቷል ሲል የኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል በምስል አስደግፎ መረጃውን ከስፍራው አድርሷል።
" ክብር ለትግሉ ሠማዕታት!
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
የዘረፈጁን ብልፅግና አገዛዝ የሚያወግዝ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ በሬማ ከተማ ተካሔደ!
ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም
ከአገዛዙ የጭቆና ቀንበር በጀግናው ሰራዊታችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ነፃ የወጣችው በመርሀቤቴ አውራጀ የሚዳ ሬማ ወረዳ የሬማ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም የዘረፈጁን የብልፅግና አገዛዝ የሚያወግዝ ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ በማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ ማካሔዳቸውን የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ከስፍራው አስታውቋል።
በሬማ ከተማ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ አገዛዙ በአንድ አንድ የወረዳና የዞን ከተሞች ህዝቡ በገዛ ፍቃዱ "የድጋፍ ሰልፍ አደረገልኝ" በሚል የተደረገውን አስገዳጅ ሰልፍ ያጋለጡ ሲሆን በሰልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮችም ተሰምተዋል።
ድምፃቸው ከፍ ብለው ከተሰሙ መፈክሮች ውስጥ ዋነኛው አገዛዙ "በሴይፍ ያላሳካውን ፖለቲካ በሰልፍ አያሳካውም!" በሚል የተወገዘ ሲሆን፣ "የእኛ አጀንዳ ህልውናችን እንጅ የብልፅግና የጦርነት ማስፈፀሚያ የወደብ አጀንዳ አይደለም!" ፣ "የኛ ወደብ በህይዎት የመኖር ጥያቄ ነው!"፣ "ብልፅግና የኤምሬት የውክልና ጦርነት አስፈፃሚ! ተላላኪ! ድርጅት ነው!" ፣ "የአማራ ግድብም ወደብም በህይዎት የመኖር ዋስትናው ሲቀድም ነው!" የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል።
ዘረፈጁ የብልፅግና አገዛዝ በነቂስ ለሰልፍ የወጣውን ህዝብ ለመበተን የድሮን ቅኝት ቢያደርግም አይበገሬው የሬማ ከተማ ህዝብ በንቂስ ወጥቶ ድምፁን አሰምቷል ሲል የኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል በምስል አስደግፎ መረጃውን ከስፍራው አድርሷል።
" ክብር ለትግሉ ሠማዕታት!
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
#ጀግንነት
#ወኔ
#አልበገርባይነት
#የነጻነትታጋይ
#ቁጭት
በተግባር ያያቸው ብቻ ሳይሆን ግንባራቸውን አይቶ መገመት አይከብድም #ከቤ እና #ተስፍሽ ደሞቼ ከይፋቶቹ ግድም ከዴቭ ወንድሞች
በሞያሌ ዳግም አመፅ ተቀሰቀሰ❗️
ከወለጋና ከአርሲ አማራዎችን ለማፅዳት የሴራ ጥቃት የከፈተው የኦሕዴድ መራሹ የብልፅግና አገዛዝ ከሞያሌ ከተማ ሶማሌዎችን አፈናቅሎ ከተማውን ለመሰልቀጥ ጥረት ማድረጉን ተከትሎ ዳግም አመፅ መቀስቀሱ ታውቋል።
በሞያሌ ከተማ እንደገና በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች ወደ ኬንያ በመሰደድ ላይ ናቸው።
በኦሮሚያ እና በሱማሌ ክልሎች የድንበር አወሳሰን ምክንያት በሞያሌ ከተማ ትላንት ረጋ ብሎ የነበረው ግጭት ዛሬ ማለዳ እንደገና መቀስቀሱ ተገለጸ።
ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በከተማዋ ውስጥ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ የሚሰማ ሲሆን፣ የከተማዋ መደበኛ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ቆሟል።
በከተማዋ ባለው የአስፓልት መንገድ ግራና ቀኝ በሱማሌ እና በኦሮሞ ተከፍሎ በሚገኘው የሞያሌ ከተማ፣ የይገባኛልና የባለቤትነት ጥያቄን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ይህ ግጭት ከቀበሌ ሁለት ተነስቶ አሁን ላይ በሙሉ ከተማዋ ውስጥ ተስፋፍቶ ይገኛል።
የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ከተማዋ የገቡ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ተኩሱን ማስቆም እንዳልተቻለ ታውቋል።
ከዚሁ አመፅ ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ እንዲሁም ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡት ዋና ዋና መንገዶች ሙሉ በሙሉ ዝግ ሆነዋል።
የግጭቱን መበርታት ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ወደ ኬንያ ሞያሌ በመሻገር ላይ ይገኛሉ። ዛሬ ጠዋት ብቻ በርካታ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ወደ ኬንያ መግባታቸው የተረጋገጠ ሲሆን፣ ሌሎች ነዋሪዎችም ከተማዋን ለቀው በመውጣት ላይ ናቸው።
ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም
አረመኒው የብልፅግና ሰራዊት ለደም ግብሩ የንፁሀንን ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል ።
ተስፋ የቆረጠው የብልፅግናው ሃይል በቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክፍለ ጦር ቀጠና በባሶ ሊበን ወረዳ ሻይ ቤት ቁጭ ያሉ ንፁሀንን የሻይ ቤቱን ባለቤት ጨምሮ ሰባት ሰወችን (7)በጥይት የደበደበ ሲሆን አምስት(5) ሰወች ወዲያውኑ የተሰው ሲሆን ሁለቱ ቁስለኛ መሆናቸው ተረጋግጧል ። አንድም ቀን የንፁሀንን ደም ሳያፈስ ውሎ አድሮ ማያቀው ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ ጦር ሻይ ቤት ቁጭ ብለው ባሉበት ደርሶ በጅምላ የገደላቸው 👇🏻
1ኛ አጉማስ ስማቸው የተገደለች
2ኛ አብኔ የተገደለች
3ኛ ይድነቅ መንግስቴ (የሻይ ቤቱ ባለቤት) የተገደለች
4ኛ ቁሜ አመራ የተገደለች
5ኛ ከባድ መንበሩ የተገደለ
6ኛ አወቀ ጌታቸው የቆሰለ
7ኛ ደርብ ላቀ የቆሰለ ሲሆን ከታች ከሟቾቹ መካከል ገሚሶቹ ከታች በምስሉ የሚታዩት ናቸው ።
አፋብን ቴዎድሮስ 2 ኛ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳና ጊዳ ኪረሙ ወረዳዎች ላይ ከጥቅምት 09/2019 ዓ/ም ጀምሮ የክልሉ ታጣቂዎች ዳግም በከፈቱት ጥቃት በርካታ ንፁኋኖች ሲገደሉ 3 ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ታወቀ።
በጊዳ አያና ወረዳ አሊ ቀበሌ ላይ ተጀምሮ ወደ አባጆ መንደር የተስፋፋው ጥቃቱ፡ አድማሱን በማስፋት በጊዳ ኪረሙ ወረዳ ወዴሳ ዲማ ቀበሌ ድረስ ዘልቆ በርካታ ንፁኋን ወገኖች በገዳ ኮማንዶና በሌሎች የክልሉ ታጣቂዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል።
ከንፁኋኖች መገደል በተጨማሪ አሊ ቀበሌ፣ አባጆ እና ወዴሣዲማ ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ታውቋል።
ከሳምንታት በፊት የክልሉ ታጣቂዎች በአከባቢው በፈፀሙት ጥቃት፡ ከአንዶዴ፣ ከመንደር 03ና መንደር 22 እንዲሁም ከሌሎች አከባቢዎች ተፈናቅለው በአሊ ቀበሌ ከ50ሺህ በላይ ተፈናቃይ ወገኖች ተጠልለው እንደነበር ይታወቃል።
ታጣቂዎቹ ተፈናቃዮቹን ያነጣጠረ ጥቃት በመፈፀም ነው ህፃናትና አቅመ ደካሞችን ጨምሮ የንፁኋንን ሕይወት በገፍ የቀጠፉትና መንደሮቹን ያወደሙት።
በማዕከላዊ ዕዝና በምዕራብ ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ሽፋን ሰጭነት፡ የአባ ገዳ ኮማንዶ፣ የረጴ ሎላ፣ የጋቼና ሲርና እንዲሁም የሚኒሻ ኃይልና በእነዚህ ታጣቂዎች ሽፋን የሚሰጣቸው ቆንጨራና ሌሎች ስለታማ መሣሪያዎችን የታጠቁ የቄሮ ቡድን አባላት በቅንጅት ከጥቅምት 09/2019 ዓ/ም ጀምሮ በከፈቱት ዘግናኝ ጭፍጨፋ ተፈናቃይ ወገኖችን ጨምሮ ሰብል በመሰብሰብ ላይ የነበሩ አርሶ አደሮች ናቸው የተገደሉት።
በጊዳ አያና ወረዳ አሊ ቀበሌ ላይ የተጀመረው ጥቃቱ፡ በቀበሌዋ ተጠልለው ከነበሩ ተፈናቃይ ወገኖች መካከል ህፃናትና አረጋውያንን ጨምሮ በርካታ ንፁኋኖች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።
በተጨማሪም የቀበሌዋ ነዋሪ የሆኑ የአኩሪ አተር ሰብል በመሰብሰብ ላይ የነበሩ ከ35 በላይ አርሶ አደሮች በአንድ ቦታ ብቻ ሲገደሉ፡ ቀሪው ሕዝብ ሕይወቱን ለማትረፍ በየአቅጣጫው መበተኑንና መንደሪቷም ሙሉ በሙሉ መውደሟን ነው ለማረጋገጥ የተቻለው።
ጥቃቱ አድማሱን አስፍቶ በወረዳው ወደ አባጆ ቀበሌ የተሸጋገረ ሲሆን፡ በዚህም ንፁኋኖች በገፍ ተገድለዋል፣ ሀብት ንብረትም ተዘርፎ ወደ አንገር ጉቲን ከተማ ተጭኖ ተወስዷል፣ መንደሪቷም መውደሟን ጣቢያችን ለማወቅ ችሏል።
የክልሉ ታጣቂዎች በመከላከያ ሠራዊቱ በሚሰጣቸው የከባድ መሣሪያ ሽፋን ታግዘው ለአሊና ለአባጆ ቀበሌዎች አጎራባች ወደሆነችው በጊዳ ኪረሙ ወረዳ ወዴሣ ዲማ ቀበሌ በመሸጋገር በርካታ የአማራ ተወላጆችን በገፍ መግደላቸውንና የአርሶ አደሩን ሰብል ጨምሮ መኖሪያ ቤቶችን ማውደማቸው ታውቋል።
አሳምንታት በፊት በተፈፀመባቸው ጥቃት ለጥቂት ተርፈው ከቤት ንብረታቸው በመፈናቀል በአሊ ቀበሌ ተጠልለው የነበሩ ንፁኋኖች፡ ዛሬም በድጋሚ በተከፈተባቸው ጥቃት በርካቶች ሕይወታቸው ሲቀጠፍ፡ ቀሪዎቹ ለዳግም መፈናቀል ተዳርገዋል።
ቀሪዎቹ በአሁን ሰዓት ሕይወታቸውን ለማትረፍ በየጫካው የተበተኑ ቢሆንም፡ የሚቀምሱት እህል ውሃ በማጣታቸው በረሃብ እየሞቱ መሆኑም ነው ጣቢያችን ያረጋገጠው።
ምስራቅ ግንባር ጀብደኛው ምኒልክ 1ኛ ዕዝ 15ኛ ኮር 154ኛ ክፍለጦር በርከታ አዲስ ምልምል የፋኖ ሰራዊት አባላትን ለሶስተኛ ጊዜ አስመረቀ!
በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ፈር ቀዳጅ ከሆኑት የቁርጥ ቀን ህዝቦች ውስጥ ባለ ታሪኩ አምኃራ ሳይንት አንዱ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት አምኃራ ሳይንት በሁለት ግዙፍ ወረዳዎች የተደራጀ ሲሆን በሁለቱም ቀጠናዎች ግዙፍ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ኃይል እያንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
ይህንን ግዙፍ ኃይል የበለጠ እንዲገዝፍ ለወጣቶች ወታደራዊ ስልጠና በመስጠት ወደ ህልውና ትግሉ መቀላቀል የወቅቱ ትልቅ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ አብይ ጉዳይ መነሻነት ነው" የአምኃራ ሳይንት ዴንሳ ወረዳ የሚንቀሳቀሰው የአፋብን 1ኛ ምኒልክ ዕዝ 15ኛ ኮር 154ኛ ክፍለጦር ለ3ኛ ጊዜ ግዙፍ ጦር አስመርቋል ፡፡
የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል የአማራን ህዝብ ከማንቃት በተጨማሪ ወታደራዊ ዝግጅት፣ ስልጠና፣ ጠላትን መምታት፣ ራሱን የማስከበር እና የህልውና አደጋውን የመቀልበስ ተጋድሎውን አጠናክሮ ቀጥሏል።
በዚህ አስገዳጅ ምክንያት ነው የአፋብን 1ኛ ምኒልክ ዕዝ 15 ኮር 154 ክፍለጦር በርካታ አድስ ምልምል ሰልጣኞችን በቀን 11/2/2019 ዓ.ም በደማቅ ስነ -ስርዓት ያስመረቀዉ ፡፡
ሰልጣኞች በምረቃ ስነ ስርዓቱ ወቅት እንደተናገሩት በስልጠና ወቅት የወሰዱትን ወታደራዊ ስልጠና በመተግበር ጠላትን ድባቅ የመምታት ከፍተኛ ሞራል እና ዝግጁነት መታጠቃቸውን የተናገሩ ሲሆን በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ በአካል የተገኙት የአፋብን አባት አርበኞች ምክርቤት ም/ሰብሳቢ ሻለቃ አብነው ታደሰ በበኩላቸው ስልጠናው ተጠናክሮ መቀጠል እና የዘወትር ዝግጁነት አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ጥቅምት 12/ 2019 ዓ/ም
⚫️#የአምባገነኑ_የአጥፍቶ_ጥፋት_ጥቃት‼️
ዘረፈጁ የአብይ አህመድ ብልፅግና በወደር አልባ ጭካኔው ለአመታት ህዝባችን ላይ የመከራ ዶፍ ሲያዘንብ መቆየቱ የሚታወቅ ነው ። ይህ አረመኔ ስርዓት በእግረኛ ሰራዊቱ ሲቭሊያን ላይ የሚፈፅመው ግፍ አላረካው ብሎ አየር ሀይሉን ተጠቅሞ ንፁሃንን ፣ነፍሰጡር እናቶችን ፣ህፃናትን ፣አረጋውያንን እንዲሁም የህዝብ መገልገያ ተቋማትን ጨምሮ በጅምላ እያወደመ ይገኛል‼️
ትላንት ማለትም ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም በ በጎጃም (አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ ) ፋግታ ለኮማ ቀጠና በተፈፀመ የጀት ድብደባ ስድስት (6)ከብት እና አራት (4)ፍየል የገደለ መሆኑ ይታወቃል። ይህ ተስፋ የቆረጠ ስርአት ህፃናትን በጅምላ ለመጨረስ አልሞ ለዚህ አሳፋሪ ተግባር አየር ሀይሉን እየተጠቀመ ይገኛል ።በዛሬው እለት ደግሞ #በጎንጅ_ቆለላ ወረዳ የሚገው #አንጎፌ ትምህርት ቤት በስርአቱ #የድሮን_ጥቃት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
...በምስሉ የምትመለከቱት በቀን 10/2/2019 ፋግታ ለኮማ በተፈፀመ የጀት ድብደባ የተገደሉ እንስሳት ናቸው
አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ !
©አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!
ለመላው ሠራዊታችን በሙሉ፦ አንደሚታወቀው የተሰጣችሁን ወታደራዊ ግዳጅ በየግንባሩ ሁሉ በብቃት እየተወጣችሁ ትገኛላችሁ። የጠላትን የማጥቃት አቅም ሙሉ በሙሉ አዳክማችሁታል። ስለሆነም በመሬት ላይ የተሸነፈው አገዛዝ በአየር ላይ ጥቃት ጉዟችንን ለመግታት የሚያደርገው ሙከራ አንዳችም ለውጥ እንደማያመጣ ይታወቃል። ይሁን እንጅ አላስፈላጊ መስዋዕትነትን ለመቀነስ ሲባል በየግዳጅ ቀጠናችሁ ሆናችሁ መሰባሰቦችን በመቀነስ ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን።
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
— አርበኛ አበበ ሙላቱ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወታደራዊ ቃል አቀባይ
• ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም
◦ በተጨማሪም በሌላ የግዳጅ ቀጠና ደቡብ ወሎ መካነ-ሰላም መቅደላ ላይ የአገዛዙ የዕዝ ም/አዛዥ ለኦፕሬሽን በሆነው በጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ ቀጥተኛ መሪነት የተመራው የዘረ-ፈጁን 11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 87ኛ ክ/ጦር 1ኛ እና 2ኛ ሻለቆችን በመደምሰስ ከ130 በላይ ተማርከዋል። በ6 ቀናት ውስጥ 1 ዲሽቃ፣ 1 ሞርተር፣ 5 ብሬን፣ 4 ስና
ይፐር፣ 2 አርፒጂ፣ ከ230 በላይ ክላሾች ተማርከዋል፤ በዚሁ ግንባር ቀደም ሲልም መስከረም 24/2019 ዓ.ም የ87ኛ ክ/ጦር 4ኛ ሬጅመንት መደምሰሱ ይታወሳል።
• ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም፦ በሰከላ ወረዳ ሰከላ ከተማ፣ ቲሊሊ ወረዳ አሽፋ፣ ባንጃ ወረዳ ጉባላ እና ፋግታ ለኮማ ወረዳ ዋዝ ላይ የጠላትን የ44ኛ ክፍለ ጦር ከበባና ጥቃት በመልሶ ማጥቃት ማክሸፍ ተችሏል።
◦ በዋዝ ከተማ የቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 44ኛ እና 55ኛ ከፍለ ጦር እንዲሁም የዕዙ ኮማንዶ ዩኒት ጥምረት 2 ብሬን፣ 26 ክላሽ፣ 5,200 የክላሽ እና 4,700 የብሬን ጥይቶች እና 5 ወታደሮች ተማርረዋል።
• ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም፦ መነሻውን ጃዊ ፈንድቃ ያደረገ እና በጄኔራል መድፍ፣ ታንክ፣ ዙ-23 እና ሞርተር የታጀበ የጠላት ሃይል ጃይማላ ከተማን ለመውረር ሲንቀሳቀስ በይላላ እና ኩብሊ የሁለት ቀን እልህ አስጨራሽ ውጊያ ተደርጎበት ወደ መጣበት ጃዊ ፈንድቃ ተመልሶ እንዲፈረጥጥ ተደርጓል።
• ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም፦ ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ ጃዊ ከተማ ሞሰቢት/አውስኮድ በተባለ ቦታ የተጠራቀመውን የአገዛዙን ካምፕ ጥዋት 11:30 ሰዓት ላይ ዘልቆ በመግባት መብረቃዊ ጥቃት ፈጽሟል፤ ሰራዊቱ ከፍተኛ ሰብአዊ ኪሳራ አድርሶበታል።
፬. ምዕራብ ግንባር፦ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ከጥቅምት 1 - 9/2019 ዓ.ም የተሰሩ ስራዎች፦
• ጥቅምት 1/2019 ዓ.ም ወጅ አምባ:- ከወረታ ዓለም በር ሲንቀሳቀስ የነበረው የአገዛዝ ኃይል በሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ነበልባሉ 23ኛ ክፍለ ጦር ቃኝ እና መሃንዲስ አባላት ከጠዋቱ 12:00 እስከ 3:00 ሰዓት በዘለቀ የተቀናጀ የደፈጣ ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዷል።
• ጥቅምት 03/2019 ዓ.ም በ4 ዋና ዋና ንዑስ ግንባሮች:-
1ኛ, ደልጊ ከተማ: የ202ኛ ኮር አሀዶች ከሰዓት በዘለቀ ውጊያ 45 የጠላት ኃይል ደምስሰዋል፤ ከ50 በላይ ቀላልና ከባድ ቁስለኞች አድርሰዋል፤ 1 ብሬን፣ 1 ስናይፐር እና 15 ክላሾች ማረከዋል።
2ኛ, ወረታ-ጉማራ መስመር: በሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር (23ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት) አማካገኝነት በነጭ አፈር፣ ታንኳ ገብርኤል እና ጉማራ በጠላት ሀይል ላይ ጥቃት ተፈፅሟል።
3ኛ, ንፋስ መውጫ፦ በ206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ገብርዬ ክፍለ ጦር እና አንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር በቅንጅት በሰሩት ስራ የቀድሞው የንፋስ መውጫ ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አንዳርጋቸው አድማስን ጨምሮ በርካታ ኃይል ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
4ኛ, ሀገረ ገነት - ዛጎች መስመር፦ በ206ኛ ኮር፣ አንበሳው ጋይንት እና ተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦሮች በተደረገ ጥቃት በታጥሮ በር እና ደንኮርኮ ከፍተኛ ምት ማሳረፍ ተችሏል።
• ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም ማሰሮ ደንብ ከተማ:- በማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ በ305ኛ ጎቤ መልኬ ኮር በተደረገ ውጊያ የጠላት ዋና መቀመጫ የነበረችው ማሰሮ ደንብ ከተማ እና የኮንክሪት ምሽጓ ተሰብሯል።
◦ በዚህም 48 የጠላት ሀይል ተደምስሰዋል፤ 41 ቁስለኛ፣ 15 ክላሽንኮቭ፣ 1 ቦቲ መኪና እና 1 ፓትሮል ተማርከዋል። ኩርቢ ላይም ተጨማሪ ኃይል በደፈጣ ተመቷል።
◦ በተመሳሳይ: በደራ እና አንዳቤት ወረዳዎች በጉና ክ/ጦር፣ ጣና ገላውዴዎስ ክፍለ ጦር እና ቃኝና መሀንዲስ ከቀኑ 12:30 እስከ ማታ 10:00 ሰዓት ድረስ በተደረገ መደበኛ አውደ ውጊያ ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል።
• ጥቅምት 07/2019 ዓ.ም፦ ከንፋስ መውጫ ተነስቶ ወደ ታች ጋይንት የተንቀሳቀሰውን ጥምር ኃይል በ206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ገብርዬ ክፍለ ጦር በሦስት ግንባሮች (በመጋ፣ አጋጥ፣ በረንታ፣ አርብ ገበያ ከተማ ዶ/ር አምባቸው ሆስፒታል አካባቢ) እስከ ማታ 1፡00 ሰዓት በተደረገ ውጊያ የሻለቃ አመራሩን ጨምሮ በርካታ ሰራዊት ተደምስሷል።
ማጠቃለያ፦
በአፋብን በየግንባሩ የተመዘገቡት እነዚህ ድሎች ተራ የአካባቢ ቁጥጥር ሳይሆኑ የአገዛዙን የውጊያና የፖለቲካ መዋቅር በማፍረስ፣ ወደ ፌደራል ማዕከል (አዲስ አበባ) ለሚደረገው ወሳኝ የነፃነት ጉዞ መንገድ ጠራጊዎች መሆናቸውን ያረጋግጣሉ።
በመጨረሻም
መሬት ላይ ብልጫ የተወሰደበት እና አቅሙን ያጣው ዘረ-ፈጁ የአብይ አህመድ ሥርአት ከምንግዜውም በላይ ሰፊ የሆነ የድሮን እና የጀት ስምሪት በመስጠት ተደጋጋሚ ጥቃት በንፁሀን ህዝባችን እና ተቋማት ላይ እየፈፀመ ይገኛል።
ለአብነት ያክል በትላንትናው ዕለት ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም በቴዎድሮስ 2ኛ እዝ ቀጠና በጎጃም አዊ ዞን ፋግታ ለኮማ በሲቪሊያን መኖሪያ መንደር ላይ በተፈፀመ የአየር ኃይል የጄት ድብደባ በቤት እንስሳትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሷል።
አገዛዙ ይህን የሽብር ጥቃት እየፈፀመ ሲሆን፣ የሰው ሕይወት መጥፋቱ በውል ባይታወቅም የቤት እንስሳት መገደላቸውና ንብረት መውደሙ ተረጋግጧል።
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መረሀቤቴ እና መንዝ አውራጃም ተመሳሳይ የአየር ላይ ጥቃት ተፈፅሞ ሲቪሊያንና ንብረት ላይ ከፍተገኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በምኒልክ 1ኛ ዕዝ ቀጠና በደቡብ ወሎ መሀል ሳይንት ዴንሳ ወርዳ ለይ በተደረገ የድሮ ጥቃት የአቢሲኒያ ባንክ እና የአማራ ባንክ ጥበቃዎችን ጨምሮ ከአስር በላይ ሲቪሊያኖች የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡ በርካታ ከፍተገኛ ቁስለገኛ ስላለ የሟቾች ቁትር ከዚህም በላይ ሊጨምረ እንደሚችል ይገመታል፡፡ በዚህም በሲቪሊያን እና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።
በተጨማሪም ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ቀጠና ላይ ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም የዘረ-ፈጁ ብልጽግና አገዛዝ በደቡባዊ ጎንደር ደራ ወረዳ ሳና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ባደረሰው የድሮን ጥቃት ተማሪዎችን በትምህርት ገበታቸው ላይ ሳሉ የጨፈጨፈ ሲሆን፣ በርካቶችንም ከከባድ እስከ ቀላል አካላዊ ጉዳት አድርሶባቸዋል። በተጨማሪም በዕለቱ ከቀኑ 5:40 ሰዓት ላይ በአንዳቤት ወረዳ ወለሽ ከተማ የሚገኘውን የከተማ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት አውድሟል።
በመሆኑም የንፁሐኖች ደም ይገደኛል የሚል የትኛውም አካል ድርጊቱን በይፋ እንዲያወግዝ እና እንዲቃወም መልዕክታችንን እናስተላለፋለን።
ለመላው የአማራ ሕዝብ
የብልፅግናው አገዛዝ የአማራ ህዝብ ጠላትነት ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው እውነት ነው። ለዚህም ነው ላለፉት ጥቂት ዓመታት ዱር ቤቴ ብለን ይህንን ዘረ-ፈጅ ስርዓት እየታገልን እና እያንኮታኮትን የምንገኘው። ጀግናው ህዝባችንም ከጎናችን ተሰልፎ እየታገለ ያለው። ይሄን ስርዓት እስከመጨረሻው አስካልቀበርነው ድረስ ሠላም የሚባል ነገር ለአማራ ህዝብ ስለማይታሰብ መላው ህዝባችን ይሔን ስርዓት ለመገርሰስ እያደረገ ያለውን ተጋድሎ ከምንግዜውም በላይ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እናስተላልፋለን።
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የወታደራዊ
የግንባር አውደ ውሎና የድል መግለጫ ከመስከረም 26 - ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ህዝባዊ ሀይል ትብብር ለህልውና (ትብብር ለህልውና) አካል የሆነው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በየግንባሩ በየዕዞቹ ባለፉት ሳምንታት ባደረጋቸው አውደ ውጊያዎች የአገዛዙን የውጊያና የፖለቲካ መዋቅር በመበጣጠስ ታሪካዊ እና ተዓምራዊ ድሎችን አስመዝግቧል። አገዛዙ ቀጠናዎችን ተቆጣጥሬያለሁ በማለት የሚነዛው የሐሰት የፖለቲካ ድራማ በመሬት ላይ በተመዘገቡ ተጨባጭ ድሎች ሙሉ በሙሉ ከንቱ የተደረገ ሲሆን፤ የዘረ-ፈጁ ሰራዊት ፍርሰትና የፋኖ እጅግ የላቀ ወታደራዊ አቅም በሚከተለው መልኩ በየዕዞች ተደራጅቶ ቀርቧል፦
፩. በደቡብ ግንባር፦ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ከመስከረም 27 - ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም ድረስ ያደረጋቸው ተጋድሎዎች፤
በደቡብ ግንባር የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ያስመዘገባቸው ድሎች የአገዛዙን የሠራዊት እንቅስቃሴና የአየር ሃይል ሙከራዎች ማክሸፍ ችሏል። በዚህ ግንባር የጠላትን ወታደራዊ አቅም እና የስነ-ልቦና ልዕልና ከመሰረቱ በመናድ የዕዙን የተከላካይነት እና የማጥቃት አቅም ያረጋገጠ ነው። የአገዛዙ ሠራዊት በቁጥርም ሆነ በቁሳቁስ የነበረውን ብልጫ በመስክ ላይ በሚገኘው የሰራዊታችን ጀግንነት፣ ቆራጥነት እና የውጊያ ስልት ተሽሯል።
• መስከረም 27 - 29/2019 ዓ.ም፦
በመንዝ አውራጃ አናዝ ቀበሌ 19 በፋኖ የማጥቃት እርምጃ የተደናገጠው የአገዛዙ ድሮን የውር ድንብሩን እየዞረ ባለበት ቅፅበት ተከስክሷል። በመሀል ሜዳ እና ዘመሮ አቅጣጫ የተሰነዘረው የአየር ድብደባ ሙከራ ሙሉ በሙሉ ከሽፏል።
◦ በሁሉም ግንባሮች በተደረገ ተጋድሎ 593 የብልፅግና ሠራዊት ተማርከዋል።
◦ 3 ድሽቃ፣ 20 ብሬን፣ 17 ስናይፐር፣ ከ1,600 በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች እና በርካታ ተተኳሾች ተማርከዋል።
◦ ቀጠናውን ያረጋጋሉ ተብለው ወደ መሀል ሜዳ የገቡት የአገዛዙ 6ኛ ዕዝ 2 ሻለቆች፣ የ52ኛ ክፍለ ጦር 28ኛ ሻለቃ እና 5ኛ ሻለቃ ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል።
◦ በአንድ ጊዜ ብቻ የ6ኛ ዕዝ 15 የመከላከያ ሠራዊት አባላት የፋኖን ድል በመመልከት ከእነ ትጥቃቸው ዕዛችንን ተቀላቅለዋል።
• መስከረም 26 - 27 (ለሁለት ቀናት):- በከሰም ቀጣና ምንታምር ከተማ በተደረገ ተጋድሎ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ሰራዊት ተደምስሷል። ጠላት በውጊያው 2 ጊዜ ድሮን የተጠቀመ ቢሆንም ምንም ለውጥ ሊያመጣለት ባለመቻሉ፣ በውጊያው የተመቱ አመራሮችን አስከሬን ለማውጣት የተላኩ ሄሊኮፍተሮች 6 ጊዜ ተመላልሰው በጀግናው ሰራዊታችን መሬት ላይ ማረፍ እንዳይችሉ ተደርገዋል።
◦ መሀል ሜዳ መውጫ ላይ የሚገኘው ከፍተኛ ወታደራዊ ቁሳቁስ የተከማቸበት የአገዛዙ ምሽግ ተሰብሮ ሠራዊቱ ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ውሏል።
◦ የመንዝ 4ቱ ከተሞች እና ታላላቅ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ከአገዛዙ ነፃ ወጥተዋል፤ መንዝ ቀያ ዘመሮ ከተማ፣ መንዝ ጌራ ምድር መሀል ሜዳ ከተማ፣ ወገሬ ከተማ፣ መራኛ ከተማ፣ ሬማ ከተማ፣ ጅሁር ከተማ፣ አንጨቆረር እና መርሐቤቴ ገዢ ቦታ የሆኑት፦ ጀማ እና ኮላሽን ጨምሮ ሌሎች መለስተኛ ከተሞች ተይዘው ህዝባዊ ውይይቶችና የአደረጃጀት ስራዎች እየተሰሩ ናቸው።
• መስከረም 30 /2019 ዓ.ም፦ በመዘዞ ከተማ እና ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም በመርሀቤቴ ዙሪያ በዞማ ተራራማ ስፍራዎች በተደረጉ አውደ ውጊያዎች የጠላት ቅስም ተሰብሯል።
• ጥቅምት 7/2019 ዓ.ም፦ የመሀል ሜዳ ከንቲባ እና የሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ኃላፊ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
• ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም፦ በአለም ከተማ በተደረገ የከተማ ውስጥ ሰርጅካል ኦፕሬሽን 2 ሚሊሻ ሲገደል 5 ቆስለዋል፤ ፋኖ ከተማ መሀል በተጠና መንገድ እርምጃ መውሰዱ የአገዛዙ ካድሬዎችን ጭንቀት ጨምሮታል።
• ጥቅምት 9 /2019 ዓ.ም ከደብረብርሃን ከተማ ወደ አንኮበር ከተማ ሁለት ዙ-23፣ አንድ ቢኤም እና አንድ መድፍ ከ40 መኪና በላይ እግረኛ ጦር ይዞ የዘለቀው የአገዛዙ መካናይዝድ ጦር በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ አማካኝነት ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ በተደረገ ከባድ የደፈጣ ውጊያ ክፉኛ ተመቷል።
◦ በዚህም ሽንፈትን የተከናነበው የአገዛዙ ጦር ተስፋ በመቁረጡ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት አካባቢ ከአንኮበር ቤተ መንግሥት እና መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን ታሪካዊ ቅርሶችን እንዲሁም የባንክ ገንዘቦችን ሙሉ በሙሉ ጠራርጎ ከቁስለኞቹ ጋር በ40 መኪና ጭኖ ወደ ደብረብርሃን ተመልሷል።
፪. ምስራቅ ግንባር፦ ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ከመስከረም 30 - ጥቅምት 8 /2019 ዓ.ም የተሰሩ ስራዎች፦
• መስከረም 30/2019 ዓ.ም (አንደኛ ዙር):- ምኒልክ 1ኛ ዕዝ 13ኛ ኮር 137ኛ (ውባንተ አባተ) ክፍለ ጦር እና 138ኛ (ራስ አንችም) ክፍለ ጦር በጋራ በመሆን ከ60 በላይ የጠላት ኃይል ደምስሰዋል፤ 30 ምርኮኞችን መማረክ ተችሏል።
◦ የተማረከ፦ 1 ብሬን፣ 2 ስናይፐር፣ 1 አራባ ጎራሽ ክላሽ፣ 52 AK-47 ክላሽንኮቭ፣ 46 የወገብ ትጥቅ፣ 27 የእጅ ቦንብ፣ 640 የብሬን እና 1,780 የክላሽ ተተኳሾች።
• መስከረም 30/2019 ዓ.ም (ሁለተኛ ዙር):-15ኛ ኮር 152ኛ እና 155ኛ ክፍለ ጦር ከለገሂዳ ወረዳ እስከ ጃማ ደጎሎ ድረስ ባደረጉት ተጋድሎ ከ50 በላይ ሰራዊት ሲደመሰስ ከ30 በላይ ቁስለኞች አድርሰዋል፤ የጃማ ወረዳ ሚኒሻ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆነውን ኮሎኔል ሃብታሙን መደምሰስ ተችሏል።
• ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም፦101ኛ ኮር ከተንታ ወደ ተሬና ጉና ተንቀሳቅሶ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ ስቦ የመምታት ስልት በመጠቀም የጠላትን 2 ሬጅመንት የ11ኛ ዕዝ 204ኛ ኮር 35ኛ ክ/ጦር 2ኛ እና 3ኛ ሬጅመንቶች ሙሉ በሙሉ መደምሰስ ተችሏል።
◦ በዚህም ከ35 በላይ ወታደሮች ሲማረኩ 3 አሥር አለቆች እና 1 ሃምሳ አለቃን ጨምሮ፤ 2 ብሬን፣ 1 ስናይፐር፣ 65 ክላሽ፣ 6,570 የክላሽ እና 5,065 የብሬን ተተኳሾች፣ 20 የእጅ ቦንቦች ተማርከዋል።
• ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም፦102ኛ ኮር እና 16ኛ ኮር በወገል ጤና ከተማ 4 ቀን ባደረጉት ከባድ ውጊያ ደላንታ ላይ ተቆርጣ የነበረችውን የጠላት 16ኛ ክፍለ ጦር አብዛኛውን አሃድ በመደምሰስ 1 ዙ-23 ጨምሮ ሜካናይዝድ መሳሪያዎችን ማውደም ተችሏል።
• ጥቅምት 08/2019 ዓ.ም፦15ኛ ኮር አጅባር ወረዳ ላይ ሬሽን ጭኖ ሲንቀሳቀስ በነበረ የጠላት ሰራዊት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በርካታ ኃይልን በመደምሰስ 3 ካሶኒ መኪናዎችን መማረክ ችሏል።
፫. ምዕራብ ግንባር፦ ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ መስከረም 30 - ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም የተሰሩ፦
• መስከረም 30/2019 ዓ.ም፦ አዲስ ቅዳም ከተማ ላይ ለአጭር ሰዓታት ከተማውን በመቆጣጠር የአድማ ብተና እና ፖሊስ አንድ ሻለቃ ሙሉ በሙሉ ደምስሷል። 113 ሙት፣ 25 ምርኮኛ፣ 26 ቁስለኛ ሲመዘገብ፤ 133 ክላሽ፣ 5 ብሬን፣ 28 የቃታ መሳሪያዎች፣ 2 መገናኛ ሬዲዮዎች እና በርካታ ተተኳሾች ተማርከዋል።
