ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

الذهاب إلى القناة على Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

إظهار المزيد
4 382
المشتركون
-924 ساعات
+2477 أيام
+1 42930 أيام
أرشيف المشاركات
ለአገዛዙ ብልፅግና ተለላኪ የነበሩ 18 ሚሊሻ፣ ፖሊስና አድማ ብተና አባላት አይበገሬው 64ኛ ክ/ጦር ተቀላቀሉ። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች የህልውና አዳጋ ውስጥ የገቡ ህዝቦችን ነፃ ለማውጣት የሚንቀሳቀሱ ሐይሎች ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑን የተረዱ፣ የአማራ ህዝብ ህልውና አዳጋን ለመቋጨት የአማራ ፋኖ እያደርገ ያለውን ተጋሃድሎ የተርዱ እና የብልፅግና አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን የድሮን ጥቃት፣ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በመቃወም ከእነማይ ወረዳ፣ ሸበል በረንታ እንዲሁም በእናርጅ እናውጋ ወረዳ አገዛዙን መሽጎ ከነበረባቸው ቦታዎች አገዛዙን በመክዳት 18 ሚሊሻ፣ ፖሊስ እና አድማ ብተና አባላት አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ተቀላቀሉ። 1ኛ. አትመን ዕውነቱ ሚሊሻ 2ኛ. ናደው አባቡ ሚሊሻ 3ኛ. እንደሻው አባይነህ ሚሊሻ 4ኛ. ባንተነው አግደው ሚሊሻ 5ኛ. ደረጀ አሸነፍ ሚሊሻ 6ኛ. አለኸኝ አያል ሚሊሻ 7ኛ. የሽዋስ በላይነህ ሚሊሻ 8ኛ. አስከጃይ ባሴ ሚሊሻ 9ኛ. አምደወርቅ አስረስ ሚሊሻ 10ኛ. የውልሰው ታመነ ሚሊሻ ‎11ኛ. ናቄ ደስ ያለው ሚኒሻ 12ኛ. አበበ ግርማ ፓራ ኮማንዶ 13ኛ. አይዋ ደመቀ ፓራ ኮማንዶ 14ኛ. እርመድ በላይነህ ፓራ ኮማንዶ 15ኛ. ዋ/ሳጅን ምህረት ፖሊስ 16ኛ. ኮንስታብል አማኑኤል ፖሊስ 17ኛ. ኮንታብል ኤርሚያስ ስታየሁ ፖሊስ 18ኛ.መልካሙ አትስሜ ሚሊሻ ሲሆኑ ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ተቀላቅለዋል። የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋሃድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል❗️ ድል ለአማራ ህዝብ‼️ ድል ለኢትዮጰያ ህዝብ‼️ ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን‼️ ‎ አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!! ጥቅምት13/2019 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት

የብልጽግና አገዛዝ በንፁሃን አማራዎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የተሰጠ መግለጫ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም በአማራ ህዝብ ላይ ሁለንተናዊ ጦርነት የከፈተው የብልፅግና አገዛዝ ሲቪሊያንን ዒላማ ያደረገ ጥቃቱን እንደቀጠለበት ይገኛል። በዚህ ያልተቋረጠ የዘረ ፈጅ ጥቃት ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ በወለጋ፣ በሸዋ፣ በጎንደር እና በጎጃም ጠቅላይ ግዛቶች በንፁሃን አማራዎች ላይ ያነጣጠረ አሰቃቂ፣ በጅምላ የሚፈጸም የድሮን እና የከባድ መሳሪያ ጥቃት ፈፅሟል። 1ኛ) በምስራቅ ወለጋ ዞን:- ከሰሞኑ ተጠናክሮ በቀጠለው ጭፍጨፋ በጊዳ አያና ወረዳ:- ፈንደቃ ፣ አንዶዴ፣ መንደር 3፣ መንደር 22፣ በጭበጭ ጊዮርጊስ እና መለከታ የተባሉ አነስተኛ ከተሞች ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል። ከጥቃቱ የተረፈ ከ65ሺ በላይ  ንፁሃን አማራወች በጫካ እየተሰቃዩ ይገኛለሉ። በቀጠለው የብልፅግና ፀረ አማራ ጥቃት ጊዳ አያና ወረዳ - አሊ ከተማ በከባድ መሳሪያ ሰፈርን በመደብደብ፣ ከቤት መውጣት ያልቻሉ አረጋውያንን እና ታማሚዎችን ጨምሮ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ አቃጥሏል። ኪረሙ ወረዳ - ወደሳ ዲማ ቀበሌ የ76 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ ንጹሃን አማራን ኢላማ ያደረገ ግድያ ዘረፋ እና ማፈናቀል ተፈፅሟል፤ በዚህ ጥቃት ምክንያት የቀበሌው ህዝብ ወደ ጫካ ተበትኗል። 2ኛ) ደቡብ ጎንደር ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ላይ  ደራ ወረዳ - ሳና ከተማ - ሳና 1ኛ ደ/ት/ቤት ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በመማር ላይ የነበሩ ከ15 በላይ ታዳጊ  ተማሪዎች ተጨፍጭፈዋል። የ60 ዓመት አዛውንት የሆኑት የት/ቤቱ ጥበቃ አቶ እሸቴ ከበደ በከባድ ሁኔታ ቆስለዋል። በተመሳሳይ በቀን ከረፋዱ 5:40 ላይ አንዳ ቤት ወረዳ - ወለሽ ከተማ በከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የነዋሪዎች ሱቆች ወድመዋል - ወጣት አበረ ክንዴ እና ወ/ሮ አህቴናት ደርብ ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል። 3) ምስራቅ ጎጃም ዞን ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም ባሶ ሊበን ወረዳ - ሻይ ቤት በሻይ ቤት ቁጭ ባሉ ንፁሃን ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት አጉማስ ስማቸው፣ አብኔ፣ ይድነቅ መንግስቴ፣ ቁሜ አመራ፣ ከባድ መንበሩ የተባሉ ሲቪሊያን ተገድለዋል፤ አወቀ ጌታቸው እና ደርብ ላቀ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። 4ኛ) ደቡብ ወሎ ዞን:- ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በሳይንት ደንሳ ወረዳ ባልታጠቁ ዜጎች  አሰቃቂ የድሮን ጥቃት ተፈፅሞ አንዷለም ጌታቸው  የተባለ የአማራ ባንክ ጥበቃ፣ ደረሰ መንግስቴ የተባለ የአቢሲኒያ ባንክ ጥበቃ፣ ቃልኪዳን ፍሰሃ የተባለች በዚህ ዓመት 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀች ተማሪ፣ ወይንሸት ላንተነው የተባለች የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ከተገደሉት መካከል ይገኙበታል። እንዲሁም  ደምሰው ንጉሴ እና ዘለቀ ኃይሌ የተባሉ የአማራ ባንክ ጥበቃወች፣ እያሱ አለሙ የተባለ የመኪና ረዳት፣ ሳባ አንባቸው የተባለች ሰላማዊ ነዋሪ፣ እሱባለው ንጉስ የተባለ የ8 ዓመት ህፃን፣ ሀና በቀለ የተባለች የአቢሲኒያ ባንክ ጥበቃ  እና ስንታየሁ የተባለች በግል ስራ የምትተዳደር  እናት ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ስማቸው እስካሁን ያልታወቀ ከ10 በላይ ንፁሃን የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል። 5ኛ) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ቡልጋ አውራጃ ፉራ እና ሲቻት ቀበሌዎች በድሮን፣ ሮኬት፣ BM፣ ሞርተር እና ዙ-23 በተፈጸመ ጥቃት  ሚጣ እንዳለ የተባለች የ3 ዓመት ህፃን ጨምሮ 4 ሰዎች ተገድለዋል፣ 5 ከባድ ቁስለኛ ሲሆኑ እና ከ10 በላይ ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል። እንዲሁም  ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በአዊ ዞን ፋግታ ድማማ በተባለ ቦታ በሲቭሊያን መኖሪያ አካባቢ በተፈፀመ የጀት ድብደ በርካታ መንደሮችን ሲያወድም 10 የአርሶ አደር ከብቶችንም ገድሏል ። የአፋብን መልዕክት ይህ ከትምህርት ቤት እስከ ባንክ፣ ከሻይ ቤት እስከ መኖሪያ ቤት ድረስ የሚፈጸመው ጥቃት የአማራን ህዝብ ዘር ለማጥፋት የታቀደ የመጨረሻው የፋሽስታዊ የጥፋት ዘመቻ ነው። አገዛዙ ንፁሃንን በምድር በታንክና መድፍ፣ በሰማይ ደግሞ በድሮን እየጨፈጨፈ ይገኛል። በመሆኑም:- 1ኛ) ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ፣ ለEU፣ ለUN እና ለሰብአዊ መብት ተቋማት ጥሪያችን በሲቪል ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የድሮን ጦርነት በገለልተኛ አካል እንዲያጣራ እንጠይቃለን፣ 2ኛ) የሰብአዊ መብት ተቋማት እና የረድኤት ድርጅቶች በአገዛዙ ጥቃት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ሲቪሊያን አስፈላጊውን የሰብአዊ እርዳታ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፤ 3ኛ) ለመላው ኢትዮጵያዊያን እና የአማራ ህዝብ አገዛዙ ሀገራችንን በጦርነት ቀውስ ውስጥ በማስገባት የሲኦል ምድር ከማድረግ ወደ ኋላ የማይል የሽብር መንግስት በመሆኑ ሁለንተናዊ ትግል በማድረግ ብልፅግና አገዛዝን በማስወገድ የሰላም አየር እንድንተነፍስ እና ሀገራችንን ከፈፅሞ መጥፋት እንድንታደግ ጥሪ እናቀርባለን። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም

የቴወድሮስ 2ኛ እዝ ስልጠና መምርያ ያወጣው የስልጠና ጥሪ ማስታወቂያ
የቴወድሮስ 2ኛ እዝ ስልጠና መምርያ ያወጣው የስልጠና ጥሪ ማስታወቂያ

አስቸኳይ የጥንቃቄ መረጃ ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ወሎ ፋኖዎች በሙሉ‼️ በአሁን ሰዓት ማለትም ከምሽቱ 01:27 ጀምሮ የድሮን ቅኝት እየተደረገ ነው ለምሳሌ በመርሳ፣ በውርጌሳ ፣ በጊራና በአምባሰል እንዲሁም በሲሪንቃ በወልድያ አካባቢ ያላችሁ ፋኖዎች ጥንቃቄ አድርጉ። ቀን 12/ 2 /2019 ዓ.ም

የብልጽግና አገዛዝ በንፁሃን አማራዎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የተሰጠ መግለጫ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም በአማራ ህዝብ ላይ ሁለንተናዊ ጦርነት የከፈተው የብልፅግና አገዛዝ ሲቪሊያንን ዒላማ ያደረገ ጥቃቱን እንደቀጠለበት ይገኛል። በዚህ ያልተቋረጠ የዘረ ፈጅ ጥቃት ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ በወለጋ፣ በሸዋ፣ በጎንደር እና በጎጃም ጠቅላይ ግዛቶች በንፁሃን አማራዎች ላይ ያነጣጠረ አሰቃቂ፣ በጅምላ የሚፈጸም የድሮን እና የከባድ መሳሪያ ጥቃት ፈፅሟል። 1ኛ) በምስራቅ ወለጋ ዞን:- ከሰሞኑ ተጠናክሮ በቀጠለው ጭፍጨፋ በጊዳ አያና ወረዳ:- ፈንደቃ ፣ አንዶዴ፣ መንደር 3፣ መንደር 22፣ በጭበጭ ጊዮርጊስ እና መለከታ የተባሉ አነስተኛ ከተሞች ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል። ከጥቃቱ የተረፈ ከ65ሺ በላይ  ንፁሃን አማራወች በጫካ እየተሰቃዩ ይገኛለሉ። በቀጠለው የብልፅግና ፀረ አማራ ጥቃት ጊዳ አያና ወረዳ - አሊ ከተማ በከባድ መሳሪያ ሰፈርን በመደብደብ፣ ከቤት መውጣት ያልቻሉ አረጋውያንን እና ታማሚዎችን ጨምሮ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ አቃጥሏል። ኪረሙ ወረዳ - ወደሳ ዲማ ቀበሌ የ76 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ ንጹሃን አማራን ኢላማ ያደረገ ግድያ ዘረፋ እና ማፈናቀል ተፈፅሟል፤ በዚህ ጥቃት ምክንያት የቀበሌው ህዝብ ወደ ጫካ ተበትኗል። 2ኛ) ደቡብ ጎንደር ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ላይ  ደራ ወረዳ - ሳና ከተማ - ሳና 1ኛ ደ/ት/ቤት ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በመማር ላይ የነበሩ ከ15 በላይ ታዳጊ  ተማሪዎች ተጨፍጭፈዋል። የ60 ዓመት አዛውንት የሆኑት የት/ቤቱ ጥበቃ አቶ እሸቴ ከበደ በከባድ ሁኔታ ቆስለዋል። በተመሳሳይ በቀን ከረፋዱ 5:40 ላይ አንዳ ቤት ወረዳ - ወለሽ ከተማ በከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የነዋሪዎች ሱቆች ወድመዋል - ወጣት አበረ ክንዴ እና ወ/ሮ አህቴናት ደርብ ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል። 3) ምስራቅ ጎጃም ዞን ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም ባሶ ሊበን ወረዳ - ሻይ ቤት በሻይ ቤት ቁጭ ባሉ ንፁሃን ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት አጉማስ ስማቸው፣ አብኔ፣ ይድነቅ መንግስቴ፣ ቁሜ አመራ፣ ከባድ መንበሩ የተባሉ ሲቪሊያን ተገድለዋል፤ አወቀ ጌታቸው እና ደርብ ላቀ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። 4ኛ) ደቡብ ወሎ ዞን:- ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በሳይንት ደንሳ ወረዳ ባልታጠቁ ዜጎች  አሰቃቂ የድሮን ጥቃት ተፈፅሞ አንዷለም ጌታቸው  የተባለ የአማራ ባንክ ጥበቃ፣ ደረሰ መንግስቴ የተባለ የአቢሲኒያ ባንክ ጥበቃ፣ ቃልኪዳን ፍሰሃ የተባለች በዚህ ዓመት 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀች ተማሪ፣ ወይንሸት ላንተነው የተባለች የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ከተገደሉት መካከል ይገኙበታል። እንዲሁም  ደምሰው ንጉሴ እና ዘለቀ ኃይሌ የተባሉ የአማራ ባንክ ጥበቃወች፣ እያሱ አለሙ የተባለ የመኪና ረዳት፣ ሳባ አንባቸው የተባለች ሰላማዊ ነዋሪ፣ እሱባለው ንጉስ የተባለ የ8 ዓመት ህፃን፣ ሀና በቀለ የተባለች የአቢሲኒያ ባንክ ጥበቃ  እና ስንታየሁ የተባለች በግል ስራ የምትተዳደር  እናት ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ስማቸው እስካሁን ያልታወቀ ከ10 በላይ ንፁሃን የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል። 5ኛ) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ቡልጋ አውራጃ ፉራ እና ሲቻት ቀበሌዎች በድሮን፣ ሮኬት፣ BM፣ ሞርተር እና ዙ-23 በተፈጸመ ጥቃት  ሚጣ እንዳለ የተባለች የ3 ዓመት ህፃን ጨምሮ 4 ሰዎች ተገድለዋል፣ 5 ከባድ ቁስለኛ ሲሆኑ እና ከ10 በላይ ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል። እንዲሁም  ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም በአዊ ዞን ፋግታ ድማማ በተባለ ቦታ በሲቭሊያን መኖሪያ አካባቢ በተፈፀመ የጀት ድብደ በርካታ መንደሮችን ሲያወድም 10 የአርሶ አደር ከብቶችንም ገድሏል ። የአፋብን መልዕክት ይህ ከትምህርት ቤት እስከ ባንክ፣ ከሻይ ቤት እስከ መኖሪያ ቤት ድረስ የሚፈጸመው ጥቃት የአማራን ህዝብ ዘር ለማጥፋት የታቀደ የመጨረሻው የፋሽስታዊ የጥፋት ዘመቻ ነው። አገዛዙ ንፁሃንን በምድር በታንክና መድፍ፣ በሰማይ ደግሞ በድሮን እየጨፈጨፈ ይገኛል። በመሆኑም:- 1ኛ) ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ፣ ለEU፣ ለUN እና ለሰብአዊ መብት ተቋማት ጥሪያችን በሲቪል ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን የድሮን ጦርነት በገለልተኛ አካል እንዲያጣራ እንጠይቃለን፣ 2ኛ) የሰብአዊ መብት ተቋማት እና የረድኤት ድርጅቶች በአገዛዙ ጥቃት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ሲቪሊያን አስፈላጊውን የሰብአዊ እርዳታ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፤ 3ኛ) ለመላው ኢትዮጵያዊያን እና የአማራ ህዝብ አገዛዙ ሀገራችንን በጦርነት ቀውስ ውስጥ በማስገባት የሲኦል ምድር ከማድረግ ወደ ኋላ የማይል የሽብር መንግስት በመሆኑ ሁለንተናዊ ትግል በማድረግ ብልፅግና አገዛዝን በማስወገድ የሰላም አየር እንድንተነፍስ እና ሀገራችንን ከፈፅሞ መጥፋት እንድንታደግ ጥሪ እናቀርባለን። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም አስቸኳይ የጥንቃቄ መረጃ ለሰሜን ወሎ ፋኖዎች በሙሉ‼️ በአሁን ሰዓት ማለትም ከምሽቱ 01:27 ጀምሮ የድሮን ቅኝት እየተደረገ ነው ለምሳሌ በመርሳ፣ በውርጌሳ ፣ በጊራና በአምባሰል እንዲሁም በሲሪንቃ በወልድያ አካባቢ ያላችሁ ፋኖዎች ጥንቃቄ አድርጉ። ቀን 12/ 2 /2019 ዓ.ም

በወለጋ የአማራ ንጹሐን ጭፍጨፋ በተባባሰበት ወቅት የአፋብን አንሻ ሰይድ 4ኛ ዕዝ ለተከታታይ አራት ወራት ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ ማስመረቁን የይበልጣል መኮነን አዲስ ዓለም ክፍለ ጦር አስታወቀ ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም በኢትዮጵያ ለዘመናት የዘለቀውን የሕዝብ አብሮነትና አገራዊ አንድነት በመሸርሸር ላይ የሚገኘውና በንጹሐን ዜጎች ደም ሥልጣኑን ለማስቀጠል የሚታገለው የብልጽግና አገዛዝ፣ በወለጋ ምድር የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን ኢላማ ያደረገ ስልታዊና መዋቅራዊ ጭፍጨፋውን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። በሁለቱ የወለጋ ዞኖች ማለትም በምስራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ የንጹሐን አማራዎች ግድያ፣ ማፈናቀል፣ የቤትና ንብረት ውድመት፣ እንዲሁም ጅምላ እስራት በፀረ-አማራውና ፀረ-ኢትዮጵያዊ በሆነው የብልጽግና ሥርዓት አሁንም አጠናክሮ መቀጠሉንና በተለይም በኪረሙ እና ጊዳ ወረዳዎች ውጥረቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የአፋብን አንሻ ሰይድ 4ኛ ዕዝ የይበልጣል መኮነን አዲስ ዓለም ክፍለ ጦር አስታውቋል። ይህ አረመኔያዊ ወረራና የሕዝብ እልቂት በስፋት በገፋበት በአሁኑ ወቅት፣ የሕዝቡን ህልውና ለመታደግና የአገዛዙን ግፍ በጽናት ለመመከት የሚደረገው ሕዝባዊ ትግል በአዲስ ወታደራዊ አቅም እየጎለበተ ይገኛል። በዚህም መሠረት የአፋብን አንሻ ሰይድ 4ኛ ዕዝ ስር የሚገኘው ለጠላት አይበገሬው የይበልጣል መኮነን አዲስ ዓለም ክፍለ ጦር ለተከታታይ አራት ወራት ያሰለጠናቸውን አዳዲስ ተዋጊ ፋኖዎች በቀን 08/02/2019 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ማስመረቁን አስታውቋል። በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የእዝ አመራሮች እንዲሁም የአንሻ ሰይድ 4ኛ ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ሻለቃ ሀብታም ጥላሁን ተገኝተው ለተመራቂዎች የትግል መመሪያና የሥራ አቅጣጫ አስተላልፈዋል። አዛዡ በመልእክታቸውም ተመራቂዎች ይህንን ዘራፊና ወራሪ ሥርዓት በልበ ሙሉነት፣ በቁርጠኝነትና በታማኝነት ታግለው የተጣለባቸውን የታሪክና የሕዝብ አደራ በአስተማማኝ ሁኔታ እንደሚወጡ ያላቸውን ሙሉ እምነት ገልጸዋል። አክለውም ይህ ነፍሰ-በላ ሥርዓት፣ የአገዛዙ ሠራዊትና የክልሉ ጥምር ኃይል የሆነው ገዳ ኮማንዶ በቅርብ ሰዓት ግብዓተ-መሬቱ እንዲፈጸምበትና የማስወገድ እርምጃው እንዲፋጠንም ጥሪ ማቅረባቸውን ክፍለ ጦሩ አብራርቷል። የፋኖን ድልና የሕዝቡን የህልውና ተጋድሎ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በተደረገው በዚህ የምረቃ መድረክ ላይ ሌሎች የክፍለ ጦሩ አመራሮችም የውጊያ ዝግጁነታቸውንና የቁርጠኝነት መልእክታቸውን ማስተላለፋቸውን ክፍለ ጦሩ አስታውቋል። ጥቅምት 12/2019 አፋብን አንሻ ሰይድ 4ኛ ዕዝ የይበልጣል መኮነን አዲስ ዓለም ክፍለ ጦር

የዘረፈጁን ብልፅግና አገዛዝ የሚያወግዝ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ በሬማ ከተማ ተካሔደ! ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም ከአገዛዙ የጭቆና ቀንበር በጀግናው ሰራዊታችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ነፃ የወጣችው በመርሀቤቴ አውራጀ የሚዳ ሬማ ወረዳ የሬማ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም የዘረፈጁን የብልፅግና አገዛዝ የሚያወግዝ ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ በማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ ማካሔዳቸውን የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ከስፍራው አስታውቋል። በሬማ ከተማ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ አገዛዙ በአንድ አንድ የወረዳና የዞን ከተሞች ህዝቡ በገዛ ፍቃዱ "የድጋፍ ሰልፍ አደረገልኝ" በሚል የተደረገውን አስገዳጅ ሰልፍ ያጋለጡ ሲሆን በሰልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮችም ተሰምተዋል። ድምፃቸው ከፍ ብለው ከተሰሙ መፈክሮች ውስጥ ዋነኛው አገዛዙ "በሴይፍ ያላሳካውን ፖለቲካ በሰልፍ አያሳካውም!" በሚል የተወገዘ ሲሆን፣ "የእኛ አጀንዳ ህልውናችን እንጅ የብልፅግና የጦርነት ማስፈፀሚያ የወደብ አጀንዳ አይደለም!" ፣ "የኛ ወደብ በህይዎት የመኖር ጥያቄ ነው!"፣ "ብልፅግና የኤምሬት የውክልና ጦርነት አስፈፃሚ! ተላላኪ! ድርጅት ነው!" ፣ "የአማራ ግድብም ወደብም በህይዎት የመኖር ዋስትናው ሲቀድም ነው!" የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል። ዘረፈጁ የብልፅግና አገዛዝ በነቂስ ለሰልፍ የወጣውን ህዝብ ለመበተን የድሮን ቅኝት ቢያደርግም አይበገሬው የሬማ ከተማ ህዝብ በንቂስ ወጥቶ ድምፁን አሰምቷል ሲል የኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል በምስል አስደግፎ መረጃውን ከስፍራው አድርሷል። " ክብር ለትግሉ ሠማዕታት! " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

+3
የዘረፈጁን ብልፅግና አገዛዝ የሚያወግዝ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ በሬማ ከተማ ተካሔደ! ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም ከአገዛዙ የጭቆና ቀንበር በጀግናው ሰራዊታችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ነፃ የወጣችው በመርሀቤቴ አውራጀ የሚዳ ሬማ ወረዳ የሬማ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም የዘረፈጁን የብልፅግና አገዛዝ የሚያወግዝ ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ በማሰማት ሰላማዊ ሰልፍ ማካሔዳቸውን የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ከስፍራው አስታውቋል። በሬማ ከተማ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ አገዛዙ በአንድ አንድ የወረዳና የዞን ከተሞች ህዝቡ በገዛ ፍቃዱ "የድጋፍ ሰልፍ አደረገልኝ" በሚል የተደረገውን አስገዳጅ ሰልፍ ያጋለጡ ሲሆን በሰልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮችም ተሰምተዋል። ድምፃቸው ከፍ ብለው ከተሰሙ መፈክሮች ውስጥ ዋነኛው አገዛዙ "በሴይፍ ያላሳካውን ፖለቲካ በሰልፍ አያሳካውም!" በሚል የተወገዘ ሲሆን፣ "የእኛ አጀንዳ ህልውናችን እንጅ የብልፅግና የጦርነት ማስፈፀሚያ የወደብ አጀንዳ አይደለም!" ፣ "የኛ ወደብ በህይዎት የመኖር ጥያቄ ነው!"፣ "ብልፅግና የኤምሬት የውክልና ጦርነት አስፈፃሚ! ተላላኪ! ድርጅት ነው!" ፣ "የአማራ ግድብም ወደብም በህይዎት የመኖር ዋስትናው ሲቀድም ነው!" የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል። ዘረፈጁ የብልፅግና አገዛዝ በነቂስ ለሰልፍ የወጣውን ህዝብ ለመበተን የድሮን ቅኝት ቢያደርግም አይበገሬው የሬማ ከተማ ህዝብ በንቂስ ወጥቶ ድምፁን አሰምቷል ሲል የኮሩ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል በምስል አስደግፎ መረጃውን ከስፍራው አድርሷል። " ክብር ለትግሉ ሠማዕታት! " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

#ጀግንነት #ወኔ #አልበገርባይነት #የነጻነትታጋይ #ቁጭት በተግባር ያያቸው ብቻ ሳይሆን ግንባራቸውን አይቶ መገመት አይከብድም #ከቤ እና #ተስፍሽ ደሞቼ ከይፋቶቹ ግድም ከዴቭ ወንድሞች
#ጀግንነት #ወኔ #አልበገርባይነት #የነጻነትታጋይ #ቁጭት በተግባር ያያቸው ብቻ ሳይሆን ግንባራቸውን አይቶ መገመት አይከብድም #ከቤ እና #ተስፍሽ ደሞቼ ከይፋቶቹ ግድም ከዴቭ ወንድሞች

በሞያሌ ዳግም አመፅ ተቀሰቀሰ❗️ ከወለጋና ከአርሲ አማራዎችን ለማፅዳት የሴራ ጥቃት የከፈተው የኦሕዴድ መራሹ የብልፅግና አገዛዝ ከሞያሌ ከተማ ሶማሌዎችን አፈናቅሎ ከተማውን ለመሰልቀጥ ጥረት ማድረጉን ተከትሎ ዳግም አመፅ መቀስቀሱ ታውቋል። በሞያሌ ከተማ እንደገና በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች ወደ ኬንያ በመሰደድ ላይ ናቸው። በኦሮሚያ እና በሱማሌ ክልሎች የድንበር አወሳሰን ምክንያት በሞያሌ ከተማ ትላንት ረጋ ብሎ የነበረው ግጭት ዛሬ ማለዳ እንደገና መቀስቀሱ ተገለጸ። ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በከተማዋ ውስጥ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ የሚሰማ ሲሆን፣ የከተማዋ መደበኛ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ቆሟል። በከተማዋ ባለው የአስፓልት መንገድ ግራና ቀኝ በሱማሌ እና በኦሮሞ ተከፍሎ በሚገኘው የሞያሌ ከተማ፣ የይገባኛልና የባለቤትነት ጥያቄን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ይህ ግጭት ከቀበሌ ሁለት ተነስቶ አሁን ላይ በሙሉ ከተማዋ ውስጥ ተስፋፍቶ ይገኛል። የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ከተማዋ የገቡ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ተኩሱን ማስቆም እንዳልተቻለ ታውቋል። ከዚሁ አመፅ ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ እንዲሁም ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡት ዋና ዋና መንገዶች ሙሉ በሙሉ ዝግ ሆነዋል። የግጭቱን መበርታት ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ወደ ኬንያ ሞያሌ በመሻገር ላይ ይገኛሉ። ዛሬ ጠዋት ብቻ በርካታ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ወደ ኬንያ መግባታቸው የተረጋገጠ ሲሆን፣ ሌሎች ነዋሪዎችም ከተማዋን ለቀው በመውጣት ላይ ናቸው። ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም

አረመኒው የብልፅግና ሰራዊት ለደም ግብሩ የንፁሀንን ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል ። ተስፋ የቆረጠው የብልፅግናው ሃይል በቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክፍለ ጦር ቀጠና በባሶ ሊበን ወረዳ ሻይ ቤት ቁጭ ያሉ ንፁሀንን የሻይ ቤቱን ባለቤት ጨምሮ ሰባት ሰወችን (7)በጥይት የደበደበ ሲሆን አምስት(5) ሰወች ወዲያውኑ የተሰው ሲሆን ሁለቱ ቁስለኛ መሆናቸው ተረጋግጧል ። አንድም ቀን የንፁሀንን ደም ሳያፈስ ውሎ አድሮ ማያቀው ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ ጦር ሻይ ቤት ቁጭ ብለው ባሉበት ደርሶ በጅምላ የገደላቸው 👇🏻 1ኛ አጉማስ ስማቸው የተገደለች 2ኛ አብኔ የተገደለች 3ኛ ይድነቅ መንግስቴ (የሻይ ቤቱ ባለቤት) የተገደለች 4ኛ ቁሜ አመራ የተገደለች 5ኛ ከባድ መንበሩ የተገደለ 6ኛ አወቀ ጌታቸው የቆሰለ 7ኛ ደርብ ላቀ የቆሰለ  ሲሆን ከታች ከሟቾቹ መካከል ገሚሶቹ ከታች በምስሉ የሚታዩት ናቸው  ።     አፋብን ቴዎድሮስ  2 ኛ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳና ጊዳ ኪረሙ ወረዳዎች ላይ ከጥቅምት 09/2019 ዓ/ም ጀምሮ የክልሉ ታጣቂዎች ዳግም በከፈቱት ጥቃት በርካታ ንፁኋኖች ሲገደሉ 3 ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ታወቀ። በጊዳ አያና ወረዳ አሊ ቀበሌ ላይ ተጀምሮ ወደ አባጆ መንደር የተስፋፋው ጥቃቱ፡ አድማሱን በማስፋት በጊዳ ኪረሙ ወረዳ ወዴሳ ዲማ ቀበሌ ድረስ ዘልቆ በርካታ ንፁኋን ወገኖች በገዳ ኮማንዶና በሌሎች የክልሉ ታጣቂዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን  ለማረጋገጥ ተችሏል። ከንፁኋኖች መገደል በተጨማሪ አሊ ቀበሌ፣ አባጆ እና ወዴሣዲማ ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ታውቋል። ከሳምንታት በፊት የክልሉ ታጣቂዎች በአከባቢው በፈፀሙት ጥቃት፡ ከአንዶዴ፣ ከመንደር 03ና መንደር 22 እንዲሁም ከሌሎች አከባቢዎች ተፈናቅለው በአሊ ቀበሌ ከ50ሺህ በላይ ተፈናቃይ ወገኖች ተጠልለው እንደነበር ይታወቃል። ታጣቂዎቹ ተፈናቃዮቹን ያነጣጠረ ጥቃት በመፈፀም ነው ህፃናትና አቅመ ደካሞችን ጨምሮ የንፁኋንን ሕይወት በገፍ የቀጠፉትና መንደሮቹን ያወደሙት። በማዕከላዊ ዕዝና በምዕራብ ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ሽፋን ሰጭነት፡ የአባ ገዳ ኮማንዶ፣ የረጴ ሎላ፣ የጋቼና ሲርና እንዲሁም የሚኒሻ ኃይልና በእነዚህ ታጣቂዎች ሽፋን የሚሰጣቸው ቆንጨራና ሌሎች ስለታማ መሣሪያዎችን የታጠቁ የቄሮ ቡድን አባላት በቅንጅት ከጥቅምት 09/2019 ዓ/ም ጀምሮ በከፈቱት ዘግናኝ ጭፍጨፋ ተፈናቃይ ወገኖችን ጨምሮ ሰብል በመሰብሰብ ላይ የነበሩ አርሶ አደሮች ናቸው የተገደሉት። በጊዳ አያና ወረዳ አሊ ቀበሌ ላይ የተጀመረው ጥቃቱ፡ በቀበሌዋ ተጠልለው ከነበሩ ተፈናቃይ ወገኖች መካከል ህፃናትና አረጋውያንን ጨምሮ በርካታ ንፁኋኖች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። በተጨማሪም የቀበሌዋ ነዋሪ የሆኑ የአኩሪ አተር ሰብል በመሰብሰብ ላይ የነበሩ ከ35 በላይ አርሶ አደሮች በአንድ ቦታ ብቻ ሲገደሉ፡ ቀሪው ሕዝብ ሕይወቱን ለማትረፍ በየአቅጣጫው መበተኑንና መንደሪቷም ሙሉ በሙሉ መውደሟን ነው  ለማረጋገጥ የተቻለው። ጥቃቱ አድማሱን አስፍቶ በወረዳው ወደ አባጆ ቀበሌ የተሸጋገረ ሲሆን፡ በዚህም ንፁኋኖች በገፍ ተገድለዋል፣ ሀብት ንብረትም ተዘርፎ ወደ አንገር ጉቲን ከተማ ተጭኖ ተወስዷል፣ መንደሪቷም መውደሟን ጣቢያችን ለማወቅ ችሏል። የክልሉ ታጣቂዎች በመከላከያ ሠራዊቱ በሚሰጣቸው የከባድ መሣሪያ ሽፋን ታግዘው ለአሊና ለአባጆ ቀበሌዎች አጎራባች ወደሆነችው በጊዳ ኪረሙ ወረዳ ወዴሣ ዲማ ቀበሌ በመሸጋገር በርካታ የአማራ ተወላጆችን በገፍ መግደላቸውንና የአርሶ አደሩን ሰብል ጨምሮ መኖሪያ ቤቶችን ማውደማቸው ታውቋል። አሳምንታት በፊት በተፈፀመባቸው ጥቃት ለጥቂት ተርፈው ከቤት ንብረታቸው በመፈናቀል በአሊ ቀበሌ ተጠልለው የነበሩ ንፁኋኖች፡ ዛሬም በድጋሚ በተከፈተባቸው ጥቃት በርካቶች ሕይወታቸው ሲቀጠፍ፡ ቀሪዎቹ ለዳግም መፈናቀል ተዳርገዋል። ቀሪዎቹ በአሁን ሰዓት ሕይወታቸውን ለማትረፍ በየጫካው የተበተኑ ቢሆንም፡ የሚቀምሱት እህል ውሃ በማጣታቸው በረሃብ እየሞቱ መሆኑም ነው ጣቢያችን ያረጋገጠው።