fa
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
3 613
مشترکین
+6624 ساعت
+5877 روز
+1 04130 روز
آرشیو پست ها
በደረቀው ሌሊት ከየት እንደሚነሳ የማያውቁት ፤ የት ላይ እንደሚወድቅ ያልተረዱት ፤ መከላከል የማይችሉት እና ኢላማውን የጠበቀ መበረቅ በገሐድ እየወረደ ሊያስመስሉ ሲጋጋጡ እንደ ማየት ሚያሳዝንም ሚያስደሰትም ነገር የለም ! የምንከተለው ፖለቲካ መር የትጥቅ ትግል ክንዱ የብረት አለሎ ከመሆኑ በላይ እንዳሸነፈ የምንረዳው ግን የገጠምነው ጠላት የመወጋት ሞራሉ የላሸቀ ፣ አንድነት የሌለው ፣ መረጃዎቹን በቀላሉ አሳልፎ የሚሰጥ እና በህዝቡ ዘንድ ተንቆ አይንህን ለአፈር ተብሎ የተተፋበት በመሆኑም ጭምር ነው ። ይሄ አገዛዝ አጭበርብሮ ስልጣን የጨበጠ ፤ ስራው ሁሉ ህገ ወጥ የሆነ ፤ የሕዝብ ደም የጠማው ፤ ጦርነት ጠማቂ ስርአት ወፍ እንኳን እኛ ሳንፈቅድ መብረር አትችልም ሲል ነበር የጤና ችግር እንዳለበት መገመት እና መጠርጠር የነበረብን ። እስከ አፈቀላጤዎቹ ድረስ ምድር እና ሰማይን ለሰው ልጆች እኩል የፈጠረውን አምላክ በመርሳት በእበሪት ሰማዩ የኛ ነው (The sky is our ) ሲሉ የነበሩ የቤተ መንግስቱ ለማዳ እንስሳቶች እነ ናትናኤል መኮነን ዛሬ ላይ ድሮንን በኢሊኮፍተር ለመከላከል ሲሞክሩ ስናይ ' ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር ' ብለን ተገርመን ሳንጨርስ የገዳዩ ስርአት መሪ ጽ/ቤት በድሮን ተመታ ሲባል ለአብይ ያጎነበሱ እና በመስቀል ለመደበቅ የሚሞክሩት ስጋ ለባሽ ሰይጣኖች እነ ዳንኤል ክብረት ምን ተሰምቷቸው ይሆን ? አሁንም ተረተ ተረት ይዘው ብቅ ይሉ ይሆን ? በራሱ ጊዜ ህዝብ የሰጠውን ተስፋ ቀርጥፎ ከበላ በኋላ መውጫ የሌለው የጦርነት አዙሪት ውስጥ የገባው አገዛዝ አሁን ላይ የሚዲያ ልሳኖቹ ሳይቀር እውነት ከስቲዲዮቻው እንዳትደርስ አድርገው ቢቀብሯትም ለህዝቡ ግን በተለያያ አማራጮች እየደረሰች የአገዛዙን ገመና በማሳየት የውሸታም ሰብሰብ መሆናቸውን ዓለም እንዲረዳ እያደረገች ነው ። የህዝቡን ሰላም እና ደህንነትን ማስጠበቅ አቅቶት በየቦታው በሞት የወጣቱን የነገ ተስፋ በመቀማት የሕዝብ ደም ማፍሰስን እንደ ተቀዳሚ ተግባሩ ያደረገው የዱርየ ስብስብ አሁን ጉሮሮውን ተይዟል ። በጌታቸው ፕሮፖጋንዳ ይሁን በፃድቃን የጦርነት ጥበብ አይድንም ፣ የአልሲስም ዲፕሎማሲ ይሁን ኢሳያስ ወዳጅነት የሚያድነውም የሚያስጠጋውም አይመስልም ። አሁን ሁለት ምርጫዋቹ ከእጁ ላይ ይገኛሉ እነሱም መሠረት ያጣበትን ስልጣን ለሽግግር መንግስትነት አሳልፎ መስጠት ወይም አይኑ እያየ አራት ኪሎን ለቆ መፈርጠጥ ብቻ ነው ። ከዚህ ውጭ የተሸከሙት የዛር መንፈስ እንኳን የሚያድናቸው ቢሆን ከዛር መንፈሱ መቀመጫው አካባቢ የተከሰተውን የደብረ ዘይቱን የድሮን ጥቃት በተከላከለ ነበር ። የትብብር ኃይሉን በአገር ክህደት ስም ሊያጠፋ የሚዳዳው ተቅበዝባዥ ፣ ጥቅመኛ እና የጥቅም ባሪያ ሁሉ ለሌላ አገር አማፂ ቡድን ለዮናይትድ አረብ ኢሚሬትስ በመላላክ አሶሳ ላይ የድሮን ቤዝ መገንባት ትክክል ነው ወይ ? ከዚህም አልፎ የሌሎች አገራትን የአየር ክልል ጥሶ የድሮን ጥቃት መፈፀምስ ልክ ነበር ወይ ? የአገር ብሔራዊ ቅርሶችን ሽጠህ የራስክን ህዝብ ለመጨፍጨፍ አቅደህ በ ድሮን መለወጥስ ልክ ነበረ ወይ ? ብለህ ጥያቄ ብታነሳ ብርሐኑ ጁላ ወጦ ልመርጥልክ ነው ፡ ድሮን የገዛነው ልንዋጋበት ነው ቻለው ይልሐል ። በዚህ ስትገረም ይልማ መርዳሳም ብቅ ብሎ UAE ወንድም አገራችን ነው አሁን ላይ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እኛ ሳንፈቅድ አይደለም ሌላ ነገር 'ወፍ' እንኳን ማለፍ አይችልም ብሎ ይናገራል ። ከሰሞኑ አይነት ድነገቴ ሲገጥመው ደግሞ ጉድጓድ ውስጥ እንደ ገባች አይጥ ድምጡን አጥፍቶ ለጥ ይላል ። አሁን በሕዝብ ላይ የለ አግባብ ሲሰሩ የነበሩ ግፎች ፣ መከራዎች እና ስቃዮች አገዛዙን የመጨረሻ ሕቅታው እንድትቋረጥ ሊያደርጉት ነው ። ለዚህም ተማርኮ የሚያዘው ወታደር የፍርሐት ድንጋጤ የወጣው ፤ በእድሜ ትንሽ እና ታፍሶ የመጣ ሲሆን ተማርኮ የሚያዘው ካድሬ የፖለቲካ ሬሳ ሁኖ በህይወት በመትረፉ ፋኖን በእልቅሶ እና ሳቅ ታጅቦ ሲያመሰገን ታየዋለህ ። አጠቃላይ አገዛዙ መውጫ እና ማምለጫ በሌለው አዙሪት ውስጥ ገብቶ በተግባር አዲስ አበባ ላይ በደረቀው ሌሊት ከየት እንደሚነሳ የማያዩት የት ላይ እንደሚወድቅ ያልተረዱት መከላከል የማይችሉት ኢላማውን የጠበቀ መበረቅ በገሐድ እየወረደ ሊያስመስሉ ሲጋጋጡ እንደ ማየት ሚያሳዝንም ሚያስደሰትም ነገር የለም ። አገር እሳት ላይ ሁና ምንም እንዳልተፈጠረ የሚያስመስሉት የጥቅም ባሪያ ሚኒስተሮች ፤ ሆድ አደር ጄነራሎች እና ቅጥረኛ አፈቀላጤዎች ዋናው ጉዳይ አገዛዙ ከአበቃለት የሚያስጠይቃቸውን አንኳር ጉዳዮች ስለሚያውቋቸው እና ከ ከባድ የአገር ክህደት ወንጀሎች ማምለጥ ስለማይችሉ ብቻ የእነሱን ልጆች ውጭ አገር በሰላም እያኖሩ ለዚህ ሁሉ ወንጀል ሽፋን እንዲሰጣቸው የድሐን ልጅ ለጥፋት የሚማግዱ መሪዎች በውስጣቸው እርስ በርስ የሚሻኮቱ ፤ ጠፍተው ከአገር ለመውጣት በር የተዘጋባቸው እንዲሁም በፈረሰ አስተሳሰብ ውስጥ የአንድነት መዋቅር ለመትከል የሚሞክሩ ደናቁርቶች ናቸው ። ለነዚህ ስልጣን ተብሎ መስዋዕት እየሆነ ያለ ሰራዊት ግንዛቤ ሊፈጠርለት እና ምክንያት ያለው ሞት እንዲሞት የሚመለከተው አገር ወዳድ ዜጋ ሁሉ መልዕክቱን እንዲያደርስ ተፈጥሯዊ ግዴታ ላይ አለበት ። በመጨረሻም የህዝብ መሠረቱን አስጠብቆ ከዚህ የደረሰው ህዝባዊ አቢዮት የማይቀለበስ የህዝብ ማዕበልነቱን አስጠብቆ ፤ ፍትህ ማስፈንን የነጻነታችን ሃይል በማድረግ ይሄን የግሳንግስ ስብስብ በትብብር ጠራርጎ ለማስወገድ የጀመረውን ውጥን የሚያሳካበት ታሪካዊ ጊዜ እና ታሪካዊ ግዴታ ላይ ይገኛል ። አዲስ ትውልድ ፣  አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ ! አርበኛ ግሩም ምሳሌ የቴዎድሮስ 2ተኛ ዕዝ ፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ

ዛሬ ሌሊት በተሰራ ልዩ ኦፕሬሽን ምዕራብ ወሎ መሃል ሳይንት ወረዳ ደንሳ ከተማ ነፃ ወጥቷል!

~~~~~||| ለአዲስ አበባ ህዝብ የጥንቃቄ ጥሪ❗️ በቀጣይ በሚኖሩ ተከታታይነት ያላቸው የድሮን እና...ድብደባዎች ሲቪሊያን ህዝብ ላመስተናገድ ሲባል በሚከተሉት ተቋማት ዙሪያ የምትኖሩ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እንመክራለን:- ✔️ጦር ኃይሎች ምድር ጦር፣ መከላከያ መረጃ ቴክኖሎጂ ዋርፌር(ካርል አደባባይ) ዙሪያ ✔️ሳርቤት ካናዳ ኢምባሲ አካባቢ ወታደራዊ መረጃ የምርመራ አካባቢ ✔️በቅሎ ቤት ፋይናንስ ደህነትነት ማዕከል ህንፃ አካባቢ ✔️ወሎ ሰፈር የኢንሳ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዋና መስሪያቤት ዙሪያ ✔️ቦሌ ኤርፖርት ብሔራዊ መረጃ የጥበቃ መምሪያ ዋና ቢሮ አካባቢ ✔️ ሜክሲኮ የፌደራል ፖሊስ ፋሲሊቲዎች እና ቢሮዎች ✔️ፋና፣ ኢቢሲ፣ ዋልታ እና የአዲስ አበባ ቲቪ አካባቢ ✔️የኦሮሞ ብልፅግና ፅህፈት ቤት መሿለኪያ አካባቢ ✔️የባህር ኃይል ዋና ማዘዣ ላንቻ አካባቢ ✔️የድሮን እና ልዩ ልዩ ኦፕሬሽኖች ማዕከል ኮተቤ እስከ አንቆርጫ አካባቢ ✔️የNISS ዋና መስሪያቤት ፍልውሃ አካባቢ ✔️ የብልፅግና ዋና ፅሕፈት ቤት አራት ኪሎ ስላሴ አካባቢ ✔️ 6ኪሎ የመከላከያ ሎጀስቲክ መምሪያ አካባቢ ነዋሪዎች ✔️ቃሊቲ የልዩ ዘመቻዎች ማዘዣ አካባቢ ✔️ ገላን የ8ኛ ስትራቴጅክ መካናይዝድ ኮር ማዘዣ አካባቢ ✔️ አዲስ አበባ ፖሊስ ዋና መስሪያቤት ዳትሰን ሰፈር አካባቢ ✔️ እንዲሁም የሥርዓቱ የፀጥታ ተቋማት ዲፖዎች እና የሎጀስቲክ ማዕከላት አካባቢ ጨምሮ ህዝቡ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ይመከራል። ለጊዜው ፍላሚንጎ የሽመልስ አብዲሳ ቢሮ እና አራትኪሎ አካባቢ በተለያየ ምክንያት ምንም ነገር አይኖርም። ለናንተ ብየ ነው😁

በአላማጣ ከተማ በከተማዋ ሚኒሻ አባላትና እራሳቸውን የሓራ መሬት ታጣቂ ብለው በሚጠሩት በነጌታቸው ረዳ ሚኒሻዎች መካከል ከባድ የእርስ በእርስ ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል። በግጭቱ መከላከያ ሠራዊቱ እና የፌደራል ፖሊስ አባላቱ ለነጌታቸው እረዳ ሚኒሻዎች በማገዝ የአላማጣ ሚኒሻዎችን ትጥቅ እያስፈቱና እየረሸኑ መሆኑን  ምንጮች ገልፀዋል። "ከፌደራሉ መንግስት ጋር ሆነን የአማራን ሕዝብና የኤርትራን ሕዝብ ማጥፋት አለብን" በሚል ዋና ምክኒያት ከሕወሓት ጋር ልዩነት የፈጠሩት እነጌታቸው ረዳና አቶ ፃድቃን ገ/ተንሣይ፡ በዚህ እሳቤያቸው ከቡድኑ ተነጥለው የራሳቸውን ታጣቂ በማደራጀት ከአገዛዙ ጋር ወግነው እየተዋጉ ይገኛሉ። <<ራያን በጉልበት ጠቅልለን እንወስዳለን፣ ሕዝቡንም ለዳግም ባርነትና ጭቆና እንዳርጋለን>> የሚሉትና ወታደራዊ ስርፀታቸውም በፀረ አማራነት የተሞላ እንደሆነ የሚነገርባቸው የነጌታቸው ረዳ የሓራ መሬት ሚኒሻዎች ሰሞኑን በራያ ግምባር በተደረገ ውጊያ: "ተባራሪ ጥይት" አገኛቸው የሚል ሽፋንን ተጠቅምው የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮችን በመግደል አስከፊ የዘር ጭፍጨፋ መፈፀም መጀመራቸው ተጋልጧል። በዚህ የተበሳጩት የራያ አላማጣ ሚኒሻዎች በነጌታቸው ረዳ ታጣቂዎች ላይ አፀፋዊ እርምጃ የጀመሩ ሲሆን፡ በዚህም ከሁለቱም ወገን ወታደሮች መገደላቸውና መቁሰላቸውን  ታማኝ ምንጮች ገልፀዋል። በዚህ ግጭት መከላከያ ሠራዊቱና የፌደራል ፖሊስ አባላቱ ከሓራ መሬት ታጣቂዎች ጋር በመወገን የራያ አላማጣ ሚኒሻዎችን ትጥቅ ከማስፈታት ጀምረው በጅምላ ሰብስበው እስከ መረሸን የደረሰ እገዛ እያደረጉ እንደሚገኙ ተነግሯል። ፋኖና ሕወሓትን ጨምሮ ከትብብር ኃይሉ ጋር ጦርነት እያካሄደ የሚገኘው የአቢይ አህመድ አገዛዝ፡ ከጎኑ ተሰልፈው ለሚዋጉለት የሓራ መሬት ታጣቂዎች ራያንና ወልቃይትን እንደሚሰጣቸው ቃል እንደገባላቸው መረጃዎች አፈትልከው ወጥተዋል።

🚨 አስቸኳይ፣ ወሳኝ እና አጣዳፊ የወታደራዊ ጥንቃቄ መልዕክት! (እባክዎን ይህንን መረጃ በየትኛውም ቦታ ለሚገኙ የትብብር ኃይሎች፣ የአካባቢ ጥበቃ አባላት እና ህዝባዊ ደጋፊዎች በፍጥነት ያክፍሉ!) ​📍 ከስርዓቱ የውስጥ ምንጮች የተገኘ የተረጋገጠ የመሬት ላይ መረጃ፦ ​በአሁኑ ወቅት በሁሉም የውጊያ ግንባሮች ባለው ተጨባጭ ሁኔታ፣ የመከላከያ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ የመውጫ እና የመግቢያ ቀዳዳዎችን በማጣቱ ምክንያት ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ይገኛል። በዚህም የተነሳ በሰራዊቱ ውስጥ የሚገኙ በርካታ አባላት እጃቸውን ለትብብር ኃይሉ ለመስጠት እና ከስርዓቱ መረብ ለመውጣት በየአቅጣጫው ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው። ​ወቅታዊው አደገኛ ሁኔታ እና የውስጥ ጭፍጨፋ ​🔴 የደቡብ እና የአማራ ልጆች ላይ እየተፈጸመ ያለ ረሸና፦በመከላከያ በሰራዊቱ ውስጥ የሚገኙ የደቡብ እና የአማራ ብሔር ተወላጅ የሆኑ አባላት እጃቸውን ሊሰጡ ነው" ወይም "ከስርዓቱ ለመውጣት አቅደዋል" በሚል ጥርጣሬ ብቻ በመከላከያ አመራሮች እና ታማኝ ተባባሪዎቻቸው በግፍ እየተረሸኑ ይገኛሉ። ​መያዣ ያጡ የመውጣት ሙከራዎች ይህንን መሰል አረመኔያዊ እርምጃ እና ግደላ እያዩም ቢሆን፣ በርካታ አባላት ሕይወታቸውን ለማዳን እና ወደ ህዝባዊ ትብብር ኃይሉ ለመቀላቀል በየግንባሩ አሁንም የመውጣት እና የመኮብለል ጥረታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። ​🛡️ ከትብብር ኃይሎች እና ከአካባቢው ህዝብ የሚጠበቁ ስልታዊ የጥንቃቄ እርምጃዎች፦ ​1. ከፍተኛ የወታደራዊ ንቃት (High Alert) ማድረግ፦ በየትኛውም አቅጣጫና ቦታ የምትገኙ የትብብር ኃይሎች፣ የደፈጣ እና የጥበቃ አባላት የጠላት ኃይል የተስፋ መቁረጥ እርምጃ ሊወስድ ስለሚችል ፍጹም የሆነ የወታደራዊ ዝግጁነት እና ንቃት ልታደርጉ ይገባል። ​2. መኮብለሎችን በጥንቃቄ እና በስልት መቀበል፦ ከስርዓቱ አምልጠው እጃቸውን ለመስጠት የሚመጡትን አባላት በጥንቃቄ፣ በስልታዊ መንገድ እና ወታደራዊ ደንብን በተከተለ ሁኔታ መያዝ እና ማስተናገድ ያስፈልጋል። የጠላት ኃይል ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሞ ሰልፎች እንዳይሰራ ወይም አደገኛ ደፈጣ እንዳያዘጋጅ ቅድመ-ምርመራ እና ጥንቃቄ ማድረግ ወሳኝ ነው። ​3. መረጃን በፍጥነት ማላቀቅ በአካባቢያችሁ የሚታዩ ማንኛቸውንም የሰራዊቱ የቦታ ለውጦች፣ የመበታተን ምልክቶች ወይም የመውጣት እንቅስቃሴዎች በአስቸኳይ ለአቅራቢያው የትብብር ኃይል አመራሮች ማሳወቅ። ወታደራዊ ጥሪ መረጃን በወቅቱ ማዳረስ የብዙዎችን ህይወት ይታደጋል፤ የትግሉንም ስኬት ያፋጥናል! መልእክቱን ሼር በማድረግ የድርሻዎን ይወጡ! Dave Amhara ሙሉ መረጃዎችን ቴሌግራም ላይ ያገኙታል!!

~~~~~|| አሁናዊ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለውጦች መረጃ❗️ ✔️ ሜ/ጀነራል ግዛው ኡማ(የ10ኛ ዕዝ አዛዥ)ሽሬን ገብተህ ተቆጣጠር ተብሎ ነበር። የኤርትራ ሠራዊት ሥለተጠጋ የምዕራብ ዕዝ ኮሮችን ይዠ ልዋጋ አልችልም ብሏል። ብ/ጀ አዲሱ መሃሐመድ እና ብ/ጀ መላኩ ገላነህ የሚመሯቸው የምስራቅ ዕዝ ኮሮች ካልመጡ ንቅንቅ አልልም ብሏል። ስለሆነም የምስራቅ ዕዝ 302ኛ ኮር እና 304ኛ ኮሮች ከጎጃም ወጥታችሁ ከፈለጋችሁ በኦማጀር ዙራችሁ አልያ አዲጎሹ ፀሊሞይ በኩል ሽራሮ ግቡ ተብለዋል። አዲሱ መሃመድ በ91 ጦርነት ደህና ልምድ ያለው የሻለቃ አዋጊ ስለነበር፤ ግዛው ኡማ በተመሳሳይ የተሻሉ ስለነበሩ የሽራሮ እና የራማ ግንባር የናንተ ነው ተብለዋል። ✔️ ሹማ አብደታ የሚመራት ኮማንዶ እና አየር ወለድ አንድ ኮር ይዞ በአፋር ግንባር ከሌ/ጀነራል አሰፋ ቸኮለ ጋር በመሆን መቀሌ ገብታችሁ መግለጫ ስጡ ተብለዋል። ሹማ አብደታ የመቀሌ ከተማን እና አየር መንገዱን ይዞ ወደ መቀሌ የሚገቡ ተንቀሳቃሽ የአየር መቃወሚያ ሚሳኤሎችን ደህንነት እንዲጠብቅ ኃላፊነት ተሰጦታል። ✔️ሜ/ጀነራል አድማሱ አለሙ የሚመራት 11ኛ ዕዝ መቀሌን አልፋ አዲግራት እስከ ኤርትራ ድንበር ድረስ ያለውን ቀጠና ከሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጋር በመቀናጀት እንድትሸፍን ታዝዛለች። ✔️ የአሰፋ ቸኮለዋ ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ከደቡብ ዕዝ ጋር በመተባበር መቀሌን ከተቆጣጠረ በኋላ ከመካናይዝድ ኃይል እና ባህር ኃይል ጋር በመሆን ወደ ቡሬ ግንባር እንዲያዘነብል ተነግሮታል። ✔️ ሜ/ጀነራል ተስፋዬ አያሌው የሚመራው 13ኛ ዕዝ ከሰቆጣ አበርገለ ከመቀሌ ወደ አብዓዲ የሚሄደውን መንገድ በመቁረጥ በቀኝ በኩል መቀሌን ለመቆጣጠር በሚደረገው ውጊያ ድጋፍ እንዲሰጥ፤ በግራ በኩል የ10ኛ ዕዝ ወደ ሽሬ የሚያደርገውን ማጥቃት ከአብዓዲ ወደ ሽሬ በመጠጋት ድጋፊ እንዲሰጥ ተልዕኮ ተቀብሏል። ✔️ ሌ/ጀነራል ብርሃኑ በቀለ የሚመራው ሰሜን ምዕራብ ዕዝ በቆራሪት እና በአዲጎሹ ደደቢትን እንዲቆጣጠር እሷን ከተቆጣጠረ በቀጣይ ኢታማዠር ሹም ለመሆን ቃል ተገብቶለታል። ✔️ በምዕራብ ግንባር ከጌታቸው ጉዲና፣ ብርሃኑ በቀለ፣ እና ግዛው ኡማ ጋር ግንባር አስተባባሪ የነበረው የምዕራብ ዕዝ አዛዡ ሜ/ጀነራል አማረ ባህታ ግንባር ያበላሻል ተብሎ አመኔታ ስላላገኘ ወደ ባህርዳር እንዲመለስ ተደርጓል። ይዟቸው የሄዱት 402ኛ እና 401ኛ ኮሮችን ይዞ ወደ ምዕራብ ጎጃም እንዲመለስ ታዝዟል። ✔️የጎንደር ቀጠና በሜ/ጀነራል መሠለ በለጠ የሚመራው 12ኛ ዕዝ እና የክልሉ ፀጥታ ይሸፈናል ተብሏል። ✔️ጎጃም ቀጠና በምዕራብ ዕዝ እና 6ኛ ዕዝ በጋራ ስምሪት እንዲሸፈን ተደርጓል። የሚሊሻ እና የአድማ ብተና ሥምሪት እንዳለ ሆኖ ይቀጥላል። ✔️ ወለጋ፣ ሸዋ፣ በማዕከላዊ ዕዝ እና 6ኛ ዕዝ ክፍሎች እንዲሸፈኑ ታዘዋል። .....ሌላውን በሂደት እናየዋለን!

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ያሳፈረው የበቅሎ ጋሪ ከመርጡለ ማርያም - መካነሰላም ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። በመርጡለ ማርያም እና አካባቢው ፈጣኑ የትራንስፖርት አገልግሎት የበቅሎ ጋሪ ከሆነ ሁለት ወራትን አስቆጥሯል። ከመርጡለ ማርያም ሰኞ -ወርያ -መካነሰላም በሚወስደው ጥቁር አስፓልት የተሽከርካሪ እቀባ ያደረገው የካድሬዎች ስብስብ በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ስቃይ እየፈፀመ ሲሆን ወደ መቅደላ ዩኒቨርስቲ የሚሔዱ ተማሪዎችን ጨምሮ ለማህበረሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ያነጋገርናቸው ባለ ጋሪዎች ተናግረዋል። ከ25 በላይ ቀበሌዎች በቀጥታ አገልግሎት የሚሰጠው ጥቁር አስፓልት በመታገዱ ከ7 በላይ እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸውን አጠዋል፣ አርሶአደሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ መምህራን ፣ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው በወረዳው የትምህርትም ሆነ የንግድ እንቅስቃሴ ከተቋረጠ ሰንብቷል። ለጤና ተቋማት የሚቀርቡ መድሐኒቶች እና የህክምና ቁሳቁሶች በወቅቱ በተቋማቱ ማድረስ ባለመቻሉ ማህበረሰቡ በህክምና እጦት እየተሰቃየ እንደሆነም ያነጋገርናቸው የጤና ባለሙያዎች የጉዳዩን አሳሳቢነት አስታውቀዋል። የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ተማሪዎች እና መምህራን መንገዱ እንዲከፈት በተደጋጋሚ በካድሬዎች ፊት ቁመው ደጅ ቢፀኑ የራሳቸውን ህዝብ በማሰቃየት በሚረኩ ባንዳዎች ስድብ ፣ ዱላ እና እስር እንደገጠማቸውም የደረሰን መረጃ ያመላክታል ። በአንፃሩ ለብልፅግና አሽከር በመሆን በታማኝነት የሚታውቀው ብርሃኑ ዋለ እና የመብራት ኃላፊው አቶ ዳኘ በጋራ በመመሳጠር በመርጡለ ማርያም ከተማ በመብራት ኃይል አቅራቢነት እየተሰራጨ ካለው የቤት መብራት ቆጣሪ ከእያንዳዱ ደንበኛ በህገወጥ መልኩ ከመብራት ኃይል እውቅና ውጭ ያለ ምንም ደረሰኝ 5,000-8500 ብር ለሚኒሻ ድጋፍ በሚል በመቀበል በመርጡለ ማርያም ከተማ ከተሰራጨ 600 የቤት የመብራት ቆጣሪ ከ4,500,000 ብር በላይ ከመብራት ኃይል ደንበኞች መዝረፋቸው ተረጋግጧል። በታላቋ ርዕሰ ርዑሳን መርጡለ ማርያም ገዳም እጁን በማስረዘም ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመጣስ ካህናትን ሲያተራምስ የነበረው ካድሪ የቤተክርስቲያኗን ቅጥር ግቢ በመጣስ እንዲሁ የዲሽቃ መጥመጃ በማድረግ በህዝቡ ዘንድ አሰነዋሪ ተግባር መፈፀማቸውን ቀጥለዋል። መስከረም 21/2018 ዓ.ም "ጎጃም አማራ"

የጥንቃቄ መረጃ!!! ከምሽቱ 2:222 ባ/ዳር መኮድ ወደ መሸንቲ አቅጣጯ በእርካታ መኪኖች አቁሟል!!! ፈረስ ቤት ና ቋሪት ለመንቀሳቀስ ጠርንፈዋል:: ሙሉ መርጃዎን ቴሌግራም ቻናላችን ላይ ያገኙታል ይወዳጁን

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ 1ኛ ዕዝ የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ ክበረ በዓልን በታላቅ ድምቀት አከበረ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ከአውደ ውጊያ ጎን ለጎን የሕዝብ ባህል፣ ወግና ሃይማኖታዊ እሴቶችን ለማስከበርና ለማሳደግ ባለው ጽኑ ቁርጠኝነት መሠረት፣ ዓመታዊ የመስከረም 𝟐𝟏 /𝟐𝟎𝟏𝟗 ዓ.ም  የግሸን ደብረ ከርቤ በዓልን በታላቅ ድምቀትና መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት አክብሯል። በዚሁ ታሪካዊና መንፈሳዊ ክብረ በዓል ላይ የምኒልክ 1ኛ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በቦታው ተገኝተው ከሕዝቡ ጋር የበዓሉ ተካፋይ የሆኑ ሲሆን፣ ለታደሙት የክብር እንግዶች፣ ምዕመናንና ለአካባቢው ማህበረሰብ ጥልቅ የነፃነት፣ የመከባበርና የወንድማማችነት መልዕክት አስተላልፈዋል። አመራሮቹ በመልዕክታቸው እንደገለጹት፤ የአማራ ፋኖ ትግል የሕዝብን ሕልውናና መብት ለማስከበር በሚያደርገው ሁለንተናዊ ትግል ውስጥ የታሪክ፣ የባህልና የእምነት እሴቶችን መጠበቅና ማክበር ዋነኛ መመሪያዊ እንደሆነ ገልጸዋል። በዚህ ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይም የምኒልክ 𝟏ኛ ዕዝ  የሰራዊቱ አባላት በዓሉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ በከፍተኛ ዲሲፕሊንና ኃላፊነት ስሜት በመንቀሳቀስ፤ የእንግዶችንና የምዕመናንን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ፣ በማስተናገድ ረገድ በከፍተኛ ሁኔታ ሲስሩ ቆይተዋል። የግሸን ደብረ ከርቤ አመታዊ በዓልን ለማክበር ከተለያዩ ቦታወች የመጡ እንግዶችም  በዓሉ በሙሉ ሰላምና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር አስተዋጽኦ ላደረጉ ለምኒልክ 𝟏ኛ ዕዝ  አመራሮች እና የሰራዊት አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ክብረ በዓሉም በታላቅ መንፈሳዊ ስሜት፣  በጋራ ደስታ ታጅቦ በሰላም ተጠናቋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን  መምሪያ!! መስከረም፦ 21/ 2019 ዓ/ም

የድል ዜና ‼ "... አ.ፋ.ብ.ን ቴወድሮስ 2ኛ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር ሻንበል መማር ጌትነት 2ኛ ሻለቃ በጥላት ላይ ከፍተኛ ምት አሳርፋለች ! መስከረም 21/2019 ዓ/ም ሜጫ "...የፋሽ
+1
የድል ዜና ‼ "... አ.ፋ.ብ.ን  ቴወድሮስ 2ኛ ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር ሻንበል መማር ጌትነት 2ኛ ሻለቃ በጥላት ላይ ከፍተኛ ምት አሳርፋለች ! መስከረም 21/2019 ዓ/ም  ሜጫ "...የፋሽስቱ ዐብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሰራዊ ህዝብ ለመዝረፍ እና  ለመግደል ለወረራ መነሻውን ማዳቀያ እና መሸቴ በማድረግ የፋኖ ቀጠና ወደሆነ ይፌሳ ሀሙሲት በጥዋት እየተግተለተለ ሲንቀሳቀስ የሻንበል መማር ጌትነት 2ኛ ሻለቃ አንድ አጋል የሆነች  ሻንበል 1 ቅድማ መንገድ ላይ በመጠበቅ በደፈጣ ከባ ስታፈዳየው አርፍዳለች እንደኑግ የተወቀጠው ጥላት ተበታትኖ ወደመጣበት ሲመለስ ተጨማሪ ሀይል ከባህርዳር አበባ ምርት አካባቢ ያለው ቢመጣም እሱም የጎቻ አናብስቶች እንደ ንብ ሲነድፉት ቁስለኛውን እና አስከሬኑን ሸክፎ ወደመጣበት ፈርጥጧል  ። "... መርዓዊ ከተማ ላይ የሰፈረው ካድሬ በከባድ ጭንቀት ውስጥ ገብቶ መውጣት መግባት አልችል ስላለ ፤ ከፋኖ ሰሞኑን በውስጥ ስራ ምክንያት ዘመቻ አልደረግባቸው ሲል ጊዜ ቆረቆንደዋ የድርቅ ከብት ኮሎኔል ይመር ገበየሁ ከልብ እንደነካው ውሻ ወደ ፋኖ ቀጠና ሰሞኑንን ጡል ጡል አብዝታ ነበር ነገር ግን ቅንድቧን እየተላጨች በገባችበት ቀጠና ሁሉ አስከሬን እየተሸከመች ነው የወጣችው ። ግድ የለም ቀጣይ ሱናሜ ተነስቶ ጠራርጎ ስለሚወስዳችሁ አትክለፍለፉ !! ድል ለተገፋው አማራ ! ድል ለአሳረኛው ፋኖ 💪!! መስከረም 21/2019 ዓ/ም

አስቻለው ደሴ ክፍለ ጦር አርማኒያ ላይ ድል መቀዳጀቱ ተገለፀ!!            መስከረም 21/2019 ዓ/ም የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር አስቻለው ደሴ ክ/ጦር 3ኛ ሻለቃ ቃኝ በሰሩት ልዩ ኦፕሬሽን አርማኒያ ከተማ  ልዩ ቦታው በርበሬና ኑሬአፋፍ ላይ ድል መቀዳጀታቸውን የኮሩ ቃል አቀባይ አስታወቀ። በቀን 20/01/2019 ዓ.ም ከምሽቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በአርማኒያ ዙሪያ በርበሬና ኑሬአፋፍ በመሸገው የፀረ-ሕዝብ አገዛዝ ጥምር ጦር ላይ ፈጣን ጥቃት ተፈፅሞበታል።  በዚሕ አውደ ውጊያ በምሽግና በእንቅስቃሴ የነበሩት የመከላከያና የሚሊሻ ሠራዊት በተፈፀመባቸው ፈጣን ጥቃት ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማስተናገዱ ተረጋግጧል። በዚሕ አውደ ውጊያ ጠላት ጥምር ጦር ብሎ ከሚጠራው ሠራዊት 13 የሚሆኑት ሲገደሉ፡ 5 የሚሆኑት ደግሞ ከባድና ቀላል ቁስለኛ መሆናቸውን በደረሰው መረጃ አመላክቷል። በተጨማሪም ከከተማ ጭማሬ ኃይል ይዞ የመጣ መኪና በመመታቱ ከጥቅም ውጪ እንደሆነ አክሎ፤ ቁስለኛቹም ከሞት የመትረፍ እድላቸው ጠባብ እደሆነ በደረሰን መረጃ አረጋግጧል። " ክብር ለትግሉ ሠማዕታት! " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

እንደምን አላችሁ የአማራ ልጆች ዛሬም የአብይ አህመድ አረመኔያዊ አገዛዝ የወንድሞቻችን ፒጅ እየመታ ስለሆነ የአርበኛ አማር ታዘዘን ፒጅ ይወዳጁት። https://www.facebook.com/profile.php?id=61595195091227&mibextid=ZbWKwL

ይህ የአርበኛ ዝናው የፊስቡክ አካውንት ነው ይወዳጁት። https://www.facebook.com/share/1CJye5uCrz/

አገዛዙ የአማራ ሕዝብን ጨምሮ ንፁኋን ኢትዮጵያውያንን የሚጨፈጭፍበት በአፋር ሰመራ በሚገኘው የድሮን ማዘዢያ ጣቢያ ላይ በተፈፀመ ጥቃት የኮሎኔልነት ማዕረግ ያለው አንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን ጨምሮ 11 የአገዛዙ ቁልፍ ወታደራዊ ሰዎች መገደላቸው ተረጋግጧል። የሲቪል አውሮፕላን ማረፊያዎችን ለድሮንና ለጦር ጄት ማኮብኮቢያነት እየተጠቀመ የሚገኘው የብልፅግናው አገዛዝ፡ "በሰፈሩት ቁና ይሰፈራል" እንዲሉ አበው ዛሬ ቀኑ ደርሶ የጦር ጄቶቹና ድሮኖቹ እንዲሁም የራዳር ሲስተሞቹ እንደ ጧፍ መንደድ ጀምረዋል። ጥቃቱ የተፈፀመው በትብብር ለሕልውና ጥምር ኃይሉ ነው የተባለ ቢሆንም፡ ትብብር ለሕልውና ኃይሉ ግን እስካሁን በግልፅ ኃላፊነቱን አልወሰደም። ነገር ግን ጥቃቱን የፈፀመው የትብብር ለሕልውና ጥምር ኃይሉ ከሆነ፡ ይህ እርምጃው በምድር የተቀዳጀውን ወታደራዊ የበላይነት በሰማይም መድገም የሚያስችል አስደማሚ አቅም መፍጠሩን በግልፅ የሚያሳይ ነው ሲሉ መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው ወታደራዊ ተንታኞች ገልፀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የዲፕሎማቲክ መቀመጫና ርዕሰ መዲናዋ አዲስ አበባ ትናንት ለዛሬ አጥቢያ ለሊት በከባድ ፍንዳታ ስትናጥ ማደሯን የከተማዋ ነዋሪዎችን በማነጋገር ፍንዳታው ከተሰማበት እኩለ ለሊት ጀምሮ በማህበራዊ ትስስር ገፆቹ መረጃዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።