ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más4 387
Suscriptores
-424 horas
+2487 días
+1 44230 días
Archivo de publicaciones
⚫️#የአምባገነኑ_የአጥፍቶ_ጥፋት_ጥቃት‼️
ዘረፈጁ የአብይ አህመድ ብልፅግና በወደር አልባ ጭካኔው ለአመታት ህዝባችን ላይ የመከራ ዶፍ ሲያዘንብ መቆየቱ የሚታወቅ ነው ። ይህ አረመኔ ስርዓት በእግረኛ ሰራዊቱ ሲቭሊያን ላይ የሚፈፅመው ግፍ አላረካው ብሎ አየር ሀይሉን ተጠቅሞ ንፁሃንን ፣ነፍሰጡር እናቶችን ፣ህፃናትን ፣አረጋውያንን እንዲሁም የህዝብ መገልገያ ተቋማትን ጨምሮ በጅምላ እያወደመ ይገኛል‼️
ትላንት ማለትም ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም በ በጎጃም (አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ ) ፋግታ ለኮማ ቀጠና በተፈፀመ የጀት ድብደባ ስድስት (6)ከብት እና አራት (4)ፍየል የገደለ መሆኑ ይታወቃል። ይህ ተስፋ የቆረጠ ስርአት ህፃናትን በጅምላ ለመጨረስ አልሞ ለዚህ አሳፋሪ ተግባር አየር ሀይሉን እየተጠቀመ ይገኛል ።በዛሬው እለት ደግሞ #በጎንጅ_ቆለላ ወረዳ የሚገው #አንጎፌ ትምህርት ቤት በስርአቱ #የድሮን_ጥቃት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
...በምስሉ የምትመለከቱት በቀን 10/2/2019 ፋግታ ለኮማ በተፈፀመ የጀት ድብደባ የተገደሉ እንስሳት ናቸው
አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ !
©አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!
ለመላው ሠራዊታችን በሙሉ፦ አንደሚታወቀው የተሰጣችሁን ወታደራዊ ግዳጅ በየግንባሩ ሁሉ በብቃት እየተወጣችሁ ትገኛላችሁ። የጠላትን የማጥቃት አቅም ሙሉ በሙሉ አዳክማችሁታል። ስለሆነም በመሬት ላይ የተሸነፈው አገዛዝ በአየር ላይ ጥቃት ጉዟችንን ለመግታት የሚያደርገው ሙከራ አንዳችም ለውጥ እንደማያመጣ ይታወቃል። ይሁን እንጅ አላስፈላጊ መስዋዕትነትን ለመቀነስ ሲባል በየግዳጅ ቀጠናችሁ ሆናችሁ መሰባሰቦችን በመቀነስ ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን።
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
— አርበኛ አበበ ሙላቱ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወታደራዊ ቃል አቀባይ
• ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም
◦ በተጨማሪም በሌላ የግዳጅ ቀጠና ደቡብ ወሎ መካነ-ሰላም መቅደላ ላይ የአገዛዙ የዕዝ ም/አዛዥ ለኦፕሬሽን በሆነው በጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ ቀጥተኛ መሪነት የተመራው የዘረ-ፈጁን 11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 87ኛ ክ/ጦር 1ኛ እና 2ኛ ሻለቆችን በመደምሰስ ከ130 በላይ ተማርከዋል። በ6 ቀናት ውስጥ 1 ዲሽቃ፣ 1 ሞርተር፣ 5 ብሬን፣ 4 ስና
ይፐር፣ 2 አርፒጂ፣ ከ230 በላይ ክላሾች ተማርከዋል፤ በዚሁ ግንባር ቀደም ሲልም መስከረም 24/2019 ዓ.ም የ87ኛ ክ/ጦር 4ኛ ሬጅመንት መደምሰሱ ይታወሳል።
• ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም፦ በሰከላ ወረዳ ሰከላ ከተማ፣ ቲሊሊ ወረዳ አሽፋ፣ ባንጃ ወረዳ ጉባላ እና ፋግታ ለኮማ ወረዳ ዋዝ ላይ የጠላትን የ44ኛ ክፍለ ጦር ከበባና ጥቃት በመልሶ ማጥቃት ማክሸፍ ተችሏል።
◦ በዋዝ ከተማ የቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 44ኛ እና 55ኛ ከፍለ ጦር እንዲሁም የዕዙ ኮማንዶ ዩኒት ጥምረት 2 ብሬን፣ 26 ክላሽ፣ 5,200 የክላሽ እና 4,700 የብሬን ጥይቶች እና 5 ወታደሮች ተማርረዋል።
• ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም፦ መነሻውን ጃዊ ፈንድቃ ያደረገ እና በጄኔራል መድፍ፣ ታንክ፣ ዙ-23 እና ሞርተር የታጀበ የጠላት ሃይል ጃይማላ ከተማን ለመውረር ሲንቀሳቀስ በይላላ እና ኩብሊ የሁለት ቀን እልህ አስጨራሽ ውጊያ ተደርጎበት ወደ መጣበት ጃዊ ፈንድቃ ተመልሶ እንዲፈረጥጥ ተደርጓል።
• ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም፦ ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ ጃዊ ከተማ ሞሰቢት/አውስኮድ በተባለ ቦታ የተጠራቀመውን የአገዛዙን ካምፕ ጥዋት 11:30 ሰዓት ላይ ዘልቆ በመግባት መብረቃዊ ጥቃት ፈጽሟል፤ ሰራዊቱ ከፍተኛ ሰብአዊ ኪሳራ አድርሶበታል።
፬. ምዕራብ ግንባር፦ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ከጥቅምት 1 - 9/2019 ዓ.ም የተሰሩ ስራዎች፦
• ጥቅምት 1/2019 ዓ.ም ወጅ አምባ:- ከወረታ ዓለም በር ሲንቀሳቀስ የነበረው የአገዛዝ ኃይል በሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ነበልባሉ 23ኛ ክፍለ ጦር ቃኝ እና መሃንዲስ አባላት ከጠዋቱ 12:00 እስከ 3:00 ሰዓት በዘለቀ የተቀናጀ የደፈጣ ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዷል።
• ጥቅምት 03/2019 ዓ.ም በ4 ዋና ዋና ንዑስ ግንባሮች:-
1ኛ, ደልጊ ከተማ: የ202ኛ ኮር አሀዶች ከሰዓት በዘለቀ ውጊያ 45 የጠላት ኃይል ደምስሰዋል፤ ከ50 በላይ ቀላልና ከባድ ቁስለኞች አድርሰዋል፤ 1 ብሬን፣ 1 ስናይፐር እና 15 ክላሾች ማረከዋል።
2ኛ, ወረታ-ጉማራ መስመር: በሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር (23ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት) አማካገኝነት በነጭ አፈር፣ ታንኳ ገብርኤል እና ጉማራ በጠላት ሀይል ላይ ጥቃት ተፈፅሟል።
3ኛ, ንፋስ መውጫ፦ በ206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ገብርዬ ክፍለ ጦር እና አንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር በቅንጅት በሰሩት ስራ የቀድሞው የንፋስ መውጫ ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አንዳርጋቸው አድማስን ጨምሮ በርካታ ኃይል ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
4ኛ, ሀገረ ገነት - ዛጎች መስመር፦ በ206ኛ ኮር፣ አንበሳው ጋይንት እና ተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦሮች በተደረገ ጥቃት በታጥሮ በር እና ደንኮርኮ ከፍተኛ ምት ማሳረፍ ተችሏል።
• ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም ማሰሮ ደንብ ከተማ:- በማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ በ305ኛ ጎቤ መልኬ ኮር በተደረገ ውጊያ የጠላት ዋና መቀመጫ የነበረችው ማሰሮ ደንብ ከተማ እና የኮንክሪት ምሽጓ ተሰብሯል።
◦ በዚህም 48 የጠላት ሀይል ተደምስሰዋል፤ 41 ቁስለኛ፣ 15 ክላሽንኮቭ፣ 1 ቦቲ መኪና እና 1 ፓትሮል ተማርከዋል። ኩርቢ ላይም ተጨማሪ ኃይል በደፈጣ ተመቷል።
◦ በተመሳሳይ: በደራ እና አንዳቤት ወረዳዎች በጉና ክ/ጦር፣ ጣና ገላውዴዎስ ክፍለ ጦር እና ቃኝና መሀንዲስ ከቀኑ 12:30 እስከ ማታ 10:00 ሰዓት ድረስ በተደረገ መደበኛ አውደ ውጊያ ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል።
• ጥቅምት 07/2019 ዓ.ም፦ ከንፋስ መውጫ ተነስቶ ወደ ታች ጋይንት የተንቀሳቀሰውን ጥምር ኃይል በ206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ገብርዬ ክፍለ ጦር በሦስት ግንባሮች (በመጋ፣ አጋጥ፣ በረንታ፣ አርብ ገበያ ከተማ ዶ/ር አምባቸው ሆስፒታል አካባቢ) እስከ ማታ 1፡00 ሰዓት በተደረገ ውጊያ የሻለቃ አመራሩን ጨምሮ በርካታ ሰራዊት ተደምስሷል።
ማጠቃለያ፦
በአፋብን በየግንባሩ የተመዘገቡት እነዚህ ድሎች ተራ የአካባቢ ቁጥጥር ሳይሆኑ የአገዛዙን የውጊያና የፖለቲካ መዋቅር በማፍረስ፣ ወደ ፌደራል ማዕከል (አዲስ አበባ) ለሚደረገው ወሳኝ የነፃነት ጉዞ መንገድ ጠራጊዎች መሆናቸውን ያረጋግጣሉ።
በመጨረሻም
መሬት ላይ ብልጫ የተወሰደበት እና አቅሙን ያጣው ዘረ-ፈጁ የአብይ አህመድ ሥርአት ከምንግዜውም በላይ ሰፊ የሆነ የድሮን እና የጀት ስምሪት በመስጠት ተደጋጋሚ ጥቃት በንፁሀን ህዝባችን እና ተቋማት ላይ እየፈፀመ ይገኛል።
ለአብነት ያክል በትላንትናው ዕለት ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም በቴዎድሮስ 2ኛ እዝ ቀጠና በጎጃም አዊ ዞን ፋግታ ለኮማ በሲቪሊያን መኖሪያ መንደር ላይ በተፈፀመ የአየር ኃይል የጄት ድብደባ በቤት እንስሳትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሷል።
አገዛዙ ይህን የሽብር ጥቃት እየፈፀመ ሲሆን፣ የሰው ሕይወት መጥፋቱ በውል ባይታወቅም የቤት እንስሳት መገደላቸውና ንብረት መውደሙ ተረጋግጧል።
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መረሀቤቴ እና መንዝ አውራጃም ተመሳሳይ የአየር ላይ ጥቃት ተፈፅሞ ሲቪሊያንና ንብረት ላይ ከፍተገኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በምኒልክ 1ኛ ዕዝ ቀጠና በደቡብ ወሎ መሀል ሳይንት ዴንሳ ወርዳ ለይ በተደረገ የድሮ ጥቃት የአቢሲኒያ ባንክ እና የአማራ ባንክ ጥበቃዎችን ጨምሮ ከአስር በላይ ሲቪሊያኖች የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡ በርካታ ከፍተገኛ ቁስለገኛ ስላለ የሟቾች ቁትር ከዚህም በላይ ሊጨምረ እንደሚችል ይገመታል፡፡ በዚህም በሲቪሊያን እና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።
በተጨማሪም ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ቀጠና ላይ ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም የዘረ-ፈጁ ብልጽግና አገዛዝ በደቡባዊ ጎንደር ደራ ወረዳ ሳና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ባደረሰው የድሮን ጥቃት ተማሪዎችን በትምህርት ገበታቸው ላይ ሳሉ የጨፈጨፈ ሲሆን፣ በርካቶችንም ከከባድ እስከ ቀላል አካላዊ ጉዳት አድርሶባቸዋል። በተጨማሪም በዕለቱ ከቀኑ 5:40 ሰዓት ላይ በአንዳቤት ወረዳ ወለሽ ከተማ የሚገኘውን የከተማ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት አውድሟል።
በመሆኑም የንፁሐኖች ደም ይገደኛል የሚል የትኛውም አካል ድርጊቱን በይፋ እንዲያወግዝ እና እንዲቃወም መልዕክታችንን እናስተላለፋለን።
ለመላው የአማራ ሕዝብ
የብልፅግናው አገዛዝ የአማራ ህዝብ ጠላትነት ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው እውነት ነው። ለዚህም ነው ላለፉት ጥቂት ዓመታት ዱር ቤቴ ብለን ይህንን ዘረ-ፈጅ ስርዓት እየታገልን እና እያንኮታኮትን የምንገኘው። ጀግናው ህዝባችንም ከጎናችን ተሰልፎ እየታገለ ያለው። ይሄን ስርዓት እስከመጨረሻው አስካልቀበርነው ድረስ ሠላም የሚባል ነገር ለአማራ ህዝብ ስለማይታሰብ መላው ህዝባችን ይሔን ስርዓት ለመገርሰስ እያደረገ ያለውን ተጋድሎ ከምንግዜውም በላይ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እናስተላልፋለን።
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የወታደራዊ
የግንባር አውደ ውሎና የድል መግለጫ ከመስከረም 26 - ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ህዝባዊ ሀይል ትብብር ለህልውና (ትብብር ለህልውና) አካል የሆነው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በየግንባሩ በየዕዞቹ ባለፉት ሳምንታት ባደረጋቸው አውደ ውጊያዎች የአገዛዙን የውጊያና የፖለቲካ መዋቅር በመበጣጠስ ታሪካዊ እና ተዓምራዊ ድሎችን አስመዝግቧል። አገዛዙ ቀጠናዎችን ተቆጣጥሬያለሁ በማለት የሚነዛው የሐሰት የፖለቲካ ድራማ በመሬት ላይ በተመዘገቡ ተጨባጭ ድሎች ሙሉ በሙሉ ከንቱ የተደረገ ሲሆን፤ የዘረ-ፈጁ ሰራዊት ፍርሰትና የፋኖ እጅግ የላቀ ወታደራዊ አቅም በሚከተለው መልኩ በየዕዞች ተደራጅቶ ቀርቧል፦
፩. በደቡብ ግንባር፦ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ከመስከረም 27 - ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም ድረስ ያደረጋቸው ተጋድሎዎች፤
በደቡብ ግንባር የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ያስመዘገባቸው ድሎች የአገዛዙን የሠራዊት እንቅስቃሴና የአየር ሃይል ሙከራዎች ማክሸፍ ችሏል። በዚህ ግንባር የጠላትን ወታደራዊ አቅም እና የስነ-ልቦና ልዕልና ከመሰረቱ በመናድ የዕዙን የተከላካይነት እና የማጥቃት አቅም ያረጋገጠ ነው። የአገዛዙ ሠራዊት በቁጥርም ሆነ በቁሳቁስ የነበረውን ብልጫ በመስክ ላይ በሚገኘው የሰራዊታችን ጀግንነት፣ ቆራጥነት እና የውጊያ ስልት ተሽሯል።
• መስከረም 27 - 29/2019 ዓ.ም፦
በመንዝ አውራጃ አናዝ ቀበሌ 19 በፋኖ የማጥቃት እርምጃ የተደናገጠው የአገዛዙ ድሮን የውር ድንብሩን እየዞረ ባለበት ቅፅበት ተከስክሷል። በመሀል ሜዳ እና ዘመሮ አቅጣጫ የተሰነዘረው የአየር ድብደባ ሙከራ ሙሉ በሙሉ ከሽፏል።
◦ በሁሉም ግንባሮች በተደረገ ተጋድሎ 593 የብልፅግና ሠራዊት ተማርከዋል።
◦ 3 ድሽቃ፣ 20 ብሬን፣ 17 ስናይፐር፣ ከ1,600 በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች እና በርካታ ተተኳሾች ተማርከዋል።
◦ ቀጠናውን ያረጋጋሉ ተብለው ወደ መሀል ሜዳ የገቡት የአገዛዙ 6ኛ ዕዝ 2 ሻለቆች፣ የ52ኛ ክፍለ ጦር 28ኛ ሻለቃ እና 5ኛ ሻለቃ ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል።
◦ በአንድ ጊዜ ብቻ የ6ኛ ዕዝ 15 የመከላከያ ሠራዊት አባላት የፋኖን ድል በመመልከት ከእነ ትጥቃቸው ዕዛችንን ተቀላቅለዋል።
• መስከረም 26 - 27 (ለሁለት ቀናት):- በከሰም ቀጣና ምንታምር ከተማ በተደረገ ተጋድሎ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ሰራዊት ተደምስሷል። ጠላት በውጊያው 2 ጊዜ ድሮን የተጠቀመ ቢሆንም ምንም ለውጥ ሊያመጣለት ባለመቻሉ፣ በውጊያው የተመቱ አመራሮችን አስከሬን ለማውጣት የተላኩ ሄሊኮፍተሮች 6 ጊዜ ተመላልሰው በጀግናው ሰራዊታችን መሬት ላይ ማረፍ እንዳይችሉ ተደርገዋል።
◦ መሀል ሜዳ መውጫ ላይ የሚገኘው ከፍተኛ ወታደራዊ ቁሳቁስ የተከማቸበት የአገዛዙ ምሽግ ተሰብሮ ሠራዊቱ ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ውሏል።
◦ የመንዝ 4ቱ ከተሞች እና ታላላቅ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ከአገዛዙ ነፃ ወጥተዋል፤ መንዝ ቀያ ዘመሮ ከተማ፣ መንዝ ጌራ ምድር መሀል ሜዳ ከተማ፣ ወገሬ ከተማ፣ መራኛ ከተማ፣ ሬማ ከተማ፣ ጅሁር ከተማ፣ አንጨቆረር እና መርሐቤቴ ገዢ ቦታ የሆኑት፦ ጀማ እና ኮላሽን ጨምሮ ሌሎች መለስተኛ ከተሞች ተይዘው ህዝባዊ ውይይቶችና የአደረጃጀት ስራዎች እየተሰሩ ናቸው።
• መስከረም 30 /2019 ዓ.ም፦ በመዘዞ ከተማ እና ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም በመርሀቤቴ ዙሪያ በዞማ ተራራማ ስፍራዎች በተደረጉ አውደ ውጊያዎች የጠላት ቅስም ተሰብሯል።
• ጥቅምት 7/2019 ዓ.ም፦ የመሀል ሜዳ ከንቲባ እና የሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ኃላፊ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
• ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም፦ በአለም ከተማ በተደረገ የከተማ ውስጥ ሰርጅካል ኦፕሬሽን 2 ሚሊሻ ሲገደል 5 ቆስለዋል፤ ፋኖ ከተማ መሀል በተጠና መንገድ እርምጃ መውሰዱ የአገዛዙ ካድሬዎችን ጭንቀት ጨምሮታል።
• ጥቅምት 9 /2019 ዓ.ም ከደብረብርሃን ከተማ ወደ አንኮበር ከተማ ሁለት ዙ-23፣ አንድ ቢኤም እና አንድ መድፍ ከ40 መኪና በላይ እግረኛ ጦር ይዞ የዘለቀው የአገዛዙ መካናይዝድ ጦር በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ አማካኝነት ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ በተደረገ ከባድ የደፈጣ ውጊያ ክፉኛ ተመቷል።
◦ በዚህም ሽንፈትን የተከናነበው የአገዛዙ ጦር ተስፋ በመቁረጡ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት አካባቢ ከአንኮበር ቤተ መንግሥት እና መድኃኔአለም ቤተክርስቲያን ታሪካዊ ቅርሶችን እንዲሁም የባንክ ገንዘቦችን ሙሉ በሙሉ ጠራርጎ ከቁስለኞቹ ጋር በ40 መኪና ጭኖ ወደ ደብረብርሃን ተመልሷል።
፪. ምስራቅ ግንባር፦ ምኒልክ 1ኛ ዕዝ ከመስከረም 30 - ጥቅምት 8 /2019 ዓ.ም የተሰሩ ስራዎች፦
• መስከረም 30/2019 ዓ.ም (አንደኛ ዙር):- ምኒልክ 1ኛ ዕዝ 13ኛ ኮር 137ኛ (ውባንተ አባተ) ክፍለ ጦር እና 138ኛ (ራስ አንችም) ክፍለ ጦር በጋራ በመሆን ከ60 በላይ የጠላት ኃይል ደምስሰዋል፤ 30 ምርኮኞችን መማረክ ተችሏል።
◦ የተማረከ፦ 1 ብሬን፣ 2 ስናይፐር፣ 1 አራባ ጎራሽ ክላሽ፣ 52 AK-47 ክላሽንኮቭ፣ 46 የወገብ ትጥቅ፣ 27 የእጅ ቦንብ፣ 640 የብሬን እና 1,780 የክላሽ ተተኳሾች።
• መስከረም 30/2019 ዓ.ም (ሁለተኛ ዙር):-15ኛ ኮር 152ኛ እና 155ኛ ክፍለ ጦር ከለገሂዳ ወረዳ እስከ ጃማ ደጎሎ ድረስ ባደረጉት ተጋድሎ ከ50 በላይ ሰራዊት ሲደመሰስ ከ30 በላይ ቁስለኞች አድርሰዋል፤ የጃማ ወረዳ ሚኒሻ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆነውን ኮሎኔል ሃብታሙን መደምሰስ ተችሏል።
• ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም፦101ኛ ኮር ከተንታ ወደ ተሬና ጉና ተንቀሳቅሶ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ ስቦ የመምታት ስልት በመጠቀም የጠላትን 2 ሬጅመንት የ11ኛ ዕዝ 204ኛ ኮር 35ኛ ክ/ጦር 2ኛ እና 3ኛ ሬጅመንቶች ሙሉ በሙሉ መደምሰስ ተችሏል።
◦ በዚህም ከ35 በላይ ወታደሮች ሲማረኩ 3 አሥር አለቆች እና 1 ሃምሳ አለቃን ጨምሮ፤ 2 ብሬን፣ 1 ስናይፐር፣ 65 ክላሽ፣ 6,570 የክላሽ እና 5,065 የብሬን ተተኳሾች፣ 20 የእጅ ቦንቦች ተማርከዋል።
• ጥቅምት 05/2019 ዓ.ም፦102ኛ ኮር እና 16ኛ ኮር በወገል ጤና ከተማ 4 ቀን ባደረጉት ከባድ ውጊያ ደላንታ ላይ ተቆርጣ የነበረችውን የጠላት 16ኛ ክፍለ ጦር አብዛኛውን አሃድ በመደምሰስ 1 ዙ-23 ጨምሮ ሜካናይዝድ መሳሪያዎችን ማውደም ተችሏል።
• ጥቅምት 08/2019 ዓ.ም፦15ኛ ኮር አጅባር ወረዳ ላይ ሬሽን ጭኖ ሲንቀሳቀስ በነበረ የጠላት ሰራዊት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በርካታ ኃይልን በመደምሰስ 3 ካሶኒ መኪናዎችን መማረክ ችሏል።
፫. ምዕራብ ግንባር፦ ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ መስከረም 30 - ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም የተሰሩ፦
• መስከረም 30/2019 ዓ.ም፦ አዲስ ቅዳም ከተማ ላይ ለአጭር ሰዓታት ከተማውን በመቆጣጠር የአድማ ብተና እና ፖሊስ አንድ ሻለቃ ሙሉ በሙሉ ደምስሷል። 113 ሙት፣ 25 ምርኮኛ፣ 26 ቁስለኛ ሲመዘገብ፤ 133 ክላሽ፣ 5 ብሬን፣ 28 የቃታ መሳሪያዎች፣ 2 መገናኛ ሬዲዮዎች እና በርካታ ተተኳሾች ተማርከዋል።
አስቸኳይ⚠️
አሁን ከምሽቱ 1:05 ላይ 3 ድሮኖች ከደብረ ዘይት ተነስተዋል!
👉ሸዋ ከፍተኛ ጥንቃቄ!!
“በሰይፍ ገጥሞ ሰልፍ የሚባል የለም“
ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር
ለደባይ ጥላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ!!!
እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ ለዘመናት እንደ ዜጋ ሳይቆጠር በየሔደበት ክብሩ ሲነካ ሲሳደድ እንዲሁም እየታደነና እየተመረጠ ሲገደል እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን እኛም አትግደሉን በሚል ከታች በሚታየው ህዝባዊ ማዕበል ከሊቅ እስከደቂቅ በነቂስ በመውጣት በሰላማዊ መንገድ እንደዜጋ መብታችንን ጠይቀናል።በወቅቱም ተረኛው የብልፅና ከፍተኛ አመራር ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ እንደ አማራ ድምፃችንን ከመስማት ይልቅ "ተዋቸው ያልቅሱ ሶፍት እናቀብላቸዋለን" በማለት ሲሳለቅብን እንደነበረ ይታወቃል።እኛም በሰላማዊ መንገድ በሰልፍ እንደማይሆን በመረዳት ፊታችንን እና ክንዳችንን ወደ ሰይፍ በማዞር ከሰፈር ወረዳ የብልፅግናን ስርዓት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ፍርስርሱን በማውጣት ታሪካችንን ለመፃፍ አሀዱ ብለን የጀመርነው የፋኖ ትግል ዛሬ ላይ ትልቅ ፍሬ በማፍራት አንድ ሐገራዊ ድርጅት መስርተን ይሔንን ጨካኝ አረመኔ የብልፅግና ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅለን ለመጣል ከመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል።
ይሁን እንጅ "የጨነቀው እርጉዝ ያገባል"ያኔ እኛ ተሰልፈን አትግደሉን ስንል ይሳለቅ የነበረው ብልፅግና ዛሬ በተራው በሰይፍ ገጥመን ሳለ እሱ በተቆጣጠራት አንድ ቀበሌ ተሰለፉልኝ በማለት እያለቀሰ ይገኛል።እኛም በተራችን ለብልፅግና ትርፍ አንጀቶችና ዳይፐሮች ሶፍት ሳይሆን የሚገባቸውን ጥይት እናቀብላቸዋለን እያልን
የተከበርከው የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማ ነዋሪዎች መውጣት ያለብህ ለብለፅግና ኮንደሞች ቀብር እንጅ እነሱ እንደሚሉት የአብራክህ ክፋይ እየሞቱልህ ላሉት ፋኖዎችን ለመቃወም እንደማትወጣ እየተማመን ይልቅ አሁን የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ በመሆኑ ለሰይፍ እንጅ ለሰልፍ ምንም አይነት ቦታ እንደሌለህ ባለመገኘት በተግባር እንደምታሳዬን ሙሉ እምነታችንን እየጣልንብህ።በተቃራኒው ለአረመኔው ስርዓት ባነር ይዘህ ብትወጣ የአረመኔው ገዳይ ብልፅግና ስርዓት ነጥለን እንደማናይህ ልናረጋግጥልህ እንወዳለን።ስለዚህ ማንኛውም ወጣት:የመንግስት ሰራተኛ:ነጋዴዎች ፡አሽከርካሪዎች እንዲሁም የከተማው ነዋሪዎች ብልፅግና ኑ ገዳይነቴን አረመኔያዊነቴን በሰልፍ ደግፉኝ ለሚለው ብሒል ገጥመህ የለ እዛ በሰይፍህ ተዋጣው በሚል እንድታሳፍሩልን ስንል በትህትና ለተከበረው ማህበረሰባችን እናሳውቃለን!!!!
"በሰይፍ ገጥሞ ሰልፍ የለም“ ቻለው
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ቴዎድሮስ 2ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ሰበር የድል ዜና!
የምኒልክ 1ኛ ዕዝ 13ኛ ኮር በሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ በብልፅግናው ስርዓት ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ አበይት ቦታዎችን ተቆጣጠረ!
የትብብር ለሕልውና አካል የሆነው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋብን) የምኒልክ 1ኛ ዕዝ 13ኛ ኮር በሰሜን ወሎ ቀጠና መቄት ወረዳ በብልፅግናው ስርዓት ሰራዊት ላይ ባካሄደው መብረቃዊ ጥቃት ከፍተኛ ድል ተጎናፀፈ።
በውጊያው የብልፅግናው ስርዓት ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ የተደመሰሰ ሲሆን፣ ደብረ ዘቢጥና አግሪት የተባሉ ስትራቴጂካዊ ስፍራዎች በፋኖዎች እጅ መግባታቸው ተረጋግጧል።
የምኒልክ 1ኛ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ በ13ኛ አሳምነው ኮር ስር የሚገኙት የቀድሞዋ 81ኛ የአሁኗ 137ኛ ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር እና 138ኛ ራስ አንችም ክፍለ ጦር በጥምረት በደብረ ዘቢጥና አግሪት ሰፍሮ በነበረው የብልፅግናው ስርዓት ሰራዊት ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።
ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 እስከ ምሽቱ 1:20 ሰዓት ድረስ በመቄት ወረዳ ሰንሰለታማ ተራሮችና ሜዳማ ቦታዎች ላይ ባካሄደው አውደ ውጊያ፦ ከ30 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት የተደመሰሱ ሲሆን፣ 9 የሰው ኃይል ተማርኳል፣ 14 ክላሽ፣ 2 የብሬን ሸንሽል፣ 1,500 የብሬን ተተኳሽ፣ 400 የክላሽ ተተኳሽ፣ 13 የወገብ ትጥቅ እና 10 ወታደራዊ ሻንጣዎች በፋኖዎች እጅ ገብተዋል።
የኮሩ ቃል አቀባይ አክለው እንደገለጹት፣ የተማረኩ የብልፅግናው ስርዓት መከላከያ አባላትን የአካባቢው እናቶች እህልና ውሃ ያቀረቡላቸው ሲሆን፣ የቆሰሉ ምርኮኞች ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ ተደርጎ ዓለም አቀፍ የምርኮኛ አያያዝ ህግን ባከበረ መልኩ ደህንነታቸው ተጠብቆ ይገኛል።
አሳዛኝ ዜና ❗❗❗
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በዘረ ፈጁ አገዛዝ ጭካኔ በተፈጸመ ጥቃት የንጹሐን ሕይወት ማለፉና ጉዳት መድረሱ ተረጋገጠ!!
ጥቅምት 11 / 2019 ዓ.ም
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ቡልጋ አውራጃ ፉራና ሲቻት በሚባሉ ቀበሌዎች ላይ አገዛዙ በከባድ መሳሪያዎች እና በድሮን በንፁሀን ላይ ጥቃት መፈፀሙን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሰምነው 5ኛ ከሠም ፪ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ።
ጥቃቱ የመኖሪያ መንደሮችን፣ የትምህርት ተቋማትን እንዲሁም አባወራዎችና እመወራዎች የእለት ተእለት የግብርና ሰብል የመሰብሰብ ተግባር ላይ በነበሩበት ወቅት ያነጣጠረ ነው። በጥቃቱም ድሮን፣ አጭር ሮኬት፣ BM፣ ጀነራል መድፍ፣ ሞርተር እና ዙ-23 የሚባሉ ከባድ መሳሪያዎችን በመጠቀም ዛሬም የአማራን ህዝብ ዘር ለማጥፋት በሸዋ የተለያዩ አካባቢዎች አገዛዙ ህዝብንና ተቋማትን ለማጥፋት ጥቅም ላይ አውሏቸዋል።
በበረኸት ወረዳ ፉራ ቀበሌና በሀገረማርያም ወረዳ ሥቻት ቀበሌ በተፈፀመው ጥቃት፦
➠ የ3 አመቷ ህፃን ሚጣ እንዳለን ጨምሮ
➠ የ4 ሰዎች ሕይወት በአሳዛኝ ሁኔታ ሲያልፍ፣
➠ 5 ንፁሐን ላይ ከባድ የአካል ጉዳት አድርሶ
➠ ከ10 በላይ የሚሆኑ ንፁሀን አረጋውያንና ሕፃናት ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተረጋግጧል።
ይህ ፀረ- ህዝብ የብልፅግና አገዛዝ በመሬት ላይ የፋኖን ክንድ መቋቋምና መመከት ሲያቅተው በእውር ድንብር በንፁሀን አርሶ አደሮች ፣በተቋማት ፣በሰብልና በእንስሳት ላይ መጠቀሙ በአማራ ህዝብ ላይ የበቀል እርምጃው ማሳያው ነው።
" ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
#አስቸኳይ_የጥንቃቄ_መልዕክት‼️
ከቀኑ 6:30 አካባቢ መነሻቸው ከደብረዘይት አየር ኃይል ግቢ ያደረጉ 3 ወይንም 4 #የጦር_ጀቶች ወደ ሁሉም የዐማራ ቀጠናዎች ተንቀሳቅሰዋል።እናም በሁሉም አቅጣጫ ያላችሁ የዐማራ ፋኖ የነፃነት ታጋይ ወንድሞቻችን እንቅስቃሴያችሁ በጥንቃቄ ይሁን።‼️
በራያ ቆቦ ከተማ የወረዳ ካድሬዎች እና የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦች ቀኝ እጅ ነው የተባለ አንድ ግለሰብ በፖሊስ አባል መገደሉን ተከትሎ በከተማዋ ውጥረት መንገሱ ታወቀ!
የፖሊስ አባሉ፡ የካድሬና የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦች ተላላኪ ነው ባለው ግለሰብ ላይ ዛሬ ረፋድ በከተማዋ አደባባይ አከባቢ ግድያውን ከፈፀመ በኋላ ወደ አንድ ንግድ ቤት የገባ ቢሆንም፡ በአሁን ሰዓት የወረዳው ታጣቂዎች ቤቱን ከበው ከፖሊስ አባሉ ጋር የተኩስ ልውውጥ እያካሄዱ እንደሚገኙ የአይን እማኞች ገልፀዋል።
በተኩስ ልውውጡ በጉልበት ስራ የሚተዳደር አንድ ሲቪል ወጣት ሲገደል ሌሎች በስራ ላይ የነበሩ ንፁኋኖች መቁሰላቸው ተሰምቷል።
🔥#አስቸኳይ_የጥንቃቄ_መልዕክት‼️
ከቀኑ 6:30 አካባቢ መነሻቸው ከደብረዘይት አየር ኃይል ግቢ ያደረጉ 3 ወይንም 4 #የጦር_ጀቶች ወደ አማራ ቀጠና ተንቀሳቅሰዋል ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች ገልፀዋል ስለሆነም አናብስቱ የአማራ ፋኖና ሁሉም የነፃነት ታጋይ በጥንቃቄ ይንቀሳቀስ‼️
መረጃው ለወገን ኃይል በአስቸኳይ ይዳረስ‼️
ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም
ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ጥልቅ ግምገማውን በስኬት አጠናቀቀ!
ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም
የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር አካል የሆነው ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር፣ የነበሩበትን ክፍተቶች በማስተካከል ይበልጥ ጥንክሮ ለመቀጠል ያስችለው ዘንድ የዕዝ፣ የክፍለ ጦር፣ የኮር እና የብርጌድ አመራሮች በተገኙበት ለሶስት ቀናት ሲያካሂደው የቆየውን ጥልቅ ውይይትና ግምገማ በስኬት አጠናቋል።
በዚሁ መድረክ የክፍለ ጦሩ አመራሮች በትግል ሂደቱ ላይ ያሳዩት ቁርጠኝነት፣ ጽናትና ተጋድሎ በታላቅ ጥንካሬ ተነስተዋል። በተጨማሪም ክፍለ ጦሩ አሁን ላይ ያለበትን ቁመና እና በስራ አፈጻጸም ላይ የተስተዋሉ ችግሮች መታረም በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ያለፉ የአመራር ስልቶችን ይበልጥ ለማስተካከል ያለመ የሂስና ግለ-ሂስ መድረኮች ተፈጥረው፤ ካለፉ ስልቶች የመማር እና የወደፊት ግልጽ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ክፍለ ጦሩ ይበልጥ ጠንክሮ እንዲወጣ ማድረግ ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።
በመጨረሻም የክፍለ ጦሩ አመራሮች ላለፉት ጊዜያት የተነሱባቸውን ድክመቶችና ትችቶች እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ፤ በነፍስ፣ በደም እና በአጥንት የተገነባውን የአማራ ህዝብ ትግል ማስቀጠልና የትግሉ አልፋና ኦሜጋ አንድነት መሆኑን በመገንዘብ ቃል የገቡ ሲሆን ክፍለ ጦሩን ለቀጣይ ግዳጅ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ የማድረግ ስራም መጠናቀቁን አስገንዝበዋል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
