ru
Feedback
ቶጳዝዮን

ቶጳዝዮን

Открыть в Telegram

"ቶጳዝዮን"ማለት ቢጫ የከበረ ድንጋይ ፣ዕንቍ ማለት ነው። በተስፋ የተቃኘዉን ሀሳባችንን እና ስሜቶቻችንን በዕንቊ ቃላቶች እያዋዛን በብዕራችን የምንገልፅበት ምርጥ ቻናል ነው። ለማንኛውም አስተያየት👇👇 @Ediwub @Tirrubel

Больше
3 611
Подписчики
+724 часа
+277 дней
+3630 дней
Архив постов
ቀስ በቀስ እንደ ሳቅ ፈገግታ እንደ ጧት ወገግታ ቀስ በቀስ እንደ ሕይወት ዳና እንደ ትላንትና ቀስ በቀስ እንደ ራስ ቅል ጠጉር እንደ ቆዳ ብጉር ቀስ በቀስ ተንሸራትቶ መምጣት ሀገር ወደ ማጣት ። ____ ©️ ሄኖክ በቀለ @topazionnn @topazionnn

....... እነሱ፡ ምድርን ቢሸፍኑ በኒውክለር ሚሳኤል፣ ለእኛ፡ በክንፉ ሚከልል አለልን ሚካኤል፤ እነሱ፡ በጊዜ ቢመኩ ቢይዙ ምንሽር፣ ለእኛ፡ ማርያም ከጎን አለች ጉልበትን የምትሽር፤ እነሱ፡ ምስኪንን ለማራድ ቢያነግቱ መውዜር፣ ለእኛ፡ አልፋና ኦሜጋ አለልን አንድ እግዜር፤ እምነት አለን እኛ ከአለት የበረታ ጎልያድን ሞገድ በጠጠር ምንረታ በምድራዊ ፍቃድ ሀሰት ብታይልም እመኑኝ 'ላመኑት' አምላክ ዝም አይልም! @Weyblann ያቡ✍

በህመሙ ብዛት በመከራው ብዛት በሀዘኑ ብዛት እያለ በቁሙ ዕድሜ እንዳያጥረው                       : የሰውን ልጅ እግዜር "ከመርሳት" ፈጠረው ! (ኤልያስ ሽታኹን) @topazionnn @topazionnn

#ፀፀት_ያንባት የ 2019 የመጀመሪያ ግጥሜ ነው ✨ ልብ የፃፈው ግጥም ነው.... . Inspired By True Story የተኖረ ፣ እየተኖረ ያለ ፣ የሚኖር . ስለ ፆታዊ ፍቅር አይደለም . [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel

(የታመመ እንጠይቅ..) ============== እውነትና ንጋት እንዲህ ከልብ ሲርቅ አምርሮ ጠያቂን መ..ምህሩ ሲያ'ንቅ የሰውነት አፍላግ ከምንጩ ሲደ'ርቅ ማን በጤናው ሊገኝ ኑ ቢያመንም እንኳ...የታመመ እንጠይቅ  ! By #kiyorna @topazionnn @topazionnn

በር እና ስንቀር -------------------------------- የፍላጎት ቤቱ፤ የምኞት ማደሪያው እያደር ሲለጠጥ' ግድግዳና ጣሪያው ኗሪው ገላው ሰፋ፤ ጎጆውም ገዘፈ ለበር የታሰበው፤ ሽንቁር ኾኖ ዐረፈ። By bewuketu siyum @topazionnn @topazionnn

አዲስ አመት . . ያ...ጠቢብ ሰለሞን.......... ያማረ ቀለበት ከእጅሽ ያጠለቀዉ፤ ምን ያክል ዉበትሽ ልቡን ቢገዛዉ ነው? ከአደይቷ ይልቅ ደምቀሽ ብትታይዉ፤ ሽንፈት የማያዉቀዉ ፍቅርሽ አሸነፈው። ትዋቢበት ዘንዳ ዉብ እንቁን ለጣትሽ፤ ችግር ሲያገኝሽ ማለፊያ ለጣጣሽ፤ አንድም ለልብሽ ነዉ ማሰሪያ ለቃልሽ፤ ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ። የካም እድል ፈንታ እንቁ ዕጣ ለወጣች፤ ጸሎቷን ለማድረስ እጇን ለዘረጋች፤ ህመምሽ ለሆነች ፈዋሽሽም እሷዉ፤ ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ ነው። ዛሬም ለሀገሬ........ መከራ እንደ ሀምሌ ፀንቶ ላጨገጋት፤ ዉሽንፍር መባርቅት አብሮ ለሚንጣት፤ ቀለበትሽን አዉሻትና........ መከራዋ ያብቃ ነጭ ልብስ ትልበስ፤ ተስፋዋ ይለምልም በፍቅር ትታደስ፤ እንባዋ ታብሶ ብርሃን ይታያት፤ በዚ በአዲስ አመት ደግ ቀን ይዉጣላት። 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 ✍✍ዔደን @ediwub @topazionnn @topazionnn

አዲሱን አመት ለመቀበል ሰዓታት ይቀሩናል ....በመጪዉ 2019 ምን ትመኛላችሁ??

​​➛➛እመ መከራ➛➛ ኢትዮጵያ እመ መከራ የግዜር መመራመሪያው የስቃይ ቤተ-ሙከራ መውደቅማ ነበር ያባት እንደ ያሬድ እስከ ሰባት እንደ በላ ብላቴና የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ የትውልዴ እጣ ፈንታ መውደቅ፣መውደቅ፣መውደቅ ብቻ! ✍ገጣሚ ፦ በእውቀቱ ስዩም @topazionnn @topazionnn

ጳጉሜ  3..❤️‍🔥 ያኔ ልጅ እያለው  በቀን ጳጉሜ 3     ልጆች ሲጠመቁ ሩፋኤል አሳድገን    እያሉ በደስታ       ልብስ እያወለቁ፤ ይቦርቁ ነበር የሰፈር ህፃናት እርቃናቸው ሆነው ያለምንም ፍርሀት! ( እኔ ግን😒) እኔ ግን በሩቁ    እመለከት ነበር      እምባ እያፈሰስኩኝ፣ እናትና አባቴ   ማስቆረጫ አጥተው      ስ  ላ  ል  ተ  ገ  ረ  ዝ  ኩ  ኝ💔! @Weyblann✍ያቡ ለፈታሄ ማህፀን ለመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሳቹ🙏❤️ @topazionnn

እጠበው አንፃው ጉድፌን መልሰው ልጅነት መልኬን ፧ በኃጢያት ያልጎሰቆለው... ያ የምታውቀው መልክ፣ ዛሬ ሌላ ቢመስልም ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ... መልኬን እስካገኝ ድረስ፣ጠበልክን አልጠለለልም። / ልጅ
እጠበው አንፃው ጉድፌን መልሰው ልጅነት መልኬን ፧ በኃጢያት ያልጎሰቆለው... ያ የምታውቀው መልክ፣ ዛሬ ሌላ ቢመስልም ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ... መልኬን እስካገኝ ድረስ፣ጠበልክን አልጠለለልም።                     / ልጅ ወርቅነህ...✍✍/ @topazionnn @semetnbegtm @semetnbegtm

_ ኢትዮጵያ ሀገሬ ፣ ቅዠትና ህልሜ የጠላቶጅሽእጅ ፣ ይጠሩ እንደ 'ጳጉሜ'! በላይ በቀለ ወያ✍️ አስፋሪ ያቡ🙌

..........ዛሬ ጷግሜ አንድ ነዉ።ወቅቱ የአዲስ አመት መግቢያ እንደመሆኑ....... ሰዉ በለሊት ተነስቶ የጷግሜን ጠበል ከተጠበለ በኋላ አዲስ ተስፋን ሰንቆ በየፊናዉ በዓሉን ተደስቶ ለማክበር ይሯሯጣል። ገሚሱ ሰንጋተራ፤ ገሚሱ በግተራ የተቀረዉ ሰዉ ደግሞ ሾላ ገበያ ከትሟል። ታዲያ በእኛ ጊቢ ከግንቦት ልደታ ባልተናነሰ መልኩ ጷግሜ አንድ በደመቀ መልኩ ይከበራል። በተለምዶ አሮጌ ልደታ ተብሎ ይጠራል።ጎረቤት አንድ ላይ ተሰብስቦ በረንዳ ላይ ቡና ይፈላል።አናባበሮዉ እና ንፍሮዉ ይቀርባል። ጋሽ ተስፋዬ የሰባ አመት የእድሜ ባለፀጋ ናቸዉ።ባለቤታቸዉ ወይዘሮ ሸዋዬ የአንገታቸዉ ንቅሳት ከሩቅ የሚታይ ዉበታቸዉ የማይደበዝዝ ድርብብ ያሉ እመቤት ናቸዉ።  ቡናዉ ካከተመ በኋላ ጋሽ ተስፋዬ የያዙትን ስኒ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠዉ ከመቀመጫቸዉ ተነስተዉ ጋቢያቸዉን አስተካክለዉ ሊመርቁን ቆሙ። ሁላችንም እጃችንን አሜን ለማለት አመቻችተን ቆም ቆም አልን። "የጎመን ምንቸት ይዉጣ።የገንፎ ምንቸት ይግባ።" "አሜን..........." "ሀገራችንን ዳሯን እሳት መሐሏን ገነት ያድርግልን።በዳር ድንበር በጦርነት  ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉትን ወደቤታቸዉ ያግባልን።ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።" "አሜን............." ለዛሬ መድረስ ያልቻሉትን፣በሞት ከእኛ የተለዩትን፤ ወዳጅ ዘመዶቻችንን  ነፍሳቸዉን ይማርልን። "አሜን............." ገበሬዉም ያረሰዉን የሚሰበስብበት የድካሙን ፍሬ የሚበላበት ያርግልን። "አሜን.........." ያላጨ የሚያጭበት፤ ያገባም የሚወልድበት፤ የወለደም የልጆቹን ወግ ማዕረግ የሚያይበት ዓመት ያድርግልን።" ለአዲሱ ዓመት በሰላም እንዳሁኑ ከቁጥሩ ሳያጎድል ያድርሰን።አይለየን!" "አሜን "በሉ ወዳጆቼ እኔ ባጎደልኩ እርሱ ይሙላበት።"ብለዉ ከወንበራቸው ላይ ተቀመጡ። ከአሜን ይቀራልና አሜን በሉ........... በዔደን ታደሰ @ediwub @topazionnn

መቃብር ምሰው አፈር አልብሰው ደረት ደልቀው ፍም ዕንባ አፍስሰው ደህና ሁን ብለው የመጡትን ሰው፤ ድንገት በር ላይ ጥላውን ቢያዩት - ድምፁን ቢሰሙት ፤ ምንድን ነው ሚሉት!? ጨርቁን አጣጥፈው ስንቁን አጥቅሰው አንገቱን አቅፈው ደረቱን ዳብሰው ከእንግዲህስ ቻው ያሉትን ፍቅር - ከልብ ቆርጠው የሸኙትን ሰው፤ ድንገት አልጋ ላይ ጋደም ብሎ ፤ እጅ እግሩን ሰቅሎ -  ሀሳቡን ጥሎ ሲስቅ ቢያገኙት፤ ምንድን ነው ሚሉት!? ይኸው እንግዲህ ዳግም ብቅ አለ ብቸኝነቴ፤ ቻው ተባብለን ከአንዴም ሁለቴ፤ ለካስ እንደ ልጅ አዲስ እንግዳ ከቤት ሲመጣ 'ጓዳ ሩጦ እንደሚገባው፤ እንግዳው ሂዶ እስከሚወጣ እያጮለቀ እንደሚያደባው፤ ይህ ብቸኝነት አይሄድም ጥሎ፤ ያደፍጣል እንጅ የሞተ መስሎ፤ By Tewodros kasa @topazionnn @topazionnn

ሰላም እንዴት ናቹ ✨ በመጀመሪያ ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን🙏 እናም ውድ ቤተሰቦች የራሴን ትንሽዬ የ T-Shirt Brand ጀምሪያለሁ " ሙሉወርቅ | Muluwerk Designs "😊 . እና
+4
ሰላም እንዴት ናቹ ✨ በመጀመሪያ ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን🙏 እናም ውድ ቤተሰቦች የራሴን ትንሽዬ የ T-Shirt Brand ጀምሪያለሁ " ሙሉወርቅ | Muluwerk Designs "😊 . እና Channel ከፍቻለሁ ገባ ገባ እያላቹ ቤቴን መርቁ ORDER ማድረግ የምትፈልጉም ORDER አድርጉ ምትፈልጉት ሁሉ አለን CUSTOM ORDERም እንቀበላለን ✨ . ቤቴን መርቁ ጅማሬዬንም ፍፃሜንም አምላክ ይባርክ🙏 THIS IS THE CHANNEL : @muluwerkdesigns

ማዘን ሲገባኝ ፥ ስትጠፊ ካይኔ መጻፍ ሲገባኝ ፥ ሙሾ ወይ ቅኔ (እንጃልኝ እኔ ...) የጤና አይመስልም ፥ ደህና መሆኔ ። ትዝ አትዪኝም ወይ ለትንሽ ደቂቃ ? አትናፍቂኝም ወይ ሳዳምጥ ሙዚቃ ? ረሳሁሽ በቃ ? እንጃልኝ እንጃልኝ ናፍቆትሽ በኋላ ምን እንዳሰበልኝ ። ሰው ባይገባው እንጂ አዕምሮው ደንዘዞ እንዴት 'እፎይ' ይላል  ስንት ኮተት ይዞ ? እባክሽ አታዘግዪብኝ ፥ ስቃዬን ዛሬ ልወጣው አንቺስ ሄደሻል እሺ ናፍቆትሽ መች ነው ሚመጣው ? By Hab HD @topazionnn @topazionnn

. . .ናቅን መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን . . . ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን

Check Out👇👇👇 https://vt.tiktok.com/ZSVWFjECK/