uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

ቶጳዝዮን

ቶጳዝዮን

Kanalga Telegram’da o‘tish

"ቶጳዝዮን"ማለት ቢጫ የከበረ ድንጋይ ፣ዕንቍ ማለት ነው። በተስፋ የተቃኘዉን ሀሳባችንን እና ስሜቶቻችንን በዕንቊ ቃላቶች እያዋዛን በብዕራችን የምንገልፅበት ምርጥ ቻናል ነው። ለማንኛውም አስተያየት👇👇 @Ediwub @Tirrubel

Ko'proq ko'rsatish
3 642
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+87 kun
+3930 kun
Postlar arxiv
የዛሬው ምስል ይሄ ነው እስኪ በግጥም ዘይሩት😁 @topazionnn @tirrubel
የዛሬው ምስል ይሄ ነው እስኪ በግጥም ዘይሩት😁 @topazionnn @tirrubel

ከቀብሬ በላይ ሰርጌን እፈራለሁ ለሚቀብረኝማ ባዳ መች አጣለሁ! ምክንያት የሚፈልግ ለማልቀስ መች ጠፍቶ መቼስ በሳቅ አይሸኝ ሰው ከስጋው ሞቶ! . ቀብሬስ ዓለም ነው ይፈፀምልኛል የቃሌ ኑዛዜ ያገቡለት
ከቀብሬ በላይ ሰርጌን እፈራለሁ ለሚቀብረኝማ ባዳ መች አጣለሁ! ምክንያት የሚፈልግ ለማልቀስ መች ጠፍቶ መቼስ በሳቅ አይሸኝ ሰው ከስጋው ሞቶ! . ቀብሬስ ዓለም ነው ይፈፀምልኛል የቃሌ ኑዛዜ ያገቡለት ግና ወዳጅ ያሉት አይደል የሚሆነው ሚዜ ! ሚዜ ከየት ላመጣ? [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel

ከቀብሬ በላይ ሰርጌን እፈራለሁ ለሚቀብረኝማ ባዳ መች አጣለሁ! ምክንያት የሚፈልግ ለማልቀስ መች ጠፍቶ መቼስ በሳቅ አይሸኝ ሰው ከስጋው ሞቶ! . ቀብሬስ ዓለም ነው ይፈፀምልኛል የውስጤ ኑዛዜ ያገቡለ
ከቀብሬ በላይ ሰርጌን እፈራለሁ ለሚቀብረኝማ ባዳ መች አጣለሁ! ምክንያት የሚፈልግ ለማልቀስ መች ጠፍቶ መቼስ በሳቅ አይሸኝ ሰው ከስጋው ሞቶ! . ቀብሬስ ዓለም ነው ይፈፀምልኛል የውስጤ ኑዛዜ ያገቡለት ግና ወዳጅ ያሉት አይደል የሚሆነው ሚዜ ! ሚዜ ከየት ላመጣ? [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel

ከ'ሳተ ገሞራ እንደማር ወለላ በጣት ዝቆ ማውጣት አውጥቶ ጣት መጥባት፣ መላስ ሲንጠባጠብ በዲን ምላስ ማርጠብ ቀላጭ ፍሙን ማኘክ ማኘክና ማድቀቅ ማድቀቅና ማላም እንደዚያች ወላድ ላም ላስ አርጎ እሳቱን ቻል አርጎ ፍጅቱን መዋጥ በዝምታ እንዲያ ነው ይቅርታ። በእግሮቻችን ዳና ባተምነው ጎዳና ስንጓዝ የቀና እንቅፋት ሲቀስፈን ጥጉን ተደግፈን ቁስላችንን ማፈን፤ እግራችን ምስኪኑን ዝምታ ክኒኑን ዋጥ አርጎ የግዱን ተወግቶ እንዳይደማ አቁሳዩ ሳይሰማ ግሽልጡን ደምድሞ ቁስል ላይ ጠምጥሞ ካህን መሆን መፍታት ጸሎት ለእንቅፋት ማድረስ በዝምታ፣ እንዲያ እንጂ... መች ዋዛ? መች ቀላል ይቅርታ? ይቅርታ መች ቀላል? ለሰጪ ይከብዳል ለሰጭ ካልከበደ፡ ተቀባይ ያለምዳል ለማዳ ተቀባይ ፡ ከርሞ ያቃልላል ከርሞ የቀለለ፡ ይነሳል ይወድቃል ከዚያ በኋላማ ፡ምኑ ይጠየቃል? እንቅፋት ይረክሳል፡ እግር ይደነዝዛል የተጠመጠመው፡ ቁስል ያመረቅዛል ድንጋይ የበዛበት፡ ድንጋይ ልብ ያፈራል ከዛ በኋላማ ፡ ምኑ ይነገራል? ማን ማንን ይፈራል? ማን ለማን ይራራል? ጠጠር ያናቀፈው፡ ዓለት ሆኖ ያድራል። ወድቀው ሳይነሱ ሳይዘሩ ሳያርሱ እንደ ኦሪት መና ይቅር ከደመና አይውረድ ከሰማይ፤ ሲያቀሉት ይከብዳል ይቅርታና ሲሳይ። የሬት የኮሶና የግራዋ ድቃይ ሲቀምሱት በስቃይ «ሁለተኛ!» ብለው እንደምጥ ላይደግሙት በወለዱት ምለው ፍም እሳት ተረግጠው በጥፍር አፈሩን፡ሳር ቅጠሉን ቧጥጠው ከፍሙ ማር ቆርጠው ጎመራ እሳት ውጠው አምጠው አምጠው ማቅቀው ተንሰቅስቀው፡ በጊዜ ይሁንታ እስኪነሱ ድረስ፡ መሞት ነው ይቅርታ። (Red-8) ይቅርታ መች ቀላል? @topazionnn

እኛ አፍቃሪዎች ነን እንደልባችን እንፃፍ ባላቹት መሰረት ይኸው በዚህ ሂዱበት😂 ግን ምመክራቹ ነገር ወጣ ያለው ምልከታ ነው የሚያሳድጋቹ...So be creative! @topazionnn @topazio
እኛ አፍቃሪዎች ነን እንደልባችን እንፃፍ ባላቹት መሰረት ይኸው በዚህ ሂዱበት😂 ግን ምመክራቹ ነገር ወጣ ያለው ምልከታ ነው የሚያሳድጋቹ...So be creative! @topazionnn @topazionnn @tirrubel

የዛሬው Challenge ይሄን ምስል ወደ ግጥም መቀየር ነው። በፍቅር Angle Express ማድረግ አይቻልም....አዲስ ምልከታ አዲስ ሀሳብ ፣ አዲስ ግጥም። እስኪ ዛሬ ዐቅማቹ ይታያል Apple ፍራ
የዛሬው Challenge ይሄን ምስል ወደ ግጥም መቀየር ነው። በፍቅር Angle Express ማድረግ አይቻልም....አዲስ ምልከታ አዲስ ሀሳብ ፣ አዲስ ግጥም። እስኪ ዛሬ ዐቅማቹ ይታያል Apple ፍራፍሬ ነው ብሎ ሚፅፍ ብዙ አለ ፣ ግን ስለ ፍራፍሬነቱ ፍራፍሬ መሆኑን ሳይገልፅ የሚገልፐው ውስን ነው።  ሀሳቤ ግልፅ ነው....አሪፍ ምልከታ ለፃፈ ሰው የ 1000 ብር ቀልድ በ Inbox እልክለታለሁ ! መልካም ዕድል @topazionnn @topazionnn @tirrubel

የዛሬው Challenge ይሄን ምስል ወደ ግጥም መቀየር ነው። በፍቅር Angle Express ማድረግ አይቻልም....አዲስ ምልከታ አዲስ ሀሳብ ፣ አዲስ ግጥም። እስኪ ዛሬ ዐቅማቹ ይታያል Apple ፍራ
የዛሬው Challenge ይሄን ምስል ወደ ግጥም መቀየር ነው። በፍቅር Angle Express ማድረግ አይቻልም....አዲስ ምልከታ አዲስ ሀሳብ ፣ አዲስ ግጥም። እስኪ ዛሬ ዐቅማቹ ይታያል Apple ፍራፍሬ ነው ብሎ ሚፅፍ ብዙ አለ ፣ ግን ስለ ፍራፍሬነቱ ፍራፍሬ መሆኑን ሚገልፅ ውስን ነው። ሀሳቤ ግልፅ ነው....አሪፍ ምልከታ ለፃፈ ሰው የ 1000 ብር ቀልድ በ Inbox እልክለታለሁ ! መልካም ዕድል @topazionnn @topazionnn @tirrubel

(ግጥም እግዜር ይስጠው) አልያስ ሽታኹን ልክ መሆን -  ደክሞኝ ጤና መሆን -  አሞኝ ጨርቄን መጣል ባፍር ለክብር ለስሜ                       : በጥበብ በውበት ቀስ ብዬ አበድኩ  ዕድሜ ለግጥሜ ። አልፎ አልፎ ቀወስ ክብሬን ማፈራረስ መናድ ልምምዴን መቀየር መንገዴን ረስቼ Ego ግብሬን ሳልጠብቅ መስመሬን የህይወት ብቅሸት መስደብ ሲከጅለኝ                      : ( ወፈፍ ነው በቃ ) ግጥም እግዜር ይስጠው የማይታዘበኝ። @topazionnn @topazionnn

ተወርዋሪ ኮከብ፤ በድቅድቅ ጨለማ፤ በጠቆረው ሰማይ፤ የብርሃን ሰበዝ በማይታይበት፤ ሰው ሰው እየፈራ፤ የሰው ዳና ፈርቶ በተጠየፈበት፤ ይኸ ጦቢያ ሁላ፤ ሰውነት ርቆት፤ በጨለማው መሃል፤ ድንብርብሩ ወጥቶ፤ ግማሹ በቆንጥር፤ግማሽ በሸለቆ፤ ጉልበቱ ሲረታ፤ ጠኔ እየረሸነው፤ በየጢሻው ወድቆ፤ ተወርዋሪ ኮከብ ፤ ከውብ ፈገግታው ጋር፤ ጨለማውን ናደው፤ ሸለቆውን ሞላው፤ ከሰማይ ፈንጥቆ።       ((((  ጃ ኖ )) @topazionnn @topazionnn

ሰላም ሰላም family🤗🤗 በዚህ ምስል ላይ በግጥም ሀሳባችሁን ጣል ጣል አድርጉበት።
ሰላም ሰላም family🤗🤗 በዚህ ምስል ላይ በግጥም ሀሳባችሁን ጣል ጣል አድርጉበት።

መንገዱ ነው እንጂ (ኤልያስ ሽታኹን)

. . . የደጄ ፈረስ ፥ ሀሙስ ሚመጣው ጊዜ እንደሚቀር ፥ ከወደ ኋላው ልክ እንደጭራው የክረምት ወዳጅ ፥ በጋ እንደሚያብል ባረጀ ሰሞን ፥ ወጥቶ እንደሚጣል ያወቀ አይመስለም ፥ ቀን አኳኋኑ በሌት ዘፈኑ ያሳዝነኛል ፥ እኔ ከአሁኑ ©ሲራክ ወንድሙ @topazionnn

....... 'ሀ'..ሴት ሆነሽ ለኔ እስከ 'ፐ' ማስብሽ፣ ድንገት ግን 'በ'...መሀል ገድፎ ታየ ልብሽ! @Weyblann ✍️ያቡ
....... 'ሀ'..ሴት ሆነሽ ለኔ እስከ 'ፐ' ማስብሽ፣ ድንገት ግን 'በ'...መሀል ገድፎ ታየ ልብሽ! @Weyblann ✍️ያቡ

#ለሰዎች_ሁለተኛ_ዕድል_በመስጠት_ታምናላቹ? አብሮአደግ bestfriend ነበረኝ እና እኔን ሚያግዘኝ አንድ ሰው ወደ ህይወቴ ድንገት ይመጣልና ከዛ ሰው በእኔ ስም ገንዘብ Advantage ለመያዝ እንደሞከረ በስካር መንፈስ ደውሎ ነገረኝ እና በሱ በኩል ያወኩት ወዳጅ ያረኩት ሰው ነበርና ጉዳዩን ለጋራ እንዳደረጉትና ያ ሰው በእኔ እንደሚቀና ነገረኝ። ሁለቱንም ከህይወቴ አሶጣዋቸው። ግን አሁን አብሮአደጌ ያልኩት ሰው ናፈቀኝ ምን ላድርግ ? ተብዬ በInbox ተጠይቄ ነውና ሀሳባቹን አውሱኝ.....አፍጥኑት😁 @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel

photo content

photo content

በፊት የምታውቁት አካውንቴን ድሬዋለሁ ድል ባለ ሰርግ😁 እና የት ጠፋ ብላቹ ግራ እንዳትጋቡ Viral ስራዎቼ በሙሉ Tiktok ላይ የሉም። እንኑር እንጂ ሁሉም ይስተካከላል ✌️ ላሳውቃቹ ብዬ ነው.
በፊት የምታውቁት አካውንቴን ድሬዋለሁ ድል ባለ ሰርግ😁 እና የት ጠፋ ብላቹ ግራ እንዳትጋቡ Viral ስራዎቼ በሙሉ Tiktok ላይ የሉም። እንኑር እንጂ ሁሉም ይስተካከላል ✌️ ላሳውቃቹ ብዬ ነው.....በቅርቡ በአዲስ መልክ እመጣለሁ....Follow ያረጋቹኝ በሙሉ አመሰግናለሁ 🙏 [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @tirrubel

ዔዱዬ እንኳን ተወለድሽ 🎂🎂🎂 ማርያም ማርያም ጎረቤቱ ጠራ አምርሮ ፈጥና እንድደርስ አዛኝቱ በውልደቷ እለተ ቀን መታሰቢያ ተወልጀሻል ለእናት አባት አይን ማያ የምትወጃት ቡትወድሽ የዝክሯን ቀን ሸለመችሽ በቀሪ እድሜሽ በሚመጣው ትጠብቅሽ ከክፉ ነገር የኔ አሳቢ የኔ ጨዋ ❤ነፍፍፍፍ አመት ኑሪል ስኬትሽን ያሳየኝ🙏 አርፍጃለሁ የልቤ ይቅርበይኝ😔🙏እወድሻለሁ❤😘 @topazionn @eluuu2112

#መልካም_ልደት_እሜቴ_ኤደን😁 በጥቅምት ጅማሬ በፀደይ አበባ ኤደን ተወለደች ብዕሯን አንግባ 😁 እሰይ እልል አሉ ገጣሚ ታቀፉ ለጋ መዳፎቿ ሙሉ መፅሀፍ ፃፉ ገና በልጅነት ጥበብ የጠራቻት ሰንበት ት
#መልካም_ልደት_እሜቴ_ኤደን😁 በጥቅምት ጅማሬ በፀደይ አበባ ኤደን ተወለደች ብዕሯን አንግባ 😁 እሰይ እልል አሉ ገጣሚ ታቀፉ ለጋ መዳፎቿ ሙሉ መፅሀፍ ፃፉ ገና በልጅነት ጥበብ የጠራቻት ሰንበት ትምህርት ቤት ወስዳ ያሳደገቻት ገጣሚ ዘማሪ መካሪ እህታችን ባለሽበት ይድረስ መልካም ምኞታችን Happy በርዝ Day 😁✌️ Don't mind the picture 😭😁😁😁 እመብርሃን የልብሽ መሻት ከኃጥያት በስተቀር ትቀበልሽ ✨ [ ጥሩቤል ] @ediwub @topazionnn @tirrubel

#መልካም_ልደት_እሜቴ_ኤደን😁 በጥቅምት መባቻ በፀደይ አበባ ኤደን ተወለደች ብዕሯን አንግባ 😁 እሰይ እልል አሉ ገጣሚ ታቀፉ ለጋ መዳፎቿ ሙሉ መፅሀፍ ፃፉ ገና በልጅነት ጥበብ የጠራቻት ሰንበት ትምህርት ቤት ወስዳ ያሳደገቻት ገጣሚ ዘማሪ መካሪ እህታችን ባለሽበት ይድረስ መልካም ምኞታችን Happy በርዝ Day 😁✌️ እመብርሃን የልብሽ መሻት ከኃጥያት በስተቀር ትቀበልሽ ✨ [ ጥሩቤል ] @ediwub @topazionnn @tirrubel

ቶጳዝዮን - Telegram kanali @topazionnn statistikasi va tahlili