አለ ሕግ
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት Alternative legal enlightenment & Service Website: alehig.com https://linktr.ee/alehig WhatsApp👉 #+251920666595 Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Больше📈 Аналитический обзор Telegram-канала አለ ሕግ
Канал አለ ሕግ (@alehig) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 16 236 подписчиков, занимая 490 место в категории Закон и право и 2 125 место в регионе Эфиопия.
📊 Показатели аудитории и динамика
С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 16 236 подписчиков.
Согласно последним данным от 27 сентября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 130, а за последние 24 часа — 0, при этом общий охват остаётся высоким.
- Статус верификации: Не верифицирован
- Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 29.20%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 9.23% реакций от общего числа подписчиков.
- Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 4 740 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 499 просмотров.
- Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 9.
📝 Описание и контентная политика
Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ”
Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 28 сентября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Закон и право.
Загрузка данных...
| Дата | Привлечение подписчиков | Упоминания | Каналы | |
| 28 сентября | +4 | |||
| 27 сентября | 0 | |||
| 26 сентября | +7 | |||
| 25 сентября | +4 | |||
| 24 сентября | +6 | |||
| 23 сентября | +8 | |||
| 22 сентября | 0 | |||
| 21 сентября | +4 | |||
| 20 сентября | 0 | |||
| 19 сентября | 0 | |||
| 18 сентября | +7 | |||
| 17 сентября | +7 | |||
| 16 сентября | 0 | |||
| 15 сентября | +2 | |||
| 14 сентября | +2 | |||
| 13 сентября | 0 | |||
| 12 сентября | +5 | |||
| 11 сентября | 0 | |||
| 10 сентября | +2 | |||
| 09 сентября | +11 | |||
| 08 сентября | +2 | |||
| 07 сентября | +2 | |||
| 06 сентября | +8 | |||
| 05 сентября | +3 | |||
| 04 сентября | +15 | |||
| 03 сентября | +17 | |||
| 02 сентября | +11 | |||
| 01 сентября | +15 |
| 2 | ©Ethiopian Ministry Of Trade (FB) | 1 419 |
| 3 | የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያን ይፋ አደረገ።
የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ በሚያስተምሩ መምህራን ላይ ተፈጻሚ የሚሆን "የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1148/2018" አውጥቷል።
ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ያዘጋጀው ይህ መመሪያ፣ በማስተማር ሥራቸው የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ መምህራንን ለማበረታታት፣ የሥራ ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በመመሪያው ድንጋጌ መሠረት የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የእድገት መሰላል በሰባት ደረጃዎች የተከፋፈለ ሲሆን፤ እነሱም ፦
- ጀማሪ መምህር፣
- መለስተኛ መምህር፣
- መምህር፣
- ከፍተኛ መምህር፣
- ተባባሪ መሪ መምህር፣
- መሪ መምህር እና ከፍተኛ መሪ መምህር ናቸው።
በመመሪያው የተቀመጠው የቆይታ ጊዜም ከጀማሪ ወደ መለስተኛ መምህርነት ለመሸጋገር 2 ዓመት፣ በቀጣዮቹ ደረጃዎች ደግሞ በእያንዳንዱ እርከን የ3 ዓመታት ቆይታ የሚጠይቅ ነው።
ይሁን እንጂ አንድ መምህር በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜ በውድድር ሁለት ጊዜ እድገት ማግኘት ካልቻለ ለሦስተኛ ጊዜ የመወዳደር ዕድል እንደማይኖረው በመመሪያው ተደንግጓል።
መምህራን ለደረጃ እድገት ውድድር ብቁ ለመሆን ማሟላት ከሚገባቸው የጋራ መስፈርቶች መካከል በመምህርነት ሙያ ዕውቅና ካለው ተቋም የተመረቁ መሆን፣ የሙያ ፈቃድ ምስክር ወረቀት መያዝ፣ እንዲሁም ለጀማሪ መምህራን የመውጫ ምዘና ማለፍ በዋናነት ተቀምጠዋል።
ከዚህ በተጨማሪም አንድ መምህር ለደረጃ እድገት ለመብቃት ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች ውስጥ ቢያንስ 75 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው በገለልተኛ አካል መረጋገጥ እንዳለበት ሰነዱ ያትታል።
በተጨማሪም ጀማሪ መምህራን ቢያንስ የ40 ሰዓታት፣ ከመለስተኛ መምህር ጀምሮ ያሉት ደግሞ የ60 ሰዓታት ሙያ ተኮር አጫጭር ሥልጠናዎችን መከታተልና የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD) ዕቅዳቸውን በአግባቡ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል።
ወደ ከፍተኛ የእድገት እርከኖች ለመሸጋገር የተቀመጡት መመዘኛዎች የማስተማር ብቃትን ብቻ ሳይሆን የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎንም ያካተቱ ናቸው።
በዚህም መሠረት መምህራን ከደረጃ ወደ ደረጃ ሲሸጋገሩ ከ70 እስከ 90 በመቶ የሚደርስ የሥራ አፈጻጸም ውጤት ማስመዝገብ፣ የተደራጀ ማኅደረ-ተግባር (Portfolio) መያዝ፣ ጀማሪ መምህራንን በአማካሪነት መደገፍ እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውንና ተጋላጭ ተማሪዎችን መርዳት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
በተለይም ከመካከለኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉት ከፍተኛ እርከኖች ለመወዳደር የመማሪያና የመምሪያ መጻሕፍትን መገምገም፣ አጋዥ የትምህርት ጽሑፎችን ማዘጋጀት እና በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮችን (Action Research) ማካሄድ የግድ እንደሚል ሰነዱ በዝርዝር አስቀምጧል።
አዲሱ መመሪያ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መምህራን የተፋጠነ የደረጃ እድገት የሚሰጥበትን አሠራርም አስተዋውቋል።
በዚህም መሠረት ከመምህርነት እስከ መሪ መምህርነት ባለው እርከን የሚገኝ ማንኛውም መምህር የሚያስተምራቸው ተማሪዎች በሙሉ 85 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት በተከታታይ ሁለት ዓመታት እንዲያስመዘግቡ ካደረገ እና ይህም በገለልተኛ አካል ሲረጋገጥ፣ የሦስት ዓመት የቆይታ ጊዜውን ሳይጠብቅ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲያድግ ይደረጋል።
በተመሳሳይም የተማሪዎቹን ውጤት 90 በመቶ እና ከዚያ በላይ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ያደረሰ መምህር አንድ የደረጃ መሰላል ዘሎ እንዲያድግ የሚፈቀድ ሲሆን፤ በከፍተኛ መሪ መምህርነት ደረጃ ላሉት ደግሞ የሁለት እርከን ደመወዝ ጭማሪ እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
በሌላ በኩል መመሪያው የወሊድ ፈቃድ ላይ ያሉ መምህራንን፣ በጤና እክል ምክንያት በቦርድ ውሳኔ ከክፍል የተገለሉ ባለሙያዎችን እና በመምህራን ማኅበራት በአመራርነት የሚያገለግሉ አባላትን የደረጃ እድገት አፈጻጸም በልዩ ሁኔታ አካቷል።
የደረጃ እድገቱ በየዓመቱ በሁለት ዙር ማለትም በጥር አንድ እና በሐምሌ አንድ ቀን ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ሂደቱም በትምህርት ቤት ቴክኒክ ኮሚቴና በደረጃ እድገት ኮሚቴ ተጣርቶ በወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አማካይነት ይጸድቃል።
አሠራሩ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን የጥቅም ግጭትን የሚከላከሉ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፣ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያላቸው መምህራንም ደብዳቤው በደረሳቸው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተደንግጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia | 1 513 |
| 4 | #እንድታውቁት: የቀድሞ የይዞታ ካርታ እያለ አዲስ ሕጋዊ የካዳስተር ምዝገባ ለምን ያስፈልጋል?
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የቀድሞ የይዞታ ካርታ ያላቸው ባለይዞታዎች አዲሱን ሕጋዊ የካዳስተር ምዝገባ ማካሄድ ለምን እንደሚያስፈልጋቸው በሚል በገጹ ያቀረበውን መረጃ እንናጋራችሁ።
ኤጀንሲው እንዳስታወቀው አዲሱ ምዝገባ የቀድሞውን ሰነድ ለመሻር ወይም ተመሳሳይ መብትን ለሁለተኛ ጊዜ ለመስጠት ሳይሆን፣ ያለውን የይዞታ መረጃ በዘመናዊና በተደራጀ የካዳስተር ሥርዓት ማረጋገጥን ዓላማ ያደረገ ነው።
የመብት ሰጪ እና የመዝጋቢ ተቋማት ልዩነት
ነባሩ ካርታ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመሬት ተጠቃሚነት መብት ሲፈቅድ የሚሰጠው የፈቃድ ሰነድ ሲሆን፤ በአዋጅ ቁጥር 1381/2017 መሠረት የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የሚሰጠው የካዳስተር ሰርተፊኬት ደግሞ የመሬቱ ወሰን በጂፒኤስ (GPS) እና በኦርቶ ፎቶ ቴክኖሎጂ ተለክቶ የመሬቱና የንብረቱ ባለቤትነት በሕግ መረጋገጡን የሚያሳይ የዋስትና ሰነድ ነው።
አዲሱ የካዳስተር ምዝገባ የሚያካትታቸው ዝርዝሮች
አዲሱ ሥርዓት የመሬት መብት፣ ክልከላ እና ኃላፊነትን በአንድ ላይ የሚያደራጅ ሲሆን የሚከተሉትን ያካትታል፦
⚫ የቁራሽ መሬቱ ትክክለኛ ወሰን፣ ስፋት፣ ርዝመት፣ ቅርጽና የኮኦርዲኔት መረጃ
⚫ የወሰን መገናኛ ነጥቦች፣ የአጎራባች ይዞታዎች፣ የመንገድና የአድራሻ መረጃ
⚫ የቁራሽ መሬቱ ልዩ መለያ ኮድ (Unique Identification Code)
⚫ በመሬቱ ላይ ያለው ሕንፃ ወይም ሌላ ቋሚ ንብረት መረጃ
የቀድሞ ካርታ ብቻውን የሚያስከትላቸው ችግሮች
የቀድሞ ካርታ ብቻ መጠቀም የመሬት ስፋት በተለያዩ ሰነዶች ላይ በተለያየ መጠን የመመዝገብ፣ የአጎራባች ወሰን የመደራረብ፣ ትክክለኛ ኮኦርዲኔት የመጣት እና በሽያጭ፣ ውርስ፣ ሞርጌጅ ወይም ካሳ ወቅት የሕግ ክርክር የመፈጠር ችግሮችን ያስከትላል። በተጨማሪም በወረቀት ላይ ያለ መረጃ ለዲጂታል አሰራር አይመችም።
የቀድሞ ሰነድ ህልውናና የካዳስተር ጥቅም
የቀድሞ ሰነድ በምዝገባ ሂደት ወቅት እንደ ዋና ማስረጃነት የሚያገለግል እንጂ በግድ የለሽነት የሚሰረዝ አይደለም። አዲሱ አሰራር አዲስ መሬት ለመስጠት ወይም ባለይዞታውን ለማስጨነቅ ሳይሆን፣ የይዞታ ዋስትናን በማጠናከር የመሬት መረጃን ከአንድ ልዩ መለያ ኮድ ጋር ለማስተሳሰር የተዘጋጀ ነው።
የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ነባሩ ካርታ የመሬት መጠቀሚያ ፈቃድ ሲሆን፣ በአዋጅ ቁጥር 1381/2017 መሠረት የሚሰጠው የካዳስተር ምዝገባ ሰርተፊኬት ግን የሀብትና የቤት የመጨረሻ ሕጋዊ ማረጋገጫ በመሆኑ ባለይዞታዎች ይዞታቸውን በወቅቱ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርቧል።
@TikvahethMagazine | 2 104 |
| 5 | የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ያዘጋጀው የክራውድ ፈንዲንግ ረቂቅ መመሪያ ምን ይዟል ?
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ ኢንቨስትመንት ክራውድ ፈንዲንግን ለመጀመሪያ ጊዜ በሕግ ለመቆጣጠር የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቶ ለሕዝብ ውይይት አቅርቧል።
መመሪያው ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች እንዲሁም ስታርትአፖች ካፒታል ለማሰባሰብ አዲስ አማራጭ እንዲያገኙ ያለመ ነው ተብሏል።
ክራውድ ፈንዲንግ ማለት ምን ማለት ነው ?
ክራውድ ፈንዲንግ ማለት አንድ ድርጅት ካፒታሉን ለማሳደግ ወይም የዕዳ ሰነድ (ወለድ ያለው ብድር) በማቅረብ ገንዘብ ለማሰባሰብ ባለሥልጣኑ ፈቃድ በሰጠው ኦንላይን መድረክ በኩል ገንዘብ የሚያሰባስብበት ስልት ነው።
ይህንን የኦላይን ገንዘብ ማሰባሰቢያ መድረክ የሚያንቀሳቅሰው "የክራውድ ፈንዲንግ አገናኝ" ተብሎ የሚጠራ፣ ባለሥልጣኑ ፈቃድ የሰጠው አካል ይሆናል።
በረቂቁ መሰረት በክራውድ ፈንዲንግ ገንዘብ ማሰባሰብ የሚችሉት እነማን ናቸው ?
በዚህ መድረክ ገንዘብ ማሰባሰብ የሚችሉት በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ መሰረት የተመዘገቡ አክሲዮን ማህበራት (Share Company) መሆን ይጠበቅባቸዋል።
በተጨማሪ፣ ከሚከተሉት ሦስት መስፈርቶች ቢያንስ ሁለቱን ማሟላት ይኖርባቸዋል ፦
⚫ ጠቅላላ የተከፈለ ካፒታል ከ50 ሚሊዮን ብር ያልበለጠ፣
⚫ ጠቅላላ የተጣራ ሀብት ከ100 ሚሊዮን ብር ያልበለጠ፣
⚫ዓመታዊ የተጣራ ሽያጭ ከ100 ሚሊዮን ብር ያልበለጠ መሆን ይጠበቅበታል
በተጨማሪም የፋይናንስ ተቋማት፣ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎችና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በክራውድ ፈንዲንግ ገንዘብ ማሰባሰብ እንደማይችሉ ተቀምጧል።
ድርጅቶች የክራውድ ፈንዲንግ አገናኝ በኩል ለመመዝገብ ስለ ኩባንያው ምስረታ፣ ስለ ዳይሬክተሮችና ቁልፍ ኢንቨስተሮች ማንነትና የወንጀል ክስ አለመኖር ማረጋገጫ፣ ከ5% በላይ ድርሻ ያላቸው ባለአክሲዮኖች ዝርዝር፣ የንግድ ገለጻና ፈቃዶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
ለትልልቅ ምድብ ኩባንያዎች ደግሞ ኦዲት የተደረገ የሒሳብ መግለጫ፣ የንግድ ዕቅድ፣ የፋይናንስ ትንበያና የስጋት ጉዳዮች ዝርዝር ተጨማሪ ይጠየቃል።
ድርጅቶች በዋናነት የአክሲዮን ድርሻን ሲያቀርቡ ጠንካራ የፋይናንስ ታሪክ (3 ዓመታት ኦዲት፣ ትርፋማነት፣ አዎንታዊ የገንዘብ ፍሰት) ያላቸው ደግሞ የዕዳ ሰነድ ማቅረብ ይችላሉ።
ምን ያህል ገንዘብ ማሰባሰብ ይቻላል ?
በረቂቅ መመሪያው መሰረት ገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ጣሪያ ተቀምጧል። በዚህም፦
⚫ ለምድብ አንድ እስከ 10 ሚሊዮን ብር፣
⚫ ለምድብ ሁለት እስከ 25 ሚሊዮን ብር፣
⚫ ለምድብ ሦስት እስከ 50 ሚሊዮን ብር ጣሪያ ሲቀመጥ በጠቅላላ ደግሞ ከ50 ሚሊዮን ብር መብለጥ የለበትም ይላል።
አንድ ሽያጭ አቅርቦት ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ጠቅላላ ጊዜ (የአቅርቦት ጊዜ) ከ120 ቀናት እንደማይበልጥ ሲጠቀስ በባለሥልጣኑ ፈቃድ ለ30 ተጨማሪ ቀናት ሊራዘም ይችላል።
በዚህ ጊዜ ውስጥ ከታቀደው መጠን ከ50% በታች ከተሰበሰበ ማሰባሰቡ ይቋረጥና ገንዘቡ ለኢንቨስተሮች ተመላሽ ሆኖ ኩባንያውም ለ6 ወራት አዲስ ጥያቄ ማቅረብ አይችልም።
እነማን ኢንቨስት ማድረግ ይችላሉ ?
መመሪያው ኢንቨስተሮችን በሁለት ይከፍላል፦
⚫ ብቁ ኢንቨስተሮች - ተቋማዊ ኢንቨስተሮችና ከፍተኛ ጥሪት ያላቸው ግለሰቦች፤ እና
⚫ መደበኛ ኢንቨስተሮች - ለራሳቸው ጥቅም ኢንቨስት የሚያደርጉ፣ ከፍ ያለ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው ተራ ግለሰቦች።
መደበኛ ኢንቨስተሮች በአንድ አቅርቦት ከዓመታዊ ገቢያቸው 5%፣ በጠቅላላ ደግሞ 10% ብቻ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ተገድበው፣ ከዚያ በፊት የስጋት ማረጋገጫ ቅጽ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
አገናኞቹ ገንዘብ አሰባሳቢውን ከመመዝገባቸው በፊት የተገቢነት ቁመና ጥናት አካሂደው በ45 ቀናት ውስጥ ውሳኔ መስጠት፣ ለእያንዳንዱ ሽያጭ የአደራ ዝግ የባንክ ሒሳብ መክፈት፣ ከሚሰበሰበው ገንዘብ ከ2% በላይ ክፍያ ያለመቀበል ይጠበቅባቸዋል።
ማስታወቂያዎችን በተመለከተም "የላቀ"፣ "አስተማማኝ"፣ "ትርፋማ" የመሳሰሉ አሳሳች ማስታወቂያዎች የተከለከሉ ሲሆን፣ ኢንቨስተሮች የግዢ ቃል ኪዳን ከሰጡ በኋላ፣ ያለ ምንም ቅጣት ውሳኔውን የሚሰርዙበት የ 48 ሰዓታት የጥሞና ጊዜ ተሰጥቷቸዋል።
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የክራውድ ፈንዲንግ በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች እና ስታርትአፖች አማራጭ የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎችን የሚያቀርብ በመሆኑ መመሪያውን ማዘጋጀቱን ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም
@TikvahethMagazine | 1 943 |
| 6 | #Crowdfunding
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ በአገሪቱ ኢንቨስትመንት ክራውድ ፈንዲንግን ለመቆጣጠር የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቶ ለውይይት አቅርቧል።
ባለሥልጣኑ ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት፣ ፍላጎት ያለው ማንኛውም ሰው ጽሑፋዊ አስተያየት እስከ ጥቅምት 04፣ 2019 ድረስ ወደ crowdfundingfeedback@ecma.gov.et መላክ ይችላል ብሏል።
በተጨማሪም ባለሥልጣኑ የሕዝብ ውይይት መድረክና ማብራሪያ ጥቅምት 05 ቀን 2019 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በስካይላይት ሆቴል ማዘጋጀቱን የገለጸ ሲሆን ፍላጎት ያለው ማንኛውም ሰው በአካል ተገኝቶ አስተያየት መስጠት እንደሚችል አስታውቋል።
@TikvahethMagazine | 1 907 |
| 7 | የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ያዘጋጀው የክራውድ ፈንዲንግ ረቂቅ መመሪያ ምን ይዟል ?
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ ኢንቨስትመንት ክራውድ ፈንዲንግን ለመጀመሪያ ጊዜ በሕግ ለመቆጣጠር የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቶ ለሕዝብ ውይይት አቅርቧል።
መመሪያው ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች እንዲሁም ስታርትአፖች ካፒታል ለማሰባሰብ አዲስ አማራጭ እንዲያገኙ ያለመ ነው ተብሏል።
ክራውድ ፈንዲንግ ማለት ምን ማለት ነው ?
ክራውድ ፈንዲንግ ማለት አንድ ድርጅት ካፒታሉን ለማሳደግ ወይም የዕዳ ሰነድ (ወለድ ያለው ብድር) በማቅረብ ገንዘብ ለማሰባሰብ ባለሥልጣኑ ፈቃድ በሰጠው ኦንላይን መድረክ በኩል ገንዘብ የሚያሰባስብበት ስልት ነው።
ይህንን የኦላይን ገንዘብ ማሰባሰቢያ መድረክ የሚያንቀሳቅሰው "የክራውድ ፈንዲንግ አገናኝ" ተብሎ የሚጠራ፣ ባለሥልጣኑ ፈቃድ የሰጠው አካል ይሆናል።
በረቂቁ መሰረት በክራውድ ፈንዲንግ ገንዘብ ማሰባሰብ የሚችሉት እነማን ናቸው ?
በዚህ መድረክ ገንዘብ ማሰባሰብ የሚችሉት በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ መሰረት የተመዘገቡ አክሲዮን ማህበራት (Share Company) መሆን ይጠበቅባቸዋል።
በተጨማሪ፣ ከሚከተሉት ሦስት መስፈርቶች ቢያንስ ሁለቱን ማሟላት ይኖርባቸዋል ፦
⚫ ጠቅላላ የተከፈለ ካፒታል ከ50 ሚሊዮን ብር ያልበለጠ፣
⚫ ጠቅላላ የተጣራ ሀብት ከ100 ሚሊዮን ብር ያልበለጠ፣
⚫ዓመታዊ የተጣራ ሽያጭ ከ100 ሚሊዮን ብር ያልበለጠ መሆን ይጠበቅበታል
በተጨማሪም የፋይናንስ ተቋማት፣ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎችና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በክራውድ ፈንዲንግ ገንዘብ ማሰባሰብ እንደማይችሉ ተቀምጧል።
ድርጅቶች የክራውድ ፈንዲንግ አገናኝ በኩል ለመመዝገብ ስለ ኩባንያው ምስረታ፣ ስለ ዳይሬክተሮችና ቁልፍ ኢንቨስተሮች ማንነትና የወንጀል ክስ አለመኖር ማረጋገጫ፣ ከ5% በላይ ድርሻ ያላቸው ባለአክሲዮኖች ዝርዝር፣ የንግድ ገለጻና ፈቃዶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
ለትልልቅ ምድብ ኩባንያዎች ደግሞ ኦዲት የተደረገ የሒሳብ መግለጫ፣ የንግድ ዕቅድ፣ የፋይናንስ ትንበያና የስጋት ጉዳዮች ዝርዝር ተጨማሪ ይጠየቃል።
ድርጅቶች በዋናነት የአክሲዮን ድርሻን ሲያቀርቡ ጠንካራ የፋይናንስ ታሪክ (3 ዓመታት ኦዲት፣ ትርፋማነት፣ አዎንታዊ የገንዘብ ፍሰት) ያላቸው ደግሞ የዕዳ ሰነድ ማቅረብ ይችላሉ።
ምን ያህል ገንዘብ ማሰባሰብ ይቻላል ?
በረቂቅ መመሪያው መሰረት ገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ጣሪያ ተቀምጧል። በዚህም፦
⚫ ለምድብ አንድ እስከ 10 ሚሊዮን ብር፣
⚫ ለምድብ ሁለት እስከ 25 ሚሊዮን ብር፣
⚫ ለምድብ ሦስት እስከ 50 ሚሊዮን ብር ጣሪያ ሲቀመጥ በጠቅላላ ደግሞ ከ50 ሚሊዮን ብር መብለጥ የለበትም ይላል።
አንድ ሽያጭ አቅርቦት ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ጠቅላላ ጊዜ (የአቅርቦት ጊዜ) ከ120 ቀናት እንደማይበልጥ ሲጠቀስ በባለሥልጣኑ ፈቃድ ለ30 ተጨማሪ ቀናት ሊራዘም ይችላል።
በዚህ ጊዜ ውስጥ ከታቀደው መጠን ከ50% በታች ከተሰበሰበ ማሰባሰቡ ይቋረጥና ገንዘቡ ለኢንቨስተሮች ተመላሽ ሆኖ ኩባንያውም ለ6 ወራት አዲስ ጥያቄ ማቅረብ አይችልም።
እነማን ኢንቨስት ማድረግ ይችላሉ ?
መመሪያው ኢንቨስተሮችን በሁለት ይከፍላል፦
⚫ ብቁ ኢንቨስተሮች - ተቋማዊ ኢንቨስተሮችና ከፍተኛ ጥሪት ያላቸው ግለሰቦች፤ እና
⚫ መደበኛ ኢንቨስተሮች - ለራሳቸው ጥቅም ኢንቨስት የሚያደርጉ፣ ከፍ ያለ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው ተራ ግለሰቦች።
መደበኛ ኢንቨስተሮች በአንድ አቅርቦት ከዓመታዊ ገቢያቸው 5%፣ በጠቅላላ ደግሞ 10% ብቻ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ተገድበው፣ ከዚያ በፊት የስጋት ማረጋገጫ ቅጽ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
አገናኞቹ ገንዘብ አሰባሳቢውን ከመመዝገባቸው በፊት የተገቢነት ቁመና ጥናት አካሂደው በ45 ቀናት ውስጥ ውሳኔ መስጠት፣ ለእያንዳንዱ ሽያጭ የአደራ ዝግ የባንክ ሒሳብ መክፈት፣ ከሚሰበሰበው ገንዘብ ከ2% በላይ ክፍያ ያለመቀበል ይጠበቅባቸዋል።
ማስታወቂያዎችን በተመለከተም "የላቀ"፣ "አስተማማኝ"፣ "ትርፋማ" የመሳሰሉ አሳሳች ማስታወቂያዎች የተከለከሉ ሲሆን፣ ኢንቨስተሮች የግዢ ቃል ኪዳን ከሰጡ በኋላ፣ ያለ ምንም ቅጣት ውሳኔውን የሚሰርዙበት የ 48 ሰዓታት የጥሞና ጊዜ ተሰጥቷቸዋል።
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የክራውድ ፈንዲንግ በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች እና ስታርትአፖች አማራጭ የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎችን የሚያቀርብ በመሆኑ መመሪያውን ማዘጋጀቱን ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም
@TikvahethMagazine | 1 |
| 8 | Нет текста... | 2 395 |
| 9 | EFAA Job Vacancy September 2026.pdf | 3 521 |
| 10 | የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር 7 ክፍት የስራ መደቦችን አውጥቷል።
ማህበራችን የጽሕፈት ቤቱን አቅም ለማጠናከር ብቁና ተነሳሽነት ያላቸው ባለሙያዎችን ይፈልጋል፦
-ዋና ጸሐፊ
-የአስተዳደር፣ የሕግ ጉዳዮች እና የኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኦፊሰር
-የተከታታይ ሕግ ትምህርት (CLE)፣ ጥናትና ስልጠና ኦፊሰር
-የኮሙኒኬሽን፣ የሕዝብ ግንኙነት እና ዲጂታል ሲስተም ኦፊሰር
-የሒሳብ ሹም
-የሕግ ባለሙያ
-የውስጥ ኦዲተር
የስራ ቦታ፦ አዲስ አበባ ደመወዝ፦ በማህበሩ የደመወዝ ስኬል መሰረት የሚቀርቡ ሰነዶች፦ CV፣ የትምህርት ማስረጃ እና የስራ ልምድ ማስረጃ (ኮፒ)
ማመልከቻ የሚላክበት ኢሜል ፦ info@efaa.et (Subject ላይ የሚያመለክቱበትን የስራ መደብ ስም ይጥቀሱ)
ቀነ ገደብ፦ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም. | 3 746 |
| 11 | Нет текста... | 3 647 |
| 12 | https://forms.cloud.microsoft/r/2TEu2dWyDn | 3 433 |
| 13 | 5_2011ስለተቀናሽ_ወጭዎች_አፈጻጸም_መመሪያ.pdf | 4 217 |
| 14 | በሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ እድገት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል የተባለዉ አዲስ የፕሮጀክት ፊዚካል አፈጻጸም መለኪያ ስታንዳርድ ከሰሞኑ ይፋ ተደርጓል።
ይህ ስታንዳርድ ለዘርፉ ምንድነዉ? የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መስፍን ነገዎ በዚህ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
#Construction #Ethiopia #ConstructionIndustry #ProjectManagement #EthiopianConstruction #Engineering #Infrastructure #BuildEthiopia #Standards #Development #BusinessNews #Capitalnewspaper | 4 810 |
| 15 | መልካም አዲስ ዓመት! 🙏
እንኳን ለ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
ይህ አዲስ ዓመት ያለፉትን ተግዳሮቶች አስወግደን አዳዲስ ስኬቶችን የምናሳካበት የሰላምና የዕድገት ዓመት ይሁንልን። በየትኛውም የዓለም ማዕዘን እንኑር ህብረታችንና ፍቅራችን የጸና ይሁን!
መልካም ምኞት ከጠበቃ እና ህግ አማካሪ Mikias Melak AleHig #ሚኪያስ #መላክ
#አለሕግ አለ ሕግ #AleHig #ከሜዲትራኒያን #ባህር 🌊🙏 | 5 437 |
| 16 | የታክስ አለመግባባትን በመስማማት ስለመፍታት
ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (የምስራቅ አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት )
በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 አንቀጽ 61 የታክሱ ባለስልጣን የታክስ አለመግባባትን በመስማማት ለመፍታት ያለውን ስልጣን በተመለከተ የሚከተለውን ይላል፡-
👉 የታክሱ ባልስልጣን የታክስ አለመግባባቶችን በመስማማት የመፍታት ስልጣን ተሰጥቶታል።
👉 ማናቸውም በስምምነት የሚፈታ የታክስ ያለመግባባት በጽሁፍ የሚደረግ እና የተስማሚ ወገኖች ፊርማ ያረፈበት ሊሆን ይገባል።
👉 የታክስ አለመግባባቶችን በመስማማት የመፍታት ስልጣን የሰጠው ድንጋጌ ቢኖርም የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲኖሩ ጉዳዩ በማስማማት ሊታይ አይችልም፦
1. የታክስ ማጭበርበር ወይም ሆን ተብሎ የተደረገ ታክስን የመሰወር ድርጊት መኖሩ ወይም ሌላ ከታክስ ጋር የተገናኘ ወንጀል መኖሩ ሲጠረጠር፤
2. በማስማማት የሚደረግ ስምምነት ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት እና ከሚመለከታቸው የታክስ ሕጎች ጋር የሚጋጭ ሲሆን፤
3. ከሁለቱ ወገኖች አንዱ በሽምግልና ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ካልሆነ።
👉 ሚኒስቴሩ የአስማሚውን የትምህርት እና ሙያ ደረጃን ጨምሮ የመስማማት ሂደት የሚመራበትን ሥርዓት የሚወስን ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ ያወጣል፡፡
ምንጭ ፣ገቢዎች ሚኒስቴር | 6 837 |
| 17 | በመኪና ሽያጭ ላይ የሚፈፀሙ የታክስ ስወራዎችንና ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት ጠንካራ የህግ ማስከበር እርምጃ ሊወሰድ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ ባወጣው እንዳሳወቀው፤ በከተማዋ አንዳንድ የመኪና አስመጪዎችና የኮሚሽን ስራ ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦች በመቀናጀት ከፍተኛ የታክስ ስወራ ወንጀል እየፈፀሙ ይገኛሉ።
ህገ-ወጥ አሰራሩ በተለይም የመኪና አስመጪዎች የሚያስገቧቸውን ተሽከርካሪዎች መደበኛ የንግድ ፈቃድና አድራሻ ለሌላቸው ደላሎች አሳልፈው በመስጠት፣ ህጋዊ ደረሰኝ ሳይቆርጡ ዋጋን ቀንሰው በመሸጥ ግብር እንዳይከፈል የሚያደርጉበት እንደሆነ ተጠቅሷል።
ይህ ድርጊት በፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ መሰረት በወንጀል የሚያስጠይቅ በመሆኑ፣ ቢሮው ከሚመለከታቸው የህግ አካላት ጋር በመቀናጀት ቁጥጥሩን እንደሚያጠናክር ገልጿል።
ቢሮው የኮሚሽን ንግድ ፈቃድ ያላቸውም ሆኑ የመኪና አስመጪዎች ከእንደዚህ አይነት ህገ-ወጥ አሰራር እንዲወጡ ያስጠነቀቀ ሲሆን፤ ማንኛውም የመኪና ሽያጭ በህጋዊ የንግድ ቦታ፣ በደረሰኝ እና መደበኛ ታክስ ተከፍሎበት ብቻ መከናወን እንዳለበት አሳስቧል።
ሀና ሰይፉ
ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም | 4 289 |
| 18 | ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ያሳየችው የንግድ እንቅስቃሴ አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ያሳየችው የንግድ እንቅስቃሴ አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ ኢትዮጵያ ስምምነቱን በቀዳሚነት ከፈረሙና ካጸደቁ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን፤ እ.ኤ.አ ጥቅምት 9 ቀን 2025 በይፋ ንግድ መጀመሯ ይታወሳል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳጋራው መረጃ ንግዱ በይፋ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ ማዝያ ወር 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ ብቻ ኢትዮጵያ ከሌሎች አባል ሀገራት ጋር ባደረገችው የንግድ ልውውጥ፦ከ14 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ምርቶችን ወደ ውጭ የላከች ሲሆን፤ ከ8 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚገመቱ ምርቶችን ደግሞ ወደ አገር ውስጥ አስገብታለች።
Read More
Source: Ethio FM 107.8
@Ethiopianbusinessdaily | 5 415 |
| 19 | የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪን ይመለከታል
ለኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር አባላት፡
ቀደም ሲል በተላለፈው ጥሪ መሰረት የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር የ2018 በጀት ዓመት መደበኛ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ቅዳሜ ነሀሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ሜክሲኮ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የኅብረት ባንክ ዋና ህንጻ (ህብረት ታወር) አዳራሽ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ እንደሚካሄድ እየገለጽን ለዝግጅት እንዲመቸን በጉባኤው የምትገኙ መሆኑን በኢሜል አድራሻችን 2014barassociation@gmail.com ስልካችሁን በመጻፍ እንድትመዘገቡ በማክበር እንጠይቃለን፡፡
የአባልነት ክፍያ ያላጠናቀቃችሁአባላት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000540887091 ገቢ በማድረግ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ በኢሜል መላክ ትችላላችሁ።
የጉባኤው ረቂቅ አጀንዳዎች፡
1. የ2018 በጀት ዓመት የማኅበሩን የስራ ክንውንና የውጭ ኦዲተር ሪፖርት መርምሮ ማጽደቅ፤
2. የማኅበሩን የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ተወያይቶ መወሰን፤
3. ለማኅበሩ በጎ ፈቃደኛ ባለውለታዎች የእውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ማካሄድና ሌሎችም ናቸው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-553-01-22 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
ኅብረት ባንክ ለማኅበራችን ለሚያደርገው የተለመደ ትብብር ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ከሰላምታ ጋር
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር (ELA) | 4 899 |
| 20 | የተሻሻለው አዋጅ ስለታክስ ማጭበርበር ምን ይላል?
ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት “የታክስ ማጭበርበር” ማለት ታክስን ለመሰወር ወይም ህጋዊ ያልሆነ የታክስ ጥቅም ለማግኘት ሲባል የሚከተሉትን ድርጊቶች መፈጸም ነው፤
👉 ሐሰተኛ የሂሳብ መዝገቦችን፣ ሰነዶችን፣ ደረሰኞችን ወይም ሌሎች ሰነዶችን ማቅረብ፣
👉 ገቢን፣ ግብይትን ወይም ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ መደበቅ፣
👉 ሐሰተኛ ደረሰኞችን ማዘጋጀት ወይም መጠቀም፣
👉 ሐሰተኛ የታክስ ማስታወቂያ ማቅረብ
👉 ሰነዶችን ማጥፋት፣ መቀየር፣ መደበቅ፣
👉 ከአንድ በላይ ወይም ትይዩ የሂሳብ መዛግብትን ወይም ሰነዶችን ማዘጋጀትና መያዝ፣ እንዲሁም ለታክስ ባለስልጣኑና ለሌሎች አካላት ማቅረብ፤
👉ሐሰተኛ የተቀናሽ ወጪዎችን፣ የግብር ወይም የታክስ ነፃ መብት፣ የተመላሽን ወይም የማካካሻ ጥያቄን ማቅረብ፤
👉 ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የታክስ ግዴታን ለመቀነስ ማናቸውንም ሌሎች ድርጊቶች መፈጸም ወይም ሕግ እንዲፈፅሙ የሚያስገድዳቸውን አለመፈጸም፡፡
በአዋጁ የተሻሻሉ የታክስ ስሌቶች እና የይርጋ ጊዜ ገደብን በተመለከተ ሲገልጽ የታክስ ባለስልጣኑ የማጭበርበር ድርጊት የተፈጸመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያገኘ እንደሆነ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 (አስር) ዓመት ውስጥ ሊያሻሽል ይችላል ይላል፡፡
ይሁን እንጂ በአዋጁ ንዑስ አንቀጽ 5 ላይ የታክስ ማጭበርበር ድርጊት መፈጸሙ በማስረጃ የተረጋገጠ በሚሆንበት ጊዜ የታክሱ ባለስልጣን የ10 (አስር) ዓመቱን የይርጋ ጊዜ ገደብ ሳያልፍ በማናቸውም ጊዜ የታክስ ውሳኔ ማሻሻያን ሊያደርግ እንደሚችል ይገልጻል፡፡ | 6 044 |
