2 154
Подписчики
Нет данных24 часа
-67 дней
+2630 дней
Архив постов
2 154
ማስታወቂያ
ለሁሉም የተማሪ ወላጆች
እንደሚታወቀው ከጥቅምት 4/2019____6/2019ዓ.ም ወርሀዊ ፈተና እንደሚሰጥ ይታወቃል።በመሆኑ በወጣላቸው የፈተና ፕሮግራም መሠረት አስፈላጊ ድጋፍ እና ክትትል እንድታደርጉ የትምህርት ቤት አስተዳደር ያሳውቃል ። ለማስታወስ ያክል
ዕሮብ
1__2
አማርኛ እንግሊዝኛ
3____6
አማርኛ ,እንግሊዝኛ እና አ/ኦሮሞ
7___8
አማርኛ,እንግሊዝኛ,አ/ኦሮሞ እና IT
2 154
ማስታወቂያ
ለተማሪ ወላጆች በሙሉ
ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው
መሰከረም 28/2019 ዓ.ም እና 29/2019 ዓ.ም በተከታታይ ለሁለት ቀናት ከወተመህ እና ከአጠቃላይ መምህራን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን አጀንዳዎች ሰፊ ውይይት በማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
1. የ2018 ዓ.ም የማጠናከሪያ ትምህርት ጠንካራ ጎኖች እና ክፍተቶችን በመገምገም
በ2019 ዓ.ም ተማሪዎች ውጤታማ ሊያደርግ ይችላል የተባለውን አዲስ አሰራር በወተመህ የቀረበውን ሀሳብ መስከረም 29/2019 ዓ ም ከመምህራን ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ከዚህ በታች በተጠቀሱ መሰረት የሚሰጥ ይሆናል።
1.ከጥቅምት 2/2019ዓ.ም ጀምሮ ማጠናከሪያ/ጥናት የሚጀመር ይሆናል።መደበኛ ክፍለ ጊዜ ሳይነካ ከሰኞ እስከ ዓርብ በየቀኑ ለ50 ደቂቃ የሚሰጥ ይሆናል፤ተማሪዎች በሰርቪስ ይመጣሉ በሰርቪስ ይመለሳሉ
1.አዲሱ አሰራር ከጥቅምት 9/2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ውጤታማነቱ ከሁለት ወር በኋላ በወተመህ እና በጥናት / በማጠናከሪያ ትምህርት ኮሚቴ የሚገመገም ይሆናል።
2.የጥናት ክፍያ የሚከፈለው ወር በገባ እስከ 10 ሲሆን የክፍያ መጠን ሁሉም /አብዛኛው ተማሪ የሚሳተፍበት ወቅቱን ታሳቢ ያደረገ በክፍለ ጊዜ 17.5 ወይም በሰዓት 21.87 ብር በድምሩ በተማሪ በወር 350(ሶስት መቶ ሃምሳ)ብር መሆኑን የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ያሳውቃል።
2 154
ማስታወቂያ
ለሰርቪስ ተጠቃሚ ተማረ ወላጆች ማንኛውም ሰርቪስ ተጠቃሚ ተማሪ የሰርቪስ መታወቂያ መያዝ እንዳለበት ይታወቃል ።በመሆኑ ከሰኞ ማለትም ከጥቅምት3/2019 ዓ.ም ጀምሮ መታወቂያ መያዝ ግዴታ መሆኑን አውቃችሁ ወይሞ የተከፈለበትን ደረሰኝ መያዝ ይጠበቅባቸዋል ይህ ባይሆን ግን ለሚፈጠረው መጉላላት ሰርቪስ ስምሪቱ ሀላፊነት የማይወስድ መሆኑን ከወዲሁ ያሳውቃል።
2 154
የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ ነገ መስከረም 22/2019 ዓ.ም ትምህርት የማይኖር መሆኑን የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ያሳውቃል።
2 154
ሰላም ጤና ይስጥልን የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች የመፅሐፍ ክፍያ ከፍላችሁ ቀሪ ተመላሽ ብር በደረሰኝ ጀርባ የተፃፈላችሁ ደረሰኝ በመያዝ ከቀን 21/1/2019 ዓ.ም ጀምሮ ከሂሳብ ክፍል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ያሳውቃል።
2 154
የተከበራችሁ የተማሪ ወላጆች ከላይ የምትመለከቱት የትምህርት ቤቱ ሎጎ በእያንዳንዱ ተማሪ ግራ ደረት ላይ የሚለጠፍ ስለሆነ ማንኛውም ተማሪ እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም አድርጎ መገኘት ይጠበቅበታል ።
2 154
የተከበራችሁ የሰርቪስ ተጠቃሚ ተማሪ ወላጆች ከቀን 7/1/2019 ዓ.ም ጀምሮ የመጀመሪያ ዙር ሰርቪሰ መነሻ ሰዓት 12:30 መሆኑን ትምህርት ቤቱ ያሳውቃል።
