ch
Feedback
Lesperance 2015

Lesperance 2015

前往频道在 Telegram
1 923
订阅者
无数据24 小时
-27
-1130
帖子存档
በነገው ዕለት የሚሰጠው ኦረንቴሽ ለግማሽ ቀን ብቻ ስለሆነ ምሳ መያዝ አይጠበቅባቸውም።

Repost from Yeka Education
✅የፈተና ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው(በድጋሜ የተለጠፈ) ። 📌 ይህም ጤናማ ፍርሀት ለፈተና እንድንተጋ ስለሚረዳ
የፈተና ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው(በድጋሜ የተለጠፈ)📌 ይህም ጤናማ ፍርሀት ለፈተና እንድንተጋ ስለሚረዳን በተሻለ ለመዘጋጀት እንዲሁም ጥሩ ትኩረት ለማድረግ ያስችለናል። ✔️ ሆኖም ግን ይህ ጭንቀት ወይም ቴንሽን መጠነኛ ካልሆነ ወደ መደናገር እና ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። በዚህም የተነሳ ፈተናችንን በጥሩ እንዳናስኬድ እና ተገቢውን ትኩረት እንዳንሰጥ ያደረፈርገናል ።  ✔️ከዚህም ሀሳብ ጋር በተያያዘ ለዚህ አይነቱ #ጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ #እንድንገባ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ #ምክንያቶች ውስጥ #ጥቂቶቹ: ➡️ አሉታዊ ሀሳቦች ወደ አዕምሮ በመምጣት ሀሳባችን በሙሉ ስለ ፈተናው አስከፊነት እና ስለውጤት መበላሸት አብዝተን ስናስብ ። ➡️ በቂ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ግመታ እና ድምዳሜ አጠቃሎ ስለፈተናው ማሰብ ። ➡️ የውጫዊ ተፅእኖ እንደ ቤተሰብ ፣ መምህራን እና ጓደኛ የሚመጡ ጫናዎች አስተሳሰባችን ላይ ይህ መሆን አለበት ወይም መሆን የለበትም የሚል አቋም መያዝ ስህተትን እንዳንቀበል እና መሳሳትን እንድንፈራ ስለሚያረግ በፈተና መዳረሻ ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። ➡️ሙሉ ሀሳብን ወደ ፈተናው ይዘት እና ሁኔታ ከማተኮር ይልቅ ወደ ውጤት እና ነጥብ ብቻ ላይ ማተኮር እና ማስላት።  እነዚህ ዋና ዋናዎቹ በፈተና ወቅት ውጥረትን እና ጭንቀትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ናቸው። ስለዚህ ተፈታኞች የተወሰነ ዘዴን በመጠቀም ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤ ⭐️  ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤ - ➡️ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት። ➡️ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ይህ ማለት ስለፈተናው ክብደት እና አስከፊነት ከማሰብ በተቃራኒው በአይነ ህሊና (visualization) ዘና ብለን ስንፈተን እና ፈተናውን በተገቢ መንገድ ስንፈተን በአእምሮችን መሳል ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በክፍል ውስጥ በብቃት የሰራናቸውን ፈተናዎች እና የገኘነውን ጥሩ ውጤቶች ማሰብ።  እናም ምን አይነት ፈተና ሊመጣ ይችላል ብለን አብዝተን አለመጨነቅ ይልቅ የሚመጣው ፈተና ከዚህ በፊት ከተማርነው የተለየ አለመሆኑን መረዳት እና መጪውም ፈተና በተመሳሳይ እንደምንሰራው ማሰብ። ➡️ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። ምክንያቱም ከላይ እንደ ምክንያት ለተቀመጡት ነጥቦች ከዚህ ሀሳብ በተያያዘ አንድ ተማሪ በፈተና ጥሩ ውጤት ባያገኝ እና ቢሳሳት ቀድሞውኑ ወደ ጭንቅላቱ የሚመጣው አለማወቁ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እና ቤተሰቦቹም ሆነ መምህራን እንደ ሰነፍ እና ዋጋ እንደሌለው ስለሚገመት ስህተትን አስተካክሎ ለቀጣይ ለማሻሻል እና ለመማር መሰናክል ይፈጥራል። ስለዚህ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን። ➡️ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። 📌ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል። ➡️ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል። ✔️ ፈተና ከጀመርን በኋላ መድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤ ➡️ ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።  ➡️አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ። ➡️ ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ። በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ።   ➡️ ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤  • ✔️በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ። ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ። 📌በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። ይልቅ በጣም ሳንንቀራፈፍ ተረጋግተን ፈተናውን  መስራት እና ፈተናውን ከጨረስን በኋላ ተመልሰን የሰራነውን ጥያቄ አጠቃላይ ማየት ያስፈልጋል።            ⭐️የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የተወሰኑ ቀናት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1 ወር ያነሱ ቀናት ይቀሩታል! #️⃣Share ⭐️ ለሁሉም ተፈታኞች መልካም የጥናትና የፈተና ጊዜ!⭐️ 🔠🔠🔠🔠 🔠🔠🔠 Our Channel ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76

የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች፣ ➊ የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ
+1
የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች ➊ የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡ ❷ በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን ክብ ብቻ መጠቆር አለበት፡፡ ➌ ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው ክብ ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡ ❹ ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን ክብ በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡ ❺ በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ ክብ ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡ ❻ ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ❼ ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ❽ መልስ በሚጠቆርበት ጊዜ እርሳሱ ከተሰጠው የክብ ሳጥን መውጣት የለበትም። ከወጣም በማጥፊያ (Eraser/Rubber) ማጥፋት ይጠበቅባችኋል። ❾ መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ ➓ ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡ ⓫ በእስክሪብቶ መፃፍ አይፈቀድም። ስለዚህ እርሳስ፣ ላጲስ እና መቅረጫ አይለያችሁ ⓬ ፈተና ጨረስኩ ብሎ አላስፈላጊ የሆነ ነገር፤ ስዕል ወይም ሌላ ከጀርባም ይሁን ከፊት አይፃፍበትም። ⓭ በጣም የተቀረፀ ሹል እርሳስ በምንጠቀም ወቅት ወረቀቱ እንዳይቀደድ መጠንቀቅ አለብን።

ማስታወቂያ ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ እንደሚታወቀው የ2018ዓ.ም ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 8____ሰኔ 12/2018ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።በመሆኑ ሰኔ 5/2018ዓ.ም በምትፈተኑበት የፈተና ጣቢያ አጠቃላይ ኦረንቴሽን ስለሚሰጥ ጠዋት2:00 በትምህርት ቤቱ ተገኝታችሁ በሰርቪስ ወደ መፈተኛ ጣቢያ እንሄዳለን።

grade 8 100 question.doc5.35 KB

2018 AMHARIC G8.docx0.37 KB

ግንቦት 25 እና 26/2018 ዓ.ም ትምህርት የማይኖር መሆኑ ያሳውቃል።

Repost from Yeka Education
✅6ኛ ክፍል የአፋን ኦሮሞ ሞዴል ፈተና ✅አዘጋጅ ➡️የካ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት 👍መንፈቀ አመት➡️የመጀመሪያ መንፈቀ አመት  ✅የትምህርት አይነት➡️ሁሉም በአፋን ኦሮሞ ✅አመት ➡️2016 ✅ክፍል ➡️6 🥰Share Our telegram channel 👇👇👇👇👇 💚💚💚💚💚 https://t.me/dam76

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ።

Repost from Yeka Education
🔼🔼 🔤-6️⃣

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡበት ጊዜ ይፋ ሆናል፡፡ (ግንቦት 13/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2
+1
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡበት ጊዜ ይፋ ሆናል፡፡     (ግንቦት 13/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን ከተማ አቀፍ የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና እና የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ፈተና  የሚሰጥበት ጊዜ ይፋ ሆናል፡፡   በዚህ መሰረትም ከተማ አቀፍ የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ሰኔ 8 ፣ 9 እና 10/2018 ዓ.ም እንዲሁም የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ፈተና  ሰኔ 11 እና 12/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሰጥ ይሆናል፡፡     ከሰኔ 8 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሚሰጠው በዚህ ከተማ አቀፍ ፈተና በ6ኛ ከፍል 84,882 ተማሪዎች 199  የመፈተኛ ጣቢያዎች  እንዲሁም በ8ኛ ከፍል 86,808 ተማሪዎች 201 የመፈተኛ ጣቢያዎች  ፈተናዉን ለመውሰድ ተመዝግበዋል፡፡     ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

photo content

photo content

የተከበራችሁ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች ከተማ አቀፍ የሞዴል ፈተና ቀን ለውጥ ተደርጎበታል ። 👉በዚሁ መሰረት ከዕሮብ12__14/2018ዓ.ም ቀናት መካከል የሚሰጥ ይሆናል።

ሰላም እንዴት ዋላችሁ 📖የ6ኛ፤ 8ኛና 12ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ የሞዴል ፈተና የቀን ለውጥ ተደርጎበታል፡፡ 👉🏻በዚህ መሰረት ከሮብ ግንቦት 12-14/2018 ቀናት መካከል የሚሰጥ ሲሆን ፕሮግራሙ እንዳለ ሁኖ የቀናት ጋብቻ ማስተካከያ ተደርጓል።ስለዚህ የተስተካከለ/ኢዲት የተደረገ ፖርግራም እንደደረሰን የምናሳውቅ ይሆናል። በዚህ ልክ ትምህርት ቤቶች ፕሮግራማቸውን እንድያዘጋጁ ይደርግ፡፡ መልካም ቀን፡፡

ማስታወቂያ ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች የእሁድ ማጠናከሪያ ትምህርት በሰርቪስ ምክንያት የማይቀጥል መሆኑን ት/ቤቱ ያሳውቃል።

Grade 6, 8 and 12 Model Exam Schedule By: AACAEB
+1
Grade 6, 8 and 12
Model Exam Schedule
By: AACAEB

ለሌስፔራንስ አድቬንቲስት ተማሪ ወላጆች ጉዳዩ፦ የትምህርት አገልግሎት ክፍያ ስለማስታወስ በቅድሚያ የከበረ ሰላምታችን እያቀረብን የትምህርት አገልግሎት ክፍያ የምትከፍሉ ወላጆች የ3ኛውና የመጨረሻው ተርም ክፍያ የሚከፈለው እስከ ሚያዝያ 5/8/2018 ዓ.ም እንደነበር ይታወቃል። በመሆኑ የትምህርት አገልግሎት ክፍያችሁን ወቅቱን ጠብቃችሁ የከፈላችሁ ወላጆች ምስጋናችንን እያቀረብን ፣ 👉 ነገር ግን የተወሰናችሁ የተማሪ ወላጆች(ህጋዊ አሳዳጊዎች ያልተከፈለ ክፍያ እንዲከፈል በትምህርት ቤቱ ፋይናንስ በኩል የማስታወስ ስራ የተሰራ ቢሆንም ወቅቱን ጠብቃችሁ እየከፈላችሁ እንዳልሆነ ለመረዳት ተችሏል ፣ 👉በመሆኑም ማንኛውም ውዝፍ ክፍያ ያለባችሁ ወላጆች ትምህርት ቤቱ በሚሰጠው አገልግሎት ላይ መጉላላት እንዳይደርስባችሁ በማሰብ ክፍያችሁን እንድታጠናቁ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር በአክብሮት እናሳውቃለን ። ት/ቤቱ

Repost from Yeka Education
🔑ለተማሪዎች ውጤታማ የአጠናን ዘዴዎች! ✔️/የጊዜ አያያዝ እና እቅድ ማውጣት ⭐️ ለእያንዳንዱ ትምህርት ዓይነት የተወሰነ የጥናት ጊዜ መመደብ ⭐️ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የትምህርት አይነቶችን መለየት
🔑ለተማሪዎች ውጤታማ የአጠናን ዘዴዎች! ✔️/የጊዜ አያያዝ እና እቅድ ማውጣት ⭐️ ለእያንዳንዱ ትምህርት ዓይነት የተወሰነ የጥናት ጊዜ መመደብ ⭐️ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የትምህርት አይነቶችን መለየት ⭐️ መነበብ ያለባቸውን ትምህርቶች በመለየት ዕቅድ ማውጣት 🤔/የጥናት አካባቢ ✅ምቹ የጥናት ቦታ  መለየት ✅ንጹህ አየር ያለበት ቦታ መምረጥ ✅ ጸጥታ የሰፈነበትና ከረብሻ ነፃ የሆነ ቦታ መምረጥ ✅ከስልክ እና ሌሎች ትኩረት ከሚሰርቁ ነገሮች መራቅ ✔️/የማስታወስ ዘዴዎች 📌አንድን ምዕራፍ ከማጥናቱ በፊት ጠቃሚ ይዘቶችን መለየት 📌የተማርነውንና ያጠናነውን ወሳኝ ይዘት እንዳይረሳ በተደጋጋሚ መከለስ 📌ዋና ዋና ነጥቦችን በጉልህ መፃፍ 📌 በደብተር ዳር አጫጭር ማስታወሻዎችን መጻፍ 📌ካነበብን በኋላ በራስ ሀሳብ በአእምሮ ማጠቃለል 📌አስፈላጊና ቁልፍ ቃላትን እና ሀረጎችን መጠቀም 📌 ቃላት አሳጥሮ መጠቀምና ለማስታወስ አጫጭር ስሞችን መጠቀም 📌ከሌሎች ጋር  መማማር ትምህርቱን ለማጠናከር ይረዳናል 📌 ነገሮችን በቀላሉ ለመያዝ ከቦታዎች ጋር ማዛመድ 📌በቀላሉ ለማስታወስ መረጃዎችን በተረት መልክ መያዝ ✔️/ንባብ እና ጽሑፍ 📣አንድን ምዕራፍ ከማጥናቱ በፊት ወሳኙን ይዘት መለየት 📣ያለፉ ፈተናዎችን በመስራት ልምምድ ማድረግ 📣ዋና ዋና ነጥቦችን በጉልህ መፃፍ 📌 ካነበብን በኋላ በራስ ሀሳብና ቃል  በአእምሮ እያሰላሰሉ ማጠቃለል ✔️/የቡድን ጥናትከሌሎች ተማሪዎች ጋር በመሆን መወያየትና መጠያየቅ በጥያቄ እና መልስ እርስ በርስ መጠያየቅ የቡድን አብሮ በመስራት መማማር ያልተረዳነውን ነገር መጠየቅ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር መረጃ መለዋወጥ 😊/ፈተና ለመፈተን ዝግጅት ➡️በፈተና ቀን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ➡️ በፈተና ወቅት መረጋጋት እና ጥያቄዎችን በጥንቃቄ ማንበብ ➡️ጭንቀትን ማስወገድና ዘና ማለት ✔️/ጤና እና ደህንነትበቂ እንቅልፍ መተኛት በየቀኑ ትንሽ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ በቂ ውሃ መጠጣት በማጥናት መካከል አጭር ዕረፍት ማድረግ 🔤🔤🔤🔤  🔤🔤🔤 ❓❓ http://t.me/dam76

Repost from Yeka Education
✔️ዝምተኛው ገዳይ ካርበን ሞኖክሳይድ(CO) (የከሰል ጭስ) ✍️ አብዛኞቻችን በቤታችን ውስጥ ከሰል የማጨስ ልምድ አለን፡፡ ታዲያ ይህ በቤታችንን የምንጠቀምበት ጭስ በአግባቡና በጥንቃቄ ካልያዝነው ለ
✔️ዝምተኛው ገዳይ ካርበን ሞኖክሳይድ(CO) (የከሰል ጭስ) ✍️ አብዛኞቻችን  በቤታችን ውስጥ ከሰል የማጨስ ልምድ አለን፡፡ ታዲያ ይህ በቤታችንን የምንጠቀምበት ጭስ በአግባቡና በጥንቃቄ ካልያዝነው ለዕድሜ ልክ ህመም ለሆኑት የአንጎል ውድመትና የልብ በሽታን ሲያጋልጥ ባስ ሲልም ሕይወታችንን ሊያሳጣን የሚችል አደገኛ ጋዥ ነው:: ✍️ እንደ አሜሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል መረጃ መሠረት የከሰል ጭስ ወይም ካርበን ሞኖክሳይድ በአይን የማይታይና ሽታ አልባ መርዛማ ጋዝ ነው፡፡ ➡️ካርበን ሞኖክሳይድ የሚፈጠረው ጋዝ፣ዘይት፣ ከሰል ወይም እንጨት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ባለማለቃቸው የሚፈጠር ነው፡፡ ✍️የእንጨት ከሰል (charcoal) የመኪና ጭስና ሲጋራ ይህንኑ ካርበን ሞኖክሳይድ በማመንጨት ይጠቀሳሉ፡፡ ከሰልን ጨምሮ የካርበን ምንጭ የሆኑ እንደ ጋዝ ስቶቭ፣ውሃ ማሞቂያ፣ የቤት ማሞቂያ፣የምግብ ማብሰያ ምድጃዎች በሙሉ በአግባቡ ካልተገጠሙ፣በአግባቡ ካልተጠገኑና ነፋስ የማያገኛቸው ጥብቅብቅ ያለቦታ ከተቀመጡ ችግሩን ሊያከትሉ ይችላሉ፡፡ ✍️የከሰል ጭስ ወይም ካርበን ሞኖክሳይድ ወደ ውስጣችን በምንስበብት ወቅት በቀጥተ በደማችን ውስጥ በመግባት የቀይ የደም ሕዋስ አካል የሆነውና ኦክስጅን ተሸክሞ ለለተያዩ የሰውነታችን ክፍል ከሚያደርሰው ሂሞግሎቢን ጋር በመቀላቀል ካርበኦክሲሄሞግሎቢን ይሆናል፡፡ ➡️ይህ ከሆነ በኃላ ደማችን ኦክሰጅን መሸከሙን ያቆማል፡፡ በዚህ የተነሳ ሕዋሳቶቻችንና የሕዋሳቶቸችን አነስተኛ ክፍሎች ይጎዳሉ፤ይሞታሉ፡፡ህይወታችንንም እናጣለን:: በመሆኑም  በከሰል ጢስ  ምክንያት በርካቶች በዝምታ እየሞቱ  በመሆኑ ጥንቃቄ እናድርግ የሚለው ምክራችን ነው:: ⭐️ዝምተኛው ገዳይ የከሰል ጭስ(CO)ስንቶች እንደዋዛ ሞቱ ጥንቃቄ እናድርግ ቻናላችን ይህ ነው 👇👇👇👇 https://t.me/dam76

Lesperance 2015 - Telegram 频道 @lesperans 的统计与分析