fa
Feedback
ዕቡህ ብዕር

ዕቡህ ብዕር

رفتن به کانال در Telegram

በ ዕቡህ ብዕራችን የሁሉንም ደጃፍ እያንኳኳን ስሜቶቻቸውን እንዳስሳለን. ብዕራችን ያቀለመውን በግጥም እያዋዛን ለእናንተ እናደርሳለን. ✍️ እንኳን ደህና መጣቹ ለማንኛውም ሀሳብ ፣ አስተያየት እና ጥያቄ @Tirrubel @ediwub @poempen ልታናግሩን ትችላላቹ🖋️

نمایش بیشتر
1 510
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-47 روز
-930 روز
آرشیو پست ها
#Question_of_the_day ህይወታችው ውስጥ ትልቅ ዋጋ የሰጣችሁት ደማቹ የሆነ ሰው ሊታለፍ በሚችል ምክንያት ብትጋጩ እና በሞት እና በህይወት መካከል እንዳላቹ እና ከመጨረሻ እስትንፋሳቹ በፊት ከእሱ ጋር ሰላም ለመሆን ስትሉ ተበድላቹ ይቅርታ ብትጠይቁና ቢገፋቹ ምን ታረጋላቹ? ነገ ላይ ወደ ህይወታቹ ልመለስ ቢል ትቀበሉታላቹ? መልሱልኝ Comment @ebuhbhr

‎ብታጭ ለምስራች ታበስረኝ ብትመጣ ‎ስለ አለማመኔ ‎እንደ ዘካርያስ ዲዳነት ነው የኔ ዕጣ ‎ይኩነኒ አላልኩም እንደ እመአምላክ ‎ከአምላክ ፊት የሚቆም ቢላክልኝ መልዓክ ‎ታንኳ ተሰዶልኝ ማህበሉን ማለ
ብታጭ ለምስራች ታበስረኝ ብትመጣ ‎ስለ አለማመኔ ‎እንደ ዘካርያስ ዲዳነት ነው የኔ ዕጣ ‎ይኩነኒ አላልኩም እንደ እመአምላክ ‎ከአምላክ ፊት የሚቆም ቢላክልኝ መልዓክ ‎ታንኳ ተሰዶልኝ ማህበሉን ማለፊያ ‎እኔን ሚያሳስበኝ ወጀቡን መቅዘፊያ ‎ገብርኤል ገብርኤል መልዓከ ራማ ‎ለደረቀ ልቤ ቃሉን ለተጠማ ‎ላላመነ ነፍሴ ገድሉን እየሰማ ‎ድረስለት ፈጥነህ! እርዳው አለማመኔን ‎ለውጥልኝ ስሜን ! ‎ [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel

پیام صوتی21:42

پیام صوتی03:06

پیام صوتی16:45

የ self development መፅሀፍ ይፈልጋሉ እንግዲያውስ ይቀላቀሉ https://t.me/Amharic_Books_storee
የ self development መፅሀፍ ይፈልጋሉ እንግዲያውስ ይቀላቀሉ https://t.me/Amharic_Books_storee

#ስጠኝ_ስትሰጥ_አይቻለሁ የእናቴ የሁልጊዜ ጸሎት ነች ።አንድ ቀን እንዲህ ብዬ ጠየኳት? “የሽዬ ይችን ጸሎት ትወጃታለሽ ለምንድን ነው የምትደጋግሚያት?” “አይ ልጄ ይስጠኝ ሲሰጥ.... አይቸዋለሁ” “አምላክን ነው ?” “እና አባትህን ነው ?” ስቄ ዝም አልኩ .....ከትንሽ ቆይታ በኋላ እንዲህ ተረከችልኝ “ድሮ ነው ያኔ በደጉ ዘመን አንድ ድሃ ገበሬ ነበር። ጫካ ገብቶ እንጨት ሰብሮ ተሸክሞ ከተማ አምጥቶ ሸጦ ቤተሰቡን የሚያስተዳድር .... አንዴ ታዲያ እንደተለመደው እንጨቱን ሰብሮ ተሸክሞ ወደ ቤቱ ሊሄድ ሲል ይደክመውና አንዱ ዛፍ ስር ደገፍ ይላል ። ከቆይታዎች በኋላ ሙዳ ስጋ የያዘ ትልቅዬ አሞራ ሰውዬው ከተቀመጠበት ዛፍ ፊት ለፊት ካለ ዛፍ ያርፍና በማንቁርቱ ሊበላ ሲጣደፍ ድንገት ስጋው ይወድቃል ይሄኔ እጥፍጥፍ ብሎ ተኝቶ የነበረ አንድ ከሲታ ውሻ አይኖቹን ባለማመን ሙዳ ስጋ ው ላይ ዘሎ ይከመርና እየተጣደፈ መብላት ሲጀምር ያ ምስኪን ሰው ይመለከታል ወደ ሰማይ አንጋጦም እንዲህ ይላል። . “አይ እግዛብሄር አንተኮ ታላቅ ነህ .....በርሃብ ሊሞት የነበረውን ውሻ እንዲህ በጥበብ ትመግበው ....ስራህ ግሩም ነው። እግዚአብሄር ሆይ እንግዲህ ስትሰጥ አይቼሃለሁና ለኔም ስጠኝ ....ስጠኝ ስትሰጥ አይቼሃለሁ” ብሎ ተናግሮ እንጨቱን ትቶ ባዶ እጁን ቤቱ ይደርሳል ባለቤቱም ያየችውን ባለማመን “አንተ ሰውየ ቤት ውስጥ የሚበላ ነገር እንደሌለ እያወክ እንዴት የሚሸጥ እንጨት ሳትይዝ ትመጣለህ?” “አይዞሽ አትፍሪ ይስጠኝ ሲሰጥ አይቸዋለሁ” ብሎ ጠፍር አልጋ ላይ ወጥቶ ተኛ:: ሚስት በቁጣ እየለፈለፈች ቀኑ መሸ:: ሊነጋጋ ሲል በአቆማዳ የሞላ ጠገራ ብር ሰርቆ ሲሮጥ የነበረ ሌባ አባራሪዎቹ እየደረሱበት እንደሆነ ሲያውቅ ከሰውዬው ጎጆ በራፍ ላይ አስደግፎት ይሮጣል። በማለዳ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ የምትወደው የምስኪኑ ገበሬ ሚስት የጎጆዋን በራፍ ስትከፍት በአቁማዳ የሞላው ጠገራ ብር ወደቤቷ ግልብጥ ብሎ ይደፋል። . ይሄኔ ሃይለኛ እንቅልፍ ላይ የነበረውን ባለቤቷን ጸሎትህን ሰምቶሃል ተነስ ብላ ቀሰቀሰችው ምስኪኑም ያየውን ባለማመን “እግዚአብሄር ሆይ አመሰግንሃለሁ .... አሁንም ስጠኝ ሰትሰጥ አይቸሃለሁ” አለ ይባላል ልጄ፡፡ ከ TikTok ገፅ ( Abeni 🥰 ) ሳነብ ካገኘውት @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel

#ኪዳን ( የመጨረሻ ክፍል ) አጭር ኢ-ልቦለድ ታሪክ . በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ . #ለመመለስ_አልረፈደም ክርስቶስ ሲሰቀል ሐዋርያት የተባሉት ሳይሆኑ ኃጥዓን ተብለው የተገፉት ናቸው ከስሩ የተገኙት ! ፀሃፊ እና አንባቢ :-  [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel

ለምናልባት ቦታ......... 😌 ወላጅ እናትህ በድገት ብትከዳህ ያፀድቃል ያልከው ሲኦል ቢነዳህ ለፈውስ የዋልከው አጉል ቢጎዳህ የስካሁን ውሎ የስኮሁን ኑሮ ቅዠት ነው ቢባል አስበህዋል⁈ አለህ ወይ
ለምናልባት ቦታ......... 😌 ወላጅ እናትህ በድገት ብትከዳህ ያፀድቃል ያልከው ሲኦል ቢነዳህ ለፈውስ የዋልከው አጉል ቢጎዳህ የስካሁን ውሎ                      የስኮሁን ኑሮ ቅዠት ነው ቢባል አስበህዋል⁈ አለህ ወይ ትከሻ አለህ ወይ መሸሻ ህመም ማስታገሻ አለህ ወይ ምንአልባት ማረፍያ ምቶንህ በዛ ጭቅ ሰአት ? ሙሉ አለም አትስራ አበጅለት ክፍተት ልክ ሆነህ አትኑር አክልበት ስተት ነፍስህ ይደናበር ዝግ ልብህን ስበር አፍርስ ግርግዳውን ለመስኮትና በር ሂወት ፀጋ ስትችር ያኔ እድትቀበል። ቻናሉን ይቀላቀሉ፧።~👇👇👇👇👇 @love_words_qutes @love_words_qutes @love_words_qutes https://t.me/love_words_qutes

<< ስትሞት ቀድመህ ምታደርገው ምንድነው >> ስትል ጠየቀችኝ ! መጨረሻዬ ምንም ሆነ ምን ለአምላኬ የማቀርበው አንድ ተማፅኖ ይኖረኛል! << ምን የሚል ? >>
<< ስትሞት ቀድመህ ምታደርገው ምንድነው >> ስትል ጠየቀችኝ ! መጨረሻዬ ምንም ሆነ ምን ለአምላኬ የማቀርበው አንድ ተማፅኖ ይኖረኛል! << ምን የሚል ? >> በማርያም አንድ ጊዜ መታቀፍን ! በማርያም አንድ ጊዜ መነካትን ! በማርያም አንድ ጊዜ ልጄ መባልን ! በማርያም አንድ ጊዜ መዳሰስን ! ተማፅኖዬ ይሄ ነው ! << መንግሥትህን አውርሰኝ ትላለህ ብዬ ስጠብቅ ነበር ! >> አቅፋ ለገሃነም እንደማትሰጠኝ አውቃለሁ! በእሷ ተዳስሼ ሲዖልም ብገባ ጠረኗ ገነት ሆኖ ያቆየኛል! [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel

#በውበት_አትለካ ከማትገምቱት ሰው ጋር Collab አድርገናል ✨✍️ ተጋበዙልን ፀሐፊ :- [ ጥሩቤል ] አንባቢ :- @Mcole ( ሚኪ ✍️ ) X [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel

#Special_Life_Lesson ይኼን Life Lesson የሰማ ብዙ ያተርፈበታል ከሁሉም Life Lesson Special የሆነ ነው የምር አድምጡት ብዙ ታተርፉበታላቹ [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel

#ኪዳን ( ክፍል - 2 ) አጭር ኢ-ልቦለድ ታሪክ . በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ . ፀሃፊ እና አንባቢ :-  [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel

#ኪዳን አጭር ኢ-ልቦለድ ታሪክ . በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ . የመጀመሪያ አጭር ድርሰቴ ነው ሀሳባቹን አሳውቁኝ ✨ ፀሃፊ እና አንባቢ :- [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel

አጀብ ዘንድሮ ሰይጣንም ጭምር ነው ስራ የፈታው.....የዘመኑ ሰው ለመንፈስም አልመች ብሏል። ቀጣዩ የተቃውሞ ሰልፍ ከሲዖል Broadcast መደረጉ አይቀሬ ነው ። [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel