1 839
المشتركون
+2724 ساعات
+1477 أيام
+34030 أيام
أرشيف المشاركات
1 837
#ያለ_ዕሜዬ_አረጀሁ
አሁን አሁን የማየው ሁሉ ያበግነኛል....የምሰማው ሁሉ ያንገበግበኛል። ያለ ዕድሜዬ ሸምግያለሁ...ሁሉ ክብሩን ጥሏል...እውር እውርን ይመራል። ግልምጫ የሚፈሩ ህፃናት በአፈ ታሪክ ቀርተዋል...የአሁኖቹ ለወለዷቸው ወላጆች ናቸው።
.
የተወለደ ህፃን ከእናቱ ጡት ቀድሞ ስልጡን የተባለ ስልክ ይጨብጣል። ቤተሰብ አይተዋወቅም....በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ባይተዋሮች ናቸው።
ቤተክርስቲያን መሄድ Hobby ከሆነ ሰንብቷል....አምላኬ አምላኬ ሲል የተገኘ የፋርነት ኒሻንን ይለብሳል.....ባለ ሽበቱ እንደ ወጣት ይፈነጥዝ እኔ ያለ ዕድሜዬ ሽበት ቸቀዳጀው።
1 837
ከአስር ዓመት በኃላ ተገናኙ....እሷ የጓደኛዋን ልደት ልታከብር እሱ ከባሌቤቱ ጋር እራት ሊበላ። አየችው! ነው ? አይደለም በሚል ጥርጣሬ ከስር እስከታች ተመለከተችው....የፈሩት ይደርሳል የናቁት ይወርሳልም አይደል የሚባለው...እራሱ ነው። ደነገጠች ! ድንጋጤዋን ያስተዋሉ ጓደኞቿም ጥያቄ ሰነዘሩ " ምን ሆነሽ ነው ? አሞሽ ነው ? " አረ ምንም ደህና ነኝ ብላ ከፊቷ የነበረውን ውሃ ጨለጠችው። ብርጭቆውን ለማስቀመጥ አስባ ስታው መሬት ወደቀ የስባሪው ድምፅ ትኩረት ሳበ። ያኔም እሱም ድምፁን ተከትሎ ወደዛ አቅጣጫ ሲዞር አያት....እሷ መሆኗን ለማስተዋል ጊዜ አልፈጀበትም....ባለቤቱ ያቺ (.....) ናት አይደል ? አለችው። ስያሜው ባይገባትም አዎ ልክ ነሽ ብሏት ፈገግ አለ።
.
.
" እግዚአብሔር ከዚህ ሁሉ ዓመት በኃላ ያገናኛቹ በምክንያት ቢሆንስ ለምን አታወራትም ? " ስትል ጠየቀችው።
እያጣጣርኩኝ ውሃ ለነሳኝ
በሙት አልጋዬ ለሞት ለረሳኝ
ምህረት አርጌ ሁሉን ምን ባልፍም
በገዳይ ብዕር ታሪክ አይፃፍም
ሲል መለሰላት.....
" ግን እኮ ! " ሀሳቧን ሳትጨርስ አስቆማት.....ይኸውልሽ ዓለሜ ይቅር ማለት ግዴታችን ነው....ምሮ ያን ሰው ህይወታችን ውስጥ ማስቀጠል ግን ምርጫችን ነው።
" ታድያ ምኑን ይቅር አልክ...ይቅርታ አርጊያለሁ ግን ህይወቴ ውስጥ አትኖርም ሚሉት ፈሊጥ ምንድነው " ? ጥያቄዋ ነበር
አበባዬ ይቅርታ ማለት ስለ ቀደመ በደል የሚለገስ ምህረት እንጂ ስለ ወደፊት የህይወት ጉዞ የሚሰጥ ማረጋገጫ አይደለም። ይቅር ስል ስለቀደመው ነው....ሳቆይ ግን ስለ ፊተኛው ነው።
" ግን እኮ የሰው ልጅ ይለወጣል በነበረበት አይቀጥልም....ተለውጣ ቢሆንስ ? "
ልክ ነሽ የሰው ልጅ ይለወጣል...ግን ህይወት ላይ ቢሆንስ የሚባል ነገር አይሰራም። ከሆነ መልካም ነው ያ ሰው ወደፊት ያን ስህተት እንዳይሰራ መስመር ይሆነዋል...እንደ እኔ ግን
የቆረጠኝን ብርጭቆ ብምረውም ብርጭቆ መቁረጥ እንደሚችል ግን አረሳም ያ ነው ልዩነቱ።
" እግዚአብሔር በዚህ ውሳኔህ ደስተኛ የሚሆን ይመስልሃል ? "
ይቅር በል እንጂ የበደሉህን ሁሉ ምረህ ህይወት ውስጥ አቆያቸው ብሎ የተናገረበት ክፍል ትዝ አይለኝም..... ተምሮ እንደ ቆመ ሰው መማር ግዴታዬ ነው....ግን ልብ ካልሽ የነዛን ሰዎች True Color ከጅምሩ Expose ያረገውም እራሱ እግዚአብሔር ነው።
ይልቅ እንውጣ...ሰዓቱ ሄዷል ልጃችንም ናፍቃኛለች እማዬም ማረፍ አለባት አናመሽም ብለን ነው አደራ ሰጥተናት የወጣነው....በዛ ላይ እሷም ሳታየኝ አትቀርም ትንሽ ተደነባብራለች....መኖሬ ለሰው ጭንቀት እንዲሆን አልፈልግም።
" እሱን ብታስብ ኖሮማ...."
ውሳኔዬን አክብሪ ! ምትይው ነገር ቢሆን ካንቺ በላይ ደስተኛው እኔ ነኝ...ያን ጊዜ እንዴት እንዳለፍኩት ታውቂያለሽ ስለዚህ please ወደ ጎጇችን ወደ ኑሯችን እንመለስ።
" የራስህ ጉዳይ...ደረቅ ነህ ድርቅ ያልክ " እጇን ሲይዛት ልቀቀኝ አለችው። እንደምንም በቀልድ አባብሎ ተቃቅፈው በፊትለፊቷ እየተሳሳቁ አለፉ።
ልታናግረው ፈልጋ ነበር.....የስራዋ ፀፀት ግን አላስጠጋትም....ይቅር እንዳላት ታውቃለች። በሞት አፋፍ ሳለ ለሞት የጣለችው ነፍስ ቆሞ እራሱን ችሏል። አይጠቅመኝም ብላ ቆርጣ የጣለችው ስጋዋ ብቻውን ሰው ወጥቶታል።
በስተመጨረሻም የተናቀው ሲነሳ የናቀው ወደቀ...በቀል የኔ ነው ያለው አምላኩ ፊቱ ተበቅሎ አሳየው።
[ ጥሩቤል ]
ልጅቷ ለልጁ ምን እንደነበረች / ምን ልትሆን እንደምትችል ግምቱን ለእናንተ ተውኩት
@ebuhbhr
@ebuhbhr
@tirrubel
1 837
አዲስ አበባ በክረምት ማምሻ ከልዩ ውበቷ ጎን ለጎን፣ ሰዎችን በለሆሳስ የምትውጥ ግዙፍ ምስጢር አላት። በቦሌ ሚካኤል አካባቢ የምትገኘው አንዲት ትንሽ እና ጸጥ ያለች የፎቶ ስቱዲዮ የበር መዝጊያ ላይ አንኳኳሁ። ሰዓቱ ከሌሊቱ አራት ሰአት አልፏል፤ ከውጭ የሚወርደው ቀዝቃዛ ጠል አጥንቴን ሰንጥቆታል።
በሩ በጭንቀት ስሜት በትንሹ ተከፈተ። የቤቱ ባለቤት ኤልያስ ነበር፤ ፊቱ ላይ ያለው የድንጋጤ ጥላ እንደተለመደው አይደለም። ዓይኖቹ ቀልተዋል፣ በሁለት እጆቹ የያዛቸው ወረቀቶች ይንቀጠቀጣሉ።
«ገባህ እንዴ? እሷስ?» አለኝ ድምፁ ተናንቆ።
«እሷ... መንገድ ላይ ነች፤ ትንሽ ታዘገያለች» አልኩት የውስጤን መረበሽ ላለመታዘብ እየሞከርኩ።
ኤልያስ ግን የያዘውን አንድ አሮጌ ፖስታ ወደ እኔ እየወረወረ፡- «ውሸትህን ነው። መቅደስ አሁን ከዚህ ከንብረት ባለቤትነት ጋር የተያያዘውን ውል ፈርማለች፤ ግን ላንተ ልታደርስልህ ያሰበችው መልእክት ይህቺ ፎቶ ናት» አለኝ።
ፖስታውን ተንቀጥቅጬ ከፈትኩት። ከውስጡ የወጣው ፎቶ እጄን አቃጠለኝ።
ፎቶው ላይ የምታየው... በትክክል ትናንት ማታ እኔና ኤልያስ የተነጋገርንበት ምስጢራዊ እቅድ አይደለም። ፎቶው ላይ ያለው እይታ—እኔ በህይወቴ ፈጽሞ ሄጄ የማላውቀው፣ የከተማዋ ጫፍ ላይ ባለ አንድ ባልታወቀ የቆርቆሮ ቤት ውስጥ፣ በትክክል ከሠዓታት በፊት የተነሳ ነው። እናም በፎቶው ዳርቻ ላይ የሚታየው የእጅ ሰዓት እኔ የምለብሰው ሳይሆን... የኤልያስ ነበር!
ኤልያስ ሽጉጡን አቀበለኝና በለሆሳስ «አሁን ሦስታችን ብቻችንን ነን... አንዱ ልናስወግደው የሚገባው አካል አለ» አለኝ።