fa
Feedback
Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

رفتن به کانال در Telegram

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Dr. Eyob Mamo

کانال Dr. Eyob Mamo (@dreyob) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 79 288 مشترک است و جایگاه 1 962 را در دسته آموزش و رتبه 379 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 79 288 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 30 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 297 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 10 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 13.05% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 5.76% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 10 350 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 4 570 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 77 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 01 ژوئیه, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته آموزش تبدیل کرده‌اند.

79 288
مشترکین
+1024 ساعت
+407 روز
+29730 روز
آرشیو پست ها
ስድስት ቀን ብቻ ቀረው !!! Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሐምሌ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ጀምሮ መጨረስ” የተሰኘው ነው፡፡ የአንዳንዶቻች
ስድስት ቀን ብቻ ቀረው !!! Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሐምሌ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ጀምሮ መጨረስ” የተሰኘው ነው፡፡ የአንዳንዶቻችን ችግር አንድን ነገር ለመጀመር አለመቻል ነው፡፡ የሌሎቻችን ደግሞ የጀመርነውን የመቀጠልና የመጨረስ ችግር ነው፡፡ አንዳንዶቻችን ግን የጀመርነውን ብንጨርሰውም በታቀደበት ጊዜና ጥራት ያለመጨረስ ችግር አለብን፡፡   ይህ መጽሐፍ፣ እነዚህንና ጀምሮ ከመጨረስ ጋር የሚነካኩ ሌሎች ወሳኝ ነጥቦችን ያነሳል፣ ተግባራዊ መመሪያም ይሰጣል፡፡ መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡ የንባብ ወር - ሐምሌ / 2018 ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ጀምሮ መጨረስ” ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሐምሌ 1 / 2018 ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሐምሌ 30 / 2018 ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!

የመላቀቅ መርሆች ("Principles of detachment") (ክፍል ሶስት) ይህንን ትምህርት ስንጀምር እንዲህ ብለን ነበር፡- ጤናማ ካልሆኑ ተጽዕኖዎች ለመላቀቅ በጣም ውጤታማ ከሆኑ መንገዶች አን
የመላቀቅ መርሆች ("Principles of detachment") (ክፍል ሶስት) ይህንን ትምህርት ስንጀምር እንዲህ ብለን ነበር፡- ጤናማ ካልሆኑ ተጽዕኖዎች ለመላቀቅ በጣም ውጤታማ ከሆኑ መንገዶች አንዱ አንድን ነገር ማቆም ብቻ ሳይሆን፣ በምትኩ የተሻለ ነገር መተካት ነው። ዘላቂ ለውጥ የሚመጣው ዝም ብለን አሮጌ ልማዶችን ለማስወገድ ከመሞከር ይልቅ፣ ሆን ብለን አዳዲስ የአኗኗር ዘይቤዎችን ስንፈጥር ነው። ባለፈው የተመለከትናቸው፣ 1) “መርዛማ (Toxic) ከሆነ ወዳጅነት ወይም ግንኙነት መላቀቅ” እና 2) ”ቁጥጥር ከሌለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መላቀቅ” የሚሉትን ነው፡፡ ዛሬ የምንመለከተው፣  “አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ቦታዎች መላቀቅ” የሚለውን ነው፡፡   አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ቦታዎች መላቀቅ ተግባራዊ ሐሳቦች ✅ ሁልጊዜ ለመጥፎ ውሳኔዎችና ተግባሮች የሚያጋልጠንን ቦታዎች መለየት። ✅ አስፈላጊና ጠቃሚ ካልሆነ በስተቀር ወደዚያ አካባቢ ከመሄድ መቆጠብ። ✅ ጊዜን በጤናማ እንቅስቃሴዎችና ተግባሮች እንዲሞሉ ፕሮግራም ማውጣት። ✅ ለዕድገት በሚረዱ ቦታዎች ብዙ ጊዜ ማሳለፍ (መንፈሳዊ ቦታ፣ ቤተ መጻሕፍት፣ የአካል ብቃት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ ፓርኮች፣ በጎ ፈቃድ ሥራዎች) ✅ ጥበብ የተሞላበት ምርጫ ለማድረግ የሚያበረታቱ ሰዎችን (ተጠያቂነትን የሚሰጠን አጋር) ማዘጋጀት። ✅ ወደዚያ ስፍራ የመሄድ ስሜት ሲመጣ በቁርጠኝነት መቋቋም፡፡ የራስ-በራስ ጥያቄ ❓ መሄድ የማይገባኝ ተገቢ ያልሆነ ቦታ እንድሄድ ተጽእኖ ያደረገብኝ የስነ-ልቦና ፍላጎት ምንድን ነው? ❓ ወደዚያ ስፍራ ለመሄድ የምነሳሳው የትኛው ቀንና ሰዓት ነው? ❓በዚህ ቀንና ሰዓት ምን አይነት ነገር ላይ ማተኮር እችላለሁ? https://m.youtube.com/user/naeleyob623

የመላቀቅ መርሆች ("Principles of detachment") (ክፍል ሁለት) ይህንን ትምህርት ስንጀምር እንዲህ ብለን ነበር፡- ጤናማ ካልሆኑ ተጽዕኖዎች ለመላቀቅ በጣም ውጤታማ ከሆኑ መንገዶች አን
የመላቀቅ መርሆች ("Principles of detachment") (ክፍል ሁለት) ይህንን ትምህርት ስንጀምር እንዲህ ብለን ነበር፡- ጤናማ ካልሆኑ ተጽዕኖዎች ለመላቀቅ በጣም ውጤታማ ከሆኑ መንገዶች አንዱ አንድን ነገር ማቆም ብቻ ሳይሆን፣ በምትኩ የተሻለ ነገር መተካት ነው። ዘላቂ ለውጥ የሚመጣው ዝም ብለን አሮጌ ልማዶችን ለማስወገድ ከመሞከር ይልቅ፣ ሆን ብለን አዳዲስ የአኗኗር ዘይቤዎችን ስንፈጥር ነው። ባለፈው የተመለከትነው፣ “መርዛማ (Toxic) ከሆነ ወዳጅነት ወይም ግንኙነት መላቀቅ” የሚለውን ነው፡፡  ዛሬ የምንመለከተው ”ቁጥጥር ከሌለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መላቀቅ” የሚለውን ነው፡፡ ቁጥጥር ከሌለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መላቀቅ ተግባራዊ ሐሳቦች ✅ አላስፈላጊ መተግበሪያዎችን (apps) ከስልክ መነሻ ገጽ ማስወገድ። ✅ አስፈላጊ ያልሆኑ ማሳወቂያዎችን (notifications) ማጥፋት። ✅ ዕለታዊ የስክሪን ጊዜ ገደብ ማውታትና በዚያ መመራት። ✅ በምግብ ሰዓት፣ በሥራ፣ በጸሎት እና ከቤተሰብ ጋር በሚሆኑበት ጊዜ ስልክን ማራቅ። ✅ ስልክ ከመነካካት ይልቅ በማንበብ፣ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም ትርጉም ባለው ውይይት ጊዜ ማሳለፍ። ✅ማታ ከመኝታ በፊት እና ጠዋት ከተነሳን በኋላ የአንድ ሰዓት "ከማህበራዊ ሚዲያ ነፃ" ጊዜ ማበጀት። የራስ-በራስ ጥያቄ ❓ ማህበራዊ ሚዲያን የምጠቀምበት ሆን ብዬና አስቤበት ነው ወይስ በልምድ? ❓ ስልክ በመነካካት ሰበብ ከየትኛው ስሜት ለማምለጥ እየሞከርኩ ነው? ❓ይህ የማሕበራዊ ሚዲያ ድርጊት እረፍት ይሰጠኛል ወይስ ያደክመኛል? https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሐምሌ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ጀምሮ መጨረስ” የተሰኘው ነው፡፡ የአንዳንዶቻችን ችግር አንድን ነገር ለመጀመ
Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሐምሌ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ጀምሮ መጨረስ” የተሰኘው ነው፡፡ የአንዳንዶቻችን ችግር አንድን ነገር ለመጀመር አለመቻል ነው፡፡ የሌሎቻችን ደግሞ የጀመርነውን የመቀጠልና የመጨረስ ችግር ነው፡፡ አንዳንዶቻችን ግን የጀመርነውን ብንጨርሰውም በታቀደበት ጊዜና ጥራት ያለመጨረስ ችግር አለብን፡፡   ይህ መጽሐፍ፣ እነዚህንና ጀምሮ ከመጨረስ ጋር የሚነካኩ ሌሎች ወሳኝ ነጥቦችን ያነሳል፣ ተግባራዊ መመሪያም ይሰጣል፡፡ መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡ የንባብ ወር - ሐምሌ / 2018 ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ጀምሮ መጨረስ” ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሐምሌ 1 / 2018 ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሐምሌ 30 / 2018 ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!

የመላቀቅ መርሆች ("Principles of detachment") (ክፍል አንድ) ጤናማ ካልሆኑ ተጽዕኖዎች ለመላቀቅ በጣም ውጤታማ ከሆኑ መንገዶች አንዱ አንድን ነገር ማቆም ብቻ ሳይሆን፣ በምትኩ የተሻለ ነገር መተካት ነው። ዘላቂ ለውጥ የሚመጣው ዝም ብለን አሮጌ ልማዶችን ለማስወገድ ከመሞከር ይልቅ፣ ሆን ብለን አዳዲስ የአኗኗር ዘይቤዎችን ስንፈጥር ነው። ዛሬንና የሚቀጥሉትን ሶስት ቀናት የመላቀቅ መርሆችን ከአራት ዘርፍ ዙሪያ እንመለከታለን፡፡ መርዛማ (Toxic) ከሆነ ወዳጅነት ወይም ግንኙነት መላቀቅ መርዛማ ባህሪያ ካላቸው ሰዎች ጋር መቅረብና መቆየት ለሁለንተናዊ ጤንነታችን ጠነቅቅ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ግን ከመርዛማ ግንኙነት መላቀቅ ያስቸግራቸዋል፡፡ ተግባራዊ መመሪያዎች ✅ ሁሉም ግንኙነት ለዘላለም የሚቀጥል እንዳልሆነ መቀበልና ራስን ማዘጋጀት። ✅ ግልጽ የሆነን የቀይ መስመር (personal boundary) ማበጀትና ክልከላን ማድረግ መልመድ፡፡ ✅ ለመለየት ተገቢ በሚሆንበት ጊዜ ድንገት ከመጥፋት ይልቅ ግንኙነቱን ቀስ በቀስ መቀነስ። ✅ ጤናማ እና አበረታች ከሆኑ ሰዎች ጋር ብዙ ጊዜ ማሳለፍ። ✅ ራሱን መቀየር የማይፈልግን ሰው ለመቀየር በመሞከር ጊዜንና ስሜንት ከማባከን መቆጠብ። ✅ ከሁሉም በፊት የእኛ ሰላምና ጤንነት እንደሚበልጥ በማወቅ ያንን መጠበቅና ያንንም ማድረግ ራስ ወዳድነት አለመሆኑን ማስታወስ። የራስ-በራስ ጥያቄ ❓ ይህ ግንኙነት የምፈልገውን ሰው እንድሆን ያቀርበኛል? ❓ ክብር እና ዋጋ እንደተሰጠኝ ይሰማኛል? ❓ ከዚህ ሰው ጋር ጊዜ ካሳለፍኩ በኋላ ሁልጊዜ እጨነቃለሁ፣ እጸጸታለሁ ወይም በስሜት እደክማለሁ?   https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

የመላቀቅ መርሆች ("Principles of detachment") (ክፍል አንድ)
የመላቀቅ መርሆች ("Principles of detachment") (ክፍል አንድ)

የተወደዳችሁ አንባቢዎቼ ከነገ ማለዳ ጀምሮ ለተወሰኑ ቀኖች “የመላቀቅ መርሆች” ("Principles of detachment") በሚል ርእስ ስር ጠቃሚ ሃሳቦችን አጋራችኋለሁ፡፡ 1. መርዛማ (Toxic)
የተወደዳችሁ አንባቢዎቼ ከነገ ማለዳ ጀምሮ ለተወሰኑ ቀኖች “የመላቀቅ መርሆች” ("Principles of detachment") በሚል ርእስ ስር ጠቃሚ ሃሳቦችን አጋራችኋለሁ፡፡ 1.    መርዛማ (Toxic) ከሆነ ወዳጅነት ወይም ግንኙነት መላቀቅ 2.   “ቁጥጥር ከሌለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መላቀቅ” 3.     “አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ቦታዎች መላቀቅ” 4.     “ጤናማ ካልሆኑ ልማዶች መላቀቅ” መላቀቅ ካስቸገራችሁ ሰውም ሆነ ሁኔታ የመላቀቅን ጉዞ አብረን እንጀምር፡፡ እንድታነቡ እና እንድትለወጡ ምኞቴ ነው፡፡ ወዳጆቻችሁ ይህንን ቻናል ጆይን በማድረግ አብረውን እንዲያነቡ ጋብዙ፡፡ Sweet dreams!

ግብን ማሳካት !!! ራስን የመግዛት (የዲሲፕሊን) ያላቸው እና የሌላቸው . . . ራስን የመግዛት ችሎታ ያላቸው ሰዎች፦ በረጅም ጊዜ ግቦቻቸው ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። ወደፊት ታላቅ ነገር ለማሳካት ሲ
ግብን ማሳካት !!! ራስን የመግዛት (የዲሲፕሊን) ያላቸው እና የሌላቸው . . . ራስን የመግዛት ችሎታ ያላቸው ሰዎች፦ በረጅም ጊዜ ግቦቻቸው ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። ወደፊት ታላቅ ነገር ለማሳካት ሲሉ የአጭር ጊዜ ደስታዎችን ለመሠዋት ፈቃደኛ ናቸው። ራስን የመግዛት ችሎታ የሌላቸው ሰዎች፦ ብዙውን ጊዜ ፈጣን እርካታን ይሻሉ። በጊዜያዊ ደስታዎች ወይም ችግሮች ሃሳባቸው ስለሚበታተን አስፈላጊ ግቦቻቸውን በቀላሉ ወደመተው ይሄዳሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ እናንተ እንዴት ናችሁ? Have a blessed evening!

Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሐምሌ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ጀምሮ መጨረስ” የተሰኘው ነው፡፡ የአንዳንዶቻችን ችግር አንድን ነገር ለመጀመ
Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሐምሌ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ጀምሮ መጨረስ” የተሰኘው ነው፡፡ የአንዳንዶቻችን ችግር አንድን ነገር ለመጀመር አለመቻል ነው፡፡ የሌሎቻችን ደግሞ የጀመርነውን የመቀጠልና የመጨረስ ችግር ነው፡፡ አንዳንዶቻችን ግን የጀመርነውን ብንጨርሰውም በታቀደበት ጊዜና ጥራት ያለመጨረስ ችግር አለብን፡፡   ይህ መጽሐፍ፣ እነዚህንና ጀምሮ ከመጨረስ ጋር የሚነካኩ ሌሎች ወሳኝ ነጥቦችን ያነሳል፣ ተግባራዊ መመሪያም ይሰጣል፡፡ መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡ የንባብ ወር - ሐምሌ / 2018 ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ጀምሮ መጨረስ” ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሐምሌ 1 / 2018 ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሐምሌ 30 / 2018 ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!

Book Club! With Dr. Eyob የተሰኘውን የንባብ ፕሮግራም ለመቀላቀል ስላሳዩት ፍላጎት ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ ለሐምሌ ወር ንባብ የተመረጠው መጽሐፍ፡- “ጀምሮ መጨረስ” ይህንን መጽሐፍ ለማን
Book Club! With Dr. Eyob የተሰኘውን የንባብ ፕሮግራም ለመቀላቀል ስላሳዩት ፍላጎት ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ ለሐምሌ ወር ንባብ የተመረጠው መጽሐፍ፡-  “ጀምሮ መጨረስ” ይህንን መጽሐፍ ለማንበብ የሚከፈለው ክፍያ፡- አንድ መቶ ብር (100 ብር) ብቻ! መጽሐፉን ለማንበብ ክፍያውን ሲከፍሉና screenshot ሲልኩ ለዚሁ መጽሐፍ ተመዝጋቢዎች ወደተዘጋጀው ቴሌግራም ግሩፕ እንቀላቅሎታለን፡፡ ቡድኑን ከተቀላቀላቸሁ በኋላ ከሐምሌ 1/2018 ጀምሮ መጽሐፉ በየቀኑ ሐምሌ 30 ድረስ ቴሌግራም ግሩፑ ላይ post ይደረጋል፡፡ የክፍያ መረጃ:- ንግድ ባንክ Eyob Mamo Account # 1000614499056 ቴሌብር Dr. Eyob ስልክ ቁጥር 0945087238 Thank you!

ስሜትን መቆጣጠር! ራስን የመግዛት (የዲሲፕሊን) ያላቸው እና የሌላቸው፡- • ራስን የመግዛት ችሎታ ያላቸው ሰዎች፦ በተለይም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ስሜታቸውን በሚገባ መግራት ይችላሉ። ቁጣ፣ ብስ
ስሜትን መቆጣጠር! ራስን የመግዛት (የዲሲፕሊን) ያላቸው እና የሌላቸው፡- • ራስን የመግዛት ችሎታ ያላቸው ሰዎች፦ በተለይም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ስሜታቸውን በሚገባ መግራት ይችላሉ። ቁጣ፣ ብስጭት ወይም ቅያሜ ሊሰማቸው ይችላል፤ ነገር ግን ምላሻቸውን በጥንቃቄ ይመርጣሉ። • ራስን የመግዛት ችሎታ የሌላቸው ሰዎች፦ ብዙውን ጊዜ በስሜቶቻቸው ይመራሉ። መዘዙን ሳያጤኑ በቁጣ ወይም በብስጭት ምላሽ ስለሚሰጡ ሁል ጊዜ ራሳቸውን ችግር ውስጥ ያገኙታል። በዚህ ጉዳይ ላይ እናንተ እንዴት ናችሁ?

ውሳኔ አሰጣጥ ! ራስን የመግዛት (የዲሲፕሊን) ያላቸው እና የሌላቸው: ራስን የመግዛት ችሎታ ያላቸው ሰዎች፦ ከመተግበራቸው በፊት ያስባሉ። የምርጫዎቻቸውን መዘዝ ያመዛዝናሉ፣ ውሳኔዎቻቸውንም በስሜታዊ
ውሳኔ አሰጣጥ ! ራስን የመግዛት (የዲሲፕሊን) ያላቸው እና የሌላቸው: ራስን የመግዛት ችሎታ ያላቸው ሰዎች፦ ከመተግበራቸው በፊት ያስባሉ። የምርጫዎቻቸውን መዘዝ ያመዛዝናሉ፣ ውሳኔዎቻቸውንም በስሜታዊነት ሳይሆን በጥበብ ላይ ይመሰርታሉ። ራስን የመግዛት ችሎታ የሌላቸው ሰዎች፦ ብዙውን ጊዜ አስቀድመው ይተገብራሉ፣ በኋላ ያስባሉ። ለፀፀት የሚዳርጉ ስሜታዊ ውሳኔዎችን የማድረግ እድላቸው ከፍተኛ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ እናንተ እንዴት ናችሁ! Have a restful night !

መጀመር! መቀጠል! መጨረስ! መነቃቃት (motivation) እንዲህ እንድንናስብና እንድናገር ያደርገናል 1. እችላለሁ! 2. እጀምራለሁ! 3. እቀጥላለሁ! 4. እጨርሳለሁ! ክህሎት (skill) እንዲህ
መጀመር! መቀጠል! መጨረስ!   መነቃቃት (motivation) እንዲህ እንድንናስብና እንድናገር ያደርገናል 1. እችላለሁ! 2. እጀምራለሁ! 3. እቀጥላለሁ! 4. እጨርሳለሁ! ክህሎት (skill) እንዲህ እንድናደርግ ያግዘናል 1. እንድናስብ! 2. እንድናቅድ! 3. እንድናደራጅ! 4. እንድንጀምር! ዲሲፕሊን (discipline) በዚህ መልኩ እንድንቀጥል ያስችለናል 1. የጀመርነውን ነገር እንድንደጋግመው! 2. የተቋረጠውን እንደገና እንድንጀምረው! 3. ችግራችንን በመገምገም እንድናርመው! 4. ከዋናው ዓላማ ባለመውጣት እንድንፈጽመው! እነዚህን ሂደቶች በሚገባ በመተግበር ወደላቀ ደረጃ ለመድረስ የሚያስችላችሁ መጽሐፍ የሐምሌ ወር የንባብ challenge  ሆኖ ቀርቧል፡፡ መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡ የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ጀምሮ መጨረስ”፡፡ የንባብ ወር - ሐምሌ / 2018 ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ጀምሮ መጨረስ” ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሐምሌ 1 / 2018 ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሐምሌ 30 / 2018 ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!

በፍጹም ልታፍሩባቸውና ይቅርታ ልትጠይቁባቸው የማይገባችሁ ነገሮች! ልታፍሩባቸው የሚገባችሁንና የማይገባችሁን ነገር ለዩ፡፡ ማፈር በማይገባችሁ ነገር ማፈር አቅማችሁን ያደክመዋል፣ ለመኖርና ለማድረግ ያ
በፍጹም ልታፍሩባቸውና ይቅርታ ልትጠይቁባቸው የማይገባችሁ ነገሮች! ልታፍሩባቸው የሚገባችሁንና የማይገባችሁን ነገር ለዩ፡፡ ማፈር በማይገባችሁ ነገር ማፈር አቅማችሁን ያደክመዋል፣ ለመኖርና ለማድረግ ያላችሁን ድፍረት ይነጥቃችኋል፣ ሁል ጊዜ ጥፋተኛ እንደሆናችሁና ይቅርታ መጠየቅ እንዳለባችሁ እንዲሰማችሁ ያደርጋል፣ እውነት እያላችሁ ውሸተኛ እንደሆናችሁ ያስመስልባችኋል፡፡ ማፈር በሚገባችሁ ነገር አለማፈር ደግሞ የሕብረተሰቡ እጅግ የወረደና ለምንም ቁም ነገር የማይውል “ተራ እና ተርታ” ሰው ያደርጋኋል፣ መልካም ተጽእኗችሁንም ያጠፋዋል፡፡ 1. ፈጣሪ በሰጣችሁ መልክ፣ ቁመና እና ዘር አትፈሩ! ይቅርታም አትጠይቁ! 2. በውስጣችሁ ትልቅ ዓላማ፣ ሕልም፣ ራእይህም ሆነ ግብ በመያዛችሁና በማራመዳችሁ አትፈሩ! ይቅርታም አትጠይቁ! 3. አንድን ነገር ለማሳካት ስላላችሁ የውስጥ ግለትና ጽኑ ፍላጎት አትፈሩ! ይቅርታም አትጠይቁ! 4. ከመስመር የወጣንና ጤና-ቢስን የሰዎች አጀንዳ ባለመቀበላችሁና ባለመተባበራችሁ አትፈሩ! ይቅርታም አትጠይቁ! 5. የግል ቀይ መስመራችሁን የሚጥስን የሰዎች ሁኔታ እና አቀራረብ “አምቢ” በማለት ክልከላ በማድረጋችሁ አትፈሩ! ይቅርታም አትጠይቁ! 6. ከእናንተ ጋር መሆን የማይፈልግን ሰው ለማቆየት የቻላችሁትን ካደረጋችሁ በኋላ የፈለገውን እንዲያደርገ በመልቀቃችሁና የራሳችሁን መንገድ በመሄዳችሁ አትፈሩ! ይቅርታም አትጠይቁ! ሃፍረትንና ይቅርታ መጠየቅን አስመሳይነት፣ ባሉት ነገር አለመገኘት፣ በሰው ላይ ክፉ ማሰብና ማድረግ፣ አጉል ጥቅመኛነት፣ ዘረኛነትና ኃይልና ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም ላለባቸው ሰዎች ተውላቸው! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyo

Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሐምሌ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ጀምሮ መጨረስ” የተሰኘው ነው፡፡ የአንዳንዶቻችን ችግር አንድን ነገር ለመጀመ
Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሐምሌ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ጀምሮ መጨረስ” የተሰኘው ነው፡፡ የአንዳንዶቻችን ችግር አንድን ነገር ለመጀመር አለመቻል ነው፡፡ የሌሎቻችን ደግሞ የጀመርነውን የመቀጠልና የመጨረስ ችግር ነው፡፡ አንዳንዶቻችን ግን የጀመርነውን ብንጨርሰውም በታቀደበት ጊዜና ጥራት ያለመጨረስ ችግር አለብን፡፡   ይህ መጽሐፍ፣ እነዚህንና ጀምሮ ከመጨረስ ጋር የሚነካኩ ሌሎች ወሳኝ ነጥቦችን ያነሳል፣ ተግባራዊ መመሪያም ይሰጣል፡፡ መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡ የንባብ ወር - ሐምሌ / 2018 ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ጀምሮ መጨረስ” ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሐምሌ 1 / 2018 ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሐምሌ 30 / 2018 ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!

ጉዞ ላይ ናችሁ! ያላችሁበት ሁኔታና ቦታ የማይመች፣ አሰልቺ፣ ለእናንተ የማይመጥንና “ራሴን እዚህ ቦታ አገኘዋለሁ ብዬ አላስብም ነበር” የሚያሰኝ ቢሆንም፣ “እንኳን በዚያ ሁኔታ አለፍኩ” የምትሉበትን
ጉዞ ላይ ናችሁ! ያላችሁበት ሁኔታና ቦታ የማይመች፣ አሰልቺ፣ ለእናንተ የማይመጥንና “ራሴን እዚህ ቦታ አገኘዋለሁ ብዬ አላስብም ነበር” የሚያሰኝ ቢሆንም፣ “እንኳን በዚያ ሁኔታ አለፍኩ” የምትሉበትን ሁኔታ መፍጠር ትችላላችሁ፡፡ ያንን ለመፍጠር ግን በጉዞ ላይ መሆን አለባችሁ፡፡ 1. ትምህርት፡- ካላችሁበት ሁኔታና ቦታ የምታገኙትን ሁሉ ትምህርት ውሰዱ፡፡ አንዳንድ የሕይወት ትምህርቶች በሁኔታው ካላለፋችሁ በስተቀር በፍጹም አትማሯቸውም፡፡ አንድ ልምምድ ጎጂን የባከነ የሚሆነው ትምህርት ካልተገኘበት ብቻ ነው፡፡ 2. ውሳኔ፡- ካላችሁበት ሁኔታና ቦታ ለመውጣት ተገቢውን ውሳኔ አድርጉ፡፡ ዋናው ነገር የላችሁበት ሁኔታ ሳይሆን በዚያ ላለመቆየት ያላችሁ ምርጫና ውሳኔ ጉዳይ ነው፡፡ 3. እቅድ፡- ካላችሁበት ሁኔታና ቦታ የምትወጡበትን ተገቢውን እቅድ አቅዱ፡፡ ካላችሁበት ሁኔታ ለመውጣት መወሰን ለብቻው በቂ አይደለም፡፡ በሚገባ የታሰበበትና ተግባራዊ ሊሆን የሚችልን እቅድ ከጊዜ ገደብ ጋር ማስቀመጥ የግድ ነው፡፡ 4. እንቅስቃሴ፡- ካላችሁበት ሁኔታና ቦታ ለመውጣ ተገቢውን እቅስቃሴ አድርጉ፡፡ ከትምህርቱ፣ ከውሳኔውና ከእቅዱ በኋላ፣ ባቀዳችሁት መሰረት ወቅቱን ጠብቃችሁ መንቀሳቀስ ከቻላችሁ የላቀ ማንነት ይዛችሁ መውጣታችሁ አይቀርም፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራዊ እውነታዎች ከተለማመዳችሁ ያላችሁበት ቦታ በእርግጥም የምትማሩበት፣ የምታድጉበትና ለነጋችሁ በስላች የምትወጡበት ትክክለኛ ሁኔታና ቦታ ይሆንላችኋል፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

ሁለቱ የፍርሃት አይነቶች (ክፍል ሁለት) በትናንትናው ፖስት እንዲህ ብለን ጀምረን ነበር፡- ፍርሃት ፈጣሪ ከጉዳት ሊጠብቀን የፈጠረው የሰው ልጅ ስሜት ነው። ይሁን እንጂ ሁሉም ፍርሃት አንድ አይደለም። አንዳንድ ፍርሃቶች ተገቢ እና ምክንያታዊ ሲሆኑ፣ ሌሎች ደግሞ ምክንያታዊ ያልሆኑ እና ለእድገት፣ ለእምነት እና ለጤናማ አኗኗር እንቅፋት የሚሆኑ ናቸው። በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ለግል እድገት እና ለስኬታማ ሕይወት አስፈላጊ ነው። እነዚህን የፍርሃት አይነቶች፣ 1) ምክንያታዊ ፍርሃት (Rational Fear) እና  2) ምክንያታዊ ያልሆነ ፍርሃት (Irrational Fear) ብለን እንጠራቸዋለን፡፡ ዛሬ ሁለተኛውን እንመለከታለን፡፡ 2. ምክንያታዊ ያልሆነ ፍርሃት (Irrational Fear) ምክንያታዊ ያልሆነ ፍርሃት እውነተኛ ወይም በቂ ምክንያት ሳይኖር የሚከሰት ፍርሃት ነው። ይህ ፍርሃት ብዙውን ጊዜ ከእውነተኛ አደጋ ይልቅ ከመላ-ምቶች፣ ከግምቶች፣ ከልክ በላይ ከማሰብ (overthinking) እና ከመሳሰሉት የተጋነነና የተዛባ አስተሳሰብ የሚመጣ ውጤት ነው። ምሳሌዎች፡ 💠 በቂ ዝግጅት አድርገው እንኳን በሕዝብ ፊት ከመናገር መፍራት። 💠 ምንም ማስረጃ ሳይኖር መገለልንና መገፋትን መፍራት። 💠 ገና ለገና ሊከሰቱ ይችላሉ ተብለው በሚታሰቡ ሁኔታዎች ምክንያት ውሳኔዎችን መፍራት። እንደነዚህ ያሉት ፍርሃቶች ብዙውን ጊዜ የግል እድገትን፣ አገልግሎትን፣ ግንኙነቶችን እና የስራ እድገትን ይገድባሉ። ካለን እምቅ ብቃት በታች ተቆጥበን እንድንኖር ያደርጉናል፡፡ የኋላ ኋላም ጸጸት ውስጥ ይጨምሩናል፡፡ ተገቢው ምላሽ ምክንያታዊ ያልሆነን ፍርሃት ለማሸነፍ በጣም ውጤታማው መንገድ ቀስ በቀስ በሚደረግ ድፍረት የተሞላበት እርምጃ ነው። ይህ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡ የሚፈሩትን ሁኔታ ከመሸሽ ይልቅ መጋፈጥ። 💠 አሉታዊ ወይም እውነታ የሌላቸውን ሀሳቦች መቃወም። 💠 አነስተኛ እና ሊከናወኑ የሚችሉ እርምጃዎችን መውሰድ። 💠በተደጋጋሚ ልምምድ በራስ መተማመንን መገንባት። 💠 በውስጣችን ለምናስበው ወይም ለራሳችን ለምናወራው አሉታዊ ሃሳብ ተቃራኒ አዎንታዊ ማሰብና መናገር፡፡ 💠 ፍርሃት ማንነታችንን እንዲቆጣጠር ከመፍቀድ ይልቅ፣ በእምነት እየተንቀሳቀሱ በፈጣሪ መታመን። መሸሽ ምክንያታዊ ያልሆነን ፍርሃት ያጠነክረዋል፤ ተገቢውን መጋፈጥ ደግሞ ያዳክመዋል። መርሆው ቀላል ነው፡፡ ፍርሃት እስኪጠፋ አንጠብቅም፤ ብዙ ጊዜ ፍርሃት የሚጠፋው እርምጃ ስንወስድ ነው። https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

ሁለቱ የፍርሃት አይነቶች (ክፍል ሁለት)
ሁለቱ የፍርሃት አይነቶች (ክፍል ሁለት)

Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሐምሌ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ጀምሮ መጨረስ” የተሰኘው ነው፡፡ የአንዳንዶቻችን ችግር አንድን ነገር ለመጀመ
Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሐምሌ ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “ጀምሮ መጨረስ” የተሰኘው ነው፡፡ የአንዳንዶቻችን ችግር አንድን ነገር ለመጀመር አለመቻል ነው፡፡ የሌሎቻችን ደግሞ የጀመርነውን የመቀጠልና የመጨረስ ችግር ነው፡፡ አንዳንዶቻችን ግን የጀመርነውን ብንጨርሰውም በታቀደበት ጊዜና ጥራት ያለመጨረስ ችግር አለብን፡፡   ይህ መጽሐፍ፣ እነዚህንና ጀምሮ ከመጨረስ ጋር የሚነካኩ ሌሎች ወሳኝ ነጥቦችን ያነሳል፣ ተግባራዊ መመሪያም ይሰጣል፡፡ መጽሐፉን ለማንበብ ከአሁኑ በመመዝገብ ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡ የንባብ ወር - ሐምሌ / 2018 ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ጀምሮ መጨረስ” ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሐምሌ 1 / 2018 ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሐምሌ 30 / 2018 ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!

ሁለቱ የፍርሃት አይነቶች (ክፍል አንድ) ፍርሃት ፈጣሪ ከጉዳት ሊጠብቀን የፈጠረው የሰው ልጅ ስሜት ነው። ይሁን እንጂ ሁሉም ፍርሃት አንድ አይደለም። አንዳንድ ፍርሃቶች ተገቢ እና ምክንያታዊ ሲሆኑ፣ ሌሎች ደግሞ ምክንያታዊ ያልሆኑ እና ለእድገት፣ ለእምነት እና ለጤናማ አኗኗር እንቅፋት የሚሆኑ ናቸው። በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ለግል እድገት እና ለስኬታማ ሕይወት አስፈላጊ ነው። እነዚህን የፍርሃት አይነቶች፣ 1) ምክንያታዊ ፍርሃት (Rational Fear) እና  2) ምክንያታዊ ያልሆነ ፍርሃት (Irrational Fear) ብለን እንጠራቸዋለን፡፡ ለዛሬ የመጀመሪያውን እንመልከትና ነገ ሁለተኛውን ይዤ እመለሳለሁ፡፡ 1. ምክንያታዊ ፍርሃት (Rational Fear) ምክንያታዊ ፍርሃት ከእውነተኛ እና ሊታወቅ ከሚችል የጉዳት ወይም የአደጋ ምንጭ የሚመጣ ፍርሃት ነው። ይህ ፍርሃት በምናብ ወይም በእሳቤ ላይ ሳይሆን በተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ነው። ለምሳሌ፡ 💠 በከባድ አውሎ ንፋስ ወቅት መኪና ሲነዱ መፍራትና ጥንቃቄ ማድረግ። 💠 ትልቅ የቀዶ ጥገና ከመደረጉ በፊት መጨነቅ። 💠 ምሽት ላይ አደገኛ በሆነ ሰፈር ብቻውን ከመሄድ መፍራትና መቆጠብ። እነዚህ ፍርሃቶች ጠቃሚ የጥበቃ አላማ አላቸው። እነዚህ ፍርሃቶች ወደ ድንጋጤ ከመምራት ይልቅ ጥበብን፣ ዝግጅትን እና ጥንቃቄ የተሞላበት ውሳኔ አሰጣጥን ያበረታታሉ። ተገቢው ምላሽ ለዚህ ፍርሃት መፍትሄው ችላ ማለት ሳይሆን፣ ምክንያቱን በጥበብ እና በኃላፊነት መፍታት ነው፤ ይህንንም በሚከተለው መንገድ ማድረግ ይቻላል፡ 💠 የፍርሃቱን ትክክለኛ ምንጭ መለየት። 💠 ትክክለኛ መረጃ መሰብሰብ። 💠 ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ። 💠 ጥበብ የተሞላበት ምክር መጠየቅ። 💠 ተግባራዊ ጥንቃቄዎችን መውሰድ። 💠 በኃላፊነት እየተንቀሳቀሱ በፈጣሪ መታመን። በሌላ አነጋገር፣ ምክንያታዊ ፍርሃት መሸሽን ሳይሆን ጥበብን፣ እቅድን እና ተግባርን ይጠይቃል። በነገው ፖስቴ ምክንያታዊ ያልሆነ ፍርሃት (Irrational Fear) ለተሰኘውን የፍርሃት አይነት አጠር ያለ ማብራሪ አደርጋለሁ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/