ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Dr. Eyob Mamo

Dr. Eyob Mamo

الذهاب إلى القناة على Telegram

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Dr. Eyob Mamo

تُعد قناة Dr. Eyob Mamo (@dreyob) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 79 134 مشتركاً، محتلاً المرتبة 1 960 في فئة التعليم والمرتبة 421 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 79 134 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 27 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -123، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -19، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 8.35‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 4.91‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 6 611 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 3 885 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 39.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 28 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة التعليم.

79 134
المشتركون
-1924 ساعات
+907 أيام
-12330 أيام
أرشيف المشاركات
“የምክር አሰጣጥ ክህሎቶች እና ዘዴዎች” (Counseling Skills and Techniques)!!! በመቶ የሚቆጠሩ ሰልጣኞች እየተከታተሉት ይገኛሉ፡፡ ሁለት የስልጠና ኃሙስ ምሽቶች አልፈዋል፡፡ ሁለ
“የምክር አሰጣጥ ክህሎቶች እና ዘዴዎች” (Counseling Skills and Techniques)!!!   በመቶ የሚቆጠሩ ሰልጣኞች እየተከታተሉት ይገኛሉ፡፡ ሁለት የስልጠና ኃሙስ ምሽቶች አልፈዋል፡፡   ሁለት ኃሙስ ምሽቶች ይቀሩናል፡፡ ሳይመዘገቡ የዘገዩ ሰልጣኞች አሁንም በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡ ሶስተኛው የስልጠና ቀን ነገ ኃሙስ ጥቅምት 19 ነው፡፡ ያለፈው ያመለጣችሁ audio and PDF note ግሩፑ ውስጥ ይገኛል፡፡ በዚህ ስልጠና ለመሳተፍ፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!

Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሕዳር ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “እይታ” የተሰኘው ነው፡፡ በሕይወታችን የሆነውን፣ በመሆን ላይ ያለውን እና ወ
Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሕዳር ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “እይታ” የተሰኘው ነው፡፡ በሕይወታችን የሆነውን፣ በመሆን ላይ ያለውን እና ወደፊት የሚሆነውን በአብዛኛው ነገር የሚወስነው አስተሳሰባችንና አመለከካታችን እንደሆነ ታውቃላችሁ? 📖 ስለምታስበው ነገር ተጠንቀቅ፣ ሃሳቦችህ ወደ ቃላት ይለወጣሉና፡፡ 📖 ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ፣ ንግግሮችህ ወደ ተግባር ይለወጣሉና፡፡ 📖  ስለምትተገብረው ነገር ተጠንቀቅ፣ ተግባርህ ወደ ልማድ (ባህሪይ) ይለወጣልና፡፡ 📖 ስለ ልማድህ ተጠንቀቅ፣ ልማድህ የመጨረሻ ፍጻሜህን ይወስናልና፡፡ የንባብ ወር - ሕዳር / 2019 ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “እይታ” ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሕዳር 1 / 2019 ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሕዳር 30 / 2019 ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!

በሕይወታችን የሚያስፈልጉን ሦስት ዓይነት ሰዎች 1. የምናስተምራቸው ሰዎች እነዚህ ያለንን በመስጠት እንድናድግ የሚረዱን ናቸው፡፡ ሌሎችን ስናስተምር፣ የበለጠ እንድንማር፣ ነገሮችን በጥልቀት እንድንረ
በሕይወታችን የሚያስፈልጉን ሦስት ዓይነት ሰዎች 1. የምናስተምራቸው ሰዎች እነዚህ ያለንን በመስጠት እንድናድግ የሚረዱን ናቸው፡፡ ሌሎችን ስናስተምር፣ የበለጠ እንድንማር፣ ነገሮችን በጥልቀት እንድንረዳና በግልጽ እንድናስረዳ እንገደዳለን። እነሱን ለማሳደግ እኛ ከምናስበው በላይ ማደግና መማር ሊያስፈልገን ይችላል። ሌሎችን ለማሳደግ በምናደርገው ጥረት፣ እኛም እናድጋለን። 2. እኩዮች እነዚህ በመቀበል እንድናድግ የሚረዱን ናቸው፡፡ እስከ ማንነታችን የሚቀበሉን፣ በስኬታችን ጊዜ ብቻ ሳይሆን በድክመታችንም ጊዜ ከእኛ ጋር የሚሆኑ ሰዎች ያስፈልጉናል። እንደነሱ ለመምሰል ሳንገደድ ራሳችንን በእውነት መግለጽ፣ ስህተታችንን መቀበልና ከሌሎች መማር እንችላለን። መቀበል ራሳችንን ሳንደብቅ ለማደግ ድፍረት ይሰጠናል። 3. አማካሪዎች እነዚህ በመሞገት እንድናድግ የሚረዱን ናቸው፡፡ ከእኛ የበለጠ እውቀት፣ ልምድ ወይም ችሎታ ያላቸው ሰዎች ያስፈልጉናል። እነሱ አስተሳሰባችንን ይሞግታሉ፣ ችሎታችንን እንድናሰፋ ያግዙናል፣ ከምቾት ቀጠናችን እንድንወጣ ያበረታቱናል። ጥሩ አማካሪ ዛሬ ያለንበትን ደረጃ ብቻ ሳይሆን፣ መሆን የምንችለውንም አይቶ እንድንደርስበት ይሞግተናል። ለማሳደግ የምናስተምራቸው፣ በፍቅር የሚቀበሉን እና ከዚህ በላይ እንድንደርስ የሚሞግቱን ሰዎች በሕይወታችን ያስፈልጉናል። ከሶስቱ የትኛው አላችሁ? የትኛውስ የላችሁም? https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

የዝምታ ጥበብ! ከተወለድን በኋላ መናገርን ለመማር ሁለት ዓመት ይበቃል፤ ዝም ማለትን ለመማር ግን ስልሳ ዓመት ሊፈጅ ይችላል። መናገር ክህሎት ነው፤ መቼ መናገር እንዳለብህ ማወቅ ጥበብ ነው፤ መቼ ዝ
የዝምታ ጥበብ! ከተወለድን በኋላ መናገርን ለመማር ሁለት ዓመት ይበቃል፤ ዝም ማለትን ለመማር ግን ስልሳ ዓመት ሊፈጅ ይችላል። መናገር ክህሎት ነው፤ መቼ መናገር እንዳለብህ ማወቅ ጥበብ ነው፤ መቼ ዝም ማለት እንዳለብህ ማወቅ ደግሞ ራስን የመግዛት ዲሲፕሊን ነው። ብዙ ጸጸቶች የሚጀምሩት በችኮላ ከሚሰጡ ምላሾች ነው፤ ብዙ ሰላም የምናገኘው ደግሞ ስሜታዊ በሆነንባቸው ወቅቶች ባልተላኩ መልዕክቶቻችን ነው። መቼ መናገር፣ መቼ ማዳመጥ፣ መቼስ ዝም ማለት እንዳለብን እንማር። ወደ አእምሯች የመጣው ሁሉ ከአፋችን መውጣት የለበትም፤ ወደእኛ የመጣ የሰዎች መልዕክት ሁሉም ምላሽ አይገባውም። አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ድክመት ሳይሆን፣ በተግባር የሚገለጥ ጥበብ ነው። መልካም እንቅልፍ የምወዳችሁ የሃገሬ ሰዎች!    https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር በአካል በመገናኘት የግል Counseling, Mentorship and Guidance ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ? 1. ያጋጠማችሁ ወቅታዊ አስቸጋሪ ሁኔታ ካለና በራሳችሁ ለመ
ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር በአካል በመገናኘት የግል Counseling, Mentorship and Guidance ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ? 1. ያጋጠማችሁ ወቅታዊ አስቸጋሪ ሁኔታ ካለና በራሳችሁ ለመወጣት ስላቃታችሁ እገዛ ከፈለጋችሁ፣ 2. የሕይወታችሁን ራእይ ወይም ዓላማ ባለማወቅ ከተወዛገባችሁና አቅጣጫን መያዝ ከፈለጋችሁ፣ 3. ካለባችሁ አጉል ልማድ በመውጣ አዲስ ልማድን ማዳበር ካስቸገራችሁና ምክርና ድጋፍ ከፈለጋችሁ፣ 4. መመለስ ያቃታችሁ የሕይወት ጥያቄዎች ከበዙባችሁና በአንድ ለአንድ ውይይት የመፍትሄ መንገድ ከፈለጋችሁ፣ 5. በራሳችሁ መወጣት ያልቻላችሁት የተያዩ የስሜትና የስነ-ልቦና ጥያቄዎች ውስጥ እንዳላችሁ ከተሰማችሁና ከሁኔታው ለመውጣት ምክር ከፈለጋችሁ፣ ከግል በተጨማሪም ቁጥራችሁ ከአስር ባልበለጠ ሁኔታ በመሰባሰብ የGroup Coaching and Training ጥያቄም ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ በቴሌግራም inbox በማድረግና በፌስቡክ መልእክት በመላክ ፍላጎታችሁን ማሳወቅ ትችላላቸሁ፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሕዳር ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “እይታ” የተሰኘው ነው፡፡ በሕይወታችን የሆነውን፣ በመሆን ላይ ያለውን እና ወ
Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሕዳር ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “እይታ” የተሰኘው ነው፡፡ በሕይወታችን የሆነውን፣ በመሆን ላይ ያለውን እና ወደፊት የሚሆነውን በአብዛኛው ነገር የሚወስነው አስተሳሰባችንና አመለከካታችን እንደሆነ ታውቃላችሁ? 📖 ስለምታስበው ነገር ተጠንቀቅ፣ ሃሳቦችህ ወደ ቃላት ይለወጣሉና፡፡ 📖 ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ፣ ንግግሮችህ ወደ ተግባር ይለወጣሉና፡፡ 📖  ስለምትተገብረው ነገር ተጠንቀቅ፣ ተግባርህ ወደ ልማድ (ባህሪይ) ይለወጣልና፡፡ 📖 ስለ ልማድህ ተጠንቀቅ፣ ልማድህ የመጨረሻ ፍጻሜህን ይወስናልና፡፡ የንባብ ወር - ሕዳር / 2019 ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “እይታ” ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሕዳር 1 / 2019 ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሕዳር 30 / 2019 ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!

እድገታችንን የሚወስነው! እድገታችንን የሚወስነው የሚያጋጥሙን ችግሮች ሳይሆኑ፣ ለችግሮቹ የምንሰጠው ምላሽ ነው። ችግሮች የሕይወት ክፍል ናቸው። የሰዎች እምቢታ፣ የእድል በሮች መዘጋት፣ የገንዘብ ጫና
እድገታችንን የሚወስነው! እድገታችንን የሚወስነው የሚያጋጥሙን ችግሮች ሳይሆኑ፣ ለችግሮቹ የምንሰጠው ምላሽ ነው። ችግሮች የሕይወት ክፍል ናቸው። የሰዎች እምቢታ፣ የእድል በሮች መዘጋት፣ የገንዘብ ጫና፣ ብስጭት፣ ያልተጠበቁ ለውጦችና ያልተሳኩ ዕቅዶች ሊያጋጥሙን ይችላሉ። የሚከሰቱብንን ሁኔታዎቻችንን ሁልጊዜ መምረጥ ባንችልም፣ ተስፋ በመቁረጥ ወይም በመበርታት፤ በፍርሃት ወይም በድፍረት፤ በአሉታዊነት ወይም በአዎንታዊነት መንፈስ ለመቅረብ የምናደርገው ምርጫ ወሳኝ ነው። ይህ ማለት ሕመምን መካድ ወይም ለሚያጋጥምህ ችግር ሁሉ ራሳችንን መውቀስ አይደለም። አንዳንድ የሰዎችን ሁኔታዎች ድጋፍና በቂ ጊዜ ይፈልጋሉ። እነዚህን ሁኔታዎች በመጠቀም በአስቸጋሪ ወቅቶች ቀጣዩን ትክክለኛ እርምጃ መወሰን እንችላለን። “ይህ ለምን ደረሰብኝ?” ብለን ከመጠየቅ በተጨማሪ፣ “ከዚህ ምን መማር እችላለሁ? ምን መለወጥ እችላለሁ? አሁን የምወስደው ብልህ እርምጃ ምንድን ነው?” ብለን እንጠይቅ። ሁሉንም የሕይወትህን ወቅቶች መምረጥ ባንችልም፣ እያንዳንዱን ወቅት በበለጠ ጥበብና ጽናት መምራትን መማር እንችላለን። https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሕዳር ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “እይታ” የተሰኘው ነው፡፡ በሕይወታችን የሆነውን፣ በመሆን ላይ ያለውን እና ወ
Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሕዳር ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “እይታ” የተሰኘው ነው፡፡ በሕይወታችን የሆነውን፣ በመሆን ላይ ያለውን እና ወደፊት የሚሆነውን በአብዛኛው ነገር የሚወስነው አስተሳሰባችንና አመለከካታችን እንደሆነ ታውቃላችሁ? 📖 ስለምታስበው ነገር ተጠንቀቅ፣ ሃሳቦችህ ወደ ቃላት ይለወጣሉና፡፡ 📖 ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ፣ ንግግሮችህ ወደ ተግባር ይለወጣሉና፡፡ 📖  ስለምትተገብረው ነገር ተጠንቀቅ፣ ተግባርህ ወደ ልማድ (ባህሪይ) ይለወጣልና፡፡ 📖 ስለ ልማድህ ተጠንቀቅ፣ ልማድህ የመጨረሻ ፍጻሜህን ይወስናልና፡፡ የንባብ ወር - ሕዳር / 2019 ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “እይታ” ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሕዳር 1 / 2019 ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሕዳር 30 / 2019 ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!

የመጽሐፍ አጻጻፍ ጥበብና ዘዴ The Art and Techniques of Book Writing የቡድን ኮቺንግ (Group Coaching) መጽሐፍ በመጻፍ ማስተላለፍ የምትፈልጉት መልእክት ካለና ሃሳባችሁ
የመጽሐፍ አጻጻፍ ጥበብና ዘዴ The Art and Techniques of Book Writing የቡድን ኮቺንግ (Group Coaching) መጽሐፍ በመጻፍ ማስተላለፍ የምትፈልጉት መልእክት ካለና ሃሳባችሁን አዋቅራችሁ እንዴት ለህትመት ማብቃት እንዳለባችሁ ተጨማሪ ስልጠና እና መመሪያ ከፈለጋችሁ ይህ የቡድን ኮቺንግ ሊጠቅማችሁ ይችላል፡፡ ይህ ኮቺንግ የተቀናጀ (hybrid) የመጽሐፍ አጻጻፍ የኮቺንግ ፕሮግራም ነው፡፡ ማለትም የግሩፕ ስልጠናን እና በግል የሚደረግ ኮቺንግን የቀላቀለ አቀራረብ ነው፡፡ የ online የቡድን ሥልጠና፦ ስለ መጽሐፍ አጻጻፍ መርሆዎች፣ ዘዴዎችና ሂደቶች በ online በቡድን መሰልጠን። የግል ፊት ለፊት (in person) ኮቺንግ፦ የ online ስልጠናው ሲጠናቀቅ ተሳታፊዎች በየራሳቸው የመጽሐፍ ፕሮጀክት ላይ ተመስርተው የግል እገዛና መመሪያ ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ በአካል ወይም በ online ማግኘት። ይህ የቡድን ኮቺንጉ የሚሰጠው ከ10 እስከ 15 ለሚሆኑ ሰዎች ብቻ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ሰልጣኞች ከዶ/ር ኢዮብ ጋር በግል የማሳለፍ እድል እንዲገኙ ነው፡፡ ኮቺንጉ የሚዳስሳቸው ደረጃዎች፡- 1.      የመጽሐፍ አጻጻፍ አጠቃላይ መመሪያ፡፡ 2.     በመጽሐፍ ማስተላለፍ የፈለጉትን ሃሳብ መወሰን፡፡ 3.     የመጽሐፉን ይዘትና ዝርዝር (content) እቅድ ማዘጋጀትና በሥርዓት ማደራጀት፡፡ 4.     በወጣው ንድፍና ይዘት መሰረት ለአንባቢያን ተግባራዊ መመሪያ የመስጠት ብቃት ማዳበር፡፡ 5.     የሌሎች ጸሐፊዎችን ምንጭ የመጠቀም ሂደትን መገንዘብ፡፡ 6.     ለመጽሐፉ ተስማሚ ሽፋን ገጽ የመምረጥ ሂደትን ማዳበር፡፡ 7.     ለሕትመት የማብቃት የሚያስፈልጉ ሂደቶችን መገንዘብ፡፡ ተጨማሪ መረጃ በቅርብ ይለቀቃል!

ገደብ የሚያደርግብን! ገደብ የሚያደርግብን የምንሰራቸው ስህተቶች ሳይሆኑ፣ ከስህተቶቻችን በኋላ የምናደርገው ነገር ነው! ሁሉም ሰው ስህተት ይሠራል፣ ውድቀት ያጋጥመዋል፣ አንዳንድ ውሳኔዎቹንም በኋላ
ገደብ የሚያደርግብን! ገደብ የሚያደርግብን የምንሰራቸው ስህተቶች ሳይሆኑ፣ ከስህተቶቻችን በኋላ የምናደርገው ነገር ነው! ሁሉም ሰው ስህተት ይሠራል፣ ውድቀት ያጋጥመዋል፣ አንዳንድ ውሳኔዎቹንም በኋላ ይጸጸትባቸዋል። እውነተኛው አደጋ ለው ግን ስህተት መሥራታችን ላይ ሳይሆን፣ ከስህተቱ ለመማር አለመፈለግ፣ በውርደት ስሜት ውስጥ መውደቅ ወይም ከስህተቱ ሳይማሩ ያንኑ ስህተት መደጋገም ነው፡፡ ስህተታችንን በቅንነት ከመረመርን፣ ኃላፊነትን ከወሰድን፣ አስፈላጊውን እርማት ካደረግንና ወደፊት በተሻለ ጥበብ ከቀጠልን፣ ስህተታችን የትምህርት እና የእድገት ምንጭ ሊሆን ይችላል። በስህተትህ ላይ በመጸጸት ብቻ አንቁም። ወደ ተሻለ ውሳኔ የሚያደርሰን ትምህርት አድርገን እንለውጠው። ያለፈው ሕይወታችን ለአሁኑ ሕይወታችን እና ለወደፊት ራእያችን መሰረት ሊሆን ይገባዋል እንጂ እንቅፋት ሊሆን አይገባውም፡፡ ከስህተቶቻችን ለመማርና ለመለወጥ ያለን ፈቃደኝነት የወደፊት ሕይወታችንን ለመቅረጽ ይረዳናል። ሶስቱ መርሆች፦ • መቀበል — ስህተቴን በቅንነት በመቀበል ሃላፊነት እወስዳለሁ! • መማር — ከስህተቴ ትምህርት በመውሰድ አድግበታለሁ። • መቀጠል — በተማርኩት መሠረት ወደፊት እገሰግሳለሁ። https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

የዛሬው “አራቱ የግል ሕይወት እድገት ምሰሶዎች” የተሰኘው ትምህርት ቅጂ!

Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሕዳር ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “እይታ” የተሰኘው ነው፡፡ በሕይወታችን የሆነውን፣ በመሆን ላይ ያለውን እና ወ
Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሕዳር ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “እይታ” የተሰኘው ነው፡፡ በሕይወታችን የሆነውን፣ በመሆን ላይ ያለውን እና ወደፊት የሚሆነውን በአብዛኛው ነገር የሚወስነው አስተሳሰባችንና አመለከካታችን እንደሆነ ታውቃላችሁ? 📖 ስለምታስበው ነገር ተጠንቀቅ፣ ሃሳቦችህ ወደ ቃላት ይለወጣሉና፡፡ 📖 ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ፣ ንግግሮችህ ወደ ተግባር ይለወጣሉና፡፡ 📖  ስለምትተገብረው ነገር ተጠንቀቅ፣ ተግባርህ ወደ ልማድ (ባህሪይ) ይለወጣልና፡፡ 📖 ስለ ልማድህ ተጠንቀቅ፣ ልማድህ የመጨረሻ ፍጻሜህን ይወስናልና፡፡ የንባብ ወር - ሕዳር / 2019 ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “እይታ” ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሕዳር 1 / 2019 ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሕዳር 30 / 2019 ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!

የዛሬውን ነጻ ስልጠና ለመካፈል ምን ላድርግ ለምትሉ . . . ልከ በ2፡30 እዚሁ ቻናል ላይ live stream ሲጀምር join የሚለውን በመጫን መከታተል ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ::

የዛሬው በዚሁ ቻናል ላይ የምሰጠው live stream ነጻ ስልጠና በ 30 ደቂቃ ውስጥ ይጀምራል!
የዛሬው በዚሁ ቻናል ላይ የምሰጠው live stream ነጻ ስልጠና በ 30 ደቂቃ ውስጥ ይጀምራል!

የዛሬው በዚሁ ቻናል ላይ የምሰጠው live stream ነጻ ስልጠና ከአንድ ሰዓት በኋላ - ልክ በ2፡30 ይጀምራል!
የዛሬው በዚሁ ቻናል ላይ የምሰጠው live stream ነጻ ስልጠና ከአንድ ሰዓት በኋላ - ልክ በ2፡30 ይጀምራል!

Tonight !!! ልክ ከምሽቱ 2፡30 በዚሁ ቻናል በምሰጠው live stream ስልጠና እንገናኝ!!!
Tonight !!! ልክ ከምሽቱ 2፡30 በዚሁ ቻናል በምሰጠው live stream ስልጠና እንገናኝ!!!

ዛሬ ማታ!!! ነጻ የስልጠና እድል! አራቱ የግል እድገት ምሰሶዎች! (The Four Pillars of Personal Development!) ቀን፡- እሁድ፣ ጥቅምት 15/2029 ሰዓት፡- ከምሽቱ 2፡30
ዛሬ ማታ!!! ነጻ የስልጠና እድል! አራቱ የግል እድገት ምሰሶዎች! (The Four Pillars of Personal Development!) ቀን፡- እሁድ፣ ጥቅምት 15/2029 ሰዓት፡- ከምሽቱ 2፡30 - እስከ 3፡30 የሚሰጥበት መንገድ፡- telegram live ዓላማው፡- በማንኛው እድሜም ሆነ የስኬት ደረጃ ያለ ሰው ቀጣይ እድገትን ለማግኘት የሚያስፈልጉትን አራት መሰረታዊ ልምምዶች ማብራራት፡፡ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች:- ይህንን ማሰታወቂያ ባገኛችሁበት በዚሁ telegram channel በእለቱ በመገኘት መካፈል ትችላላችሁ፡፡ የFace Book ተጠቃሚዎች:- ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀምና የዶ/ር ኢዮብ ማሞን official telegram channel በመቀላቀል ስልጠናውን መውሰድ፣ ወዳጆቻችሁም እንዲቀላቀሉ መጋበዝ ትችላላችሁ፡፡ https://t.me/Dreyob

Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሕዳር ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “እይታ” የተሰኘው ነው፡፡ በሕይወታችን የሆነውን፣ በመሆን ላይ ያለውን እና ወ
Book Reading Challenge with Dr. Eyob ለሕዳር ወር reading challenge የተመረጠው መጽሐፍ፣ “እይታ” የተሰኘው ነው፡፡ በሕይወታችን የሆነውን፣ በመሆን ላይ ያለውን እና ወደፊት የሚሆነውን በአብዛኛው ነገር የሚወስነው አስተሳሰባችንና አመለከካታችን እንደሆነ ታውቃላችሁ? 📖 ስለምታስበው ነገር ተጠንቀቅ፣ ሃሳቦችህ ወደ ቃላት ይለወጣሉና፡፡ 📖 ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ፣ ንግግሮችህ ወደ ተግባር ይለወጣሉና፡፡ 📖  ስለምትተገብረው ነገር ተጠንቀቅ፣ ተግባርህ ወደ ልማድ (ባህሪይ) ይለወጣልና፡፡ 📖 ስለ ልማድህ ተጠንቀቅ፣ ልማድህ የመጨረሻ ፍጻሜህን ይወስናልና፡፡ የንባብ ወር - ሕዳር / 2019 ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “እይታ” ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - ሕዳር 1 / 2019 ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - ሕዳር 30 / 2019 ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Join now!!!

ዛሬ ማታ!!! ነጻ የስልጠና እድል! አራቱ የግል እድገት ምሰሶዎች! (The Four Pillars of Personal Development!) ቀን፡- እሁድ፣ ጥቅምት 15/2029 ሰዓት፡- ከምሽቱ 2፡30
ዛሬ ማታ!!! ነጻ የስልጠና እድል! አራቱ የግል እድገት ምሰሶዎች! (The Four Pillars of Personal Development!) ቀን፡- እሁድ፣ ጥቅምት 15/2029 ሰዓት፡- ከምሽቱ 2፡30 - እስከ 3፡30 የሚሰጥበት መንገድ፡- telegram live ዓላማው፡- በማንኛው እድሜም ሆነ የስኬት ደረጃ ያለ ሰው ቀጣይ እድገትን ለማግኘት የሚያስፈልጉትን አራት መሰረታዊ ልምምዶች ማብራራት፡፡ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች:- ይህንን ማሰታወቂያ ባገኛችሁበት በዚሁ telegram channel በእለቱ በመገኘት መካፈል ትችላላችሁ፡፡ የFace Book ተጠቃሚዎች:- ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀምና የዶ/ር ኢዮብ ማሞን official telegram channel በመቀላቀል ስልጠናውን መውሰድ፣ ወዳጆቻችሁም እንዲቀላቀሉ መጋበዝ ትችላላችሁ፡፡ https://t.me/Dreyob

ዛሬ ከተነበበው የንባብ challenge የተቀነጨበ ላጋራችሁ፡-   ለውጥን ትሸሻለህ? ራስህን መዝነው 1.      መለወጥ የሚገባህን ጤና ቢስ ልማድ “ያን ያህል መጥፎ አይደለም” በሚል ሰበብ ለማለፍ ትሞክራለህ? 2.     የለመድከውን አጉል ነገር ለመለወጥ ስታስብ ትጨናነቃለህ? 3.     በመበላሸት ላይ ያለን አንድ ሁኔታ ለማስተካከል ለውጥ ብታደርግ ሁኔታው የበለጠ የሚባባስ ስለሚመስልህ ትፈራለህ? 4.     ለውጥን ስታመጣ በዚያ ለውጥ የመቆየት ነገር ያስቸግርሃል? 5.     በቅርብህ ያሉ ሰዎች አንተን የሚነካ ለውጥ ሲያደርጉ ለውጡ ትክክል ቢሆንም እንኳ ለውጡን መቀበል ያስቸግርሃል? 6.     አንዳንድ ነገሮችን ለመለወጥ እየተመኘህ ሂደቱን ከመጀመር ይልቅ የማስተላለፍ ልማድ አለህ? 7.     አንድን ለውጥ ብታደርግ ለውጡ የማይጸና ስለሚመስልህ ችላ ትላለህ? 8.     እንደሚጠቅምህ እያወቅህ እንኳ ከለመድከው ምቹ ስፍራ መውጣት ያስቸግርሃል? 9.     ለጥቅምህ የሚሆንን ለውጥ የማምጣት እርምጃ ከባድ ስለሚመስልህ መነሳሳቱ የለህም? 10.    አንድን ለውጥ ላለማምጣት ምክንያት ስታበዛ ራስህን ታገኘዋለህ? ከላይ ለተጠየቁት አስር ጥያቄዎች ከግማሽ በላይ ለሆኑት “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ በዚህ ምእራፍ ለተጠቀሱት ነጥቦች አስፈላጊ ትኩረት በመስጠት ለውጥን ለማስተናገድ ጥረት አድርግ፡፡   ለውጥን የመሸሽ መንስኤው ለውጥ የማይቀር ክስተት ከሆነ ከለውጥ የምንሸሽበትን መንስኤ ለይቶ በማወቅና ራሳችንን አሳምነን በማሸነፍ ወደ ፊት መዝለቅ እንችላለን፡፡ ያልተለመደውን መፍራት ከምናውቀውና ከለመድነው ሁኔታ ትንሽ እንኳ ለየት የሚልን ሁኔታ በስጋትና በጥርጣሬ እንደምንመለከተው ሁላችንም የማንክደው እውነታ ነው፡፡ ምቹውን መውደድ  የተመቸንና የተደላደልንበት ሁኔታ አለ የተባለውና የተሻለው ሁኔታ ነው ብሎ መቀመጥ እጅግ ታላቅ የሆነ ስህተት ነው፡፡ ከመለየት የሚመጣ ሃዘን ሰው በተፈጥሮው መለየት አይወድም፡፡ ከአንድ ነገር መለየት የሚባለውን ሃሳብ ከኃዘን ጋር የማያያዝ ባህሪይ አለው፡፡