fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

አለ ሕግ

አለ ሕግ

رفتن به کانال در Telegram

ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት Alternative legal enlightenment & Service Website: alehig.com https://linktr.ee/alehig WhatsApp👉 #+251920666595 Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام አለ ሕግ

کانال አለ ሕግ (@alehig) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 16 399 مشترک است و جایگاه 492 را در دسته قانونی و رتبه 2 187 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 16 399 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 01 نوامبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 145 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 3 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 21.91% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 7.49% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 3 593 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 229 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 5 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት Alternative legal enlightenment & Service Website: alehig.com https://linktr.ee/alehig WhatsApp👉 #+251920666595 Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 02 نوامبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته قانونی تبدیل کرده‌اند.

16 399
مشترکین
+324 ساعت
+157 روز
+14530 روز
آرشیو پست ها
በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) ውስጥ ግብይት እንዴት እንደሚከናወን፣ ስርዓቶቹና ሂደቶቹስ ምንድናቸው? የሚሉትን ቁልፍ ሀሳቦች በዛሬው የኢንቨስትመንት ትምህርት ክፍላችን የምንዳስሰው
በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) ውስጥ ግብይት እንዴት እንደሚከናወን፣ ስርዓቶቹና ሂደቶቹስ ምንድናቸው? የሚሉትን ቁልፍ ሀሳቦች በዛሬው የኢንቨስትመንት ትምህርት ክፍላችን የምንዳስሰው ይሆናል። በዚህ የትምህርት ክፍል፤ በገበያው ላይ የግብይት ዑደት (Trading Cycle) ክንውኖችን እና ዋና ዋና ደረጃዎችን በዝርዝር የምናይ ሲሆን፤ የግዢ እና የሽያጭ ትዕዛዞች በስርዓቱ ውስጥ እንዴት እንደሚዛመዱ፣ የግብይት አገናኝ አባላትን (Trading Members) ሚና እና ኃላፊነት እንዲሁም ግብይት ስፈጸም (Trade Execution) እና በኋላ ባሉት ሂደቶች (Post-trade Settlement and Clearing) መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ እንመለከታለን። Read More Source: Ethiopian Securities Exchange Telegram @Ethiopianbusinessdaily

የታክስ ደረሰኝ ያለመስጠት የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነት 🔵 ❶ ደረሰኝ ባለመስጠት፦ ሊሰጥ ሲገባ ደረሰኝ ያልሰጠ ታክስ ከፋይ ለእያንዳንዱ ደረሰኝ 100,000 ብር ቅጣት ይቀጣል። 🟡 ❷ ቅጣት የ
የታክስ ደረሰኝ ያለመስጠት የሚያስከትለው የሕግ ተጠያቂነት 🔵 ❶ ደረሰኝ ባለመስጠት፦ ሊሰጥ ሲገባ ደረሰኝ ያልሰጠ ታክስ ከፋይ ለእያንዳንዱ ደረሰኝ 100,000 ብር ቅጣት ይቀጣል። 🟡 ❷ ቅጣት የማይነሳ መሆኑ፦ በደረሰኝ አለመስጠት የተጣለው ቅጣት በባለሥልጣኑ ሊነሳ አይችልም። 🔵 ❸ የሽያጭ ዋጋን ማሳነስ፦ በአንድ ግብይት ላይ የተለያዩ ዋጋዎችን በመመዝገብ ወይም የሽያጭ ዋጋን በማሳነስ ደረሰኝ የሰጠ ሰው 100,000 ብር ቅጣት እና ከ5 እስከ 7 ዓመት ጽኑ እስራት ይቀጣል። 🟡 ❹ የሽያጩ ትክክለኛ ዋጋ ከ100,000 ብር በላይ ሲሆን፦ በደረሰኞቹ ላይ ከተመለከቱት ከፍተኛው የገንዘብ መጠን ጋር በተያያዘ የገንዘብ ቅጣት እና ከ7 እስከ 10 ዓመት ጽኑ እስራት ይጣላል። 🔵 ❺ ግብይት ሳይፈጸም ደረሰኝ መስጠት ወይም መቀበል፦ ከ100,000 እስከ 200,000 ብር የገንዘብ ቅጣት እና ከ7 እስከ 10 ዓመት ጽኑ እስራት ያስከትላል። 🟡 ❻ ግብይት ሳይፈጸም የተሰጠ ደረሰኝ ከ200,000 ብር በላይ ሲሆን፦ በደረሰኙ ላይ ከተገለጸው የገንዘብ መጠን ጋር እኩል የሆነ ቅጣት እና ከ10 እስከ 15 ዓመት ጽኑ እስራት ይጣላል። 🔵 ❼ ያለባለሥልጣኑ ፈቃድ የታክስ ደረሰኝ ማተም፦ ከ300,000 እስከ 500,000 ብር ቅጣት እና ከ2 እስከ 5 ዓመት ጽኑ እስራት ያስከትላል።

" የአሜሪካ ዜጋ ልጆች፣ የትዳር አጋሮች እና ወላጆች ጭምር ወደ አሜሪካ ለመምጣት ቪዛ አይሰጣቸውም ! " - የህግ ባለሙያው ሙሉአለም ጌታቸው ከዛሬ ጀምሮ ሁሉም የአሜሪካ የኢሚግራንት ቪዛዎች መስጠት
+1
" የአሜሪካ ዜጋ ልጆች፣ የትዳር አጋሮች እና ወላጆች ጭምር ወደ አሜሪካ ለመምጣት ቪዛ አይሰጣቸውም ! " - የህግ ባለሙያው ሙሉአለም ጌታቸው ከዛሬ ጀምሮ ሁሉም የአሜሪካ የኢሚግራንት ቪዛዎች መስጠት ተቋርጧል። በዚህም የአሜሪካ ዜጋ ልጆች፣ የትዳር አጋሮች እና ወላጆች ጭምር ወደ አሜሪካ ለመሄድ ቪዛ እንደማይሰጣቸው በአሜሪካ የሚኖሩ የህግ ባለሙያቅ አቶ ሙሉአለም ጌታቸው ገልጸዋል። ይህ ተግባራዊ የተደረገው #ኢትዮጵያን ጨምሮ በ75 ሀገራት ላይ የታወጀውን የጉዞ እገዳ ተከትሎ ነው። " ይሄ እገዳ ከሁሉም በላይ የአሜሪካ ዜጎችን ከሚስቶቻቸው፣ ልጆቻቸው እና ወላጆቻቸው የሚነጥል ነው " ሲሉ የህግ ባለሙያው ገልጸዋል። የአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት የውጪ ሃገር ዜጎች ዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV)ን ጨምሮ ወደ አሜሪካ ሄደው በቋሚነት መኖር ሲፈልጉ የሚሰጣቸው ቪዛ (Immigrant Visa) ሂደት ኢትዮጵያን ጨምሮ በ75 ሃገራት እንደሚቋረጥ አሳውቆ እንደነበር አይዘነጋም። #USA #VISA @tikvahethiopia

የቴምብር ቀረጥ ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር) 1. የቴምብር ቀረጥ ምንነት የቴምብር ቀረጥ በዋናነት በሰነዶች ላይ የሚጣልና የሚሰበሰብ የመንግሥት የገቢ ምንጭ ነው፡፡ 2. የቴምብር ቀረጥ ለምን ይጣላል? ቀረጡ የታክስ ፍትሃዊነትን እና የሃብት ክፍፍልን በማመጣጠን የመንግሥትን የገቢ ምንጭ ለማስፋት ያግዛል፡፡ እንዲሁም በኢኮኖሚ አውታር ውስጥ በሚፈጠር የዜጎች እንቅስቃሴ የኢኮኖሚ ዋጋ ያላቸውን ሰነዶች የማስረጃ ተቀባይነት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በቴምብር ቀረጥ አዋጅ ቁጥር 110/1990 መሠረት ቀረጡ የኪነ-ጥበብ ዕድገትን፣ የፋይናንስ ተቋሞችን እንቅስቃሴ እና የካፒታል ንብረት ዝውውርን የማገዝ ዓላማ አለው፡፡ 3. የቴምብር ቀረጥ የሚከፈልባቸው/ የሚጣልባቸው ሰነዶች 👉 የማንኛውም ንግድ ማህበር፣ የሕብረት ሥራ ማህበር ወይም የማንኛውም ዓይነት ማህበር መመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ (ከምዝገባ በፊት ወይም በምዝገባ ጊዜ)፤ 👉 ግልግል የተፈጸመበት ሰነድ ሲረጋገጥ (ውሳኔው ከመሰጠቱ በፊት ወይም በሚሰጥበት ጊዜ)፤ 👉 ማገቻ (bonds)፡- ሰነድ ሲረጋገጥበት እና ሲመዘገብበት፤ 👉 የዕቃ ማከማቻ ማረጋገጫ ሰነድ፤ 👉 ውል፣ ስምምነትና የእነዚህ መግለጫ (ከመፈረማቸው በፊት ወይም በሚፈረምበት ጊዜ)፤ 👉 የመያዣ ሰነዶች (ከባንክ ብድር ለመውሰድ፣…)፤ 👉 የህብረት ስምምነት፤ 👉 የሥራ (የቅጥር) ውል፤ 👉 የኪራይ፣ የተከራይ አከራይ እና መሰል መብት የማስተላለፊያ ሰነዶች (ውል ከመፈረሙ በፊት ወይም በሚፈረምበት ጊዜ)፤ 👉 ለማስረጃነት ማረጋገጫ የሚያስፈልጋቸው ሰነዶች (ማረጋገጫው በሚሰጥበት ጊዜ)፤ 👉 የውክልና ሥልጣን 👉 የንብረት ባለቤትነትን ማስመዝገቢያ ሰነድ (ከምዝገባው በፊት ወይም በሚፈረምበት ጊዜ) ናቸው፡፡

የቴምብር ቀረጥ ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር) 1. የቴምብር ቀረጥ ምንነት የቴምብር ቀረጥ በዋናነት በሰነዶች ላይ የሚጣልና የሚሰበሰብ የመንግሥት የገቢ ምንጭ ነው፡፡ 2. የቴምብር
የቴምብር ቀረጥ ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር) 1. የቴምብር ቀረጥ ምንነት የቴምብር ቀረጥ በዋናነት በሰነዶች ላይ የሚጣልና የሚሰበሰብ የመንግሥት የገቢ ምንጭ ነው፡፡ 2. የቴምብር ቀረጥ ለምን ይጣላል? ቀረጡ የታክስ ፍትሃዊነትን እና የሃብት ክፍፍልን በማመጣጠን የመንግሥትን የገቢ ምንጭ ለማስፋት ያግዛል፡፡ እንዲሁም በኢኮኖሚ አውታር ውስጥ በሚፈጠር የዜጎች እንቅስቃሴ የኢኮኖሚ ዋጋ ያላቸውን ሰነዶች የማስረጃ ተቀባይነት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በቴምብር ቀረጥ አዋጅ ቁጥር 110/1990 መሠረት ቀረጡ የኪነ-ጥበብ ዕድገትን፣ የፋይናንስ ተቋሞችን እንቅስቃሴ እና የካፒታል ንብረት ዝውውርን የማገዝ ዓላማ አለው፡፡ 3. የቴምብር ቀረጥ የሚከፈልባቸው/ የሚጣልባቸው ሰነዶች 👉 የማንኛውም ንግድ ማህበር፣ የሕብረት ሥራ ማህበር ወይም የማንኛውም ዓይነት ማህበር መመስረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ (ከምዝገባ በፊት ወይም በምዝገባ ጊዜ)፤ 👉 ግልግል የተፈጸመበት ሰነድ ሲረጋገጥ (ውሳኔው ከመሰጠቱ በፊት ወይም በሚሰጥበት ጊዜ)፤ 👉 ማገቻ (bonds)፡- ሰነድ ሲረጋገጥበት እና ሲመዘገብበት፤ 👉 የዕቃ ማከማቻ ማረጋገጫ ሰነድ፤ 👉 ውል፣ ስምምነትና የእነዚህ መግለጫ (ከመፈረማቸው በፊት ወይም በሚፈረምበት ጊዜ)፤ 👉 የመያዣ ሰነዶች (ከባንክ ብድር ለመውሰድ፣…)፤ 👉 የህብረት ስምምነት፤ 👉 የሥራ (የቅጥር) ውል፤ 👉 የኪራይ፣ የተከራይ አከራይ እና መሰል መብት የማስተላለፊያ ሰነዶች (ውል ከመፈረሙ በፊት ወይም በሚፈረምበት ጊዜ)፤ 👉 ለማስረጃነት ማረጋገጫ የሚያስፈልጋቸው ሰነዶች (ማረጋገጫው በሚሰጥበት ጊዜ)፤ 👉 የውክልና ሥልጣን 👉 የንብረት ባለቤትነትን ማስመዝገቢያ ሰነድ (ከምዝገባው በፊት ወይም በሚፈረምበት ጊዜ) ናቸው፡፡

በELMIS ፕሮጀክት ላይ የተፈጸመ የሙስና ወንጀል ምርመራ አጣርቶ ክስ መመስረቱን ፖሊስ አስታወቀ ++++++++++++++++ ጋዜጣ- ፕላስ- የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ(ELMIS) ፕሮጀክት ላይ የተፈጸመ ከባድ የሙስና ወንጀል ምርመራ አጣርቶ መዝገቡን ለፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ልኮ ክስ መመስረቱን አስታወቀ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (Ethiopian Labor market information system (ELMIS)) ፕሮጀክት ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠረውን የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ የነበረው አቶ ብርሀኑ አለቃ አስገዶም እና በግብረ-አበሮቹ ላይ ከሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲያካሂድ የቆየውን ምርመራ በማጠናቀቅ ለፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ልኮ ክስ መመስረቱን አስታውቋል። ብርሃኑ አለቃ አስግዶም እና ሌሎች የተቋሙ ሠራተኞች፣ የሠራተኛና አሠሪ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶችና ሌሎች ግለሰቦችን ጨምሮ 13 ሰዎች በዚህ ወንጀል ተሳትፈዋል። ተጠርጣሪዎቹ የተሰጣቸውን የመንግሥት ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ፕሮጀክቱን ከአሠራር ውጭ በማንቀሳቀስ ከጅምሩ የሲስተሙ የጥራት ደረጃ በተገቢው ሳይረጋገጥ ሥራ እንዲጀምር ማድረጋቸውን ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል። ብርሃኑ አለቃ አስግዶም በቂ ሥልጠና ላልወሰዱ ለ81 ሺህ 236 ግለሰቦች ሕገ-ወጥ የሙያ ብቃት ምዘና ሰርተፍኬት በሲስተም እንዲሰጣቸው ያስደረገ ሲሆን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሠራተኛ ላልሆኑና ተቋሙ ከማያውቃቸው ሦስት ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር ልዩ የሲስተም አስተዳዳሪ መብት በመስጠት ዜጎች ያልሰለጠኑበትን ሐሰተኛ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንዲያገኙ ማድረጉን በምርመራ ተደርሶበታል። ለዚህ የወንጀል ድርጊት ሁለት ሐሰተኛ የባንክ ሒሳብ ደብተሮች እንዲከፈቱ በማድረግ በዚህ ሕገ-ወጥ መንገድ አጠቃላይ 1 ቢሊየን 13 ሚሊየን 609 ሺህ 241ብር ከ93 ሣንቲም መሰብሰቡ በምርመራ ተረጋግጧል። የወንጀሉ ፍሬ የሆነ በባንክ ሂሳብ ውስጥ ይገኝ የነበረ 249 ሚሊዮን ብር የታገደ ሲሆን ወንጀለኞቹ በረቀቀ ዘዴ ገንዘቡን ወደ የክሪፕቶከረንሲ በመቀየር ያስቀመጡትን 965 ሺህ 508 ዶላር ከፍተኛ ጥበብ በተሞላበትና በቴክኖሎጂ በታገዘ ምርመራ በፍርድ ቤት በማሳገድ ወደ ብሄራዊ ባንክ እንዲገባ ተደርጓል። ተጠርጣሪዎቹ የውጭ ምንዛሪ ሳያስገቡ የታገዱ ኤጀንሲዎችን እግድ ያለአግባብ በማንሳት 10 ሚሊዮን 100 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበሉ እና 64,500 ዜጎችን በሐሰተኛ ቪዛ ሰነድ ወደ ጆርዳንና ወደ ሌሎች የዓረብ ሀገራት በመላክ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸውን ፖሊስ ባደረገው የተጠናከረ ምርመራ ማረጋገጥ ችሏል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍትህ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ ከፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከልና ከብሄራዊ ባንክ ጋር በመቀናጀት ባካሄደው ምርመራ በተጠርጣሪው ስም በለሚ ኩራ፣ በቦሌና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች የተገዙ ከ55 ሚሊዮን እስከ 68 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ 6 ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች፣ በ68 ሚሊዮን ብር የተገዛ አንድ V6 ዘመናዊ መኪና በኤግዚቢትነት እንዲያዙ አድርጓል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዚህ ወንጀል ውስጥ የተሳተፉ እና ሕጋዊነትን ሽፋን በማድረግ መንግሥት ማግኘት የነበረበትን የውጭ ምንዛሪ ሳያስገቡ በቀሩ ኤጀንሲዎች ላይ እያደረገ ያለውን ምርመራ አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ልጆቻቸው ወደ ውጭ ሀገር ሄደው መዳረሻቸው የጠፋባቸው ቤተሰቦችና ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ መረጃ ያላቸው በዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp)፣ በነፃ የስልክ መስመር (991) እና በሰው አልባ ስማርት ፖሊስ ጣቢያ (SPS) አማካኝነት ጥቆማ እንዲሁም በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ በመቅረብ ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

በአዲስ አበባ የሕጻናት ምግብና ጁስን ጨምሮ ጊዜ ያለፈባቸው በርካታ ምርቶች ከገበያ ተወገዱ👉 33 የለውዝ ቅቤ አምራቾች ፈቃድና የምርት ጥራት ሰርተፍኬት ሳይኖራቸው ሲያመርቱ ተገኝተዋል በአዲስ አበ
በአዲስ አበባ የሕጻናት ምግብና ጁስን ጨምሮ ጊዜ ያለፈባቸው በርካታ ምርቶች ከገበያ ተወገዱ👉 33 የለውዝ ቅቤ አምራቾች ፈቃድና የምርት ጥራት ሰርተፍኬት ሳይኖራቸው ሲያመርቱ ተገኝተዋል በአዲስ አበባ የሕጻናት ምግብና ጁስን ጨምሮ ጊዜ ያለፈባቸው በርካታ ምርቶች ከገበያ ተወገዱ 👉 33 የለውዝ ቅቤ አምራቾች ፈቃድና የምርት ጥራት ሰርተፍኬት ሳይኖራቸው ሲያመርቱ ተገኝተዋል ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ባለፉት ሶስት ወራት ባደረገው የገበያ ቅኝትና ክትትል የሕጻናት ምግብን እና ጁስን ጨምሮ የተለያዩ ጊዜያቸው ያለፈባቸውና ሸማቾችን ሊጎዱ የሚችሉ ምርቶች ከገበያ እንዲወገዱ ማድረጉን አስታወቀ። በቢሮው የሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጸጋዬ ደበሌ እንደገለጹት በየደረጃው በሚገኘው የሸማቾች መብት ጥበቃ ቡድን በተካሄደው በዚህ የገበያ ቅኝት በ1,561 የንግድ ድርጅቶች ላይ ክትትል ተደርጓል። Read More Source: Ahadu Radio @Ethiopianbusinessdaily

Repost from አለ ሕግ
የአፍሪካ #አህጉራዊ ነጻ #ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አተገባበር፣ የስምምነቱ መሠረታዊ ዓላማው #AfCFTA ምንድን ነው? የአፍሪካ አገራት የራሳቸውን ምርት ያለምንም የቀረጥ መሰናክል እርስ በእርሳቸ
+4
የአፍሪካ #አህጉራዊ ነጻ #ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አተገባበር፣ የስምምነቱ መሠረታዊ ዓላማው #AfCFTA ምንድን ነው? የአፍሪካ አገራት የራሳቸውን ምርት ያለምንም የቀረጥ መሰናክል እርስ በእርሳቸው እንዲገበያዩ የተፈጠረ ታሪካዊ ስምምነት ነው። ዓላማው፦ የአፍሪካን ምርቶች ማሳደግ፣ የኢኮኖሚ ትስስር መፍጠር እና አህጉራዊ የንግድ ተወዳዳሪነትን መጨመር ነው። የአገራት ብዛት፦ እስካሁን 54 አገራት ስምምነቱን የፈረሙ ሲሆን፣ ይህም በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ የንግድ ቀጠናዎች አንዱ ያደርገዋል። 2. የኢትዮጵያ ተሳትፎና የሕግ ማዕቀፍ ፊርማ፦ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ መጋቢት 21/2018 በኪጋሊ ፈርማለች። ማጽደቅ፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 1124/2011 አጽድቆታል። ለትግበራው ይረዳ ዘንድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 574/2017 ጸድቋል። መመሪያ፦ የጉምሩክ ኮሚሽን በጥቅምት 04/2018 በቁጥር 4/0755/18 ባወጣው ሰርኩላር ትግበራውን በይፋ ጀምሯል። 3. የቀረጥ ቅነሳው እንዴት ይፈጸማል? (የዕቃዎች ምድብ) ኢትዮጵያ ያቀረበቻቸው የዕቃ ዓይነቶች በሦስት ምድብ ተከፍለዋል፦ ምድብ ሀ (Category A)፦ 90% የሚሆኑ ዕቃዎች (እንደ ቆዳ ጥሬ ዕቃዎች ያሉ)። በ10 ዓመት ውስጥ ቀረጣቸው 0% ይገባል። ምድብ ለ (Category B)፦ 7% የሚሆኑ ዕቃዎች (እንደ ጫማና ቦርሳ ያሉ ስሱ ምርቶች)። በ 8 ዓመት ውስጥ ቀረጣቸው 0% ይገባል። ምድብ ሐ (Category C)፦ 3% የሚሆኑ ዕቃዎች (ምንም ዓይነት ቅናሽ የማይደረግላቸው)። 4. የቀረጥ ቅነሳው የጊዜ ሰሌዳ ምድብ ሀ፦ እ.ኤ.አ ከጥር 2021 ጀምሮ በየዓመቱ እኩል እየቀነሰ ሄዶ በ2030 ሙሉ በሙሉ ነጻ ይሆናል። ምድብ ለ፦ እ.ኤ.አ ከጥር 2026 ጀምሮ ቅነሳው ተጀምሮ በ8 ዓመታት ውስጥ (እ.ኤ.አ እስከ 2033) ሙሉ በሙሉ ነጻ ይሆናል። ምርቱ ሙሉ በሙሉ ነጻ በሚሆንበት ዓመት ሱርቻርጅ (Surcharge) እና የሶሻል ዴቨሎፕመንት ሌቪ (Social Development Levy) አብረው ይነሳሉ።
5. ተጠቃሚ የሚሆኑ አባል አገራት (የ24ቱ ዝርዝር) የቀረጥ ቅናሹ የሚሰራው ስምምነቱን ለሴክሬታሪያቱ አሳውቀው በይፋ በጀመሩት 24 አገራት ላይ ብቻ ነው፦ ምሥራቅ አፍሪካ፦ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን። ምዕራብ አፍሪካ፦ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ካሜሩን፣ ጋምቢያ። ሰሜን አፍሪካ፦ ግብፅ፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ አልጄሪያ። ደቡብ አፍሪካ፦ ደቡብ አፍሪካ፣ ቦትስዋና Namibia፣ ዛምቢያ፣ ማላዊ፣ ኢስዋቲኒ፣ ሌሶቶ። ሌሎች፦ ሞሪሸስ፣ ሲሸልስ፣ ሞዛምቢክ።
6. ለቆዳ ዘርፍ SMEs የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች የአገር በቀል ምርት ምስክር ወረቀት (Certificate of Origin)፦ ምርቱ "በኢትዮጵያ የተመረተ" መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ከጉምሩክ ኮሚሽን ማግኘት ግዴታ ነው። የታሪፍ ኮድ (HS Code)፦ ምርትዎ በየትኛው የምድብ ኮድ ውስጥ እንደሚወድቅ ማረጋገጥ። የንግድ ሰነዶች፦ የንግድ ደረሰኝ (Invoice)፣ የይዘት ዝርዝር (Packing List) እና የጽሑፍ ውል ማዘጋጀት። 7. ተቋማዊ ኃላፊነቶች ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፦ አገራቱን የመለየትና የንግድ ድርድሩን የመምራት ኃላፊነት። ጉምሩክ ኮሚሽን፦ የምስክር ወረቀት የመስጠት፣ የዕቃዎችን አመዳደብ የመቆጣጠርና ቀረጡን የመቀነስ ኃላፊነት። ገንዘብ ሚኒስቴር፦ የቀረጥ መጠኑን በየዓመቱ የማሳወቅና የማስተካከል ኃላፊነት። 8. የሂደት ቅደም ተከተል (Step-by-Step Approach) ምርትዎን ይለዩ፦ የትኛውን የቆዳ ውጤት (ጫማ፣ ቦርሳ ወዘተ) ለመላክ እንደፈለጉ መወሰን። ገበያ ይምረጡ፦ ከላይ ከተጠቀሱት 24 አገራት ውስጥ የተሻለ ገበያ ያለውን መምረጥ። የአገር በቀል ምስክር ወረቀት ይውሰዱ፦ ምርቱ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ከጉምሩክ ያረጋግጡ። ገዢ ያግኙ፦ የዲጂታል መሣሪያዎችን (WhatsApp, Email) በመጠቀም ከውጭ ገዢዎች ጋር ይደራደሩ። ጭነት ይጀምሩ፦ በደንብ ቁጥር 574/2017 መሠረት የቀረጥ ቅናሹን ተጠቅመው ምርትዎን ይላኩ። ይህ ስምምነት ለቆዳ ዘርፍ አምራቾች አዲስና ሰፊ በር የከፈተ በመሆኑ፣ አምራቾች የጥራት ደረጃቸውን በማሻሻልና ሕጋዊ ሰነዶችን በማሟላት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይመከራል። ስልጠናው በጠበቃና የሕግ አማካሪ Mikias Melak ተሰጠ🙏 #ሚኪያስ_መላክ አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት Alternative legal enlightenment & Service Website: alehig.com https://linktr.ee/alehig WhatsApp👉 #+251920666595 Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ

Repost from አለ ሕግ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ቀን ሊከበር ነው! ⚖️💎 በሺዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ጠበቆች አምረው፣ ደምቀው እና ተውበው በሚታዩበት ልዩ ቀን‼️ ሁሉንም የፌዴራል ጠበቆች በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስበው
+1
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ቀን ሊከበር ነው! ⚖️💎
በሺዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ጠበቆች አምረው፣ ደምቀው እና ተውበው በሚታዩበት ልዩ ቀን‼️
ሁሉንም የፌዴራል ጠበቆች በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስበው ታላቅ "የጠበቆች ቀን" (Lawyers' Day) በቅርብ ቀናት ውስጥ በደማቅ ሁኔታ ሊካሄድ መሆኑን በዝግጅት ኮሚቴው ይፋ ሆነ! ✔️💎 ጠበቆች በሀገር ግንባታ፣ በሕግ የበላይነት እና በፍትህ ማረጋገጥ ሂደት ውስጥ የሚጫወቱት ሚና የማይተካ በመሆኑ፤ የሙያዊ ህብረት እና አወንታዊ ተፎካካሪነትን ማሳደግ፣ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በጋራ መፍትሔ መስጠት እና የሙያ ትስስራቸውን ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ የጠበቆች ቀን ተዘጋጅቷል‼️ ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ታሪካዊ መርሃ-ግብር የሙያውን ክብር ከፍ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ፣ በፌዴራል ጠበቆች ማህበር አዘጋጅነት ሁሉም ጠበቆች የሚታደሙበት የማይረሳ ምሽት ይሆናል! 🍷ይህ ደማቅ ፕሮግራም ምን ምን ያካተተ ነው?⁉️
🍽 የራት ግብዣ (Gala Dinner) 🎶 የተለያዩ ማራኪ የመዝናኛ ፕሮግራሞች 🤝 የኔትወርኪንግና የእርስ በእርስ ትውውቅ መድረክ 📺 የሀገር ውስጥና የውጭ ትልልቅ ሚዲያዎች ሽፋን ⚖️ የፍትሃዊነትና የጠበቆችን ማህበራዊ ሚና ማጎልበቻ ውይይቶች
ቀን እና ቦታው በጥቂት ቀናት ልዩነት ይፋ ይደረጋል!💡 #የኢትዮጵያፌዴራልጠበቆች #የጠበቆችቀን #FirstLawyersDay #EthiopianLawyers #Networking #GalaDinner #LegalExcellence

photo content
+1

ኢንቨስትመንትት_ማበረታቻን_ለማስፈጸም_የወጣ_መመሪያ_3.pdf5.46 KB

#ለመረጃ: ለአትክልት እና ፍራፍሬ ማቀናበር እና ማቆየት የሥራ ዘርፍ የሚያስፈልጉ የካፒታል ዕቃዎች ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆነው እንዲገቡ የገንዘብ ሚኒስቴር የማሻሻያ ደብዳቤ አውጥቷል! መመሪያ ቁጥር
#ለመረጃ: ለአትክልት እና ፍራፍሬ ማቀናበር እና ማቆየት የሥራ ዘርፍ የሚያስፈልጉ የካፒታል ዕቃዎች ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆነው እንዲገቡ የገንዘብ ሚኒስቴር የማሻሻያ ደብዳቤ አውጥቷል! መመሪያ ቁጥር 1064/2017 የኢንቨስትመንት ማበረታቻን ለማስፈጸም የወጣውን መመሪያ ማንበብ ለምትፈልጉ ከታች ተቀምጧል!

#ለመረጃ፡ የIMF አዲስ የ2026 የኢኮኖሚ ትንበያ ሰነድ ማንበብ ለምትፈልጉ ከላይ ሙሉ ሰነዱን ታገኛላችሁ!

ኢትዮጵያ ለቱርኩ ስራ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኩባንያ 213 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር እንድትከፍል ተወሰነ ኢትዮጵያ ለቱርኩ ስራ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኩባንያ 213 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር እንድትከፍል ተወ
ኢትዮጵያ ለቱርኩ ስራ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኩባንያ 213 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር እንድትከፍል ተወሰነ ኢትዮጵያ ለቱርኩ ስራ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኩባንያ 213 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር እንድትከፍል ተወሰነ ለያፒ መርከዚ ኩባንያ እንዲከፈለው ከተወሰነለት ውስጥ 89 ሚሊዮን ዶላር በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ለደረሱ ጉዳቶች የሚከፈል ነው ተብሏል። በአዋሽ ኮምቦልቻ ወልደያ ሀራ ገበያ የባቡር መስመር ግንባታ ክርክር ጉዳይ በኢትዮጵያ እና በስራ ተቋራጩ ያፒ መርከዚ መካከል ሲካሄድ የቆየው የክስ ሂደት ተጠናቋል፡፡ Read More Source: Capital Ethiopia @Ethiopianbusinessdaily

ሰላም ሚኪ ዳግም እባላለሁ የህግ ባለሙያ ነኝ ይህ ቪዲዮ INSA ባዘጋጀው የሶስት ደቂቃ የቪዲዮ ውድድር  ስለ ህፃናት የኦንላይን ደህንነት ከህጉ አንፃር  የሰራሁት ቪዲዮ ነው። እንዲታይልኝ  አለ ሕግ ግሩፕ ላይ share ብታደርግልኝ አመሰግናለሁ።

https://vm.tiktok.com/ZSgREgHVF/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite

ሕግ ሰላምን ይጠብቃል፣ ሰላም ደግሞ ሕግ እንዲፈጠርና እንዲጸና ያደርጋል