HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
رفتن به کانال در Telegram
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239
نمایش بیشتر2 296
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-1130 روز
آرشیو پست ها
የቄስ አፈወርቅ እጅግ አሳፋሪ ተግባር በማስረጃ ተጋለጠ ያሳዝናል!! እባካችሁን ሴቶች እህቶች ተጠንቀቁ ዘመኑ ከፍቷል!! የቀሱ የጅንጄና መንገድ ይገርማል!! https://youtu.be/QfFYZOkPY2c
«መስከረም ሃያ ዘጠኝ በዚች ቀን ከቅድስት አርሴማና ከእመምኔቷ ከአጋታ ጋር ደናግል በሰማዕትነት አረፉ። እንኳን አደረሳችሁ ውድ ቤተሰቦቼ የሰማዕቷ ረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን። ከልባችሁ በጸሎት ጠይቋት ታደርገዋለች። መልካም ቀን ለሁላችሁ ይሁን።»
መምህር ተስፋዬን ያስለቀሰው እጅግ ከባዱ ገጠመኝ ይገርማል!! ደጋግማችሁ እየቆረባችሁም ቢሆን መከራው ይቀጥላል!! ጴንጤዎችን ያስደነገጠ ከባዱ ክስተት!! https://youtu.be/njqOZ4v9umk
ይሄንን ጉድ ተመልከቱ! በሁለት ሺ ድርሃም የተላከ መተትና ያስከተለው መዘዝ! በትዳር ውስጥ ባልን የሚያስመርሩና የማይነገሩ ነገሮች! ንስሐ አባት አያስፈልግም! https://youtu.be/s16C6PywABk
ይሄንን ጉድ ተመልከቱ! በሁለት ሺ ድርሃም የተላከ መተትና ያስከተለው መዘዝ! በትዳር ውስጥ ባልን የሚያስመርሩና የማይነገሩ ነገሮች! ንስሐ አባት አያስፈልግም! https://youtu.be/s16C6PywABk
"ዲያብሎስ አእምሮአችንን ወይም ዕውቀታችንን አይፈራም፤ ከእኛ የበለጠ ዕውቀት አለውና። ቅድስናችንን (በጎ ምግባራችንን) እንኳ አይፈራም፤ ከእኛ የበለጠ በጎ ምግባራት አሉትና። ነገር ግን ሰይጣን የሌለው አንድ በጎ ምግባር አለ፤ እርሱም ትሕትና ነው። እርሱ ይህን ሲያይ ይቃጠላል፣ እኛን ግን ያድነናል። ታዲያ ይህች ምግባር ምንድን ናት?
...አንድ ቀን በሕይወቴ አንድ ነገር ላይ ስደርስ በኩራት ወደ መንፈሳዊ አባቴ ሄድኩ። አባቴ ሲያየኝ ወዲያውኑ እንደተደናቀፍኩ (እንደተሸነፍኩ) አወቀ። የልቤን ቃል ሳይጠብቅም እንዲህ አለኝ፦ "ልጄ ሆይ፣ ለምን እንኮራለን? ምንስ አድርገን ነው የምንኮራው? ጾመን፤ ጥቂት ምግብ ስለበላን ነው? ዲያብሎስ እኮ ከእኛ በላይ ይጾማል፤ ፈጽሞ አይበላም። በሌሊት ስለማንተኛ፣ ጥቂት ስለመተኛታችን ነው? ዲያብሎስ እኮ ከእኛ በላይ ነቅቶ ይኖራል፤ ፈጽሞ አይተኛም። በጾም ተወስነን ድንግልናችንን ስለጠበቅን ነው? ዲያብሎስ እኮ ከእኛ በላይ ድንግል ነው፤ እንኳን ሊያገባ ቀርቶ አካል እንኳን የለውምና።"
ጆሮዬን ማመን አቃተኝ። እኛ የምንጠራቀማቸው የትኛዎቹም በጎ ምግባራት ቢሆኑ ዲያብሎስም አሉት። ነገር ግን ዲያብሎስ ሊኖረው የማይችለውን ምግባር እኛ በሕይወታችን ልናገኘው አይቻለንም። ዲያብሎስ ሊቀሰቅሰው በማይችለው በዚያ የክብር መላእክት (መላእክት በነበሩበት) ጊዜ የነበረችው በጎ ምግባር ትሕትና ነበረች፤ እርሷን በማጣቱ ምክንያት ግን ሁሉንም ነገር አጣ። ታዲያ ለምን? ምክንያቱም አንድ በጎ ምግባር ጎድሎት ነበርና። ለመዳን የግድ ይህችን በጎ ምግባር ልናገኝ ይገባል።
ሰይጣን የሚያሸንፈን በኃጢአት ብቻ አይደለም። ከኃጢአት በበለጠ በበጎ ምግባር (በክብር) ያሸንፈናል። ኃጢአትን እናየዋለን፣ ልንርቀውም እንችላለን፤ ነገር ግን ለበጎ ምግባር እንታገላለን፤ ስናገኘውም እንኮራበታለን።
አንድ ቅዱስ አባት እንዲህ አለ፦ "ልትጾም ትፈልጋለህን? ዲያብሎስ ይረዳሃል። ምጽዋት ልትሰጥ ትፈልጋለህን? ዲያብሎስ ይረዳሃል። አብያተ ክርስቲያናትን ልትገነባ ትፈልጋለህን? ዲያብሎስ ይረዳሃል። ለምን? ምክንያቱም እነዚህን ሁሉ ስታሳካ እንድትኮራና በመጨረሻም ሁሉን ነገር እንድታጠፋ ያውቃልና።" ስለዚህ ሰይጣን የሌለውን ያንን በጎ ምግባር ልናገኘው ይገባል። ትሑት ሁን!"
ቅዱስ ኒቆዲሞስ እንደተናገረው
=> በቀኑ ማገባደጃ ላይ፣ የዕለት ተዕለት ሥራህ እንደተጠናቀቀ፣ የቀኑ እንቅስቃሴ ምን ያህል እንዳደከመህ ሳታስብ ፈጽሞ ለዕረፍት አትሽነፍ። አንድ ክርስቲያን በዚህ መንገድ ምስጋና ቢስ ሆኖ መገኘቱ ተገቢ አይደለም። ሥራህን እንደፈጸምክ፣ ሐሳብህን ወደ ጌታ ወደ እግዚአብሔር አንሳ፤ በቀኑ ውስጥ ከእርሱ ለተቀበልካቸው መልካም ነገሮች ሁሉ በቅን ልቦና አመስግነው።" — ሊቀ ጳጳስ ግሪጎሪ (ፖስትኒኮቭ)
=> የኛ ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? በየቀኑ ላገኘናቸው በረከቶች ሁሉ እግዚአብሔርን ማመስገን እንመርጣለን ወይስ ከመተኛታችን በፊት እንደገና ኢንተርኔት (ማኅበራዊ ሚዲያ) ላይ እንዋልላለን? "ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።" (ማቴዎስ ፮፥፳፩)። በእነዚህ ትናንሽ ነገሮች ላይ የምናደርገው ምርጫ ሕይወታችንንና ፍሬዋን ይወስናል። አባቶች እንደሚሉት፣ "በምሽት እግዚአብሔርን ያመሰገነ ነፍስ፣ በጠዋት ደግሞ የእግዚአብሔርን ረድኤት ታገኛለች።" እስቲ ከአሁን በኋላ መኝታ ከመሄዳችን በፊት ለአምላካችን ቢያንስ ፭ ደቂቃ የምስጋና ጸሎት እናድርግ።
"ከክፋት ራቅ፣ መልካምም አድርግ" (መዝ. ፴፫፥፲፬) የሚለው ቃል ትርጉሙ ይህ ነው፦ በመጀመሪያ በውስጥህ ያሉትን ክፉ ምኞቶች (ስሜቶች) ለመቀነስ ጠላትን (ዲያብሎስን) ተዋጋ፤ ከዚያም እነርሱ እንደገና እንዳያድጉ በአንተ ውስጥ እንዲጠፉ ንቁ ሆነህ ጠብቅ። እንደዚሁም መልካም ባሕርያትን (ምግባራትን) ለማግኘት ታገል፤ ካገኘሃቸው በኋላ ደግሞ እንዳይጠፉብህ ነቅተህ ጠብቃቸው። የኦሪት ዘፍጥረት ቃል "ለማልማትና ለመጠበቅ" (ዘፍ. ፪፥፲፭) ያለውም ትርጉም ይህ ነው።
— ቅዱስ ማክሲሞስ
=> አቤቱ ጌታዬ ሆይ፣ ያለ እልልታና ያለ ጉጉት ብጸልይ ይቅር በለኝ፤ እኔ የምጸልየው በልቤ ውስጥ ባለው ባዶነት ነው። ጉጉትንና ሙቀትን (መንፈሳዊ ፍቅርን) የምትሰጠኝ አንተ ነህ፤ መለኮታዊ እሳትህን በልቤ ውስጥ የምታፈስስም አንተ ነህ። ጸሎቴን እንደ ሁኔታው፣ ከነ እንከኑ ሁሉ ተቀበለኝ። ነገሮች ከመጀመሪያው ፍጹም ሆነው አይጀምሩምና፣ ፍጹምነት የሚገኘው ካንተ ብቻ ነው። መንፈስ ሳይሰማኝም ቢሆን እየጸለይኩ ነው። መንፈስ ቅዱስን እንደምትሰጠኝ አምናለሁ። አቤቱ ጌታ ሆይ! በሰው ልጅ ጥንካሬና በራስ ፈቃድ ብቻ መንፈሳዊ ሰው ልሆን እችላለሁ ብል ተሳስቻለሁ። ያንን ማድረግ የምችልበት መንገድ የለምና፤ የሚሆነው በአንተ ኃይል ብቻ ነው። አንተ እንድሆን የምትፈልገውን አርአያ (ምሳሌ) የምለብሰው በአንተ በረከት፣ በጸጋህና በመንፈስ ቅዱስህ ብቻ ነው። ይህ ሁሉ ሊሆን የሚችለው በአንተ መሪነት ብቻ ነው፤ ልክ እንደምትመራው ትንሽ ሕፃን እጄን ይዘህ፣ እርምጃ በ እርምጃ እየመራኸኝ ብቻ ነው።"
— ፓፓ ሸኑዳ
የፎቶ አልበማችሁን በጭራሽ ለሰዎች አታሳዩ እባካችሁን ተጠንቀቁ!! የሃይማኖት መሀል ሰፋሪዎች አርፋችሁ ተቀመጡ!! ንስሐችንን ዋጋ የሚያሳጡ 3ቱ ነገሮች!! https://youtu.be/Xxxfx80b2IA
«እውነተኛ_ወዳጅ»
እውነተኛ ወዳጅ፥ ወዳጅ መኾኑ የሚታወቀው ጓደኛውን መገሠጽ ሲችል ነው። ኹላችንም በየጊዜው ኃጢአት እንሠራለን። አብዛኞቻችን ደግሞ ኃጢአታችንን እንዳላየነው ኾነን ለማለፍ እንጥራለን። ለራሳችን ይቅርታ እንቸራለን። በእንደዚህ ዓይነት ሰዓት እውነታውን በትክክል እናይ ዘንድ ዓይናችንን የሚከፍት እውነተኛ ወዳጅ ያስፈልገናል። አንተ ሆይ! እስኪ ራስህን መርምር። ጓደኛህ እውነታውን እንዲያይ ታደርጋለህን? ጓደኛህ ኀጢአት ሠርቶ ሲያበቃ ለራሱ ይቅርታ ሲያደርግ፥ ያደረገው ይቅርታ ትክክል እንዳልኾነ እንዲያውቅ ታደርገዋለህን? እንዲህ እውነታውን ስትነግረው ምናልባት ጓደኛህ አለአግባብ ሊቆጣህ ይችላል። ታዲያ ሲቈጣህ ለመታገሥ ዝግጁ ነህን? ወይስ ከዚህ በተቃራኒ የጓደኛህን ኀጢአት አይተህ እንዳላየህ ነው የምትኾነው?
ጓደኛ ስንመርጥ ከእኛ ጋር እውነተኛ ወዳጅ ሊኾን የሚገባውን መኾን አለበት፤ ስንቈጣው እንኳን ቍጣችንን ታግሦ ስናጠፋ የሚያርመን ሊኾን ይገባል። እንደዚህ ካልኾነ ጓደኝነት ጥልቀት አይኖረውምና፤ ጓደኞች ነን መባባላችን ጥቅም የለውምና። ልናውቀው የሚገባ ነገር ግን አለ። ጓደኛችን በሚያጠፋበት ሰዓት ተግሣጽ አስመስለን እንዲሁ ክብሩን በሚነካ መልኩ ልንናገረው አይገባንም። ተግሣጻችን ኹል ጊዜ እውነቱን ብቻ እንጂ የተጋነነና ልላውን መልካምነቱን የሚክድ መኾን የለበትም። ጥፋቱን ስንነግረው ኹል ጊዜ በቀና ልብ እንደምንነግረው እርግጠኛ እንዲኾን ማድረግ አለብን። ይህን የምናደርገው ከፍቅራችን የተነሣ እንጂ ከቅናት ወይም ከንቀት እንዳልኾነ እንዲያውቅ ማድረግ አለብን። እውነተኛ ወዳጅነት ማለት ይህ ነውና። (ገ/እግዚአብሔር ኪደ፣ አምስቱ የንስሐ መንገዶች እና ሌሎችም በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 100-101)።
ቤተሰቦቻችን ምህረት እንዲያገኙ ማድረግ ያለባችሁ 6 እጅግ ወሳኝ ነገሮች!! እሬቻን መንፈሳዊ ለማድረግ የምትጋጋጡ እባካችሁን እረፉ!! በማለዳ ንቁ!! https://youtu.be/SjYI_KjGvqk
2ቱ እጅግ አደገኛ ክፉ መናፍስቶችና መጠንቀቅ ያለባችሁ ነገሮች!! ገዳም ከመሄዳችሁ በፍት ይሄንን በደንብ አስተውሉ!! ከመንፈሳዊነት መውረድ ሀገር ያፈርሳል!! https://youtu.be/gY-q0zDgprA
የተዋሕዶ እምነት ብቻ፡ ከእግዚአብሔር፥ ሌሎች እምነቶች በሙሉ፡ አንድም ሳይቀሩ፡ ከዲያቢሎስ እንደኾኑ ከማውቅባቸው በጣም በርካታ ማስረጃዎች መካከል አንዱና ዋነኛው ምን መሰላችሁ?
ኹሉም ነገር (ኹሉም ስላችሁ፡ ያለምንም exception፡ ክፉውንም በጎውንም ማለቴ ነው)፡ እኛ ስንሠራው ብቻ ስኅተት፥ እነርሱ ሲሠሩት ደግሞ ትክክል እንደኾነ ስለሚያምኑ ነው።
ሰላሙም፥ ጦርነቱም፥ በዓል ማክበሩም፡ አለማክበሩም፥ መሥራቱም መተኛቱም፥ ንጹሕ አምልኮውም፡ ጥንቆላውም፥ መንገሡም፡ መውረዱም፥ መብዛቱም ማነሱም፥ መስፋቱም መጥበቡም፥ መግደሉም መሞቱም፥ ማስተማሩም አለማስተማሩም፥ መስገዱም አለመስገዱም፥ ታቦት መቅረጹም፡ ጣዖት ማቆሙም፥ ማመኑም አለማመኑም፥ መበልጸጉም መደኅየቱም፥ መታመሙም፡ መዳኑም፥ ደግሦ ማብላቱም መለመኑም፥...በጥቅሉ ኹሉም ነገር፡ እኛ የተዋሕዶ ልጆች ስንሠራው ብቻ ስኅተት ይኾንና፡ እነርሱ ሲሠሩት ግን ትክክል ይኾናል። ይኽ፡ ከተዋሕዶ እምነት ውጪ ያሉ እምነቶች በሙሉ፡ አንድ እንኳ ሳይቀሩ፡ የተመሠረቱበት ምንታዌነት (double standard) ያነቀዘው የአሸዋ መሠረት ነው።
እንዲህ ያለ ኹለንተናዊ ተቃርኖ፡ አንድ ሰብአዊ ፍጡር፡ ከራሱ አስተሳሰብ በመነሳት ብቻ፡ በሌላ ሰብአዊ ፍጡር ላይ ሊኖረው አይችልም። በዚህ ልክ፡ ሥራ ፈትቶና በኹሉም ነገር ላይ ተናድዶ፡ አንድን መንፈሳዊ ዘር ለመቃወም የሚያበቃ negative energy ሊኖረው የሚችለው፡ ያ በአሸዋ ላይ የቆመው ዘንዶ ብቻ ነው።
Philosophically ስታዩት፡ በተዋሕዶ እምነት ላይ፡ ከውስጥም ከውጭም የሚነሳው የተቃርኖና የፀብ ዓይነትና መጠን፡ ብቻውን የዓለምን ታሪክ ማስረዳት የሚችል fundamental case study ነው። Documentary ልሥራበት ብትሉ፡ ኹሉንም ዓይነት logical fallacy, thinking error ብቻ ሳይኾን neurotic and psychotic tendencies የሚያብራራ የሰው ልጆችን የማሰነ ባሕሪ ገጽታ (fallen nature) ማሳየት ኹሉ የሚችል አስገራሚ የዓለማችን የታሪክ ክስተት ነው።
ተዋሕዶ ብቸኛዋ የክርስቶስ እምነት መኾኗን በዚህ አውቃለሁ።
«እነሆ ዓይኖቼ ታወሩ። ሕሊናዬ ተለወጠ። ልቡናዬም ጠቆረ፤ ተመልሼም ወደ ትፋቱ እንደ ሚመለስ ውሻ ኾንሁ። ሕሊናዬ በጎ፣ ንጹሕ አይደለችም። በጸሎት ጊዜም ዕንባ የለኝም፤ በምጭነቅበት ጊዜም የፊቴ ዕንባ ይደርቃል። ከማፈሬ የተነሣም ደረቴን እመታለሁ። ይህችም የሥቃይ ኹሉ መዝገብ ናት። ጌታ ሆይ፣ ስለዚህ አቤቱ፣ አቤቱ ከሚሉት ፈቃድህንም ካላደረጉት ጋር እንዳትጨምረኝ ፈቃድህን አላደረጉምና፣ አንተን ባገለገሉህ ኹሉ አማላጅነት እለምንሃለሁ። በውስጤ ያለውን ስውር ሥቃይ አንተ ታውቃለህና።» (ውዳሴ አምላክ ዘሠሉስ፣ ቍ 23)።
መምህር ግርማን ያስገረሙ 2ቱ አባቶችና ድንቅ ምስክርነታቸው!! 3ቱ ያልተነቃባቸው ሃይማኖት የለሾችና መጠንቀቅ ያለባችሁ ነገር!! በማለዳ ንቁ!! https://youtu.be/kAjq8su2g0s
አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለምዕመናን ተሰጠች።
ጽዮን ድንግል ማርያም ለምዕመናን ተሰጠች።
የእውነት ተቀብለናታል ወይ?!
ድንግል ማርያምን እጅግ የሚወድዱ መስለው፤ ማንነታቸውን፣ ስብከቶቻቸውን፣ መጻሕፍቶቻቸውን፣ ወይም መዝሙሮቻቸውን በርሷ ዙርያ አድርገው፥ በሥውር ግን እጅግ ጠላቶቿ የኾኑ የሳጥናኤል ወዳጆች በዝተዋል። እኛን ሳይቀር ስለድንግል ማርያም እያስተማሩን ያሉ እነሱ ኾነዋል። ይኽ እግዚአብሔር እንዳይረዳን ትልቅ እንቅፋት ኾኗል። በግልጥ ክደዋት ወደአዳራሽ ከኼዱት ይልቅ፡ በሥውር ክደዋት በቤቷ ወዳጆቿ መስለው ቁጭ ያሉት የእግዘብሔርን ቁጣ እያነደዱት ነው።
እግዚአብሔር ሆይ ይቅር በለን!
በልቡ ሽንገላ የሌለበት ሰው ብፁዕ ነው።
የግሸኗ ንግሥት ሸንጋይ ከመኾን ታድናችሁ!
