HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
前往频道在 Telegram
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239
显示更多2 292
订阅者
+124 小时
-37 天
-1030 天
帖子存档
መተት በስልክ ሲላክ የሚታዩ 8 ግልጽ ምልክቶችና መፍትሔው!! ምልክቱን ካዩ በኋላ ማድረግ የሚገባችሁ ነገሮች!! መተትና የስልክ አጠቃቀማችን!! https://youtu.be/o7aMlrWd8Oo
በመከራና በፈተና ጊዜ ይሄንን 5 መዝሙረ ዳዊት ደጋግማችሁ ጸልዩ!! እንደ ሀገር ለምን መጸለይ ያስፈልጋል መዝሙረ ዳዊትና የአጋንንት ፈተና በዘመናችን! https://youtu.be/YhyYBkHDMIM
ይሄንን ምልክት ካያችሁ የቢሮ መተት ተደርጎባችኋልና ንቁ!! የቡዳን መንፈስ ለማሸነፍ ይሄንን በማድረግ አሁኑኑ ጀምሩ!! ስለ ይቅርታ 2ቱ ድንቅ ምስጢሮች!! https://youtu.be/JFYFa8o3EO8
"የእምነት መለወጥ ምስጢር" — የዛር መንፈስ አንድን ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ሃይማኖቱን የሚያስቀይርበት 5 ረቂቅ መንገዶች
የዛር መንፈስ (አመቺሳ) እና የጨለማ ኃይላት አንድን ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በቀጥታ "ሃይማኖትህን ቀይር" ብለው አይገፋፉትም፤ ምክንያቱም ያኔ ክርስቲያኑ ነቅቶ በጸሎትና በመስቀል ኃይል እንደሚመክታቸው ያውቃሉ። ይልቁኑ መናፍስቱ ሰውን ከተዋሕዶ እምነቱና ከምስጢራተ ቤተክርስቲያን አውጥተው ለዘላለም ጥፋት ለመዳረግ 5 ረቂቅና ስልታዊ የሆኑ የወጥመድ መንገዶችን ይጠቀማሉ [ዮሐንስ 10፥10]።
ይህ ትምህርት ትውልዱን ከተኩላዎች ስውር ሴራ የሚጠብቅ፣ በፈተና ውስጥ ላሉት ደግሞ ነቅተው እምነታቸውን እንዲጠብቁ የሚያግዝ እውነተኛ የማንቂያ ደወልና የድል ወንጌል ነው።
1. ማዕበል ማስነሳትና ተስፋ ማስቆረጥ (The Storm of Despair)
ረቂቅ ሴራው፦ ሰይጣን መጀመሪያ የሚያደርገው በሰውየው ሕይወት ላይ ከባድ ማዕበል ማስነሳት ነው። ያለምክንያት በትዳር ውስጥ ከባድ ጥላቻና መበታተንን ይፈጥራል፤ በሥራና በምድራዊ ስኬት ላይ መክሰርን ያመጣል፤ በአእምሮ ላይ ደግሞ ተስፋ አስቆራጭ የሆነ የከባድ ድብርት (Depression) እና የጭንቀት መንፈስ ይጭናል። ዓላማው ክርስቲያኑ "እግዚአብሔር ጥሎኛል፤ ጸልዬ ምንም ለውጥ አላገኘሁም" በሚል ፍጹም ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንዲወድቅ ማድረግ ነው። "ጌታ ሆይ፥ ስንት ጊዜ ትመለከታለህ? ነፍሴን ከአጥፊዎቻቸው አድናት..." [መዝሙር 35፥17]። ጠላት ሰውን በፈተና አደንዝዞ ማማረርና እግዚአብሔርን መክሰስ ውስጥ እንዲገባ ይገፋፋዋል።
2. የኅሊና ውግረትና የሃይማኖት ጥርጣሬ መዝራት (Intellectual Doubt)
ረቂቅ ሴራው፦ ሰይጣን በወጣቱ ኅሊና ላይ ረቂቅ የጥርጣሬ ቀስቶችን ይወረውራል። "ለምንድነው የምትሰግደው? ለምንድነው የምትጾመው? እግዚአብሔር ቢወድህ ኖሮ ይህንን ሁሉ መከራ በትዳርህና በጤናህ ላይ ያመጣ ነበር?" እያለ ሃይማኖታዊ ሕጎችንና ትውፊቶችን እንደ ኋላ ቀርነትና እንደ ሸክም አድርጎ እንዲያስብ አእምሮውን ይበጠብጠዋል። "እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አእምሯችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ እፈራለሁ።" [2ኛ ቆሮንቶስ 11፥3]።
3. ከመቅደስና ከምስጢራት ማራቅ (Spiritual Isolation)
ረቂቅ ሴራው፦ ሦስተኛው ደረጃ የሰውን መንፈሳዊ ጉልበት ማድከም ነው። ወጣቱ ወይም ምዕመኑ በሕይወቱ መናወጥ ምክንያት "ጸሎት ምን ያደርጋል?" ብሎ የዘወትር ጸሎቱን እንዲተው፣ የንስሐ አባቱን እንዲሸሽ፣ እና ከቅዱስ ቁርባን ሕይወት እንዲርቅ ያደርገዋል። ሰይጣን በበሽታና በጭንቀት ሽፋን ሰውን ከመንፈሳዊ አጥሩ ያስወጣዋል። ከበግ ጥጋቱ የወጣ በግ ደግሞ ለአንበሳ (ለሰይጣን) ቀላል ሲሳይ ይሆናል። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፦ "ዲያብሎስ አንድን ነፍስ ሊያጠፋ ሲፈልግ፣ መጀመሪያ ከእረኛዋ (ከንስሐ አባት) እና ከምስጢራት ማዕድ ያርቃታል። ያለ ጋሻና ጦር ሜዳ ላይ የቆመ ወታደር ደግሞ በቀላሉ ይማረካል" ይላል።
4. "ባህል ነው" በሚል ስም የዛርን አምልኮ ማቅረብ (Cultural Deception)
ረቂቅ ሴራው፦ ቤተክርስቲያን ሲርቅና ቤቱ ሲቀዘቅዝ፣ ሰይጣን በቤተሰብ ወይም በወዳጆች በኩል "ይህ እኮ የሃይማኖት ጉዳይ አይደለም፤ የአያቶችህ ባህል ነው፤ ቡና አፍልተህ ቆሌውን ካላስታገስክ ሕይወትህ አይቃናም" የሚል ስውር የጣዖት አምልኮ መፍትሔ ያቀርባል። ሰውየውም በቅንነትና በባህል ስም የዛርን ስም መጥራትና ደም ማፍሰስ ይጀምራል። ይህ አዲስ የባርነት ውል መፈራረም ነው። "ለአጋንንት እንጂ ለእግዚአብሔር እንደማይሠዉ... ከአጋንንትም ጋር ማኅበረተኞች እንድትሆኑ አልወድም።" [1ኛ ቆሮንቶስ 10፥20]።
5. የሐሰት ተአምራትና "የእምነት መፍትሔ" ማቅረብ (The Trap of False Miracles)
ረቂቅ ሴራው፦ ይህ የመጨረሻውና አደገኛው ወጥመድ ነው። ክርስቲያኑ በድብርትና በችግር ተስፋ ቆርጦ፣ መንፈሳዊ መከላከያ ጋሻው (ጸሎትና ቁርባን) ሲደክም፣ ሰይጣን በወዳጅ ወይም በማኅበራዊ ሚዲያ በኩል መፍትሔ አቅራቢዎችን ያመጣል። "እዚያ እምነት ጋር ሂድ፣ እዚያ ጋ አጭብጭብ፣ ፈጣን ፈውስ ታገኛለህ፣ ችግርህ ይወገዳል" የሚሉ ድምፆች ይሰማሉ። ሰውየው በሥጋ ተስፋ ስለቆረጠ፣ ከኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ቀኖናና ምስጢራት ውጪ ወደሆኑ የባዕድ አምልኮና የስሜት መድረኮች ይኮበልላል። መንፈሳዊ ኪሳራው፦ ሰይጣን ያመጣውን የጭንቀትና የትዳር መበላሸት ውግረት በራሱ ፈቃድ ለጊዜው ያነሳለታል። ሰውየው "እንዴ! እዚያ ሄጄ እኮ ተፈወስኩ/ተሳካልኝ" ብሎ ሃይማኖቱን በይፋ ይለውጣል። ነገር ግን ይህ ፈውስ ሳይሆን የነፍስ ምርኮኝነት ነው። ሰይጣን የሥጋ ጤና ወይም ሀብት የሰጠ አስመስሎ የዘላለም የነፍስ ባለቤትነቱን ይረከባል።
የድል መሣሪያዎች (ኦርቶዶክሳዊ መፍትሔ)
አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ይህንን የዛር መንፈስ የእምነት ማስቀየር ሴራ ሰብሮ ለማሸነፍ የሚከተሉትን 4 መሣሪያዎች በጥብቅ መታጠቅ አለበት፡
- የቅዱስ ጥምቀት ማኅተም መረዳት፦ አንተ በሜሮን የታተምክ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ [ዮሐንስ 3፥5]። ሰይጣን ማዕበል ቢያስነሳብህም በአንተ ላይ ፍጹም ሥልጣን የለውም።
- የጽናት መሠዊያ፦ ፈተና ሲበዛ ጸሎት ማቆም ሳይሆን፣ ጸሎትን ማበርታትና በትዕግሥት መቆም ጠላትን ያሳፍረዋል [ሉቃስ 21፥19]።
- የንስሐ ዕርቅ፦ በችግርህ ጊዜ የመጡብህን የጥርጣሬ ሐሳቦች በሙሉ ለንስሐ አባትህ በግልጽ በመናገር የጠላትን የክስ ሰነድ ቀደህ ጣለው [1ኛ ዮሐንስ 1፥9]።
- የቅዱስ ቁርባን ግንብ፦ የክርስቶስን ሥጋና ደም በውስጡ የሰነቀ ክርስቲያን የሚበላ እሳት ስለሚሆን፣ የዛር መንፈስ ሊያስታምመው ቀርቶ ሊቀርበው አይችልም [ዮሐንስ 6፥56]。
የማንቂያ ደወልና ምክር
የተወደድክ ወንድሜ/እህቴ ሆይ! በትዳርህ፣ በጤናህ ወይም በአእምሮህ ላይ የመጣው ከባድ ፈተና ሃይማኖትህን እንድትጠራጠርና እግዚአብሔርን እንድትክድ የተዘጋጀ የአጋንንት ረቂቅ ሴራ ሊሆን እንደሚችል አስተውል። ሰይጣን ዛሬ የሰጠህ የሚመስለው ምድራዊ እረፍት ነፍስህን ለመማረክ የዘረጋው ወጥመድ ነው። ፈተናው ቢበረታም ከተዋሕዶ እምነትህና ከምስጢራተ ቤተክርስቲያን ፈጽመህ እንዳትወጣ!
ስለዚህ ዛሬውኑ ንቃ፡
በትዕግሥት ጽና፡ በችግርህ ጊዜ ከመቅደሱ አትስሽ፤ ይልቁኑ ወደ መሠዊያው ተጠጋ። ምስጢራትን አትተው፡ ንስሐ ግባ፣ ሥጋ ወደሙን ተቀበል፤ የደም ሐረግህ በክርስቶስ ደም ይባረክ። በድፍረት ቁም፦ አንተ ድል አድራጊ ነህ፤ የዛር መንፈስ በአንተ ላይ ያለው የውሸት ሥልጣን በክርስቶስ መስቀል ፊት የፈረሰ ነው!
የዩቱብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ላይክና ሸር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!!
=> https://www.youtube.com/@haileG2239
ይህን በሕልም አይተው ያውቃሉ?! የተሰበረ ብርጭቆ፣ እሬት፣ ቄስ፣ ሽጉጥና የቤተክርስቲያን ሕልሞች! በሕልም ከባድ ማስጠንቀቂያ ማየት?! https://youtu.be/_fBByJBLz7M
ወንዶችን ክፉ መንፈስ ቶሎ የማይለቃቸው ለምንድነው!? ያገባችሁ ሴቶች በጭራሽ ማድረግ የሌለባችሁ 3 ነገሮች!! በከባድ መከራ ውስጥ ከሆናችሁ!! https://youtu.be/A-0t9ZAFVn0
«ብዙውን ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጡ ሰዎች በግድግዳዎች ላይ ባሉት ስዕሎች ብዛት ይገረማሉ። እነዚህ ስዕሎች ከመጽሐፍ ቅዱስና ከቤተክርስቲያን ታሪክ የተወሰዱ ትዕይንቶችን፣ ቅዱሳንን፣ እመቤታችንን ማርያምንና ክርስቶስን ይወክላሉ። እኛም ከግሪክ ቋንቋ “ምስሎች” ከሚለው ቃል በመነሳት “አዶዎች” (Icons) እንላቸዋለን። በጥንት ዘመን፣ እነዚህ ቅዱሳን ስዕሎች ማንበብ ለማይችሉ (በወቅቱ ጥቂት ሰዎች ብቻ ነበሩ ማንበብ የሚችሉት) ሰዎች እንደ ቋንቋ እና እንደ ማስተማሪያ ያገለግሉ ነበር። በአሁኑ ጊዜም እንኳ ስዕል “እንደተሳለ” ሳይሆን “እንደተጻፈ” (Icon writing) እንገልጸዋለን።
እኛ አዶዎችን (ቅዱሳን ስዕላትን) አናመልክም፤ የምናመልከው እግዚአብሔርን ብቻ ነው፤ ለቅዱሳን ግን አክብሮትና ስግደት እንሰጣለን። አዶዎች (ቅዱሳን ስዕላት) የማስተማሪያ፣ የማስታወሻ እና የእምነት መግለጫ መንገዶች ናቸው። እነርሱም መልካሙንና ሰማያዊውን ነገር ሁሉ ይወክላሉ።
“ቅዱሳት ስዕሎች በእግዚአብሔር ቅዱሳት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥና በቤቶች እንዲቀመጡ እንወስናለን። እነርሱም ሊሳለሙ፣ ለአክብሮትና ለሰገዳ የሚገቡ ናቸው። አዶውን (ቅዱሳን ስዕላትን) የሚያከብር/የሚሳለም፣ በእርሱ የተወከለውን እውነተኛ ማንነት ያከብራል።”»
— ሰባተኛው ዓለም አቀፍ የቤተክርስቲያን ጉባኤ (የኒቂያ ጉባኤ)
ወደ ሀገረ #ስዊዘርላንድ የላክነው እጣን፣ ዘቢብ፣ ቅባዕ ቅዱስ፣ የናርዶስ ሽቶ፣ መቁጠሪያና የአንገት መስቀል በጥንቃቄ ደርሷል ቤተሰቦቼም መቀበላቸውን አሳውቀውኛል። ሌሎቻችሁም ለጸሎት ቤት የሚሆናችሁንና ማንኛውም አስፈላጊ የሆኑ ድርሳናትን፣ ገድላትና መጽሀፍቶችን አዘጋጅተን እንልካለን በቀጥታ በዚህ ስልክ ቁጥር መደወል ትችላላችሁ። 0939241162 ወይም በተለግራም አናግሩን። በተጨማሪም ደግሞ የምቁረቢያ ልብስ የምትፈልጉ ቤተሰቦቼ አናግሩኝ ተዘጋጅቶ መላክ ይቻላል። መልካም ቀን ለሁላችሁ ይሁን።
ባሕታዊ ገብረመስቀል የመምህር ግርማ ጉባኤ ላይ ለምን ተገኙ!! የዘመድኩንና የባህታዊ ገብረመስቀል ግንኙነት ምንድነው ዘመድኩን መምህር ግርማን ለምን ይቃወማል! https://youtu.be/cbrRn63ZUA4
አርሲ ላይ በሰይፍ ከመሸነፍህ በፊት፡ መጀመሪያ የተሸነፍከው፡ በፕሮፓጋንዳ ነው።
አንተ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ሆይ!
ላንተ ገለልተኛ፡ እንዲያውም ኦርቶዶክስ የሚመስሉህ፡ ነገር ግን ጥልቅ ፀረ ተዋሕዶ ጥላቻና ዒላማ ያላቸው መናፍቃንና አሕዛብ ፖለቲከኞች የኾኑ ምሑራን፣ የስነ ጽሑፍ ሰዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የታሪክ ተመራማሪዎች፣ ደራሲዎች፣ መጣጥፍና መነባንብ አቅራቢዎች፣ ኮሜድያኖች፥ የድርጅት ሥራ አስኪያጆች፣ አንባቢዎችና ፈላስፎች፣ ኹሉን አቃፊ የሚመስሉ የሶሻል ሚድያ ዜናና ወሬ አቅራቢዎች፣ በየራድዮው የምትሰማቸው መዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጆች፥ ወዘተ... ለረዥም ጊዜ በአእምሮህ ሲስሉብህ የኖሩት፡ አንተና መሰሎችህ ኦርቶዶክሶች፡ እና አባቶቻችሁ፡ ሰው ስትገድሉ እንደኖራችሁ፥ ስትረግጡና ስትበድሉ፣ ስታፍኑ እንደኖራችሁ፣ ፈላሻውንና ሙስሊሙን፣ ካቶሊኩንና ጴንጤውን ስታሳድዱ እንደኖራችሁ፣ አሁንም በደማችሁ ያ ዝንባሌ እንዳለ፣ ኹሉንም በግድ ኦርቶዶክስ ለማድረግ ስትጫኑ እንደኖራችሁ፣ ረጋጭ እና ጨቋኝ ባሕሪ እንዳላችሁ፥ ሌላው ቀርቶ፡ ለእምነታችሁ እንኳ የምትቆረቆሩት፡ በመኃይምነትና በድንቁርና ምኑንም ሳታውቁትና እግዚአብሔርን ሳትወድዱት እንደኾነ አድርገው፡ በቀልድም በቁም ነገርም ሲነግሩህና በገዛ እምነትህ ላይ እምነት እንድታጣ፥ ኃይል ያለውም እንዳይመስልህ ሲሠሩ ነው የኖሩት።
ስለዚህ፡ አሁን ያንን ለማካካስ፡ ለስላሳ፣ ቅልስልስ መኾን እንዳለብህ፥ የሌላ እምነት ተከታዮችን ለማባበልና ለማስደሰት፡ የራስህን እምነት ጠንካራ አገልጋዮችን እንድትነቅፍ፥ "አክራሪ ናቸው" ብለህ እንድትወቅስ፥ ከኹሉም በላይ ደግሞ፡ የኹሉም እምነት ተከታዮች approval ያልሰጡትን የራስህን አገልጋይ እንዳትቀበልና የእውነተኛ መምህር/አገልጋይ መለኪያው ኹሉንም እምነቶች የሚወድና የሚቀበል መኾን እንዳለበት እንድታምን፥ እውነተኛ የሃይማኖት ሰው ማለትም ለኹሉም ሃይማኖቶች ጥቅም እኩል የሚሠራ እንደኾነ እንዲመስልህ አድርገው፡ የተልመጠመጠ መሥፈርት በየአጋጣሚው አእምሮህ ውስጥ ጠቅጥቀውብሃል። ያንን ለማውጣት በጣም ከብዶሃል። አሁን "ኦርቶዶክሳውያን በእምነታቸው ተለይተው እየተገደሉ ነው" ስትባል፡ ለራስህ እምነት መቆም ተሥኖሃል። "ኃጢአት ነው" ብለው ሲነግሩህ ኖረዋላ! "ወገንተኝነት ነው" ብለው ሲያንቋሽሹብህ ኖረዋላ! "ለራስህ ሃይማኖት ማዳላት ነውር ነው" ብለውሃላ! እና በየት በኩል ሙሴ ትኾናለህ? በየት በኩል የነኢያሱና የነሶምሶን፥ የነአስቴርና የነዮዲት፥ የነዳዊትና የነሰሎሞን፥ የሐዋርያትና የሰማዕታት በረከት ይደርብህ? እነሱ'ኮ የቆሙት አንዲት ብቻ ለኾነችው የእግዚአብሔር እውነት ነው?!
አደንዛዦችህ፡ "ወገንተኝነት ተው" የሚል ስብከት የሚነግሩህ፡ ላንተ ብቻ እኮ ነው?! እነሱ አያምኑበትም። የምትጠፋበትን መንገድ ብቻ ነው የሚቆምሩልህ።
በያጋጣሚው፡ ፊት ለፊት በሽልማት በእውቅናና በምስጋና ፕሮግራም ሲያሞግሡና ሲያደንቁልህ የምታያቸው፡ ለአንተ አርአያ እንዲኾኑ የሚፈልጓቸውን መንፈሳዊ አቋም የሌላቸው መሃል ሰፋሪዎችን ነው። ለሃይማኖቱ የቆመ ሰው፡ በዚህ ዘመን "አደገኛ" እና "በኅብረተሰቡ መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚሠራ" እንደኾነ አሳምነውሃል። አንተም ተቀብለኸዋል።
ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ሆይ!
ብዙዎቻችሁ፡ በማይመስሏችሁ ሰዎች የሶሻል ሚድያ account ሥር follower እና subscriber ኾናችሁ ተኮልኩላችሁ ሳያችሁ እጅግ ይገርመኛል። Atheist, መናፍቅ፥ ፀረ-ኦርቶዶክስ የኾኑ ገጾች ላይ ምን ትሠራላችሁ? የግድ የሚያስቅ ነገር ስለጻፈ እኮ follow ማድረግ አለባችሁ ማለት አይደለም? የግድ መልኳን አሳምራ ስለመጣች እኮ እንደምታምር ለመንገር ገጿ ላይ ተሰልፋችሁ መዋል አለባችሁ ማለት አይደለም? እሷ እኮ ሥራዋን እየሠራች ነው? እሱ እኮ ከላይ የዘረዘርኩላችሁን ደካማ ሥነ ልቦና እያሠረጸባችሁ ነው? ምን ኾናችሁ ነው አፋችሁን ከፍታችሁ በየatheist እና በየመናፍቁ ገጽ ስትጃጃሉ የምትውሉት?
ለነገሩ፡ በአንድ ጥሪ 2000 ዓመት የኖረ የገና ማኅሌት ትቶ አደባባይ ያመሸ ትውልድ አይደል? ነገ ጠዋት አንዱ ተነሥቶ፡ "ባሁኑ እሑድ ቅዳሴ የለም፤ ፍኖተ ጽድቅ አዳራሽ ተገናኝተን እንዘምር" ቢሉት ተከትሎ ይኼዳል። ይኽ ሰይፍና ገጀራን የሚቋቋም ትውልድ አይደለም።
መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ "ይኽ ትውልድ እንደጎመን የሚቀረደድ ትውልድ ነው፤ ቡዳ በልቶታል" ብለዋል።
እውነታቸውን ነው!
ማንም በቀላሉ እንደ ጓሮ ጎመኑ ይቀነጥሰዋል።
አደንዛዦችህ፡ ቀን ቢሮ ገብተው ሲያደነዝዙህ የሚውሉ፡ አስቀድመው ሌሊት ለዲያቢሎስ ሠውተው ነው። ከላይ ስታያቸው፡ አለባበሳቸው፥ አነጋገራቸው፥ አጻጻፋቸው፡ እንዲህ ያለ የመንፈስ ነገር የሚገባቸው አይመስሉም። "የምን ኢሉሚናቲ ነው? እንዲህ ያለ የተጨናነቀ ወሬ አታውራብኝ። እኔ በሰብአዊነት፥ ደግ በመኾን፥ ኹሉን እኩል በመውደድ ነው የማምነው፤ ክርስቶስ ፍቅርን አይደል ያስተማረው?" ይሉሃል። የማይጠቅሱልህ ፈላስፋና የፈረንጅ ወይም የዐረብ ባለቅኔ የለም። የእውቀት ሰው መስለውሃል። የእምነትና የገርነት ቢበዛም የሜካፕ ሰው ብቻ መስላሃለች። ግን፡ በሌሊት ለዲያቢሎስ የሚሠዉትን ሠውተው ነው የሚመጡት። አጀንዳቸውም አንተ ነህ--ኦርቶዶክሳዊው ወጣት። ትፈዝዝና ትደነግዝ ዘንድ፥ ትጃጃል ዘንድ፥ አምላክህ ሊነግርህ የሚፈልገውን እንዳትሰማ፥ ዓይንህን ሊገልጥልህ ለሚፈልገው እውነት እንዳትገልጥ፡ በፍቅርና በወሲብ፥ በፍልስፍናና በ"ሥልጡን ባሕሪ" ስም፡ ልፍስፍስነትን አስተምረው የተቀቀለ ፓስታ አድርገውሃል።
እና... ተኝተህ ተኝተህ ድንገት ትነሣና፡ እርምህን ብትቃወም፡ የምትቃወመው የራስህን ሰው ነው። ለቤተክርስቲያን ጥብቅና የቆመውን፥ ድምጹ እስኪነቃ የሚጮኸውን "ይኼ ሰውዬ አይመቸኝም! እንደዚህ ክርር ሲሉ ይደብሩኛል" እያልህ ትተቻለህ። ጅላንፎ!
እና በየትኛው ጸሎትህና እምነትህ ነው የአሩሲዋን እመቤት ዘንዶ ተዋግተህ የምታሸንፈው? በየትኛው ጾምህና ስግደትህ ነው በየወንዙና በየተራራው በአገሪቱ ሲመለክ የኖረውንና አሁን ፖለቲካ ኾኖ መጥቶ ጠምዝዞ ሊውጥህ የደረሰውን ዛር ተዋግተህ ወደ ጥልቁ የምትጥለው?
እየተነገራችሁ አሁንም ትጃጃላላችሁ። ይገርመኛል።
አርሲ ኼዶ ለመዋጋት የሚያበቃ ዝግጅት ላይኖርህ ይችላል።
እስኪ ከአንድ ዘፋኝ፥ መናፍቅ፥ ኤቴይስት የsocial media ገጽ ላይ unsubscribe አድርጎ ከመውረድ ጀምር?
እሱንም ከቻልህ አንድ ነገር ነው!
ዱሮ ከጣልያን ጋር ተዋግተው ያሸነፉት ኢትዮጵያውያን እኮ፡ ልጃቸው ዘፋኝ ስትኾንባቸው፡ ከቤት አስወጥተው ያባርሩ የነበሩ ጠንካሮች መንፈሳውያን ነበሩ?!
አንተ፡ አሩሲ ፈረቀሳ በሌሊት እየኼደች፡ የድምፅ፥ የመወደድ ሞገስ፥ የዝና፥ የገንዘብ፥ የአነሁላይ የሰውነት ቅርጽና የወጣትነት ድግሞት አስደግማ የምትመጣ አርቲስት አድናቂና አጃቢ ኾነህ ትኖርና፡ ድንገት "በአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ተጨፈጨፉ" ሲባል ጭንቅላትህ ዜናውን መረዳት ራሱ ያቅተዋል። ስታስተውል ስላልኖርክ ኹሉ ነገር ድንገት ይኾንብሃል። "ሌላ ችግር ቢኖር ነው እንጂ ነገሩ የሃይማኖት አይደለም፤ የኛዎቹ ገገማ አክራሪዎች ናቸው እንደዚያ የሚያጮሁት" ብለህም ራስህን ታጽናናለህ።
አንተ የምትኖርበት የሽንጥና የዳሌ ዓለም እና መሬት ላይ ያለው እውነታ አንድ አይደሉም።
እስኪ፡ ሰው ለመኾን፡ ከምትችለው ጀምር።
የግድ አርሲ ኼደህ መዋጋት አይጠበቅብህም።
ሰሞኑን ቀዝቃዛ ጠበል በጠዋት ተነሥተህ ከመጠመቅ ጀምር። እሱንም ከቻልክ አንድ ነገር ነው።
በስውሯ ማሪያም ምን እየተካሄደ ነው እባካችሁን ተጠንቀቁ!! ተማሪ ከሆናችሁ ደብተራችሁን በጭራሽ እንዳታውሱ!! ሞታችንን የቅዱስ ሲኖዶስ ዝምታ!! https://youtu.be/kbBr-J258t0
10 የናርዶስ ሽቶ መንፈሳዊ ምሥጢራት!! ኦርቶዶክሳዊ አጠቃቀሙና የማይታወቁ ጥቅሞቹ !! የሰውነት ጠረን መፍትሔ!! https://youtu.be/MMxZMEsCn0E
☦️ የአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ጭፍጨፋ
• ቤተ ክህነት ~ ዝም ጭጭ።
• መንግሥት ~ ዝም ጭጭ
• ኢትዮጵያውያን ~ ዝም ጭጭ
• መከላከያው ~ ዝም ጭጭ
• ፌደራል ፖሊስ~ ዝም ጭጭ
• የክልሉ ፖሊስ ~ ዝም ጭጭ
• ሚዲያዎች ~ ዝም ጭጭ
• አክቲቪስቶች ~ ዝም ጭጭ
☦️ እግዚአብሔር ሆይ እባክህን ፍረድልን፡ የሚሰማን አጣን፡ የሚጨነቅልን አባት አጣን፡ የሚጨነቅ መሪም አጣን፡ እባክህን ፍረድልን። እባክህን ጌታ ጌታ ሆይ ማረን ይቅርም በለን። በቃችሁ በለን። ረሀቡን፥ ጦርነቱን፥ መከራውን፥ መሳደዱን በቃችሁ በለን በገዛ ሀገራችን ባዳ፥ ሀገር አልባ ሆነናልና ይቅር በለን። የሕፃናቱ ደም፥ የአዛውንቱ፥ የካህናቱ፥ የእናቶች ደም ይፍረድ። እባክህን ጌታ ሆይ ይቅር በለን።
እጅግ ያሳዝናል የሀገራችን ጉዳይ! ☦️
🔥 እነዚህን ህልሞች በተደጋጋሚ እያያችሁ ነው 😱 ፍቅረኛ፣ ትልቅ ንስር፣ ራቁትነት፣ መስቀልና የእመቤታችን ስዕል!! የህልም ትርጓሜ ከመምህራን ጋር!! https://youtu.be/d5--UfYs5-k
ኤረ!! ይሄ ምን ዓይነት አስደናቂ ታሪክ ነው! ተረጋግተን መጸለይና መስገድ ለምን አቃተን! ይህንን እውነት ያወቀ ሰው ፕሮቴስታንት አይሆንም!! https://youtu.be/vzfy3R8F7vI
