የጥበብ ማዕድ
📈 تحلیل کانال تلگرام የጥበብ ማዕድ
کانال የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 15 880 مشترک است و جایگاه 5 407 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 2 116 را در منطقه أثيوبيا دارد.
📊 شاخصهای مخاطب و پویایی
از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 15 880 مشترک جذب کرده است.
بر اساس آخرین دادهها در تاریخ 24 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 628 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 31 بوده و همچنان دسترسی گستردهای حفظ شده است.
- وضعیت تأیید: تأیید نشده
- نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 2.61% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 2.09% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب میکند.
- دسترسی پستها: هر پست به طور میانگین 415 بازدید دریافت میکند. در اولین روز معمولاً 332 بازدید جمعآوری میشود.
- واکنشها و تعامل: مخاطبان بهطور فعال حمایت میکنند؛ میانگین واکنش به هر پست 9 است.
📝 توضیح و سیاست محتوایی
نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاههای شخصی توصیف میکند:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!”
به لطف بهروزرسانیهای پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 25 ژوئن, 2026)، کانال همواره بهروز و دارای دسترسی بالاست. تحلیلها نشان میدهد مخاطبان بهطور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کردهاند.
ነገሩ እንደአደንዛዢ እፅ ነው...ልጆች ወይም ወጣቶች ተደብቀው የወደቀች ሲጋራ ጫት ወይም ቤት ውስጥ ጠላ መቀማመስ ይጀምራሉ...ተደብቀው "ይሳሳሙ "ይሆናል። መደበቅ የይሉኝታና የአክብሮት ስሜት አለው። የምሰራው ልክ አይደለም ሌሎች አይዮብኝ የሚል ፀፀት አለው። ከፍ ሲሉ ሲጋራው ተራ ይሆንባቸዋል ፣ ወደመጠጥ ቤት ወደሽሻ ቤት ይሄዳሉ፣ መደበቁን ይተውታል። ያም አያረካቸውም ወደከባድ መጠጦች፣ ወደአደንዛዢ እፅ ይሄዳሉ፣ ሴተኛ አዳሪወች ጋር ባለጌ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ ፣ ወሲብ ፣ማርገዝ ፣ወልዶ መጣል፣ ማስወረድ ወዘተ ተራ ነገር ይሆንባቸዋል። ጥርሳቸው መልካቸው ሰውነታቸው በቁማቸው መፈራረስ ይጀምራል ...እንኳን ምክርና ይሉኝታ ሞት ከሱሳቸው በላይ አያስፈራቸውም። ቤተሰብ ፣ ዕምነት ሕዝብ ተራ ይሆንባቸዋል። ከሞት አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው ወደሞት ያዘግማሉ። እንደውም "ኖርማል ሰው" ሲመለከቱ ጤነኛ አይመስላቸውም። ለሱሳቸው ይዋሻሉ፣ ማንንም አሳልፈው ይሰጣሉ፣ ይሰርቃሉ፣ ይገድላሉ።
አሁን ያለው ኢትዮጵያዊ የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ሱስ በዚያ ደረጃ ላይ ነው። ጥበብ፣ ውይይት አሽሙር፣ ቅኔ ፣ የሰከነ ሐሳብ ፣ ይሉኝታ ሞራል የሚባለውን ጉዳይ አልፏል። ተራ ስድድቦችንም ዘሏል። ወሲብ ነክ ጉዳዮች አደባባይ ላይ የማይታዮ ገመናወችን ዘሏል። ስለመገዳደል ካልተወራ ሬሳ ካላየ፣ ያዛጋዋል። የለየለት ፖርኖግራፊ እና የቆሸሸ የግል ገመና ገበያ ሆኗል። በየሚሴንጀርና ቴሌግራም እንደቆሸሸ የከተማ ወንዝ ዝሙት ሲፈስ ውሎ ያድራል፣ ገምቷል ሸቷል። በውስ የተራቆተው ከላይ ተከናንቦ ብቅ ይላል። ከፈጣሪ እስከነብያት ከአገር እስከህዝብ ከማንነት እስከተፈጥሮ ስብዕና የማይዘለፍ የማይንቋሸሽ የለም።
ብዙ ሺወች ከየመንደሩ የከረፋ ባህሪያቸውን ተሸክመው አደባባይ ወጥተዋል። የመላ ከተማው ቆሻሻ ተሰብስቦ እንደሚጣልበት ቆሸ ቆሻሻ መጣያ ሆኗል። ቤተሰብ እንኳን የሚፀየፋቸው ሰወች ሺህ ሚሊየን ሰው አስከትለው አደባባይ ውለዋል። የታዳሚው አእምሮ የቆሻሻ ሱስ ይዞት ቆሻሻ ያነፈንፋል። ቆሻሻው ላይ ሚሊየን ዝንቦች ያርፋሉ። "ማን ብዙ ዝንብ አለው " የሚለው ሐሳብ ኩራት ሆኗል። ድግሪ ያለው ዝንብ፣ ማስተርስ ያለው ዝንብ፣ ፒኤች ዲ የተሸከመ ዝንብ፣ ሐብት ያለው ዝንብ፣ ስልጣን ያለው ዝንብ፣ ሐይማኖተኛ ነኝ የሚል ዝንብ፣ ፖለቲከኛ ነኝ የሚል ዝንብ፣ ዲያስፖራ ነኝ የሚል ዝንብ፣ ቆንጆ ነኝ የምትል ዝንብ... ዝንባዊ ማንነት የሚኮራበት ሆኗል። "ለመኖር ስል ዝንብ ሆንኩ" ይልሃል።
ንቦች ቆሻሻ ላይ ያበቀለ አበባ ፍለጋ አፍንጫቸውን ይዘው በቆሻሻ ክምር ላይ ክንፋቸው እስኪዝል ይበራሉ! የጨነቀው አየሩ ያፈነው ጨዋ ትውልድ በዚህ ቆሻሻ ታፍኖ እየተጨነቀ ነው። አየሩ ቆሽሿል.... ንቦች የሚሰሩት ጥቂት ማርም ቢሆን ዝንብ ይሰፍርበታል። ዝንብ በቆሻሻና በማር መካከል ያለው ልዮነት አይገባውም። ሱሱ ግን አሁንም አልቆመም ነገ የከፋ ቆሻሻ ሊያዋልድ እያማጠ ነው።
✍ Alex Abraham
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
