የጥበብ ማዕድ
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 የጥበብ ማዕድ 的分析概览
频道 የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 880 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 407,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 116 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 880 名订阅者。
根据 24 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 628,过去 24 小时变化为 31,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 2.61%。内容发布后 24 小时内通常能获得 2.09% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 415 次浏览,首日通常累积 332 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 9。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“ዝም ብለህ ተቀላቀል!”
凭借高频更新(最新数据采集于 25 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
15 880
订阅者
+3124 小时
+1507 天
+62830 天
帖子存档
15 880
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በህ-ወጥ መንገድ ለገበያ ሊቀርብ የተዘጋጀ ስጋ ተያዘ
በጥብቅ ፍተሻ ጤንነታቸው ያልተረጋገጡ 13 የታረዱ በጎች፣ 14 ፍየሎች እንዲሁም ፅዳቱ ያልተጠበቀ 312 ኪሎ ግራም ስጋ ተይዟል።
ስጋውም እንዲወገድ ለአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተረከበ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸሙ ግለሰቦችም በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል።
ሲታይ ባያምርም ሳናይ ምንበላው እያለን መወገዱ ያሳዝናል።😒
15 880
'ሚታደል ለማደል
ሳድን እድለኛ
ከ'እድለኛው ዝርዝር
ተገኘው 'ባንደኛ
እድሌ ሆነና
አልከሰርኩም ከቶ
እጣው ለኔ ወጣ
እድለኛ ሸሽቶ!
Abu(Alazar Tewodros)
15 880
የሆነ ሰው ራሱ ላይ የማይሆን ውሳኔ እንዲወስን ከገፋፋችሁና suicide እንዲያደርግ፤እልፍ ቀናትን እስከ ወራት የደም እንባ እንዲያለቅስ ካደረጋችሁ በኋላ ቀብሩ ላይ ተገኝታችሁ ሰይጣን ገፋፍቶት ነው አትበሉ 😔🥺ማርያምን ከናንተ አንፃር እንደውም ሰይጣን ያ ሰው ራሱ ላይ እንዳይጨክን ሲገረግረው ነበር 🥺 ......
የምር ከናንተና ከሰይጣን ግን ማነው ሰይጣን¿??
15 880
መኖርን ሳታውቀው መኖር ጀምረህ ትገኛለህ።
መማር ሚገባን ቀለም ብቻ አልነበረም! ቀለም ከማወቅ በተጨማሪ ፍርሐትንም ነው የሚያስተምረን።
መኖርን መማር ነበረብን ብዙ ግራ የሚያጋቡ ሁነቶችን ስንደርስባቸው መቼ እንደተጠጋናቸውና እንዴት እንደምናልፋቸው አናውቅም!
እስቲ መኖርን አስተምሩን!
15 880
ነገሩ እንደአደንዛዢ እፅ ነው...ልጆች ወይም ወጣቶች ተደብቀው የወደቀች ሲጋራ ጫት ወይም ቤት ውስጥ ጠላ መቀማመስ ይጀምራሉ...ተደብቀው "ይሳሳሙ "ይሆናል። መደበቅ የይሉኝታና የአክብሮት ስሜት አለው። የምሰራው ልክ አይደለም ሌሎች አይዮብኝ የሚል ፀፀት አለው። ከፍ ሲሉ ሲጋራው ተራ ይሆንባቸዋል ፣ ወደመጠጥ ቤት ወደሽሻ ቤት ይሄዳሉ፣ መደበቁን ይተውታል። ያም አያረካቸውም ወደከባድ መጠጦች፣ ወደአደንዛዢ እፅ ይሄዳሉ፣ ሴተኛ አዳሪወች ጋር ባለጌ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ ፣ ወሲብ ፣ማርገዝ ፣ወልዶ መጣል፣ ማስወረድ ወዘተ ተራ ነገር ይሆንባቸዋል። ጥርሳቸው መልካቸው ሰውነታቸው በቁማቸው መፈራረስ ይጀምራል ...እንኳን ምክርና ይሉኝታ ሞት ከሱሳቸው በላይ አያስፈራቸውም። ቤተሰብ ፣ ዕምነት ሕዝብ ተራ ይሆንባቸዋል። ከሞት አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው ወደሞት ያዘግማሉ። እንደውም "ኖርማል ሰው" ሲመለከቱ ጤነኛ አይመስላቸውም። ለሱሳቸው ይዋሻሉ፣ ማንንም አሳልፈው ይሰጣሉ፣ ይሰርቃሉ፣ ይገድላሉ።
አሁን ያለው ኢትዮጵያዊ የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ሱስ በዚያ ደረጃ ላይ ነው። ጥበብ፣ ውይይት አሽሙር፣ ቅኔ ፣ የሰከነ ሐሳብ ፣ ይሉኝታ ሞራል የሚባለውን ጉዳይ አልፏል። ተራ ስድድቦችንም ዘሏል። ወሲብ ነክ ጉዳዮች አደባባይ ላይ የማይታዮ ገመናወችን ዘሏል። ስለመገዳደል ካልተወራ ሬሳ ካላየ፣ ያዛጋዋል። የለየለት ፖርኖግራፊ እና የቆሸሸ የግል ገመና ገበያ ሆኗል። በየሚሴንጀርና ቴሌግራም እንደቆሸሸ የከተማ ወንዝ ዝሙት ሲፈስ ውሎ ያድራል፣ ገምቷል ሸቷል። በውስ የተራቆተው ከላይ ተከናንቦ ብቅ ይላል። ከፈጣሪ እስከነብያት ከአገር እስከህዝብ ከማንነት እስከተፈጥሮ ስብዕና የማይዘለፍ የማይንቋሸሽ የለም።
ብዙ ሺወች ከየመንደሩ የከረፋ ባህሪያቸውን ተሸክመው አደባባይ ወጥተዋል። የመላ ከተማው ቆሻሻ ተሰብስቦ እንደሚጣልበት ቆሸ ቆሻሻ መጣያ ሆኗል። ቤተሰብ እንኳን የሚፀየፋቸው ሰወች ሺህ ሚሊየን ሰው አስከትለው አደባባይ ውለዋል። የታዳሚው አእምሮ የቆሻሻ ሱስ ይዞት ቆሻሻ ያነፈንፋል። ቆሻሻው ላይ ሚሊየን ዝንቦች ያርፋሉ። "ማን ብዙ ዝንብ አለው " የሚለው ሐሳብ ኩራት ሆኗል። ድግሪ ያለው ዝንብ፣ ማስተርስ ያለው ዝንብ፣ ፒኤች ዲ የተሸከመ ዝንብ፣ ሐብት ያለው ዝንብ፣ ስልጣን ያለው ዝንብ፣ ሐይማኖተኛ ነኝ የሚል ዝንብ፣ ፖለቲከኛ ነኝ የሚል ዝንብ፣ ዲያስፖራ ነኝ የሚል ዝንብ፣ ቆንጆ ነኝ የምትል ዝንብ... ዝንባዊ ማንነት የሚኮራበት ሆኗል። "ለመኖር ስል ዝንብ ሆንኩ" ይልሃል።
ንቦች ቆሻሻ ላይ ያበቀለ አበባ ፍለጋ አፍንጫቸውን ይዘው በቆሻሻ ክምር ላይ ክንፋቸው እስኪዝል ይበራሉ! የጨነቀው አየሩ ያፈነው ጨዋ ትውልድ በዚህ ቆሻሻ ታፍኖ እየተጨነቀ ነው። አየሩ ቆሽሿል.... ንቦች የሚሰሩት ጥቂት ማርም ቢሆን ዝንብ ይሰፍርበታል። ዝንብ በቆሻሻና በማር መካከል ያለው ልዮነት አይገባውም። ሱሱ ግን አሁንም አልቆመም ነገ የከፋ ቆሻሻ ሊያዋልድ እያማጠ ነው።
✍ Alex Abraham15 880
..
ባለመግባባትና ጥል መሃከል የኔ ኣስተዋጾ ምንድነው ማለቱ የራስን ጉድለትና ተጠያቂነት ለማየት መሞከሩ ትልቅ ኣዋቂነትን ይጠይቃል።
ሁሌ ራስን እንደተበዳይ ማባበል እውነቱን ይጋርዳል....
15 880
Happy mother's day መባል የሚገባን ያልወለድን እናቶች አለን መልካም የእናቶች ቀን ለኛ ለመጀመርያ ሴት ልጆች እንዲሁ ለሁሉም ታላላቅ እህቶች እንኳን አደረሳችሁ💞🥹
15 880
፡
ከአይኖቿ ህያው ቃል አለ
ይቀዳል ፍቅር ከደጇ
ችሮታ ፀጋ አድሏታል
መሰሰት ጭራሽ አታውቅም
ለጋስ ነው በረከት እጇ
ሸክሟ ቢበረታባት
ውስጧ በጭንቀት ቢላወስ
አዝና እንኳ ብታቀረቅር
ቅጥ አልባ ኑሮ ቢወዛ
እንደልብ ኑሮ ቢቸግር
ደክማ እንኳ ልታበረታ
ቀን ተዳፍኖ ቢጨልማት
ሳይደላት ደልቶት ያደገ
የልጇ ሳቅ ነው የሚያቀናት
ሲወድቅ እኔን ትላለች
ለልጇ ጥሩን ስትመኝ
ሲያመውም እኔን ይመመኝ
ሲርበው እኔን ትላለች
ሲጠማው እኔን ትላለች
የጌታ የአንድዬን እናት
ማርያምን ተመስላለች
አካሏ ጥቁርቁር ቢል
ጭንቀቷን በሳቅ ብትደብቅ
በእንክብክብ ልጇን ልትጠብቅ
የሕይወት ተስፋን ሰንቃ
ብትዝል ልትበቃ ለግብ
ነውና ልጇን ልትመግብ
ሸክሟ ቢበረታባት
ውስጧ በጭንቀት ቢላወስ
አዝና እንኳ ብታቀረቅር
ቅጥ አልባ ችግር ቢወዛ
እንደልብ ኑሮ ቢቸግር
በልጇ ደስታ 'ምትረካ
በሳቅ ውበቱ የምተፈካ
ትጉህ ብርታቷ ፅናት
ከሰው ልብ የማትጠፋ
ዘልአለም ተወዳ 'ምትኖር
እናት ምንጊዜም እናት ናት
✍ Mekdi
@amen1995
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
