fa
Feedback
ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa

ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa

رفتن به کانال در Telegram

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa

کانال ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa (@ibnshifa) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 19 990 مشترک است و جایگاه 3 913 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 1 735 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 19 990 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 25 سپتامبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 246 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 28 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 11.60% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 4.63% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 2 319 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 926 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 0 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 26 سپتامبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کرده‌اند.

19 990
مشترکین
+2824 ساعت
+757 روز
+24630 روز
آرشیو پست ها
🎙🎙 ​የተከበሩ ሼይኽ  ዶክተር ኻሊድ ቢን ሙሐመድ አል-ጉፈይሊ (ሪያድ / ሳዑዲ ) ገብተዋል ሼር ሼር         ሼር ሼር                 ሼር ሼር ሸር በማድረግ  የአጅሩ ተከፋይ ይሁኑ!! 👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 . Click the link to join us! https://s.imoim.net/tBLAMO?from=other በቴሌግራም 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bilalmesji?videochat https://t.me/bilalmesji?videochat

🌸 ጥያቄ 🌸 📖 ወደ አድ ሕዝቦች ተውሒድን እንዲሰብክ የተላከው ነብይ ማነው? ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ✅ ትክክለኛውን መልስ በመጫን 📲 ወደ ሰለፊዮች ቻናል ይቀላቀሉ!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ዓለም አቀፍ የሙሃዶራ ፕሮግራም ተጀመረ ገባ ገባ በሉ ↘️↘️↘️↘️ https://t.me/bilalmesji?videochat

👉 ይህ ታላቅ የ online ፕሮግራም ዛሬ ነው አንዘናጋ በያለንበት ለመከታተል እናስታውስ!!

የዓለም አቀፍ online ደዕዋ  ፕሮግራም መርሃ ግብር 🎙🎙​ ከቡኻሪ — የፕሮግራሙ መሪዎች —ቡኻሪ መስጂድ  🔑 ርዕስ—  የፕሮግራሙ ትውውቅ (8:00 ሰዓት) 🎙 ​ሼይኽ ሐሰን ገላው ሐሰን ( ባህር ዳር ) 🔑 ርዕስ —  ወደ አላህ ተጠሪዎችና የተጠሪዎች ስነምግባር (8:10 ሰዓት) 🎙🎙 ​የተከበሩ ሼይኽ  ዶክተር ኻሊድ ቢን ሙሐመድ አል-ጉፈይሊ (ሪያድ / ሳዑዲ ) —  የመጀመሪያ ክፍል 🔑 ርዕስ — የደዕዋ መልእክት  ( 8:30 ሰዓት)  🎙 ​ሸይኽ አብዱልሀሚድ  (ስልጤ / ለተሞ ) 🔑 ርዕስ  —በሰዓቱ ይገለፃል ( 8:40 ሰዓት ) 🎙 ​ሸይኽ ዶ /ር ሁሴን ሙሐመድ ( አዲስ አበባ ) 🔑 ለአላህ ብሎ በመዋደድ ላይ ( 9:30 ሰዓት) 🎙 ​ሸይኽ መህቡብ  አደም (ወራቤ / ሳንኮራ ) 🔑 ርዕስ — በቁርኣንና በሱና መመራት (ከአስር በኋላ) 🎙 ​ሸይኽ  አህመድ አወል ( አዲስ አበባ ) 🔑 ርዕስ — ነፍስን መተሳሰብ ( 10:20 ሰዓት) 🎙 ​ሸይኽ ሰይፉልላህ (ምስራቅ ስልጤ ) 🔑 ርዕስ —  የሺርክ አደገኛነት (10:50ሰዓት) 🎙 ​ኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን ( አዲስ አበባ ) 🔑 በወቅቱ ይገለፃል ( 11:20 - 11:35) 🎙 ​ሸይኽ  ሙባረክ ( ወልቂጤ ) 🔑 ርዕስ —  ለሀቅ መተናነስ ( 11:40 ሰዓት) 🎙 ​ኡስታዝ ሙሐመድ እባቡ (ቻግኒ)  🔑 በወቅቱ ይገለፃል (12:00 - 12:15) 🎙​ሸይኽ  ሁሴን ከረም (ሀራ ) 🔑 ርዕስ —  ስለተውሂድ (12:20 ሰዓት) 🎙 ​ኡስታዝ ሰዓድ አብዱለጢፍ  (ባህር ዳር ) 🔑 አላህን መፍራት (12:30 - 12:45) 🎙 ​ሸይኽ ሙሐመድ ሲራጅ (ሀሮ ) 🔑 ርዕስ — በወቅቱ ይገለፃል ( ከመغሪብ በኋላ (12:40)) 🎙 ​ሸይኽ ሙሐመድ ሀያት ( ሀራ) 🔑 ርዕስ — የሽርክ እውቀት አስፈላጊነት ( ከመغሪብ በኋላ) 🎙 ​ሸይኽ  አቡዘር ሐሰን ( ኮምቦልቻ ) 🔑 ርዕስ —  በወቅቱ ይገለፃል (1:05 ሰዓት) 🎙 ​ኡስታዝ አብዱልቃድር ሐሰን (አዳማ ) 🔑 ርዕስ —  የታዋቂነትና መሪ ለመሆን የመመኘት በሽታ ( 1:30 - 1:45) 🎙 ​ሸይኽ ጧሃ ኸድር  ( አዲስ አበባ ) 🔑 ርዕስ —  ለጥመት ሰበብ የሚሆኑ ነገሮች ( ከዒሻ በኋላ) 🎙 ​ሸይኽ  ሙሐመድ ጀማል (ኮምቦልቻ ) 🔑 ርዕስ —  የአንድነትና የመተባበር አስፈላጊነት  ከዒሻ በኋላ (2:20 ሰዓት) 🎙 ​ኡስታዝ በድሩ  ሰኢድ ( እሁዲት ) 🔑 ርዕስ — በወቅቱ ይገለፃል ( 2:45 - 3:00) 🎙🎙 ​የተከበሩ ሸይኽ  ዶክተር ኻሊድ ቢን ሙሐመድ አል-ጉፈይሊ  (ሪያድ / ሳዑዲ ) — (ሁለተኛ ክፍል) 🔑 ርዕስ— ሱናን አጥብቆ መያዝ | ከ3:00 ጀምሮ 🎙 ​ሸይኽ የሱፍ አህመድ (ባህር ዳር ) 🔑 ርዕስ — ሱፊይነት የጃሂልያ መግለጫ ነው  ( ማታ 3:50 ሰዓት) 🎙 ​ኡስታዝ ሙሐመድ ኢብራሂም (መዲና /ሳዑዲ) 🔑 ርዕስ — በወቅቱ ይገለፃል ( ማታ 4:20ሰዓት) 🎙 ​ኡስታዝ ሰልማን (መዲና/ሳዑዲ  ) 🔑 በወቅቱ ይገለፃል (ማታ 4:50 ሰዓት) 🎙 ​ወንድም አቡ ሷሊህ  አል ኡሰይሚን ኤልያስ  (ኩዌት ) 🔑 ርዕስ  በወቅቱ ይገለፃል ( ማታ 5:20ሰዓት) የፕሮግራም መሪወች 1) ኡስታዝ ባህሩ ተካ 2) ኡስታዝ አቡ በክር ዩሱፍ 3) ኡስታዝ ሪድዋን ዳውድ 4) ኡስታዝ አብደረህማን ሰኢድ 5) ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ በቴሌግራም👇👇👇👇 https://t.me/bilalmesji https://t.me/bilalmesji https://t.me/bilalmesji በኢሞ 👇👇👇👇 We're talking about በጉጉት የሚጠበቀው አለም አቀፍ ፕሮግራም እየቀረበ ነው!!!!!!. Click the link to join us! https://s.imoim.net/tBLAMO?from=copy_link ይህን ታላቅ የደዕዋ ና የኒያ ፕሮግራም ላልደረሳቸው ወገኖቻችን በማደረስ የተጣለብንን ሀላፍትና እንወጣ ።
ደዕዋችንን እያዳመጥን  መስጂዱንም እንሰራዋለን

የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች ————— ① መታጠብና መቀባባት ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል] ② ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል] ③ በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ  ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል] ④ መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ) ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል] ⑤ ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ) ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።] ⑥ ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ)  የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።] ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።] ⑦ በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።] ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም። ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

ከአምሳ ምክሮች ለዲን ተማሪዎች… ——— ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:- “አንተ የዲን ተማሪ ሆይ! በሱንና ዑለማዎች መደባበቅን ተጠንቀቅ!፣ ስሜትህን ሲገጥሙህ ታከብራቸዋለህ፣ ሲቃረኑህ አለያም ሀሳብህን ሲቃወሙህ ትተቻቸዋለህ፣ አለያም የሆናቸውን የምትወድ በመምሰል ትጎላለህ፣ አለያም በመካከላቸው ለመለያየት ጥረት ታደርጋለህ፣ ይህ ሁሉም የሱንና ዑለማዎች ያስጠነቀቋቸው የሆኑት ሰርጎ ገቦች ባህሪና በሰለፊዮች መካከል ለመለያየት የሚታገሉ ሰዎች መለያ ነው። እውነተኛ ሠለፊይ የሆነ ሰው ወደ እውቀት ባለቤቶች በመመለስ በጉዳዮች ላይ ያመላክታል፣ የሚሰጡትንም ሀቅን የሚገጥም የሆነውን ሀሳብ እንደ ብርሃን በመጠቀም ይመራበታል፣ አላህን በሚያስቆጣ ነገር ላይ አይወድቅም!፣ አታላይና ስውር ሴረኛ አይሆንም!!።” [ኸምሱነ ነሲሀህ ሊጦላብ አል ዒልም ገፅ 29] ✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

የሙስሊም መሪዎችን የምትተቹ ሰዎች አላህን ልትፈሩና ከባድ አደጋ ላይ ከመውደቅ ልትጠነቀቁ ይገባል!! ——— የሳዑዲው ጠቅላይ ሙፍቲ ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዶ/ር ሷሊህ ፈውዛን አል-ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ) የሙስሊም መሪዎችን ስለሚተቹ ሰዎች ተጠይቀው የመለሱት እነሆ… = አላህ መልካም ይዋልሎትና ጥያቄዬ:- አንድ ሰው በሙስሊም መሪዎች ላይ በሚሰነዝረው ትችት እንደ ሸሪዓችን ተገቢ እንዳልሆነ መከርኩት፣ ከመቀበል ይልቅ በዚህ ምክንያት ዘጋኝ፣ አንድ ቦታ ስንገናኝም ሰላምታ ሳቀርብለት አልመለሰልኝም፣ ከዚያ በኋላ እኔም ዘጋሁት (ራቅኩት) በዚህ ላይ ወንጀለኛ እሆናለሁን? መልስ:- ይህ በሙስሊም መሪዎች ላይ የሚያነሳሳ አካል - በአላህ እንጠበቃለን - ኸዋሪጅ ከሚባሉት ጠማማ ቡድኖች ነው። እንዲህ ያለው ተግባር (የሙስሊም መሪዎችን መተቸት) አይፈቀድለትም!፣ የሙስሊም መሪዎች ራሱን የቻለ ሐቅ አላቸው፣ ለመሆኑ ያለ መሪዎች (በሰላም) ትኖራላችሁን?፣ ለአላህ ጥራት ይገባው! ይህ ሰው ያለ መሪዎች በቤቱ ማደር፣በንግድ ቦታዎች መንቀሳቀስ… ወዘተ፣ ይችላልን? በፍፁም! ለአንድ ሀገር መሪ መኖር ግዴታ ነው!።  አንድም አካል ከመሪዎች ሊብቃቃ አይችልም!፣ ይልቅ ዱዓ ይደረግላቸዋል፣ እገዛ በሚያስፈልጋቸው ነገር ይታገዛሉ፣ አላህን በማመፅ እስካላዘዙ እነሱን መታዘዝ ግዴታ ነው፣ በንግግር እነሱን ሰዎች ዘንድ ማቃለል (ማዋረድ) አይፈቀደም፣ ይህ ሷሃቦች የተጋደሏቸው የሆኑት ኸዋሪጅ የሚባሉት የጥመት ቡድኖች ተግባር ነው። በዚህ መልኩ በምድር ላይ ብልሽትን ስለሚያስፋፉ ሷሃቦች ተጋድለዋቸዋል። በመሆኑም አንተ በመምከርህ ልክ ነህ፣ እንዲሁም ምክርን የማይቀበል እስከሆነ እሱን ዘግተህ በመራቅህም ልክ ነህ፣ ይህ ግን በቂ አይደለም እጃቸው እስኪያዝ ከእርሱም ከተከታዮቹም ማስጠንቀቅና ነገራቸውን ማጋለጥ ይገባሃል።” [ከድምፅ ተወስዶ በኢብን ሽፋ የተተረጎመ] https://t.me/IbnShifa/7389 - በልቡ ኒፋቅ የተተከለበት ይመስል ዘውትር ሚዲያ ላይም በአካልም ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ እዚህ ቁጭ ብሎ በጭፍን ጥላቻ የሙስሊም ሀገራትንና ዐረብ መሪዎችን የሚያብጠለጥል ሰው ከባድ አደጋ ላይ እንዳለና ልቡ በሽተኛ እንደሆነ አውቃችሁ ተጠንቀቁት!! - ሙስሊም መሪዎች በሀገራቸው በሚችሉት ያህል የዜጎቻቸው ደህንነት የተጠበቀ እንዲሆን ሰበብ አድርሰዋል፣ የትኛውም አካል እንደዋዛ ተነስቶ የሰው ህይወት አያጠፋም፣ የሰው ንብረት አይዘርፍም!፣ ዜጎቻቸው በሰላምና በደስታ ወጥተው ይገባሉ። እዚህ ቁጭ ብለህ ምታብጠለጥላት ሳዑዲ ከወንጀል ሁሉ ከባዱና አንድ ሰው በዚያው ያለ ተውበት ከሞተ ምህረት የሌለው የሆነው ሺርክ ምንም ቦታ እንዳይኖረው አድርገዋል። ሁለቱን የተቀደሱ ቦታዎችን ደህንነት በአግባቡ ጠብቀዋል። አላህ መልካም ምንዳቸውን ይመንዳቸው!! ለመልካሙም ይግጠማቸው!! ከውስጥም ከውጪም ሴረኞችና ምቀኞች ይጠብቃቸው!! ✍🏻ኢብን ሽፋ #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

لو ترجمتم  هذه الصوتية يا مترجمي السلفيين كشيخنا يوسف وابن شفا وجبريل وسمير وغيرهم كثر الله من أمثالكم وثبتكم على الهدى حتى الموت.

‏فيديو من حسين عبد الله

ظاهرة اضطراب الدعوة السلفية في هذا العصر يرجع سببه إلى التصدر قبل التأهل والتسرع وادعاء العلم قال الإمام الألباني: "إن الدعوة السلفية الآن -مع الأسف- في اضطراب، وأعزو السبب في ذلك إلى تسرع كثير من الشباب المسلم في ادعاء العلم، فهو يتجرأ على الإفتاء والتحريم والتحليل قبل أن يُعرف، بعضهم -كما سمعنا كثيرا- لا يحسن أن يقرأ آية من القرآن، ولو أنها أمامه في المصحف الكريم، فضلا عن أنه كثيرا ما يلحن في قراءة حديث الرسول عليه الصلاة والسلام، فيصدق فيه المثل المعروف في بعض البلاد: "تزبب قبل أن يتحصرم" أي: العنب حينما يبدأ يصير حباً أخضر، وهذا هو الحصرم، ويكون حامضا جدا، فهو قبل أن يتحصرم جعل نفسه كالزبيب، أي: كالعنب الذي نضج وصُيِّرَ زبيباً، ولذلك فركوب كثير من هؤلاء الناس رءوسهم وتسرعهم في ادعاء العلم والكتابة، وهم لَمْ يمشوا بعد إلى منتصف طريق العلم، هو الذي جعل الذين ينتمون للدعوة السلفية الآن -مع الأسف- شيعا وأحزابا".

🌊✨ ጥያቄ ! ✨🌊 📖❓ በሸሪዓችን «ቢድዓቱል ሐሰና» (ጥሩ ቢድዓ) የሚባል ነገር አለንዴ? 👇 ትክክለኛውን መልስ በመንካት የሚመጣላችሁን የሰለፊዮች ቻናል ይቀላቀሉ! 📲🌊

የዕውቀት ባለቤቶችን (ዑለማዎችን) መቀማመጥና ማማከር—በተለይም በሀገራችን ኢትዮጵያ የባህርዳር መሻይኾችን... በዚህ በጊዜያችን ካሉት የብልሃት፣ የዕውቀትና የርጋታ ባለቤቶች መካከል የባህር ዳር መሻ
የዕውቀት ባለቤቶችን (ዑለማዎችን) መቀማመጥና ማማከር—በተለይም በሀገራችን ኢትዮጵያ የባህርዳር መሻይኾችን... በዚህ በጊዜያችን ካሉት የብልሃት፣ የዕውቀትና የርጋታ ባለቤቶች መካከል የባህር ዳር መሻይኾችንና ወጣቶቻቸውን በበጎ እንቀናባቸዋለን። እነሱ የዳዕዋን ጥቅም የሚመለከት ማንኛውንም ውሳኔ በመመካከር (በሹራ) እንጂ አይወስኑም። አንዳቸው ሌላውን አያቃልሉም፤ በእነሱ ዘንድ የራስን ሃሳብ ብቻ መጫን (አምባገነንነት)፣ እራስ ወዳድነትና የመሪነት ፍላጎት (የስልጣን ጥመኝነት) የለም። በዚህም ምክንያት በእነሱ ዘንድ ልዩነቶችን፣ ግጭቶችን፣እንዲህ አሉ ታባለ፣ ቅሬታዎችን አታገኝም። ለመመካከር ባላቸው ከፍተኛ ጉጉትና ጥንቃቄ የተነሳ ውሳኔዎቻቸው ሁሉ ትክክለኛና ስኬታማ ናቸው። ይህም አላህ ለሚሻው ሰው የሚሰጠው ትልቅ ችሮታ (ፈድል) ነው። ሰለፊይ ወንድሞቼን የእነሱን ፈለግ እንዲከተሉና በአስቸጋሪ (በተወሳሰቡ) ጉዳዮች ላይ እንዲያማክሯቸው እመክራለሁ።
📚ምንጭ፦ አምሳ ምክሮች ለዲን ተማሪዎች ከሚለው ሪሳለህ (ቁጥር 23)]
✍ ሸይኽ ዶክተር ሁሰይን ቢን ሙሐመድ አስ-ሱልጢይ (ሀፊዘሁላህ) https://t.me/semirEnglish https://t.me/semirEnglish

Repost from Abdusomed Muhamed
ከመግሪብ እስከ ዒሻ ባለው ከገፅ 1 ዛሬ ኢንሻአላህ ይጀምራል! በቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን

Repost from Abdusomed Muhamed
الواضح_في_تيسير_منهج_السلف_الصالح .pdf

🔷ለሰለፍዮች ምክር ዶክተር ሸይኽ ሁሴን ሙሀመድ አስስልጢ - ሀፊዞሁሏሁ - እንዲህ ብለዋል :- "ሰለፍይ ወንድምህ ስህተት ከሰራ ፣ ለመውቀስ ወይም ለማዋረድ አትቸኩል።  በምትኩ በጥበብ በምክር እና በትእግስት (እርሱ የሚስተካከልበትን መንገድ) መፍትሄ አፈላልግ። እንደ ሀዳድያ አትሁን። አንዳንድ ወደ ሱና የተጠጉ፣ ለእርሷ ጉጉት ያላቸው ሰዎች ይህ አካሄድ ከሰለፎች የመጣ መስሏቸው ፣ ሱና እና ሰለፎች በምን ላይ እንዳሉ ባለማወቃቸው ምክንያት ይህ የሰለፎች ጎዳና ነው ብለው በመጠርጠር በዚህ (ችግር) ውስጥ ወድቀው ይገኛሉ። ስለዚህ ወንድምህ ለእውነትና ለምክር ምላሽ ካልሰጠ ፣ ማስረጃህን ሰብስብና ጉዳዩን ለታመኑ የእውቀት ባለቤቶች አቅርብ ፣ እነርሱንም አማክር።" الرسالة خمسون النصيحة لطلاب العلم ص/١٩ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

Repost from N/a
✨️ ነጻ የሰለፊዮች ቻናል ግብዣ ✨️ 🔴ይህን ቀላል 🤏 ጥያቄ ለመለሰ ነጻ የሰለፊዮች ቻናል ግብዣ አለው ⚡️ ♻️ አላህ {سبحانه وتعالى } ስራችንን ሊያሳምርልን እና ወንጀላላችንን ሊምርልን ዘንድ ከኛ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል⁉️ 🔹️______________________________🔹️ 📎 ምንጭ :- ከላይ ካለው ቪዲዮ 👆

Repost from N/a
✨️ ነጻ የሰለፊዮች ቻናል ግብዣ ✨️ 🔴 ይህን ቀላል ጥያቄ ለመልስ ነጻ የሰለፊዮች ቻናል ግብዣ አለው ⚡️ ♻️ አህል {سبحانه وتعالى } ስራችንን ለማሳሰብ እና ስህተታችንን ለማስተካከል ከእኛ ምን ዓይነት ተግባር ይጠበቅብናል⁉️ 🔹️________________________________🔹️ 📎 ምንጭ :- ከላይ ካለው ቪዲዮ 👆