uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa

ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa

Відкрити в Telegram

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa

Канал ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa (@ibnshifa) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 20 152 підписників, посідаючи 3 929 місце в категорії Релігія і духовність та 1 789 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 20 152 підписників.

За останніми даними від 24 жовтня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 192, а за останні 24 години на 8, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 10.56%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 4.53% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 2 129 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 914 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 0.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 25 жовтня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

20 152
Підписники
+824 години
+477 днів
+19230 днів
Архів дописів
ሠለፊይነት ሲሞቅ የሚወልቅ ሲበርድ የሚለበስ ካቦርት አይደለም!! ——— የ የመኑ ሙሀዲስ በመባል የሚታወቁት በሺዓና በኢኽዋን መሃል ቁጭ ብለው በጊዜያቸው ጥርት ያለውን የሠለፊያን ደዕዋ ያስፋፉት ታላ
ሠለፊይነት ሲሞቅ የሚወልቅ ሲበርድ የሚለበስ ካቦርት አይደለም!! ——— የ የመኑ ሙሀዲስ በመባል የሚታወቁት በሺዓና በኢኽዋን መሃል ቁጭ ብለው በጊዜያቸው ጥርት ያለውን የሠለፊያን ደዕዋ ያስፋፉት ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙቅቢል አል-ዋዲዒይ (ረሂመሁላህ) ሠለፊያን አጠር ባለ መልኩ ሲገልጿት እንዲህ አሉ:- “ሠለፊያ እንደ ካቦርት ማውለቅ ሲፈልጉ የሚያወልቋት አይደለችም። ይልቅ በደጋግ ሠለፎች ግንዛቤ በቁርኣንና በሐዲስ ላይ መጣበቅ ነው” [ቱህፈቱል ሙጂብ 171] ➣ ዛሬ ላይ ሀቂቃ የብዙ ሰዎች ሁኔታ ሲታይ በጣም ያሳዝናል!! 🔹 አንዳንዱ የነፍሲያን ነገር ጨምሮበት በሆነ ነገር ሲያኮርፍ ሌላውን የጎዳ መስሎት ከቢድዐህ ባለ ቤቶችና ከጭፍሮቻቸው ጋር ሲያብርና የሠለፊይ ወንድሞቹን ስም ሲያጎድፍ፣ በሰለፊይ ወንድሞቹ መካከል ፊትና ለመፍጠር ሲታትር ይስተዋላል። ሌላኛው ደግሞ ዒልሚይ በሆኑ ነጥቦች የተሳሳቱ ሰዎችን በማስረጃ አንስቶ ሲተች ይከርምና በዚህች ጠፊ በሆነችው ዱኒያዊ ጥቅማጥቅም ምክንያት አፉ ተለጉሞ ቆይቶ በመጨረሻም ሰለፊይነቱን አውልቆ ይጥልና በሱንና ሰዎች ላይ አንበሳ በቢድዐህ ሰዎች ላይ ደግሞ ሬሳ ሆኖ ብቅ ይላል። እንዲሁም ከፊሉ የሰለፊያን መንገድ ጫፍ ላይ ሆኖ ይዣለሁ ይልና መሀይምነቱም ተጨማምሮበት የሆነ የሚያደንቀው አካል ሰለፊያን እንደ ካቦርት አውልቆ ሲጥላት ተመልክቶ ጓዙን ጠቅልሎ ሲከተለው ይስተዋላል። አላህ በሐቅ ላይ እርሱን እስክንገናኘው ድረስ ያፅናን!! ✍🏻ኢብን ሺፋ የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት #join ↘️↘️ በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

📖📚 አዲስ መፅሐፍ 📚📖
✅ የዝንባሌ ባለቤቶችን በመራቅና ከእነርሱ በማስጠንቀቅ ላይ የዑለሞች ስምምነት
"إجماع العلماء على الهجر والتحذير من أهل الأهواء "
🖋 ኻሊድ ብን ዶሃዊይ አዝ’ዞፊሪ በዐረብኛ ያዘጋጀው የጥናት ፅሁፍ፤ 📝 🖋 በአቡ ዐብዲል0ዚዝ ሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ (ሐፊዞሁሏህ) ወደ አማርኛ ተመልሶ ለአንባቢያን ቀርቧል፤ ታላላቅ መሻኢኾች መቅድም ያዘጋጁለት 🖌 የተከበሩ ሸይኽ ረቢዕ ብን ሃዲ ዑመይር አል’መድኸሊ 🖌የተከበሩ ሸይኽ ዘይድ ብን ሙሐመድ ብን ሃዲ አል’መድኸሊ 🖌የተከበሩ ሸይኽ ዑበይድ ብን ዐብዲ’ላህ አል’ጃቢሪ 📚 ሁሉም ሊያነበው የሚገባ ድንቅ መፅሐፍ‼️ 🔄 ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን‼️ 🤲 አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን‼️ የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ كن على بصيرة https://t.me/alateriqilhaq

🔷 አእምሯችንን  ለማንም አናስረክብ ኢማም አልሙሐዲስ ሸይኽ ሙቅቢል ብን ሓዲ አልዋዲዒይ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ አሉ :- "የሱና ሰዎች ሆይ! አስጠነቅቃችኋለሁ! አስጠነቅቃችኋለሁ! የምትወዱት ሰው ማንም ቢሆን፣ አእምሯችሁን በእርሱ እጅ አትስጡ።  'በእኛና በእናንተ መካከል የሚያጣቅሰን የአላህ መጽሐፍ (ቁርኣን) እና የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሱና ይሁን' በሉ። ማንም ይሁን ማን ፣ አእምሯችንን በእርሱ ፈቃድ እንዲያስተዳዶረው ለማንም አናስረክብ።" والله المستعان المصدر : (الإمام الألمعي : (٢٦٧) https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

ሳምንታዊ የዳር አስ-ሱንና የእለተ እሁድ ደርስ 🕰 ከረፋዱ 3:50 እስከ ዙህር የሚቆይ በኡስታዝ አቡ ሙዓዝና በኡስታዝ ሻኪር የሚሰጥ ኪታቦች:- ኪታብ ① الحث على المودة والإئتلاف والتحذير من الفرقة والاختلاف በመወዳጀትና በመግባባት ላይ ማነሳሳትና ከልዩነትና ከቡድንተኝነት ማስጠንቀቅ!! لفضيلة الشيخ الدكتور ربيع بن هادي عمير المدخلي رحمه الله የኪታብ pdf ↘️ https://t.me/DarASSunnah1444/15820 🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ - ታጁዲን (ሀፊዘሁላህ) ኪታብ ② كتاب نور التوحيد وظلمات الشرك في ضوء الكتاب والسنة የተውሒድ ብርሃንነትና የሺርክ ጨለማነት በቁርኣንና በሀዲስ ብርሃን ሲቃኝ የኪታብ pdf ↘️ https://t.me/DarASSunnah1444/15819 🎙በኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን (ሀፊዘሁላህ)

ከሙመይዓና ከአስተሳሰቧ ማስጠንቀቅ!! ——— ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ “የሙመይዓን ተጣሪዎች ተጠንቀቃቸው፣ ሌሎችንም ከቢድዐህ ባለቤቶች ጋር መቀማመጥን፣ መተባበርንና የቢድዐህ ባለቤትን ማወደስን የሚያቃልሉትን (ተጠንቀቅ)፣ ከአንበሳ እንደምትሸሸው ሽሻቸው!። ሙመይዓዎች ሰለፊዮችን የደጋግ ቀደምቶችን መንገድ በመከተላቸው ምክንያት በአጥባቂነት ይወርፏቸዋል።” [አት-ተመሱኩ ቢሱነቲ ነጃት ገፅ 9] #join ↘️ ቴሌግራም https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa

✅ ቅድሚያ በዲን ላይ መፅናትና በሱንና ላይ መጣበቅ!! ሰውሪይ - ረሂመሁላህ - እንዲህ አሉ:- “ይህ ዘመን ትርፍ ነገር የሚፈለግበት ሳይሆን ይልቅ በዲኑ ላይ በመጣበቅ የሚፀኑበት ዘመን ነው።” [አንሳቡ'ል አሽራፍ] ሸይኽ ጦሃ - ሀፊዘሁላህ - ከሰውሪይ ንግግር ስር በማንጠልጠል እንደነ ሰውሪይ በነበሩ ታላላቅ ሊቃውንቶች ዘመን ይህ ከተባለ "እኛ ባለንበት ዘመን ደግሞ እንዴት ሊሆን ነው?" በማለት ይጠይቃሉ። የሰውሪይ ንግግር ለሌሎች ዒባዳዎች ትኩረት አይሰጥ ማለት እንዳልሆነ ግልፅ ነው፣ ይልቅ ከሁሉም በላይ በተውሒድና ሱንና ላይ በመፅናት ጉዳይ ልዩ ትኩረት ይሰጥ ማለታቸው ነው!! #join ↘️ ቴሌግራም https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa

✅ ቅድሚያ በዲን ላይ መፅናትና በሱንና ላይ መጣበቅ!! ሰውሪይ - ረሂመሁላህ - እንዲህ አሉ:- “ይህ ዘመን ትርፍ ነገር የሚፈለግበት ሳይሆን ይልቅ በዲኑ ላይ በመጣበቅ የሚፀኑበት ዘመን ነው።” [አንሳቡ'ል አሽራፍ] ሸይኽ ጦሃ - ሀፊዘሁላህ - ከሰውሪይ ንግግር ስር በማንጠልጠል እንደነ ሰውሪይ በነበሩ ታላላቅ ሊቃውንቶች ዘመን ይህ ከተባለ "እኛ ባለንበት ዘመን ደግሞ እንዴት ሊሆን ነው?" በማለት ይጠይቃሉ። የሰውሪይ ንግግር ለሌሎች ዒባዳዎች ትኩረት አይሰጥ ማለት እንዳልሆነ ግልፅ ነው፣ ይልቅ ከሁሉም በላይ በተውሒድና ሱንና ላይ በመፅናት ጉዳይ ልዩ ትኩረት ይሰጥ ማለታቸው ነው!! #join ↘️ ቴሌግራም https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa

التمسك والثبات أولا قال الثوري رحمه الله: "ليس هذا بزمان طلب فضل ولكنه زمان تمسك" "أنساب الأشراف" وكيف بزماننا؟

የተውሒዷን እንዲሁም በዓለማችን ብቸኛዋ በሸሪዓ ሕግ ምትተዳደረዋን ሀገር ጠል የሆነውና የኢኽዋን አል-ሙስሊሙን አቀንቃኝ የሆነው አቶ ራያ አባ መጫ—ሁሲየዎች በሳዑዲ አረቢያ ላይ ጥቃት በመፈፀማቸው ሲያሾፍና ሲሳለቅ እንዲህ በማለት በፌስቡክ ገፁ ላይ ለጥፏል: «Saudiiyee ????? gaafa Gazzaan ibiddaan gubamaa turte isin wollistoota awurophaadhaa fiddanii wollisiisaa turtanii yeroo isin tuqamtan meerre deeggartoonni keessan??» የራያ ፅሁፍ በግርድፉ ሲቶረገም የሚከተለው ነው፦ «ሳዑዲዬ???! ጋዛ በእሳት ስትቃጠል ጊዜ፣ እናንተ የአውሮፓ ዘፋኞችን እያመጣችሁ ታዘፍኑ ነበር፤ አሁን እናንተ ስትነኩ  ደጋፊዎቻችሁ ታዲያ የታሉ??» ሸይኽ ጦሃ ኸድር—አቡ ዐብዲላህ (ሀፊዘሁላህ) ለራያ የሚከተለውን ምላሽ ሰጡ፦ «የራፊዷ (የሺዓ) ጫጩቶችና ጭራዎች፣ ሁሲዎች የሁለቱን የተከበሩ መስጂዶች ያሉባትን ምድር (ሳዑዲ ዐረቢያን) በመደብደባቸው ደስታቸውን መግለጻቸውና በጥቃቱ ማመካኘታቸው — አመፀኛው ዘፋኝ ራያ አባ መጫ እንደ ማሳያ/ናሙና።» ✍ ግርድፍ ትርጉም፦ አቡ ሐፍሳ https://t.me/semirEnglish

Repost from N/a
─── 🕌 ─── ✨ ዒልምን በቤትዎ! በቤቶ ሳይወጡ የዲን #ዕውቀትዎን ለማዳበር እና የመንፈስ እረፍት ለማግኘት ይፈልጋሉ? ─ የሚያገኙዋቸው ይዘቶች ── ▫️ 📖 የቁርኣን ተፍሲርና የሐዲስ ትምህርቶች ▫️ ✍️ አስተማሪ ኢስላማዊ ጽሑፎች ▫️ 🧠 ዕውቀትዎን የሚያድሱ ጥያቄና መልሶች ─ 🌙 ─ የኸይርን መንገድ #እቤትዎ ሆነው ይከተሉ፤ አሁኑኑ ይቀላቀሉን! ───────────

አትቀያየር! መቀያየር ከአህሉሱንናዎች ባህሪ አይደለም!! ————— ሑዘይፋ ኢብኑል የማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- “ጥመት ብሎ ማለት፣ ትክክለኛው ጥመት የምታወግዘው የነበረውን ነገር እውቅና መስጠትህ ነው። የምታውቀው የነበረን ሀቅ ደግሞ ማውገዝህ ነው። ወዮልህ በዲን ላይ መቀያየርን ተጠንቀቅ!፣ የአላህ ዲን አንድ ነው።” [አል-ኢባነቱል ኩብራ 571] ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:- “…የስሜት ባለቤት ስሜቱ እውርና ደንቆሮ ያደርገዋል። በዚህ የተነሳም አላህንና መልእክተኛውን አያስታውሱም። ማስታወስም አይፈልጉም። አላህና መልእክተኛው የወደዱትንም ነገር አይወዱም። አላህንና መልእክተኛውን ለሚያስቆጣቸው ነገር አይቆጣም። ይልቅ ስሜቱ የሚወደው ነገር ሲከሰት ነው የሚወደው፣ ስሜቱ የሚጠላው ነገር ሲከሰትም ነው የሚጠላው…።” [ምንጭ:- ሚንሀጅ አስሱና 5/256] በአሁን ሰዓትም በብዛት እየታየ ያለው ተጨባጭ ይህ ነው። የቢድዓ ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች መድረክ ሲያገኙ ደስታቸውን የሚገልፁና ያሻቸውን የሚናገሩት ስሜታቸው የወደደውና የጠላውን ነው። የሚናገሩት ነገር አላህንና መልእክተኛውን የሚያስቆጣና በቀጥታ የቁርኣንና የሀዲስ ማስረጃዎችን የሚጋጭ ቢሆንም ጉዳያቸው አይደለም!። ምክንያቱም እነርሱ በስሜት ታውረዋል፣ ሲነገራቸውም አይሰሙም በስሜት ደንቁረዋል። በመሆኑም የሀቅ ሰዎች ከምንጊዜውም በላይ ነቅተው የቢድዓ ሰዎች በተግባራቸውና በምላሳቸው በህዝቡ ከባጢል ጋር የሚያቀላቅሉበትን ሀቅ ለህዝቡ ግልፅ ሊያደርጉና ሊያብራሩ ይገባል!። ታላቁ ዓሊም ኢብኑ ዐጣር (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:- “ሀቅን ግልፅ ከማድረግና ከማብራራት፣ መደበቅን ከመተው፣ እውነቱን ከውሸት ግልፅ አድርጎ ለይቶ ከማብራራት ቅሮት የለውም!!። የላቀው አላህ የሚያበላሸውን ከሚያሳምረው፣ የሚሸፋፍነውን ግልፅ ከሚያደርገው ለይቶ ያውቀዋል።” [ምንጭ:- ሪሳለቱ ሰማዕ 48] አል ሃፊዝ ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:- “ሀቁ ከባጢሉ ከተመሳሰለና ሀቁን ግልፅ ከማድረግ ዝም ከተባለ፣ በመካከላቸው ከእውነት ይልቅ መሀይምነትና ፍጡርን ማጥመም ይወለዳል።” [አስሶዋዒቅ አልሙርሰለህ 52] ታላቁ ዓሊም ሸይኽ አህመድ ቢን የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:- “እነዚያ ለሰዎች እውነትን ግልፅ ከማድረግና ከማብራራት ዝም ያሉ ሰዎች በዝምታቸው ዑዝር አይሰጣቸውም። ምንም እንኳን እኛ ከባጢል ሰዎች አይደለንም ቢሉም ዑዝር አይሰጣቸውም።” [ምንጭ:- ተህዚሩ ሰለፊይ ሚን መንሀጅ አትተምይዕል ኸለፊይ 311] ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:- “በሀገርህ ወደ ሱንና እና ቀደምቶችን ወደ መከተል የምትጠራው አንተ ብቻ ከሆንክ፣ ውዳቂ ወደሆነው መንገዳቸው የሚጣሩ ጠላቶችህ ከበዙ፣ በአንተ ላይ ግዴታው ተስፋ አለመቁረጥ ነው!!። ተስፋ ከቆረጥክ ከሀቅ ነው ተስፋ የቆረጥከው። ይልቅ ፅና! ጠላቶችህ የፀናህ ሆነህ ማየት ነው የሚያስፈራቸው።” [ሸርህ አል ካፊያ አሻፊያ 1/201] ታላቁ ዓሊም ሙሀዲስ ሸይኽ ሙቅቢል (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:- “ደዕዋ እኛ ዘንድ ከነፍሳችን፣ ከቤተሰባችን፣ ከንብረታችን በላይ ነው። አፈር መብላት ካለብን አፈር ለመብላት ዝግጁ ነን። ዲናችንና ሀገራችንን አናታልልም። አንቀያየርም። መቀያየር ከአህሉሱንና ባህሪ አይደለም!።” [ምንጭ:- አልባዒስ ዐላ ሸርህ አል ሀዋዲስ 87] ታላቁ ሸይኽ ዶ/ር ሙሀመድ ቢን ሰዒድ ረስላ (አላህ ይጠብቃቸውና) እንዲህ ይላሉ:- “…እኛ በመዋለል ላይ አይደለንም!። አህሉሱንናዎች አይዋልሉም!። እንዴት ይዋልላሉ? አላህ በቁርኣኑ እና በነቢዩ ﷺ ሱንና አብቃቅቷቸው እያለ፣ አህሉሱንናዎች አንድም ቀን እንኳን በመዋለል ላይ አይሆኑም!!።” [ከድምፃቸው የተወሰደ] ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

photo content

📎📔 አዲስ ፒዲኤፍ 📄
ስለሰይድ ቁጥብ ኢብራሂም ሁሰይን የሙሐመድ ሃሚዲንን ጥርጣሬዎች እና የተሳሳቱ አመለካከቶች ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል ግልጽ ምዕራፍ
🖋 በዶክተር ሸይኽ ሑሰይን ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲላህ አስ'ስልጢይ (ሐፊዞሁሏህ) በዐረብኛ ተዘጋጅቶ፤ 📝 🖋 በአቡ ዐብዲል0ዚዝ ሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ (ሐፊዞሁሏህ) ወደ አማርኛ ተመልሶ ቀረበልዎ‼️ 🔄 ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን‼️ 🤲 አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን‼️ የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ كن على بصيرة https://t.me/alateriqilhaq

🎁ስጦታ እውቀትን ለምትወዱ ሰዎች ከታች ያለችውን OPEN የምትሉዋን ነገር በመጫን የሰለፊዮችን ቻናል ይቀላቀሉ

የላ! ኢላሀ ኢለላህን ቃል ምስክርነት ማረጋገጥ!! ——— ሸይኹ'ል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “ከአንድ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም!፣ የሚለውን የምስክርነት ቃል ማረጋገጥ፣ ለአላህ ብሎ እንጂ አለመውደድን፣ለአላህ ብሎ እንጂ አለመጥላትን፣ለአላህ ብሎ እንጂ አለመወዳጀትን፣ጥላትነትንም ለአላህ ብሎ እንጂ እንዳይመሰርት፣ እንዲሁም አላህ የወደደውን መውደድን፣ አላህ የጠላውን መጥላት ያስፈርዳል!!።” [መጅሙዕ አልፈታዋ 8/337] #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

قال شيخ الإسلام ابن تيمية -رحمه الله-: " إن تحقيق شهادة أن لا إله إلا الله يقتضي أن لا يحب إلا لله، ولا يبغض إلا لله، ولا يوالي إلا لله، ولا يعادي إلا لله، وأن يحبّ ما أحبّه الله، ويبغض ما أبغضه الله ". 📚مجموع الفتاوى 8/337

በአንድ ነገር ላይአቋም ከመያዝህ በፊት ጠንካራ ማስረጃ አጥብቀህ ያዝ!! ————— አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዙ በፊት አስተማማኝና ጠንካራ ማስረጃ ከያዘ፣ ዱኒያ ላይ ሰዎች ፊት፣ በአኼራም አላህ ፊት አይዋረድም። እውነተኛ የሆነ ሰው በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዙም በፊት ሆነ ከመናገሩ በፊት በቂ ማስረጃ መያዝ እንዳለበትና እርግጠኛ መሆን እንዳለበት ግልፅና ለማንም የማይሰወር ነገር  ነው። አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዙ በፊት ትክክለኛ የሆነን ማስረጃ ካልያዘ፣ የያዘው አቋምና አመለካከት ትክክል ሳይሆን ቀርቶ በሌሎች ሲተችበት ለጭንቀቱ ማምለጫ ሊሆነኝ ይችላል: ብሎ ያሰበውን ሁሉ እያመጣ ሲደረድር ይበልጥ ወደ ሌላ ጥፋት ያመራል። ለዚያም ነው፣ በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዝ በፊት ትክክለኛ የሆነን ማስረጃ መያዝ የአህሉሱንናዎች መገለጫ ነው። በተቃራኒው ደግሞ በአንድ ነገር ላይ አቋም ከያዙ በኋላ ማስረጃ መፈለግ የቢድዐ ሰዎች ባህሪና ልዩ መገለጫ ነው። ምናልባትም አንዳንዴ በራሳቸው ላይ ማስረጃ ሊሆንባቸው የሚችልን ማስረጃ ያለቦታው ሲያቀርቡት ይስተዋላል። አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ ያለ በቂ ማስረጃ አስቀድሞ አቋም ከያዘ የምታመጣለትን ማስረጃ ሁሉ በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ ሳይሆን ራሱ አስቀድሞ ለያዘው አቋም በሚመቸው መልኩ ብቻ መቀበል ነው የሚፈልገው። ይህ ደግሞ ወደ ጥመት የሚመራው በጣም ከባድ አደጋ ነው!!። ለዚያም ነው የሱንና ሰዎች በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዛቸው በፊት ትክክለኛውን ማስረጃ በደጋግ ቀደምቶቻቸው ግንዛቤ መሰረት ከቡድንተኝነትና ወገንተኝነት ገለልተኛ ሆነው ይፈልጋሉ፣ ከዚያም በኋላ አቋም ይዛሉ። የቢድዐ ሰዎች ደግሞ አስቀድመው አቋም ይዛሉ ከዚያም በኋላ ለያዟት አቋም ትሆነናለች ብለው ያሰቧትን ብዥታ ሁሉ እንደ ማስረጃ አንግበው ይንቀሳቀሳሉ። ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) እንዳሉትም "ለቢድዐ ሰዎች ብዥታ እንጂ ማስረጃ የላቸውም።" ለዚያም ነው፣ አስቀድሞ በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ መሰረት ትክክለኛውን ማስረጃ ከመያዙ በፊት አቋም የያዘ ሰው፣ ቁርኣንና ሀዲስን በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤና አካሄድ መሰረት ይዘህለት ብትቀርብም ለራሱ አቋም በሚመቸው መልኩ ቀዶ ካልሰፋው የማይሆንለት። ከዚህም አልፎ አንዳንዴ የያዘውን አቋም ትክክል አለመሆኑን በማስረጃ ስታወግዝበት በቂ ማስረጃ ሲያጣ ከገባበት ማጥ ለማምለጥ ጉዳዩን በተዘዋዋሪም ይሁን በቀጥታ የግል የግጭት ጉዳይ ለማስመሰል ይኳትናል። ምናልባትም በማስረጃ የነቀፉትን ሰዎች ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ የግል ታሪካቸውን፣ (መቼም የሰው ልጅ ባህሪ ይለያያልና) በግል ባህሪያቸው… የመሳሰሉ ከዲን ነጥብ ውጪ ወይም ከተተቹበት አጀንዳ ውጪ የሆኑ ጉዳዮችን እያነሱ ሲወርፉ ማየትም ሊስተዋል ይችላል። ይህ ይበልጥ በቂ ማስረጃ ሳይኖራቸው አቋም መያዛቸውን የሚያሳብቅ ሲሆን! ምንም እንኳን የግል ፀብ ቢኖርም ባይኖርም ማንኛውም ገለልተኛ አካል ይህ ሰው አቋም የያዘበት ጉዳይ ሲነቀፍ ከተመለከተ ማየት ያለበት ሰውዬው አቋም የያዘበትን ማስረጃና ነቃፊው አካል የሚያቀርበውን ማስረጃ ክብደት ብቻና ብቻ ነው!። በመሆኑም አንድ ሱኒይ ነኝ የሚል ሰው የሚጠበቅበት፣ በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዙ በፊት ተረጋግቶ ግራና ቀኙን በማየት ትክክለኛውን ማስረጃ በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ መሰረት አጥብቆ መያዝ ግድ ይለዋል!!። ✍🏻 ኢብን ሽፋ t.me/ibnshifa የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join አድርገው ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f