ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa

ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa

前往频道在 Telegram

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

显示更多

📈 Telegram 频道 ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa 的分析概览

频道 ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa (@ibnshifa) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 20 156 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 3 929,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 789 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 20 156 名订阅者。

根据 24 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 192,过去 24 小时变化为 8,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 10.56%。内容发布后 24 小时内通常能获得 4.53% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 2 129 次浏览,首日通常累积 914 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 0。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን”

凭借高频更新(最新数据采集于 25 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

20 156
订阅者
+824 小时
+477 天
+19230 天
帖子存档
ከሙመይዓና ከአስተሳሰቧ ማስጠንቀቅ!! ——— ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ “የሙመይዓን ተጣሪዎች ተጠንቀቃቸው፣ ሌሎችንም ከቢድዐህ ባለቤቶች ጋር መቀማመጥን፣ መተባበርንና የቢድዐህ ባለቤትን ማወደስን የሚያቃልሉትን (ተጠንቀቅ)፣ ከአንበሳ እንደምትሸሸው ሽሻቸው!። ሙመይዓዎች ሰለፊዮችን የደጋግ ቀደምቶችን መንገድ በመከተላቸው ምክንያት በአጥባቂነት ይወርፏቸዋል።” [አት-ተመሱኩ ቢሱነቲ ነጃት ገፅ 9] #join ↘️ ቴሌግራም https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa

✅ ቅድሚያ በዲን ላይ መፅናትና በሱንና ላይ መጣበቅ!! ሰውሪይ - ረሂመሁላህ - እንዲህ አሉ:- “ይህ ዘመን ትርፍ ነገር የሚፈለግበት ሳይሆን ይልቅ በዲኑ ላይ በመጣበቅ የሚፀኑበት ዘመን ነው።” [አንሳቡ'ል አሽራፍ] ሸይኽ ጦሃ - ሀፊዘሁላህ - ከሰውሪይ ንግግር ስር በማንጠልጠል እንደነ ሰውሪይ በነበሩ ታላላቅ ሊቃውንቶች ዘመን ይህ ከተባለ "እኛ ባለንበት ዘመን ደግሞ እንዴት ሊሆን ነው?" በማለት ይጠይቃሉ። የሰውሪይ ንግግር ለሌሎች ዒባዳዎች ትኩረት አይሰጥ ማለት እንዳልሆነ ግልፅ ነው፣ ይልቅ ከሁሉም በላይ በተውሒድና ሱንና ላይ በመፅናት ጉዳይ ልዩ ትኩረት ይሰጥ ማለታቸው ነው!! #join ↘️ ቴሌግራም https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa

✅ ቅድሚያ በዲን ላይ መፅናትና በሱንና ላይ መጣበቅ!! ሰውሪይ - ረሂመሁላህ - እንዲህ አሉ:- “ይህ ዘመን ትርፍ ነገር የሚፈለግበት ሳይሆን ይልቅ በዲኑ ላይ በመጣበቅ የሚፀኑበት ዘመን ነው።” [አንሳቡ'ል አሽራፍ] ሸይኽ ጦሃ - ሀፊዘሁላህ - ከሰውሪይ ንግግር ስር በማንጠልጠል እንደነ ሰውሪይ በነበሩ ታላላቅ ሊቃውንቶች ዘመን ይህ ከተባለ "እኛ ባለንበት ዘመን ደግሞ እንዴት ሊሆን ነው?" በማለት ይጠይቃሉ። የሰውሪይ ንግግር ለሌሎች ዒባዳዎች ትኩረት አይሰጥ ማለት እንዳልሆነ ግልፅ ነው፣ ይልቅ ከሁሉም በላይ በተውሒድና ሱንና ላይ በመፅናት ጉዳይ ልዩ ትኩረት ይሰጥ ማለታቸው ነው!! #join ↘️ ቴሌግራም https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa

التمسك والثبات أولا قال الثوري رحمه الله: "ليس هذا بزمان طلب فضل ولكنه زمان تمسك" "أنساب الأشراف" وكيف بزماننا؟

የተውሒዷን እንዲሁም በዓለማችን ብቸኛዋ በሸሪዓ ሕግ ምትተዳደረዋን ሀገር ጠል የሆነውና የኢኽዋን አል-ሙስሊሙን አቀንቃኝ የሆነው አቶ ራያ አባ መጫ—ሁሲየዎች በሳዑዲ አረቢያ ላይ ጥቃት በመፈፀማቸው ሲያሾፍና ሲሳለቅ እንዲህ በማለት በፌስቡክ ገፁ ላይ ለጥፏል: «Saudiiyee ????? gaafa Gazzaan ibiddaan gubamaa turte isin wollistoota awurophaadhaa fiddanii wollisiisaa turtanii yeroo isin tuqamtan meerre deeggartoonni keessan??» የራያ ፅሁፍ በግርድፉ ሲቶረገም የሚከተለው ነው፦ «ሳዑዲዬ???! ጋዛ በእሳት ስትቃጠል ጊዜ፣ እናንተ የአውሮፓ ዘፋኞችን እያመጣችሁ ታዘፍኑ ነበር፤ አሁን እናንተ ስትነኩ  ደጋፊዎቻችሁ ታዲያ የታሉ??» ሸይኽ ጦሃ ኸድር—አቡ ዐብዲላህ (ሀፊዘሁላህ) ለራያ የሚከተለውን ምላሽ ሰጡ፦ «የራፊዷ (የሺዓ) ጫጩቶችና ጭራዎች፣ ሁሲዎች የሁለቱን የተከበሩ መስጂዶች ያሉባትን ምድር (ሳዑዲ ዐረቢያን) በመደብደባቸው ደስታቸውን መግለጻቸውና በጥቃቱ ማመካኘታቸው — አመፀኛው ዘፋኝ ራያ አባ መጫ እንደ ማሳያ/ናሙና።» ✍ ግርድፍ ትርጉም፦ አቡ ሐፍሳ https://t.me/semirEnglish

Repost from N/a
─── 🕌 ─── ✨ ዒልምን በቤትዎ! በቤቶ ሳይወጡ የዲን #ዕውቀትዎን ለማዳበር እና የመንፈስ እረፍት ለማግኘት ይፈልጋሉ? ─ የሚያገኙዋቸው ይዘቶች ── ▫️ 📖 የቁርኣን ተፍሲርና የሐዲስ ትምህርቶች ▫️ ✍️ አስተማሪ ኢስላማዊ ጽሑፎች ▫️ 🧠 ዕውቀትዎን የሚያድሱ ጥያቄና መልሶች ─ 🌙 ─ የኸይርን መንገድ #እቤትዎ ሆነው ይከተሉ፤ አሁኑኑ ይቀላቀሉን! ───────────

አትቀያየር! መቀያየር ከአህሉሱንናዎች ባህሪ አይደለም!! ————— ሑዘይፋ ኢብኑል የማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- “ጥመት ብሎ ማለት፣ ትክክለኛው ጥመት የምታወግዘው የነበረውን ነገር እውቅና መስጠትህ ነው። የምታውቀው የነበረን ሀቅ ደግሞ ማውገዝህ ነው። ወዮልህ በዲን ላይ መቀያየርን ተጠንቀቅ!፣ የአላህ ዲን አንድ ነው።” [አል-ኢባነቱል ኩብራ 571] ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:- “…የስሜት ባለቤት ስሜቱ እውርና ደንቆሮ ያደርገዋል። በዚህ የተነሳም አላህንና መልእክተኛውን አያስታውሱም። ማስታወስም አይፈልጉም። አላህና መልእክተኛው የወደዱትንም ነገር አይወዱም። አላህንና መልእክተኛውን ለሚያስቆጣቸው ነገር አይቆጣም። ይልቅ ስሜቱ የሚወደው ነገር ሲከሰት ነው የሚወደው፣ ስሜቱ የሚጠላው ነገር ሲከሰትም ነው የሚጠላው…።” [ምንጭ:- ሚንሀጅ አስሱና 5/256] በአሁን ሰዓትም በብዛት እየታየ ያለው ተጨባጭ ይህ ነው። የቢድዓ ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች መድረክ ሲያገኙ ደስታቸውን የሚገልፁና ያሻቸውን የሚናገሩት ስሜታቸው የወደደውና የጠላውን ነው። የሚናገሩት ነገር አላህንና መልእክተኛውን የሚያስቆጣና በቀጥታ የቁርኣንና የሀዲስ ማስረጃዎችን የሚጋጭ ቢሆንም ጉዳያቸው አይደለም!። ምክንያቱም እነርሱ በስሜት ታውረዋል፣ ሲነገራቸውም አይሰሙም በስሜት ደንቁረዋል። በመሆኑም የሀቅ ሰዎች ከምንጊዜውም በላይ ነቅተው የቢድዓ ሰዎች በተግባራቸውና በምላሳቸው በህዝቡ ከባጢል ጋር የሚያቀላቅሉበትን ሀቅ ለህዝቡ ግልፅ ሊያደርጉና ሊያብራሩ ይገባል!። ታላቁ ዓሊም ኢብኑ ዐጣር (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:- “ሀቅን ግልፅ ከማድረግና ከማብራራት፣ መደበቅን ከመተው፣ እውነቱን ከውሸት ግልፅ አድርጎ ለይቶ ከማብራራት ቅሮት የለውም!!። የላቀው አላህ የሚያበላሸውን ከሚያሳምረው፣ የሚሸፋፍነውን ግልፅ ከሚያደርገው ለይቶ ያውቀዋል።” [ምንጭ:- ሪሳለቱ ሰማዕ 48] አል ሃፊዝ ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:- “ሀቁ ከባጢሉ ከተመሳሰለና ሀቁን ግልፅ ከማድረግ ዝም ከተባለ፣ በመካከላቸው ከእውነት ይልቅ መሀይምነትና ፍጡርን ማጥመም ይወለዳል።” [አስሶዋዒቅ አልሙርሰለህ 52] ታላቁ ዓሊም ሸይኽ አህመድ ቢን የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:- “እነዚያ ለሰዎች እውነትን ግልፅ ከማድረግና ከማብራራት ዝም ያሉ ሰዎች በዝምታቸው ዑዝር አይሰጣቸውም። ምንም እንኳን እኛ ከባጢል ሰዎች አይደለንም ቢሉም ዑዝር አይሰጣቸውም።” [ምንጭ:- ተህዚሩ ሰለፊይ ሚን መንሀጅ አትተምይዕል ኸለፊይ 311] ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:- “በሀገርህ ወደ ሱንና እና ቀደምቶችን ወደ መከተል የምትጠራው አንተ ብቻ ከሆንክ፣ ውዳቂ ወደሆነው መንገዳቸው የሚጣሩ ጠላቶችህ ከበዙ፣ በአንተ ላይ ግዴታው ተስፋ አለመቁረጥ ነው!!። ተስፋ ከቆረጥክ ከሀቅ ነው ተስፋ የቆረጥከው። ይልቅ ፅና! ጠላቶችህ የፀናህ ሆነህ ማየት ነው የሚያስፈራቸው።” [ሸርህ አል ካፊያ አሻፊያ 1/201] ታላቁ ዓሊም ሙሀዲስ ሸይኽ ሙቅቢል (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:- “ደዕዋ እኛ ዘንድ ከነፍሳችን፣ ከቤተሰባችን፣ ከንብረታችን በላይ ነው። አፈር መብላት ካለብን አፈር ለመብላት ዝግጁ ነን። ዲናችንና ሀገራችንን አናታልልም። አንቀያየርም። መቀያየር ከአህሉሱንና ባህሪ አይደለም!።” [ምንጭ:- አልባዒስ ዐላ ሸርህ አል ሀዋዲስ 87] ታላቁ ሸይኽ ዶ/ር ሙሀመድ ቢን ሰዒድ ረስላ (አላህ ይጠብቃቸውና) እንዲህ ይላሉ:- “…እኛ በመዋለል ላይ አይደለንም!። አህሉሱንናዎች አይዋልሉም!። እንዴት ይዋልላሉ? አላህ በቁርኣኑ እና በነቢዩ ﷺ ሱንና አብቃቅቷቸው እያለ፣ አህሉሱንናዎች አንድም ቀን እንኳን በመዋለል ላይ አይሆኑም!!።” [ከድምፃቸው የተወሰደ] ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

📎📔 አዲስ ፒዲኤፍ 📄
ስለሰይድ ቁጥብ ኢብራሂም ሁሰይን የሙሐመድ ሃሚዲንን ጥርጣሬዎች እና የተሳሳቱ አመለካከቶች ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል ግልጽ ምዕራፍ
🖋 በዶክተር ሸይኽ ሑሰይን ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲላህ አስ'ስልጢይ (ሐፊዞሁሏህ) በዐረብኛ ተዘጋጅቶ፤ 📝 🖋 በአቡ ዐብዲል0ዚዝ ሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ (ሐፊዞሁሏህ) ወደ አማርኛ ተመልሶ ቀረበልዎ‼️ 🔄 ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን‼️ 🤲 አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን‼️ የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ كن على بصيرة https://t.me/alateriqilhaq

🎁ስጦታ እውቀትን ለምትወዱ ሰዎች ከታች ያለችውን OPEN የምትሉዋን ነገር በመጫን የሰለፊዮችን ቻናል ይቀላቀሉ

የላ! ኢላሀ ኢለላህን ቃል ምስክርነት ማረጋገጥ!! ——— ሸይኹ'ል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “ከአንድ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም!፣ የሚለውን የምስክርነት ቃል ማረጋገጥ፣ ለአላህ ብሎ እንጂ አለመውደድን፣ለአላህ ብሎ እንጂ አለመጥላትን፣ለአላህ ብሎ እንጂ አለመወዳጀትን፣ጥላትነትንም ለአላህ ብሎ እንጂ እንዳይመሰርት፣ እንዲሁም አላህ የወደደውን መውደድን፣ አላህ የጠላውን መጥላት ያስፈርዳል!!።” [መጅሙዕ አልፈታዋ 8/337] #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

قال شيخ الإسلام ابن تيمية -رحمه الله-: " إن تحقيق شهادة أن لا إله إلا الله يقتضي أن لا يحب إلا لله، ولا يبغض إلا لله، ولا يوالي إلا لله، ولا يعادي إلا لله، وأن يحبّ ما أحبّه الله، ويبغض ما أبغضه الله ". 📚مجموع الفتاوى 8/337

በአንድ ነገር ላይአቋም ከመያዝህ በፊት ጠንካራ ማስረጃ አጥብቀህ ያዝ!! ————— አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዙ በፊት አስተማማኝና ጠንካራ ማስረጃ ከያዘ፣ ዱኒያ ላይ ሰዎች ፊት፣ በአኼራም አላህ ፊት አይዋረድም። እውነተኛ የሆነ ሰው በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዙም በፊት ሆነ ከመናገሩ በፊት በቂ ማስረጃ መያዝ እንዳለበትና እርግጠኛ መሆን እንዳለበት ግልፅና ለማንም የማይሰወር ነገር  ነው። አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዙ በፊት ትክክለኛ የሆነን ማስረጃ ካልያዘ፣ የያዘው አቋምና አመለካከት ትክክል ሳይሆን ቀርቶ በሌሎች ሲተችበት ለጭንቀቱ ማምለጫ ሊሆነኝ ይችላል: ብሎ ያሰበውን ሁሉ እያመጣ ሲደረድር ይበልጥ ወደ ሌላ ጥፋት ያመራል። ለዚያም ነው፣ በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዝ በፊት ትክክለኛ የሆነን ማስረጃ መያዝ የአህሉሱንናዎች መገለጫ ነው። በተቃራኒው ደግሞ በአንድ ነገር ላይ አቋም ከያዙ በኋላ ማስረጃ መፈለግ የቢድዐ ሰዎች ባህሪና ልዩ መገለጫ ነው። ምናልባትም አንዳንዴ በራሳቸው ላይ ማስረጃ ሊሆንባቸው የሚችልን ማስረጃ ያለቦታው ሲያቀርቡት ይስተዋላል። አንድ ሰው በአንድ ነገር ላይ ያለ በቂ ማስረጃ አስቀድሞ አቋም ከያዘ የምታመጣለትን ማስረጃ ሁሉ በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ ሳይሆን ራሱ አስቀድሞ ለያዘው አቋም በሚመቸው መልኩ ብቻ መቀበል ነው የሚፈልገው። ይህ ደግሞ ወደ ጥመት የሚመራው በጣም ከባድ አደጋ ነው!!። ለዚያም ነው የሱንና ሰዎች በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዛቸው በፊት ትክክለኛውን ማስረጃ በደጋግ ቀደምቶቻቸው ግንዛቤ መሰረት ከቡድንተኝነትና ወገንተኝነት ገለልተኛ ሆነው ይፈልጋሉ፣ ከዚያም በኋላ አቋም ይዛሉ። የቢድዐ ሰዎች ደግሞ አስቀድመው አቋም ይዛሉ ከዚያም በኋላ ለያዟት አቋም ትሆነናለች ብለው ያሰቧትን ብዥታ ሁሉ እንደ ማስረጃ አንግበው ይንቀሳቀሳሉ። ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) እንዳሉትም "ለቢድዐ ሰዎች ብዥታ እንጂ ማስረጃ የላቸውም።" ለዚያም ነው፣ አስቀድሞ በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ መሰረት ትክክለኛውን ማስረጃ ከመያዙ በፊት አቋም የያዘ ሰው፣ ቁርኣንና ሀዲስን በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤና አካሄድ መሰረት ይዘህለት ብትቀርብም ለራሱ አቋም በሚመቸው መልኩ ቀዶ ካልሰፋው የማይሆንለት። ከዚህም አልፎ አንዳንዴ የያዘውን አቋም ትክክል አለመሆኑን በማስረጃ ስታወግዝበት በቂ ማስረጃ ሲያጣ ከገባበት ማጥ ለማምለጥ ጉዳዩን በተዘዋዋሪም ይሁን በቀጥታ የግል የግጭት ጉዳይ ለማስመሰል ይኳትናል። ምናልባትም በማስረጃ የነቀፉትን ሰዎች ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ የግል ታሪካቸውን፣ (መቼም የሰው ልጅ ባህሪ ይለያያልና) በግል ባህሪያቸው… የመሳሰሉ ከዲን ነጥብ ውጪ ወይም ከተተቹበት አጀንዳ ውጪ የሆኑ ጉዳዮችን እያነሱ ሲወርፉ ማየትም ሊስተዋል ይችላል። ይህ ይበልጥ በቂ ማስረጃ ሳይኖራቸው አቋም መያዛቸውን የሚያሳብቅ ሲሆን! ምንም እንኳን የግል ፀብ ቢኖርም ባይኖርም ማንኛውም ገለልተኛ አካል ይህ ሰው አቋም የያዘበት ጉዳይ ሲነቀፍ ከተመለከተ ማየት ያለበት ሰውዬው አቋም የያዘበትን ማስረጃና ነቃፊው አካል የሚያቀርበውን ማስረጃ ክብደት ብቻና ብቻ ነው!። በመሆኑም አንድ ሱኒይ ነኝ የሚል ሰው የሚጠበቅበት፣ በአንድ ነገር ላይ አቋም ከመያዙ በፊት ተረጋግቶ ግራና ቀኙን በማየት ትክክለኛውን ማስረጃ በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ መሰረት አጥብቆ መያዝ ግድ ይለዋል!!። ✍🏻 ኢብን ሽፋ t.me/ibnshifa የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join አድርገው ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

"በእራሳቸው ጥፋት አንተን የሚወነጅሉ ሰዎች ምናልባት የመርሳት ችግር ላይ ወድቀው ይሆናል!!" አንድ የመርሳት ችግር የነበረበት ባል ነበር ይባላል።ይህ ባል ከዕለታት አንድ ቀን  ሚስቱን ሊያስደስት በማሰብ ስጦታ ገዝቶ ወደ ቤት ይመጣል።ባል ወደ ቤት እንደገባ ሚስቱን ጠርቶ የያዘውን ስጦታ ከኃላ በመደበቅ "ዓይንሽን ጨፍኚ" አላት።ምስኪኗም ሚስት ዓይኗን ትጨፍናለች። ይህም የመርሳት ችግር ያለበት ባል ወዲያውኑ ጨፍኚ ያላትን ረስቶ በቁጣ ድምፅ "እኔን ማየት ደብሮሽ ነው አይደል ዓይንሽን የጨፈንሽው?" በማለት ከቤት ያባርራታል።የዚህ ሲገርም ደግሞ በድጋሚ ከቤት እራሱ እንዳባረራትም ረስቶ "እቺ ሴትዬ ወዴት ዙረት ሄዳ ነው?" ብሎ እርሷን ፍለጋ ወጣ ይባላል። ልክ እንደዚሁም በየቦታው በእራሳቸው ሴራና ተንኮል ተጠላልፈው ሲወድቁ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በውሸትና በቅጥፈት ክስ እያለቃቀሱ እዛም እዚህም ድስኩራቸውን ሲደሰኩሩ ይስተዋላል።ይህም አካሄድ አላህ ዘንድ መጠላቱ የበረታ የሆነውን ለእራሳችሁ የማትሰሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ የሚለው ላይ ይጥላል። (يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفْعَلُونَ (2) كَبُرَ مَقْتًا عِندَ اللَّهِ أَن تَقُولُوا مَا لَا تَفْعَلُونَ (3)) አላህ ከዚህ  አይነት ችግር ሰላም ያድርገን። اللهم آمين ✍አቡ ሙዓዝ https://t.me/ibnbaz1212

🔴 ልዩ የትምህርት ማስታወቂያ 📚 የአረብኛ ሰዋሰው ትምህርት 📖 مُتْنُ الْمُقَدِّمَةِ الْآجُرُّومِيَّةِ ✍️ የኪታቡ አዘጋጅ፦ الإِمَامُ النَّحْوِيُّ أَبُو عَبْدِ اللهِ مُحَمَّدُ بْنُ دَاوُدَ الصَّنْهَاجِيُّ، الشَّهِيرُ بِابْنِ آجُرُّومَ رَحِمَهُ اللهُ تَعَالَى ❇️ የአረብኛ ሰዋሰውን ከመሠረቱ እንማር! የአረብኛ ቋንቋን በትክክል ለመረዳት፣ የቁርኣንንና የሐዲስን አገላለጾች ለመገንዘብ እንዲሁም የዑለማዎችን መጻሕፍት በጥልቀት ለማንበብ የሚረዳውን የናሕው ኪታብ በሥርዓት እንማር። 📌 የትምህርቱ ጥቅሞች፦ ✅ የአረብኛ ሰዋሰውን (عِلْمُ النَّحْوِ) መሠረታዊ ደንቦች መማር። ✅ ቃላት በአረብኛ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ያላቸውን የሰዋሰው ሚናና የኢዕራብ ሁኔታ (الإِعْرَابُ) መረዳት። ✅ የቁርኣንን አንቀጾችና የነቢዩን ﷺ ሐዲሶች በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት መቻል። ✅ የሐዲስ፣ የፊቅህና የሌሎች የኢስላማዊ ዕውቀት መጻሕፍትን ለማንበብና ለመገንዘብ ጠንካራ መሠረት መገንባት። ✅ በንባብና በንግግር ጊዜ የሰዋሰው ስህተቶችን ለመቀነስ መቻል። ✅ ለቀጣይ የአረብኛ ሰዋሰው ኪታቦች ጥናት ጠንካራ መሠረት መጣል። 🎙 ትምህርቱን የሚሰጠው፦ አቡ ኢልሓም ሙሐመድ ኑር (وفقه الله) 🗓 የትምህርት ቀን፦ ቅዳሜና እሁድ 🕰 ሰዓት፦ ከዒሻእ ሶላት በኋላ 📍 ቦታ፦ መድረሰቱል ሙሃጂሪን مدرسة المهاجرين – معهد علمي ودعوي 📢 ግብዣ ለሁሉም የዕውቀት ፈላጊዎች! የአረብኛ ቋንቋን በመሠረታዊ ደረጃ ለመማር የምትፈልጉ፣ የዲን ዕውቀታችሁን ለማሳደግ የምትጥሩና የዑለማዎችን መጻሕፍት በትክክል ለመረዳት የምትመኙ ሁሉ በዚህ ጠቃሚ ትምህርት እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጋብዛችኋለን። 💎 ዕውቀትን በትጋት፣ በትዕግሥትና በተከታታይነት እንቅሰም! 📖 مَنْ سَلَكَ طَرِيقًا يَلْتَمِسُ فِيهِ عِلْمًا سَهَّلَ اللَّهُ لَهُ بِهِ طَرِيقًا إِلَى الْجَنَّةِ "ዕውቀትን ለመፈለግ መንገድ የተጎዘ ሰው፣ አላህ በዚያ ምክንያት ወደ ጀነት የሚያደርሰውን መንገድ ያቀልለታል።" 📚 ምንጭ፦ ሰሒሕ ሙስሊም https://t.me/sunah123

🔷ለተማሪዎች ምክር ዶክተር ሸይኽ ሁሴን - ሀፊዞሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "ከታዋቂነትና ከአመራር ውዴታ መራቅ ፤ ምክንያቱም እርሷ የሰለፍያን እንቅስቃሴ የከፋፈለችና ያፈራረሰች አስጸያፊ እና እጅግ የተወገዘች መጥፎ ባህሪ ነችና። ባለቤቶቿ አስተሳሰባቸው ደካማ እና ጤናማ ያልሆኑ ናቸው።" الرسالة : خمسون نصيحة لطلاب العلم   ص/41 https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة