es
Feedback
Alex Abreham - በነገራችን ላይ

Alex Abreham - በነገራችን ላይ

Ir al canal en Telegram

በገበያ ላይ የሚገኙ የአሌክስ አብረሃም መፅሐፍት ዝርዝር 1- አልተዘዋወረችም 2- ከዕለታት ግማሽ ቀን 3- ዙቤይዳ 4 - ዶክተር አሸብር 5 - እናት ሀገር ፍቅር 6 - አንፈርስም አንታደስም 💚💛❤️ Official Fan Channel ! አሌክስ ማለት በቃ አሌክስ ነው:: Contact me @akexeth

Mostrar más
7 050
Suscriptores
+624 horas
+407 días
+6030 días

Carga de datos en curso...

Nube de Etiquetas
Sin datos
¿Algún problema? Por favor, actualice la página o contacte a nuestro gerente de soporte.
Menciones Entrantes y Salientes
---
---
---
---
---
---
Atraer Suscriptores
junio '26
junio '26
+115
en 0 canales
mayo '26
+100
en 0 canales
Get PRO
abril '26
+87
en 2 canales
Get PRO
marzo '26
+97
en 1 canales
Get PRO
febrero '26
+102
en 1 canales
Get PRO
enero '26
+61
en 0 canales
Get PRO
diciembre '25
+65
en 0 canales
Get PRO
noviembre '25
+64
en 0 canales
Get PRO
octubre '25
+76
en 2 canales
Get PRO
septiembre '25
+123
en 2 canales
Get PRO
agosto '25
+106
en 0 canales
Get PRO
julio '25
+112
en 1 canales
Get PRO
junio '25
+96
en 1 canales
Get PRO
mayo '25
+124
en 2 canales
Get PRO
abril '25
+172
en 1 canales
Get PRO
marzo '25
+109
en 1 canales
Get PRO
febrero '25
+112
en 2 canales
Get PRO
enero '25
+190
en 2 canales
Get PRO
diciembre '24
+178
en 3 canales
Get PRO
noviembre '24
+85
en 0 canales
Get PRO
octubre '24
+124
en 1 canales
Get PRO
septiembre '24
+96
en 1 canales
Get PRO
agosto '24
+118
en 0 canales
Get PRO
julio '24
+97
en 1 canales
Get PRO
junio '24
+77
en 0 canales
Get PRO
mayo '24
+129
en 0 canales
Get PRO
abril '24
+144
en 0 canales
Get PRO
marzo '24
+86
en 0 canales
Get PRO
febrero '24
+124
en 0 canales
Get PRO
enero '24
+165
en 0 canales
Get PRO
diciembre '23
+51
en 0 canales
Get PRO
noviembre '23
+40
en 1 canales
Get PRO
octubre '23
+44
en 0 canales
Get PRO
septiembre '23
+33
en 0 canales
Get PRO
agosto '23
+36
en 0 canales
Get PRO
julio '23
+58
en 0 canales
Get PRO
junio '23
+57
en 0 canales
Get PRO
mayo '23
+72
en 0 canales
Get PRO
abril '23
+62
en 0 canales
Get PRO
marzo '23
+77
en 0 canales
Get PRO
febrero '23
+73
en 0 canales
Get PRO
enero '23
+142
en 0 canales
Get PRO
diciembre '22
+148
en 0 canales
Get PRO
noviembre '22
+207
en 0 canales
Get PRO
octubre '22
+152
en 0 canales
Get PRO
septiembre '22
+141
en 0 canales
Get PRO
agosto '22
+150
en 0 canales
Get PRO
julio '22
+191
en 0 canales
Get PRO
junio '22
+278
en 0 canales
Get PRO
mayo '22
+94
en 0 canales
Get PRO
abril '22
+83
en 0 canales
Get PRO
marzo '22
+97
en 0 canales
Get PRO
febrero '22
+50
en 0 canales
Get PRO
enero '22
+67
en 0 canales
Get PRO
diciembre '21
+65
en 0 canales
Get PRO
noviembre '21
+55
en 0 canales
Get PRO
octubre '21
+42
en 0 canales
Get PRO
septiembre '21
+114
en 0 canales
Get PRO
agosto '21
+152
en 0 canales
Get PRO
julio '21
+232
en 0 canales
Get PRO
junio '21
+191
en 0 canales
Get PRO
mayo '21
+267
en 0 canales
Get PRO
abril '21
+266
en 0 canales
Get PRO
marzo '21
+132
en 0 canales
Get PRO
febrero '21
+129
en 0 canales
Get PRO
enero '21
+140
en 0 canales
Get PRO
diciembre '20
+5 006
en 0 canales
Fecha
Crecimiento de Suscriptores
Menciones
Canales
22 junio0
21 junio+9
20 junio+10
19 junio+10
18 junio+11
17 junio+4
16 junio+4
15 junio+6
14 junio+3
13 junio+3
12 junio+12
11 junio+1
10 junio+6
09 junio+4
08 junio+10
07 junio+6
06 junio+2
05 junio+3
04 junio+1
03 junio+3
02 junio+2
01 junio+5
Publicaciones del Canal
ቴምር ሪል ስቴት የሀብታሙ ሃደራን የግጥም መድብል መፅሐፍ ከዛሬ ጀምሮ በተከታታይ ለመቶ ሰወች ይሸልማል። እንዲሁም የመረጥኳቸውን መፅሐፍት ለአንባቢወቸ እንድሸልም የቴምር ሪል ስቴት ሴልስ ማን የሆነው አብርሃም ተስፋየ ነግሮኛል። ቴምሮች ከስነፅሁፉ ቤተሰብ ጋር የበለጠ በመስራት አዲስ ፈር ቀዳጅ እየሆኑ ነው። ምክንያቱም ንባብን በማበረታታት የሪል ስቴት ሳይቶቻቸውን ማስተዋወቅ ስለሚፈልጉ ነው። ማሳሰቢያ ከቴምር ሪል ስቴት ለማሰታወቂያ ሰባራ ሳንቲም አልተቀበልኩም! መፅሐፍ ገዝተው ደራሲወችን ያበረታታሉ፣ በዚህ በጎ ስራቸው ደራሲያን አንባቢወች ይጠቀማሉ። እኔም ማስታወቂያቸውን ያለምንም ክፍያ እለጥፍላቸዋለሁ።(የሪል ስቴት ማስታወቂያ እየሰራህ ነው ብር አበድረን፣ ባለአንድ መኝታ ከሳርቤቱ ሳይት አበድረን ምናምን እንዳትሉኝ😁) ቴምር ሪል ስቴቶች የላኩትን ማስታወቂያ እነሆ። ቴምር ሪል ስቴት በመሃል ከተማ ሳር ቤት አደባባይ እንዲሁም በቡልጋሪያ አፍሪካ ህብረት አዲስ ሳይቶች አሉት...ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ አፓርታማዎችን በተለያየ የ ካሬ አማራጭ ከ20 % ወይም ከ 1.5 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ወይም ከ 5.2 ሚሊዮን ብር ጠቅላ ዋጋ ያቀርባል። ፒያሳ አደባባይ ግንባታቸው 50% በላይ የተጠናቀቀ ከ 20 ካሬ ጀምሮ ዘመናዊ የንግድ ሱቆች አሏቸው። ቴምር ሪል እስቴት በ11 ዓመት 10ፕሮጀክት ጥንቅቅ አድርጎ ያስረከበ ግዙፍ ታማኝ ተቋም ነው * ምንም ዓይነት የዋጋ ግሽበት አይመለከተዎትም እንዲሁም ቀስ ብለው ካለ ምንም ወለድ በ ሶስት ዓመት ከፍለው ያጠናቀቃሉ ብሏል። በውጭ አገራት ለምትኖሩ ያሉበት አገር በ DHL ልከን እናስፈርመዎታለን ቅድመ ክፍያ ከተከፈለ በኋላ ቀሪው በግንባታ ሂደት በ16 ዙር ከፍለው የሚያጠናቅቁበት የአከፋፈል ስርዓት ተመቻችቷል። * የምንሸጣቸው ቤቶች ሁሉንም ነገር ያሟሉ ዘመናዊ አፓርታማዎች ናቸው ሳርቤት እና ቡልጋሪያ ቤቶቹ የሚከራዩት በዶላር ስለሆነ ለኢንቨስትመንት በጣም አዋጭ ናቸው ሳርቤት በዚህ ዋጋ አፓርታማዎችን ማግኘት አይታሰብም ብለዋቸኋል። ለማንኛውም መረጃ Abreham Tesfaye ን አግኙት ብዙ ዝርዝር ብዙ አማራጭ አለው። ወይም በዚህ ደውሉለት 0910798353 / 0908770077 https://wa.me/251910798353?text ወደመፅሐፍ ሽልማት! ....የሐብታሙ ሐደራን መፅሐፍ መሸለም የሚፈልግ ኮሜንት ላይ አለሁ ማለት ብቻ ነው።

2
Sin texto...
810
3
የሆነ ጊዜ ጧት የስራ ባልደረባየ ጋር ታክሲ ውስጥ በአጋጣሚ ተገናኝተን ወደቢሯችን አብረን እየሄድን ነበር። ልክ ስንደርስ ክንዴን ያዝ አድርጎኝ ሰዓቱን ተመለከተና... "ልክ በሰዓቱ ደረስን፣ ትንሽ እናርፍድ" አለኝ። "እ? ለምን?" "በሰዓቱ ከገባን አለቃችን ይለምዳል"😁 ትቸው ገባሁ እርሱ አርፍዶ መጣ። ሌላ ቀን አርፍጀ ስገባ አለቃየ ተነጫነጨ፣ በማርፈዴ ድርጅቱ ሊደርስበት የሚችለውን የመሬት መንቀጥቀጥ አስረዳኝ። ይቅርታ ጠይቄ ገባሁ። ከእኔ በኋላ ብዙ ቆይቶ ያ እናርፍድ ያለኝ ጓድ ሲደርስ "በቃ አይሞላልህም አንተ " ምናምን ብሎ በሞቀ ሰላምታ ተላለፉ። በየቢሮው ስንት ስትራጀቲሴት አለ እናንተ?
1 036
4
አምባሩን ያጌጠበት ሌላ... (አሌክስ አብርሃም) አንድ ቀን ከመዝሙርና ከግዜር ቃል ውጭ ምንም የማያውቅ ጴንጤ ጓደኛየ ፊቱ ቅጭም ብሎ መጣና እቤቴ አደረ። ሌሊት ድንገት ተነሳና ተንበርክኮ እያለቀሰ መፀለይ ጀመረ። ለምን ጌታ ሆይ ለምን? እያለ! እና በመሃል በቀስታ ሲዘምር ተመሰጨ ሳዳምጠው መዝሙሩ ለየት አለብኝ።ገርሞኝ በደንብ አዳመጥኩት። አሃ ይሄ ነገር .... ጧት ቁርስ ስንበላ ጠየኩት "ይሄ ዘፈን ጌታን ተቀበለ እንዴ?" "የቱ ዘፈን?" የፀጋየ እሸቱ ... ፀጋ እሸቱ ማነው? ፀጋ አላልኩም ፀጋየ ነው...ሌሊት እየፀለይክ "አምባሩን ያጌጠበት ሌላ ተከሳሽ አምሮት ያጣ ገላ" ስትል ነውኮ ያደርከው። "ጌታ ይገስፅህ" አለና ሳቁ አመለጠው። ለካስ ሚስኪን ወዳጀ አንዲት የቸርች እህት "አባለክ" ተብሎ ከቸርች ታግዶ አንጀቱ እርር ብሎ ነው። ብዙ ጴንጤወች እንደሚሉት "ታክሲ ውስጥ የሰማው ዘፈን" አእምሮውን ተቆጣጥሮት ይሆናል። አሳዛኙ ነገር ትክክለኛው አባላጊና ይሄ ሚስኪን ስማቸው ከነአያት ከመገጣጠሙ ውጭ ምንም ግንኙነት አልነበራቸውም። የልጅቱ የተከበሩ ቤተሰቦች ማርገዟን ሲያውቁ አበዱ። ወደክፍለ ሐገር ላኳትና በስልክ ሲያናዝዟት ስሙን ተናገረች። ሽማግሌወች ደውለው ሲጠይቋትም ደገመችው። ሽማግሌወች "አገኘነው" አሉና ሚስኪን ወዳጀ ሻላላላባ እያለ ሲሄድ የምን ሻላላላባ ነው! ባልተገባ.. ባልተቀደሰ... ባልተፈቀደ...ባልተወደደ.. መንገድ ጌታን በድልሃል... የምዕመኑንም አሳዝነሀል፣ ቤተክርስቲያኗ በመተዳደሪያ ደንቧ አንቀፅ ቀ፣ ንኡስ አንቀፅ ጰ መሠረት ለአንድ ዓመት ከማንኛውም አገልግሎት ታግደህ እየፆምክ እየፀለይክ በንስሃ እንድትቆይ ወስናለች።" ነገሩ ተጣርቶ ወዳጀ ላልሰራው ሀጢያት በፆም ከስቶ ሲመለስ፣ ጉባኤው ፊት በስህተት መታገዱ ተገለፀ። ፓስተሩ የተናገረው ነገር ግን ብስጭት አደረገው ። "ሰይጣን የቅዱሳንን ልብ ለማውረድ በሐሰት ይወነጅላል ነፃ የሚያወጣ አምላክ ግን ስራ ላይ ነው ወገኖቸ.....እና ወንድማችን እህታችንን አላባለገም፤ ጌታ ይረዳዋል ወደፊትም አያባልግም"😁
1 148
5
አከራይ ተከራይ ሲባል ምንጊዜም ትዝ የሚለኝ አስቂኝ ነገር... (አሌክስ አብርሃም) አንድ ሰፊ የግለሰብ ግቢ ውስጥ ተከራይቸ እኖር ነበር። ብዙ ነበርን ተከራዮቹ ፤ ከእኔ ቤት ቀጥሎ የሚኖረው ተከራይ አንድ አስተማሪ ሲሆን ቅዳሜ ቅዳሜ ብቻ ጢንቢራው እስኪዞር ከመስከርና "ገንዘብ አለያየን ደሃ በመሆኔ" እያለ ከመዝፈን ውጭ ሽቁጥቁጥ፣ የግቢውን በር እንኳን ሲያልፍ ጫማውን ሊያወልቅ የሚዳዳው ትሁት ሰው ነበረ። አንድ ቅዳሜ ግን ምናባቱ...ማለቴ ምን ጠጥቶ እንደመጣ እንጃ ግቢውን በአንድ እግሩ አቆመው። የሆነ ለማሽቃበጥ የሚረዳ መጠጥ ይመስለኛል የጠጣው። ገና ከመግባቱ "ሁላችንም ኪራይ መጨመር አለብን " ብሎ ጮኸ። "አከራዮቻችን ዝም ስላሉ ብቻ ዝም ማለት ልክ ነው? አይደለም! ቤት መስራት ብዙ ዋጋ ያስከፍላል ካርታ አለ...ፕላን አለ...ለመሃንዲስና ምናምን ጉቦ አለ...ብሎኬት አለ...ሲሚንቶ አለ...ለአከራይ ማን ያስብለት?... መሯቸው ሸጠውት ቢሄዱስ? እኔ ከነገ ጀምሮ ሃምሳ ብር ጨምሪያለሁ...ሁልሽም ኪራይ ጨምሪ...እንትና መቶ ብር...እንትና ስልሳ ብር ... አንተ አብርሃም ሰባ ብር ፣ የውሃም እኛ መክፈል አለብን.....(በቃ ይሄ ሰው ራሱን ሊያጠፋ ወስኗል ማለት ነው ብየ አሰብኩ) አከራያችን ጋቢያቸውን ለብሰው ብቅ አሉና እንደወትሮው "እንዲህ ከረበሽክ ከነገ ጀምሮ ቤት ፈልግ" ይሉታል ብለን ስንጠብቅ ፍቅር በሆነ ድምፅ "መምህር ና እራት ብላ እስቲ... " ወሬ ልመለከት ስንወጣ አከራየ ጋር እንደመጋኛ ተገጣጠምን። ወደእኔ እያዮ "የሚጠጣ ሰውኮ በሆዱ ክፋት የለም..." 🤔 እና ልጠጣልወት?
2 052
6
የኢትዮጵያ ዘፈንና መዝሙር ሳይቀር ወደ AI እጆቹን ዘርግቷል። ገና ሙሉ አካሉ ኤአይ ውስጥ ይዘፈቃል። የዛሬ አመት ይህን ስል የተነጫነጨው ሁሉ ዛሬ በኤፍኤሞች ሳይቀር እያዳመጠ ነው። መጀመሪያ አካባቢ ብዙዎች «AI የጥበብን ስሜትና ለዛ ያጠፋዋል» ብለው ሲከራከሩና ሲነጫነጩ ነበር። አሁን ግን የኢትዮጵያ የሙዚቃና የመዝሙር ኢንዱስትሪ ውስጥ የAI አሻራ በግልጽ እየታየ ነው። ከድምፅ ቅንብርና ማስተሪንግ ጀምሮ፣ የድሮ ድምፃውያንን ድምፅ በAI በማደስ አልፎ ተርፎም ሙሉ በሙሉ በAI የተሰሩ ዜማዎችና ግጥሞች በኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያዎቹ እና በሶሻል ሚዲያ መደበኛ እየሆኑ መጥተዋል። ሁልጊዜ አደዋ የለም፤ አንዳንዴ በሰላም እጅ ሰጥቶ ለራስ በሚመች መንገድ ነገሮችን መጠቀም የተሻለ ነው!!
2 424
7
እየመጡ ነው! (አሌክስ አብርሃም) ቦሌና መገናኛ ጫማ ልትገዙ ስትሄዱ ድንገት አግኝታችሁት እንዳትደነግጡ ከወዲሁ ልንገራችሁ። የቻይናው ብሔራዊ የሕክምና ምርቶች አስተዳደር NEO (Neural Electronic Opportunity) ጭንቅላት ውስጥ የሚቀበር ቺፕ ለገበያ እንዲውል በይፋ ፈቅዷል። በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የጭንቅላት ውስጥ ቺፕ የንግድ ፈቃድ ተሰጠ ማለት ነው። (እንደፈራነው) ጦቢያዊያን ለአመታት ችብስ 666 ...ስንለው የነበረው ጉዳይ ያው እየመጣ ነው። ነገ እንደጥርስ ማስታወቂያ በተወሳሰቡ የህክምና ቃላት ታጅቦ "አስመጥተናል" የሚል ማስታወቂያ መነገሩ አይቀሬ ነው። ለጊዜው ለአካል ጉዳተኞች ረዳትነት ብቻ ይውላል ብለዋል። ያው አንድ ነገር ከተመረተ በኋላ የቴክኖሎጅውን ፍጥነት በስልክ ማየት ነው። ዝርዝሩ ይቅርብን ግን ኤሎን ማስክ 'Neuralink' ብሎ የጀመረውን ፕሮጀክት ቻይናወቹ ቀድመው ለገበያ አውለውታል።የሆነ ቀን ቱርክ ፀጉር ከቱርክ አንጎል ከቻይና አሰገጥመን ሸገር ላይ እንግሊዝኛውን ልናዶለዱለው እንችላለን። ችግሩ ሀክ ሊደረግም ይችላል የሚል ስጋት መኖሩ ነው። አስበሽዋል እናት የሰርግሽ ቀን የባልሽ አንጎል ሃክ ቢደረግ? ወጩ ጋር ተዳምሮ...😁
2 846
8
ባሰብኩት ቁጥር ፈገግ የሚያደርገኝ የምርጫ ክርክር..ምርጫ ዘጠና ሰባት ላይ ኢህአዴግን ወክለው የተወዳደሩ ሁለት የመብራት ሐይል ሰራተኞች ነበሩ። አጋጣሚ ይሁን ታስቦበት እኔጃ ! እና የጦፈ ክርክር ላይ"እኛ ብንመረጥ በብርሃን ነው መንገዱን ሁሉ የምናጥለቀልቀው.... ምናምን ሲሉ የቅንጅት ተፎካካሪያቸው ጣልቃ ገብቶ ምን ቢል ጥሩ ነው " እነዚህን ሰወች ብትመርጧቸው አንዱ መብራት ያጠፋል ሌላው ያበራል፣ ከዚያ ሽፍት ይቀያየራሉ አብሪው ያጠፋል አጥፊው ያበራል" 😁
2 482
9
ዛሬ አዳሬን አንድ ሁለት መርከብ በሚሳኤል አኖጋሁ ትላለች ኢራን፤ አዳሬን አንድ ስድስት የሚሳኤል ጣቢያ አደባየሁ ትላለች አሜሪካ፤ የነዳጅ ጉድጓድ ሲኦል አደረኩ ትላለች ኢስራኤል፣ የሀይል ማመንጫ አደባየሁ ትላለች ሩሲያ በዮክሬን። የሱዳኖቹ ጎረምሶች ድሮን ጣልኩ ከተማ አነደድኩ ይባባላሉ፤ የኛም አገር አከርካሪ ሰበርኩ ቅልጥም ሰበርኩ ይባባላሉ(አጥንት ነክ ነው ጦርነታችን) እና በአንድ ሌሊት በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር እየነደደ ዓለምን ሲያሞቅ ለምንድነው እኔ ቀዳዳ ጫማ የማደርገው፣ ለምንድነው የቤት ኪራይ የምጨነቀው? ለምንድነው ልጆቸ ልኳንዳ የተሰቀለ ስጋ እያዮ ምራቃቸውን የሚውጡት? ለምንድነው መታከሚያ አጥቸ እያቃሰትኩ የምኖረው? ለምንድነው ሰላሳ ቀን ለፍቸ እንደይሁዳ ሰላሳ ዲናር ደመወዜ ከንቱ የሚሆነው? ማለት አያምራችሁም? ለምን? ወይስ በዚህ ሁሉ ጦርነት ህዝብ ሲረግፍ እኔ መትረፌ ለምን እንበል?
2 225
10
ብዢታ ​(አሌክስ አብርሃም) ​የሆነ ቀን ሶፋ ላይ ጋደም እንዳለች እንቅልፍ ወሰዳት። ስትነቃ ብዢ ብሎባታል። የግድግዳውን ሰዓት ተመለከተች፤ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ይላል። ተበሳጨች፣ ባሏ አልገባም። "ይሄ ደደብ ዛሬም ሰክሮ ሊመጣ ነው!" አለች። ትንሽ ቆይታ አእምሮዋ ከእንቅልፍ ሙሉ ለሙሉ ሲነቃና በደንብ ማሰብ ሲጀምር ግን ብቻዋን በሳቅ ፈረሰች... ባሏ ከሁለት ወር በፊት መሞቱን ረስታው ነበር።
2 076
11
"እኔን ዋትስ አፕ ወላንሳ? (አሌክስ አብርሃም) የሆነ ጊዜ ከልተው ከልተው እያልኩ ከስራ ስመለስ የተከራየሁበት ቤት ድግስ ተደግሶ፣ ሙዚቃ ተከፍቶ ደረስኩ። የሆነ አሰልቺ «ልዩ ልዩ ቀን ነው...» የሚል ዘፈን ያላዝናል፣ ከዚያ ደግሞ የብሔር ብሔረሰቦች ዘፈን ይጮኻል። እናትየዋ ጥርስ ብቻ ሆነው «ካልገባህ» ሲሉኝ ገባሁ። ጎረቤቱ ቢራ ይራጫል፤ ክትፎው ወጡ በዓይነት ቀርቧል። ጎረቤቱ ሁሉ «እንኳን ደስ ያላችሁ!» ይላል። በኋላ ስሰማ፣ የሐኪሞች ይሁን የሕክምና ቦርድ የሚባል የባለቤቶቹን ልጅ ወላንሳን «ውጭ አገር ትታከም» የሚል ውሳኔ በማሳለፉ ኖሯል። ጭራሽ እዛ ሁሉ ሰው ፊት " በቸሩ መድሃኒያለምና በአንተ እርዳታ ለዚህ በቃች" ብለው የጎረቤት ቆነጃጅቶች ሁሉ ከዚያ በኋላ "አሜሪካ የሚልከው ልጅ" እያሉ በፍቅር ያዮኝ ጀመር። ​በእርግጥ ለቦርዱ «ይህን ጻፍልኝ»፣ ለሆነ ድርጅት «ኢሜይል ላክልኝ» እያሉ ወደ አንድ ዓመት ፍዳዬን አብልተውኛል። በተለይ ቁጥር ስፍር የሌለውን የመድኃኒት ማዘዣ (የሐኪም ጽሕፈት አስባችሁታል?) «አንብብልን» እያሉ ያበሉኝ መከራ አልረሳውም። ኧረ ስንት ቀን ሰው ጠፍቶ እኔና እናቷ እየደገፍን ዋናው መንገድ ድረስ ወስደናታል። የሆነ ሆኖ ልጅቱ «ለሕክምና» ሄደችና በዚያው ቀረች ቀረች። እኔም በሰላምና በጤና አራት ዓመት ኖርኩ። ​በኋላ ግን፣ ያውም በክረምት፣ «ልጄ ከአሜሪካ ልትመጣ ስለሆነ ቤት ልቀቅ» ተባልኩ። ነገረኛ መሆን ፈለግኩና «ኧረ እለቃለሁ! እንኳን ሕክምናዋን ጨረሰች እንጂ» ስላቸው ፊታቸው እንዴት እንደተቀያየረ! 😁 ሁላችንም «ሾርት ሜሞሪ» ያለን ነው እንዴ የሚመስላቸው? ​አጋጣሚ ሆኖ እዚያው ሦስት ግቢ አልፎ ቤት አገኘሁ። ተከራዮ የነበረው ልጅ በትንሽ ፀብ (ስድስት ጥርስ አውልቆ፣) ሦስት ዓመት ተፈርዶበት ታስሮ እስኪፈታ ድረስ «ኑርበት» ተብዬ። ​እናም ልጅቱ ከአሜሪካ መጣች። ከሳምንት በኋላ በሁለት ጎረምሶች በግራና በቀኝ ተደግፋ እየተንቀጠቀጠች ስትሄድ አየኋት። እንደገና ያመማት መስሎኝ (መቼም ቂም የሚባል ነገር አላውቅም) «እኔን እህቴን!» ብዬ በቅንነት ብጠጋ፣ ለካስ ያደረገችው ባለ ረዢም ሂል ጫማ መራመድ አስቸግሯት ኖሯል! (ምንስ ውድ ብራንድ ቢሆን እንዲህ መሰቃየት ምን ይባላል?) ደግሞ ደጋፊወቹስ ቢሆኑ ያኔ የት ነበሩ?! ጭራሽ ስታየኝ አራት ጣቶቿን በቄንጥ አውለብልባ «ዋስ አፕ!» አለችኝ። ​ፋሲል ደመወዝ «እኔን ዋትስ አፕ ፍቅር አዲስ?!» ያለው ወዶ ነው! እኔን ዋትስ አፕ ወላንሳ?!
3 407
12
የእሹሩሩ ሆርሞን! (አሌክስ አብርሃም) ለተመልካች በጣም አስገራሚ እና የብዙ ሰዎችን ቀልብ የሚስብ ነገር ነው። ስጋ በል የሆኑ አዳኝ እንስሳት (ነብር፣ አንበሳ ወይም አቦሸማኔ ወዘተ) የትንሽ ሚዳቆዎችን ወይም የሌሎች እንስሳት ግልገሎችን ድንገት ይይዛሉ። እና ሳይገድሏቸው ሲያጫውቷቸው ወይም ጥበቃ ሲያደርጉላቸው ይታያል። የእንስሳት ዶክሜንተሪወች ላይ አይታችሁ አታውቁም? ​ ይህ ባህሪ በባለሙያወቹ አጠራር "Maternal Instinct" ይባላል። "የወላድ ደመነፍስ" ልትሉት ትችላላችሁ። በተለይ ያደነችው እንስሳ በቅርብ የወለደች እናት ነብር ፣ አንበሳ ... ከሆነች፣ኦክሲቶሲን እና ፕሮላክቲን የሚባሉትን ሆርሞኖች በውስጧ ከፍ ይላሉ። እነዚህ ሆርሞኖች የአዳኝነት ስሜታቸውን ለጊዜው በመጫን የማቀፍ፣ የመጠበቅና የመንከባከብ የእናትነት ባህሪ እንድታሳይ ያደርጋታል። በደሟ ውስጥ ያለው የሆርሞን መጠን የትኛውንም ህጻን ግልገል የመንከባከብ ስሜት ሊያድርባት ይችላል። እንደው ከሌሎች አዳኝ እንስሳ ሁሉ እየተፋለመች ትከላከልላቸዋለች። ለግልገሎች አንጀቷ ይንሰፈሰፋል። መጨረሻቸው ምን ይሆናል ነው ጥያቄው....አሳድገው ለወግ ማረግ ያበቋቸዋል?(በሰውኛ) በአጭሩ የእነዚህ ህጻናት ሚዳቆዎች የመጨረሻ እጣ ፈንታ አያምርም!! የአዳኟ እንስሳ የእናትነት ሆርሞን ሲቀንስ ፣ መራብ ስትጀምር ወይም የዱር እንስሳነቱ የአዳኝነት ተፈጥሮ ድንገት ሲቀሰቀስ፣ ያ ሲንከባከቡት የነበረውን ግልገል ክትፎ መስሎ ይታያቸው ይጀምራል፣ ቁርጥ መስሎ ይታያቸዋል.... ባልታሰበ ቀን ገነጣጥለው ይሰለቅጡታል። ምንም እንኳን ነብሮችና አንበሳወች ለተወሰነ ጊዜ የዋህነትና የእናትነት ስሜት ቢያሳዩም፣ ተፈጥሮ ጨካኝ በመሆኗ የእነዚህ ህጻናት ሚዳቆዎች ታሪክ መጨረሻው አያምርም። በህይወት የመትረፍ ዕድላቸው ወደ ዜሮ የተጠጋ ነው። ምን ለማለት ነው? (((ከእሹሩሩ ሆርሞን ራሳችሁን ጠብቁ! እንክብካቤ ሁሉ ፍቅር አይደለም! )))
2 981
13
Sin texto...
2 176
14
ስማ አብርሽ አሁን የወፎች ጫጫታ ምኑ ነው ዝማሬ እየተባለ የሚሞካሸው? እኔጃ አስቸ! ጭጭጭጭ ሲያስጠሉ። መርካቶ ይሻላል። የሰው ልጅ አሽቃባጭ ስለሆነ እንጅ የወፍ ጩኸት ከውሻ ከጅብ ከድመት ጩኸት በምን ይለያል? ዛሬኮነው ድንገት በጧቱ ነቅቸ በደንብ የሰማኋቸው። እና ደበረህ? ቀላል ደበረኝ! ጆሮየን ሁሉ ነው የያዝኩት። የጅብ ጩኸት ከእነሱ የተሻለ ዜማ አለው። እኔ የምልህ ዶሮ የወፍ ዘር ነው? መሠለኝ የዶሮ ጩኸት ይሻላል...አይንህን ከድነህ ስትሰማው ዶሮ ወጥ ያስታውስሃል የሆነ የሚፍለቀለቅ አጥንቱ ብቅ ጥልቅ የሚል ቀይ ወጥ። የዶሮ ጩኸት ነው መዝሙር። መዝሙር ያለተስፋ ምን መዝሙር ነው?!😁 ሁልጊዜ መቃሚያ ሊጠይቀኝ ከፈለገ ይፈላሰፋል😁
2 509
15
አሜሪካ ሄጀ ወያላ ልሁን የሚል ኮሜንት እንዳትሰጡ! (አሌክስ አብርሃም) ባለፈው አንድ መኪና ከፊቴ ቆመና የ "STOP" ምልክቱን ዘረጋ። ሁላችንም ከኋላ ተደርድረን ቆምን። ልክ እንደስኩል ባስ አይነ+1
አሜሪካ ሄጀ ወያላ ልሁን የሚል ኮሜንት እንዳትሰጡ! (አሌክስ አብርሃም) ባለፈው አንድ መኪና ከፊቴ ቆመና የ "STOP" ምልክቱን ዘረጋ። ሁላችንም ከኋላ ተደርድረን ቆምን። ልክ እንደስኩል ባስ አይነት ግን ትንሽ ቫን ነገር ነው። እና በሩ ተከፍቶ አንድ ውሻ ሮጦ ወጣና ቁማ ወደምትጠብቀው ሴት ጋር ሄዶ በደስታ ይቦርቅ ጀመር። አቅፋ ሳመችው። ውሾች ልክ እንደትምህርት ቤት ውለው ሲመለሱ የሚመላለሱበት የውሻ ሰርቪስ ነው። Doggy Daycare Bus” ወይም “Puppy School Bus” እየተባለ ይጠራል። ​ ውሾቹ የት ነው የሚውሉት? ብየ ጎግል ሳደርግ ​እነዚህ ውሾች የሚሄዱት ባለቤቶቻቸው ስራ ሲሄዱ "Doggy Daycare" ወደሚባሉ ቦታዎች ነው። ​እዚያ ቀኑን ሙሉ ብቻቸውን ቤት ውስጥ ከመቀመጥ ይልቅ እንደልጆች ጧት ከየቤታቸው በሰርቪስ ሄደው ከሌሎች ውሾች ጋር ይጫወታሉ፣ ዋና ይዋኛሉ፣ እንቅልፍ ይተኛሉ፣ እንዲሁም አንዳንድ የስነ ምግባር ስልጠናዎችን ያገኛሉ። ​ ባለቤቶች ጠዋት ወደ ስራ ከመሄዳቸው በፊት ውሻቸውን ማቆያ ቦታ ድረስ መውሰድ ስለሚደክማቸው፣ ይህ የባስ አገልግሎት ትልቅ እፎይታ ሆኖላቸዋል። አስባችሁታል "ውሻሽ የት ነው የሚማረው?" ምናምን ሲባባሉ! ወደቲክቶክ ስመለስ አንዲት መንግስት ቤት 20 ዓመት የሰራች ሴትዮ ከኮየ ፈጨ በሰልፊ ቪዲዮ ቅሬታዋን እያቀረበች ነው። "ለሚመለከተው አድርሱልኝ... 56 ቁጥር ባስ ቀረችብኝ ይሄው ሕዝቡ ተሰልፎ እየጠበቀ ... ከስራ አረፈድን " እያለች።
2 076
16
ቻይናዊው ሻወር እየወሰደ እያለ፣ ድንገት ቤቱ በእሳት ይያያዛል... ራቁቱን በመስኮት ዘሎ ይወጣል። ትንሽ እንደተረጋጋ ሚስቱ የሚቃጠለው ቤት ውስጥ መቅረቷን ያስታውሳል፤ ነገር ግን "እንግዲህ ቀኗ ካ
ቻይናዊው ሻወር እየወሰደ እያለ፣ ድንገት ቤቱ በእሳት ይያያዛል... ራቁቱን በመስኮት ዘሎ ይወጣል። ትንሽ እንደተረጋጋ ሚስቱ የሚቃጠለው ቤት ውስጥ መቅረቷን ያስታውሳል፤ ነገር ግን "እንግዲህ ቀኗ ካልደረሰ መውጣቷ አይቀርም" ብሎ ችላ ይላታል። ወዲያው ግን አንድ በጣም አስደንጋጭ ነገር ትዝ ይለውና፣ በአስደናቂ ጀግንነት ድጋሚ ዘሎ ወደሚቃጠለው ቤት ይገባል። ሚስቱንም አንከብክቦ ይዟት ይወጣል። ​በኋላ ላይ ጋዜጠኞች ተሰብስበው፦ "እንዴት በዚህ ድፍረት ወደሚቃጠለው ቤት ገብተህ ሚስትህን ልታተርፋት ቻልክ? ስታገኛትስ በምን ሁኔታ ላይ ነበረች?" ብለው ጠየቁት። ​ስሜቱን በራሱ ቋንቋ እንስማው... ​我不能把手机和妻子单独留在家里。我一直担心她会拿起我的手机偷看信息。当我急匆匆地冲进家门时,果然不出所料,她正一边被浓烟包围着剧烈咳嗽,一边在翻看我的手机。最终,我把她和手机一起救了出来。 ​አቻ ትርጉም ከትንሽ ቅመም ጋር ​"ስልኬንና ሚስቴን ብቻቸውን እቤት ውስጥ መተው ፈጽሞ አልችልም! 'የተላላኩትን መልዕክት እያነበበች ይሆን?' የሚለው ስጋት እረፍት ነሳኝ። ​ዘልዬ እቤት ውስጥ ስገባ ልክ እንደፈራሁት፤ በጭስ ተከባ የቀሚሷ ጫፍ በእሳት እየተቀጣጠለና እያሳለች ስልኬን ስትፈትሽ አገኘኋት! በጨዋነት ስልኬን ተቀብየ ልወጣ ስሞክር 'ዢዋን ማናት? ለምንስ የልብ ኢሞጂ ላክህላት?' እያለች በዚያ ጭስ ውስጥ መጨቃጨቅ ጀመረች። ሌላ አማራጭ ስላልነበረኝ፣ ከነስልኩ አንጠልጥዬ ይዣት ወጣሁ።" ​ክፉ ጊዜ ላይ ነን እ? 😁
2 637
17
ግንቦት ሃያ ማይደል ሁለት አስገራሚ ነገሮች! (አሌክስ አብርሃም) ​1 ​እዚህ ከመጣሁ ያወቅኋቸው በጣም የተረጋጉ ባልና ሚስቶች አሉ። እርሷ ከትግራይ፣ እርሱ ደግሞ ከደቡብ ክልል ነው። ርግት ያሉ ጴንጤዎች ናቸው። አቤት መከባበር! አቤት ፍቅር! ​እና የሆነ ቀን በምን እንደተነሳ እንጃ፤ "እንዴት ተገናኛችሁ?" አልኳቸው። ተሳሳቁና "ንገረው እንጂ፤ ራስህ ንገረው" ሲባባሉ ቆይተው እርሱ መናገር ጀመረ፦ ​"ማርካ ነው ያገባችኝ" አለና እየሳቀ በፍቅር እጇን በእጁ ያዘ። ​"በፍቅር ነው?" ለመቀለድ ሞከርኩ። ​"የምን ፍቅር... እኔ ወታደር ነበርኩ፤ እርሷ የወያኔ ታጋይ... 'ክምር ድንጋይ' በሚባል ቦታ በ1983 ዓ.ም. ስንዋጋ ማረከችኝ። ሁሉም አልቆ እኔና አንድ ሻለቃ ብቻ ነን የተማረክነው። ትውውቃችን እዚያ ነው። በኋላ በ1986 ዓ.ም. አዲስ አበባ ላይ እንደገና ተገናኘን። ቆይቶ ጌታ ሁለታችንንም ማረከን" በማለት በሳቅ አጀበው። 😁 ​2. ​አሁን በቅርቡ የሰሜኑ ጦርነት ወቅት "ከዕለታት ግማሽ ቀን" የሚል መጽሐፍ አሳትሜ ነበር። አንባቢዎቼ ከተለያየ ቦታ መጽሐፉን ይዘው ፎቶ እየተነሱ ይልኩልኛል። ​አንድ ወታደር ከወራት በኋላ መጽሐፉን ይዞ የተነሳውን ፎቶ ላከልኝና እንዲህ የሚል መልዕክት ጨመረበት፦ ​"አሌክስ፣ አድናቂህ ነኝ፤ የእግዚአብሔር ነገር ይገርማል። አዲስ መጽሐፍ ማውጣትህን አላወቅሁም ነበር። እንደምታየው ችግር ላይ ነን (ጦርነቱን ማለቱ ነው)፤ አንድ ቦታ በነበረ ውጊያ የተገደሉ የጠላት ወታደሮችን ስንፈትሽ፣ አንዱ የሞተ ወታደር ቦርሳ ውስጥ አዲሱን መጽሐፍህን አገኘሁት።"
2 548
18
"ምን ጎዳና ጎዳና ትላላችሁ? አሜሪካም ጎዳና ተዳዳሪ አለ" እንዲ የሚሉ ቅን አሳቢ ሰዎች አያለሁ። ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጭምር እንዲህ ሲናገሩ ማየቴ ይገርመኛል። ልክ ናቸውኮ፤ አሜሪካ ያለ ጎዳና ተዳዳሪ ቁጥር ስፍር የለውም። ግን የአሜሪካ ጎዳና ተዳዳሪ ከኢትዮጵያ ጎዳና ተዳዳሪ ጋር ሳይሆን፣ ከኢትዮጵያ ሀብታም ጋር ነው መነጻጸር ያለበት የሚል ሐሳብ አለኝ። መረጃ ላቅርብ፦ 1. ​አንድ የአሜሪካ የጎዳና ተዳዳሪ ነጻ የህክምና አገልግሎት ያገኛል። የሚያገኘው ህክምና ኢትዮጵያዊ ሀብታም ወይም ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ወደአሜሪካ ሄዶ የሚያገኘውን፣ ወይም አንድ ደሃ በሐኪሞች ኮሚቴ ተወስኖለትና በህዝብ ተዋጥቶለት የሚያገኘውን በአለም አቀፍ ደረጃ የተመሰከረለትን ህክምና ነው። እንዲህም ሆኖ አሜሪካ ለጎዳና ተዳዳሪወች የምትሰጠው ህክምና በቂ አይደለም፣ የአእምሮና ከሱስ የማገገም ህክምና በደንብ በነፃ ሊሰጥ ይገባል እያሉ ዜጎች ፖለቲከኞች ይሞግታሉ። አንዲት ሆምለስ ብታረግዝ ከእርግዝና ክትትል እስከማዋለድ የምታገኘው ነፃ ህክምና ኢትዮጵያዊያን ሴት አርቲስቶችና የሐብታም ሚስቶች አሜሪካ ሄደው ከሚያገኙት ህክምና ጋር እኩል ነው። 2. ​ከሁለት ዓመት በፊት የተሰራ ጥናት አንብቤያለሁ፤ USDA ወይም WHO ይመስለኛል ያስጠናው። የአሜሪካ ጎዳና ተዳዳሪወች ከብዙዎቹ የአፍሪካና ኤዢያ እንዲሁም ደቡብ አሜሪካ አገራት ነዋሪዎች የተሻለ ብዛትና ጥራት ያለው በካሎሪ ይዘቱም የተሻለ ምግብ ያገኛሉ። 3. ​ስለ ልብስ የሚጨነቅ የጎዳና ተዳዳሪ አለ ማለት ይከብዳል። ልብስና ጫማ እንደ አሜሪካ ዶኔት የሚደረግበት ሕዝብ በምድር ላይ የለም። አንድ አሜሪካዊ ከአውሮፓዊ ጋር ሲነፃፀር በአመት ከ6-8 ዕጥፍ ልብስ ይሸምታል። ያንኑ ያህል በየአመቱ እያወጣ ዶኔት ያደርጋል። በቁማቸው ቆሽሸው፣ አሳዛኝ ጠረናቸው አካባቢውን የሚረብሽ፣ በድራግ ራሳቸውን የረሱ የጎዳና ተዳዳሪዎች በብዛት አሉ። ከፈለጉ ግን ልብስ ያን ያህል አሳሳቢ አይደለም። በርካታ ድርጅቶች ልብስ ይሰጧቸዋል። 4. ​ትራንስፖርትን በተመለከተ፤ ከአመት እስከ አመት የነጻ አውቶቡስና የባቡር ኮፖን የሚሰጡ በርካታ ድርጅቶች አሉ። እየጫሩ ወደፈለጉበት ይሄዳሉ። መኪና ያላቸው ሆምለሶችም በጣም ብዙ ናቸው። 5. ኢንተርኔት የ24 ሰዓት የማይቆራረጥ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት የሌለው የጎዳና ተዳዳሪ ካጋጠማችሁ። ብሶበት ነገር አለሙን የተወ መሆን አለበት። 6.ንፅህና የገላ መታጠቢያና የልብስ ማጠቢያ በርካታ የበጎ አድራጎት ተቋማት አሉ። 7. ትምህርት፦ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ ልማር ካለ እልል ብለው የትምህርት ወጭውን የሚሸፍኑ፣ የግልም የመንግስትም በጎ አድራጎት ድርጅቶች አሉ። እንደውም የከተማ አስተዳደሮች በጀት መድበው የጎዳና ተዳዳሪወችን ለማስተማር በየጊዜው እንደለመኑና ማበረታቻ ቃል እንደገቡ ነው። 8. ሰብዓዊ ክብር፦ አንድን የጎዳና ተዳዳሪ ማነው ዝንምቡን እሽ የሚለው? እንኳን ሌላ አንዴ የቀመስክለትን ምግብ በቅንነት ብትሰጥ ነውርም ወንጀልም ተደርጎ ይታያል። ንፁህ ምግብ የማግኘት መብቱ የተጠበቀ ነው። ማንኛውም የህዝብ መገልገያ ውስጥ በአለባበሱ በማንነቱ እንዳይጠቀም መከልከል ነውርም ወንጀልም ነው። ። 9. ፍትህ፦ ተበደልኩ ብሎ ለፖሊስ ቢደውል ለምን ቢሊየነር አትሆንም ፖሊስ በእኩል አይን ያስተናግድሃል። ካርቶን አንጥፈህ የምተኛበት በረንዳ ድረስ እየተንቀለቀ ከች የሚለና "ማናባቱ ነው ያስቀየመህ" የሚል የፍትህ ስርዓት አላቸው። አንድ አይምሮውን ነካ የሚያደርገው የጎዳና ተዳዳሪ ወደአርባ ጊዜ እየደወለ "ሰወች ሊገድሉኝ ነው" በማለቱ አርባውንም ጊዜ ፖሊሶች ሄደው ቸክ እንዳደረጉት አንዴ ሰምቻለሁ። ከአርባው አንዱ እውነት ቢሆንስ? 10. ህዝብም መንግስትም የእውነት ይራራላቸዋል። እንዲህ ስልህ አሜሪካን ገነት አድርገህ ካየህ የዋህ ነህ። እነዚህ ሰወች ይሄ ሁሉ ቢሳካላቸውም ከቆሙት በታች ከሞቱት በላይ ሆነው በሚዘገንን የአካልና የመንፈስ ስብራት የሚኖሩ ሰወች ናቸው። ህይወት ከቁስ ያለፈ ነገር እንዳላት የሚታይበት አገር ነው። በተለይ አደንዛዢ እፅ ሰውን እንደበቆሎ ፈልፍሎ ቆረቆንዳውን ሲያስቀር የሚታይበት ዘግናኝ ህይወት። ከላይ የዘረዘርኩት አንድ አገር ለዜጎቹ የሚያሳየውን እውነተኛ ክብር ማሳየትና አንዳንዴ ከማይሆን ንፅፅር ወጥተን እንደአቅማችን ለህዝባችን እንድንሰራ ለመጠቆም ያህል እንጅ የአሜሪካን ሐብት መስበክ አይደለም። አሜሪካ ግራ ታጋባሀለች። ለምሳሌ ግሮ ጥሮ የሚያድረውን ሕዝብ ተመልከት። በቀን ሁለት ሰዓት እንኳ የማይተያዮ ባልና ሚስት ። ለሁለት ሰርተው በቢል አናታቸው የዞረ ሚስኪኖች ታያለህ። ባጭሩ ስትሰራ ታስከፍልሃለች ካልሰራህ ትረድሃለች። ደሃው በቀላሉ የሚያገኘውን መካከለኛ ገቢ ያለው ፍዳውን በልቶ ያገኘዋል። ወዘተ።
3 061
19
ነበርንም አለንም! (አሌክስ አብርሃም) ​እኔ ያደግኩበት ልጅነት በስልክ አልተረበሸም፤ በሰላሳ ለዛ ቢስ የቴሌቪዥን ቻናሎች አልተወረረም፤ በኢንተርኔት ሶሻል ሚዲያ አልተበከለም። ንፁህ ነበር እንደ ተፈጥሮ፤ ፍንትው ያለ፣ ብሩህና ጣፋጭ ነበር እንደ ጧት ፀሐይ። ​ትምህርት ቤት እንሄዳለን፤ ስንመለስ ተሰብስበን ኳስ እንጫወታለን። እነ ኃይሌ ሲሮጡ፣ ወርቅና ብሩን ሲጠራርጉት እናያለን። የሆነ ቀን የአባባ ተስፋዬን ተረት አለ፤ ነፍሳችን ደስ ይላታል። ቤተሰብ የጀርመንንና የአሜሪካን ሬዲዮ እያንኮሻኮሹ ሲሰሙ ተደብረን ይሆናል፤ ቢሆንም የነጃርሶን ትረካ በዛው ሬዲዮ አጣጥመናል። ​እነ ብርቱካን ሐረገወይን፣ ዓለምነህ ዋሴ፣ እነ ነጋሽ መሐመድ የዓለምን ምስቅልቅል እንደ ወተት በዜና አጠቡን። እነ ጋሽ ደጀኔ ጥላሁን ፣ አነጌትነት እንየው በሬዲዮ መጻሕፍትን ተረኩ፤ ጓጉተን ሰማናቸው። ከፍ ስንል መጻሕፍት ጠበቁን። እንደነ ሐዲስ አለማየሁ፣ ፀጋየ ገብረ መድህን በዓሉ ግርማ፣ ስብሃት ለዓብ፣ ሀይለመለኮት መዋዕል፣ እነጃርሶ፣ እነሲሳይ ንጉሱ፣ ፍቅረማርቆስ ደስታ፣ ሰርቅ ዳ ስራወች ጠበቁን። የምስራቅና የምዕራብ ፍልስፍና ቀመስ መጻሕፍት ከተማችንን ወረሩ፤ "አርፋችሁ ትምህርታችሁን አታጠኑም?" እየተባልን በትርጉም አነበብን። የነኦሾን ቅማንጅር ፣ የእነ አጋታ ክርስቲ የወንጀልና የምርመራ ልብ-ወለዶች፣ የእነ ሲድኒ ሸልደን የሴራና ልብ ሰቃይ ልብ-ወለዶች፣ የእነ ማክሲም ጎርኪ የመረሩ ውብ የሩሲያ ተረኮች፣ የነ ኒኮላይ ጎጎል አስደማሚ አጭር ልብ-ወለዶች፣ የነ ኧርነስት ሄሚንግዌይ የሕይወት ትግል... አነበብን። ጋዜጣና መፅሄቶች መጡ " ከረቫት የሚለብስ ወንድ ደስ ይለኛል የሚሉ ቆነጃጅት የሽፋን ፎቶ ሆኑ ወጣት ልባችን በሙቀት አያቸው። ​ይህ ሁሉ ሲሆን ዕድሜያችን ከአስራዎቹ አልዘለለም። ዛሬ የአርባና የአምሳ ዓመት ሰዎች መጥተው፣ እንደ ተአምር በልጅነት ያለፍናቸውን ተረቶች እንደ አስደማሚ ነገር ጢማቸውን እየላጉ፣ ከረቫታቸውን እያስተካከሉ፣ ሂውማን ሄራቸውን እየነሰነሱ "ካልነገርናችሁ" ሲሉን ትዕግሥት ብናጣ ይፈረድብናል? ቢሰለቸን፣ ቢያንገሸግሸን ትታዘቡናላችሁ? ከሰለቻችሁ አትሄዱም ይሉናል የት? በእድሜና በሀብት በስልጣንና ስም የቀደሙን ከፊታችን ይጃጃላሉ። መንገድ ዘግተው። ኋላችን ሮንቃ ነው የአሳማ ግልገሎች የሚቦርቁበት። "እናቅልለው" ብለን ቀለን፣ "እናክብደው" ያሉት በቀለለባቸው ፍዳችንን እንብላ? ቅንጡ መኪና ሰልችቶት "ለጤናዬ" ብሎ በእግሩ የሚሄድን ሰው በባጃጅ ሊያስደምሙ የሚጋጋጡ ዜጎች ዓይነት ባሕርይ ሞላው ዘመኑን! ጭራችንን እያወዛወዝን "አይ ጊዜ!" አንል ነገር ገና ሰላሳ ውስጥ ነን። አርጅተናል ወይስ ዘመኑ እንጩጭ ሆኖብናል? እንጃ... እንጃ! ብቻ ነበርንም አለንም!
3 400
20
"ዱርየነት" የሚባለውን ባህሪ ፣ ሱሰኝነት፣ ወሲብ፣ ባህልና ወግ መጣስ ከከተማ ልጆች ጋር አያይዞ ማሰብና የገጠር ልጆችን ባህላቸውን ጠባቂ፣ ቁጥብ፣ ሐይማኖተኛ፣ በትምህርታቸው ጎበዝ፣ ቤተሰብና ማህበረሰባቸውን አክባሪ ወዘተ አድርጎ መሳል በጣም የተለመደ ነው። የኔ ጌታ (አጠቃላይ ገጠርን አይወክልም ይሄ ንግግሬ) ግን ቲክቶክ ላይ ያሉ የገጠር ልጆችን ተመልከት። በቃ ስልክና ኔትወርክ እጃቸው ላይ ከገባ ሴቶቹ አንድ የባለጌ ፋብሪካ የተመረቱ እስኪመስል የመጨረሻ ዘግናኝ ከሆነ የወሲብ ወሬ ውጭ ምንም አያወሩም። መሰልጠን ማለት ይሄ ልቅነት ይመስላቸዋል። በዚህ ጉልድፍነት ላይ ትንሽ ገንዘብ ከተጨመረማ በቃ! ደግሞ አወራራቸው ሲቀፍ፣ ሲያስጠላ። ቲክቶክ ላይ ከየትኛውም ብሔር ይምጡ ብቻ የገጠር ሴቶችን ከሶስት ርዕሰ ጉዳዮች ውጭ ካገኘሃቸው እኔ ልቀጣ... * ልቅና የቆሸሸ የወሲብ ወሬ... ባል ውሽማ ምናምን፣ አካላዊ ነገር ጋር የተያያዘ አቅለሽላሽ ቀልድ፣ *በለው ውቃው፣ ፍለጥ ቁረጥ ዘፈን ከፍቶ መደለቅ፣ እና * ሐይማኖተኛ መምሰል፤ ግን ሐይማኖት ስለሚባለው ጉዳይ ርጋፊ ንባብም ዕውቀትም አለመኖር፤ የሐይማኖት ፀብ ንትርክ ካለ ዳይቭ ገብተው በዛ ጉልድፍ ዕውቀት ማንቦጫረቅ። የወንዶቹን ተወው! ፖለቲካ ይጨምሩበታል። እንዴ የከተማ ልጅኮ "ሸም" የሚባል ነገር ያውቃል። የእውነት ከጤፍና ከበቆሎ ጋር ባለጌም ከገጠር ወደከተማ ይጫናል? (እደግመዋለሁ የገጠር ሰው ሁሉ እያልኩ አይደለም)
2 672