uk
Feedback
Alex Abreham - በነገራችን ላይ

Alex Abreham - በነገራችን ላይ

Відкрити в Telegram

በገበያ ላይ የሚገኙ የአሌክስ አብረሃም መፅሐፍት ዝርዝር 1- አልተዘዋወረችም 2- ከዕለታት ግማሽ ቀን 3- ዙቤይዳ 4 - ዶክተር አሸብር 5 - እናት ሀገር ፍቅር 6 - አንፈርስም አንታደስም 💚💛❤️ Official Fan Channel ! አሌክስ ማለት በቃ አሌክስ ነው:: Contact me @akexeth

Показати більше
7 055
Підписники
+424 години
+67 днів
+7130 день

Триває завантаження даних...

Хмара тегів
Немає даних
Виникли проблеми? Будь ласка, оновіть сторінку або зверніться до нашого support-менеджера.
Вхідні та вихідні згадування
---
---
---
---
---
---
Залучення підписників
червень '26
червень '26
+138
в 0 каналах
травень '26
+100
в 0 каналах
Get PRO
квітень '26
+87
в 2 каналах
Get PRO
березень '26
+97
в 1 каналах
Get PRO
лютий '26
+102
в 1 каналах
Get PRO
січень '26
+61
в 0 каналах
Get PRO
грудень '25
+65
в 0 каналах
Get PRO
листопад '25
+64
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '25
+76
в 2 каналах
Get PRO
вересень '25
+123
в 2 каналах
Get PRO
серпень '25
+106
в 0 каналах
Get PRO
липень '25
+112
в 1 каналах
Get PRO
червень '25
+96
в 1 каналах
Get PRO
травень '25
+124
в 2 каналах
Get PRO
квітень '25
+172
в 1 каналах
Get PRO
березень '25
+109
в 1 каналах
Get PRO
лютий '25
+112
в 2 каналах
Get PRO
січень '25
+190
в 2 каналах
Get PRO
грудень '24
+178
в 3 каналах
Get PRO
листопад '24
+85
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '24
+124
в 1 каналах
Get PRO
вересень '24
+96
в 1 каналах
Get PRO
серпень '24
+118
в 0 каналах
Get PRO
липень '24
+97
в 1 каналах
Get PRO
червень '24
+77
в 0 каналах
Get PRO
травень '24
+129
в 0 каналах
Get PRO
квітень '24
+144
в 0 каналах
Get PRO
березень '24
+86
в 0 каналах
Get PRO
лютий '24
+124
в 0 каналах
Get PRO
січень '24
+165
в 0 каналах
Get PRO
грудень '23
+51
в 0 каналах
Get PRO
листопад '23
+40
в 1 каналах
Get PRO
жовтень '23
+44
в 0 каналах
Get PRO
вересень '23
+33
в 0 каналах
Get PRO
серпень '23
+36
в 0 каналах
Get PRO
липень '23
+58
в 0 каналах
Get PRO
червень '23
+57
в 0 каналах
Get PRO
травень '23
+72
в 0 каналах
Get PRO
квітень '23
+62
в 0 каналах
Get PRO
березень '23
+77
в 0 каналах
Get PRO
лютий '23
+73
в 0 каналах
Get PRO
січень '23
+142
в 0 каналах
Get PRO
грудень '22
+148
в 0 каналах
Get PRO
листопад '22
+207
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '22
+152
в 0 каналах
Get PRO
вересень '22
+141
в 0 каналах
Get PRO
серпень '22
+150
в 0 каналах
Get PRO
липень '22
+191
в 0 каналах
Get PRO
червень '22
+278
в 0 каналах
Get PRO
травень '22
+94
в 0 каналах
Get PRO
квітень '22
+83
в 0 каналах
Get PRO
березень '22
+97
в 0 каналах
Get PRO
лютий '22
+50
в 0 каналах
Get PRO
січень '22
+67
в 0 каналах
Get PRO
грудень '21
+65
в 0 каналах
Get PRO
листопад '21
+55
в 0 каналах
Get PRO
жовтень '21
+42
в 0 каналах
Get PRO
вересень '21
+114
в 0 каналах
Get PRO
серпень '21
+152
в 0 каналах
Get PRO
липень '21
+232
в 0 каналах
Get PRO
червень '21
+191
в 0 каналах
Get PRO
травень '21
+267
в 0 каналах
Get PRO
квітень '21
+266
в 0 каналах
Get PRO
березень '21
+132
в 0 каналах
Get PRO
лютий '21
+129
в 0 каналах
Get PRO
січень '21
+140
в 0 каналах
Get PRO
грудень '20
+5 006
в 0 каналах
Дата
Залучення підписників
Згадування
Канали
29 червня+1
28 червня+5
27 червня+2
26 червня+2
25 червня+4
24 червня+3
23 червня+6
22 червня0
21 червня+9
20 червня+10
19 червня+10
18 червня+11
17 червня+4
16 червня+4
15 червня+6
14 червня+3
13 червня+3
12 червня+12
11 червня+1
10 червня+6
09 червня+4
08 червня+10
07 червня+6
06 червня+2
05 червня+3
04 червня+1
03 червня+3
02 червня+2
01 червня+5
Дописи каналу
በየትኛው ዕድሜ እንሰደድ? (አሌክስ አብርሃም) አንድ ቀን ዶክተር ፍስሃ ጋር እያወራን  ትክክለኛ ለስደት ጥሩ የሆነ እድሜ  የትኛው  ነው አለኝ....አሰብኩ.... ከ1- 15ዓመት ? የህፃንነት ውብ ዕድሜ ጭቃና ውሃ መራጨቱ ትንንሽ እግሮች የአገራቸው አቧራ ላይ መፈንጠዣቸው ፣ በተወለዱበት አገር ቋንቋ መዝሙሮቹ ተረቶቹ... በቁንጥጫ መመዢለጡ በቀበቶ መዢለጡ የህይወት ትንሽ ህመም ፍቅር የወለዳት ከወላጅ የምትበረከት መንገድ መሪ ቁንጥጫ.... ከ15 -20 ውብ እድሜ ባዮሎጅ ባህል ከወፍጮቤቱ ኋላ ያለው ሰፈር ውስጥ የምትኖረው ጠይም ልጅ እና ወዘተ ተባብረው የሆነ ገነት የሚፈጥሩበት የምንፈቀርና የምናፈቅርበት እሳትነት። እሳት ውቅያኖስ ከተሻገረ ምኑን እሳት ሆነ? ከ20-30 ዮኒቨርስቲው፣ የአገር ፖለቲካው፣ አብዮቱ፣ ንብቡ ፣ ተስፋው፣ መማሩ፣ መመረቁ፣ ትንታግነቱ ፣ ውበቱ ትዳሩ ወግ ማረጉ ህዝብህ ጋር .... 30-50 ቁም ነገሩ የስራ እድገቱ፣ ስልጣኑ ፣  የልጆችና የትዳር የአባትነትና የማዕረግ ቤት መስራቱ ፣ ዕድሩ መሃበሩ .... ከ50- 70 ሽምግልናው ፣ ማስታረቁ፣ የልጅ ልጁ አንቱታው ዕቁቡ የወገብ ህመሙ ደም ግፊቱ ሽበቱ፣ ማህበረሰቡ ውስጥ ያለው ቦታ ቀበሌው ስብሰባው ምክሩ .... የሰው ልጅ ፈፅሞ መሰደድ የሌለበት ፍጡር ነው። ምንም ያህል ቁሳዊ ለውጥ ቢመጣም ስሩን ትቶ የተሰደደ ዛፍ ቆንጅ ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ ወይም ማገዶ እንጅ ዛፍ አይሆንም። በስንት ዓመቴ ልሰደድ ጥያቄ አይደለም ፣በስንት ዓመትህ ጠቅልለህ ትመለሳለህ ግን የሁሉም ስደተኛ የዕድሜ ልክ ጥያቄ ነው!

2
በተለይ ኑሮ ጋር እየታገሉ ገና በሁለት እግራቸው ለመቆም የሚሞክሩ ሰወች ሲጋቡ መፅሐፍ ቅዱስ ስጦታ የምታበረክቱ ሰወች ጥሩ ነውኮ...ግን መጥበሻ፣ ብረት ድስት፣ የአልጋ ልብስ፣ ብር ምናምን ብትጨምሩበት🙏 ሁለት ሚስኪኖች ተጋብተው አንድ አይነት 16 መፅሐፍ ቅዱስ ስጦታ እንደተቆለለባቸው ሲናገሩ ሰምቸ ነው። ፅደቅ ላለው አንዱ ይበቃል። ኧረ የምድሩንም እየተደጋገፍን ወገኖች። ክርስቲያን ከሆኑ መቸስ ቤታቸው መፅሐፍ ቅዱስ ይኖራል። ባይኖሩም ማግኘቱ ከባድ አይደለም። ይመስለኛል ብዙ ሰው እቤቱ ገና ያልተነበበ አዲስ መፅሐፍ ቅዱስ አለው ስጦታ ከመግዛት ያችን ወስዶ ይሰጣል። "ከምድርና ከሰማይ የከበደውን የአምላክ ቃል በዚህ ዕለት ስሰጣችሁ ለእናንተ ካለኝ ፍቅርና ምንም ስጦታ ከማይመጥነው ወዳጅነቴ...." ከሚል ስብከት ጋር። ይሄ የኔ ቢጤን እግዚአብሔር ይስጥህ ብለን እንደምናባርረው ያለ ነገር ነው።
523
3
የ130 ሚሊየን ነብያት አገር የደፈሩት መድረክ ላይ ወጡ እንጅ 130 ሚሊየኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ ነብይ ነው። ላረጋግጥላችሁ? ለምሳሌ በቅርቡ አገራችን ላይ ፍትሐዊ ዲሞክራሲያዊ አካታች እና ፍፁም ሰላማዊ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆን የአፍሪካ ህብረት የታዘበው ምርጫ መካሄዱ ይታወሳል። እሽ ይሄን የምታነበው ወይም የምታነቢው እህትና ወንድሞች በዚህ ምርጫ ቀድማችሁ ማን እንደሚያሸንፍ ውስጣችሁ ተንብዮ ነበር ወይስ አልተነበየም? ተንብዮ ነበር! ትንቢታችሁ ተሳሳተ? አንድም ኢትዮጵያዊ አልተሳሳተም። ጃሉድ ራሱ በትክክል ተንብዮ ነበር። የ130 ሚሊየን ነብያት አገር። ፕሮፌሳይ ሻርፕ ሹተር ሜጀር ዋን ፕሮፌት...ፕሮፌሳይ!
687
4
አንዳንድ ወላጆች ከበድ ያለ ጠባብነት አለባቸው። (አሌክስ አብርሃም) ስለግ*ብረሰ* ዶም፣ ስለሱስ፣ ስለልቅ ወሲብና ስለተለያዮ ከባህል እና ከሰብአዊነት ስላፈነገጡ የስነምግባር ጉዳዮች መስፋፋት ሲነሳ "እግዚአብሔር ይመስገን እኔ ልጀን ቅዱስ ማንትስ የክርስትያን ት/ቤት አስገብቻለሁ፣ አልሃምዱሊላሂ ልጀ የሚማረው የሙስሊም ትምህርት ቤት፣ የካቶሊክ የፕሮቴስታንት.... አገር ከተበላሸ እንኳን ሐይማኖት መር ትምህርት ቤት፣ ቤተ ክርስቲያንና መስጅዶች ራሳቸው የወመኔ መናህሪያ ነው የሚሆኑት። ድራግ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ወዘተ በስፋት እምነትን ተገን አድርገው ስንቱን ሲያጠፉት አላነበባችሁም? መጥፎ አገር ላይ የትኛውም ጥሩ ተቋም ቢመሰረት ሰወችን አይታደግም። ከ12 ዓመት በፊት የአንድ ኢንተር ናሽናል ስኩል ተማሪ ያለችኝን አልረሳም "ሽመልስ ሀብቴና እኛ ጋ 'የሚነፋው' ኳሊቲ ይለያያል" የኳሊቲ ጉዳይ ነው። መፍትሄው ልጆችን በእምነት በባህልና ማንነታቸው ማሳደግ እጅግ ጠቃሚ ጉዳይ ነው። ግን ከየትኛውም የእምነት የዘርና የኑሮ ደረጃ አጥር በላይ አገር የምትባል ነገር ስለመገንባት ማሰብ አለብን። እንደአገር የሚወጡ ፖሊሲወች አሰራርና ህገወጥነቶችን ልጅን ቅዱስ ማንትስ አጥር ውስጥ በማቆየት አንታደገውም። ትልቅ ማህበራዊ ውዥንብር እና የተሳሳተ የመደገፍያ ግንብ ነው። ክንፍ ያለን ቅዱስ ብንሆን ራሱ የተሻለ አገር ከሌለን የትኛውም እምነት ከባርነት ስነልቦና፣ ከማንነት አልባ ባዶነት ከጥፋትም አይታደገንም!! ከሁሉም ነገር በፊት አገር!!
809
5
የሆነ ጊዜ ነዳጅ የሚባለው አስቀያሚ ቅርናታም ድፍድፍ ከሽንትቤት ፍሳሽ በላይ ፀያፍ ቆሻሻ መሆኑ አይቀሬ ይመስለኛል። ዓለማችን ወደኤሌክትሪክና ኒውክሌር ኢነርጅ ፊቷን ማዞሯ አይቀርም። (ቱ ምናለ በሉኝ😁) ያኔ የነዳጅን መቶ እጥፍ ተወዶ ዙፋኑ ላይ የሚነግሰው ምን ይመስላችኋል? ውሃ! የአለማችን ውቂያኖሶች ሁሉ ውሃ እንደወርቅ የሚነጠርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። ይልቁንም እግዜር አንጥሮ ንፁህ ውሃ ያሸከማት አገራችን ያኔ የማንም አይን ማረፊያ ትሆናለች። አለም ባግበሰበሰችው የስልጣኔ ጉርሻ ስትታነቅ እጇን ወደቡትሊያችን መዘርጋቷ አይቀርም። እኔ መሪ ብሆን ግብፅን ችላ ብየ መቶ ተጨማሪ ግድብ የሚሰራበት ቦታ ነበር የማስጠናው። በውሃ ዙሪያ ብቻ የሚያስተምሩና የሚያጠኑ አንድ ሶስት ዮኒቨርስቲወችን ነበር የምገነባው። ከቦኖ ውሃ እስከአገር አቋራጭ ወንዞቻችን ጋር በተያያዘ ጉዳይ የውሃ ማህንዲሶችን ነበር የምመድበው። የውሃ ጥበቃ ላይ ከትራፊክ ህግ በላይ ነበር የምጋደለው። ካለአግባብ ወንዝ በመሻገር ሁሉ ልቀጣ እችላለሁ። (ማውራት እንደመስራት ባይቀልም) ትንቢቴ ካልተፈፀመ የልጅ ልጆቻችሁ ውሸታም ነብይ" እንዲሉኝ የአደራ ደብዳቤ ፅፋችሁ ሙቱ። ለምን እርግጠኛ ሆንክ ካላችሁኝ በሰፊው አብራራለሁ።
1 021
6
እናቴዋ ዛላ! ​(አሌክስ አብርሃም) ​ትምህርት ቤቶች ዕድሚያቸው የገፉ ልጆችን ከሕፃናት ጋር ቀላቅለው ማስተማር የለባቸውም የሚል ፅኑ እምነት አለኝ። ሕፃናቱን እንዳልነበሩ አድርገው ነው የሚያበላሿቸው፤ አደገኛ ነገር ነው። ወላጆች ይህንን ነገር በዝምታ ማለፍ የለባቸውም፤ ትምህርት ቤቶችም ጭምር። በእኛ ጊዜ የተለመደ ነበር፣ አሁን ግን እንጃ! ​አምስተኛ ክፍል ሆነን፣ እንዴት እንደሆነ እንጃ፣ ትልልቅ ልጆች ወደ ክፍላችን ገብተው ከኋላ ተቀመጡ። ድምፃቸው የጎረነነና የተስረቀረቀ ጎረምሶች ነበሩ። ሦስቱ እስከ አሁን አይረሱኝም። መዓዛ የምትባል፣ ማርያም ፊቷ ላይ አራት ቦታ ላይ የሳመቻት ድምቅ ያለች ቀይ ልጅ፣ ሕፃን ሕፃን የማትሸት፣ አጠገባችን ስትቀመጥ ሽቶና የላብ ጠረን ከላይዋ ላይ የሚተን ልጅ፤ ማስቲካ ከአፏ የማይለይ፣ ደግሞ ስታላምጥ «ቀጭ ቀጭ» የምታደርግ... በመጀመሪያው ቀን «ራሳችሁን አስተዋውቁ» ሲባል፣ «መዓዛ እባላለሁ፤ የምሠራው ቢዝነስ ነው» አለች እየተሽኮረመመች። «ቢዝነስ» የሚለውን ቃል መጀመሪያ የሰማሁት ከእሷ ነው። ደግሞ «ተማሪ ሥራ አለው እንዴ?» ብለናልም።​ቆይታ፣ በተለይ የሳይንስ ትምህርትን ትደፍነው ጀመር። «እንዴት ነው የደፈንሽው?» አልናት በልጅነት ጉጉት። «ወንድ ያችን ነገር ካገኘ... ሂሂሂሂ...» ነበር መልሷ። ያች ነገር ምን እንደሆነች ለማወቅ የደከምነው ድካም! በኋላ፣ እዚያ ፊቱ የማይፈታው የሳይንስ አስተማሪያችን ጋር የሆነ አልጋ ቤት ሲገቡ የአልጋ ቤቱ ባለቤቶች ልጅ አይቶ ነገረን (ጠባብ ከተማ!)። ቆይቶ ሴተኛ አዳሪ እንደነበረች አወቅን። በከተማችን ውስጥ ማታ ማታ ሴቶች ለዚሁ ሥራ የሚቆሙበት ሰፈር አለ፤ እኔ ራሴ አንዴ አየኋት። ከእህቴ ጋር ዘመድ ቤት አምሽተን በታክሲ እየተመለስን ነበር። እያለፍን ያኔ ያየኋት መዓዛ (በውልብታ ቢሆንም) ያ ቀይ ፊቷ ከመንገዱ መብራት ጋር በአእምሮዬ ላይ ታትሞ ቀርቷል። በደንብ የታተመው ደግሞ በግርምት አንገቴ እስኪሰበር ዙሬ በታክሲው መስኮት መንገድ ላይ ወደተደረደሩት ሴቶች ስመለከት፣ መብረቅ የሚያስንቅ የእህቴ ጥፊ ጭንቅላቴን 360 ዲግሪ አዞረው (ቸንቧ!)። ከዚያ ቀን ጀምሮ ሰፈሩን እራሱን ዙሬ ባይ፣ እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዓምድ ሆኜ የምቀር ነው የሚመስለኝ። ሴተኛ አዳሪ ምን እንደሆነችም ያወቅነው ያኔ ነው። የሚገርመው፣ ብዙ ሴት ተማሪዎች ነፍሳቸው እስኪወጣ መዓዛን ይወዷት ነበር። አረማመድና አወራራቸው፣ ማስቲካ አለማመጥና አሳሳቃቸው ሁሉ እንደ እሷ ሆኖ ነበር። ነፍሳቸውን ይማረውና እሷም፣ የሳይንስ አስተማሪያችንም መሞታቸውን አሥረኛ ክፍል ሆነን ሰማን። ​ሁለተኛው ልጅ ታጋይ ነበር፤ ዕድሜው 20 ገደማ የሚሆን። አስተማሪያችንን ሁሉ የሚቆጣ፣ በማትስ ክላስ ሳይቀር «ዲሞክራሲ!» የሚል ነበር። ሰብስቦ ስለ ትግል ያወራናል፦ «አነጣጠርኩና ቃታ ስስብ ጠላት ጭንቅላቱ እንደ ሰርዲን ተነደለ... ደሙ ፊን ብሎ ... አንጎሉ...» እያለ ምድረ ሕፃን ስንቃዥ እናድራለን። አስታውሳለሁ እኔ ራሱ ሌሊት ስጨነቅ ነበር የማድረው። ለቤተሰብ ደግሞ አንናገርም። አፋችሁን ከፍታችሁ ወሬ ብለው እኛው ላይ ይዞሩብናል። ​ሦስተኛው ልጅ ከገጠር የመጣ ነበር፤ ያኔ ዕድሜው 17 ወይም 18፣ ኧረ ቀንጭሮ ነው እንጂ 25ም ሊሆን ይችላል። ወሬው ሁሉ የወሲብና የሴት ሰውነት ነው። ደግሞ የክፍል አለቃ ነበር። ((አሁን ላይ ሳስበው ከከሰዓት ፈረቃ በኋላ «የቤት ጠረጋ» የሚባል ፕሮግራም ነበር፤ በየሳምንቱ የመማሪያ ክፍል እናፀደለን። ይሄ ልጅ ደጋግሞ ከኋላ የሚያስቀረው ሴቶችን ብቻ ነበር። ልጆቹ አንዳንዶቹ ያለቅሱ ነበር፣ ግን ጊዜው እንደ አሁኑ አልነበረም። አሁን ላይ አስባለሁ፣ ደፍሯቸው ይሆን? ያኔ ምንም አይገባንም ነበር።)) ​አንድ ቀን የማትስ አስተማሪያችን ቲቸር ፀሐይ ብላክቦርድ ላይ «ሒሳብ» ብላ ልትጽፍ ስትንጠራራ፣ ድብልቅ ባለ ድምፅ ምላሱን «ጧ» አድርጎ አጣጣመና «እናቴዋ ዛላ!» አለ። ዛላ ማለት ሰውነት፣ አቋም ማለት ነው። ለመደብን! ምድረ ማቲ ሬንቦውንም ቡርስሊንም ስናይ «እናቴዋ ዛላ!» እንላለን። ​አንድ ቀን «120» ፕሮግራም ላይ ቴሌቪዥን እያየን፣ የሆነች ገጸ ባህሪ(መሠረት መብራቴ ትመስለኛለች) ስትንጠራራ «እናቴዋ ዛላ!» አልኩ። ከእናቴና ከእህቴ እኩል የተወረወሩ ነጠላ ጫማዎች ጎንበስ በማለቴ በባዶ አየር ላይ ተጋጩ (አልበርት አንስታይን ራሱ «በሚሊዮን የብርሃን ዓመት አንዴ የሚከሰት ግጭት» እንዳለው በኋላ ፊዚክስ ስማር ደረስኩበት 😁)። ((((((((​ቁም ነገሩ፣ በዕድሜ የጎረመሱ ልጆች በልዩ ሁኔታ የሚማሩበት ፕሮግራም ሊመቻችላቸው ይገባል እንጂ ከሕፃናት ጋር ተቀላቅለው መማር የለባቸውም!!))))))
1 119
7
ድግምት ነው! ትላንት ምን እንደቀሰቀሰኝ እንጃ በደረቅ ሌሊት በሬን ከፍቸ ወጣሁና ቁሜ መንደሩን ስቃኝ ኤሎን መስክ የሚባለው ሰውየ ነጭ ጅብ እየጋለበ ሲያልፍ አየሁት... እንደውም የግራ እጁን አንስቶ ፈጣን ሰላምታ ሰጠኝ። ለነገሩ ቴስላ ትራክ የሚባለው መኪና ቅርፁ የጅብ መምሰሉ ያለነገር አይደለም። ያንን በየሲግመንድ ፍሩድ ሳይኮአናሊሲስ የተጠመቀ ጓደኛየን ስነግረው "አብርሽ የሆነ ነገር አናትህ ላይ ወጥቶ እያቃዠህ ነው አበርክተህ ተቃቀፍ" አለኝ። የሚቀፍ ይቀፍህ! ድሮም ከዛሬ ሳይኮ ምናምኒስት እማማ ዝናሽ ይሻላሉ። .... ቁም ነገር ግን ጓዶች...ሁሉም ገንዘብ የራሱ የሆነ አቅም አለው። ይሄ ዶላር የሚሉት ነገር ግን የሆነ ድግምት ነገር ነው። ባብራራላችሁ ደስ ይለኝ ነበርኮ ችግሩ ድግምትን የሚያውቀው ደጋሚው ብቻ ነው። እንዴት አድርገው ነው ዓለምን እግር ከወርች ያሰሩበት በፈጠራችሁ? እሽ 1944 የማንትስ ውል የሚል ነገር ተዋዋሉና ዶላር ነው ቋንቋችን አሉ! ይሄን ሁሉ አመት ወርቅ ቢባል ነዳጅ፣ ሚሊታሪ ቢባል ሲቪል፣ ሰላም ቢሆን ጦርነት ዶላር ምንተዳው! ስለዶላር ብዙ ኢኮኖሚስቶች፣ የፋይናንስና የታሪክ ባለሙያወች የሰጡትን ሌክቸር ሰምቻለሁ፣ የፃፉትን አንብቢያለሁ የደረስኩበት ድምዳሜ ዶላር ድግምት ነው የሚል ነው😁 ቀልድ እንዳይመስላችሁ ዶላር ከኤቲኤም ማሽን ስታወጡ (የሀብታም ምሳሌ ሰጠሁ ይቅር በሉኝ እኔም Bilal M Guwale ባለፈው ሲያወጣ ነው የሰማሁት ) ብቻ ስታወጡ ማሽኑ ተረረረረረረረ አይልም። በጥሞና ከሰማችሁት ያንደርብ... ያንጀርብ... የዠዣጥ... ያናዢጭ... ብሎ ዶላር ይሰጣችኋል። ወደቁም ነገሩ...😁 ይታያችሁ ዶላር የዓለማችን ውዱ ገንዘብ አይደለም! እንደውም 10ኛ ደረጃ ላይ ነው። የአንድ ገንዘብ "ውድ መሆን" እና "ኃያል መሆን" የተለያዩ ናቸው። የሌሎቹ ሀገራት ገንዘብ ዋጋቸው ከፍ ያለ ቢሆንም፣ የዓለም ንግድ የሚሽከረከርበትን የደም ዝውውር የተቆጣጠረው ግን የአሜሪካ ዶላር ነው። ወረቀቱ ከአሜሪካ ይሄዳል ነዳጅና ወርቅ ሆኖ ይመለሳል። እና ይሄ ድግምት አይደለም? የኩዌት ዲናር ዶላርን ሶስት እጥፍ ይበልጠዋል። ​የባህሬን ዲናር የኦማን ሪአል፣ ​የዮርዳኖስ ዲናር፣​የእንግሊዝ ፓውንድ፣ ​የካይማን ደሴቶች ዶላር(የት ናት አሁን ይች በፈጠራችሁ?) ፣​የጀርሲ ፓውንድ ፣​የስዊዘርላንድ ፍራንክ፣​ዩሮ ....ብላችሁ ​የአሜሪካ ዶላር ነው የሚመጣው። ወደገባየው ስትመጡ ይሄ ሁሉ "ጨዋ" ነው፤ ለዶላር ይንበረከካል። ነገሩኮ ያው ሳይንስ ነው፤ መቸስ አሳምረው ቀምረውታል። ግን ይሄን ያህል ጊዜ ዓለማችን ላይ ዋጋውም ክብሩም ሳይነካ የተዘባነነ ነገር አለ ወይ? ደግሞኮ ብዙ አገራት ይነጫነጫሉ ይሄን ነገር ይቃወማሉ፣ ግን የሚነጫነጩት ራሱ ዶላር ከፍለው ነው። (አዙረውባቸው ነዋ) እኔ አሁን የምፈልገው Abdulkadir Hajj Nureddin ይሄን ነገር ትፈስርልናለህ ወይስ ወርልድ ቢዝነስ ሴንተርን ጠበል እንርጨው? ወይ ደህና ደህና አሊም ይዘን እናስቀራበት?
1 358
8
Немає тексту...
1 232
9
ብር ያስገኝ እንጅ ምንም ነገር ይሁን እሰራለሁ የሚሉ ሰወች የትም አይደርሱም!! ነገሩ የመቸገር ብቻ አይደለም፤ የመባከን የመግበስበስ በሽታም ነው። ለሆነ ነገር ሕይወትህን ጭምር እስከመክፈል የሚደርስ ፍቅር ይኑርህ። አንድ ነገር ላይ ዓይኖችህ ያተኩሩ፣ ኢላማ ይኑርህ እዛ ግብህ ላይ ለመድረስ ግን ማንኛውንም ነገር ስራ። በተለይ ይሄ ሶሻል ሚዲያና ድህነት ምንም ያልሆኑ ግን ሁሉንም ነገር ነን የሚሉ ማማሰያወችን ለጉድ እየፈለፈለብን ነው። የወሲብና ፖርኖግራፊ አስተማሪነትን ከሐይማኖት ሰባኪነት ጋር፣ ጋዜጠኝነትን ከካድሬነት፣ ትዳርን ከወንድ አተራማሽነት፣ በጎ አድራጊነትን ከሌብነት ጋር እኩል ሲያሳልጡት ስታይ አትገረምም ወይ ያ ጀመዓ?
1 707
10
ውድም! ብዙ ሰወች ብር ማግኘት የመጨረሻ ያስደስታቸዋል፤ የባንክ አካውንታቸው በሆነች ቁጥር ከፍ ሲል ሳይበሉ ይጠግባሉ ሳይ...ይረካሉ (ሳይጠጡ ለማለት ነው) የሆነ ሆኖ ብዙሃኑ የፋይናንስ ሰው የማይነግራችሁ እውነተኛው ደስታ ያለው ብር በማጠራቀም ውስጥ ባለው ጭንቀት የተሞላ መቆናቆን ሳይሆን ብር ማጥፋት፣ መክፈል፣ ቀልብ ለወደደው መዘርዘር፣ መመንዘር ላይ ነው። በተለይ ባጠፋኸው ብር ነገህ እንደማይበላሽ፣ ያወጣኸውን ያህል ወይም የበለጠ በቀላሉ የመተካት አቅሙ ካለህ፣ ማን ብር እንደማጥፋት! ውድም ርክት! ካርዱን ስትጭረው፣ ካሹን ስትዘረዝረው፣ ኤቲኤሙን ስታስተፋው ወዳጅህን "ስርዓት ያዝ እኔ ነኝ የምከፍለው" ስትል፣ ሳትከራከር ጠቅልይው ስትል፣ ነገ መለሰ አልመለሰ ሳትል ለተቸገረ ስትሰጥ...እውነተኛ ደስታ ያለው ብርን አፈር አባቱ አስበልተህ ለተፈጠረት ዓለማ ስታውለው ነው። ውድም! አስበው "ይችን ቆጥቤ ጫማ ብገዛ ፣ ይችን አጠራቅሜ መኪና ስትል ድፍት ብለህ "ውይ ትላንት ማዞሪያው ጋ እርጥብ ሲበላ አይቸው አልነበር ምን ነካው?" ሲሉህ😁 የሰው ልጅ የተፈጠረው ለማውደም ነው። መቆጠብ ማጠራቀም ይሉት ብሂል በኋላ የመጣ ጣጣ! "ለነገ አትጨነቁ" አለ ራሱ ጌትየው። እህሳ ብንል እያወደምክ ተመስገን እያልክ ኑር። አቦ የምታወድሙት ገንዘብ ከአውዳሚ ልብ ጋር ይስጣችሁ። ከየት አባቱ እያመጣ ነው የሚል ብስጩ ቢከባችሁም... ውድም!
1 740
11
የወለደች ሴት አግባ! (አሌክስ አብርሃም) ትዳር ብዙ ግላዊና የወል ምርጫዎች ያሉት ጉዳይ ነው። ግን በፍቺም ይሁን በሌላ ምክንያት ልጅ ብቻቸውን የሚያሳድጉ ሴቶችን እንደማግባት ጀነት የለም። የሕይወትን ትርጉም በሚገባ የተረዱ፣ ሕፃን ሕፃን የማያጫውታቸው፣ በክፉም በደጉም የትዳርን ጫና መቋቋም የሚችሉ፣ ከሚስትነት በላይ የእናትነት ክብርና የሰውን ልክ ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ ለሚደረግላቸውም ለሚያደርጉትም ነገር በምስጋና የተሞሉ፣ በሁሉም ነገር በመቶ የኮሌጅ ድግሪ የሚመነዘር በተግባር የተፈተነ ክህሎት ያላቸው፣ ስህተትና ቸልተኝነት የሚያስከፍለውን ዋጋ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ለሚያደርጉት ነገር ጥንቁቅ የሆኑ ምርጥ ፍጥረቶች ናቸው። ልጅ በሚባለው በር በኩል ከራስ ወዳድነት ወጥተዋል። ለአካባቢያቸው ለቤተሰብ ህያው ናቸው። ​ይሁንና ያልወለዳችሁ ሴቶች ከጋብቻ ውጭ እንዳትሞክሩት። እነዚህ ሴቶች ለዚህ ማንነት የሚበቁት እናንተ በቀላሉ የምታልፉትን የሕይወት መንገድ በብዙ እጥፍ የስጋና የስነ-ልቦና ስቃይ አልፈው ነው። ብዙዎቹ ብዙ የደከሙለትን ነገር መንገድ ላይ ትተውታል፤ መድረስ ከሚገባቸው ቦታ ሳይደርሱ ወርደዋል። ይሁንና ሌላ የተከበረ ማንነት ላይ ደርሰዋል።
1 856
12
ቴምር ሪል ስቴት የሀብታሙ ሃደራን የግጥም መድብል መፅሐፍ ከዛሬ ጀምሮ በተከታታይ ለመቶ ሰወች ይሸልማል። እንዲሁም የመረጥኳቸውን መፅሐፍት ለአንባቢወቸ እንድሸልም የቴምር ሪል ስቴት ሴልስ ማን የሆነው አብርሃም ተስፋየ ነግሮኛል። ቴምሮች ከስነፅሁፉ ቤተሰብ ጋር የበለጠ በመስራት አዲስ ፈር ቀዳጅ እየሆኑ ነው። ምክንያቱም ንባብን በማበረታታት የሪል ስቴት ሳይቶቻቸውን ማስተዋወቅ ስለሚፈልጉ ነው። ማሳሰቢያ ከቴምር ሪል ስቴት ለማሰታወቂያ ሰባራ ሳንቲም አልተቀበልኩም! መፅሐፍ ገዝተው ደራሲወችን ያበረታታሉ፣ በዚህ በጎ ስራቸው ደራሲያን አንባቢወች ይጠቀማሉ። እኔም ማስታወቂያቸውን ያለምንም ክፍያ እለጥፍላቸዋለሁ።(የሪል ስቴት ማስታወቂያ እየሰራህ ነው ብር አበድረን፣ ባለአንድ መኝታ ከሳርቤቱ ሳይት አበድረን ምናምን እንዳትሉኝ😁) ቴምር ሪል ስቴቶች የላኩትን ማስታወቂያ እነሆ። ቴምር ሪል ስቴት በመሃል ከተማ ሳር ቤት አደባባይ እንዲሁም በቡልጋሪያ አፍሪካ ህብረት አዲስ ሳይቶች አሉት...ከባለ አንድ እስከ ባለ ሶስት መኝታ አፓርታማዎችን በተለያየ የ ካሬ አማራጭ ከ20 % ወይም ከ 1.5 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ወይም ከ 5.2 ሚሊዮን ብር ጠቅላ ዋጋ ያቀርባል። ፒያሳ አደባባይ ግንባታቸው 50% በላይ የተጠናቀቀ ከ 20 ካሬ ጀምሮ ዘመናዊ የንግድ ሱቆች አሏቸው። ቴምር ሪል እስቴት በ11 ዓመት 10ፕሮጀክት ጥንቅቅ አድርጎ ያስረከበ ግዙፍ ታማኝ ተቋም ነው * ምንም ዓይነት የዋጋ ግሽበት አይመለከተዎትም እንዲሁም ቀስ ብለው ካለ ምንም ወለድ በ ሶስት ዓመት ከፍለው ያጠናቀቃሉ ብሏል። በውጭ አገራት ለምትኖሩ ያሉበት አገር በ DHL ልከን እናስፈርመዎታለን ቅድመ ክፍያ ከተከፈለ በኋላ ቀሪው በግንባታ ሂደት በ16 ዙር ከፍለው የሚያጠናቅቁበት የአከፋፈል ስርዓት ተመቻችቷል። * የምንሸጣቸው ቤቶች ሁሉንም ነገር ያሟሉ ዘመናዊ አፓርታማዎች ናቸው ሳርቤት እና ቡልጋሪያ ቤቶቹ የሚከራዩት በዶላር ስለሆነ ለኢንቨስትመንት በጣም አዋጭ ናቸው ሳርቤት በዚህ ዋጋ አፓርታማዎችን ማግኘት አይታሰብም ብለዋቸኋል። ለማንኛውም መረጃ Abreham Tesfaye ን አግኙት ብዙ ዝርዝር ብዙ አማራጭ አለው። ወይም በዚህ ደውሉለት 0910798353 / 0908770077 https://wa.me/251910798353?text ወደመፅሐፍ ሽልማት! ....የሐብታሙ ሐደራን መፅሐፍ መሸለም የሚፈልግ ኮሜንት ላይ አለሁ ማለት ብቻ ነው።
2 059
13
Немає тексту...
1 767
14
የሆነ ጊዜ ጧት የስራ ባልደረባየ ጋር ታክሲ ውስጥ በአጋጣሚ ተገናኝተን ወደቢሯችን አብረን እየሄድን ነበር። ልክ ስንደርስ ክንዴን ያዝ አድርጎኝ ሰዓቱን ተመለከተና... "ልክ በሰዓቱ ደረስን፣ ትንሽ እናርፍድ" አለኝ። "እ? ለምን?" "በሰዓቱ ከገባን አለቃችን ይለምዳል"😁 ትቸው ገባሁ እርሱ አርፍዶ መጣ። ሌላ ቀን አርፍጀ ስገባ አለቃየ ተነጫነጨ፣ በማርፈዴ ድርጅቱ ሊደርስበት የሚችለውን የመሬት መንቀጥቀጥ አስረዳኝ። ይቅርታ ጠይቄ ገባሁ። ከእኔ በኋላ ብዙ ቆይቶ ያ እናርፍድ ያለኝ ጓድ ሲደርስ "በቃ አይሞላልህም አንተ " ምናምን ብሎ በሞቀ ሰላምታ ተላለፉ። በየቢሮው ስንት ስትራጀቲሴት አለ እናንተ?
1 849
15
አምባሩን ያጌጠበት ሌላ... (አሌክስ አብርሃም) አንድ ቀን ከመዝሙርና ከግዜር ቃል ውጭ ምንም የማያውቅ ጴንጤ ጓደኛየ ፊቱ ቅጭም ብሎ መጣና እቤቴ አደረ። ሌሊት ድንገት ተነሳና ተንበርክኮ እያለቀሰ መፀለይ ጀመረ። ለምን ጌታ ሆይ ለምን? እያለ! እና በመሃል በቀስታ ሲዘምር ተመሰጨ ሳዳምጠው መዝሙሩ ለየት አለብኝ።ገርሞኝ በደንብ አዳመጥኩት። አሃ ይሄ ነገር .... ጧት ቁርስ ስንበላ ጠየኩት "ይሄ ዘፈን ጌታን ተቀበለ እንዴ?" "የቱ ዘፈን?" የፀጋየ እሸቱ ... ፀጋ እሸቱ ማነው? ፀጋ አላልኩም ፀጋየ ነው...ሌሊት እየፀለይክ "አምባሩን ያጌጠበት ሌላ ተከሳሽ አምሮት ያጣ ገላ" ስትል ነውኮ ያደርከው። "ጌታ ይገስፅህ" አለና ሳቁ አመለጠው። ለካስ ሚስኪን ወዳጀ አንዲት የቸርች እህት "አባለክ" ተብሎ ከቸርች ታግዶ አንጀቱ እርር ብሎ ነው። ብዙ ጴንጤወች እንደሚሉት "ታክሲ ውስጥ የሰማው ዘፈን" አእምሮውን ተቆጣጥሮት ይሆናል። አሳዛኙ ነገር ትክክለኛው አባላጊና ይሄ ሚስኪን ስማቸው ከነአያት ከመገጣጠሙ ውጭ ምንም ግንኙነት አልነበራቸውም። የልጅቱ የተከበሩ ቤተሰቦች ማርገዟን ሲያውቁ አበዱ። ወደክፍለ ሐገር ላኳትና በስልክ ሲያናዝዟት ስሙን ተናገረች። ሽማግሌወች ደውለው ሲጠይቋትም ደገመችው። ሽማግሌወች "አገኘነው" አሉና ሚስኪን ወዳጀ ሻላላላባ እያለ ሲሄድ የምን ሻላላላባ ነው! ባልተገባ.. ባልተቀደሰ... ባልተፈቀደ...ባልተወደደ.. መንገድ ጌታን በድልሃል... የምዕመኑንም አሳዝነሀል፣ ቤተክርስቲያኗ በመተዳደሪያ ደንቧ አንቀፅ ቀ፣ ንኡስ አንቀፅ ጰ መሠረት ለአንድ ዓመት ከማንኛውም አገልግሎት ታግደህ እየፆምክ እየፀለይክ በንስሃ እንድትቆይ ወስናለች።" ነገሩ ተጣርቶ ወዳጀ ላልሰራው ሀጢያት በፆም ከስቶ ሲመለስ፣ ጉባኤው ፊት በስህተት መታገዱ ተገለፀ። ፓስተሩ የተናገረው ነገር ግን ብስጭት አደረገው ። "ሰይጣን የቅዱሳንን ልብ ለማውረድ በሐሰት ይወነጅላል ነፃ የሚያወጣ አምላክ ግን ስራ ላይ ነው ወገኖቸ.....እና ወንድማችን እህታችንን አላባለገም፤ ጌታ ይረዳዋል ወደፊትም አያባልግም"😁
2 115
16
አከራይ ተከራይ ሲባል ምንጊዜም ትዝ የሚለኝ አስቂኝ ነገር... (አሌክስ አብርሃም) አንድ ሰፊ የግለሰብ ግቢ ውስጥ ተከራይቸ እኖር ነበር። ብዙ ነበርን ተከራዮቹ ፤ ከእኔ ቤት ቀጥሎ የሚኖረው ተከራይ አንድ አስተማሪ ሲሆን ቅዳሜ ቅዳሜ ብቻ ጢንቢራው እስኪዞር ከመስከርና "ገንዘብ አለያየን ደሃ በመሆኔ" እያለ ከመዝፈን ውጭ ሽቁጥቁጥ፣ የግቢውን በር እንኳን ሲያልፍ ጫማውን ሊያወልቅ የሚዳዳው ትሁት ሰው ነበረ። አንድ ቅዳሜ ግን ምናባቱ...ማለቴ ምን ጠጥቶ እንደመጣ እንጃ ግቢውን በአንድ እግሩ አቆመው። የሆነ ለማሽቃበጥ የሚረዳ መጠጥ ይመስለኛል የጠጣው። ገና ከመግባቱ "ሁላችንም ኪራይ መጨመር አለብን " ብሎ ጮኸ። "አከራዮቻችን ዝም ስላሉ ብቻ ዝም ማለት ልክ ነው? አይደለም! ቤት መስራት ብዙ ዋጋ ያስከፍላል ካርታ አለ...ፕላን አለ...ለመሃንዲስና ምናምን ጉቦ አለ...ብሎኬት አለ...ሲሚንቶ አለ...ለአከራይ ማን ያስብለት?... መሯቸው ሸጠውት ቢሄዱስ? እኔ ከነገ ጀምሮ ሃምሳ ብር ጨምሪያለሁ...ሁልሽም ኪራይ ጨምሪ...እንትና መቶ ብር...እንትና ስልሳ ብር ... አንተ አብርሃም ሰባ ብር ፣ የውሃም እኛ መክፈል አለብን.....(በቃ ይሄ ሰው ራሱን ሊያጠፋ ወስኗል ማለት ነው ብየ አሰብኩ) አከራያችን ጋቢያቸውን ለብሰው ብቅ አሉና እንደወትሮው "እንዲህ ከረበሽክ ከነገ ጀምሮ ቤት ፈልግ" ይሉታል ብለን ስንጠብቅ ፍቅር በሆነ ድምፅ "መምህር ና እራት ብላ እስቲ... " ወሬ ልመለከት ስንወጣ አከራየ ጋር እንደመጋኛ ተገጣጠምን። ወደእኔ እያዮ "የሚጠጣ ሰውኮ በሆዱ ክፋት የለም..." 🤔 እና ልጠጣልወት?
2 785
17
የኢትዮጵያ ዘፈንና መዝሙር ሳይቀር ወደ AI እጆቹን ዘርግቷል። ገና ሙሉ አካሉ ኤአይ ውስጥ ይዘፈቃል። የዛሬ አመት ይህን ስል የተነጫነጨው ሁሉ ዛሬ በኤፍኤሞች ሳይቀር እያዳመጠ ነው። መጀመሪያ አካባቢ ብዙዎች «AI የጥበብን ስሜትና ለዛ ያጠፋዋል» ብለው ሲከራከሩና ሲነጫነጩ ነበር። አሁን ግን የኢትዮጵያ የሙዚቃና የመዝሙር ኢንዱስትሪ ውስጥ የAI አሻራ በግልጽ እየታየ ነው። ከድምፅ ቅንብርና ማስተሪንግ ጀምሮ፣ የድሮ ድምፃውያንን ድምፅ በAI በማደስ አልፎ ተርፎም ሙሉ በሙሉ በAI የተሰሩ ዜማዎችና ግጥሞች በኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያዎቹ እና በሶሻል ሚዲያ መደበኛ እየሆኑ መጥተዋል። ሁልጊዜ አደዋ የለም፤ አንዳንዴ በሰላም እጅ ሰጥቶ ለራስ በሚመች መንገድ ነገሮችን መጠቀም የተሻለ ነው!!
3 167
18
እየመጡ ነው! (አሌክስ አብርሃም) ቦሌና መገናኛ ጫማ ልትገዙ ስትሄዱ ድንገት አግኝታችሁት እንዳትደነግጡ ከወዲሁ ልንገራችሁ። የቻይናው ብሔራዊ የሕክምና ምርቶች አስተዳደር NEO (Neural Electronic Opportunity) ጭንቅላት ውስጥ የሚቀበር ቺፕ ለገበያ እንዲውል በይፋ ፈቅዷል። በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የጭንቅላት ውስጥ ቺፕ የንግድ ፈቃድ ተሰጠ ማለት ነው። (እንደፈራነው) ጦቢያዊያን ለአመታት ችብስ 666 ...ስንለው የነበረው ጉዳይ ያው እየመጣ ነው። ነገ እንደጥርስ ማስታወቂያ በተወሳሰቡ የህክምና ቃላት ታጅቦ "አስመጥተናል" የሚል ማስታወቂያ መነገሩ አይቀሬ ነው። ለጊዜው ለአካል ጉዳተኞች ረዳትነት ብቻ ይውላል ብለዋል። ያው አንድ ነገር ከተመረተ በኋላ የቴክኖሎጅውን ፍጥነት በስልክ ማየት ነው። ዝርዝሩ ይቅርብን ግን ኤሎን ማስክ 'Neuralink' ብሎ የጀመረውን ፕሮጀክት ቻይናወቹ ቀድመው ለገበያ አውለውታል።የሆነ ቀን ቱርክ ፀጉር ከቱርክ አንጎል ከቻይና አሰገጥመን ሸገር ላይ እንግሊዝኛውን ልናዶለዱለው እንችላለን። ችግሩ ሀክ ሊደረግም ይችላል የሚል ስጋት መኖሩ ነው። አስበሽዋል እናት የሰርግሽ ቀን የባልሽ አንጎል ሃክ ቢደረግ? ወጩ ጋር ተዳምሮ...😁
3 791
19
ባሰብኩት ቁጥር ፈገግ የሚያደርገኝ የምርጫ ክርክር..ምርጫ ዘጠና ሰባት ላይ ኢህአዴግን ወክለው የተወዳደሩ ሁለት የመብራት ሐይል ሰራተኞች ነበሩ። አጋጣሚ ይሁን ታስቦበት እኔጃ ! እና የጦፈ ክርክር ላይ"እኛ ብንመረጥ በብርሃን ነው መንገዱን ሁሉ የምናጥለቀልቀው.... ምናምን ሲሉ የቅንጅት ተፎካካሪያቸው ጣልቃ ገብቶ ምን ቢል ጥሩ ነው " እነዚህን ሰወች ብትመርጧቸው አንዱ መብራት ያጠፋል ሌላው ያበራል፣ ከዚያ ሽፍት ይቀያየራሉ አብሪው ያጠፋል አጥፊው ያበራል" 😁
2 943
20
ዛሬ አዳሬን አንድ ሁለት መርከብ በሚሳኤል አኖጋሁ ትላለች ኢራን፤ አዳሬን አንድ ስድስት የሚሳኤል ጣቢያ አደባየሁ ትላለች አሜሪካ፤ የነዳጅ ጉድጓድ ሲኦል አደረኩ ትላለች ኢስራኤል፣ የሀይል ማመንጫ አደባየሁ ትላለች ሩሲያ በዮክሬን። የሱዳኖቹ ጎረምሶች ድሮን ጣልኩ ከተማ አነደድኩ ይባባላሉ፤ የኛም አገር አከርካሪ ሰበርኩ ቅልጥም ሰበርኩ ይባባላሉ(አጥንት ነክ ነው ጦርነታችን) እና በአንድ ሌሊት በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር እየነደደ ዓለምን ሲያሞቅ ለምንድነው እኔ ቀዳዳ ጫማ የማደርገው፣ ለምንድነው የቤት ኪራይ የምጨነቀው? ለምንድነው ልጆቸ ልኳንዳ የተሰቀለ ስጋ እያዮ ምራቃቸውን የሚውጡት? ለምንድነው መታከሚያ አጥቸ እያቃሰትኩ የምኖረው? ለምንድነው ሰላሳ ቀን ለፍቸ እንደይሁዳ ሰላሳ ዲናር ደመወዜ ከንቱ የሚሆነው? ማለት አያምራችሁም? ለምን? ወይስ በዚህ ሁሉ ጦርነት ህዝብ ሲረግፍ እኔ መትረፌ ለምን እንበል?
2 810