fa
Feedback
የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ

የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ

رفتن به کانال در Telegram

📝👉በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻነል በወራቤ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ መድረሳዎች የሚሰጡ የሰለፊዮች ደርስ ፣ሙሃደራ እንዲሁም መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናል !!! https://t.me/ibnbaz1212

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
3 392
مشترکین
+4824 ساعت
+1687 روز
+30830 روز
آرشیو پست ها
💥#የጁሙዓ_ኹጥባ💥      √√√√√√√√√√ 📄ርዕስ:- በአላህ ገመድ ላይ መተሳሰር 🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ - ታጁዲን (ሀፊዘሁላህ) 🕌 በዳር አስ-ሱና መስጂድ አዲስ አበባ - አለም ባንክ 📅፦ ጁሙዓ ረቢዐል አወል 8 /1448 ሂጅሪያ http://t.me/DarASSunnah1444 http://t.me/DarASSunnah1444

👉 አዲስ pdf عنوان: حكم التعاون مع أهل البدع وبيان عواقب التعاون مع دعاة التجميع . نصيحة للمتساهلين في التعاون مع أهل البدع. ርእስ:- ከቢድዐህ ባለቤቶች ጋር መተባበርና ወደ ሰብሳቢነት ተጣሪዎች ጋር መተባበር መጨረሻው ላይ ያለው አደጋ!፣ እንዲሁም ከቢድዐህ ባለቤቶች ጋር በመተባበር ለተዘናጉ ሰዎች ምክር 📝 بقلم الشيخ الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله الإثيوبي السلطي حفظه الله 📝 አዘጋጅ፦ ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ ቢን ዐብደላህ አል ኢትዮጲ አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ) (ዐረቢኛ የምትችሉ pdf  አውርዳችሁ አንብቡት) #join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/HussinAssilty https://t.me/HussinAssilty

[(قذف الأبرياء من الدعاة إلى الله بالحق والبرهان أخطر من قذف المحصنات المؤمنات..]) الشيخ ربيع بن هادي المدخلي رحمه الله.

آداب الجمعة وسننها التي جاءت بها السنة 1. الاغتسال يوم الجمعة؛ قال ﷺ: «غُسل يوم الجمعة واجب على كل محتلم» متفق عليه، والمراد عند جمهور العلماء تأكد السنية. 2. التطيب والتعطر عند الذهاب إلى الجمعة. 3. لبس أحسن الثياب والتجمل للجمعة. 4. السواك وتنظيف الفم. 5. التبكير إلى المسجد وعدم التأخر. 6. المشي إلى المسجد بسكينة ووقار. 7. الإكثار من الصلاة على النبي ﷺ يوم الجمعة وليلتها. 8. قراءة سورة الكهف يوم الجمعة، وقد ورد فيها حديث حسن بمجموع طرقه. 9. الإكثار من الدعاء؛ فإن في يوم الجمعة ساعة إجابة. 10. الإنصات للخطبة وعدم الكلام أثناءها. 11. عدم تخطي رقاب الناس للوصول إلى الصفوف. 12. عدم التفريق بين اثنين إلا بإذنهما. 13. الجلوس حيث ينتهي به المجلس وعدم مزاحمة الناس. 14. تحري الصف الأول والمبادرة إليه. 15. الصلاة ركعتين تحية المسجد إذا دخل والإمام يخطب، ثم يجلس للخطبة؛ لحديث سُليك الغطفاني في صحيح مسلم. 16. عدم العبث أثناء الخطبة بالثوب أو الحصى أو الهاتف ونحو ذلك. 17. الجلوس أثناء الخطبة والاستماع إليها بقلب حاضر. 18. الصلاة مع الإمام وعدم الانشغال عن الجمعة بأمور الدنيا. 19.قراءة سورة الجمعة والمنافقون في صلاة الجمعة أحيانًا، أو الجمعة والغاشية، فقد ثبت ذلك عن النبي ﷺ. 20. صلاة السنة بعد الجمعة؛ فقد ثبت أنه ﷺ صلى بعد الجمعة ركعتين، وثبت عنه أيضًا أربع ركعات، فيُشرع فعل هذا تارة وهذا تارة. https://t.me/abu_abedelah_Ezedin_inbnu_Siraj

ሱፍያን አሰውሪ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል: "አላህን ከፈራክ ከሰዎች ይበቃካል፣ ሰዎችን ከፈራክ ግን ከአላህ በምንም ነገር አያብቃቁክም።" ስለዚህ ሰለፍይ ወንድም እህት ሆይ! ከዚህ ታላቅ ዓሊም
ሱፍያን አሰውሪ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል: "አላህን ከፈራክ ከሰዎች ይበቃካል፣ ሰዎችን ከፈራክ ግን ከአላህ በምንም ነገር አያብቃቁክም።" ስለዚህ ሰለፍይ ወንድም እህት ሆይ! ከዚህ ታላቅ ዓሊም ምክር አንፃር የት ነው ያለነው? እራሳችንን እንፈትሽ። بارك الله فيكم

ተጠንቀቅ!! ሰዎችን በጭፍን አትከተል!! ————— ሰዎች በሐቅ ይመዘናሉ እንጂ ሐቅ በሰዎች አይመዘንም!! የሀቅ እንጂ የሰዎች ጭፍን ተከታይ አትሁን!። ምክንያቱም የታዘዝከው ሐቅን እንጂ ሰዎችን እንድትከተል አይደለም!። በጭፍን ውዴታ ጥግ መድረስ አደጋ አለው። ጭፍን ተከታይ መሆን ሐቅ ከመቀበል ያውርሃልና ተጠንቀቅ!። በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም። አላህ ይጠብቀንና በጭፍን የተከተልከው ሰው ከተንሸራተተ አለያም ድንበር አላፊ ከሆነ አንተም አብረሀው ገደል ልትገባ ትችላለህና ጭፍን ተከታይ አትሁን!!። ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) “በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም” ብለዋል። በመሆኑም የሰዎች ጭፍን ተከታይ መሆንን ተጠንቀቅ። ወደ ቁል ቁል ሲወርዱ እንዳያወርዱህ፣ ድንበር ሲያልፉም በጭፍን ተከትለሃቸው እንዳታልፍ። የሰዎች ንግግር ትክክል ካልሆነ ተመላሽ ነው። ፍፁም የሆነውና ሊመለስ የማይችለው የመልእክተኛው ﷺ ንግግርና ተግባር ብቻና ብቻ ነው። ኢማሙ ማሊክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ማለታቸውን አትዘንጋ:- "ሁላችንም ተመላሾችና የተናገርነውም የሚመለስ ነው የዚህ ቀብር ባለ ቤት ሲቀር።" አሉ። የቀብሩ ባለ ቤት በማለታቸው የፈለጉበት መልአክተኛውን ﷺ ነው። ሐቅን እወቅ! ከዚያም ሰዎችን በሀቅ ትመዝናቸዋለህ። የሀቅ ሰዎችንም ታውቃለህ። ሰዎችን አውቀህ በጭፍን የምትከተላቸው ከሆነ ግን የሐቅ መመዘኛ መሰረትህ ትክክለኛ ማስረጃ ላይ የተገነባ ሳይሆን የሰዎች ጭፍን ውዴታና ጭፍን ተከታይነት ይሆንና ሲገለባበጡም አብሮ መገለባበጥ ይሆናል። ቆም ብለህ አስተውል! ቡድንተኝነትና ጭፍን ውዴታ አያውርህ!። ነገ አላህ ፊት ወዳጅህ ጠላት ሊሆንብህ ይችላል። አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:- الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ «ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡» አዝ-ዙኽሩፍ 67 ታዲያ ስትወድም ሆነ ስትጠላ በጭፍን አይሁን!። የወደድከው አቅጣጫ ከሳተና ለየት ያሉ ነገሮችን ካስተዋልክበት ቆም በል።  በጭፍን መውደድም መጥላትም አደጋው የከፋ ነውና ተጠንቀቅ!!። ሳታስበው በሰለፊያ መንሀጅ ስም በተመሰረተ ልዩ በሆነ ቡድንተኝነትና ዘመናዊ ሙሪድነት አዘቅጥ ውስጥ እንዳትዘፈቅ!!። በጭፍን በውዴታው የከነፍከለት አካል መንገድ ከሳተ ተከትለሀው መሳትህ አይጠቅምህም! ከባድ አደጋ ነው። የሚጠቅምህ በየትኛውም ወቅት ሀቅን አጥብቀህ መያዝህ ነው!!። በተለይ በፊትና ጊዜ ምንም ያህል በአንዳንድ መልካም ስራዎቹ የምትወደው በዳዒነት የገነነ ነገር ግን እውቀቱ እዚህ ግባ የማይባል የምትወደው ሰው ቢኖር እንኳ ጠንካራ ነጥቦች ሲነሱ፣ የሆነ ጊዜ "እኔ እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን አንስቼ ለመናገር እውቀቴ አይፈቅድልኝም" እያለ በሌላ ጊዜ ደግሞ የእውቀት ደረጃው በማይፈቅደው አጀንዳ ውስጥ ገብቶ ሲዘባርቅ እያየሀው ስለ ወደድከው ብቻ በጭፍን መከተል የለብህም!። በየትኛውም ወቅት የጠንካራ እውቀት ባለ ቤቶችን እና በዳዒነት የገነኑ ያለ እውቀት ደረጃቸው ተከታይ ስላላቸው ብቻ በድፍረት የሚናገሩና ተከታዮቻቸውን ይዘው ወደፈለጉበት አቅጣጫ የሚዋዥቁ ያለ እውቀት ታዋቂ የሆኑ ሰዎችን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። ሐቅ በጋጋታና ከተለያየ አቅጣጫ በሚጮሁ በተደራጁ ቲፎዞዎች ጩሀት አይለካም!። እውነትን ቆም ብሎ በማስረጃ መለየት ነው እንጂ ጭፍን ተከታይ መሆን አደጋው የከፋ ነው!። ትላንት በጥሩ አቋምና በትክክለኛው መንሀጅ እያለ ጠላቶቹ የነበሩ ኢኽዋንን ጨምሮ "አይንህ ላፈር" የሚሉት ሰዎች ዛሬ እንዴት ወዳጆቹ ሊሆኑና እሱን ሊያደንቁ፣ ሊያሞግሱ እንደቻሉ? ቆም ብለህ ፈትሽ!!። እሱ ተለሳልሶ ከአቋሙ ሸርተት ብሎ ነው ወይስ እነሱ ወደ ትክክለኛው አቋምና መንሀጅ ተመልሰው ነው? ብለህ እራስህን ጠይቅ። ያለፉ ሂደቶችንና በወቅቱ ያሉ ሂደቶችንም በተረጋጋና በገለልተኝነት መንፈስ ቃኝ!። እውነት ጭፍን ተከታይነትና ቡድንተኝነት ሳያውረው ከልቡ ለፈለጋት ሰው ግልፅ ትሆናለች!። ታላቁ ሸይኽ አሕመድ ኢብኑ የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ: - “ወላሂ! በጌታዬ ይሁንብኝ አላህ ዘንድ እገሌና አገሌ አይጠቅሙህም!። የሚጠቅምህማ በሀቅ ላይ መቆምህና ለሀቅና ለተከታዮቹ ረዳት መሆንህ ነው።” [ረዱል ጀዋብ 54] »» ሐቅን ተከተል!። ለሸይኽ አሕመድ ቢን የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) ድንቅ ንግግር ትኩረት ስጠው!። ወገንተኝነት አያጥቃህ፣ ለሀቅ ብቻ ወግን! ሀቁ በበቂና በትክክለኛ ማስረጃ ከተነገረህ አንተም ሆንክ የምትወደው ዳዒ አለያም ከጎንህ ያሉ ወዳጆችህ መንገድ ስህተት እስከሆነ ወደ ሀቁ ለመመለስ አታንገራግር!! የተነገረህ እውነት እሰከሆነ ለመቀበል ቆራጥ አቋም ይኑርህ!። ምክንያቱም ወገንተኛ የምትሆንለት አካል ከአላህና ከመልእክተኛው ﷺ በላይ የለምና ለአላህ እና ለመልእክተኛው ﷺ እና ለሐቅ ብቻ ወገንተኛ ሁን!!። ሐቅ ከየትም ይምጣ ከማንም ሐቅ እስከሆነ መቀበል ነው። ሀቁ ካልተገለጠልህ ደግሞ እስኪገለጥልህ ከቡድንተኝነትና ጭፍን ተከታይነት ገለልተኛ ሆነህ በአደብ ፈልገው፣ በንፁህ ኒያ እስከፈለግከው ኢንሻአላህ ቢዘገይ እንኳ ፍንትው ብሎ ይታይሃል!!። ግን ግን አደራ ምን ጊዜም ለግለሰቦች ከወገንተኝነት፣ ከጭፍን ተከታይነትና ከቡድንተኝነት ራስህን አርቅ!!። ምን ጊዜም ወገንተኝነታችሁ ለሐቅ ከሆነ ሐቅን የሚከተልን ትወዱታላችሁ ታከብሩታላችሁ እንጂ ጭፍን ተከታይ አትሆኑለትም!!። አላህ ሐቁ ለተደበቀበት ግልፅ ያድርግለት!!  የሀቅ ተከታዮችና በሐቅ ላይ ከሚፀኑ ባሮቹም ያድርገን!! ✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

⑥, በመቀጠል 4ኛ ላይ ያስቀመጥከው "በመግለጫው ላይ መግለጫውን የሰጡ ዑለሞች ስም ዝርዝርና ፊርማ ቢኖር ኖሮ ጥሩ ነበር ብዬም አምናለሁ።" እዚህ ላይ እንዳንተ እይታ ልክ ልትሆን ትችላለህ፣ ነገር ግን ስም ዝርዝርና ፊርማቸውን አደባባይ አላዋሉትም ማለት "የለም" ማለትንም አያስይዝም!፣ ባይኖር እንኳ መግለጫው እንከን እንዳለበት ተደርጎ እንዲታይ የሚያደርገው ነገር አይደለም!!። ⑦, የእውነት ለጀመዓው አንድነት የምትጨነቅ ከሆነ በአደባባይ ፅፈህ በመልቀቅ ብዙዎችን የሚረብሽና ጥርጣሬ ውስጥ የሚጥል ከእውነታው የራቀ ፅሁፍ ከማሰራጨት በመግለጫው ያልተስማማህ ሀሳብ ካለ ከመሻይኾች በስልክም በአካልም ብትነጋገር መልካም ነበር። ለዑለማዎችም የእውነት በተግባር ቦታ የምትሰጥ መሆንህን ያጠናክርልህ ነበር። አላህ ሁላችንም ለሐቅ እጅ የምንሰጥ ያድርገን!! በየትኛውም መንገድ ከማስመሰልና በሰለፊዮች መካከል ከፊትና ፈጣሪነት ይጠብቀን!! ✍🏻ወንድማችሁ:- ኢብን ሽፋ #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

ኡስታዝ ባህሩ ተካ በዑለማዎቻችን የአቋም መግለጫ ላይ የሰነዘርከውን ትችት ቆም ብለህ ብትመለከተውና ብትታረም መልካም ነበር!! ————— ፅሁፍህን እንዳነበብኩት መልስ ለመፃፍ ወስኜ በ2 ምክንያቶች ለማዘግየት ሀሳቤን ቀየርኩ፣ 1ኛ, ዑለማዎች ራሳቸው መልስ ይሰጡበታል በሚል ነበር፣ ለምን እንዳዘገዩት ራሳቸው ያውቃሉ… በነሱ በኩል መልስ መስጠቱ አስፈላጊ ሆኖ ላይታያቸውም ይችላል፣ አለያም ጊዜ ጠብቀውለት ሊሆን ይችላል…ወዘተ። 2ኛ, ፅሁፍህ ፍፁም ትክክል አለመሆኑን ተረድተህ ስትረጋጋ በእራስህ ጊዜ መልስ ትሰጣለህ ብዬም ተስፋ አድርጌ ነበር። ይህም አልሆነም። በእራስህ ጊዜ እርማት እስካላደረግክ ግን በአደባባይ የተሳሳተን ሰው በአደባባይ እንዲታረም ምላሽ መስጠትና ብዥታን ከሰለፊይ ወንድምና እህቶች የመግፈፍ ግዴታ አለብን!! ኡስታዝ ባህሩ እኔንም አንተንም አላህ በሐቅ ጎዳና ያፅናንና "በአቋም መግለጫው ላይ የማነሳቸው ነጥቦች" በሚል ርእስ የፃፍከው ፅሁፍ እጅግ ከእውነት የራቀ ለመሆኑ የሚከተሉትን ነጥቦች እንመልከት:- ①, በፅሁፍህ መንደርደሪያ ላይ "ከሀገራችን የሰለፍይ መሻኢኾች ውስጥ የተወሰኑት…" በማለት የሰጡትን መግለጫ የውስን መሻይኾች እንጂ አንድነት የሌለውና መሻይኾችም ላይ የሆነ ልዩነት የተፈጠረ አስመስሎ የማቅረብ ዘይቤ ተጠቅመሃል፣ ይህ ትልቅ ስህተት ነው!! ቢታረም መልካም ነው። ②, አስከትለህም "…በዐረብኛውና በአማርኛው ትርጉም መካከል የተወሰኑ ልዩነቶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ በዐረብኛ የተወሰኑ ዑለሞች የሚለውን በአማርኛ ዑለሞች ተብሎ ተተርጉሟል።" ብለሃል፣ ዐረቢኛው ላይ لعدد من علماء السنة በሚል ነው የተቀመጠው፣ ይህ ደግሞ ትርጉሙ አንተ እንደምትለው "ከፊል ዑለማእ" ወይም በዐረቢኛው بعض العلماء ማለት ሳይሆን!፣ ትክክለኛው ትርጉሙ " ከ3 በላይ የሆኑ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሱንና ዑለማዎች" ማለት ሲሆን ብዙሃነትን ገላጭ ነው። በዚህ ቃል ከመተቸትህ በፊት ዐረቢኛው ሀሳቡ ግልፅ ካልሆነልህ የተለያዩ የዐረቢኛ ማብራሪያዎችን ብትመለከት መልካም ነበር፣ እኔም በዚህ አገላለፄና ትሩጓሜ ከተሳሳትኩ በዘርፉ ላይ ከአንተም ከኔም የተሻለ አቅምም ብቃትም ያላቸው ከኡስታዝ እስከ ታላላቅ መሻይኽ አሉን ያርሙናል ስህተት ከሆነም በበኩሌ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ!!። በመሆኑም በዚህ መሰረት አማርኛው "ከሱንና ዑለማዎች የተሰጠ መግለጫ" ከሚለው ይልቅ ዐረቢኛው ላይ የተቀመጠው ይበልጥ ብዙሃነትን ገላጭ ነው እንጂ ምንም አይነት የትርጉም ልዩነት አልለ ሊያስብል የሚችል አይደለም!!። ቀጥታ ሲተረጎም ስለሚሰፋ የአማርኛውን ቀለል ባለ መልኩ ተመሳሳይ ብዙሃነትን ገላጭ ቃል ተጠቅመዋል እንጂ ምንም የትርጉም ልዩነት የሚፈጥርና የሚያስተች ነገር የለውም!!። ይልቁንም በተቃራኒው ትችቱን ራሱ በስህተት ላይ የተመሰረተ አድርጎታልና ታረም!!። ③, ሌላው ከባዱና ዐይን ያወጣ ውሸት የሚመስል ነገር ደግሞ ቁ,1 ብለህ ያስቀመጥከው ነጥብ ላይ "…ይሁን እንጂ የተገኙት እኔ በማውቀው ከሀገራችን የሱና ዑለሞች ውስጥ ግፋ ቢል 1/3 የሚሆኑት ናቸው። ስብሰባው ተነግሯቸው በዑዝር ምክንያት የቀሩና ያልሰሙም በጣም ብዙ ናቸው።" ማለትህ ነው። እዚህ ላይ አንድ ነገር ግልፅ ብታደርግ መልካም ነበር… እርሱም #ከዚህ_በፊት የዑለማዎችን ጉባዔ የሚሳተፉ የነበሩት #ዑለማዎች (መሻይኾች) አጠቃላይ ብዛታቸው ስንት እንደነበረና በአሁኑ ጉባዔ (ሹራ) ላይ ምን ያህሉ እንደቀሩ ግልፅ አድርገህ ብትኮንን ጥሩ ነበር። የሚያሳፍረው የተገኙት መሻይኾች "…ግፋ ቢል 1/3 የሚሆኑት ናቸው" የሚለው ነው። ይህ ማለትኮ እንደ ፅሁፍህ አቀማመጥ ለምሳሌ 9 መደበኛ ተሰብሳቢ መሻይኾች ካሉ 3ቱ ብቻ ናቸው ተሰባስብው ተወያይተው መግለጫ ያወጡት ማለት ነው። አለያም ደግሞ 3 ወይም 4 የሚሆኑት ናቸው ተሰባስበው 2ቀን ሙሉ ተነጋግረው መግለጫ የሰጡት እያልከን ነው። ይህ ታዲያ ዐይን ያወጣ ግልፅ የሆነ ውሸት አይሆንም ወይ? ዐይን ያወጣ ውሸት የሚመስል ነገር… ያልኩበት ምክንያት ምን ያህል መሻይኾች እንደቀሩና ምን ያህሉ እንደተሳተፉ ልብህ ጠንቅቆ ያውቀዋል!! = ለአንባቢያንና በመሻይኾች መካከል ልዩነት የተፈጠረ መስሏቸው ለተጨነቁ ወንድም እህቶች ግልፅ ለማድረግ ያህል፣ የቀሩ መሻይኾች እራሱም በዑዝር ምክንያት መቅረታቸውን እንደገለፀውም ነው፣ ነገር ግን ዋናው ነጥብ እሱ እንደሚለው "የቀሩት በጣም ብዙ ናቸውን?…" ትክክለኛው ቁጥራቸውስ ምን ያህል ነው? የሚለው ነው፣ #ከዚህ_በፊት_በነበሩ መደበኛ የዑለማእ ጉባዔዎች (ሹራዎች) ይሳተፉ ከነበሩት #መሻይኾች ይህ መግለጫ የወጣበትን ሹራ ያልተሳተፉት 2 (ሁለት) መሻይኾች ብቻ ናቸው። ታዲያ ቅጥፈትና ማምታታት አይሆንም ወይ?!! ባረከላሁ ፊክ፣ ባታውቅ ዑዝር እሰጥህ ነበር ልብህ እያወቀ ነው በዚህ መልኩ የፃፍከው። ④, ሌላው በቁ,2 ላይ እንደ ሀሳብ "… የአቋም መግለጫውን ላልተገኙት ልከው የሚጨመርም የሚቀነስም ካለ ሐሳብ እንዲሰጡበት አድርገው… " ብለህ ያስቀመጥከውም ሊሆን የማይችል ሀሳብ ነው። ምክንያቱም 1, እነዚህ በርካታ የተሰበሰቡ መሻይኾች ለ2 ቀናት ሲወያዩ በመስለሀና መፍሰዳው ሲያወጡ ሲያወርዱ የቆዩበትን ጉዳይ ያልተገኙት መሻይኾች የሆነ የተለየ ሀሳብ ቢሰነዝሩ እንደ አዲስ እንዲከፈት ሌላ ጊዜ የሚፈልግ ተግባር ነው። 2, ይህን መግለጫ ለማውጣት ብዙሃኑ ተገኝተው የወሰኑት ጉዳይ ስለሆነ ቀሪዎቹ የሚስማሙበት እንጂ ለክፍተት የሚዳርግ ጉዳይ ስላልሆነ። 3, በርካታው አባላት ውድ ጊዜያቸውን አቃጥለው ተሰባስበው በ2 ሰው መቅረት ምክንያት ተብሎ የሚደናቀፍ አሰራርም ሆነ የሚሻር ውሳኔ የለም!!። ይህ ያንተ ሰፋ አድርገህ ነባራዊ ሁኔታዎችን ሳታገናዝብ የሰነዘርከው ትክክለኛ ያልሆነ ሀሳብ ነው። ⑤, ዐሊ ሁሴንን በተመለከተ "…ከዛ በኋላም ቢሆን በዋነኝነት ከዛ በፊት ሲዘምተባቸው በነበሩ ሰዎች ላይ ውስጥ ለውስጥ ፊትናውን እስካሁንም እያሰራጨ ለመሆኑ በቂ ማስረጃ ያለ በመሆኑ አሁን የተሰጠው ምስክርነት ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጋጭ ነው እላለሁ።" ብለሃል፣ እዚህ ላይም ከጠቀስከው አይቀር "ይህን ባህሪውን አልተወም" ብለህ ማስረጃ መጥቀስ ነበረብህ፣ ምክንያቱም በአደባባይ ግልፅ የሆነን ተውበት አድርጓል፣ ድምበር ያለፈባቸውንም ሰዎች አንተን ጨምሮ ይቅርታ ጠይቋል፣ መሻይኾች ግልፅ ባደረገው ነገር ነው ብይን የሚሰጡት እንጂ በልቡ ውስጥ ስላለው አይመለከታቸውም!፣ የውስጡን ወደ አላህ አስጠግተው ባደረጉት ክትትል ልክ ብይን ሰጥተዋል። አንተ ደግሞ ተውበት ካደረገ በኋላ ከማስተካከል ይልቅ ወደነበረበት ተግባር እየተመለሰ ነው ካልክ ሌላ ጊዜ እንደምታደርገው መሻይኾች ከመሰባሰባቸው በፊት ማስረጃህን መላክ ነበረብህ፣ አሁንም ግልፅ ማስረጃ ካለህ ለመሻይኾች ላከው፣ እራሱ ማብራሪያ ይሰጥበታል፣ መሻይኾችም ለማየት የሚከብዳቸው ነገር የለም። አለያ ግን በአደባባይ ከስህተታቸው ተውበት አድርገው የተመለሱ ሰዎችን የምንፈልገውን እያቀረብን፣ የማንፈልገውን ምክንያት እየደረደርን ከጀመዐህ ለማራቅ ጥረት የምናደርግ ከሆነ፣ የእኛም ልብ በአላህ እጅ ነው ያለውና ነገ ሰዎች የወደቁበት ስህተት ላይ ላለመውደቃችን ማናችንም ዋስትና የለንም!!፣ ሌላው:- ትላንትም እውነት በጥፋታቸው ልክ ለአላህ ብለን ነበር ወይ የጠላናቸውና ያራቅናቸው?! የሚለውም ጥርጣሬ ውስጥ ይከተናልና ቆም ማለት ተገቢ ነው።

+1
↪️◉አዲስ የሚንሐጅ ደርስ 📝የጂናየቱ አት'ተመዩዕ ኪታብ ማብራሪያ      ╭─••°─═•°•═─•••─╮      📖➽➤ደርስ ክፍል  01📖      ╰─••°─═•°•═─•••─➥ 📝የኪታቡን PDF ለማግኘት ➴➷ https://t.me/ibnbaz1212/13 🏢በወራቤ ከተማ ዘሞ ባቴ ሐጢባ 02 መድረሳ ለይ የሚሰጥ ትምህርት 🎙በኡስታዝ አቡ ኑህ የቴሌግራም ቻነል ➘➷➴➘➷ https://t.me/ibnbaz1212 ➥➥➥➥➥➥➥➥➥➥➥ https://t.me/MisbahMohammed_6682

​ 🔖አስደሳች ሰበር ዜና ━━━━━━━ ━━━━━━━ ​📢 ለአል-ወሰጢያ መድረሳ እና መርከዝ አካባቢ ነዋሪዎችና ደርስ ተከታታዮች በሙሉ! ~ ​ዛሬ እሮብ ነሓሴ 13/2018 ከወትሮው ለየት ያለ ታላቅ
​            🔖አስደሳች ሰበር ዜና           ━━━━━━━  ━━━━━━━ ​📢 ለአል-ወሰጢያ መድረሳ እና መርከዝ አካባቢ ነዋሪዎችና ደርስ ተከታታዮች በሙሉ!   ~ ​ዛሬ እሮብ ነሓሴ 13/2018 ከወትሮው ለየት ያለ ታላቅ ወቅታዊ የደዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። ​🎙 ተጋባዥ እንግዳችን፦ └─ ኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን(ሀፊዘሁላህ) ​📌 የደዕዋው ርዕስ፦ └─
«መውሊድ የሽርክ እና የብደዐህ ምንጭ ነው፣ ግልፅ የሆነው ከእስልምና መንገድ የሚያስወጣው ክህደት የሚባልበት ቦታ መሆኑም ግልፅ ማድረግ!
!! ​⏰ ሰዓት፦ [ ከመغሪብ  እስከ ኢሻ ] 📍 ቦታ፦ [ አለም ባንክ - ስልጤ ሰፈር በአል-ወሰጢያ መድረሳ ] 📲 ለሌሎችም ሼር (Share) በማድረግ የኸይር ሥራው ተካፋይ ይሁኑ! https://t.me/AbraribnAwal https://t.me/AbraribnAwal

​ 🔖አስደሳች ሰበር ዜና ━━━━━━━ ━━━━━━━ ​📢 ለአል-ወሰጢያ መድረሳ እና መርከዝ አካባቢ ነዋሪዎችና ደርስ ተከታታዮች በሙሉ! ~ ​ዛሬ እሮብ ነሓሴ 13/2018 ከወትሮው ለየት ያለ ታላቅ
​ 🔖አስደሳች ሰበር ዜና ━━━━━━━ ━━━━━━━ ​📢 ለአል-ወሰጢያ መድረሳ እና መርከዝ አካባቢ ነዋሪዎችና ደርስ ተከታታዮች በሙሉ! ~ ​ዛሬ እሮብ ነሓሴ 13/2018 ከወትሮው ለየት ያለ ታላቅ ወቅታዊ የደዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። ​🎙 ተጋባዥ እንግዳችን፦ └─ ኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘሁላህ) ​📌 የደዕዋው ርዕስ፦ └─ «መውሊድ ቢደዕ ነው» ​⏰ ሰዓት፦ [ ከመغሪብ እስከ ኢሻ ] 📍 ቦታ፦ [ አለም ባንክ - ስልጤ ሰፈር በአል-ወሰጢያ መድረሳ ] 📲 ለሌሎችም ሼር (Share) በማድረግ የኸይር ሥራው ተካፋይ ይሁኑ! https://t.me/AbraribnAwal https://t.me/AbraribnAwal

"እንቁላል ከውጪ ከተሰበረ ህይወቱ ያባቃል፣ ከውስጥ ከተሰበረ ህይወት ይዘራል" ይባላል። ለምንወስዳቸው የትኛውም አቋም ቀድመን በጥንቃቄ ተገቢ ማስረጃ ካልያዝን ነገራቶች ከቁጥጥር ውጪ ሆነው ከአስተካካዬች ሳይሆን ካበላሾች፣የሸርን በር ለመዝጋት ብሎም የኸይርን በር ለመክፈት ሰበብ ከመሆን ይልቅ በተቃራኒው የሸርን በር ለመክፈት የኸይርን በር ለመዝጋት ሰበብ እንሆናለን። አላህ በእኛም በእኛ ሰበብ ትክክለኛውን መንገድ በሚለቁ ሰዎች እንደሚተሳሰበን ልንዘነጋ አይገባንም።ስለዚህም ተገቢ አቋም ለመያዝ ገንዘብ፣ ቡድንተኝነት፣ ውሸት፣ ህብሪተኝነት፣ ኩራተኝነት፣ ትህቢተኝነት የመሳሰሉ ነገራቶች ሳይሆን የሚያስፈልጉት ይልቁንም በቂ ማስረጃና ፍትሃዊነትን መታጠቅ ነው።ማስረጃ አልባ እና ኢ—ፍትሃዊ አካሄድ ሃቅን ባጢል፣ ባጢልን ሃቅ የማድረግ ሃቅምም የላቸውም ለግዜው እንጂ ይከስማሉ የደፈረሰው ውሃ ሳይጠራ አይቀርምና። ያለማስረጃ በፕሮፖጋንዳ፣ በሴራ ፣ በጩኸት ጋጋታ የሚያዝ አቋም እንቁላሉን ከውጪ እንደመስበር ግዚያዊ እንጂ ዘለቄታዊ ቁመና አይኖረውምና።ነገራቶችን ከወገንተኝነት ነፃ በሆነ ስብህና፣ የአላህን ተቆጣጣሪነት በማሰብ ለዘለቄታዊው ስኬት በተረጋጋ እና ነገራቶችን በማስተዋል በእሾክ በበዛበት መሬት ላይ በባዶ እግሩ እንደሚራመድ ሰው በጥንቃቄ ነገራቶችን ማስኬድ ይገባናል።ግዜው የፈተና ግዜ መሆኑን ልንዘነጋ አይገባንም። بارك الله فيك ✍አቡ ሙዓዝ

ልባችሁን አስተካክሏት… !! ——— አንገብጋቢና ወሳኝ ምክር ‏قال الشيخ العلامة المحدث ربيع بن هادي المدخلي رحمه الله أصلحوا قلوبكم تسلم ألسنتكم، وت
ልባችሁን አስተካክሏት… !! ——— አንገብጋቢና ወሳኝ ምክር ‏قال الشيخ العلامة المحدث ربيع بن هادي المدخلي رحمه الله أصلحوا قلوبكم تسلم ألسنتكم، وتسلم جوارحكم. لابد من العناية بإصلاح القلوب بالتزام الصدق والإخلاص والتوبة والإنابة ومراقبة الله عز وجل، والحذر من الرياء، والحذر من الحسد، والحذر من الحقد، والحذر مما يفسد القلب. مفاسد الكذب – ص 36 ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ረቢዕ አል-መድኸሊይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “ልባችሁን አስተካክሏት ምላሳችሁ ሠላም ትሆናለች፣ ሰውነታችሁም ሠላም ይሆናል። ልብን ወደ አላህ በመመለስ፣ በኢኽላስ፣ እውነተኝነትን በመያዝ፣ ወደ አላህ በመመለስና በምሰራው ስራ የላቀው አላህ ያይኛል ይሰማኛል ብሎ በማሰብ ማስተካከል ላይ ትኩረት ማድረግ ቅሮት የሌለው ጉዳይ ነው!!። ከይዩልኝ ይስሙልኝ እና ከመመቀኛኘትም ተጠንቀቁ!!፣ ከርስበርስ ጥላቻና ልብን ከሚያበላሽ ነገር ሁሉ ተጠንቀቁ!!።” [መፋሲዱ'ል ከዚብ 36] = አጭር ሆና ግን ደግሞ እጅግ በጣም ወሳኝና የነገሮችን ሁሉ ቁንጮ የያዘች ምክር ናት! እንመከርባት!! ✍🏻ኢብን ሽፋ #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

🔷ሱና ከሁሉም ነገር ይቀደማል ኢማም ኢብን ከሲር - አላህ ይዘንላቸው - እንዲህ አሉ :- "ሱና ከእያንዳንዱ ተናጋሪ ቃል ተቀዳሚ ነው ፤ እንዲሁም በእያንዳንዱ አሊምና ጃሂል  ላይ ማስረጃ ነው።" الأحكام الكبير (٥٥/١) https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

قال الإمام ابن كثير -رحمه الله-: ً" السُّنّة؛ مُقدّمة على قَوْل كُلِّ قائل، وحُجّة على كُلِّ عالم، وجاهل ". 📚الأحكام الكبير (٥٥/١)

🛑የሀገራችን የሰለፊያ ዓሊሞች አላህ ይጠብቃችሁ !!! ➥ለሰለፊዮች አንድነት ዘወትር የሚጨነቁ ➤በተለያዩ ፕሮግራሞች ሁሉ በሱና ለይ ወንድማማችነት እንድንጠብቅ አጠንክረው የሚመክሩ ➽ከቢደዐህ ሰዎች
🛑የሀገራችን የሰለፊያ ዓሊሞች አላህ ይጠብቃችሁ !!! ➥ለሰለፊዮች አንድነት ዘወትር የሚጨነቁ ➤በተለያዩ ፕሮግራሞች ሁሉ በሱና ለይ ወንድማማችነት እንድንጠብቅ አጠንክረው የሚመክሩ ➽ከቢደዐህ ሰዎች በመለየት እራስን ችሎ ሰለፊያን መርዳት እንዳለብን አበክረው የሚመክሩ ◉በሰለፊዮች መካከል በደል እነ ፍትህ መጓደል እንዳይኖር ሁሉ የሚሰሩ ብርቅዬ ዑለሞች አሉን አልሃምዱሊላህ ። ሰሞኑንም ተሰብስበው ከመከሩ በኋላ ያወጡት መግለጫ ይህንኑን የሚያጠናክር ነው ። ◉አሁንም በድጋሚ ታላላቅ ዑለሞች አሉን አላህ ይጠብቃቸው!!! 📝ተጨማሪ  ትምህርቶችን   ለማግኘት የቴሌግራም➷➴ Channeሉን  ይቀላቀሉ !!! https://t.me/MisbahMohammed_6682

አሳ ያለ ውሃ መኖር እንደማይችለው ሁሉ ሴት ልጅ ያለ……………መኖር አትችልም 🌺ትክክለኛውን መልስ በመንካት የሚመጣላቹን ቻናል ተጋበዙ🌺
አሳ ያለ ውሃ መኖር እንደማይችለው ሁሉ ሴት ልጅ ያለ……………መኖር አትችልም 🌺ትክክለኛውን መልስ በመንካት የሚመጣላቹን ቻናል ተጋበዙ🌺

ያሳላም ምንኛ ወርቃማ የሆ ንግግር ነው ሸኽ ረቢዕ ቢንሀዲ አልመድኸሊ ረሂመሁሏህ በጣም በዚህ ዘመን የተፈተንበት ከቁርአን ከሀድስ ይልቅ የሰዎች ክብር የሚያስጨንቀን አቡ በክር ተሳሳተ ኢማሙሻፊዕይ ተሳሳቱ ሲባል እየሳቅን ፈገግ እያልን ፀጥ ብለን እንሰማል እገሌ ሸኽ ተሳሳተ ሲባል ኡኡኡ አገር ይያዝልን እንላል ያአሏህ እስኪ ይሄን ያማረ ንግግር ተጋበዙልኝ ከዚህ በሽታም አሏህ ይጠብቀን አሏህ ከ ሀቅ ጋር የምንጓዝ ያድርገን https://t.me/Menhajeaselefya https://t.me/Menhajeaselefya

🔷በምትሰሙት ፣ በምታነቡት ነገር ጥንቃቄ አድርጉ ሸይኽ ሙቅቢል አልዋዲዒ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ አሉ :- "ወጣቶች ሆይ! በምትሰሙት ፣ በምታነቡት ነገር ጥንቃቄ እንድታደርጉ እመክራለሁ። አደራ የእውቀትና የልምድ ባለቤት ፣ ለነገሮች ትእግስትና አስተውሎት ባላቸው ታላላቅ ኡለሞችና  ሸይኾች ዙሪያ ሁኑ።" "قرة عيون السلفية بالأجوبة الجامعية (٢٦٢) https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة