cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Arada FM 95.1

This is AradaFm 95.1 Official Telegram Channel መልዕክት መቀበያ @AradaFmbot

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 264
Suscriptores
+724 horas
+677 días
+34730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
ሃንሲ ፍሊክ ባርሴሎናን ለማሰልጠን ተስማሙ ግንቦት 16፣ 2016 (አራዳ ኤፍ ኤም) አሰልጣኝ ሃንሲ ፍሊክ የባርሴሎና አሰልጣኝ ለመሆን መስማማታቸው ተገለፀ፡፡ አሰልጣኙ ዣቢን በመተካት ክለቡን ለማሰልጠን ተስማምተዋል ተብሏል፡፡ በካታላኑ ክለብ ለሁለት አመታት ለመቆየት የተስማሙ ሲሆን፥ ሁለት ረዳት አሰልጣኞችን ከጀርመን ያመጣሉ፡፡ አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት!  💬 8545 Telegram:https://t.me/Arada_Fm  Website:https://aradafm.com/  Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/  Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1  Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1  @Arada_Fm
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት! 💬 8545 Telegram:https://t.me/Arada_Fm Website:https://aradafm.com/ Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1 @Arada_Fm
Mostrar todo...
👍 1
የሱዳንን ግጭት ተከትሎ 128 ሺህ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገለጸ ግንቦት 16፣ 2016 (አራዳ ኤፍ ኤም) በሱዳን የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ የ17 ሃገራት ዜግነት ያላቸው 128 ሺህ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገለጸ። በሱዳን የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱ ሱዳናውያን እና የሌሎች ሃገራት ዜጎችን አያያዝ እንዲከታተል የተቋቋመው ብሄራዊ ግብረ-ኃይል የአፈጻጸም ግምገማ አካሄዷል። ስደተኞችን በተገቢው ሁኔታ ለማስተናገድ፣ እንዲሁም በሱዳን ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን ከግጭት ቀጠናው ለማስወጣት የተቋቋመው እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የሚመራው ብሄራዊ ግብረ-ኃይል ባካሄደው ስብሰባ እስከ አሁን ድረስ የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርጓል። በስብሰባው በቀረበው ሪፖርት 128 ሺህ የሚሆኑ ስደተኞች በመተማ እና ኩምሩክ ባሉ የድንበር ኬላዎች በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገልጿል። ከእነዚህ ውስጥ ከ47 ሺህ በላይ የሚሆኑት ተመላሽ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ከድንበር ጀምሮ አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነም ተብራርቷል። ወደ ስደተኛ መጠለያ ጣቢያ እና ማዕከላት ከገቡት በተጨማሪ ሌሎች በአዲስ አበባ እና በሌሎች ትላልቅ ከተሞች ከ15 ሺህ የሚበልጡ ሱዳናውያን ቪዛ በነፃ እየታደሰላቸው እየኖሩ መሆኑ፥ ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታ አልፈው ከለላዋን ለጠየቁ ስደተኞች ያላትን ጠንካራ አጋርነት የሚያሳይ መሆኑ ተመላክቷል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ከፍተኛ ጥረት ተረድተው ተገቢውን እገዛ ሊያደርጉ እንደሚገባ የግብረ-ኃይሉ አባላት ማሳሰባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት!   💬 8545  Telegram:https://t.me/Arada_Fm   Website:https://aradafm.com/   Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/   Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1   Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1   @Arada_Fm
Mostrar todo...
Arada FM 95.1

This is AradaFm 95.1 Official Telegram Channel መልዕክት መቀበያ @AradaFmbot

Photo unavailableShow in Telegram
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ግሪክና ፖላንድ አውሮፓውያን አህጉር አቀፍ የጋራ የአየር መቃወሚያ እንዲያቋቁሙ ጥያቄ አቀረቡ የግሪክና የፖላንድ መሪዎች አንድ ላይ በጻፉት ደብዳቤ በአውሮፓ የጋራ የአየር መቃወሚያ እንዲቋቋም የሚጠይቅ ደብዳቤ ለአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን አስገብተዋል፡፡ መሪዎቹ እንዲቋቋም የጠየቁት የጋራ ኃይል የፋይናንስ ምንጭ ሁሉም ኣባል አገራት ሆነው አሁጉረ አውሮፓን ከተለያዩ የአየር ላይ ጥቃቶች እንዲጠብቅ ነው ብለዋል፡፡ መሪዎቹ በጻፉት ደብዳቤ የሕብረቱ ምክር ቤት የፊታችን ሰኔ ወር መጨረሻ ላይ በሚያካሄደው ጉባዬ ጉዳዩ ቀርቦ ውይይት እንዲደረግበት መጠየቃቸውን ግሪክ ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ ለ2ኛ ጊዜ እንደሚወዳደሩ የሚጠበቁት የአወሮፓ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በጉዳዩ ላይ ስለመስማማታቸው ፍንጭ የሚሰጥ መልዕክት በኤክስ ገፃቸው ላይ ጽፈዋል ተብሏል፡፡ ለዩክሬን የሚደረገው ድጋፍ መቀጠል እንዳለበት በገለፁበት መልዕክት የመከላከል አቅማችንን ማጠናከር አለብን ብለዋል፡፡ የግሪክና የፖላንድ መሪዎች ዕቅድንም በምሳሌነት አያይዘው ጠቅሰውታል፡፡
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የሳይንስ ፈጠራ አውደ ርዕይና ውድድር ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚጫወተው ሚና የጎላ ነው ተባለ በአዲስ አበባ ከተማአቀፍ የሳይንስ ፈጠራ አውደርዕይና ውድድር ዛሬ በወደጅነት ፓርክ የተጀመረ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ላይም የሳይንስ ፈጠራ አውደርዕይና ውድድሮች ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ወደ ተግባር እንዲለውጡ ሚናው ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል ። የሳይንስ ፈጠራ አውደርእይና ውድድሩ ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት የሚካሄድ መሆኑ ተመላክቷል። በዚህ መርሃ ግብርም ተማሪዎች የሰሯቸው ልዩ ልዩ የፈጠራ ስራዎች ለእይታ የቀረቡ ሲሆን በየደረጃው በተለያዩ ውድድሮች ያለፉና ክፍለ ከተሞቻቸውን ወክለው የመጡ ተማሪዎች የአሸናፊዎች አሸናፊን ለመለየት ይወዳደራሉ ተብሏል ። ከዚህ በተጨማሪም የዚሁ መርሃ ግብር አካል የሆነ ብሄራዊ የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስም በነገው እለት እንደሚካሄድ ተጠቁሟል። በታሪኩ ጋሹ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ከሳምንት በፊት 24 አምባሳደሮች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ብቻ መሾማቸው በታሪክ የመጀመሪያው ነው ተባለ ግንቦት ሰባት በምሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተሾሙት አምባሳደሮች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ብቻ የተወጣጡ ናቸው ሲሉ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ ተናገሩ፡፡ አምባሳደሩ ይህን ያሉት ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ ላይ ነው፡፡ ቃል አቀባዩ ከዚህ በፊት የሚሰጡ ሹመቶች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውጭ በተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት የሚያገለግሉ ሰዎች የሚሾሙበት ነበር ማለታቸውን አራዳ ሰምቷል፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት 10 በባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነትና 14 ደግሞ በአምባሳደርነት ማእረግ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሹመት መስጠታቸው ይታወሳል፡፡ እነዚህ 24 አምባሳደሮች ግን መሉ በመሉ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ ዘርፎች ሲያገለግሉ የነበሩ መሆናቸው በታሪክ የመጀመሪያው ያደርገዋል ያሉት ቃል አቀባዩ ናቸው፡፡ የተሰጠው ሹመትም፣ በዲፕሎማሲ ብቃት፣በስራ ልምድና በትምህርት ዝግጅታቸው ለቦታው ይመጥናሉ ተብለው መመረጣቸውን አራዳ ከሚኒስቴሩ ያገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡ ቃል አቀባዩ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በተቋሙ የቅርብ ታሪክ እንደዚህ አይነት ሹመት ሲሰጥ ይህ የመጀመሪያው እደሆነ ተናግረዋል፡፡ ዮሐንስ አበበ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የብሪክስ አባል አገራት በመሬት ምልከታ ሳተላይት የጋራ አጠቃቀምና መረጃ መለዋወጥ ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል የብሪክስ አባል አገራት ብሔራዊ የስፔስ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ስብሰባ በሞስኮ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ አገራቱ በድምሩ 1 ሺ 200 የመሬት ምልከታ ሳተላይት እንዳላቸው የተነገረ ሲሆን በትብብር ሊሠሩ እንደሚገባ ተመክሮበታል፡፡ የብሪክስ ምስረታ መርህ አገራቱ በመስኩ ያላቸውን አቅም ለጋራ ጥቅማቸው እንዲያውሉ የሚያስችላቸው መሆኑን አራዳ ከኢኖቫሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ በኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻያል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማም በስብሰባው እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ እንጦጦ የሚገኘው የብዝሐ- ሳተላይት መረጃ መቀበያ ጣቢያ እና በቀጣይ ለማምጠቅ የታቀደው የመሬት ምልከታ ሳተላይት የብሪክስ ህብረ - ሳተላይት አካል ለማድረግያግዛል ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡ በየነ ወልዴ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ማድሪድ የፍጻሜውን ጨዋታ በበርናባው በስክሪን ለሚከታተሉ ደጋፊዎች ትኬት መሸጥ ሊጀምር ነው ግንቦት 16፣ 2016 (አራዳ ኤፍ ኤም) በሚቀጥለው ሳምንት በዌምብሌይ ስታዲየም የሚደረገውን የፍፃሜ ጨዋታ በሳንቲያጎ በርናባው ጨዋታውን በስክሪን ለሚከታተሉ የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች የመግቢያ ቲኬት ሽያጭ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ እንደሚከናወን ተረጋግጧል። ሪያል ማድሪድ በይፋዊ ገጹ እንዳስታወቀው የክለቡ አባላት እና ለክለቡ ቀረቤታ ያላቸው ሰዎች ጨዋታውን በነፃ የሚከታተሉ ሲሆን የማድሪድ ፕሪሚየም ወይም ቪ አይ ፒ ተመልካቾች ደግሞ 10 ዩሮ ይከፍላሉ ተብሏል። በተጨማሪም ማንኛውም ተመልካች 15 ዩሮ በመክፈል ጨዋታውን በሳንቲያጎ በርናባው ይመለከታሉ። አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት! 💬 8545 Telegram:https://t.me/Arada_Fm Website:https://aradafm.com/ Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1 @Arada_Fm
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የኢራን ጦር ፕሬዚዳንቱ የሞቱበትን የሄሊኮፕተር አደጋ የተመለከተ ግኝቱን ይፋ አደረገ ግንቦት 16፣ 2016 (አራዳ ኤፍ ኤም) የኢራን ጦር የሃገሪቱን ፕሬዚዳንት ለህልፈት የዳረገውን የሄሊኮፕተር አደጋ የተመለከተ የመጀመሪያውን የምርመራ ግኝት ይፋ አድርጓል። ከጦሩ የተውጣጣው የመርማሪዎች የባለሙያዎች ኮሚቴ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ በሄሊኮፕተሯ አካል ላይ ምንም አይነት የጥይት ወይም ሌላ ተመሳሳይ ምልክት አለማግኘቱን አስታውቋል። ተጨማሪ ለማንበብ https://www.facebook.com/aradafm95.1/posts/pfbid02mScNRtUZtQVL28ABgnAYYbXFswnfKzLBfaxSxSKkLKzcWBVHwhRsjEKprNwNERt8l አራዳ ኤፍኤም 95.1 ፤ ውለው የሚያመሹበት! 💬 8545 Telegram:https://t.me/Arada_Fm Website:https://aradafm.com/ Facebook: https://www.facebook.com/aradafm95.1/ Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1 @Arada_Fm
Mostrar todo...