cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Ethio Fm 107.8

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
19 415
Suscriptores
+724 horas
+187 días
+21930 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የነገ የግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ሁሉም የመዝናኛ ቦታዎች ከምሽት አራት ሰአት በኃላ አገልግሎት እንዳይሰጡ ተደረገ፡፡ የወልቂጤ እና አካባቢዋ ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት ከግንቦት 22/2016 ጀምሮ በተለዋጭ መግለጫ እስከሚሻር ድረስ የሰዓት ገደብ እና ክልከላ ማድረጉ ተሰምቷል፡፡ የሰአት ገደብ ከተጣለባቸው ጉዳች መካከል የባጃጅ ተሽከርካሪ ከምሽቱ 3:00 እስከ ንጋት 11:00 ሰአት ድረስ በከተማዋ ማንቀሳቀስ እንደማይችሉ እገዳ ተጥሎባቸዋል፡፡ እነደዚሁም ሁሉም መዝናኛ ቤቶች ማለትም ጭፈራ ቤቶች ፣ ክለቦች ግሮሰሪዎች ፣ፑልና መሰል መሰብሰቢያ ቦታዎች ከምሽቱ 4:00 በኋላ አገልግሎት መስጠት እና ያለ በቂ ምክንያት መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል፡፡ በከተማው እና በአካባቢው በየትኛውም ሰዓት በደስታም ሆነ በሃዘን፤ መሳሪያ ፣ርችት መተኮስ እና ማንኛውም አካባቢን የሚያውክ ያልተለመደ ድምጽ ማሰማት በጥብቅ እንደተከለከለ ነው ያስታወቀቀው፡፡ ከጸጥታ አስከባሪዎች እና በጸጥታ አካላት እውቅና ከሚንቀሳቀስ የጤና አንፑላንስ ውጪ የተዘረዘሩ ክልከላዎች የተላለፈ ማንኛውም ሰው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ ገልጻል። ስለሆነም የከተማው እና የአካባቢው ነዋሪ የየአካባቢያቸው ሰላም ከመጠበቅ በተጨማሪ በጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ የተጣሉ ክልከላዎች እንዲያከብር ጥሪ አቅርቧል። በሔኖክ ወ/ገብርኤል ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም
Mostrar todo...
👍 16
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በእስር ላይ ያሉ ሰባት የኦነግ አመራሮችን ሁኔታ በተመለከተ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማጣራት አድርጎ ከሆነ እንዲያሳውቀው በደብዳቤ ጠየቀ። ምርጫ ቦርድ በእስር ላይ ያሉ ሰባት የፓርቲው አመራሮች ሕይወት የሚያሰጋ መሆኑን ከኦነግ አቤቱታ እንደደረሰው በመጥቀስ ነው ደብዳቤውን ግንቦት 19/ 2016 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ተቋም ኮሚቴ የጻፈው። ኦነግ ሚያዝያ 6/ 2016 ዓ.ም ለምርጫ ቦርድ በጻፈው ደብዳቤ “አመራሮቹ በፍርድ ቤት ነጻ የተለቀቁ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ከእስር ያልተፈቱ መሆኑን፤ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከአገሪቱ ሕጎች በተጻረረ መልኩ በቁጥጥር ስር” ያቆያቸው መሆኑን በመጥቀስ ቦርዱ የአመራሮቹን እስር ሁኔታ መፍትሄ እንዲሰጣቸው መጠየቁን ደብዳቤው አመላክቷል። ሰባቱ የታሰሩ የኦነግ አመራሮች አቶ አብዲ ረጋሳ፣ አቶ ሚካኤል ቦራን፣ አቶ ኬነሳ አያና፣ አቶ ለሚ ቤኛ፣ ዶ/ር ገዳ ገቢሳ፣ አቶ ዳዊት አብደታ እና አቶ ግርማ ጥሩነህ እንደሆኑም በምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ ጌጤ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ አመላክቷል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ለሚ ገመቹ ፓርቲያቸው የጻፈውን ደብዳቤ በተመለከተ ሲናገሩ፣ የኦነግ አመራሮች በአሁኑ ወቅት ያሉበት ሁኔታ በጣም አሳሳቢ እንደሆነ በተደጋጋሚ ለተለያዩ አካላት ሲገልፁ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል። ከዚህ ቀደምም ለአፍሪካ ኅብረት፣ ለአውሮፓ ኅብረት፣ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና ለምርጫ ቦርድ የፓርቲው አመራሮች “በእንግልት ለተለያዩ በሽታዎች ተጋልጠው በቡራዩ ከተማ በእስር ላይ ይገኛሉ በማለት ድርጅቱ ይመለከታቸዋል ላለው አካል ሁሉ ቅሬታውን እያቀረበ ነው” ብለዋል። አቶ ለሚ በእስር ላይ የሚገኙት የድርጅቱ አመራሮች “በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት። በተለይ ደግሞ አቶ ኬኔሳ እና አቶ ገዳ ገቢሳ የጤንነት ሁኔታቸው በጣም የሚያሳስብ ነው፤ ክፉኛ ተጎድተዋል” ብለዋል። ከፍርድ ቤት ውሳኔ ውጪ ለሦስት ዓመት ታስረው የሚገኙ የኦሮሞ ተቃዋሚ አመራሮች እንዲፈቱ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪው ሂውማን ራይትስ ዋች ሐምሌ 17/ 2016 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት ጠይቆ ነበር። ተቋሙ ሰባቱ የኦሮሞ ተቃዋሚ አመራሮች በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ለዘፈቀደ እስር የተዳረጉት በፖለቲካ ሚናቸው ነው ብሏል። ሌላኛው ከእነዚህ አመራሮች ጋር ታስረው የነበሩት የፓርቲው የፖለቲካ ኦፊሰር በቴ ኡርጌሳ ከጤና ጋር በተያያዘ ከእስር ቢለቀቁም ሚያዝያ 3/2016 ዓ.ም. በመቂ ከተማ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው መገኘታቸው ይታወሳል። ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም
Mostrar todo...
👍 5👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮ የምግብ እና መጠጥ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሊዘጋጅ ነው ። የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ማዕከል ከአሜዚንግ ኘሮሞሽንና ኢቨንት  እና ከዳብ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር ከሰኔ 5 -9 የሚቆይ ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ለማካሄድ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል ። ኢትዮ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል የውጪ ሀገራት ዲፕሎማቶችን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሀገራችን በምግብና መጠጥ ረገድ ያላትን የቱሪዝም አቅም በቅርበት እንዲያውቁት የሚያደርግ ፌስቲቫል እንደሆነ ተገግሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ፌስቲቫሉ የገበያ ትስስር ለመፍጠርና ቱሪዝምን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ሰምተናል፡፡ በፌስቲቫሉ ላይ የተለያዩ የሀገራችን ክልሎች ምግቦች እና መጠጦች ለታዳሚው እንደሚቀርቡ እና ልዩ ልዩ የውይይት መድረኮች፣ የእርስ በርስ ግንኙነት መፍጠሪያ ፕሮግራሞች እና አዝናኝ ዝግጅቶች የፌስቲቫሉ ዋና ዋና መርኃግብሮች ናቸው ተብሏል ። የፊስቲቫሉ መግቢያ በነፃ መሆኑን እና ሁሉም ህብረተሰብ መካፈል እንደሚችሉ ተነግሯል ። የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ማዕከል በኢንዱስትሪ ልማቱ ላይ ድርሻ ካላቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት በምርምርና ስርአት ፣በቴክኒክ ምክር እና ድጋፍ ፣በመረጃ ፣በገበያ በስልጠና ኢንዱሰትሪዎችን በማገዝ የበኩልን አስተዋዕኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ ማዕከል ነው። የኢትዮ ምግብ መጠጥ ፌስቲቫል ተባባሪ አካላት የሆኑት አሚዚንግ ኘሮሞሽንና ኢቨንት እንዲሁም ዳብ ትሬዲንግ በሁነት ዝግጅት ፣በቴሌቪዥን ፣በሬዲዮና ህትመት ማስታወቂያ ኘሮሞሽኖች ሰፊ ልምድ ያላቸው ሲሆን ለአመታት ያዳበሩትን ልምድ በመጠቀም ፌስቲቫሉን በተሳካ መልኩ ለማካሄድ ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ  ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል ። በሐመረ ፍሬው ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም
Mostrar todo...
👍 2

የዛሬ የግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን
Mostrar todo...
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሴራሊዮን በረራ ጀመረ፡፡ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ሴራሊዮን 64ኛው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻ ሆነች። በዛሬው እለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፍሪታዎን ሴራሊዮን ለመብረር የሚስችላት ስምምነት በማድረግ በረራውን ጀምሯል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ከጊዜ ወደጊዜ መዳረሻዎችን በመስፋት ላይ ሲሆን በዛሬው እለት ፍሪታዎን ሴራሊዮን 64ኛው የመዳረሻ ሆና ሰፍራለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃና በአፍሪካ አህጉር በረራዋን ማስፋቷ በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣በኢኮኖሚ እንድንቀራረብና እንድንተሳሰር በማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በዚህም አየር መንገዱ በዛሬው እለት አንድ ብሎ ወደ ሴራሊዮን ፍሪታዎን በረራውን የጀመረ ሲሆን በረራው በሳምንት ሶስት ጊዜ ይሆናልም ተብሏል። ኢትዮጵያ የበረራ አድማሷን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማስፋት ላይ እንደምትገኝና በቀጣይም ወደ ሌሎች የአፍሪካና አለም አቀፍ ሃገራት መዳረሻዋን ለማስፋፋት እቅድ እንዳላትም ተገልጿል። በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአለምአቀፍ ደረጃ ከ136 ሀገራት በላይ መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን በአፍሪካ ደግሞ 64 መዳረሻዎች አሉት። በልዑል ወልዴ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም
Mostrar todo...
👍 8
Photo unavailableShow in Telegram
ትራምፕ በተከሰሱባቸው 34 ክሶች ጥፋተኛ ተባሉ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታሪካዊ በሆነ የክስ ሂደት በጠቅላላ ጥፋተኛ ተብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ከንግድ መዝገቦች ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በቀረቡባቸው 34 ክሶች በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል። በአሜሪካ ታሪክ በሥልጣን ላይ ያለም ይሁን ከሥልጣን የወረደ ፕሬዝዳንት በወንጀል ክስ ጥፋተኛ ሲባል ትራምፕ የመጀመሪያው ናቸው። የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው ትራምፕ ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም. የቅጣት ፍርድ ይተላለፍባቸዋል ተብሏል። ፍርድ ቤቱ ስድስት ሳምንታት በዘለቀው ችሎት ላይ ከ22 ሰዎች ምስክርነትን ሰምቷል። ከእነዚህ መካከል የቀድሞ የልቅ ወሲብ ተዋናይት ስቶርሚ ዳንኤልስ ትገኝበታለች ሲል ሮይተርስ ዘግቧል። ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም
Mostrar todo...
👍 8