es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

BUREAU OF FINANCE - ADDIS ABABA CITY ADMINISTRATION - Page

BUREAU OF FINANCE - ADDIS ABABA CITY ADMINISTRATION - Page

Ir al canal en Telegram

AACABOF PUBLIC PAGE

Mostrar más
3 464
Suscriptores
+1524 horas
+1657 días
+26530 días
Archivo de publicaciones
‎“ለዕድገት መምራት” በሚል መሪ ቃል ዛሬ መካሔድ በጀመረው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ በመገኘት ንግግር አድርጌያለሁ። የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ይህንን ታላቅ አህጉራዊ መድረክ ማስተናገዷ ለሁላችንም ታላቅ ኩራት ነው። ‎ ‎በመደመር እሳቤ እየተመራን፤ ሕዝባዊ አንድነትን፣ ተጠያቂነትንና አካታች አስተዳደርን ማረጋገጥ የፖለቲካ አመራር የዜጎችን ሕይወት እንዲያሻሽል የሚያስችሉ ወሳኝ መሠረቶች ናቸው። ይህም ፓርቲዎች ከምርጫ ውድድር ባለፈ አሻግረው እንዲመለከቱ፣ በመንግሥት ለውጦች የማይቀያየሩ፣ ብሔራዊና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የረጅም ጊዜ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጥሩ እና ለሀገር ጥቅም በጋራ እንዲሠሩ ይጠይቃል። ‎ ‎በሌላ በኩል፣ ተተኪው ትውልድ ኃላፊነቶችን እየወሰደ የሚያድግበትን ዕድሎችን እያገኘ እንዲሄድ ለማድረግ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ በኩል የምትሰጠውን ሥልጠና በአህጉሪቱ ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክፍት ማድረጓን ትቀጥላለች። ‎ ‎ለሕዝባችን የተሻለ መጻኢ ዕድል የመገንባት ኃላፊነታችን ሊቀጥል ይገባል! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

የአዲስ አበባ ከተማ አንጸባራቂ ዕድገት፡ የመደመር እሳቤ ህያው ተምሳሌት! ኢትዮጵያ የጀመረችው ጥልቅ የመደመር ስትራቴጂ፤ የከተሞችን ዕድገት ለማፋጠን፣ የተቋማትን የመፈጸም አቅም ለማገዝ፣ ሀገር በቀል ሀብቶችን አሟጦ ለመጠቀምና ለዘመናት የተንከባለሉ የከተማ ልማት ማነቆዎችን በተደራጀ፣ በተቀናጀና ዘላቂነት ባለው ሥርዓት ለመፍታት የሚያስችል ታሪካዊ አቅም ፈጥሯል። በተለይም የኮሪደር ልማትን በስፋት በመተግበር፣ የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ዕድል በማሳደግ፣ አካታች የሆነ የከተማ ልማትን እውን በማድረግና የኢትዮጵያን ከተሞች የኢኮኖሚ ማዕከል በማድረግ ተጨባጭ የሆነ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ትንሳኤ ማምጣት ተችሏል። በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች፣ ከተማዋን ለኑሮ ምቹ፣ ማራኪና ለቱሪስቶች ተመራጭ እንድትሆን አድርገዋታል። በአዲስ መልክ የተገነቡት ውብ የኮሪደር ልማቶችና ግዙፍ የኢንዱስትሪ ማምረቻዎች የከተማዋን የኢኮኖሚ የደም ዝውውር በከፍተኛ ደረጃ በማነቃቃት ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና የጎላ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። በመደመር እሳቤና በቅንጅታዊ አሠራር ማዕቀፍ ውስጥ፣ ለኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር መፋጠን ዋነኛው መነሻና መድረሻ ከተሜነት መሆኑ በግልጽ ተሰምሮበታል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የመደመር መንግሥት” በተሰኘው መጽሐፋቸው ይህንኑ ሐሳብ በጥልቀት ሲተነትኑ፤ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ ሀገራት የነገ ዕጣ ፈንታቸው ያለው በከተሞቻቸው ውስጥ መሆኑን በማስገንዘብ፤ ከተሞች ለሀገራዊ ጥቅል ምርት (GDP) ያላቸውን ከፍተኛ ድርሻ አጉልተው አሳይተዋል። የአሁኑም ሆነ የመጪው ዘመን የሀብት ማመንጫ ምንጮች ከተሞች መሆናቸውን አበክረው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከተሞችን በፍጥነት ማሳደግ፣ ፈጠራን ማጎልበት፣ ተሰጥዖዎችን መሳብ፣ ምቹ የንግድ ሥነ-ምህዳርን መፍጠርና ለዘላቂ ዕድገት ወሳኝ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን ማሟላት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ሽግግር እውን ለማድረግ ሞተር እንደሚሆኑ አብራርተዋል። በከተሞች ላይ የተጠናና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ሙዓለ ንዋይ ማፍሰስ፣ የብልጽግናን በሮች በሰፊው ከመክፈቱም በላይ፣ አካታችና የማይበገር አቅም በመፍጠር ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ሥርዓት ጋር በጥብቅ እንድትተሳሰር ያደርጋታል። የተበታተኑ አቅሞችን፣ ሐሳቦችንና ግቦችን በአንድነት በማቀናጀት የላቀ የጋራ ውጤት ለማምጣት የሚያስችለው ይህ እሳቤ፣ በአዲስ አበባ ልማት ላይ በተግባር ታይቷል። ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በታቀደላቸው ጊዜ የማጠናቀቅ ባህል፣ ከተማዋ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እያበረከተች ያለው ጉልህ አስተዋጽዖ፣ እንዲሁም በተጨባጭ እየታየ ያለው ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጥ የዚህ ታላቅ እሳቤ ህያው መገለጫ ነው። በአጠቃላይ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሁለንተናዊ ዕድገት ኢትዮጵያ በመደመር ጎዳና የጀመረችው ጉዞ ሊቀለበስ የማይችልበት የብልጽግና ምዕራፍ ላይ መድረሱን የሚያበስር ደማቅ ማሳያ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የድጎማ በጀት አጠያየቅና አፈቃቀድ ሳይንሳዊ ፣ ግልጽና ተጠያቂነትን ባረጋገጠ መልኩ ለመምራት የሚያስችል አዲስ ረቂቅ መመሪያ ይፋ ተደረገ። ######################## ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም ፋይናንስ ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የፊስካል ፖሊሲ እና ገቢ ጥናት ዳይሬክቶሬት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት በጀት ድጎማ ጥያቄ አቀራረብና አፈቃቀድ ረቂቅ መመሪያ ቁጥር ……2019 መዘጋጀቱ ተገልጿል። የፊስካል ፖሊሲ እና ገቢ ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ በለጠ ሞገስ ይህ መመሪያ የተዘጋጀበት ዋና ዓላማ የከተማ አስተዳደሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የዕለት ተዕለት የኑሮ ጫና ለማቃለል፣ መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች፣ የህዝብ ትራንስፖርት፣ የባህልና መዝናኛ አገልግሎቶች እንዲሁም ስትራቴጂካዊ ተቋማት በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያደርገውን የበጀት ድጎማ አሰራር ይበልጥ ዘመናዊና ግልጽ ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል። ሰነዱን ያቀረቡት የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳግማዊ መሰረት ሲሆኑ መመሪያዉ  ከዚህ ቀደም ይደረግ የነበረው የድጎማ በጀት አጠያየቅ ሳይንሳዊ ይዘቱን የተከተለ እንዳልነበር ገልፀው የድጎማ ጥያቄ  የሚያቀርቡ የድጎማ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝር የጥናት ሰነድ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የድጎማ በጀት በከተማ አስተዳደሩ ሲፈቅድ ቢሮው ከተቋማቱ ጋር የዕቃዎች ጥራት፣ የተመጣጣኝ ዋጋ ወሰን እና የአገልግሎት ሽፋን ያካተተ የውጤት ስምምነት እንደሚፈራረም እና የተመደበው የበጀት ድጎማ ከሌሎች የራሳቸው ገቢዎች ጋር ሳይቀላቀል በልዩ መዝገብ መያዝ እንዳለበትና፣ ህጉን ተላልፎ የተገኘ ወይም ገንዘቡን ያባከነ አካል አግባብ ባለው የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ተጠያቂ እንደሚሆን መመሪያው ላይ በግልጽ መደንገጉን አብራርተዋል። ተሳታፊዎችም መመሪያዉ በተቋማቱ ከአሠራር አንፃር የሚያጋጥሙ ችግሮች እንደሚፈታ ጠቅሰዉ ቢካተት እና ቢቀነስ ያሉትን አስተያየትና ጥቄዎች አንስተዉ በዳይሬክቶሬቱ ምላሽ ተሰቶባቸዋል፡፡ ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን !! ዌብሳይት:- aacbof.gov.et ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/aabof.gov.et?mibextid=ZbWKwL ቴሌግራም:- https://t.me/AACABOFP ዩቲዩብ:- youtube.com/channel/UCTPN7Re7T7tp_ekAhVuw2uA ዋትሳፕ:-https://chat.whatsapp.com/FLSn12vRmsR9JsKUVDWxgtuuuu ቲክቶክ፡- Addis Ababa finance bureau

የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች በመዲናዋ የተለያዩ ተቋማትንና መሠረተ ልማቶችን እየጎበኙ ናቸው የሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ አካል የሆነው የአፍሪካ ሴቶች ፖለቲካ አመራሮችና የአፍሪካ ወጣቶች በፖለቲካ ፎረም ጉባኤ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የተለያዩ ተቋማትንና መሠረተ ልማቶችን እየጎበኙ ናቸው። ተሳታፊዎቹ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤትን የጎበኙ ሲሆን ፣ በጉብኝታቸውም ስለፓርቲው ገለፃና ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል። AMN

የመመሪያዎቹ መሻሻል የከተማዋን ወቅታዊ የልማትና የበጀት እንቅስቃሴ ያገናዘበ፣ ግልጽና ቀልጣፋ አሠራርን ለመዘርጋት መሆኑ ተገለጸ። ############################   ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ፋይናንስ ቢሮ  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፋይናንስ ቢሮ የከተማዋን የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓት ይበልጥ ለማጠናከር፣ ግልጽነትን ለማስፈንና ተጠያቂነትን አስተማማኝ በሆነ ደረጃ ለማረጋገጥ የተዘጋጁ 13 ረቂቅ መመሪያዎችን ለባለድርሻ አካላት አስተዋውቆ ግብአት ለመሰብሰብ ያለመ ሰፊ የምክክር መድረክ  ተካሄደ። በምክክር መድረኩ ላይ የተቋሙ አመራሮች፣ የፋይናንስ ዘርፍ ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው ልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን፣ የመመሪያዎቹ መሻሻል ወቅታዊውን የከተማዋን የልማትና የበጀት እንቅስቃሴ አሰራር ያገናዘበ፣ ግልጽና ቀልጣፋ አሰራርን ለመዘርጋት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። ዋና ዋና ረቂቅ መመሪያዎች የካፒታልና የሥራ ገንዘብ አስተዳደር፣ የክፍያ አፈጻጸም፣ የሂሳብ አያያዝ፣ የፋይናንስ ኃላፊነትና ኃላፊነትን በብቃት ባለመወጣት የሚወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎች፣ የንብረት ርክክብ አፈጻጸም፣ የውስጥ ኦዲት እና የውስጥ ኦዲት አስተዳደር፣ የውስጥ ቁጥጥር ደረጃዎች፣ የፔቲ ካሽ (Petty Cash) አስተዳደርና አደረጃጀት እንዲሁም የፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት መመሪያዎችን ያካተቱ ናቸው። የመመሪያዎቹ መሻሻል ዋና ዓላማ የህዝብና የመንግሥት የፋይናንስ ሀብት ለተፈለገው ልማትና አገልግሎት ብቻ በአግባቡ መዋሉን ማረጋገጥ፣ የአሰራር ክፍተቶችንና ብክነትን መቀነስ እንዲሁም የፋይናንስ ቁጥጥር ሥርዓቱን ዓለም አቀፍና ዘመናዊ አሰራሮችን በተከተለ መንገድ ማጠናከር እንደሆነ ተመልክቷል። በውይይቱ ወቅት ተሳታፊዎች በረቂቅ መመሪያዎቹ ይዘት፣ በትግበራ ወቅት ሊያጋጥሙ በሚችሉ ማነቆዎችና መፍትሔዎች ላይ በርካታ አበልጻጊ ሐሳቦችንና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን፣ የተነሱት ገንቢ አስተያየቶች በሰነዶቹ ላይ ታክለውና አስፈላጊው ማሻሻያ ተደርጎባቸው ለመጨረሻ ትግበራ እንደሚዘጋጁ ተገልጿል። ይህ የሕግና አሰራር ማዕቀፍ ማሻሻያ በሙሉ አቅሙ ወደ ትግበራ ሲገባ በከተማ አስተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች ዘንድ የበጀትና የንብረት አስተዳደር ውጤታማነትን በእጅጉ እንደሚያሳድግ፣ የሀብት ብክነትን እንደሚያስቀርና የህዝብን እምነት የሚያጎለብት የፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት አየር ሁኔታ እንደሚፈጥር ይጠበቃል።   ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን !! ዌብሳይት:- aacbof.gov.et ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/aabof.gov.et?mibextid=ZbWKwL ቴሌግራም:- https://t.me/AACABOFP ዩቲዩብ:- youtube.com/channel/UCTPN7Re7T7tp_ekAhVuw2uA ዋትሳፕ:-https://chat.whatsapp.com/FLSn12vRmsR9JsKUVDWxgtuuuu ቲክቶክ፡- Addis Ababa finance bureau

ማስታወቂያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፤ ከተማ አስተዳደሩን አስፈፃሚ አካላት እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 95/2019 የተቋቋመ ሲሆን፣ በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 51/2009 ፣በግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 92/2018 በፋይናንስ ደንብ  የተሰጡትን ኃላፊነቶች ለመወጣት የተለያዩ መመሪያዎችን አውጥቶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። በሥራ ላይ የነበሩት ነባር መመሪያዎችም የመንግስት በጀት አዘገጃጀት፣ የገንዘብ አሰባሰብ፣ የክፍያ ሒሳብ አያያዝ እና የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓትን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ይሁን እንጂ ወቅቱ የሚጠይቀውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ፍላጎት ማሟላት፣ የከተማዋን ፈጣን ዕድገት እና የልማት እንቅስቃሴዎች በይበልጥ መደገፍ፣ እንዲሁም  ለቢሮው የተሰጡትን ሥልጣኖችና ኃላፊነቶች በብቃት መወጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እንደ አዲስ መመሪያዎችን ማዘጋጀት ግድ ሆኗል።በዚህም መሰረት  በአዲስ መልክ በረቂቅ የተዘጋጁ መመሪያዎች ፦ 1. ረቂቅ መመሪያዎች የዕቃና አገልግሎት ዋጋ መመሪያ /ረቂቅ/ የበጀት አስተዳዳር መመሪያ /ረቂቅ/ የጥሬ ገንዘብ አስተዳዳር መመሪያ /ረቂቅ/ የገንዘብ ክፍያ መመሪያ /ረቂቅ/ የመንግስት ሰራተኞች የዋስትና አሰጣጥ መመሪያ /ረቂቅ/ የሂሳብ አያያዝ መመሪያ /ረቂቅ/ የፋይናንስ ኃላፊነት መመሪያ /ረቂቅ/ የውስጥ ኦዲት መመሪያ /ረቂቅ/ የውስጥ ቁጥጥር ደረጃዎች መመሪያ /ረቂቅ/ የውስጥ ኦዲት አስተዳደር መመሪያ/ረቂቅ/ የርክክብ አፈጻጸም መመሪያ /ረቂቅ/ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር የጋራ ፑል መመሪያ /ረቂቅ/ የወጪ ቁጠባ መመሪያ /ረቂቅ/ የታክስ ምህረት አፈጻጸም መመሪያ /ረቂቅ/ የፋይናንስ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት መመሪያ /ረቂቅ/ የድጋፍ ሀብት አሰባሰሰብ እና አስተዳደር አፈፃፀም መመሪያ /ረቂቅ/ የመንግስት ፕሮጀክቶች ክትትልና ግምገማ መመሪያ /ረቂቅ/ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ክትትልና ግምገማ መመሪያ /ረቂቅ/ የመንግስት ንብረት አስተዳደር መመሪያ /ረቂቅ/ የመንግስት ንብረት ኦዲት መመሪያ /ረቂቅ/ የፋይናንስ ኃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት የሚጣሉ ቅጣቶች መመሪያ /ረቂቅ/ የመንግስት ድጎማ አሰጣጥ ምደባና አስተዳደር መመሪያ /ረቂቅ/የግብአት ማሰባሰብ እና አስተያየት መስጫ ጊዜ ቢሮው ከላይ የተጠቀሱትን ነባር መመሪያዎች ለማሻሻል እና አዳዲሶችን ለማርቀቅ ቅድመ ዝግጅት አጠናቋል። ከ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ በቢሮው ድረ-ገጽ aacbof.gov.et ማግኘት ይቻላል። ረቂቅ መመሪያዎቹ በድረ-ገጽ ከተለቀቁበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ፤ አስተያየቶቻችሁን በአማርኛ ቋንቋ በጽሑፍ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 (ከአዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊት ለፊት በሚገኘው 1888 ህንጻ 6ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 603 በሚገኘው የህግ አገልግሎት ቡድን) በአካል በመገኘት ማቅረብ ትችላላችሁ።መመሪያዎቹን ለማውጣት የተደራጁ መረጃዎችን መመሪያው ከፀደቀ በኋላ በቢሮው በአካል በመገኘት ማግኘት ይቻላል። በሚረቁት መመሪያዎች ላይ የውይይት ጊዜ የሚካሄድበትን ቀን  በሚከተሉት ይፋዊ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን እናሳውቃለን፦ ·         ዌብሳይት:- aacbof.gov.et ·         ፌስቡክ:https://www.facebook.com/aabof.gov.et?mibextid=ZbWKwL ·         ቴሌግራም:- https://t.me/AACABOFP ·         ዩቲዩብ:- youtube.com/channel/UCTPN7Re7T7tp_ekAhVuw2uA ·         ዋትሳፕ:https://chat.whatsapp.com/FLSn12vRmsR9JsKUVDWxgtuuuu ·         ቲክቶክ፡- Addis Ababa finance bureau የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ

የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ የተመደበው 2 ቢሊዮን ብር ያመጣው ለውጥ በ1ኛው ሩብ ዓመት ግምገማ ተቃኘ፡፡ ########################   ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም ፋይናንስ ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ በማህበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም (ESAP-IDA20) ስር በተመረጡ የሙከራ ወረዳዎች የተከናወኑ የ1ኛ ሩብ ዓመት ተግባራትን አስመልክቶ የማህበራዊ ተጠያቂነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ተክሉ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የከተማ አስተዳደሩ በ2019 በጀት ዓመት የህብረተሰቡን የመሰረተ ልማትና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥያቄዎች መነሻ በማድረግ ወደ 2 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት መድቦ ወደ ተግባር ገብቷል። ይህ የተመደበ በጀት በአገልግሎት አቅራቢዎችና በተጠቃሚው ማህበረሰብ መካከል በተደረጉ ውይይቶች የተለዩ የአገልግሎት ክፍተቶችን ዘላቂ በሆነ መልኩ ለመፍታት እየዋለ መሆኑን አቶ ተስፋዬ  ጠቁመዋል። ባለሙያው አያይዘውም በየወረዳው የተዘጋጁ የጋራ ድርጊት መርሃ-ግብሮች (JAP) ህብረተሰቡ ባነሳቸው ቅሬታዎችና ጥያቄዎች ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ አብራርተዋል። በሩብ ዓመቱ በተደረገው የመስክ ምልከታና የJAP አፈፃፀም ግምገማ በትምህርት ዘርፍ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የገለጹት ባለሙያው፤ በተለይም በትምህርት ቤቶች ውስጥ የተገነቡ የመማሪያ ህንፃዎች፣ የመጫወቻ ሜዳዎች እና የመመገቢያ ክፍሎች በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። የዚህ ግምገማና የመስክ ክትትል ዋና ዓላማ የታቀዱ ስራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መከናወናቸውን ማረጋገጥ፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየት በወቅቱ የእርምት እርምጃ መውሰድና ህብረተሰቡ ያነሳቸው ጥያቄዎች በአግባቡ ምላሽ ማግኘታቸውን መከታተል መሆኑን አቶ ተስፋዬ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል። በቀጣይም የተጀመሩ የልማትና የአገልግሎት ማሻሻያ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና ህብረተሰቡ በውሳኔ አሰጣጥና በክትትል ሂደት ያለው ንቁ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ባለሙያው ተናግረዋል።   ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን !! ዌብሳይት:- aacbof.gov.et ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/aabof.gov.et?mibextid=ZbWKwL ቴሌግራም:- https://t.me/AACABOFP ዩቲዩብ:- youtube.com/channel/UCTPN7Re7T7tp_ekAhVuw2uA ዋትሳፕ:-https://chat.whatsapp.com/FLSn12vRmsR9JsKUVDWxgtuuuu ቲክቶክ፡- Addis Ababa finance bureau