es
Feedback
Ethio Fm 107.8

Ethio Fm 107.8

Ir al canal en Telegram

በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Ethio Fm 107.8

El canal Ethio Fm 107.8 (@ethiofm107dot8) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 18 482 suscriptores, ocupando la posición 12 086 en la categoría Noticias y medios y el puesto 1 892 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 18 482 suscriptores.

Según los últimos datos del 29 septiembre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de -15, y en las últimas 24 horas de -4, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 9.45%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 6.94% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 1 747 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 283 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 3.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 30 septiembre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Noticias y medios.

18 482
Suscriptores
-424 horas
+177 días
-1530 días
Archivo de publicaciones
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) በኬንያ ላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ የመሠረት ድንጋይ የማኖር ሥነ-ሥርዓት ላይ ተሳተፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) በኬንያ ላሙ ወደብ በተካሄ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) በኬንያ ላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ የመሠረት ድንጋይ የማኖር ሥነ-ሥርዓት ላይ ተሳተፉ   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር )  በኬንያ ላሙ ወደብ በተካሄደው የዳንግቴ ምስራቅ አፍሪካ ነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ የማኖር ሥነ-ሥርዓት ላይ ተሳትፈዋል።   በተባበሩት መንግሥታት እና ቀጣናዊ መሪዎች በተገኙበት በዚህ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ እንዲሁም የቤኒን፣ የቶጎ እና የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ተገኝተዋል።   በ16 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር (2.2 ትሪሊዮን የኬንያ ሺሊንግ) ኢንቨስትመንት የሚገነባው ይህ ነዳጅ ማጣሪያ፤ በቀን 700,000 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ የማጣራት አቅም ያለው ሲሆን፣ ለ60,000 የኬንያ ወጣቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርና ለምሥራቅና ማዕከላዊ አፍሪካ 8 ገበያዎች የኃይል ዋስትና እንደሚሰጥ ተገልጿል።   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ ፕሮጀክቱ የአፍሪካን የኢንዱስትሪ አቅም ለማሳደግ፣ መጠነ ሰፊ እድሎችን ለመፍጠር እና በምስራቅ አፍሪካ ለላቀ ኢኮኖሚያዊና የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነት መሰረት የሚጥል ትልቅ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም የሀጉሪቱ የኢንዱስትሪ መሪዎችና ባለሀብቶች በአፍሪካ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉና የአፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ በጋራ እንዲገነቡ ጥሪ አቅርበዋል።   መስከረም 20/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አህጉራዊ የበላይነቱን የሚያጎላ አዲስ ስምምነት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ፈፀመ   አየር መንገዱ አስር እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የቦይንግ የጭነት አውሮፕላኖችን ለመግዛት የሚያስችለውን ስምምነት በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል።   በስምምነቱ መሠረት አየር መንገዱ ስምንት እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የቦይንግ 777-8 እንዲሁም ሁለት የቦይንግ 777 ኤፍ የጭነት አውሮፕላኖችን የራሱ ያደርጋል።   የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት፣ አየር መንገዱ እነዚህን አውሮፕላኖች እ.ኤ.አ ከ2033 እስከ 2035 ባሉት ዓመታት ውስጥ ተረክቦ ሥራ ላይ ያውላቸዋል።     ከዚህ በተጨማሪም በቅርብ ዓመታት (ማለትም በ2027 እና 2028) ሁለት ተጨማሪ አዲስ የቦይንግ 777 የጭነት አውሮፕላኖችን እንዲሁም ከተሳፋሪነት ወደ ጭነት የተለወጡ አራት ተጨማሪ አውሮፕላኖችን እንደሚረከብ አቶ መስፍን አበስረዋል፤ ይህም የአየር መንገዱን የካርጎ አቅም ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል ተብሏል።   የቦይንግ ኩባንያ የንግድ ሽያጭና ማርኬቲንግ ምክትል ፕሬዝዳንት ብራድ ማክሙለን በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዘመናዊውን የቦይንግ 777-8 የካርጎ አውሮፕላን በማዘዝ በአፍሪካ የመጀመሪያው አየር መንገድ በመሆኑ ትልቅ ዕውቅና የሚሰጠው ውሳኔ ነው ብለዋል።   በአሁኑ ወቅት የአየር መንገዱ የካርጎ አገልግሎት ከአጠቃላይ ገቢው 23 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን፣ ይህ አዲስ ስምምነት ባለፈው ዓመት የተመዘገበውን የ897 ሺህ ሜትሪክ ቶን የጭነት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ የአየር መንገዱን የዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የበለጠ የሚያጠናክር ይሆናል።   የውልሰው ገዝሙ   መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content

የካሊፎርኒያ ጓደኛሞች የሌጎ ካርታ ሪከርድን ሰበሩ ​ሁለት የካሊፎርኒያ ጓደኛሞች 11,695 ቁርጥራጮች ያሉት ግዙፉን የሌጎ የዓለም ካርታ በ4 ሰዓት ከ59 ደቂቃ እና ከ51 ሰኮንዶች ውስጥ ብቻ በመገ
የካሊፎርኒያ ጓደኛሞች የሌጎ ካርታ ሪከርድን ሰበሩ ​ሁለት የካሊፎርኒያ ጓደኛሞች 11,695 ቁርጥራጮች ያሉት ግዙፉን የሌጎ  የዓለም ካርታ በ4 ሰዓት ከ59 ደቂቃ እና ከ51 ሰኮንዶች ውስጥ ብቻ በመገጣጠም አዲስ የጊነስ የዓለም ሪከርድ አስመዝግበዋል። ​አቲና ሊዮንግ እና ሴቪ ስዊፍት የተባሉት ሁለቱ ወዳጆች፣ ይህንን ታላቅ ውድድር ያከናወኑት  በሃይዋርድ በሚገኘው "ብሪክ ባይ ብሪክ ቶይስ" የተሰኘ መደብር ውስጥ ነው።   ለዚህ ፈተና ለአንድ ሙሉ ወር ያህል ተግተው የተለማመዱት ሁለቱ ወጣቶች፣ በልጅነታቸው ከሌጎ ጋር የነበራቸው ጥልቅ ትዝታና የፈጠራ ፍቅር ዛሬ ላይ ለአንድ ዓላማ አብረው እንዲቆሙ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል። ​ጊነስ የዓለም ሪከርድ ድርጅት ያስቀመጠው የ5 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ግብ በሰዓቱ እንዲሳካ ካደረጉዋቸው ዋና ዋና ምስጢሮች መካከል፣ ቀለሞችን በቅደም ተከተል አንድ በአንድ በመያዝ መገጣጠም እንደሚገኙበት ገልጸዋል።   ይህ ስልት ክፍት ቦታዎችን በቀላሉ ለመሙላትና ከፍተኛ ጊዜን ለመቆጠብ እንደረዳቸውም አስረድተዋል። ​በውጤቱ የተሰማቸውን ደስታ የገለጹት ሁለቱ ጓደኛሞች፣ በቀጣይም ከዚህም የበለጠ ትልቅና ፈታኝ የሆኑ የሌጎ ስብስቦችን በመሥራት አዳዲስ ዓለም አቀፍ ሪከርዶችን ለመስበር ዕቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል ሲል ዩናይትድ ፕረስ ኢንተርናሽናል ዘግቧል። ሐመረ ፍሬው መስከረም 20/2019 ዓ.ም

ቡሩንዲ ከአሜሪካ የሚባረሩ ስደተኞችን ለመቀበል ተስማማች ቡሩንዲ ከራሷ ዜጎች ውጭ ከዩናይትድ ስቴትስ የተባረሩ ስደተኞችን ለመቀበል ከተስማሙ የአፍሪካ ሀገራት አንዷ ሆናለች። የቡሩንዲ ዉሳኔ የተሰማዉ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፖሊሲው ላይ መደበኛ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የ‹‹ሦስተኛ ሀገር›› ዲፖርቴሽን እንዲቀጥል እንደሚፈቅድ ባስታወቀ በሰዓታት ውስጥ ነው። የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ናንሲ ኒኔት ሙቶኒ ‹‹ፕሬዝዳንቱ ቡሩንዲ የምትቀበለው የወንጀል ክስ የሌለባቸውንና ከሽብርተኝነት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸውን ሰዎች ብቻ እንደሆነ ግልጽ አድርገዋል›› ብለዋል። ቃል አቀባይዋ ለተባረሩት ሰዎች መጠለያ ለማዘጋጀትና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ተቀላቅለው እንዲኖሩ ለመርዳት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፤ይህም ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት ዕቅድ እንደሚጠይቅ አክለው ተናግረዋል። ቃል አቀባይዋ፤ አገራቸዉ ምን ያህል ስደተኞችን ለመቀበል እንደተስማማች ወይም መቼ እንደሚደርሱ ባይገልጹም፤ ቡሩንዲ ‹‹ችግር የገጠማቸውን ሰዎች ከመቀበል አኳያ ረጅም ታሪክ ያላት ሀገር ናት›› ብለዋል። ይህ ደግሞ ከሌሎች ሀገራት ጋር ያለውን ትብብር ያጠናክራል። ሰዎች ያስፈልጋሉ፤ ቡሩንዲ ደግሞ ለሰላምና መልካም ግንኙነት ትልቅ ዋጋ ትሰጣለች ብለዋል። የትራምፕ አስተዳደር የኢሚግሬሽን ቁጥጥር እርምጃዎቹ አካል አድርጎ በሦስተኛ ሀገር የሚፈጸሙ ዲፖርቴሽኖችን አስፋፍቷል። አስተዳደሩ ይህንን ፖሊሲ፤ የዲፖርቴሽን ሰለባ የሆኑ ሰዎች ትውልድ ሀገራቸዉ እነሱን ለመቀበል እምቢተኛ በሚሆኑበት ጊዜ አስፈላጊ እርምጃ ነው በማለት ተከላክሏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የባለሙያዎች ሪፖርት እንደገለጸው ከሆነ ግን፤ ስደተኞችን ወዳልመጡበት ሀገር መላክ ለሕይወት አስጊ የሆኑ አስከፊ መዘዞች ሊኖሩት ስለሚችል እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል። እስከዳር ግርማ መስከረም 20/2019 ዓ.ም

photo content

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የተለያዩ ሹመቶችን ለከተማ አስተዳደሩ ም/ቤት አቅርበዋል። በዚሁም፡- 1. አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ
+3
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የተለያዩ ሹመቶችን ለከተማ አስተዳደሩ ም/ቤት አቅርበዋል። በዚሁም፡- 1. አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ እና ክህሎት ኃላፊ 2. አቶ ጥላሁን ከበደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ በአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ 3. አቶ ሀፍታይ ገብረእግዚአብሄር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ 4. አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቀረቡትን ሹመቶች አጽድቋል።   መስከረም 20/2019 ዓ.ም

ከ1.8 ሚሊየን በላይ ሰዎችን የደገፈው የሰብአዊ እርዳታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ ዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በግጭት፣ በድርቅ፣ በቦታ መፈናቀል እና ሌሎች ሰብዓዊ ፈተናዎች የተጎዱ ከ1.8 ሚሊየን በላይ ሰዎች ተጠቃሚ የሆኑበት የሶስት ዓመት የተቀናጀ የሰብዓዊ ምላሽ ፕሮጀክት ማጠናቀቁን አሳውቋል። ፕሮጀክቱ በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በትግራይ ክልሎች በሚገኙ 27 ወረዳዎች ውስጥ ተተግብረዋል።  ይህ አጠቃላይ ፕሮጀክት በጤና፣ በስነ-ምግብ፣ በውሃ፣ ንፅህና ፣ ኤችአይቪ፣ በህፃናት ጥበቃ እንዲሁም በህይወት ማሻሻያ ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራትን አስተባብሮ የያዘ ሲሆን፥ተጎጂ ማህበረሰቦች ከችግር እንዲያገግሙና የወደፊት የመቋቋም አቅማቸውን እንዲገነቡ አስችሏል።  በፕሮጀክቱ ከ41 ሺህ በላይ ህፃናት ለከባድ የምግብ እጥረት ህክምና አግኝተዋል ከ2መቶ9 ሺህ በላይ ህፃናት ደግሞ ለቅድመ ምርመራ እና ህክምና ተመዝግበዋል። በተጨማሪም ከ3መቶ 53 ሺህ በላይ የህክምና ምክክሮች ተሰጥተዋል።  2ሺህ 6መቶ40 የጤና ባለሙያዎች ስልጠና ያገኙ ሲሆን፥61 የጤና ተቋማትም ታድሰዋል።  በተጠገኑ የውሃ መስመሮች አማካኝነት ከ53ሺህ በላይ ሰዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ እና ተያያዥ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ሆነዋል።  የዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ሀገራዊ ዳይሬክተር ካርመን ቲል እንደተናገሩት፥ "የዚህ ፕሮጀክት አላማ እርዳታ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ህፃናት ከችግር ተላቀው በህይወት ለመቆየት፣ ለማንሰራራት እና የተሻለ መፃኢ እድል ለመገንባት የሚያስፈልጓቸውን አገልግሎቶች፣ ጥበቃ እና እድሎች ማግኘታቸውን ማረጋገጥ ነው" :: ድርጅቱ እንደገለፀው፥በአካባቢው የነበሩ የጸጥታና የተደራሽነት ፈተናዎች ሳይበግሩት ከመንግስት፣ ከሀገር ውስጥ አካላት እና ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ድጋፉን ሳያቋርጥ ማዳረስ ችሏል። ዎርልድ ቪዥን አሁንም በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች ከፍተኛ የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት እንዳለ በመጠቆም ለህፃናት ጤና፣ ስነ-ምግብ፣ ጥበቃ እና ውሃ አገልግሎቶች ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል። ሀና ሰይፉ መስከረም 20/2019 ዓ.ም

photo content

አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃ
አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ   የአዲስ አበባ ምክር ቤት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ሾሟል፡፡   አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ቀደም ሲል የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩ ሲሆን በተለያዩ የስራ ሃላፊነቶችም አገልግለዋል፡፡   አዲሱ ተሿሚ በዚህ የኃላፊነት ቦታ ላይ የተኩት የቀድሞውን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ የነበሩትን አቶ ዣንጥራር አባይን ነው።   መስከረም 20/2019 ዓ.ም

የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እስራኤል በጋዛ እያደረሰች ያለውን ጥቃት ኮንነዋል የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራህማን ቢን ጃሲም አል ታኒ በጋዛ እየተካሄደ
የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እስራኤል በጋዛ እያደረሰች ያለውን ጥቃት ኮንነዋል የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራህማን ቢን ጃሲም አል ታኒ በጋዛ እየተካሄደ ያለውን አስከፊ ጦርነት አጥብቀው አውግዘዋል። በባህረ ሰላጤው አካባቢ ለሚታየው ውድመት ተጠያቂ የሆኑት አካላት ሁሉ “የጦር ወንጀለኛ” ናቸው ሲሉ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ“ፒርስ ሞርጋን አንሴንሰርድ” ፕሮግራም ላይ ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ፥የሃማስ የጥቅምት 7 ጥቃት መኮነን ያለበት “ጭፍጨፋ” ቢሆንም፣ የእስራኤል ምላሽ ግን ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውና ሆስፒታሎችንና ትምህርት ቤቶችን ኢላማ ያደረገ ነው ብለዋል። እስራኤል በጥቅምት 2025 የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት በየቀኑ በመጣስ ከ1ሺህ 4መቶ በላይ ፍልስጤማውያንን መግደሏንና የጋዛን 70 በመቶ መሬት መቆጣጠሯን በመጥቀስ ፥ዶሃ የጀመረችው የሰላም ጥረት በእስራኤል እጅ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ መስተጓጎሉን ገልጸዋል። በተጨማሪም እስራኤል የሃማስ ከፍተኛ አመራሮች ለድርድር ተሰብስበው በነበሩበት ወቅት በኳታር መዲና ዶሃ ላይ የሰነዘረችውን የሚሳኤል ጥቃት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የጣሰና በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ “አስታራቂን ማጥቃት” ሲሉ አውግዘውታል። በአሁኑ ወቅት ኳታር ከፓኪስታን ጋር በመሆን በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ እያሸማገለች እንደምትገኝ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በክልሉ ያለውን ጦርነት ለማቆም መሰረታዊ የሚባሉ ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። ሳራ ዮሐንስ መስከረም 20/2019 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር 2.9 ሚሊዮን ብቻ ነው ሲል መንግስት አስታወቀ የረጂ ድርጅቶች አሃዝ የተጋነነ ነው፤ በስማችን የሚነገደው የዕርዳታ ንግድ መቆም አለበት ተብሏል
+1
በኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር 2.9 ሚሊዮን ብቻ ነው ሲል መንግስት አስታወቀ የረጂ ድርጅቶች አሃዝ የተጋነነ ነው፤ በስማችን የሚነገደው የዕርዳታ ንግድ መቆም አለበት ተብሏል በመንግስት በኩል በተከናወነ ጥናትና ከክልሎች በተሰበሰበ ትክክለኛ መረጃ መሰረት፣ በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቁጥር 2.9 ሚሊዮን ብቻ ነው ያለው የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ነው። ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች የተረጂዎችን ቁጥር እያጋነኑ ይገልጻሉ ሲሉ የገለጹት የኮሚሽኑ የሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም ማስተባበሪያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሻግሬ ተሾመ፤ ድርጅቶቹ ለራሳቸው የፕሮጀክትና የሰራተኛ ደመወዝ በጀት ማሟያ ሲሉ መረጃዎችን እንደሚያዛቡ ነው ያስረዱት። አቶ አሻግሬ ተሾመ ይህንን ያሉት በአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አዘጋጅነት በኤል-ኒኖ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለፌደራልና ለክልል የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አካላት በተዘጋጀ የምክክር መድረክ ላይ ነው። በመድረኩ በሰጡት ማብራሪያ "በስማችን የሚነገደው የዕርዳታ ንግድ መቆም አለበት" ያሉት አቶ አሻግሬ፤ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች በአካል ጉዳት፣ በእርጅና፣ በመፈናቀል፣ በከተማና ገጠር ሴፍቲኔት እንዲሁም ከስደት ተመላሾች በሆኑ ስድስት የህብረተሰብ ክፍሎች የተለዩና በድምሩ 2.9 ሚሊዮን የሆኑ ዜጎች ናቸው በማለት ተናግረዋል።   አዲስዓለም አበበ   መስከረም 20/2019 ዓ.ም

ገዳ ባንክ «ገዳ ዲጂታል ኦንቦርዲንግ » የተሰኘ አዲስ የዲጂታል ምዝገባ ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ፡፡ ገዳ ባንክ ከደንበኞች ጋር ያለውን ቁርኝት ለማጠናከር እና የባንክ አገልግሎቶችን ከቀጠሮና ከቢሮ ውጭ
ገዳ ባንክ «ገዳ ዲጂታል ኦንቦርዲንግ » የተሰኘ አዲስ የዲጂታል ምዝገባ ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ፡፡   ገዳ ባንክ ከደንበኞች ጋር ያለውን ቁርኝት ለማጠናከር እና የባንክ አገልግሎቶችን ከቀጠሮና ከቢሮ ውጭ ለማድረግ የሚያስችል «ገዳ ዲጂታል ኦንቦርዲንግ» የተሰኘ አዲስ የዲጂታል ምዝገባ ቴክኖሎጂ አስታውቋል።   ይህ አዲስ ዘመናዊ ፕሮዳክት ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ በመሆኑ፣ ደንበኞች ባንክ በአካል በመገኘት ወይም ቅርንጫፍ በመጎብኘት ጊዜ ሳያባክኑ በማንኛውም ሰዓት እና ቦታ ያለ ምንም እንከን የባንክ አገልግሎቶችን ማግኘት እንዲችሉ ያስችላል ተብሏል። ​ፕሮዳክቱ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የደንበኞችን ማንነት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ ግለሰቡ በህይወት መኖሩን የሚያረጋግጥ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሂደቱን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከማጭበርበር የጸዳ እንደሚያደርገው ተጠቅሷል።   በተጨማሪም የደህንነት ማረጋገጫ ኮዶች በቀጥታ በጽሁፍ መልእክት እና በኢሜይል የሚላኩበት ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ ስርዓት ተካቶበታል።   ይህ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አዲስ መፍትሄ የባንኩን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ከፍ ከማድረጉም በላይ፣ የደንበኞችን ተለዋዋጭ ፍላጎቶች ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።   ሐመረ ፍሬው መስከረም 20/2019 ዓ.ም

በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት በአዲስ ዌስት ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የትራንስፎርመር ብልሽት ምክንያት ዛሬ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም የኃይል አቅርቦት የተቋረጠባቸው እና የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፡፡ ✅ከጠዋት 12፡00 - ቀኑ 8፡00 👉አዲስ ዌስት ሰብስቴሽን፣ ኮልፌ መናፈሻ፣ ፊሊጶስ፣ ኮልፌ ጤና ጣቢያ በከፊል፣ ቀራንዮ መድኃኒዓለም ቤ/ክ፣ ቤተል ሆስፒታል፣ ቤተል ቢጫ ፎቅ፣ መስኪድ፣ ቤተል ፓስታ ቤት አካባቢ፣ ኮልፌ ወ.8 ፅህፈት ቤት እና አካባቢው፣ 👉አማኑኤል ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ሰባተኛ፣ ድሬ ህንጻ ፊት ለፊት፣ ኮልፌ 18 ጤና ጣቢያ፣ ኮልፌ 18 ድልድዩ ድረስ፣ አውጉስታ፣ ወይራ ሰፈር፣ ወይራ ኮንዶሚኒየም፣ ሞቢል፣ ራሺያ ካምፕ የነበረው፣ ተዘንአ ሆስፒታል፣ ሙስና ሰፈር፣ ጦር ኃይሎች ጎልፍ ክለብና አካባቢው፣ ✅ከቀኑ 8፡00 - ምሽት 4፡00 👉አማኑኤል ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ሰባተኛ፣ ድሬ ህንጻ ፊት ለፊት፣ ኮልፌ 18 ጤና ጣቢያ፣ ኮልፌ 18 ድልድዩ ድረስ፣ አውጉስታ፣ ወይራ ሰፈር፣ ወይራ ኮንዶሚኒየም፣ ሞቢል፣ ራሺያ ካምፕ የነበረው፣ ተዘንአ ሆስፒታል፣ ሙስና ሰፈር፣ ጦር ኃይሎች ጎልፍ ክለብና አካባቢው፣ 👉እህል በረንዳ፣ አማኔኤል ቤ/ክ ፊትለፊት፣ ሻንቅላ ወንዝ፣ 18 ማደያው ጋር፣ ፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምርሄንሲቭ ት/ቤት እና አካባቢው፣ ✅ከምሽት 4፡00 - ጠዋት 12፡00 👉 እህል በረንዳ፣ አማኔኤል ቤ/ክ ፊትለፊት፣ ሻንቅላ ወንዝ፣ 18 ማደያው ጋር፣ ፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምርሄንሲቭ ት/ቤት እና አካባቢው፣ 👉አዲስ ዌስት ሰብስቴሽን አካባቢ፣ ኮልፌ መናፈሻ፣ ፊሊጶስ፣ ኮልፌ ጤና ጣቢያ በከፊል፣ ሎሚ ሜዳ፣ ኢንዱስሪ መንደር፣ ቀራንዮ መድኃኒዓለም ቤ/ክ፣ ቤተል ሆስፒታል፣ ቤተል ቢጫ ፎቅ፣ መስኪድ፣ ቤተል ፓስታ ቤት አካባቢ፣ ኮልፌ ወ.8 ፅህፈት ቤት እና አካባቢው፣ ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ እስኪመለስ ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁ በአክብሮት እናሳውቃለን።   መስከረም 20/2019 ዓ.ም

photo content

“ስልጣን የግል ጥቅም ማካበቻ እንዳይሆን እንሰራለን” — ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን መንግሥት ምስረታ እና የ4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መ
“ስልጣን የግል ጥቅም ማካበቻ እንዳይሆን እንሰራለን” — ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን መንግሥት ምስረታ እና የ4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል። በዚሁ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ ስልጣን የግል ጥቅም ማካበቻ እንዳይሆን በጽናት እንደሚሰራ ተናግረዋል። ከንቲባዋ በንግግራቸው ከተማዋን በድጋሚ እንድመራ ለተጣለብኝ እድል እና ኃላፊነት የከተማውን ህዝብ ከልብ አመሰግናለሁ ያሉ ሲሆን፣ በ7ኛው ዙር ምርጫ የተመዘገበው ውጤትም ህብረብሔራዊ ብዙሃንነትን በግልጽ ያሳየንበት ነው ብለዋል። አያይዘውም ሙስናን የሚጠየፍና የሚታገል የከተማ ነዋሪ እንዲሁም የመንግሥት ሰራተኛ ለመፍጠር በቅንጅት እንደሚሰራ የገለጹት ከንቲባዋ፣ በቀጣይ የሥራ ዘመናት የሕዝቡን መሠረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል። በተለይም ህብረተሰቡን እየፈተነ የሚገኘውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠርና የኑሮ ውድነትን ለማቃለል በቀጣይ ጊዜያት በበለጠ ትጋት እንደሚሰራ የጠቆሙ ሲሆን፣ የንጹሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና የመኖሪያ ቤት ተደራሽነትን ለማሳደግ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።   ለዓለም አሰፋ መስከረም 20/2019 ዓ.ም

በመንግሥት ግዥ ሂደት የሚታየውን ብክነት እና የአሰራር ክፍተት ለመግታት ያለመ አዲስ አዋጅ ተግባራዊ መደረግ ጀመረ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላለፉት 16 ዓመታት ሲሰራበት በነበረው አሰራር ይስ
በመንግሥት ግዥ ሂደት የሚታየውን ብክነት እና የአሰራር ክፍተት ለመግታት ያለመ አዲስ አዋጅ ተግባራዊ መደረግ ጀመረ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላለፉት 16 ዓመታት ሲሰራበት በነበረው አሰራር ይስተዋሉ የነበሩ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶችንና የአሰራር ክፍተቶችን ለመቅረፍ፣ አዲስ የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ አጽድቆ ወደ ሥራ አስገብቷል። በአዲሱ አዋጅ ቁጥር 92/2018 መሠረት፤ ቀደም ሲል በነበረው አሰራር በከተማዋ የልማት ድርጅቶች ላይ ይፈጠር የነበረውን የቁጥጥር ክፍተት ለማረም፣ ድርጅቶቹ ተገቢው ክትትልና ተጠያቂነት እንዲሰፍንባቸው በህጉ ማዕቀፍ ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል። ከዚህም ባሻገር በሰው ንክኪ ምክንያት የሚፈጠሩ የአሰራር ብልሹነቶችን ለማስቀረት፣ አጠቃላይ የግዥ ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክ (e-Procurement) ቴክኖሎጂ እንዲመራ የሚያስገድድ ድንጋጌ መካተቱ ታውቋል። በ13 ምዕራፎችና በ83 አንቀጾች የተዋቀረው ይህ አዋጅ፤ የመንግሥት ገንዘብ ያላግባብ እንዳይባክን እና በግዥ ሂደት ውስጥ ሙሉ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።   ልዑል ወልዴ መስከረም 20/2019 ዓ.ም

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሾሙ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ወ/ሮ አዳነች አቤቤን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አድርጎ ሰይሟል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሾሙ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ወ/ሮ አዳነች አቤቤን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አድርጎ ሰይሟል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደር መንግሥት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል። መስከረም 20/2019 ዓ›ም

ትናንት ጨፌ ኦሮሚያ የመጀመሪያ ጉባኤውን ሲያደርግ ካስተላለፋቸው ውሳኔዎች አንደኛው ለአመታት ክልሉ መስተዳድሩን የዘረጋበትን የዞን መዋቅር በማፍረስ ክልሉ ስድስት ዞኖች ብቻ እንዲኖሩት ያስተላለፈው ወሳኔ ነው። የክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ማምሻውን ባወጣው ዘገባ ስድስቱ የኦሮሚያ አስተዳደራዊ አካባቢዎች እና ከተሞቻቸው፦ የምስራቅ ኦሮሚያ ማዕከል ሆነው የሚያገለግሉ ከተሞች፦ ሀ. ሐረር ለ. ጭሮ ሐ. ገለምሶ መ. ጉራዋ የመካከለኛው ኦሮሚያ መቀመጫ (ማዕከል) ሆነው የሚያገለግሉ ከተሞች፦ ሀ. ሸገር እና አዳማ ለ. ወሊሶ ሐ. ፍቼ መ. አምቦ የደቡብ-ምዕራብ ኦሮሚያ ማዕከል ሆነው የሚያገለግሉ ከተሞች፦ ሀ. ጅማ ለ. በደሌ ሐ. ሊሙ ገነት መ. መቱ የደቡብ ኦሮሚያ ማዕከል ሆነው የሚያገለግሉ ከተሞች፦ ሀ. ያቤሎ ለ. አዶላ ሐ. ነገሌ ቦረና መ. ቡሌ ሆራ የምዕራብ ኦሮሚያ ማዕከል ሆነው የሚያገለግሉ ከተሞች፦ ሀ. ነቀምቴ ለ. ጊምቢ ሐ. ሻምቡ መ. ደምቢ ዶሎ የደቡብ-ምስራቅ ኦሮሚያ ማዕከል ሆነው የሚያገለግሉ ከተሞች፦ ሀ. ሮቤ ለ. ጊንዲር ሐ. አሰላ መ. ሻሸመኔ ልዑል ወልዴ መስክረም  19/2019 ዓ.ም

photo content