es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Kirkos curriculm

Kirkos curriculm

Ir al canal en Telegram

ለትምህርት ጥራት እንተጋለን We strive for the quality of education

Mostrar más
3 814
Suscriptores
+124 horas
+197 días
-1030 días
Archivo de publicaciones
ቀን 25/02/2019 ዓ.ም በጣም አስቸኳይ የአዲስ አበባ F.M 94.7 የትምህርት ሬድዮ ጣቢያ https://t.me/FM94_7 በመጠቀም ሁሉንም የሬድዮ ፕሮግራሞች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን እስካሁን ወደ ተግባር ያልገባችሁ ት/ቤቶች ከፍተኛ የስርዓተ ትምህርት ጥሰት መሆኑን አውቃችሁ ወደ ስራ እንድትገቡ እያሳወቅን ከዚህ ውጪ የሚሆን ተቋም ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት

photo content

photo content
+6

photo content

photo content

photo content

photo content
+4

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በ19 የመንግሥት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመማር ብቃት መለያ ፈተና (MLC) እየተሰጠ ይገኛል ቂርቆስ፣ ጥቅምት 2019 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት ትግበራና ክትትል ቡድን አማካኝነት በ19 የመንግሥት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ–4ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የአጥጋቢ የመማር ብቃት መለያ ፈተና (MLC) ከጥቅምት 18–20/2019 ዓ.ም እየተሰጠ ይገኛል። የአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት ትግበራና ክትትል ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ዘመቻ ዮሐንስ እንደገለጹት የመለያ ፈተናው ዋና ዓላማ ተማሪዎች በየክፍላቸው ሊያሟሉ የሚጠበቅባቸውን መሠረታዊ የመማር ብቃት ደረጃ መለየት፣ ያላቸውን የክህሎት ደረጃ መገምገምና በመማር ሂደታቸው የሚታዩ ጠንካራ ጎኖችንና የማሻሻያ ፍላጎቶችን ለመለየት ነው። በተጨማሪም የፈተናው ውጤት በተማሪዎች የመማር ክፍተቶች ላይ ተመስርቶ ተገቢውን የትምህርት ድጋፍ ለማቀድና የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማሻሻል ያግዛል። በፈተናው አተገባበር ሂደት የፈተና መመሪያዎች በተገቢው መንገድ መተግበራቸው፣ የፈተና አሰጣጡ በሥርዓት መከናወኑ፣ ተማሪዎች በነፃነትና በተረጋጋ ሁኔታ ፈተናውን እንዲያከናውኑ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩና የፈተና ሂደቱ በተገቢው መንገድ መከታተሉ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው። የትምህርት ጽ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት ትግበራና ክትትል ቡድን የፈተናው አፈጻጸም በታቀደው መሠረት መከናወኑን በመከታተል፣ በሂደቱ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በመለየትና አስፈላጊውን የሙያ ድጋፍ በመስጠት የፈተናው ዓላማ እንዲሳካ የሚያግዝ ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል። የመለያ ፈተናው ከተጠናቀቀ በኋላ የሚገኙ ውጤቶች በአግባቡ ተተንትነው የተማሪዎችን የመማር ደረጃ ለመለየት፣ ተጨማሪ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ተማሪዎች ለመለየትና ተማሪዎች በመሠረታዊ የመማር ክህሎቶች የሚጠበቅባቸውን ውጤት እንዲያሳኩ የሚያስችሉ የማሻሻያ ሥራዎችን ከህዳር 01/2019 ዓ.ም እስከ ጥር 30/2019 ዓ.ም ለሁለት ወራት ተከታታይነት ያለው የማብቃት ስራ የሚሰራ ይሆናል። በአጠቃላይ የMLC የመለያ ፈተና በተማሪዎች የመማር ብቃት ላይ ተመስርቶ የተሻለ የመማር ማስተማር ሂደት ለመፍጠር፣ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻልና ለሁሉም ተማሪዎች ተመጣጣኝ የመማር ዕድል ለማረጋገጥ ወሳኝ አስተዋጽኦ

ይነበብ
ይነበብ

+4
ቀን 17/2019 ዓ.ም አስቸኳይ መልዕክት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የመማሪያ ጥጎች አደረጃጀት እና አጠቃቀም ማኑዋል እና የቅድመ አንደኛ ደረጃ ህጻናት እድገትና ትምህርት ምዘና ማኑዋል ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ አሳውቆናል፡፡ በዚሁ መሠረት ሁሉም የመንግስትና የግል ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሁለቱም ቋንቋ የተዘጋጁትን ማኑዋሎች ለመምህራን በማስተዋወቅ ወደ ተግባር እንድትገቡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት

ቀን 17/2019 ዓ.ም አስቸኳይ መልዕክት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የመማሪያ ጥጎች አደረጃጀት እና አጠቃቀም ማኑዋል እና የቅድመ አንደኛ ደረጃ ህጻናት እድገትና ትምህርት ምዘና ማኑዋል ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ አሳውቆናል፡፡ በዚሁ መሠረት ሁሉም የመንግስትና የግል ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሁለቱም ቋንቋ የተዘጋጁትን ማኑዋሎች ለመምህራን በማስተዋወቅ ወደ ተግባር እንድትገቡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት

+3
NEW CTE BOOKs

የቂርቆስ ክ/ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአጠቃላይ ትምህርት ትግበራና ክትትል ቡድን በ2019 በጀት ለትበራ በተመረጡ የ11ኛ ክፍል የሥራና ተግባር ትምህርት CTE በተመረጡ አዲስ የሙያ ትምርት ዓይነቶ
+2
የቂርቆስ ክ/  ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአጠቃላይ ትምህርት ትግበራና ክትትል ቡድን በ2019 በጀት ለትበራ በተመረጡ የ11ኛ ክፍል የሥራና ተግባር ትምህርት CTE በተመረጡ አዲስ  የሙያ  ትምርት ዓይነቶች  የተማሪዎች ምዝገባ እና ምርጫ የአተገባበር ዙሪያ ከ2ኛ ደረጃ ክላስተር ሱፐርቫይዘሮች ፤ ከቂርቆስ ማኑፋክቸሪን ኮሌጅ አመራሮች እና ከ2ኛ ደረጃ ትምህት ቤቶች  ዋና ር/መምህራን ጋር  ውይይት አካሄደ፡፡  በመድረኩም 1.  የሙያ  ዓይነት  አመራረጥ  ሂደት 2.  በ2019ዓ.ም ሚተገበሩ የተመረጡ  ሙያ ትምህርቶች 3.  ትምህርት ቤቶች የሙያ አይነቶችን ሲመርጡ በትምህርት ቤቱ አካባቢ ያለውን ምቹ ሁኔታ 4.  ተማሪዎች የሚመርጡት ተጨማሪ የሙያ ዓይነት ከራሳቸው ፍላጎትና ችሎታ ጋር የተያያዘ መሆን አለበት እና በመሳሰሉት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ሰፊ ገለፃ  በአቶ ዘመቻ ዮሐንስ  የተደረገ ሲሆን የቂርቆስ ማንፋክቸርን ኮሌጅ የስልጠን ዘርፍ ም/ዲን ስለ ኮሌጁ የስልጠና ሂደት እና ትምህርቱን ውጤታማ ለመድግ በሚቻልባቸው ስልቶች ዙርያ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት የጋራ መግባባት ተደርሷል፡፡

ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም አስቸኳይ መልዕክት ለሁሉም የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ2019 ዓ.ም የ11ኛ ክፍል የስራና ተግባር ትምህርት የተማሪዎች ምርጫ እስከ ነገ አርብ 13/2019 ዓ.ም ድረስ ሞልታችሁ እንድትልኩ እያሳሰብን 12ኛ ክፍል በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች መረጃ ጭምር በቅጹ መሠረት ሞልታችሁ እንድትልኩልን፡፡ ማሳሰቢያ፡- መረጃው በሀርድ ኮፒ በደብዳቤ ጭምር እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡

ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም አስቸኳይ መልዕክት ለሁሉም የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ2019 ዓ.ም የ11ኛ ክፍል የስራና ተግባር ትምህርት የተማሪዎች ምርጫ እስከ ነገ አርብ 13/2019 ዓ.ም ድረስ ሞልታችሁ እንድትልኩ እያሳሰብን 12ኛ ክፍል በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች መረጃ ጭምር በቅጹ መሠረት ሞልታችሁ እንድትልኩልን፡፡ ማሳሰቢያ፡- መረጃው በሀርድ ኮፒ በደብዳቤ ጭምር እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡

photo content

photo content

photo content

ቀን 09/02/2019 ዓም አሰቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ለሁሉም የመንግስት እና የግል 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ነገ ጥቅምት 10/2019 ዓም በ2019 ዓም የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የCTE የሙያ ትምህርት ምርጫ በተመለከተ እና የአተገባበር ማኑዋል ትውውቅ መድረክ ስለተዘጋጀ ከመንግስት ት/ቤት የመማር ማስተማር ም/ር/መመህር ከግል ት/ቤት ዋና ር/መምህር ከሰዓት በዃለ 7:30 ክፍለ ከተማ ትምህርት ቤት ጽ/ቤት 6ኛ ፎቅ ሀላፊ ቢሮ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባለን። ማሳሰቢያ:- ሰዓት ይከበር

ጥቅምት 07/02/2019 ዓ.ም ለCTE ትምህርት ግንዛቤ መፍጠሪያ ሰነድ ሥለሆነ አሻሽላችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።