Kirkos curriculm
الذهاب إلى القناة على Telegram
3 769
المشتركون
+224 ساعات
-37 أيام
+4230 أيام
أرشيف المشاركات
3 769
ቀን 11/12/2018 ዓም
ለሁሉም 1ኛ እና 2ኛ ደረጀ የመንግስት እና የግል ት/ቤቶች
ከክልል በተለያዩ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ መጥተው በ2019 ዓም ለመማር የመመመጡ ተማሪዎች በምዝገባ ወቅት የሚያጋጥማችሁ ችግር ካለ በየቀኑ ከላይ በያያዘው ቅጽ መሠረት ሞልታችሁ እንድትልኩልን እናሳውቃለን።
3 769
📚 ትምህርት የነገ መሣሪያ
መጽሐፍ በእጄ፣ ሕልም በልቤ፣
እውቀት ነው ብርሃን በመንገዴ።
ዛሬ ብታገል ለትምህርት ብዬ፣
ነገን እገነባለሁ በእጄ ይዤ።
መሣሪያ ሳይሆን ብዕር እንድይዝ፣
በእውቀት ኃይል ዓለምን እንድለውጥ።
ትምህርት ይሁን ጋሻዬ ለነገ፣
ተስፋ ይሁን ብርሃኔ በሕይወቴ።
“የእውቀት ኃይል ከማንኛውም መሣሪያ ይበልጣል።”
3 769
ቀን 05/12/2018 ዓም
በጣም አስቸኳይ
ለሁሉም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቾ በሁለተኛ ዙር ከትምህርት ሚ/ር በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት 11 የሙያ መስኮች የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲመርጡ ግንዛቤ ፈጥራችሁ የመድረክ ሪፖርት በፎቶ አስደግፋችሁ ሀሙስ ነሀሴ 1/2018 ዓም በሀርድ እና ሶፍት ኮፒ እንድታሳውቁን።
የስርዓተ ትምህርት ትግበራና ክትትል ብድን
ግልባጭ:-
ለአቶ ሰማኝ አስታጥቄ
3 769
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ11ኛ ክፍል ተግባራዊ የሚደረጉ 11 የሥራና ተግባር የሙያ ዓይነቶችን ይፋ በማድረግ የክልልና የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የመምህራን ቅጥርን ጨምሮ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ መመሪያ አስተላለፈ።
አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የሙያ ትምህርትን ለማካተት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት፣
በሁለተኛው ዙር ለሚተገበሩት በእነዚህ 11 የሙያ ዓይነቶች የመርሐ ትምህርት፣ የተማሪ ሞጁል እና የመምህራን መምሪያ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል።
ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉት 11 የሙያ
ዓይነቶች፦
ብረታ ብረት ሥራ ቴክኖሎጂ
አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ
አልባሳት ቴክኖሎጂ
ህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋት
ቧንቧ ስራ
ሶፍትዌር ማበልጸግ
ሰብል አመራረት
ጤና ክብካቤ አገልግሎት
ሆቴል አገልግሎት
ፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት
ምግብ ዝግጅት
3 769
Repost from Addis Abeba Education Bureau
+1
የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ዛሬ ከሰዓት የ2018 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ተፈታኞችን ውጤት ይፋ ያደረገ ሲሆን ማለፊያ ውጤቱ 50% ለአካል ጉዳተኞች 45 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን መወሰኑን ገልጿል።
የትምህርት ቢሮው መረጃ በሚያሳየው መሰረት ለፈተና ከተቀመጡ 85 ሺሕ 737 ተማሪዎች መካከል 82 ሺሕ 193 (95.85%) የሚሆኑት 50 እና ከዚያ በላይ ማለፊያ ውጤት አምጥተዋል።
ከተፈታኞቹ መካከል 3 ሺሕ 544 የሚሆኑት ማለፊያ ውጤት አላመጡም።
የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 96.25 ሲሆን ይህን ያመጣውን አንድ ተማሪ ነው።
60 ተፈታኞች 93% ውጤት አምጥተዋል።
1 ሺሕ 316 ተፈታኞች 90% እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ታውቋል።
የዘንድሮው ውጤት ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ምን ይመስላል ?
በ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት 70 ሺሕ 525 ተፈታኞች፣ 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡት 62 ሺሕ 639 (88.8%) ሲሆኑ፣ 7 ሺሕ 886 ተፈታኞች ማለፊያ ውጤት አላመጡም ነበር።
የዘንድሮ የተፈታኞች ብዛት ከአምናው በ15 ሺሕ 212 የጨመረ ሲሆን፣ ማለፊያ ውጤት ያላመጡ ተፈታኞች ደግሞ፣ ከአምናው በ4 ሺሕ 342 ቀንሷል።
ዘንድሮ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 96.25 በአንድ ተማሪ ብቻ ሲሆን፣ በ2017 ዓ/ም ግን 113 ተማሪዎች 94% ውጤት አምጥተው ነበር።
በአንጻሩ፣ ዘንድሮ 90% እና በላይ ያመጡት ተፈታኞች 1 ሺሕ 316 ተማሪዎች ሲሆኑ፣ በ2017 ደግሞ ይህን ውጤት ያመጡት 712 ተማሪዎች ናቸው። በዚህም የዘንድሮው የ604 ብልጫ አለው።
በተያያዘ መረጃ፣ ዘንድሮ ተማሪዎቻቸውን ካስፈተኑ 669 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 441ዱ 100% ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል። እንዲሁም በከተማ ደረጃ ከ93% በላይ ከፍተኛ ውጤት ያመጡት 60 ተማሪዎች ናቸው።
3 769
+1
#Grade12
#NationalExam
የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆነ።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።
በዚሁ መሠረት በኦንላይን (Computer-based Testing (CBT) የሚፈተኑ ተፈታኞች በስድስት ዙር የሚፈተኑ ሲሆን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ይፈተናሉ። ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች የሚፈተኑ ይሆናል።
ፈተናውን በወረቀት የሚፈተኑ ተፈታኞች የተፈጥሮ ሳይንስ በሶስተኛ ዙር ላይ የሚፈተኑ ሲሆን የማህበራዊ ሳይንስ በአራተኛ ዙር በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚፈተኑ ይሆናል።
(ዝርዝሩን ከላይ ይመልከቱ)
@tikvahethiopia
3 769
ሰላም እንዴት ናቹ የመኪና ስምሪት ይህ ነው ከዚህ የሽፌሮቹ ስልክ በሠውስድ አድራሻቹ በመለዋወጥ ሰኞ ከሊቱ 11:00 ሰአት ፖሊስ ጣብያ መድረስ ይጠበቅባችዋል።የመኪና አስተባባሪ ሁናቹ በአግባቡ ሰው ወደ አማካይ ቦታ እንዲወጣ በአግባቡ ማስተባበር ይኖርባችዋል።
