es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር(አቡ ዓማር)

ኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር(አቡ ዓማር)

Ir al canal en Telegram

የአላህ  መልዕክተኛ (ﷺ)  እንዲህ  ብለዋል፦ (ከሰዎች መካከል የመልካም በር ከፋች የሆኑና የመጥፎ በር ዘጊዎች የሆኑ አሉ ፤ እንዲሁም ከሰዎች መካከል የሸር  በር ከፋች የሆኑና የመልካም በር ዘጊ የሆኑ አሉ። አላህ የመልካም በር መክፈቻ ቁልፍ በእጁ ላደረገለት ‘ጡባ’ አለለት ፤  አላህ  የመጥፎ  በር መክፈቻ  ቁልፍ  በእጁ  ላደረገለት  ‘ወይል’ አለለት።) [ኢብኑ ማጃህ (237) ዘግበውታል። 

Mostrar más
7 634
Suscriptores
Sin datos24 horas
+47 días
-2630 días
Archivo de publicaciones
🌿አዲስ ደርስ 📚መሳኢሉል ጃሂሊያ 🎙ቁጥር፡2 💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🕌 በኢማሙ ነወዊይ የሂፍዝ ማዕከል የተሰጠ። @ibnukedir

🌿አዲስ ደርስ 📚ረውደቱል አንዋር 🎙ቁጥር፡86 💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🕌 ቃሊቲ ነስር መስጂድ የተደረገ @ibnukedir

📚የቁርአን ተፍሲር ቁ፡263 📖ሱረቱል-አንከቡት          🎙ክፍል፡5 💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🕌  አቃቂ ቢላል መስጂድ የተሰጠ @ibnukedir

📤📤📤📤📤📤📤 🌿የጁምዓ ኹጥባ ቁ፡126 🔖መብቃቃት እና ፍሬዎቹ⁉️     💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🔻ሊደመጥ የሚገባ ወቅታዊ ኹጥባ! 💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር! 🕌  ቃሊቲ ነስር መስጂድ የተደረገ @ibnukedir

🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿 ጥቂት ነጥቦች ከልጆች አያያዝ ጋር 🔻 ሰባት ዓመት የሞላቸውን ልጆች ሶላት እንዲሰግዱ ማዘዝ ላይ ልንዘናጋ አይገባም። አስር ከሞላቸው ካልሰገዱ መቅጣት ይገባል። በጊዜ ያልተያዘ ነገር ኋላ ተራራ ከመውጣት በላይ ሊከብዳቸው ይችላል። ከተዋሃዳቸው ግን ከራሳቸው አልፈው ለሌላ ይተርፋሉ። 🔻ከልጆቻችን ጋር የተመጠነ አቀራረብ ሊኖረን ይገባል። አያያዛችን ጨካኝና አስበርጋጊ መሆን የለበትም። ይልቁንም እንደ ልጅ ብቻ ሳይሆን እንደ ጓደኛም ዘና ብለው የሚያማክሩን እንዲሆኑ ልናደርጋቸው ይገባል። በሌላ በኩል ምንም ቢያጠፉ፣ እንደፈለጉ ቢቀብጡም ቅጣት ቀርቶ ቁጣ እንኳ የማይከተላቸው ካደረግናቸው ይሄ ማዘን ሳይሆን ማጨማለቅ ነው። ልጆች እንግዳ የሚያከብሩ፣ ሌሎችን የማይበጠብጡ፣ ከትልቅ ሰው ፊት አደብ ያላቸው እንዲሆኑ መስራት ይገባል። 🔻ልጆች ቁርኣን እንዲቀሩ፣ ቢያንስ መሰረታዊ ኢስላማዊ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ትኩረት መስጠት ይገባል። ከዚህም ባሻገር ለሰው ህይወት ክብር ያላቸው፣ የሰው ሐቅ የሚፀየፉ እንዲሆኑ ማስተማር ጥሩ ነው። ይሄ በየ ጫካው ነፍስ እየነጠቀ፣ ሰው እያገተ ያለው፣ በየ ገበያው የሚያጭበረብረው፣ በየ ቢሮው ሰው የሚያጉላላውና የሚያንገላታው፣ ህዝብ የሚጨቁነው ባለ ሥልጣን ሁሉ በአብዛኛው አሳዳጊ የበደለው፣ ጤነኛ ተርቢያ ያላገኘ ስድ አደግ ነው። ልጆቻችን ነገ ሰው የሚያስለቅሱ እንዳይሆኑ ዛሬ አስተዳደጋቸውን እናሳምር። 🔻በልጅ አስተዳደግ ላይ መታየት ካለባቸው ነገሮች ውስጥ ሌላው ነጥብ አንዳንዴ ለልጆቻችን ያለንን ፍቅር ደበቅ ማድረጉ አስፈላጊ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ነው። በተለይ ልጆች ይህንን ስስ ስሜታችንን ላልተገባ አካሄድ የሚያውሉት ሲሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። የኛ መንሰፍሰፍ የሚያቀብጣቸውና የሚያንዘላዝላቸው እንዳይሆን አንዳንዴ ፍቅራችንን ደበቅ፣ ኮስተር፣ አስፈላጊ ሲሆን ቆንጠጥ፣ እንደ ሁኔታው ከዚያም ያለፈ አቀራረብ ሊኖረን ይችላል። 🔻ከምናደርጋቸው ጥረቶች ውስጥ መረሳት የሌለበት ወሳኝ ነጥብ ደግሞ ዱዓእ ነው። የምንደሰትባቸው እንጂ የምንከፋባቸው እንዳይሆኑ፣ በዱንያም ይሁን በኣኺራ ለኛም ለራሳቸውም የሚበጁ ሷሊሖች እንዲሆኑልን አላህ አዘውትሮ መለመን ይገባል። ✍IbnuMunewor https://t.me/ibnukedir

🌿አዲስ ደርስ 📚መሳኢሉል ጃሂሊያ ቁ፡1 🎙ቁጥር፡85 💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🕌 ቃሊቲ ነስር መስጂድ የተደረገ @ibnukedir

🌿አዲስ ደርስ 📚ረውደቱል አንዋር 🎙ቁጥር፡85 💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🕌 ቃሊቲ ነስር መስጂድ የተደረገ @ibnukedir

📚የቁርአን ተፍሲር ቁ፡262 📖ሱረቱል-አንከቡት          🎙ክፍል፡4 💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🕌  አቃቂ ቢላል መስጂድ የተሰጠ @ibnukedir

📤📤📤📤📤📤📤 🌿የጁምዓ ኹጥባ ቁ፡125 🔖እራስን ማጥፋት(መግደል)!     💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🔻ሊደመጥ የሚገባ ወቅታዊ ኹጥባ! 💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር! 🕌  ቃሊቲ ነስር መስጂድ የተደረገ @ibnukedir

🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿 ለመሆኑ መጨረሻችን ወዴት እየሄደ ነው? እስቲ ቆም ብለን ቤታችንን እንመልከት፡ ⛔️አባት ጥግ ይዞ ስልኩ ላይ ተጥዷል... ⛔️ እናት በበኩሏ ሌላ አለም ውስጥ ገብታለች... ⛔️ልጆች ደግሞ እያንዳንዳቸው በየስክሪኑ ስር ተቀብረዋል... ⛔️ቤት ውስጥ የሚሰማው ድምፅ የ«ኖቲፊኬሽን» እና የ«ቲክቶክ» ድምፅ ብቻ ሆኗል። አፍ ለአፍ ተጋጥሞ ማውራት፣ አብሮ መሳቅ፣ የውሎን ነገር መጠያየቅ ስለ ዲን መማማር የቀን ቅዠት ከሆነ ቆየ። ⛔️ስልክ አለምን አንድ አደረገ ይባላል... ቤተሰብን ግን ከአንድ ጣሪያ ስር ሆኖ አራርቋል ቀድሞ በነበረው ፍቅር፣ እና ጨዋታ  ቦታ የሞባይል ጨረርና ቅዝቃዜ ተተክቷል። 🌿ሀቢቢ! ስልክህን አንዴ አስቀምጠውና አጠገብህ ያለውን ውድ ቤተሰብህ ላይ አይንህን ትከል፤ ዛሬ ሳናወራቸው እና ሳናደምጣቸው ነገ በሞት ወይም በሌላ ምክንያት በሩቅ ስንናፈቃቸው እንዳንቆጭ! ዛሬውኑ እንጀምር፡ 🔻የምግብ  ሰአት ላይ ስልክ መጠቀም ይከልከል! 🔻ከመተኛታችን በፊት ቢያንስ 30 ደቂቃ ስልክ ዘግተን እንደ ቤተሰብ እንጨዋወት! 🔻በቀን ውስጥ ስልካችንን ከፍተን ሳይሆን ልባችንን ከፍተን አንዱ የሌላውን ውሎ ይወቅ! 🌿እስቲ እናንተስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አስተያየት አላችሁ? በ እናንተ ቤትስ የስልክ ሁኔታ እንዴት ይገለፃል?እርስ በእርስ ተወያዩበት ባረከላሁ ፊኩም ✍️የተወሰደ https://t.me/ibnukedir

🌿አዲስ ደርስ 📚ኪፋየቱል ሙተዓቢድ..... 🎙ክፍል፡27 💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🔻የመጨረሻ ክፍል! 🕌 በኢማሙ ነወዊይ የሂፍዝ ማዕከል የተሰጠ። https://t.me/ibnukedir

🌿አዲስ ደርስ 📚ረውደቱል አንዋር 🎙ቁጥር፡84 💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🕌 ቃሊቲ ነስር መስጂድ የተደረገ @ibnukedir

📚የቁርአን ተፍሲር ቁ፡261 📖ሱረቱል-አንከቡት          🎙ክፍል፡3 💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🕌  አቃቂ ቢላል መስጂድ የተሰጠ @ibnukedir

📤📤📤📤📤📤📤 🌿የጁምዓ ኹጥባ ቁ፡124 🔖ወንጀል የሚያስምሩ ሰበቦች!     💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🔻ሊደመጥ የሚገባ ወቅታዊ ኹጥባ! 💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር! 🕌  ቃሊቲ ነስር መስጂድ የተደረገ @ibnukedir

🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿 እኛ ብንሆን ኖሮስ! ~ ለኢማሙ አሕመድ የሆነ ሰው ስም ተነሳላቸው። 🌿 "እኔ ስለሱ መልካምን እንጂ አላውቅም" አሉ። 🍃"አንተ በሱ ላይ የምትናገረው እሱ ባንተ ላይ ከሚናገረው ይለያል" አላቸው አንዱ። (በክፉ ያነሳሀል ማለቱ ነው።) 🌿 ፈገግ ብለው "እኔ ስለሱ መልካምን እንጂ አላውቅም። ስለሚናገረው እሱ ያውቃል። የማላውቀውን እንድናገር ነው የምትፈልገው?" አሉ። ቀጥለውም እንዲህ አሉ፦ "ሳሊምን አላህ ይዘንላቸው። (ሳሊም የኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ልጅ ናቸው።) አንዴ ግመላቸው የሌላን ሰው ግመል ገፋች። ሰውየው በዚህን ጊዜ ለሳሊም፡ 'ክፉ ሽማግሌ ትመስለኛለህ!' አላቸው። 'አልራቅክም!' አሉት። (ልክ ነህ! እያሉት ነው። ኢማሙ አሕመድም ለራሳቸው ተመሳሳይ ነገር መጠቀማቸው ነው።) ምንጭ፦ [አልወረዕ ሊልመርወዚ፡ 197] 🔻እስኪ እራሳችንን በሳሊም ቦታ አድርገን እናስብ። ምን ይሆን ነበር ምላሻችን? አላሁል ሙስተዓን! 🔻እስኪ እራሳችንን በኢማሙ አሕመድ ቦታ አድርገን እናስብ። ምን ይሆን ነበር ምላሻችን? አላህ ይድረስልን። ~ ✍IbnuMunewor https://t.me/ibnukedir

🌿አዲስ ደርስ 📚ኪፋየቱል ሙተዓቢድ..... 🎙ክፍል፡26 💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🕌 በኢማሙ ነወዊይ የሂፍዝ ማዕከል የተሰጠ። https://t.me/ibnukedir

🌿አዲስ ደርስ 📚ረውደቱል አንዋር 🎙ቁጥር፡83 💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🕌 ቃሊቲ ነስር መስጂድ የተደረገ @ibnukedir

📚የቁርአን ተፍሲር ቁ፡260 📖ሱረቱል-አንከቡት          🎙ክፍል፡2 💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🕌  አቃቂ ቢላል መስጂድ የተሰጠ @ibnukedir

📤📤📤📤📤📤📤 🌿የጁምዓ ኹጥባ ቁ፡123 🔖የዱዓ አደብና አህካም     💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር 🔻ሊደመጥ የሚገባ ወቅታዊ ኹጥባ! 💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር! 🕌  ቃሊቲ ነስር መስጂድ የተደረገ @ibnukedir

🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿 🔖ለበጎ ሊሆን ይችላል ኢብኑ መዒን እንዲህ አሉ ፦ኢብኑ ዚያድ ለሶፍዋን ብኑ ሙሕሪዝ ሁለት ሺህ ዲርሀም እንዲስሰጠው አዘዘለት። ከተሰጠው በኋላ ግን ገንዘቡ ተሰረቀ። ሶፍዋንም ፦ “ምናልባት ለበጎ ሊሆን ይችላል” አለ። ቤተሰቦቹም፦ “ገንዘቡ ተሰርቆ እያለ ይህ እንዴት በጎ ሊሆን ይችላል?!” አሉት። ይህ ወሬ ለኢብኑ ዚያድ በደረሰ ጊዜ ሌላ ተጨማሪ ሁለት ሺህ ዲርሀም እንዲስሰጠው አዘዘ። ከዚያ በኋላ ያ የተሰረቀው ሁለት ሺህ ዲርሀም ተገኘ፤ አጠቃላይ ገንዘቡ አራት ሺህ ሆነለት። እውነትም መጥፋቱ ለበጎ ነበር። 📗 [አል-ቢዳያህ ወን-ኒሃያህ ](በትንሹ ተነካክቶ የተወሰደ) ✍IbnuMunewor https://t.me/ibnukedir