ግጥም
Open in Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Show more5 366
Subscribers
-124 hours
+437 days
+19130 days
Posts Archive
5 366
#የከበረ_የለም
ሁሉም እዩኝ እዩኝ ልውጣ ከአደባባይ
የሚለው ሰው በዝቶ ከነነውሬ ልታይ
ለዝና ለክብር ፈጥኖ ሲሽቀዳደም
ውርደቱን ይዘግናል የከበረ የለም
እውቀትን ፍለጋ በጥበብ ካልወጣ
በአቋራጭ ጎደና ከዝናው ቢወጣ
መልሶ ይወርዳል ቁልቁል ተንደርድሮ
ሁሉም አንቱ በሉኝ አዛዥ ነው ዘንድሮ
5 366
አጥብቄ እይዛለሁ ቀሚስሽን ጠፍሬ
እናቴ ባንቺ ነው የቆምኩኝ ጠንክሬ
አንቺን ሲነኩብኝ አምርሬ እቆጣለሁ
በእንባ በለቅሶዬ አትንኳት እላለሁ
ብርታት የማገኘው በጠረንሽ ናርዶስ
በክፉ የሚያይሽ ሁለት ዓይኑ ይፍሰስ
5 366
#የቀበጦች_ቀበጥ
አንድ ላም አለችኝ ከሰማይ መስክ ላይ
ማንም የማያልባት ወተቷንም አላይ
ባዶ ተስፋ ብቻ ወተትን የማትሰጥ
አለችኝ አንድ ላም የቀበጦች ቀበጥ
5 366
አንገቴ ጎንበስ በል ይለፍ ይኼ ግዜ
ለሁሉም መልስ አለው ለዛሬው ትካዜ
ነገ ሌላ ቀን ነው ዛሬን አይወክልም
ሀዘን መከራውም በዚህ አይቀጥልም
ቅዝምዝሙ ይለፍ ገንበስ ልበልና
ጨለማው ሲገፈፍ ብርሃን ነውና
5 366
#ሸማኔ_የለንም
ጥበበኛ ጠፍቶ በጥበበኛ ሀገር
አስማምቶ አሻጋሪ በእውነተኛ ፍቅር
ፈታይ ሳይቸግረን ድርና ማግ ሞልቶ
ሸማኔ የለንም ሀገር ሰሪ አስማምቶ
5 366
#አልተኛም_ከእንግዲህ
በህልም ዓለም መጥተሽ
በሁኔ ከማጣሽ
አትምጪ ልንገርሽ
ድሮም ስቃዬ ነሽ
ስተኛ አይሻለለሁ
ስነቃ አጣሻለሁ
አንቺ የጠዋት ጤዛ
መጥተሽ መሄድ በዛ
በህልሜ እየመጣሽ መንገዴን ከምስት
አልተኛም ከእንግዲህ አንቺን ላለማየት።
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 366
ይነጋል ያልነው ቀን መልሶ ጨለመ
ይሻለዋል ያልነው ይብሱን ታመመ
ማንጋጠጥ ይሻላል ለሰማዩ ጌታ
የምድሩስ ተክኗል በውሸት እስክስታ
ሀገር ታማ ታማ መድሀኒቷ ጠፍቶ
እህ እህ ነው ዛሬም ሁሉም ሰው ተከፍቶ
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
5 366
ከሀይማኖት በላይ እምነት ስጠኝና
ጌታዬ ሰው ልሁን ልነሳ እንደገና።
የስናፍጭ ታህል ቅንጣት እምነት ቢኖር
ተራራው መከራ በተናደ ነበር።
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
