ግጥም
Open in Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Show more5 366
Subscribers
-124 hours
+437 days
+19130 days
Posts Archive
5 366
"#እኔም_ልቤን_ልስጥሽ"
ከልብሽ ከሆነ በፍቅር ተመርጠሽ
እኔነቴን እንኪ እራሴንም ልስጥሽ
ለንዋይ ከሆነ ለገንዘብ አምልኮ
ልብሽ ልብ ሳይል በጥቅም ተማርኮ
ከእኔ ድሃ ጎጆ ከእኔ ምስኪን መንደር
ገንዘብን አምልኮ አይኖርም መከበር
ልብ እንጂ ቀለቡ ፍቅር እንጂ መጠጡ
ዙፋኑን አይለቅም በጥቅም ለመጡ!!!
ቀለቡ ፍቅር ነው ያሳደገኝ መንደር
አንቺ ትብሽ አንተ ሰክኖ መነጋገር
ስለዚህ ልንገርሽ ቢገባሽ ባይገባሽ
ፍቅርን ይዘሽ ግቢ እኔም ልቤን ልስጥሽ
5 366
❤️ዙፋኑ ልብ ነው❤️
ልብ ካልታሰረ በፍቅር ሰንሰለት
በጣቶቻቸው ላይ ቢሰካ ቀለበት
ይወልቃል ሲላላ የፍቅር ማገሩ
ዙፋኑ ልብ ነው ዋናው ቁምነገሩ
#GOOD_NIGHT_I_LOVE_YOU_ALL
5 366
ትኩረት ማረግ አለብሽ
መምህርት: የኢራቅ ፕሬዝዳንት ማን ነው ?
.
አቤ: አላቀውም
.
መምህርት: ጥናት ላይ ትኩረት ማድረግ አለብህ !
.
አቤ: ቲቸር ጥያቄ ልጠይቅሽ
.
መምህርት: ይቻላል
.
አቤ: ፍቅርተን ታውቂያታለሽ ?
.
መምህርት: አላውቃትም ምነው
.
አቤ: ባልሽ ላይ ትኩረት ማረግ አለብሽ !
5 366
#መቼ_ስጠን_አልንህ?
እኛን የናፈቀን ጥላቻን ሰባሪ
ፍቅርን አንግሦ ሀገር አሻጋሪ
ከዘር ዛር የራቀ እውነተኛ መሪ
ለፍትሕ አድልቶ ሰላም ዘማሪ
መቼ ስጠን አልንህ? ጌታ ነገር ሰሪ
ቂም እያረገዘ የሰው ዘር ቆጣሪ
ወይስ ከዙፋኑ ከወንበሩ ማርጀት
የታላቅ ህዝብ ሀገር ሁሌ መሪ ማጣት
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
5 366
/// " አፋቅሮ ያስማማን "///
በጥላቻ ኖረን ዘርን ከምንቆጥር
አፈር ያስማማናል ሞተን እንፋቀር
መግባባት ከአቃተን በህይወት እያለን
ሞታችን ይምጣና አፋቅሮ ያስማማን።
አሁን በዚህ ዘመን መኖሮ ለማን ሊበጅ
የተጣላ ሁሉ በአፈር ፍቅር ይወዳጅ።
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
5 366
#ችግር_የለም_አትበል
የሀገር ካዝና ጎድሎ ያንተ ስለሞላ
ሚሊዮን ጦም አድሮ ግለሰብ ቢበላ
እንዴት ይመዘናል በጥቂቶች ጥጋብ
ይፋለስ የለም ወይ በብዙዎች ራብ
ህዝብ ተቸግሮ አንተ ሽህ ብትከምር
አይሆንህም ጤና አትዝረፍ ከሀገር
ችግር የለም አትበል ቤትህ ስለሞላ
ሚሊዮን ጦም ያድራል እራቱን ሳይበላ
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
5 366
#አብረህ_አትርመጥመጥ
ከትርምስ ዓለም ጋጋታ ከሞላው
እየተጋፋፋ ከሚዘላለፈው
ጥቂት ፈቀቅ በል እራስህን አድምጥ
የአንተነህ ዋጋ በሌሎች አይዋጥ
ጡዘቱ ከናረው ጠብቆ ከከረረው
መናገር ብቻ እንጂ ማድመጥ ከሰለቸው
ጥቂት ፈቀቅ በል ጥቂት እፎይ ምረጥ
ከሚተራመሰው አብረህ አትርመጥመጥ
ከልብህ ዋጋ ጋር እራስህን አድምጥ
ከተፈጥሮ ጋራ ሀሳብ ተለዋወጥ!!!
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
5 366
#አልቻለም_ሊወለድ
የእናት ውለታዋን መጣኝ ቃል ፍለጋ
ሊቃውንት ተማክረው ቢሉ ቆላ ደጋ
አዲስ ዜማ ቅኔ ገላጭ ቃል የላቸው
እናት ከማለት ውጭ መጥራት ተሳናቸው
ሽህ ዘመናት መጥቶ ሽህ አዋቂ ቢሄድ
ከእናት በላይ ቃላት አልቻለም ሊወለድ
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
5 366
መኖር ትርጉም ካጣ ከተብከነከነ
ከህይወት ተኳርፎ እዲው ከመነነ
አለም ባዶ ሁና ከቆረጥክ ተስፋ
ከጎንህ ሰው ካጣህ አዝነህ ስትከፋ
ዛሬ ነገ አደለም አለው አዲስ ተስፋ
ብትወድቅም ጠንክረህ ለመነሳት ልፋ
የእውነት ቀን ላንተ አለ የብርሀን መንገድ
በመውደቅም መሀል መነሳትን ልመድ
ሰው እንደው ጥፍር ነው የሰውነት ባዳ
ስሞ የሚሸጥህ ልክ እንደ ይሁዳ።
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
5 366
" ነጎደ!!! በረረ!!! "
ዙፋኑ ተሰርቶ በቂም ውርስ ጥላቻ
መሪው ቢቀያየር ወጥ ላይሆን ጉልቻ
የሚጣፍጥ ፍትህ የሚያረካ ሰላም
ሁሌም እንዳማረን የመቻቻል ቀለም
እንኳንስ በጥንቱ ታሪክ በሰነደው
በእኛ እድሜም ብዙ አየን ወጥቶ በወረደው
ስንቱን ስንሾም ስንሽር ትውልድ ተገብሮ
መኖር እያቃተን አብሮ ተከባብሮ!!!
ከጥንቱም እያነስን የጥንቱን እየናቅን
ሙት ወቃሽ ሙት አንጋሽ ሁለት ሀሳብ ይዘን
ይኸው የእኛ እድሜ እንኳን ነጎደ በረረ
ለውጥም ሳናመጣ ቅሉም ተሰበረ!!!
ስንት መሪ ቆጥረን ስንት ትውልድ ቀብረን
ዛሬም የማንማር መላው የጠፋን ነን።
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
5 366
#ማን_ያስተምረናል?
ገድሎ መፈክርን ተክነንበታል፣
ታግሶ ማለፍን ማን ያስተምረናል?
ምህረት እንጂ ለሰው የቸገረው ዛሬ፣
ገድሎ ሸላይማ መቺ አጣች ሀገሬ።
የበደለን ምረን ይቅርታ አለማወቅ፣
ውርሳች ነው ዛሬም በግፍ መተላለቅ።
https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0
