uz
Feedback
ግጥም

ግጥም

Kanalga Telegram’da o‘tish

በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor

Ko'proq ko'rsatish
4 850
Obunachilar
+1424 soatlar
+537 kunlar
+21330 kunlar
Postlar arxiv
#መነሳቴ_ላይቀር ❤ ከትላንት ውድቀቴ ከአለፈው ተምሬ ልበል ዳዴ ዳዴ ችዬ ልቁም በእግሬ ጠላቴ አትደሰት ወድቆ ቀረ ብለህ የእኔ ከስር መቅረት አንተን ለማይጠቅምህ በእግዚአብሔር እርዳታ መነሳቴ ላይቀር አብዝተህ አትሳቅ እንባባል ይቅር!!! https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0

#የእኔና_አንቺ_ታሪክ ከሽህ ጦር አለቃ ከሽህ መውዜር ጓንዴ የእኔና አንቺ ፍቅር ይማርካል ውዴ ❤ ዘርሽን ሳልጠይቅ ዘሬን ሳታጣሪ በልቤ ውሰጥ ገብተሽ ፍቅርን ስታበሪ በሰውነት ሚዛን አክብረሽ ስትከብሪ ስወድሽ ስቶጅኝ ሳኮራሽ ስትኮሪ! ከሽህ ታንክ ጋጋታ ከሽህ መድፍ ማጓራት እኔና አንቺ ውዴ ማርኮናል ሰውነት ❤❤ ከዘር ዛር እርቀን በልባችን ጀልባ ቀጥፌ ስሰጥሽ የፍቅርን አበባ ሰውነቴ ገዝቶሽ ሰው መሆንሽ ገብቶኝ እኔነቴ ማርኮሽ አንችነትሽ ገዝቶኝ!!! በእቅድ ከሚመራ ከብዙ ጦር ልቆ የእኔና አንቺ ታሪክ ይነበባል ደምቆ https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0

እያስተዋልን እንጂ የጊዜውን ነገር እናውራ ካልንማ ስንት አለ የሚነገር። ያየነውን ሁሉ በሆድ ይፍጀው ዜማ በማለፋችን ነው የኖርነው እኛማ። https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0

#እኔነት_ሲለካ በዝምታ ቅኔ በማስተዋል ዜማ ከግርግር እርቀት በብቻ ከተማ እራሴን ፍለጋ ውስጤን ስፈትሸው ለካስ ባዶ በርሜል ጫጫታ ብቻ ነው በተፈጥሮ ሚዛን እኔነት ሲለካ መመለስን ትቶ መጠየቅ ሲተካ ሁሉም ከንቱነቱን ይረዳል ከእራሱ ከስጋው ባሻገር ሲታወሰው ነፍሱ https://t.me/+HsixAeVq6tJlNTI0