cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Mitike.W Legal Buffet

legal materials for all

Show more
Advertising posts
313
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ይግባኝ ማስፈቀጃ/ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድ የሚቀርብ አቤቱታ #በሕጉ የተቀመጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድ የሚቀርብ አቤቱታ አንድ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈበት ምክንያት በቂ መሆኑን ሲረዳ ይግባኙ እንዲቅርብ ሊፈቅድ እንደሚገባ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 326/1/ ስር ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ፍ/ቤቱ የቀረበለት ምክንያት በቂ መሆን አለመሆኑን በአግባቡ ሊመረምረው ይገባል፡፡ በእርግጥ በቂ ምክንያት የሚባሉት ነገሮች ሕጉ ዘርዝሮ ያላስቀመጣቸው በመሆኑ ለመወሰን አስቸጋሪ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም የምክንያቱ በቂ መሆን አለመሆን በእያንዳንዱ ጉዳይ ከሚቀርቡ ፍሬ ነገሮች ጋር ተገናዝበው ሊመዘኑ ይገባል፡፡ ሰ/መ/ቁ. 38145 ቅጽ 8፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 326/1/ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ መሠረት ለአንድ ፍርድ ቤት መዝገብ ሹም የተሰጠው ሥልጣን ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ማለፍ አለማለፉን በመመልከት ይግባኝ መዝገቡ እንዲከፈት ማድረግ ሲሆን ይግባኙ ጊዜውን ጠብቆ ያልቀረበ ከሆነ ማመልከቻውን መመለስ፣ ማመልከቻው የተመለሰበት ወገን የይግባኝ ጊዜው ያለፈበት ሕጋዊ ምክንያት ካለው ማስፈቀጃ አቤቱታውን በማቅረብ ይኸው ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለማቅረብ እንዲፈቀድለት ራሱን የቻለ አቤቱታ አቅርቦና ይህ መዝገብ ተከፍቶ ጉዳዩ ለችሎት ቀርቦ ችሎቱ የይግባኝ ማስፈቀጃውን በመመርመር በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 መሠረት ተገቢ ነው ያለውን ትእዛዝ የሚሰጥበት ነው፡፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 325 እና 326 ድንጋጌዎች ጋር አንድ ላይ ሲነበቡ የመዝገብ ቤት ሹም ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለችሎት እንዲቀርብ የመፍቀድ ስልጣን የሌለው መሆኑን የሚያሳዩ ሲሆን ፋይሉ ተከፍቶ ቀርቦ ከሆነም ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ ይግባኙ የቀረበው ጊዜው ከአለፈ በኋላ ነው በማለት መዝገቡን ከመዝጋት የሚከለክለው አይደለም፡፡ ሰ/መ/ቁ. 61843 ቅጽ 11፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 324-326 የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎች ድምጽ ገጽ ተገኘ #የሕግመረጃ #አለሕግ #Alehig 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/lawsocieties 👉Facebook Page 👈 https://www.facebook.com/lawsocieties/ 👉YouTube 👈 https://youtube.com/@Lawsocieties
Show all...
አለሕግ🔵AleHig

Alternative legal enlightenment(ALE)አለሕግ Affordable&Accessible Legal Expertise ለጠበቃ 0920666595 አማራጭ የሕግ እውቀት፣ ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ የሕግ ማብራርያ፣ መሰረታዊ የሕግ እውቀት ያገኛሉ

https://linktr.ee/alehig

[email protected] @LawsocietiesBot

1
የካርታ ይምከንልኝ ጥያቄ መጀመሪያ በአስተዳደር አካል በአዋጅ ቁጥር 1183/12 መሠረት መታየት ያለበት እንጂ ለፍርድ ቤት ቀጥታ የሚቀርብ አይደለም። በመጨረሻው የአስተዳደር ውሳኔ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ሰው የተሰጠው ውሳኔ እንዲከለስለት ቅሬታውን ለከፍተኛ ፍ/ቤት ማቅረብ እንደሚችል ባልታተመ የሰበር ውሳኔ ተሰጥቷል።
Show all...
በይርጋ የማይታገዱ የፍትሀብሄር ጉዳዬች 🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑♨️♨️♨️ የይርጋ መሰረታዊ ዓላማ ማንኛውም በህግ በግልፅ የተደነገገ መብትና ግዴታ በህጉ በተወሰነው ወይም በተገደበው ጊዜ ውስጥ ስልጣን ላለው አካል እንዲቀርቡ ግዴታን በማስቀመጥ መብቴ ተጣሰብኝ የሚል ወገን ዳተኛ ሳይሆን በትጋት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን አንዳንድ ጉዳዬች ከንብረቶቹ ልዩ ባህሪና የመንግስት ፖሊሲ አንፃር ህግ አውጪው በይርጋ እንዳይታገዱ አድርጎ ያስቀመጣቸው የፍትሀብሄር ጉዳዬች አሉ። ከእነዚህ መካከል፦ #የመፋለም ክስ ( petitory action) ♨️♨️♨️🛑🛑🛑🛑♨️ ለባለሀብቱ የባለቤትነት መብት ከሚሰጣቸው መብቶች መካከል ንብረቱ ያለ እርሱ ፈቃድ ከህግ ውጪ በሌላ ሰው ወይም ሀይል ከተወሰደ ንብረቱን ካለበት ድረስ በመከታተል የማስመለስ ወይም የመፋለም መብት አንዱ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1206 ድንጋጌ ያስረዳል፡፡ ባለሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን” በሚል ርዕስ ስር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1192 የተመለከተው በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት በአስር ዓመት የጊዜ ወሰን /ይርጋ/ ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ ያመላከተ ሲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ግን አያሳይም፡፡ ድንጋጌው የሚንቀሳቀስ ንብረትን የባለሀብትነት ጥያቄ የጊዜ ገደብ ካስቀመጠ በኋላ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ቀሪ መሆን በዝምታ ያለፈው ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት በሌለው በፍ/ብ/ህግ አንቀፅ 1845 ስር የተመለከተው ተመሳሳይ የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚ እንደሆን ተፈልጎ ካለመሆኑ በላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሚንቀሳቀስ ንብረት በተለየ ሁኔታ የዘላቂነት ባህሪ ያለው እና ከትውልው ወደ ትውልድ የሚተላለፍ በመሆኑ የባለሀብትነቱ መብት ቀሪ የሚሆነው በይርጋ ሳይሆን በሌሎች ሁኔታዎች( አንቀፅ 1168....) ይሆን ዘንድ ተፈልጎ የተቀመጠ ድንጋጌ መሆኑን እንገነዘባለን። በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፋለም ክስ (petitory action) በይርጋ ቀሪ አይሆንም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/መዝ/ቁ 43600) N.B= ይህ ሲባል ግን ከውርስ፣ ከሽያጭ፣ ከስጦታና ከሌሎች ውሎች በመነጨ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ክርክር ይርጋ የለውም ማለት የሚቻል ሳይሆን ለጉዳዩ አግባብነት ባላቸው ህጎች በተቀመጡ የይርጋ ጊዜዎች የሚስተናገዱ ይሆናል። #ህገ ወጥ ውል (unlawful contrat) ♨️🛑🛑🛑🛑♨️♨️♨️🛑 እንድ ውል የፀና ውል ለመሆን መሟላት ከሚገባው አንዱ ነጥብ ውሉ ህጋዊ በሆነ ጉዳይ ላይ የተመሰረተ መሆን የሚገባው እንደሆነ የፍ/ብ/ህግ 1678 ይደነግጋል። አንድ ውል ህገ ወጥ ውል ነው የሚባለው ደግሞ ተዋዋዬቹ የተዋዋሉበት መሰረታዊ ጉዳይ ዓላማ በመሰረታዊና ሞራላዊ ይዘቱ ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት በማድረግ መብትና ግዴታ እንዲፈጥሩበት በህግ ያልተፈቀደ ወይም በህግ ክልከላ የተደረገበት ሆኖ ሲገኝ ነው። አንድ ውል የተመሰረተበት መሰረታዊ ጉዳይ (object of contract) በህግ ክልከላ የተደረረበት በሆነ ጊዜ ውሉ በህግ ፊት እንደሌለና ምንም አይነት ህጋዊ ውጤት የማያስከትል (null and void contrat) እንዲሁም ችግሩን በማስተካከል ህጋዊ ውጤት እንዲኖረው ማድረግ የማይቻል ነው። ለምሳሌ፦ የመሬት ሽያጭ ውል፣ በሰው ለመነገድ የተደረግ ውል፣ ወንጀል ለመፈፀም የተደረገ ውል...... ህገ ወጥ የሆነውን ውል ውድቅ ለማድረግ ደግሞ በህጉ የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ መቃወሚያ ሊቀርብ የማይችልና ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ በይርጋ የሚታገዱ አይደሉም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት/ሰ/መዝ/ቁ 43226) N.B= ይህ ሲባል ግን የህጉን መስፈርት ያላሟሉ ውሎች (illegal contract) ከህገ ወጥ ውል በተለየ ሁኔታ ታይተው የይርጋ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ የሚሆንባቸው መሆኑን መረዳት ይገባል። #የመንግስትን መሬት የማስመለስ ክስ ♨️♨️🛑🛑🛑♨️♨️🛑 ግለሰቦች በፌደራሉ እና በክልሉ መንግስት በወጡ የገጠር መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር አዋጅ በሚደነግጉት መሰረት በህጋዊ መንገድ ሳይሰጣቸው ከህግ ውጪ የወል ወይም የመንግስትን መሬት ይዘው መቆየታቸው እና የመሬቱ ባለይዞታ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ማግኘታቸው የመሬቱ ህጋዊ ባለይዞታ ሊያደርጋቸው አይችልም። በወረራ የተያዘ የመንግስት መሬትም ይርጋ የሌለው መሆኑን የአብክመ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀፅ 55 በግልፅ ያስቀምጣል። በመሆኑም ከህግ ውጭ በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶችን መኖራቸውን ሲረዳ መሬት አስተዳደርም ሆነ የመንግስት ወኪል የሆነ አካል መሬቶቹን ለማስመለስ የሚያቀርበው ክስ በይርጋ የሚታገድ አይደለም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት/ሰ/መዝ/ቁ 93013 እና 96203 ያልታተሙ) #በህገ ወጥ መንገድ የተያዘ የግለሰብ ይዞ መሬት 🛑🛑🛑🛑🛑🛑♨️♨️ ከላይ እንደተመለከትነው ህገ ወጥ ውልን መሰረት አድርጎ የግለሰብን መሬት በያዘ ሰው ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ የሌለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በአብክመ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀፅ 55 መሰረት ህጉ በማይፈቅድበት መንገድ በሀይልም ሆነ በህገ ወጥ አግባብ የገጠር መሬትን ይዞ የተገኘ ግለሰብ ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ የለውም። N.B= በህገ ወጥ መንገድ የሚለው ሀሳብ በህግ ተቀባይነት በሌለው አኳኋን የያዘን በሚመለከት እንጂ የህጉን መስፈርት ባላሟላ ውል ወይም ተግባር (illegal contrat) አማካኝነት የተያዘን መሬት የሚመለከት አይደለም። ምክንያቱም መሬቱን የያዘው በህጉ በተፈቀደ የውል ተግባር ሆኖ የሚፈለገውን ፎርማሊቲ ወይም መስፈርት አለማለቱ ብቻ አያያዙ ህገ ወጥ ነው የሚያስብል ስላልሆነ ነው። #የአደራ ውል 🛑🛑🛑🛑♨️♨️ አደራ ተቀባይ በአደራ የሚጠብቀውን ዕቃ የሚመልስበት የጊዜ ገደብ በውል ተመልክቶ ከሆነ ይህ ጊዜ ሲያበቃ ዕቃውን መመለስ ያለበት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2781(1) የተመለከተ ሲሆን በውል ላይ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ ከሌለ ግን አደራ ሰጪው እንደጠየቀ ወዲያውኑ እንደሚመለስ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2989(1) ስር ተመላክቷል። ከእነዚህ ድንጋጌዎች ለመረዳት የሚቻለው አደራ ተቀባይ ዕቃውን የሚመልስበት የጊዜ ገደብ ከሌለ በቀር አደራ ሰጪው በአደራ እንዲቀመጥ የሰጠው ዕቃ ያለምንም የጊዜ ገደብ በማንኛውም ጊዜ እንዲመለስለት መጠየቅ የሚችል መሆኑን ነው። #የውርስ ሀብት ክፍፍል 🛑♨️♨️♨️♨️🛑 ወራሾች ተለይተው እና የውርስ ሀብቱ ድርሻ ታውቆ ነገር ግን ክፍፍል ሳይደረግ የቆየን የውርስ ሀብት በማናቸውም ጊዜ መጠየቅ እንደሚችልና በይርጋ የሚታገድ እንዳልሆነ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1060 እና ተከታዬቹ ድንጋጌዎች መረዳት ይቻላል። እንዲሁም ከውርስ ሀብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የውርስ ሀብቱን በእጁ አድርጎ በመገልገል ላይ ያለ ተከራካሪ የሆነ ወራሽ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የውርስ ንብረት በጋራ ይዞ ከቆየ ሰው ላይ የውርስ ድርሻዬን ልወቅ ወይም ይለይልኝ ጥያቄ በይርጋ ይታገዳል የሚባልበት አግባብ የለም። @ethiolawtips Join
Show all...
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 208865 በማኅበር ተደራጅቶ የቤት መሥሪያ ቦታ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ እያሉ በሥራ ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወር ከመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበር አባልነት የሚያሰርዝ ስላለመሆኑ የሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም፡፡
Show all...
የመንግስት (የቀበሌ/የኪራይ) ቤቶችን በተመለከተ የፌደሬሽን ምክር ቤት የሰበር ውሳኔን በመሻር ውሳኔ አስተላለፈ። ከዚህ ቀደም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት "በሠ/መ/ቁ. 189707 እና በሠ/መ/ቁ. 228002" ቤትን ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት አያጎናጽፍም ሠ/መ/ቁጥር 228002  አንድን ቤት ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት የማያጎናጽፍ በመሆኑ እንዲሁም ቤቱ የመንግስት ቤት መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌሉበት ሁኔታ በተቋሙ የመረጃ ስርአት ቅጽ 008 በቀበሌ ቤትነት መመዝገቡ ብቻ ቤቱ በመንግስት የተወረሰ የቀበሌ ቤት ነው ሊያስብለው አይችልም በሚል ውሳኔ ወስኖ የነበረ ሲሆን ይህንን ውሳኔ የኢፌድሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ባደረገው 6ተኛ የፓርላማ ዘመን 3ተኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤው በህገ መንግስት አጣሪው በቀረበለት መሰረት በመ/ቁጥር 108/15 የሠ/መ/ቁ .189707 ህገመንግስታዊነት አጣርቶ ውሳኔውን ሽሮታል። ስለሆነም የመንግስት ቤትን ለረጅም ጊዜ ከአዋጅ 47/67 በኋላ ይዞ ያስተዳድር የነበረው "ኪራይ ቤቶች" ሁለቱ ቅፆች ቅፅ 003 እና 004 ባይኖሩትም የቤቱ ባለይዞታነት የመንግስት ሆኖ ይቀጥላል። ዝርዝር የውሳኔውን ፍሬ ነገር ከላይ ከተያያዘው ሰነድ ይመልከቱ 👉 Join Us On #Whatsapp 👌 https://whatsapp.com/channel/0029Va9MhjZ4inonPxTuff3M 👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn 👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn 👉 @tebekasamuel 👉 @tebeka #Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ጠበቃ #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma #law #construction አዲስ አበባ ኢትዮጵያ 🇪🇹 ሳሙኤል ግርማ የሕግ አማካሪና ጠበቃ ☎️ +251-911-190-299 https://t.me/+gd2cs_m2f4IyOWRk @SAMUELGIRMA
Show all...
👍 3
ቤትን ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት አያጎናጽፍም ሠ/መ/ቁጥር 228002 - አንድን ቤት ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት የማያጎናጽፍ በመሆኑ እንዲሁም ቤቱ የቀበሌ / የመንግስት / ቤት መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌሉበት ሁኔታ በተቋሙ የመረጃ ስርአት ቅጽ 008 በቀበሌ ቤትነት መመዝገቡ ብቻ ቤቱ በመንግስት የተወረሰ የቀበሌ /የመንግስት ቤት ነው ሊያስብለው አይችልም። በአዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሶ ለረጅም ግዜ በመንግስት እጅ የነበረ ቤትን በሚመለከት በስህተት አላግባብ ያለህጋዊ ምክንያት ተሰጥቷል የተባለው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የመከነና በመንግሰት ባለቤትነት የሚታወቅ ስለመሆኑ በተገለጸበት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት መንግስት የወረሰው መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌለበት ቤቱን የመንግስት ንብረት አያሰኘውም። @samuelgirma @tebekasamuel @tebeka 👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn 👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn አዲስ አበባ ኢትዮጵያ መስከረም 2016 #Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ጠበቃ #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba የቀበሌ ቤት የመንግስት ቤት የተወረሰ ቤት #samuelgirma #law @SAMUELGIRMA
Show all...
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 216608 ጥቅምት 03 ቀን 2015 ዓ/ም በአብላጫ ድምፅ በሰጠው ውሰኔ ላይ የቀረበ አጭር አስተያየት ( ከሰለሞን እምሩ) በዚህ መዝገብ በተያዘው ክርክር አመልካቹ ቤት ገዢ ሲሆን ተጠሪዎቹ ደግሞ ቤት ሻጮች ናቸው፡፡ታህሳስ 23 ቀን 2014 ዓ/ም በውል አዋዋይ ፊት በተደረገ ውል አመልካቹ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት ከተጠሪዎች ላይ  በብር 600,000 (ስድስት መቶ ሺ ብር) ገዝቶታል፡፡ ከዚህ የቤቱ ዋጋ ውስጥ አመልካች ለተጠሪዎች ብር 440,000 (አራት መቶ ሺ ብር) ከፍሎ ቤቱንና ሰነዶቹን ተረክቦ ካርታ ማሰራቱ ተረጋግጧል፡፡ ሻጮች የሆኑት ተጠሪዎች  ታህሳስ 23 ቀ2010 ዓ/ም በውል አዋዋይ ፊት ቤቱን በብር 600,000 (ስድስት መቶ ሺ ብር) ለመሸጥ ተስማምተን ብር 440,000 (አራት መቶ አርባ ሺ ብር) የተቀበልን ቢሆንም በውል አዋዋይ ፊት ውል ካደረግን በኃላ ጥር 01 ቀን 2015 ዓ/ም ይህንኑ ቤት በተመለከተ የመንደር ውል አድርገናል፡፡ በዚህ የመንደር ውል ላይ የቤቱ ዋጋ ብር 1,300,000 (አንድ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺ) ብለን ተስማምተናል፤ በመሆኑም በመንደር ውሉ በተመለከተው ዋጋ መሰረት ቀሪ ብር 860,000 ሊከፈለን ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡ ጉዳዩ በየደረጃው ሲታይ ቆይቶ በመጨረሻ ፍርድ የሰጠው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ  ችሎት በርዕሱ ላይ በተጠቀሰው መዝገብ ቁጥር እና ቀን በሰጠው ፍርድ ምንም እንኳ በውል አዋዋይ ፊት በተደረገው ውል ቤቱን በብር 600,000 (ስድስት መቶ ሺ ብር) ለመሻሻጥ የተስማሙ ቢሆንም ከዚህ ውል በኃላ በመንደር ባደረጉት ውል ላይ የቤቱን ዋጋ ብር 1,300,000 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺ ብር) እንዲሆን ተስማምተዋል፡፡ ገዢው (አመልካች) የመንደር ውሉን ክዶ ስላልተከራከረ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 36887 (ቅፅ 10 ) በሰጠው አስገዳጅ ትርጉም መሰረት የመንደር ውሉ ሕጋዊ ውጤት አለው፣ በመሆኑም በመንደር ውሉ ላይ በተመለከተው ዋጋ መሰረት አመልካች ቀሪውን የቤትን ዋጋ ብር 860,000 (ስምንት መቶ ስልሳ ሺ ብር) ይክፈል በማለት በውል አዋዋይ ፊት በተደረገው ውል ላይ የተመለከተውን የቤቱን ዋጋ ትቶ በመንደር ውሉ በተመለከተው ዋጋ መሰረት ቀሪ ክፍያ ይከፈል በማለት በአብላጫ ድምፅ ወስኗል፡፡ በአስተያየት ሰጪው እምነት ይህ ውሳኔ ሕግን የተከተለ ነው ብዬ ለመቀበል ተቸግሬያለሁ፡፡ ጭብጡ  የመንደር ውሉ የመታመኑ ወይም ያለመታመኑ ጉዳይ አይደለም፡፡ ሰበር ሰሚው ችሎት ፍርዱን ለመደገፍ የተጠቀመበት በመ/ቁ 36887 (ቅፅ 10 ) የተሰጠው ውሳኔ የጠቀሰውም ያለቦታው ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ምክንያቱም በሰበር መ/ቁ 36887 (ቅፅ 10) ውሳኔ በተሰጠበት ጉዳይ ለክርክሩ መነሻ ሆኖ የቀረበው አንድ ውል ብቻ ነው፡፡ ይህም ውል በመንደር የተደረገ ሆኖ በሌላኛው ወገን እስካልተካደ ድረስ በተዋዋዮቹ መካከል ውጤት ሊሰጠው ይገባል ተብሎ አቋም የተወሰደበት ውሳኔ ነው፡፡ አሁን በተያዘው ጉዳይ ግን ለክርክር የቀረበው አንድ የመንደር ውል ብቻ ሳይሆን ዋጋን አስመልክቶ ቀደም ብሎ ከመንደር ውሉ በፊት ልዩ ፎርም ተከትሎ የተደረገ ማለትም በፅሁፍና በአዋዋይ ፊት በፅሁፍ የተደረገ ውል ቀርቦአል፡፡ ጭብጡ መሆን የነበረበት  የመንደር ውሉ ታምኗል? ወይስ አልታመነም? ሳይሆን ተፈፃሚ ሊደረግ የሚገባው በየትኛው ውል ላይ የተመለከተው ዋጋ ነው? የሚለው መሆን ነበረበት፡፡ አመልካች ቀሪ ክፍያውን መክፈል ያለበት በውል አዋዋይ ፊት በተደረገው ውል ላይ በተመለከተው ዋጋ መሰረት ነው? ወይስ በኃላ በመንደር ባደረጉት የሽያጭ ውል ላይ በተመለከተው ዋጋ ነው? የሚለውን ጭብጥ ለመመለስ አግባብነት ያለው የፍተሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1722 እንጂ 1723 አይደለም፡፡ ውልን ስለመለወጥ (variations)  አስመልክቶ  የተደነገገው የፍ/ብሔር ሕግ ቁጥር 1722 "ዋናውን ውል የመለወጥ ጉዳይ ለዚሁ ውል በተደነገገው አጻጻፍ (ፎርም) መሰራት አለበት" ይላል፡፡ በእንግሊዘኛው “ A contract made in a special form shall be varied in the same form” በሚል ተመልክቷል፡፡ አሁን በተያዘው ጉዳይ አመልካችና ተጠሪ ልዮ ፍርም ተከትለው ማለትም በውል አዋዋይ ፊት በፅሁፍ ባደርጉት ውል የቤቱ ዋጋ ብር 600,000 (ስድስት መቶ ሺ ብር) ብለው ተስማምተዋል፡፡ ይህን አስቀድመው የተዋዋሉበትን ዋጋ ለመቀየር ከፈለጉ ውሉ የተደረገበትን ተመሳሳይ ፎርም ተከትለው ማለትም ውል አዋዋይ ፊት ቀርበው በሚያደርጉት የፅሁፍ ውል ዋጋውን ከሚቀይሩ በቀር በመንደር ባደረጉት ውል ቀደም ሲል በውል አዋዋይ ፊት የተስማሙበትን ዋጋ ለመቀየር የሚያደርጉት ስምምነት በፍተሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1722 መሰረት ሕጋዊ ተቀባይነት አለው ብዬ አላምንም፡፡ በመሆኑም የሰበር ሰሚው ችሎት አብላጫው ድምፅ አግባብነት ያለውን ጭብጥና ሕግ በመጥቀስ መወሰን ሲገባው አግባብነት የሌለውን ጭብጥና ከጉዳዩ ጋር ተመሳሳይነት የሌለው በሰበር መ/ቁ 36887 (ቅፅ 10) የተሰጠውን አስገዳጅ ውሳኔ በመጥቀስ በውል አዋዋይ ፊት ስምምነት የተደረገበትን ዋጋ ትቶ በኃላ በመንደር ውል ላይ የተመለከተውን ዋጋ መሰረት አደርጎ የሰጠው ውሳኔ ሕጋዊ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ ይህ ውሳኔ በኃላ ብዙ መዘዝ ሊያመጣ ይችላል የሚል ስጋትም አሳድሮብኛል፡፡ ሰዎች ታክስን ለመሸሽ እያሉ በመንደር ውል ከፍ ያለ ዋጋ በውል አዋዋይ ፊት ደግሞ ዝቅ ያለ ዋጋ እያደረጉ እንደሚስማሙ ይታወቃል፡፡  የሰበሩ ውሳኔ ይህንን አሰራር በዘወርዋራ እየደገፈው እንዳይሆን እሰጋለሁ፡፡ የልዩነቱ ሀሳቡ በይበልጥ ሕጉን የተጠጋ ይመስለኛል፡፡ እናነተስ ምን ታስባላችሁ?  እንወያይበት፡፡ የሰበሩን ሙሉ ውሳኔ ስላያያዝኩት ዝርዝሩን ተመልከቱና የተለየ ሀሳብ ካላችሁ ብንሰማው፡፡ ይለናል ሰለሞን እምሩ ምን ትላላችሁ
Show all...