SECONDARY SCHOOL NEWS/2ኛ ደረጃ ት/ቤት መረጃ Odeeffannoo Mana b/saa Sadarkaa 2ffaa
Open in Telegram
secondary school is government school in Addis Ababa ,Ethiopia which is located around UNESA near ODA bus highway to TuluDimitu. The school strives for educational quality.📚🖊🖍✏️🇪🇹
Show more1 628
Subscribers
No data24 hours
-77 days
-5030 days
Posts Archive
+6
ደራርቱ ቱሉ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተማራዎች ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል፣የሂሳብና እንግሊዝኛ ትምህርቶች ስትራቴጂዎች፣ በ2ኛ ሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ጽብረቃና 2ኛ ሩብ ዓመት የስራ ግምገማ ላይ ከመምህራን ጋር እጅግ በጣም መግባባት የተሞላበት ውይይት በ11/04/2017ዓ.ም ተካሂዷል።
AddisWalta በኢትዮ ጃፓን ህዳሴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ23/03/2017ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ9-10ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በተካሄደ የፈጠራ ስራ ውድድር 2ኛ በመውጣት ተሸላሚ የሆነው እጅግ አስደማሚ ከሆነው ተማሪ ሀብታሙ ደምሴ ጋር የተደረገ አስተማሪ ቆይታ🙏🙏🙏
ለሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤቶች ር/መ/ራን ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘሩ መምህራን ነገ ማለትም 15/02/2017 ዓ.ም የማህደረ ተግባር ምዘና የሚመዘኑ ሰለሆነ የተደራጀ መረጃቸውን ይዘው ከቀኑ 8 ሰአት በተመደቡበት የምዘና ጣቢያ እንዲገኙ አድርጉ፡፡
Repost from Ethiopian Digital Library
የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ
በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።
ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፦
በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot
የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል። #MoE
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
I am inviting you to download telebirr SuperApp, register and make a transaction to get reward. https://superapp.ethiomobilemoney.et:38443/customer/mgm/index0902.html#/?notoolbar=true&CampaignId=MGM1635518748044544&inviterId=978602734720004&language=en&time=Sept-03-2024-Dec-02-2024
Repost from Ministry of Education Ethiopia
ማስታወቂያ
የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫን ይመለከታል
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ መሙላት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
መስከረም 2017
2. ማስታወቂያ
በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች
በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ እና በRemedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
መስከረም 2017
የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያጋጥም ጊዜ መደረግ የሚገባቸዉ የጥንቃቄ እርምጃዎች
👉 ከቤት ውጭ ከሆኑ - ከዛፎች፣ ከሕንፃዎች፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።
👉በቤት ውስጥ ከሆኑ - በበር መቃኖች፣ በኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።
👉 አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።
👉መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ- የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም መሆናቸውን ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
