cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopian Digital Library

በዚህ ቻናል 👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን 👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን 👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን 👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን 👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና 👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ! For any comments: @ethiodlbot

Show more
Advertising posts
64 358Subscribers
+1924 hours
+1457 days
+52930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

👍 30 13 2💯 2
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ " ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው " ብለዋል። በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ሲሉ አሳውቀዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፤ ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል። ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል። የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል። #MoE @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Show all...
👍 11👏 2 1💯 1
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር ይሰጣል2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ በርካቶች ጥያቄ አድርሰውናል። የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል። (የዩንቨርሲቲ መውጫ ፈተና ሰኔ መጀመሪያ ከተሰጠ በኋላ የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ይሰጣል) በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁም ይታወሳል፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡ @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Show all...
👍 53🤷 7🤔 6 4👏 4❤‍🔥 2 2💯 1
👍 23 9💯 4 2👏 1
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሥር የሚገኙት ዘንዘልማ እና ሰባታሚት ካምፓሶች በፀጥታ ችግር ምክንያት መዘጋታቸውን ሪፖርተር ዩኒቨርሲቲውን በመጥቀስ ዘግቧል በሁለቱ ካምፓሶች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ የግብርና፣ የጤና፣ የጂኦሎጂ እና የዲዛስተር ማኔጅመንት ተማሪዎች የፀጥታው ችግር እስኪቀረፍ ከተማ ውስጥ ባሉ ካምፓሶች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማድረጉን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ብርሃኑ ገድፍ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዘንዘልማ እና በሰባታሚት ካምፓሶች ውስጥ ይማሩ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች ከተማ ውስጥ ያሉ ካምፓሶች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው፡፡ ዘንዘልማ እና ሰባታሚት ካምፓሶች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የተኩስ ድምፅ በየጊዜው እንደሚሰማ የገለፁት ም/ፕሬዝዳንቱ፤ በተማሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከአንድ ወር በፊት ወደተለያዩ የተቋሙ ካምፓሶች እንዲዘዋወሩ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ በከተማዋ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች ውስጥ በቂ ቦታ በመኖሩ ተማሪዎቹ ምንም ዓይነት መጉላላት ሳይደርስባቸው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው ብለዋል፡፡ አሁን ላይ ከሁለቱ ካምፓሶች ውጪ በሌሎች ካምፓሶች ላይ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንደሌለ ም/ፕሬዝዳንቱ ገልጸው፤ በባህር ዳር ከተማ ካለው አንፃራዊ ሰላም አኳያ በርካታ ተማሪዎች ምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡ ከሁለቱ ካምፓሶች ውጪ አለመረጋጋቱ የተሻሻለ ቢሆንም፤ አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰሙ ተማሪዎቹ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ የዘንድሮ ተመራቂዎች የምረቃ ቀን መቼ እንደሆነ እስካሁን እንዳልተነገራቸውም አክለዋል፡፡ #ሪፖርተር @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Show all...
👍 17 3😢 1😭 1
የሪሚዲያል ፈተና የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ፈተና ከሰኔ 3 -14 በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል! #Remedial @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Show all...
👏 19👍 15 4🙏 4💯 3 2
ሚያዝያ 15 (April 23) ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን የዓለም መጽሐፍ ቀን በየዓመቱ ሚያዝያ 15 ይከበራል። ሚያዝያ 15 ለዓለምአቀፍ የመጽሐፍ ቀንነት የተመረጠበት ምክንያት የዊልያም ሼክስፒር እና ስፔናዊው የታሪክ ጸሐፊ ኢንካ ጋርሲላሶ ዴ ላ ቬጋ የሞቱበት ቀን በመሆኑ እንደመታሰቢያ እንዲሆን ነው። በእዚህ ቀን በዓለምአቀፍ ደረጃ በተለይ ወላጆች ለልጆቻቸው መጻሕፍትን በስጦታ መልክ በመስጠት ያከብሩታል። @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Show all...
👍 15 4👏 4🤬 1
👍 26😭 11🙊 7 3😢 3❤‍🔥 2😁 2😡 2
በ2016 ዓ.ም 8.8 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር በፀጥታ ችግር ምክንያት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች 8.8 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት 8,977 ትምህርት ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 6,483 ሙሉ በሙሉ ዝግ መሆናቸውን በሚኒስቴሩ 'ትምህርትን በአደጋ ማስቀጠል' ባለሙያ ንጋቱ አበበ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ ሚኒስቴሩ እና የክልል ትምህርት ቢሮዎች በጋራ በመሆን የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማስቀጠል ጥረት ቢያደርጉም፤ አሁንም በተለያዩ ቦታዎች በቀጠሉት ግጭቶች ምክንያት ችግሩን ለመፍታት አስቸጋሪ እንደሆነ ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማስቀጠል የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ባለሙያው ጥሪ አቅርበዋል። @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library
Show all...
👍 15😢 6💯 2 1😁 1