en
Feedback
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

Open in Telegram

ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

Channel መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese (@rodas9) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 39 803 subscribers, ranking 1 556 in the Religion & Spirituality category and 867 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 39 803 subscribers.

According to the latest data from 06 September, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by -80 over the last 30 days and by 7 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 22.92%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 8.39% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 9 119 views. Within the first day, a publication typically gains 3 337 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 94.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 07 September, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

39 803
Subscribers
+724 hours
+167 days
-8030 days

Data loading in progress...

Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
September '26
September '26
+54
in 0 channels
August '26
+178
in 1 channels
Get PRO
July '26
+210
in 0 channels
Get PRO
June '26
+288
in 0 channels
Get PRO
May '26
+181
in 0 channels
Get PRO
April '26
+167
in 2 channels
Get PRO
March '26
+62
in 0 channels
Get PRO
February '26
+55
in 2 channels
Get PRO
January '26
+66
in 1 channels
Get PRO
December '25
+512
in 5 channels
Get PRO
November '25
+44
in 0 channels
Get PRO
October '25
+354
in 0 channels
Get PRO
September '25
+1 441
in 4 channels
Get PRO
August '25
+199
in 2 channels
Get PRO
July '25
+75
in 3 channels
Get PRO
June '25
+139
in 4 channels
Get PRO
May '25
+201
in 2 channels
Get PRO
April '25
+269
in 3 channels
Get PRO
March '25
+133
in 1 channels
Get PRO
February '25
+353
in 3 channels
Get PRO
January '25
+840
in 5 channels
Get PRO
December '24
+657
in 7 channels
Get PRO
November '24
+576
in 4 channels
Get PRO
October '24
+498
in 1 channels
Get PRO
September '24
+582
in 4 channels
Get PRO
August '24
+55
in 2 channels
Get PRO
July '24
+93
in 0 channels
Get PRO
June '24
+51
in 1 channels
Get PRO
May '24
+178
in 3 channels
Get PRO
April '24
+415
in 2 channels
Get PRO
March '24
+295
in 0 channels
Get PRO
February '24
+163
in 0 channels
Get PRO
January '24
+240
in 7 channels
Get PRO
December '23
+265
in 3 channels
Get PRO
November '23
+101
in 0 channels
Get PRO
October '23
+55
in 1 channels
Get PRO
September '23
+2 683
in 0 channels
Get PRO
August '23
+65
in 0 channels
Get PRO
July '23
+51
in 0 channels
Get PRO
June '23
+121
in 0 channels
Get PRO
May '23
+216
in 0 channels
Get PRO
April '23
+282
in 0 channels
Get PRO
March '23
+94
in 0 channels
Get PRO
February '23
+172
in 0 channels
Get PRO
January '23
+700
in 0 channels
Get PRO
December '22
+575
in 0 channels
Get PRO
November '22
+767
in 0 channels
Get PRO
October '22
+898
in 0 channels
Get PRO
September '22
+205
in 0 channels
Get PRO
August '22
+50
in 0 channels
Get PRO
July '22
+28
in 0 channels
Get PRO
June '22
+63
in 0 channels
Get PRO
May '22
+305
in 0 channels
Get PRO
April '22
+458
in 0 channels
Get PRO
March '22
+92
in 0 channels
Get PRO
February '22
+117
in 0 channels
Get PRO
January '22
+827
in 0 channels
Get PRO
December '21
+575
in 0 channels
Get PRO
November '21
+90
in 0 channels
Get PRO
October '21
+49
in 0 channels
Get PRO
September '21
+3 928
in 0 channels
Get PRO
August '21
+81
in 0 channels
Get PRO
July '21
+126
in 0 channels
Get PRO
June '21
+143
in 0 channels
Get PRO
May '21
+409
in 0 channels
Get PRO
April '21
+951
in 0 channels
Get PRO
March '21
+879
in 0 channels
Get PRO
February '21
+1 726
in 0 channels
Get PRO
January '21
+1 310
in 0 channels
Get PRO
December '20
+34 029
in 0 channels
Date
Subscriber Growth
Mentions
Channels
08 September0
07 September+15
06 September+7
05 September+3
04 September+9
03 September+7
02 September+13
01 September0
Channel Posts
34. 🇪🇨 የቅዱስ ሩፋኤል ፓሪሽ (San Rafael Parish) — ኢኳዶር፤ ይፋዊ የአካባቢው መረጃ ስሙ በሊቀ መልአኩ ክብር መሰጠቱን በቀጥታ ያረጋግጣል። 35. 🇬🇹 የቅዱስ ሩፋኤል ፔትሳል ማዘጋጃ ቤት (San Rafael Pétzal) — ጓቲማላ፤ አጠቃላይ የማዘጋጃ ቤቱ ስም የሊቀ መልአኩን ስም ይይዛል። 36. 🇳🇮 የቅዱስ ሩፋኤል ዴል ኖርቴ ማዘጋጃ ቤት (San Rafael del Norte) — ኒካራጓ፤ ቅዱስ ሩፋኤል በይፋ የከተማዋ ጠባቂ ነው። 37. 🇳🇮 የቅዱስ ሩፋኤል ዴል ሱር ማዘጋጃ ቤት (San Rafael del Sur) — ኒካራጓ፤ ቅዱስ ሩፋኤል ዋና የአካባቢው ጠባቂ መሆኑ በመንግሥታዊ የባህል ምንጭ ተመዝግቧል። ✨ ከጥናቱ የሚታየው ❤ የቅዱስ ሩፋኤል ስም ከከተማ አልፎ ለማዘጋጃ ቤት፣ ዲስትሪክት፣ ወንዝ፣ ተራራ፣ በረሃ፣ የድንጋይ ሰንሰለት፣ ደሴት፣ የጂኦሎጂ ንብርብር እና የከተማ አርማ ድረስ ደርሷል። በተለይ በሰሜን አሜሪካ USA 🇺🇸 ዩታ ውስጥ የቅዱስ ሩፋኤል ወንዝ (San Rafael River) → የቅዱስ ሩፋኤል ስዌል (San Rafael Swell) → የቅዱስ ሩፋኤል ሪፍ (San Rafael Reef) → የቅዱስ ሩፋኤል በረሃ (San Rafael Desert) → የቅዱስ ሩፋኤል ግሩፕ (San Rafael Group) ተብሎ አንድ ስም በጂኦግራፊና በጂኦሎጂ ውስጥ መስፋፋቱ ልዩ ነው። ከሁሉ አስገራሚው ግን 🇫🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (Saint-Raphaël) በፈረንሳይ ያለው ክብሩ ነው፤ ስሙ ብቻ ሳይሆን በከተማዋ አርማ ላይ ሩፋኤል ሊቀ መልአክ ከጦቢያ ጋር ጦቢያ ዓሣ ይዞ በይፋ ተሥሏል። ❤ በሀገራችን በኢትዮጵያ በስሙ የተሰየሙ በጣም ጥቂት አብያተ ክርስቲያናት እንጂ በስሙ የተጠሩ ተራራዎች፣ ወንዞች፣ ሀገሮች እስካኹን በግሌ አልሰማኹም። ወደፊት ግን እንደሚኾን አምናለኹ። እመኛለኹም። 👉 በአስተያየት መስጫው ላይ ቅዱስ ሩፋኤልን በፍቅር አወድሱት https://t.me/+xN518gdGKvswNzE0 ✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (ጳጉሜን 2 ሌሊት ተጻፈ)

2
🌍 በቅዱስ ሩፋኤል ስም የተሰየሙ 37 ከተሞች፣ ወንዞች ✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ በዓሉን በደመቀ መልኩ ጳጉሜን 3 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምናከብረው የስሙ ፍቺ “ፈውሰ እግዚአብሔር” የተባለው የፈውስ መልአክ፣ የመንገደኞች ጠባቂ፣ የጋብቻ መልአክ የቅዱስ ሩፋኤል ዐለም ዐቀፍ ክብሩን በጥቂቱ በበዓሉ ዕለት አስነብባችኋለሁ፡፡ 1. 🇫🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (Saint-Raphaël) — ፈረንሳይ፤ በቫር ግዛት የሚገኝ ከተማ። የከተማዋ ይፋዊ ታሪክ ስሟን ከሊቀ መልአኩ ሩፋኤል ጋር ያያይዛል፤ በአርማዋም ቅዱስ ሩፋኤልና ጦቢያ ይታያሉ። 2. 🇺🇸 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — ካሊፎርኒያ፣ አሜሪካ፤ ከተማዋ በ1817 ስትመሠረት ቅዱስ ሩፋኤል ሕሙማንን የሚፈውስ መልአክ መኾኑን በማሰብ ከተማው በስሙ ይጠራል። 3. 🇵🇭 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — ቡላካን፣ ፊሊፒንስ፤ የማዘጋጃ ቤቱ ይፋዊ ታሪክ ለቅዱስ ሩፋኤል ክብር ስሙን እንደሰጡት ያረጋግጣል። 4. 🇵🇭 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) የመልአክ በዓል ከተማ — ቡላካን፤ ይህችው ከተማ በየዓመቱ የመላእክት በዓል በቅዱስ ሩፋኤል ክብር ታከብራለች። 5. 🇨🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — ሄሬዲያ፣ ኮስታ ሪካ፤ በ1818 በቅዱሳን ስሞች ዕጣ የአካባቢዎች ስም ሲመረጥ የቅዱስ ሩፋኤል ስም ደረሰው። ይህን የማዘጋጃ ቤቱ ይፋዊ ታሪክ ያረጋግጣል። 6. 🇨🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — ቫዝኬዝ ዴ ኮሮናዶ፣ ኮስታ ሪካ፤ የዲስትሪክቱ ስም ለሊቀ መልአኩ ሩፋኤል ክብር እንደተሰጠ ተመዝግቧል። 7. 🇨🇷 ቅዱስ ሩፋኤል አሪባ (San Rafael Arriba) — ዴሳምፓራዶስ፣ ኮስታ ሪካ፤ የአካባቢው መለያ ስም ከሩፋኤል ጋር በጥብቅ የተያያዘ ሲሆን ሊቀ መልአኩ የአካባቢው ጠባቂ ነው። 8. 🇨🇴 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — አንቲዮኪያ፣ ኮሎምቢያ፤ በ1871 ስሙ ሲሰጥ መሥራቾቹ ሩፋኤል ሊቀ መልአክ “ሐኪማቸውና መሪያቸው” እንዲኾን ባላቸው እምነት እንደነበር ታሪኩ ይመዘግባል። 9. 🇵🇪 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — አምቦ፣ ሁዋኑኮ፣ ፔሩ፤ የማዘጋጃ ቤቱ የ2023 ዓመታዊ ሰነድ በግልጽ፣ “ራፋኤል” የሚለው ስም ከሊቀ መልአኩ ሩፋኤል እንደመጣ ይገልጻል። 10. 🇪🇨 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — ካርቺ፣ ኢኳዶር፤ የክልሉ ይፋዊ የቱሪዝም መረጃ፣ “የቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) ስም ለሊቀ መልአኩ ሩፋኤል ክብር ተሰጠ” ብሎ ይገልጻል። 11. 🇬🇹 ቅዱስ ሩፋኤል ፔትሳል (San Rafael Pétzal) — ሁዌዌቴናንጎ፣ ጓቲማላ፤ “ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael)” የሚለው የስሙ ክፍል ለሩፋኤል ሊቀ መልአክ ክብር የተሰጠ ነው። 12. 🇳🇮 ቅዱስ ሩፋኤል ዴል ኖርቴ (San Rafael del Norte) — ኒካራጓ፤ “የሰሜኑ ቅዱስ ሩፋኤል” ማለት ነው። ሩፋኤል ሊቀ መልአክ የከተማው ጠባቂ ሲሆን የእርሱ በዓል በይፋ ይከበራል። 13. 🇳🇮 ቅዱስ ሩፋኤል ዴል ሱር (San Rafael del Sur) — ኒካራጓ፤ “የደቡቡ ቅዱስ ሩፋኤል” ማለት ነው። የኒካራጓ መንግሥታዊ የባህል መረጃ ሩፋኤል ሊቀ መልአክ የማዘጋጃ ቤቱ ጠባቂ መሆኑን ያረጋግጣል። 14. 🇨🇱 ቅዱስ ሩፋኤል ዴ ሮሳስ (San Rafael de Rozas) — ቺሊ፤ የዛሬዋ ኢያፔል ከተማ ታሪካዊ ስም ሲሆን የቅዱስ ሩፋኤል ስም በከተማዋ ታሪክና ምልክት ውስጥ ቀርቷል። 15. 🇫🇷 የቅዱስ ሩፋኤል (Saint-Raphaël) ከተማ አርማ — ፈረንሳይ፤ ይህ ቦታ ብቻ አይደለም፤ የከተማዋ ይፋዊ አርማ ሩፋኤል ሊቀ መልአክን ከጦቢያ ጋር ያሳያል። ይህ እጅግ ጠንካራ የሕዝብ ክብር ምስክር ነው። 16. 🇺🇸 የቅዱስ ሩፋኤል ተራሮች (San Rafael Mountains) — ካሊፎርኒያ፣ አሜሪካ፤ የተራራ ሰንሰለት ሲሆን ጥንታዊ የካሊፎርኒያ የቦታ ስሞች ጥናት ከ“ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መልአክ” ጋር ያያይዘዋል። 17. 🇺🇸 የቅዱስ ሩፋኤል ወንዝ (San Rafael River) — ዩታ፣ አሜሪካ፤ በዩታ የሚፈስ ወንዝ፤ የ“ቅዱስ ሩፋኤል ወንዝ (San Rafael)” ተብሎ ይጠራል። 18. 🇺🇸 የቅዱስ ሩፋኤል ስዌል (San Rafael Swell) — ዩታ፣ አሜሪካ፤ ትልቅ የጂኦሎጂ ከፍታና የድንጋይ አወቃቀር ነው። የዩታ ጂኦሎጂ ተቋምም “ቅዱስ ሩፋኤል ስዌል (San Rafael Swell)” በሚል ይመዘግበዋል። 19. 🇺🇸 የቅዱስ ሩፋኤል ሪፍ (San Rafael Reef) — ዩታ፣ አሜሪካ፤ በቅዱስ ሩፋኤል ስዌል (San Rafael Swell) ምሥራቃዊ ጠርዝ የሚገኝ ረጅም የድንጋይ አወቃቀር በስሙ ይጠራል። 20. 🇺🇸 የቅዱስ ሩፋኤል በረሃ (San Rafael Desert) — ዩታ፣ አሜሪካ፤ የቅዱስ ሩፋኤል ወንዝ (San Rafael River) እና ስዌል አካባቢ ያለ በረሃዊ ክልል ይገኛል። 21. 🇺🇸 የቅዱስ ሩፋኤል ግሩፕ (San Rafael Group) — ዩታና የአሜሪካ ደቡብ ምዕራብ፤ የቦታ ስሙ እስከ ጂኦሎጂያዊ የድንጋይ ንብርብር ሳይንሳዊ ስም ድረስ ገብቷል። 22. 🇵🇭 የቅዱስ ሩፋኤል ወንዝ አካባቢ (San Rafael River) — ቡላካን፣ ፊሊፒንስ፤ የከተማው የሩፋኤል በዓል የውሃ ሰልፍ በዚህ የወንዝ አካባቢ እንደሚከናወን የማዘጋጃ ቤቱ ይገልጻል። 23. 🇵🇭 የቅዱስ ሩፋኤል ደሴት (San Rafael Island) — ኩዌዞን፣ ፊሊፒንስ፤ በጂኦግራፊ መዝገቦች በ“ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael)” ስም የተመዘገበ ደሴት ነው። 24. 🇨🇴 የቅዱስ ሩፋኤል ደሴት (San Rafael Island) — ቦሊቫር፣ ኮሎምቢያ፤ “ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael)” በሚል የተመዘገበ ደሴት ነው። 25. 🇧🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (São Rafael) — ሪዮ ግራንዴ ዶ ኖርቴ፣ ብራዚል፤ ዛሬ በይፋ የተመዘገበ ማዘጋጃ ቤት ነው። 26. 🇧🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (São Rafael) — ሳኦ ፓውሎ፣ ብራዚል፤ በሳኦ ፓውሎ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ዲስትሪክት ነው። 27. 🇧🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (São Rafael) — ሳልቫዶር፣ ብራዚል፤ “ቅዱስ ሩፋኤል (São Rafael)” የሚባል የከተማ አካባቢ አለ። 28. 🇻🇪 ቅዱስ ሩፋኤል ዴል ሞሃን (San Rafael del Moján) ቬንዙዌላ፤ በዙሊያ ግዛት ያለ ከተማ፤ ሩፋኤል ሊቀ መልአክ በአካባቢው ታሪካዊ ክርስቲያናዊ ስያሜ ውስጥ ይታያል። 29. 🇻🇪 ቅዱስ ሩፋኤል ዴ ኦሪቱኮ (San Rafael de Orituco) — ቬንዙዌላ፤ በጓሪኮ ክልል የሚገኝ ከተማ። 30. 🇲🇽 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — ሜክሲኮ፤ “ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael)” የሚባሉ በርካታ ከተሞችና ሰፈሮች አሉ። 31. 🇧🇴 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — ቦሊቪያ፤ በተለይ በሳንታ ክሩዝ ክልል የ“ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael)” ስም ያላቸው ሰፈሮችና አካባቢዎች አሉ። 32. 🇦🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (San Rafael) — መንዶዛ፣ አርጀንቲና፤ ትልቅ ከተማና ዲፓርትመንት። የሩፋኤል ስም በከተማዋ ሃይማኖታዊና የሀገረ ስብከት ሕይወት በጥልቅ የተቀመጠ ነው። 33. 🇵🇪 የቅዱስ ሩፋኤል ዲስትሪክት (San Rafael District) — ፔሩ፤ ይፋዊ የፔሩ መንግሥት ሰነድ ራሱ የዲስትሪክቱን ስም በቀጥታ ከሩፋኤል ሊቀ መልአክ ጋር ያያይዛል።
1 262
3
+1
No text...
5 176
4
ያስገረመኝ ግርዶሹ በሑት ♓ Pisces = 12ኛው የዞዲያክ ምልክት ነው፤ ግርዶሹም በኢትዮጵያ የተከሰተው በ12ኛው ወር — ነሐሴ ውስጥ ነው። ውሃ፣ ስሜት፣ ሕልም፣ ውስጣዊ እውቀት (intuition)፣ ርኅራኄ፣ መንፈሳዊነት፣ መልቀቅና የአንድ ዑደት ፍጻሜ ጋር ይያያዛል። ስለዚኽ በተለያየ ቦታ ከውሃ መድረቅ ወይም ከውሃ መጥለቅለቅ ጋርም ሊያያዝ ይችላል።
10 473
5
🌌 ✦ 🌕 ✦ 🌍 ✦ ☀️ ✦ 🌑 ✦ 🌌 🌸ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
10 338
6
🌕🌑 በዓመቱ የ2018 ዓ.ም. የመጨረሻዋ ሙሉ ጨረቃ የሚታይ ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ በኢትዮጵያ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ 🔭 ሳይንሳዊ፣ 📖 መጽሐፍ ቅዱሳዊና 🇪🇹 የኢትዮጵያ ሥነ ፈለክ እይታዬ 💥 ባለፈው ዓመት 2017 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የዓመቱ መጨረሻ የመጨረሻዋ ሙሉ ጨረቃ ጳጉሜን 2 ከምሽቱ 2 ሰዓት ሙሉ የጨረታ ግርዶሽ በአድናቆት አይተናል። 🌓 በዚህም 2018 ዓ.ም በድጋሚ የነሐሴ 22 ማለዳ (ሊነጋጋ) በ2018 ዓ.ም. የመጨረሻዋ ሙሉ ጨረቃ ዕለት ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ (Partial Lunar Eclipse) ይታያል። በተለይ ይህ ግርዶሽ የሚያስደንቀው በከፍተኛው ደረጃ ጨረቃዋ ሙሉ በሙሉ ሳትጋረድ እስከ 96% ገደማ የሚሆነው ክፍሏ በምድር ዋና ጥላ ውስጥ መግባቱ ነው። 🌓 ለአንባብያን በተራ ቁጥር ጥቂት ለመጻፍ ያህል:- 🌍 1. የጨረቃ ግርዶሽ ምንድን ነው? ☀️ ፀሐይ 🌍 ምድር 🌕 ጨረቃ በአንድሮሜዳ መጽሐፍ ላይ በስፋት እንደተጻፈው የጨረቃ ግርዶሽ የሚፈጠረው ምድር በፀሐይና በጨረቃ መካከል ስትገባ ነው። ፀሐይ ብርሃኗን ወደ ጨረቃ ትልካለች፤ ነገር ግን ምድር በመካከል ስትገባ የምድር ጥላዋ በጨረቃ ላይ ያርፋል። 🌑 የምድር ጥላ ኹለት ዋና ክፍሎች አሉት፦ 🔸 Penumbral Shadow ደብዛዛው የውጭ ጥላ 🔸 Umbral Shadow ጥቁሩና ዋናው ጥላ ጨረቃ ከፊል ክፍሏን ወደ Umbra ስታስገባ Partial Lunar Eclipse ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ ይባላል። ስለዚኽ በስፋት ለማወቅ የኢትዮጵያ የከዋክብት ሊቃውንት የተራቀቁበትን "ትርጓሜ ሚጠተ ብርሃናት ዘሔኖክ" መጽሐፍ አንብቡ። 🇪🇹 2. የዚህ ግርዶሽ መጀመሪያውን ከኢትዮጵያም ማየት ይቻላል። 🌘 ዛሬ ሊነጋጋ በኢትዮጵያ ሰዓት ሌሊት 10:23 ወይም በፈረንጆች 4:23 አካባቢ Penumbral ግርዶሽ ይጀምራል። 🌑 ሊነጋጋ 11:33 ወይም (5:3 አካባቢ የሚታየው ከፊል ግርዶሽ ይጀምራል። 🌅 12:17 ጠዋት (6:17) ጠዋት አካባቢ ጨረቃ በአዲስ አበባ ትጠልቃለች። ስለዚህ በኢትዮጵያ የምናየው የግርዶሹን መጀመሪያ ክፍል ብቻ ነው፤ የግርዶሹ ዓለም ዐቀፍ ከፍተኛ ደረጃ ሲደርስ ጨረቃዋ በአዲስ አበባ ከአድማስ በታች ትሆናለች። 👁️ የሚመከረው የመመልከቻ አቅጣጫ፦ ምዕራብ ደቡብ ምዕራብ ⛰️ ሕንፃና ተራራ ያልጋረደው የምዕራብ አድማስ ያለው ከፍ ያለ ቦታ የተሻለ ነው። 🌑 ይህ ግርዶሽ ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ (Total Lunar Eclipse) አይደለም። ነገር ግን ጨረቃዋ በጣም ጥልቅ ምድር ጥላ ስለምትገባ፣ በከፍተኛው ደረጃ 96% ገደማ የሚሆነው የጨረቃ ዲስክ በምድር ዋና ጥላ ውስጥ ይሆናል። 🌕➡️🌖➡️🌗➡️🌘 በመሆኑም በዓይን ሲታይ ወደ ሙሉ ግርዶሽ በጣም የቀረበ ይመስላል። 🔴 4. “የደም ጨረቃ” ለምን ትባላለች? በጨረቃ ግርዶሽ ጊዜ ጨረቃ አንዳንድ ጊዜ ቀይ፣ መዳብማ ወይም ብርቱካናማ መልክ ልትይዝ ትችላለች። ይህ የሚፈጠረው ብርሃን በምድር ከባቢ አየር ሲያልፍ ነው። 🌍 የምድር ከባቢ አየር አጭር ሞገድ ያለውን ሰማያዊ ብርሃን በብዛት ይበትናል፤ ቀይና ብርቱካናማ ብርሃን ግን ወደ ምድር ጥላ ውስጥ ተጣምሞ ሊደርስ ይችላል። ይህ በሳይንስ Rayleigh scattering ከሚባለው የብርሃን መበተን ጋር የተያያዘ ነው። 🌅 ፀሐይ ስትጠልቅ ሰማዩ ቀይ የሚመስለውና በጨረቃ ግርዶሽ ጨረቃ ቀይ የምትመስለው ተዛማጅ የብርሃን ሂደት ነው። 📖 5. ጨረቃ፣ ፀሐይና ከዋክብት በመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ፀሐይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን በተደጋጋሚ ይጠቅሳል። «“እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን አደረገ፤ ታላቁን ብርሃን ቀንን እንዲገዛ፥ ታናሹንም ብርሃን ሌሊትን እንዲገዛ።” ✠ ዘፍጥረት 1፥16» እንዲሁም፦ «“ለምልክቶችና ለዘመናት፥ ለዕለታትና ለዓመታትም ይሁኑ።” ✠ ዘፍጥረት 1፥14» ይህ ክፍል የሰማይ ብርሃናት ቀን፣ ዘመንና ዓመትን ለመለየት እንደሚያገለግሉ ያሳያል። 🌕 6. “ጨረቃ ወደ ደም እንደምትለወጥ” በነቢዩ ኢዩኤል፦ «“ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም ትለወጣለች፥ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ።” ✠ ኢዩኤል 2፥31» ይህንኑ ቃል ቅዱስ ጴጥሮስ በሐዋርያት ሥራ ይጠቅሳል፦ «“ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም ትለወጣለች።” ✠ ሐዋርያት ሥራ 2፥20» ⚠️ ነገር ግን አንባብያን በእዚህ ላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። እያንዳንዱን የጨረቃ ግርዶሽ “ይህ የኢዩኤል ትንቢት ፍጻሜ ነው” ብሎ መወሰን አይገባም። መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ምስሎች በትንቢታዊና በፍጻሜያዊ ዐውድ ይጠቀምባቸዋል፤ የጨረቃ ግርዶሽ ደግሞ በሥነ ፈለክ ሕግ ሊሰላና አስቀድሞ ሊታወቅ የሚችል የተፈጥሮ ክስተት ነው። ✨ 7. ሰማያት የፈጣሪን ሥራ ይናገራሉና ግርዶሽን መመልከት ፍርሃት ብቻ የሚፈጥር ነገር መሆን የለበትም። የፍጥረትን ሥርዓትና ድንቅነት ለማሰብም ዕድል ነው። «“ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ ጠፈርም የእጆቹን ሥራ ያወራል።” ✠ መዝሙር 19፥1» ☀️ ፀሐይ 🌍 ምድር 🌕 ጨረቃ በተወሰነ ሥርዓት መጓዛቸው የሰማይ አካላት እንቅስቃሴ በሕግና በሥርዓት መሆኑን ያሳያል። 🇪🇹 8. ጨረቃና የኢትዮጵያ የዘመን የሥነ ፈለክ እውቀት ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ከፀሐይ፣ ከጨረቃ፣ ከከዋክብትና ከዘመን አቆጣጠር ጋር የተያያዘ ረጅም ታሪክና ዕውቀትና ሀብት አላት። ከ88ቱ ሕብራተ ከዋክብት ውስጥ እንደ ሀገር ለ3 ጊዜያት የተጠቀሰችው ኢትዮጵያ ብቻ ናትተ በቤተ ክርስቲያንም የበዓላት አቆጣጠር፣ በፀሐይም በጨረቃም ይለካሉና የባሕረ ሐሳብ ስሌት ትልቅ ቦታ አለው። ስለዚህ የሰማይ አካላትን መመልከት ለአባቶቻችን የማይታወቅ ነገር አልነበረም፤ ዘመንን ለመለየት፣ ወራትን ለማስላትና የበዓላትን ጊዜ ለመወሰን የሥነ ፈለክ ምልከታና ስሌት ከዘመን አቆጣጠር ጋር ተያይዞ ኖሯል። እጅግ የብዙ ብዙ የአስትሮኖሚ መጻሕፍት ጽፈውልናል። በመኾኑም ትውልዱ ይህንን ሀብቱን በሚገባ መጠበቅ ይገባዋል። 🌓 ሳይንስ በዘመናችን በብዙ የተራቀቁ መሣሪያዎች ታግዞ የሚነግረንን ግርዶሽ ቀደምቶቹ ኢትዮጵያውያን ተራቀውበት መርምረውት ጽፈውበት ኖረዋል። 👁️ 9. ግርዶሹን እንዴት እንመልከት? ለሚለው 🌑 ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ በዓይን ማየት ደህንነቱ የተጠበቀ ነው። ☀️ የፀሐይ ግርዶሽ እንደሚያስፈልገው ልዩ eclipse glasses አያስፈልግም። 🔭 Binoculars ወይም Telescope ካለ የምድር ጥላ በጨረቃዋ ላይ ሲገባ በተሻለ ሁኔታ ለመመልከት ይረዳል። 📷 ፎቶ ለማንሳትም ከ11:30 ጠዋት በኋላ ጨረቃዋ ወደ ምዕራብ አድማስ በጣም ዝቅ ስለምትል ከፍ ያለና አድማሱ ክፍት የሆነ ቦታ ይመረጥ። 🌕🌑 10. በጨረቃ ግርዶሽ ጊዜ የምናየው በጨረቃ ላይ የወደቀውን የምድራችንን ጥላ ነው። 🌍➡️🌑 ስለዚህ ነሐሴ 22 ሊነጋጋ ሲል ማለዳ ወደ ጨረቃ ስንመለከት፣ በሌላ የሰማይ አካል ላይ የራሳችንን ዓለም ጥላ እያየን ነው። በመጨረሻም 🌕 ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. 🌑 August 28, 2026 🇪🇹 ኢትዮጵያ — አዲስ አበባ ማለዳ ደመና ከሌለ ወደ ምዕራብ ሰማይ ተመልከቱ። የምድር ጥላ በጨረቃ ላይ ሲገባ፣ የሰማይ አካላትን ሥርዓት ያስረዳናል፤ እምነት ደግሞ ፍጥረትን በድንቅነትና በምስጋና እንድናይ ይጋብዘናል። «“ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ ጠፈርም የእጆቹን ሥራ ያወራል።” ✠ መዝሙር 19፥1»
9 229
7
https://youtu.be/-iHylvTKDt4?si=TXwDwfOBMPIQ5psX
8 489
8
https://youtu.be/Q35REYjkwB4?si=bhb5EZpa3DAyFnr8
10 450
9
https://youtu.be/lHLdL61Sd5U?si=49hZh2cWuVJLueDA
9 323
10
🌍👑 የእመቤታችንን ዕርገት በብሔራዊ በዓልነት የሚያከብሩ የዓለማችን ሀገራት ✍️ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ 🌸 የቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገት የአንድ ሀገር፣ የአንድ ቋንቋ ወይም የአንድ ባህል በዓል ብቻ አይደለም። 💥 "እነሆም ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ኹሉ ብፅዕት ይሉኛል" (ሉቃ 1፥48) ያለቸው ትውልደ ሴም፣ ትውልደ ካም፣ ትውልደ ያፌት በመላ የሚያመሰግናት የሕዝቦች ኹሉ እናት በመኾኗ የዕርገቷ ክብረ በዓል ከአህጉር ወደ አህጉር፣ ከሕዝብ ወደ ሕዝብ፣ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ ተሻግሮ የሚከበር ዓለም ዐቀፍ መንፈሳዊ በዓል ነው። 🌍 ከኹሉም የሚያስደንቀው ግን በብዙ ሀገራት ይህ በዓል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብቻ የሚከበር መንፈሳዊ በዓል ሳይሆን፣ Assumption of Mary — የድንግል ማርያም ዕርገት በመባል መንግሥታዊ ዕውቅና ያለው የሕዝብ ዕረፍት ቀን መሆኑ ነው። 🌍 የእመቤታችንን ዕርገት በሕጋዊ የሕዝብ ዕረፍት የሚያከብሩ ሀገራት 🇦🇩 አንዶራ የእመቤታችን ዕርገት በAugust 15 ሀገር አቀፍ የሕዝብ ዕረፍት ሆኖ ይከበራል። 🇦🇹 ኦስትሪያ Assumption Day በሚል ስም August 15 በሕጋዊ የዕረፍት ቀንነት ይከበራል። 🇧🇪 ቤልጂየም የድንግል ማርያም ዕርገት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ ዕረፍት ነው። 🇭🇷 ክሮኤሺያ የእመቤታችን ዕርገት በሀገሪቱ ታላቅ የክርስቲያን በዓልና የሕዝብ ዕረፍት ነው። 🇨🇾 ቆጵሮስ በኦርቶዶክሳዊ ትውፊት የእመቤታችን ዕረፍት በከፍተኛ ክብር ይከበራል፤ August 15 የሕዝብ ዕረፍት ነው። 🇫🇷 ፈረንሳይ Assomption (ዕርገታ ለማርያም) በሚል ስም August 15 በመላ ሀገሪቱ የሕዝብ ዕረፍት ነው። 🇬🇷 ግሪክ ☦️ የእመቤታችን ዕረፍት ከታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት አንዱ ነው። በብዙ ደሴቶችና ከተሞች ሕዝቡ በሥርዓተ አምልኮ፣ በሰልፍ፣ በዝማሬና በታላቅ ሕዝባዊ ጉባኤ ያከብረዋል። 🇮🇹 ጣሊያን August 15 Ferragosto በሚለው የታወቀ ስም ይከበራል፤ የእመቤታችን ዕርገት የዕለቱ ዋና ሃይማኖታዊ በዓል ነው። 🇱🇹 ሊቱዌኒያ የእመቤታችን ዕርገት August 15 የሕዝብ ዕረፍት ሆኖ ይከበራል። 🇱🇺 ሉክሰምበርግ Assumption Day በሚል ስም የሀገር አቀፍ ዕረፍት ቀን ነው። 🇲🇹 ማልታ የእመቤታችን ዕርገት እጅግ ታላቅ ሃይማኖታዊና ሕዝባዊ በዓል ሲሆን August 15 ሕጋዊ የዕረፍት ቀን ነው። 🇲🇨 ሞናኮ Assumption of Mary በሚል ስም በሀገር አቀፍ ደረጃ ይከበራል። 🇵🇱 ፖላንድ የድንግል ማርያም ዕርገት August 15 ታላቅ የሃይማኖት በዓልና የሕዝብ ዕረፍት ነው። 🇵🇹 ፖርቱጋል የእመቤታችን ዕርገት በመላ ሀገሪቱ የሕዝብ ዕረፍት ሆኖ ይከበራል። 🇷🇴 ሮማኒያ ☦️ Adormirea Maicii Domnului “የእግዚአብሔር እናት ዕረፍት” በሚል ስም ይከበራል፤ ይህም ሕጋዊ የሕዝብ ዕረፍት ነው። 🇸🇲 ሳን ማሪኖ የእመቤታችን ዕርገት August 15 ሀገር አቀፍ የሕዝብ ዕረፍት ነው። 🇸🇮 ስሎቬኒያ Assumption of Mary (ዕርገታ ለማርያም) በሚል ስም በሀገር አቀፍ ደረጃ ይከበራል። 🇪🇸 ስፔን August 15 የእመቤታችን ዕርገት በብዙ ከተሞች በሃይማኖታዊ ሰልፍና በታላቅ ክብር ይከበራል፤ ሀገር አቀፍ የሕዝብ ዕረፍትም ነው። 🇻🇦 ቫቲካን የድንግል ማርያም ዕርገት ከታላላቅ የድንግል ማርያም በዓላት አንዱ ሆኖ በታላቅ ሥርዓት ይከበራል። 🇱🇧 ሊባኖስ ብዙ ሃይማኖቶች የሚኖሩባት ሀገር ቢሆንም፣ የድንግል ማርያም ዕርገት ሕጋዊ የሕዝብ ዕረፍት ነው። ይህም የእመቤታችን ክብር ከአንድ ሃይማኖታዊ ማኅበረሰብ በላይ የማኅበራዊ ስፋት እንዳለው ያሳያል። 🇨🇱 ቺሊ በላቲን አሜሪካ የእመቤታችንን ዕርገት August 15 በሕጋዊ የሕዝብ ዕረፍት ደረጃ ከሚያከብሩ ሀገራት አንዷ ናት። 🌍 በአፍሪካ የሚያከብሩ ሀገራት 🇧🇯 ቤኒን የእመቤታችን ዕርገት August 15 ሕጋዊ የሕዝብ ዕረፍት ነው። 🇧🇫 ቡርኪና ፋሶ የዕርገት በዓል በመንግሥት ዕውቅና ያለው የሕዝብ ዕረፍት ነው። 🇧🇮 ቡሩንዲ August 15 የእመቤታችን ዕርገት በሕጋዊ የዕረፍት ቀንነት ይከበራል። 🇨🇲 ካሜሩን Assumption Day በሚል ስም ሀገር አቀፍ የሕዝብ ዕረፍት ነው። 🇨🇫 ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የእመቤታችን ዕርገት በሀገሪቱ ሕጋዊ የሕዝብ ዕረፍት ነው። 🇨🇮 ኮትዲቯር August 15 የእመቤታችን ዕርገት በሕዝባዊ ዕረፍት ደረጃ ይከበራል። 🇬🇦 ጋቦን የዕርገት በዓል መንግሥታዊ ዕውቅና ያለው የሕዝብ ዕረፍት ነው። 🇬🇳 ጊኒ August 15 የእመቤታችን ዕርገት ሕጋዊ የዕረፍት ቀን ነው። 🇲🇬 ማዳጋስካር የድንግል ማርያም ዕርገት በሀገር አቀፍ ደረጃ ይከበራል። 🇲🇺 ሞሪሸስ የእመቤታችን ዕርገት በሕጋዊ የሕዝብ ዕረፍት ደረጃ ይከበራል። 🇷🇼 ሩዋንዳ August 15 የእመቤታችን ዕርገት ሕጋዊ የሕዝብ ዕረፍት ነው። 🇸🇳 ሴኔጋል ብዙዎቹ ሕዝቦቿ ሙስሊም ቢሆኑም የእመቤታችን ዕርገት የሕዝብ ዕረፍት ቀን ሆኖ ይከበራል። 🇸🇨 ሲሸልስ የእመቤታችን ዕርገት August 15 ሕጋዊ የሕዝብ ዕረፍት ነው። 🇹🇬 ቶጎ Assumption Day በሚል ስም ሀገር አቀፍ የሕዝብ ዕረፍት ሆኖ ይከበራል። ✨ እነዚህ ሀገራት በቋንቋ፣ በባህል፣ በአህጉር፣ በታሪክና በማኅበራዊ አወቃቀር የተለያዩ ቢሆኑም፣ በአንድ ዕለት የአምላክን እናት ዕርገት ክብር በማሰብ ይገናኛሉ። 🌹 በአውሮፓ ትከበራለች፤ 🌍 በአፍሪካ ትከበራለች፤ 🌎 በላቲን አሜሪካ ትከበራለች፤ 🌏 በመካከለኛው ምሥራቅም ትከበራለች። 👑🌹 የንጉሡ የክርስቶስ እናት በዕርገቷ በሰማይ ባሉ መላእክት እንደተመሰገነች ስሟም በምድር ላይ በብዙ ሕዝቦች ይመሰገናል። 🌸 ኢትዮጵያ ሀገራችንም የእመቤታችንን ክብር በጥልቅ መንፈሳዊ ትውፊት ከጠበቁ ጥንታዊ ክርስቲያናዊ ሀገራት አንዷ ናት። ☦️ ጾመ ፍልሰታ ከነሐሴ 1 እስከ 16 ድረስ በጾም፣ በጸሎት፣ በቅዳሴ፣ በሰዓታት፣ በስብሐተ ነግህ፣ በውዳሴና ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ በማሕሌት፣ በምስጋና ይከበራል። 💥 እመቤታችን ለኢትዮጵያውያን በበዓል ቀን ብቻ የምትታሰብ እናት አይደለችም። ስሟ በየዕለቱ በቅዳሴ፣ በውዳሴ፣ በማሕሌት፣ በሰዓታት፣ ይዘከራል። 💐 ይኹን እንጂ የፍልሰታ በዓል በኢትዮጵያ የፌዴራል ሕጋዊ የሕዝብ ዕረፍት አይደለም። ይህም ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ለ60 ሚሊየን አማኞቿ በእጅጉ ያሳዝናል። 🌸 ቅዱስ ሲኖዶስም ይኽ በበዙ ሀገራት በብሔራዊ በዓልነት የሚከበረውን የእመቤታችንን ዕርገት ከሚመለከታቸው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመመካከር የቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕርገቷን በብሔራዊ በዓል ደረጃ እንድናከብር እንዲያደርግ በታላቅ አክብሮት እጠይቃለሁ። 💐 በአስተያየት መስጫው ላይ እናንተም ጥያቄያችሁን አቅርቡ። https://t.me/+xN518gdGKvswNzE0 💥 መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (ነሐሴ 15/ 2018 ዓ.ም.)
12 251
11
https://www.youtube.com/live/EplYb5IkeIM?si=xbr4X98kuuwAG8xC
6 851
12
https://www.youtube.com/live/-T_qhCmAS-0?si=AU9AoQasYa_o3oBx
7 099
13
https://www.youtube.com/live/dob38hvXNMY?si=1WzJt5sVvy9Qly7O
9 416
14
💥 ጌታችን ጌትነቱን ገልጦበታል። የአብ ድምፅ ተሰምቶበታልና ታቦር ተራራ ቅዱስ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስም በመልእክቱ "ከገናናው ክብር፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይኽ ነው የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ምስጋናን ተቀብሎአልና፤ እኛም በቅዱሱ ተራራ ከእርሱ ጋር ሳለን ይኽን ድምፅ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን።" በማለት ገልጦታል (2ኛ ጴጥ 1:17-18) ♥❖ ሌላው ሙሉሙሉ ዳቦ መጋገሩ በትውፊት እንደምንረዳው ጌታ ብርሃኑን ሲገልጽ ብርሃኑ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ ያበራ ስለነበር እረኞች ሌሊቱ ኹሉ ቀን መስሏቸው እዛው ስለዋሉ ቤተሰቦቻቸው “ኅብስት” ይዘውላቸው ኼደዋልና የዚያ ምሳሌ እንደኾነ በአበው ትውፊት ይነገራል፡፡ 💥[በደብረ ታቦር ላይ ብርሃኑን የገለጠው አምላካችን ክርስቶስ ምስጋና ይግባው]፡፡ [መልካም በዓል] ✍ መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ የተለጠፈ)
8 559
15
[ደብረ ታቦር] ✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ♥❖ ይኽ በዓል ከጌታችን 9ኙ ዐበይት በዓላት አንደኛው ሲኾን በዓሉ በየዓመቱ ነሐሴ 13 ላይ በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ታሪኩ በ3ቱ ወንጌላት ላይ የተጻፈ ሲኾን ጌታችን አምላችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሎቹን ሐዋርያትን ከእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ የምስጢር ደቀ መዛሙርት የሚባሉት፣ በእምነት በተስፋ በፍቅር የሚመሰሉት፤ ዳግመኛ በነገደ ሴም በነገደ ካም በነገደ ያፌት የተመሰሉት ሦስቱን (ጴጥሮን፣ ያዕቆብን፣ ዮሐንስን) ይዟቸው ወደ ታቦር ተራራ ወጣ። 💥 የሞተውን ሙሴን ከ1644 ዓመታት በኋላ አምጥቶ፤ የተሰወረውን ኤልያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ የሕያዋን አምላክና የሙታን አሥነሺያቸው ርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን የገለጸበት ታላቅ ምስጢር የተከናወነበት ነው፡፡ (ማቴ 17፡1-9)። ♥❖ ጌታ 8ቱን ሐዋርያት ይዟቸው ያልወጣበት በይሁዳ ምክንያት ነው ምክያቱም ከምስጢረ መንግሥቱ ቢለየኝ ከሞቱ ገባኹበት ባለ ነበርና ነው፤ ነገር ግን በተራራው ላይ ለ3ቱ የተገለጸው ምስጢር ከተራራው ሥር ላሉት ከይሁዳ በስተቀር ተገልጾላቸዋል፤ ለእኛም እንደ ሐዋርያት ምስጢሩን ጥበቡን ይግለጽልን፡፡ ♥❖ ብዙ ተራሮች ሳሉ የታቦር ተራራን የመረጠበት 1)አስቀድሞ የጌትነት ክብሩ በዚያ ተራራ ላይ እንደሚገልጽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 88፡12 ላይ፦ “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ” (ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ይደሰታሉ) በማለት ጌታ በዚያ ተራራ ላይ ብርሃኑን ሲገልጽ የብርሃኑ ነጸብራቅ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ እንደሚታይ የተናገረውን ትንቢት ለመፈጸም ነው፡፡ ♥❖ ሌላው ታቦር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ 12 ጊዜያት ሲጠቀስ በተለይ በመሳ 4 እና 5 ላይ እንደተጻፈው አስቀድሞ በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ጠላት የነበረው ሲሳራን መስፍኑ ባርቅ በተራራው ላይ ድል ነሥቶበት ነቢይቱ ዲቦራም በተራራው ላይ በደስታ አመስግናበታለች ዘምራበታለች። በተመሳሳይ መልኩ የእስራኤል ዘነፍስ የክርስቲያኖችን ጠላት የኾነውን ዲያብሎስን የኹላችን ፈጣሪ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ላይ አምላክነቱን ገልጦ ድል ስለነሣው ነቢያት ሐዋርያት ምእመናን የሚያመሰግኑት ስለኾነ ለምሳሌነቱ ተስማሚነት ያለውን የታቦርን ተራራን መርጦታል፡፡ ❤ በሲና ተራራ የአባቱን ክብር እንዳየን የርሱን ክብር ደግሞ በብሩህ ደመና በታቦር ገልጦታል። ♥❖ ለምን ሙሴንና ኤልያስን ከነቢያት መኻከል መረጠ? ቢሉ፦ ሀ) በማቴ 16፡13 ላይ ሐዋርያትን ስለማንነቱ እንደጠያቃቸው እንደመለሱለት ኹሉ በእውነት ጌታችን የሙሴና የኤልያስ በአጠቃላይ የነቢያት ፈጣሪ የእግዚአብሔር ልጅ መኾኑን ሲገልጽላቸው ነው። ለ) በዘፀ 33፡17-23 ላይ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ጥልቅ ግንኙነት የተነሣ “እባክኽ ክብርኽን አሳየኝ” ብሎ ልመናን አቀረበ፤ እግዚአብሔርም "ወአነብረከ ውስተ ስቊረተ ኰኲሕ ወእከድን እዴየ በላዕሌከ እስከ አኃልፍ" (በሰንጣቃው ዐለት አኖርሃለኍ፤ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይኽ እጋርዳለኍ፤ ካለፍኍ በኋላ እጄን አንሥቼልኽ ጀርባዬን ታያለኽ፤ ፊቴ ግን አይታይም) ብሎታል (ዘፀ ፴፫፥፲፯-፳፫)፡፡ ♥❖ ይኸውም ጀርባ በስተኋላ እንደሚገኝ ኹሉ በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በታቦር ተራራ ላይ እንደሚገለጽለት ሲያመለክተው ነው። ♥❖ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብም ስለ ታቦር በሚተነትነው መጽሐፉ ሙሴ በቃዴስ ባለው በመሪባ ውሃ ከእስራኤል ጋር በበደለው በደል ምክንያት ምድረ ርስት ኢየሩሳሌም እንዳይገባ አይቷት ብቻ በናባው ተራራ ላይ እንዲያርፍ ኾኗል (ዘፀ ፴፪፥፶፪፤ ዘፀ ፴፬፥፩-፰)፡፡ ♥❖ ይኽ ለሙሴ አሳዛኝ ቢኾንም በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሙሴ በፊት በሩቁ ያያት ግን ያልገባባት በምድረ ርስት በኢየሩሳሌም ያለች ታቦር ተራራ ላይ አምጥቶት በዘመነ ብሉይ በአካለ ሥጋ ያልገባባትን ርስት እንዲገባባት አድርጎታል፤ ይኸውም አዳምና ልጆቹ በአካለ ሥጋ ያጡትን ርስታቸው ገነትን በአካለ ነፍሳቸው ዳግመኛ ሊያገባቸው እንደመጣ የሚያመለክት መኾኑን በስፋት አስተምሯል፡፡ ♥❖ ጌታችን በብሉይ ኪዳን ከነበሩት ከነቢያት ሙሴንና ኤልያስን በሐዲስ ኪዳን ከነበሩት ከሐዋርያት ሦስቱን በታቦር ተራራ ላይ ማውጣቱ፦ 1) የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ በመኾኗ ሲኾን በቤተ ክርስቲያናችን ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን እንደሚነገሩ ለማመልከት 2) በተራራ በተመሰለች በጉባኤ ቤት ብሉይና ሐዲስ እንደሚነገሩ ለመግለጽ፡፡ 3) ሌላው የታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ስትኾን ይኸውም ጌታ ነቢያትንና ሐዋርያትን በተራራዋ ላይ መሰብሰቡ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም ሐዋርያትም እንደሚወርሷን ለማመልከት 4) ሙሴ ያገባ ሲኾን ኤልያስ ድንግል ነውና መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም ያገቡም እንደሚወርሷት ለማጠየቅ ነው፡፡ 5) እንደ ያዕቆብ ዘሥሩግ ትርጓሜ ሙሴ ኦሪት ዘፍጥረትን ሲጽፍ፦ “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1፡1) እንዳለ፤ ዮሐንስም “በመጀመሪያ ቃል ነበር” (ዮሐ 1፡1) ብሎ እንደ ሙሴ አምላክነቱን የሚመሰክር ነውና ሙሴ አስቀድሞ የጻፈልኝ፤ አኹንም ዮሐንስ አምላክነቴን የሚጽፍልኝ እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡ 6) ሙሴና ኤልያስ ይመሳሰላሉ፤ ይኸውም በሲና ተራራ 40 ቀንና ሌሊት እንደጾመ ኤልያስም በደብረ ኮሬብ 40 ቀንና ሌሊት የጾመ ነውና፨ 7) ሙሴ ንጉሡ ፈርዖንን የገሠፀ እንደነበር ኤልያስም ንጉሡ አክዐብን የገሠፀ ነውና፨ 8) ሙሴ ከንጉሡ ፈርዖን ፊት ሸሽቶ እንደሄደ ኤልያስም ከንግሥቲቱ ኤልዛቤል ፊት ሸሽቶ ሄዶ ነበር። 9) ዳግመኛም ሰማይኑን ዝናብ እንዳያዘንም በተሰጠው ሥልጣን ባሰረውና ከ3 ዓመት ከ6ወር ቆይታ በኋላ እንዲዘንብ በፈታው ኤልያስን እንዳመጣ ኹሉ የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሥልጣነ ተሰጥቶት “እኔም እልሃለኹ፥ አንተ ጴጥሮስ ነኽ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥኻለኹ፤ በምድር የምታስረው ኹሉ በሰማያት የታሰረ ይኾናል፥ በምድርም የምትፈታው ኹሉ በሰማያት የተፈታ ይኾናል” (ማቴ 16፡18-19) ላለው ለጴጥሮስን ታላቅ ሰማያዊ ሥልጣን መስጠቱን ለማመልከት አምጥቷቸዋል፡፡ ♥❖ በቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን ያለው መንፈሳዊ አከባበር ደማቅ ነው፤ ይኽ በዓል በቤተ ክርስቲያን በማሕሌት በቅዳሴ በትምህርት የሚከበር በዓል ሲኾን በሀገርኛ የቡሄ በዓል ይባላል፤ ቡሔ ማለት ሊቁ ደስታ ተክለ ወልድ በመዝገበ ቃላት ላይ ሲገልጹት ቧ ብሎ በደብረ ታቦር የተገለጠው የጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል የልብሱን እንደ በረዶ ነጭ መኾን ያስረዳል ስለዚኽ የብርሃን፣ ብርሃናዊ ማለት ነው፡፡ ♥❖ በዚህ በዓል በታቦር የታየው የብርሃኑ ምሳሌ የሚሆን ችቦ ይበራል፤ ሌላው በዚኽ በዓል ሰሞን በገጠር ከተራራ ላይ እረኞች ሕጻናት ዥራፍ እየገመዱ ማስጮኻቸው ጌታ በተራራ ላይ ብርሃኑን በገለጸ ጊዜ አብ በደመና ኾኖ “እርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” ባለ ጊዜ ሐዋርያት በድምፁ ደንግጸው መውደቃቸውን ለማመለክት ነው፡፡
9 117
16
https://www.youtube.com/live/SfPl-ua3KT4?si=JxTp8CX_2XuSyyUg
8 092
17
https://www.youtube.com/live/Gv3xgU4Q_v4?si=mewzi2rzrrDIsWBa
9 862
18
https://www.youtube.com/live/D1qv6tfvq0I?si=8qXcltth1HAX-V0u
10 127
19
https://www.youtube.com/live/t2QL-GHx95Q?si=Q8WB6AASw_E_CIzO
10 594
20
https://www.youtube.com/live/wFKQlG6y83o?si=XCgk8UZpxMqFrW87
10 268