en
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Open in Telegram

📈 Analytical overview of Telegram channel EEP Communication

Channel EEP Communication (@eepcommuication) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 692 subscribers, ranking 8 036 in the Technologies & Applications category and 2 171 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 692 subscribers.

According to the latest data from 03 September, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 143 over the last 30 days and by -1 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 27.84%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 16.00% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 4 369 views. Within the first day, a publication typically gains 2 511 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 10.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
EEP Communication

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 04 September, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Technologies & Applications category.

15 692
Subscribers
-124 hours
+47 days
+14330 days
Posts Archive
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ ......///....... "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/E
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ ......///....... "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም

የብሔራዊ ኤሌክትሪክ ግሪድ ሚና .....///..... ብሔራዊ ኤሌክትሪክ ግሪድ በሀገሪቱ ውስጥ የሚመረት ማናቸውንም የኃይል አቅርቦት በደህንነት፣ በጥራት እና በብቃት ለአገልግሎት ለማዋል የሚያስችል
የብሔራዊ ኤሌክትሪክ ግሪድ ሚና  .....///..... ብሔራዊ ኤሌክትሪክ ግሪድ በሀገሪቱ ውስጥ የሚመረት ማናቸውንም የኃይል አቅርቦት በደህንነት፣ በጥራት እና በብቃት ለአገልግሎት ለማዋል የሚያስችል ሀገራዊ የኃይል ኔትወርክ ነው። ይህ ኔትወርክ በልዩ ልዩ አካባቢዎች የሚገኙ የውሃ፣ የነፋስ፣ የፀሐይ እና የጂኦተርማል ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ወደ አንድ ማዕከላዊ ሥርዓት ያገናኛል።   ዋነኛ ተግባራት፦ ኃይል ማጓጓዝ፦ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ከፍተኛ ቮልቴጅ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች አማካይነት ኤሌክትሪክን ከተመረተበት ቦታ ወደ ሩቅ ከተሞችና የኢንዱስትሪ ማዕከላት ያጓጉዛል። ፍላጎትና አቅርቦትን ማመጣጠን፦ በየቀኑ እና በየሰዓቱ የሚቀያየረውን የኤሌክትሪክ ፍላጎት (Demand) እና ማመንጫዎች የሚያቀርቡትን ኃይል (Supply) በማመጣጠን የኃይል መቋረጥን ይከላከላል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የብሔራዊ-ኤሌክትሪክ-ግሪድ-ሚና&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም

አረንጓዴ አሻራ - ለዘላቂ የኃይል ዋስትና .....///..... በኢትዮጵያ በየዓመቱ የሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የአካባቢ ጥበቃ እና የደን ሽፋን ማሳደጊያ ስልት ብቻ አይደለም። ከዚህ
አረንጓዴ አሻራ - ለዘላቂ የኃይል ዋስትና  .....///..... በኢትዮጵያ በየዓመቱ የሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የአካባቢ ጥበቃ እና የደን ሽፋን ማሳደጊያ ስልት ብቻ አይደለም። ከዚህ ባሻገር የሀገሪቱን የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ለሆኑት የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድቦች ህልውና እና ዘላቂነት እጅግ ወሳኝ የሆነ ግብዓት ነው። ከ90% በላይ የሚሆነውን የኤሌክትሪክ ኃይል ከውሃ የምታመነጨው ኢትዮጵያ የግድቦቿን ህልውና ለማስጠበቅ እና አቅማቸውን ለማጎልበት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከግድቦች ደህንነት እና ጥበቃ ጋር በቀጥታ የተሳሰረ ነው።  የአረንጓዴ አሻራ ከአባባቢ ጥበቃ በዘለለ በርካታ ጠቀሜታዎች ይኖሩታል፡፡ 1. የደለል ክምችትን የመከላከል ሚና የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድቦች በአግባቡ ኃይል እንዳያመነጩ ከሚያደርጓቸው ችግሮች መካከል አንዱ የደለል ክምችት ነው። የደን ጭፍጨፋ እና የአፈር መሸርሸር በሚኖርበት ጊዜ ከባድ የክረምት ዝናብ ለም አፈርን እያጠበ ወደ ወንዞች እና በቀጥታ ወደ ግድቦች እንዲገባ ያደርጋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=አረንጓዴ-አሻራ-ለዘላቂ-የኃይል-ዋስትና&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም

የኤልኒኖ (El Nino) ክስተት እና የኃይል አቅርቦት ብዙ ጊዜ የኤልኒኖ ክስተት ሲነሳ አእምሯችን ወደ ድርቅ፣ የምግብ እጥረት እና የግብርና መስተጓጎል ያደላል። ነገር ግን ኤልኒኖ ከአየር ጠባይ መ
የኤልኒኖ (El Nino) ክስተት እና የኃይል አቅርቦት   ብዙ ጊዜ የኤልኒኖ ክስተት ሲነሳ አእምሯችን ወደ ድርቅ፣ የምግብ እጥረት እና የግብርና መስተጓጎል ያደላል። ነገር ግን ኤልኒኖ ከአየር ጠባይ መዛባት ባሻገር በቀጥታ ከምንጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እና ደህንነት ጋር እጅግ ጥብቅ የሆነ ትስስር አለው። በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አብዛኛው የኤሌክትሪክ ኃይላቸውን ከውሃ (Hydropower) በሚያመነጩ ሀገራት ላይ የኤልኒኖ መከሰት በኃይል አቅርቦት ስርዓቱ ላይ ግዙፍ ፈተና ይደቅናል።   1. የኤልኒኖ ክስተት ምንድን ነው? ኤልኒኖ በፓሲፊክ ውቅያኖስ አካባቢ የሚከሰት የአየር ጠባይ መዛባት ሲሆን የውቅያኖሱ ወለል የሙቀት መጠን ከተለመደው በላይ ሲጨምር የሚከሰት ነው። ይህ የሙቀት መጨመር፡- ·         የዓለም አቀፍ የንፋስና የዝናብ ስርጭትን ያዛባል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ የክረምት ዝናብ ስርጭትን በመቀነስ ለከፍተኛ ድርቅ እና የውሃ እጥረት ይዳርጋል። በሌሎች የዓለም ክፍሎችም ያልተለመደ ከባድ ጎርፍ ያስከትላል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኤልኒኖ-el-nino-ክስተት-እና-የኃይል-አቅርቦት&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም

ከማብሪያና ማጥፊያ የሚዘለው የብርሃን ጉዞ ……///…….. ብዙዎቻችን ቤታችን ስንገባ እንደምናገኘው የማብሪያና ማጥፊያ ቁልፍ ኃይልን የምናገኝበት እና ሲቋረጥም ወደነበረበት የምንመልስበት ሂደት ቀላል
ከማብሪያና ማጥፊያ የሚዘለው የብርሃን ጉዞ  ……///…….. ብዙዎቻችን ቤታችን ስንገባ እንደምናገኘው የማብሪያና ማጥፊያ ቁልፍ ኃይልን የምናገኝበት እና ሲቋረጥም ወደነበረበት የምንመልስበት ሂደት ቀላልና አፍታ የማይወስድ ተግባር ይመስለናል። ነገር ግን ማብሪያና ማጥፊያውን በተጫንንበት ቅጽበት በቤታችን ወይም በሥራ ቦታችን የሚበራው የኤሌክትሪክ ኃይል እኛ ዘንድ ለመድረስ የሚያልፍበት መንገድ እጅግ ውስብስብ፣ አደገኛ እና በሺዎች የሚቆጠሩ የዘርፉ ባለሙያዎችን የሌሊትና ቀን የማይቋረጥ አድካሚ ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን ምን ያህል እንረዳለን፡፡   በሸለቆዎችና በበረሃዎች የሚጀመር የኃይል ማመንጨት ሂደት የኃይል አቅርቦት ጉዞው የሚጀምረው ከኃይል ማመንጫዎች ነው። በኢትዮጵያ አብዛኞቹ የውሃ ኃይል ማመንጫዎች የሚገኙት ከመኖሪያ በራቁ አካባቢዎች፣ ከፍተኛ ንፋስና ሙቀት ባለባቸው በረሃዎች እና ሸለቆዎች ውስጥ ነው። በእነዚህ አስቸጋሪ አየር ጠባይና መልክዐ ምድር ውስጥ የሚሰሩ መሐንዲሶችና ቴክኒሻኖች ግዙፍ የውሃ እና የንፋስ ተርባይኖችንና ጄነሬተሮችን በከፍተኛ ጥንቃቄ... ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ከማብሪያና-ማጥፊያ-የሚዘለው-የብርሃን-ጉ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም

የወደቀው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምር የኃይል ፍሰት የማመጣጠን ሥራ ይሰራል ………///…….. በለገጣፎ - ቃሊቲ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመ
+3
የወደቀው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምር የኃይል ፍሰት የማመጣጠን ሥራ ይሰራል ………///…….. በለገጣፎ - ቃሊቲ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት የወደቁ 5 የብረት ምሰሶዎችን በመጠገን ዳግም አገልግሎት መስጠት እስኪጀምሩ ድረስ የኃይል ፍሰት የማመጣጠን ሥራዎች እንደሚሰሩ የትራንስሚሽን ቢዝነስ ዘርፍ አስታወቀ፡፡ በዘርፉ የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ተወካይ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ግርማ ዘለቀ እንደገለፁት የብረት ምሰሶዎቹ የወደቁት በከባድ አውሎ ንፋስ ምክንያት ቢሆንም ቀደም ሲል በምሰሶዎቹ አካላት ላይ ይፈፀም የነበረው ተደጋጋሚ የስርቆት ወንጀል ለጉዳቱ መከሰት አሉታዊ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በወደቁት የብረት ምሰሶዎች ላይ በተደረገው የቴክኒክ ፍተሻ መሰረት የተሰረቁ የምሰሶ አካላትን መልሶ ለመተካት በማሻሻያ (Modification) መልክ ይገጠሙ የነበሩት ብረቶች የምሰሶዎቹን መደበኛ ጥንካሬና የመሸከም አቅም ማምጣት አለመቻላቸው መረጋገጡን ተናግረዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የወደቀው-የኃይል-ማስተላለፊያ-መስመር-ተ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም

ጥብቅ የውሃ አስተዳደር ሥርዓት የመዘርጋት አስፈላጊነት! .....///..... ውሃ ለኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማት ዋነኛውና ዋናው የኃይል ምንጭ ነው። በተለይም በውሃ ኃይል ማመንጫዎች የሚመረተው እ
ጥብቅ የውሃ አስተዳደር ሥርዓት የመዘርጋት አስፈላጊነት!  .....///..... ውሃ ለኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማት ዋነኛውና ዋናው የኃይል ምንጭ ነው። በተለይም በውሃ ኃይል ማመንጫዎች የሚመረተው እያንዳንዱ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የሚጀምረው ከአንዲት የውሃ ነጠብጣብ በመጠራቀም በመሆኑ የውሃ አጠቃቀምና አስተዳደር ሥርዓት በኃይል ማመንጨት ሂደት ቁልፍ ሚና አለው!   ጥብቅ የውሃ አስተዳደር ለኃይል ዘርፉ ያለው ወሳኝ ፋይዳ የኃይል ብክነትን መቀነስ በወቅታዊ የአየር ንብረት መለዋወጥና ያላግባብ በሚባክን የውሃ ሀብት ምክንያት የሚፈጠርን የኤሌክትሪክ ማመንጨት አቅም መቀነስ ይከላከላል።   ዘላቂ የኃይል አቅርቦት ግድቦች ሙሉ የማመንጨት አቅማቸውን ውጤታማ በሆነ መንገድ እና ሥርዓት ባለው ሁኔታ እንዲጠቀሙ ያስችላል።   ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እያንዳንዷ የምትባክን የውሃ ነጠብጣብ በኃይል ማመንጨት ሂደት ላይ የምታሳድረው ተጽዕኖ በቀጥታ በመኖሪያ ቤቶች፣ በፋብሪካዎች፣ በንግድና በማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር ውጤታማ ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም።   ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ጥብቅ-የውሃ-አስተዳደር-ሥርዓት-የመዘርጋ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም

በሥራ ላይ ደህንነት እና ጤንነት ዙሪያ ሥልጠና እየተሰጠ ነው ……///……. በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እና ሪጅኖች ለተመደቡ የሥራ ላይ ደህንነትና ጤና አስተባባሪ መሐንዲሶች በሥራ ላይ ደህንነት ላይ
+3
በሥራ ላይ ደህንነት እና ጤንነት  ዙሪያ ሥልጠና እየተሰጠ ነው ……///……. በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እና ሪጅኖች ለተመደቡ የሥራ ላይ ደህንነትና ጤና አስተባባሪ መሐንዲሶች በሥራ ላይ ደህንነት ላይ ያተኮረ ሥልጠና መስጠት መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ ላይ ደህንነትና ጤና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ሥራ አስኪያጅ አቶ ኮርሳ ተሬሳ እንደገለፁት ሥልጠናው መሐንዲሶቹ በተመደቡባቸው የሥራ ቦታዎች ላይ በሚኖራቸው የሥራ ላይ ደህንነት እና ጤንነት ክትትልና ቁጥጥር ላይ ያላቸውን የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው። ሥልጠናው ባለሙያዎቹ በሥራ ላይ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ስጋቶችን በመለየት መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማድረግ ታስቦ መዘጋጀቱን  ነው የገለፁት። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=በሥራ-ላይ-ደህንነት-እና-ጤንነት-ዙሪያ-ሥ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል መቋረጥን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ ዘመናዊ የአደጋ ጊዜ የብረት ምሰሶዎች 🏗   በኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ድንገተኛ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ፈጣን መልሶ ጥገና ለመስጠት የሚያስችሉ ዘመናዊ የአደጋ ጊዜ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች (Emergency Restoration Towers) በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ተደርገዋል።   ይህ ቴክኖሎጂ ምን ዓይነት ጥቅሞችን ይዞ መጥቷል?   ፈጣን መልሶ ጥገና  ቀደም ሲል በአደጋ ወቅት ከ18 እስከ 20 የሚደርሱ የእንጨት ምሶሶዎችን መትከል ይጠይቅ የነበረ ሲሆን አዲሶቹ ምሰሶዎች ግን በደጋፊ ገመዶች (Anchor Wire) በቀላሉ የሚገጣጠሙ በመሆናቸው የተቋረጠውን መስመር በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ወደ ሥራ ለማስገባት ያስችላሉ።   የኃይል ጭነት ማመጣጠን የተጨናነቁ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን አነስተኛ የኃይል ፍሰት ወደሚገኝባቸው በማዘዋወር ከአገልግሎት ውጭ የነበሩ አካባቢዎች በፍጥነት ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ያደርጋል።   የሠራተኞች ደህንነትና የአሰራር ዘመናዊነት የጥገና ሠራተኞችን ለጉዳት እንዳይጋለጡ በማድረግ ደህንነታቸውን አስተማማኝ ያደርጋል።   በተግባር ምን ውጤት ተገኘ? በሞጆ አካባቢ በተደረገ ሥልጠናና ልምምድ ባለሙያዎቹ የምሰሶ ተከላ ጊዜን ከግማሽ ቀን በታች ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡ በተጨማሪም ከቢሾፍቱ ወደ ቆቃ እና ሁርሶ እንዲሁም ከገላን ወደ ሞጆ በሚሄዱ ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመሮች ላይ ተከሰተው እስከ 7 ቀናት ሊወስዱ ይችሉ የነበሩ የኃይል መቋረጦችን በእነዚህ ምሰሶዎች አማካኝነት ፈጣን መፍትሔ መስጠት ተችሏል።   በቀጣይ ምን ታስቧል? ቴክኖሎጂውን ወደ ሁሉም ሪጅኖች ለማስፋትና የጥገና ምላሽ ጊዜን ይበልጥ ለመቀነስ የሚያስችሉ ዝግጅቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content

የፕሮጀክት አስተዳደርን ማዘመን ለተቋም ዘላቂ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ አለው .....///..... የተቋሙን ስትራቴጂካዊ ግቦች በስኬት ለማሳካትም ሆነ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን፣ ዘመናዊና ጠ
+5
የፕሮጀክት አስተዳደርን ማዘመን ለተቋም ዘላቂ ዕድገት ትልቅ ፋይዳ አለው  .....///..... የተቋሙን ስትራቴጂካዊ ግቦች በስኬት ለማሳካትም ሆነ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን፣ ዘመናዊና ጠንካራ የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት መሠረታዊና ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ ተጠቆመ።   የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተቀላጠፈ ደረጃውን የጠበቀና ውጤታማ የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት ለመገንባት የሚያስችለውን አራተኛ ዙር የከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ሥልጠና ለፕሮጀክት ዳይሬክተሮችና ሥራ አስኪያጆች መስጠት ጀምሯል።   በዕለቱ ሥልጠናውን የሰጡት በተቋሙ የአሰላ ንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅና አሰልጣኝ ኢንጂነር ጌቱ ጌቱ ያደቴ እንደገለጹት ይህ ሥልጠና ተቋሙ በፕሮጀክት አስተዳደር ረገድ የሚያጋጥሙትን መዋቅራዊና አሰራር ነክ ፈተናዎች በዘላቂነት በመሻገር፣ ከልማዳዊ አሰራር ወደ ተመራጭና ዘመናዊ የፕሮጀክት መሪነት ሥርዓት እንዲሸጋገር አቅም ይፈጥራል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የፕሮጀክት-አስተዳደርን-ማዘመን-ለተቋም&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ .....///..... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአውቶ ሜካኒክ 1ኛ፤ አውቶ ኤሌክትሪሺያን 1ኛ እና በአውቶ ቦዲ 1ኛ የሥራ መደቦች ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር መጋቢት 3
+5
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ .....///..... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአውቶ ሜካኒክ 1ኛ፤ አውቶ ኤሌክትሪሺያን 1ኛ እና በአውቶ ቦዲ 1ኛ የሥራ መደቦች ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የውጭ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል። በዚህ መሠረት ከዚህ በታች ስማችሁ የተገለፀው አመልካቾች በሙሉ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ ብረታ ብረት ፊትለፊት በሚገኘው የተቋሙ ዋና መሥሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ የፅሁፍ ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና እንድትገኙ እናሳስባለን። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል መቋረጥን ለመቀነስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ....///.... በኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ድንገተኛ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ፈጣን መልሶ ጥገና ለመስጠት የሚያስ
+4
የኃይል መቋረጥን ለመቀነስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው  ....///....   በኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ድንገተኛ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ፈጣን መልሶ ጥገና ለመስጠት የሚያስችሉ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የትራንስሚሽን ቢዝነስ ዘርፍ አስታወቀ።              በዘርፉ የቴክኒካል ድጋፍ መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አበባው ያለው እንደገለፁት በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ የተደረጉት የአደጋ ጊዜ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች (Emergency Restoration Tower) በተለያየ ምክንያት የሚወድቁ የብረት ምሰሶዎችን በአጭር ጊዜ በመተካት የኃይል መቋረጥን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ ናቸው።  በተጨማሪም የብረት ምሰሶዎቹ የተጨናነቁ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን አነስተኛ የኃይል ፍሰት ወደሚገኝባቸው ለማዘዋወርና ከአገልግሎት ውጭ የነበሩትን በፍጥነት ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ ሚናቸው የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኃይል-መቋረጥን-ለመቀነስ-የሚያስችል-ቴ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል መሠረተ ልማት ደህንነትን ለማረጋገጥ በተሰሩ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል፤ ......///...... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመሠረተ ልማት ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የአሰራር ሥርዓቶች
የኃይል መሠረተ ልማት ደህንነትን ለማረጋገጥ በተሰሩ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል፤ ......///...... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የመሠረተ ልማት ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የአሰራር ሥርዓቶች በመተግበር ለውጥ መምጣቱን የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ በጽ/ቤቱ የአስተዳደራዊ ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ ግርማ ግዛቸው (ዶ/ር) እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ ለዋና ሥራ አሰፈጻሚ የሚቀርቡ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ተፈጻሚነት ለማሻሻል፣ ተቋማዊ እና የኃይል መሰረተ ልማት ደህንነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የፖሊሲ፣ ፕሮሰስና ለውጥ ማኔጅመንት ተግባራትን በማከናወን ስትራቴጅካዊ ግቦችን ለማሳካት በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል። በዚህም በበጀት ዓመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ 5 ሪጅኖች 1 ሺህ 411 የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችን በማኅበረሰቡ ለማስጠበቅ ታቅዶ በ1 ሺህ 279 ምሰሶዎች ላይ ተፈጻሚ ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኃይል-መሠረተ-ልማት-ደህንነትን-ለማረጋ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም

ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የተቋሙን ጥቅምና ገጽታ የሚያስጠብቁ ሥራዎችን ተከናውነዋል ………///…….. በ2018 በጀት ዓመት ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የተቋሙን ጥቅምና ገጽታ የሚያስጠብቁ የተለያ
ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የተቋሙን ጥቅምና ገጽታ የሚያስጠብቁ ሥራዎችን ተከናውነዋል ………///…….. በ2018 በጀት ዓመት ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የተቋሙን ጥቅምና ገጽታ የሚያስጠብቁ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮምፕሊያንስና ገቨርናንስ ዘርፍ ገለጸ፡፡ የዘርፉሥራ አስፈጻሚ ተወካይ ወ/ሮ መስከረም በቀለ እንደገለጹት የተቋሙን ስትራቴጅክ ዕቅድ መሰረት በማድረግ የተቋሙን ገጽታ ከመገንባት፣ ብልሹ አሰራሮችን ከመከላከል፣ የተቋሙን ጥቅም ከማስጠበቅ፣ ግልጸኝነትንና ተጠያቂነትን ከማስፈን እንዲሁም የሴቶችን ተሳትፎ ከማሳደግ አንጻር የተለያዩ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ 10 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ መጠን ባላቸው 355 የፍትሐብሄር እና 57 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር መጠን ባላቸው 37 የሥራ ክርክር መዝገቦች ላይ ክትትል ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ብልሹ-አሰራሮችን-በመከላከል-የተቋሙን-ጥ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

በከባድ ንፋስ ምክንያት የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ወደቁ ………///…….. ከለገጣፎ - ቃሊቲ በተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ አምስት የብረት ምሰሶዎች መውደቃ
+5
በከባድ ንፋስ ምክንያት የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ወደቁ ………///…….. ከለገጣፎ - ቃሊቲ በተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ አምስት የብረት ምሰሶዎች መውደቃቸውን የማዕከላዊ 1 ሪጅን አስታወቀ። የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ገዛኸኝ እንደተናገሩት ምንም እንኳ የብረት ምሰሶዎች በከባድ ንፋስ የወደቁ ቢሆንም በምሰሶዎቹ አካላት ላይ ስርቆት መፈፀሙ ለኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎቹ መውደቅ አሉታዊ አስተዋፅኦ አድርጓል። በዚህ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተደጋጋሚ የስርቆት ወንጀል እንደሚፈፀም የገለፁት ዳይሬክተሩ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማና ከወረዳው የአስተዳደር አካላት ጋር በመነጋገር ለችግሩ እልባት መስጠት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የወደቁ የኃይል ምሰሶዎችን በአፋጣኝ በመጠገን መስመሩን ወደ አገልግሎት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን አቶ ደረጀ ተናግረዋል። አምስቱ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከሌሊት 7 ሰዓት አካባቢ መውደቃቸውንና በሰው እና በእንስሳት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱ ታውቋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

ጥራት ያለው ሪፖርት የተቋሙን ገጽታ ከመገንባት ባሻገር የሀብት አጠቃቀምን ለማሻሻል እንደሚረዳ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ተናገሩ ……///……. ጥራት ያለው ሪፖርት የተቋሙን ገጽታ ከመገንባቱ ባሻገር የ
+4
ጥራት ያለው ሪፖርት የተቋሙን ገጽታ ከመገንባት ባሻገር የሀብት አጠቃቀምን ለማሻሻል እንደሚረዳ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ተናገሩ ……///……. ጥራት ያለው ሪፖርት የተቋሙን ገጽታ ከመገንባቱ ባሻገር የሀብት አጠቃቀምን ለማሻሻል እንደሚያግዝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ተናገሩ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ በጋራ በመሆን በሪፖርት ዝግጅትና አቀራረብ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሂደዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የኢነርጂ እና ኮኔክቲቪቲ ፖርትፎሊዮ ዳይሬክተር ዶክተር ጌትነት መላክ በሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ላይ ያተኮረ የንድፈ-ሐሳብ እና ገቢራዊ ተሞክሮዎችን ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ጥራት-ያለው-ሪፖርት-የተቋሙን-ገጽታ-ከመገ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈፀመው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ …....///….…. በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ በሚገኝ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ከባድ የስርቆት ወንጀል የፈጸመውን ግለሰ
+6
በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈፀመው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ …....///….…. በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ በሚገኝ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ከባድ የስርቆት ወንጀል የፈጸመውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረዳው ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አዳነ ቡርጄ እንደገለጹት ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 አካባቢ ከወላይታ ሶዶ-ሳውላ በተዘረጋው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የስርቆት ወንጀል የፈጸመውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ተጠርጣሪው ከ7 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማት በተለያዩ ጊዜያት በባለ ሦስት እግር ባጃጅ በማጓጓዝ በቁጫ ወረዳ ጋሌ 2 ቀበሌ ልዩ ሥፍራ ሞጎላ ማዞሪያ ከሚባል አካባቢ ከደበቀበት ቦታ በሕብረተሰቡ ጥቆማ ፖሊስ ንብረቱን በቁጥጥር ሥር መዋሉን ጠቁመዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=በኤሌክትሪክ-መሰረተ-ልማት-ላይ-ስርቆት-የ-3&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

ተቋሙ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከ805 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል …….////……… የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ከ805 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረ
+2
ተቋሙ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከ805 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል …….////……… የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ከ805 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የተለያዩ የማህበራዊ ኃላፊነት ተግባራትን ማከናወኑን በተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እንደገለጹት ተቋሙ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት ከሚያከናውናቸው ሥራዎች ጎን ለጎን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም በበጀት ዓመቱ 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የፋይናንስ ወጪ በማድረግ ለመቄዶኒያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ማዕድ ማጋራቱን ተናግረዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ተቋሙ-ማህበራዊ-ኃላፊነቱን-ለመወጣት-ከ805-ሚ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

ግድቡ “የሚሊየኖችን ቤት ወደ ብርሃን ቀይሯል” - ሲኤንኤን ..///…. ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ “የሚሊየኖችን ቤት ወደ ብርሃን የቀየረ ግድብ ነው” ሲል ዓለም አቀፉ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲ ኤን
+1
ግድቡ “የሚሊየኖችን ቤት ወደ ብርሃን ቀይሯል” - ሲኤንኤን ..///…. ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ “የሚሊየኖችን ቤት ወደ ብርሃን የቀየረ ግድብ ነው” ሲል ዓለም አቀፉ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲ ኤን ኤን ዘገበ፡፡ በሲኤንኤን የኬንያ ዘጋቢ ቪክቶሪያ ሩባደሪ ወደ ህዳሴ በመጓዝ ባሰናዳችው ዘገባ ግድቡን ኢትዮጵያውያን ያለማንም ድጋፍ በራሳቸው አቅም ገንብተው ለውጤት ማብቃታቸውን ገልፃለች፡፡ በአፍሪካ በግዙፍነቱ ቀዳሚ የሆነው የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ከኢትዮጵያ አልፎ ለቀጣናው የኃይል አቅርቦት ትስስር ሚናው ከፍተኛ መሆኑን በፕሮግራምዋ አንስታለች፡፡ ግድቡ ለኢትዮጵያውያን ኃይል ከማቅረብ ባለፈ የቱሪስት መዳረሻ በመሆን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በመደገፍ ረገድ ትልስ ተስፋ ይዞ እንደመጣ አብራርታለች፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በዘገባው ላይ ግድቡ 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው አስረድተዋል፡፡ ግድቡ ከኢትዮጵያ አልፎ ጎረቤት ሀገራትን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይ ደግሞ ለሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ኃይል ለመሸጥ ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 145 ሜትር ከፍታ እና 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመት ሲኖረው በዓመት በአማካይ 15 ሺህ 670 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ያመነጫል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ቲክቶክ↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገጽ https://www.eep.com.et ሐምሌ 28