cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

Advertising posts
161 685Subscribers
-4224 hours
-4627 days
-1 57730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ዝርዝር መረጃውን ላማየት ሊንኮቹን ይጠቀሙ 1. https://rb.gy/5yp52r 2. https://rb.gy/tgt570 3 https://rb.gy/bus73f 4 https://rb.gy/bus73f
Show all...
👍 49🤔 8 7👏 7
የኦንላይን ባንኪንግ ደህንነትዎን ይጠብቁ! #security #Securitytip #tips #BoAmobile #mobilebanking #Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
Show all...
59👍 39👏 8
እንኳን ደስ አላችሁ!! ባንካችን አቢሲንያ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ እ.ኤ.አ. በማርች ወር ላይ ባካሄደዉ የሴቶች የተሰጥኦ ዉድድር ላይ ተሳትፈዉ ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች ተለይተዋል፡፡ በድምፅ ዉድድር ተሳትፈዉ ከነበሩት ተወዳዳሪዎች በአንደኛነት በአምላክ ጌትነት መወዳደሪያ ኮድ (M2) (100,000) የአንድ መቶ ሺ ብር ተሸላሚ በሁለተኛነት ኢትዮጵያ ኢሳያስ መወዳደሪያ ኮድ (M6) (75,000) ሰባ አምስት ሺ ብር ተሸላሚ እንዲሁም በሶስተኛነት ብሩክታዊት ቱጂ መወዳደሪያ ኮድ (M5) (50,000) ሀምሳ ሺ ብር ተሸላሚ በመሆን ያሸነፉ ሲሆን ዳኝነቱም የተካሄደዉ በያሬድ ትምህርት ቤት መምህራን እና በተመልካች ምርጫ ነበር፡፡ በቲክ ቶክ በነበረዉ ዉድድር ደግሞ በአንደኛነት ሜርሲ የቲክቶክ ስም (@enun088 ) (100,000) የአንድ መቶ ሺ ብር ተሸላሚ በሁለተኛነት ካልኪዳን የቲክቶክ ስም (@kal.baba10) (75,000) ሰባ አምስት ሺ ብር ተሸላሚ እንዲሁም በሶስተኛነት ያይኔአበባ የቲክቶክ ስም (@yayne_a ) (50,000) ሀምሳ ሺ ብር ተሸላሚ በመሆን ለማጠናቀቅ ችለዋል፡፡ የመዝጊያ መርሀግብራችንንም በቅርቡ የምናከናዉን ሲሆን ተወዳዳሪዎችን በድጋሚ እያመሰገንን አሸናፊዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡
Show all...
👍 107 23🤔 5🤩 5👌 5🔥 3
አዲሱን የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ በመጠቀም ደንበኞች እንዴት ወደ አዋጭ አካውንት ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉ? ሊንኩን በመጠቀም መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ! ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking&hl=en&gl=US ለአፕል ስልኮች  https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765 ለሁዋዌ ስልኮች https://appgallery.huawei.com/app/C110106115 #BankofAbyssina #mobilebanking #boamobile #bankinginethiopia #banksinethiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
Show all...
👍 90 16🤔 13👌 3
ባንካችን ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡ ኢድ ሙባረክ! አቢሲንያ አሚን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዕሴትዎን ያከበረ! #AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
Show all...
👍 118 20😁 7👌 7🥰 5🤔 5
በቅርቡ! #bankofabyssinia #Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
Show all...
👍 232 49👌 30👏 27🤔 18🤩 3
አፖሎ የገንዘብ እንቅስቃሴዎ ያለ ድካም እና እንግልት የሚያቀላጥፉበት መተግበሪያ ነው። ጊዜ ሳያጠፉ ህይወትዎን ያቅልሉ። መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ። ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.apollo&hl=en&gl=US ለአፕል ስልኮች https://apps.apple.com/us/app/apollo-digital/id1601224628 #Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
Show all...
👍 81 18😁 8👏 4😱 4🤩 4
👍 119 56👏 15🤔 7
ባንካችን አቢሲንያ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ በአቢሲንያ አሚን በኩል የተለያዩ ኢፍጣር ፕሮግራሞችን አካሄደ። ባንካችን አቢሲንያ የ2016 ዓ.ም. የረመዳን ጾምን ምክንያንት በማድረግ በአቢሲንያ አሚን በኩል በተለያዩ የሀገራችን ቦታዎች ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋር የኢፍጣር ፕሮግራም አካሂዷል። የኢፍጣር ፕሮግራሞቹ በዋናነት የተካሄዱት በአምስት የባንካችን ዲስትሪክቶች ሥር ሲሆን፣ በባህርዳር፣ ሐዋሳ፣ ድሬዳዋ፤ ምሥራቅ አዲስ ዲስትሪክት እንዲሁም በደሴ ዲስትሪክት የሚገኙበት ሲሆን፤ በደሴ ዲስትሪክት ከተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለው በሎጊያ ከተማ ለሚገኙ ወገኖቻችን በኢማን ኢስላሚክ አሶሴሽን በኩል ለማፍጠሪያ የሚሆኑ ምግቦችን በአይነት በመግዛት ለተፈናቃዮቹ አበርክቷል። የ ባንካችን ባህርዳር ዲስትሪክት በኩል በቻግኒ ከተማ የሚገኙ ምስኪኖችንና ከተለያዩ የሀገራችን ክፍል ተፈናቅለው በከተማዋ ተጠልለው ከሚገኙ ወገኖቻችን ጋር በመስጊድ ራህማን ኮሜቴዎች አማካኝነት በዕለቱ የሩዝ፣የዘይትና ፍየል ድጋፍ በማድረግ ያስፈጠረ ሲሆን፣ በተጨማሪም በጎንደር ከተማ በሚገኘው ነጃሺ መስጊድ በተካሄደው የኢፍጣር ፕሮግራም ላይም ተሳትፏል። በተጨማሪም፡- የሐዋሳ ዲስትሪክት አመራሮች ከሀላባ ፣ ከሻሸመኔና ይርጋ ጨፌ ከተማ ደንበኞቻችን ጋር የኢፍጣር ፕሮግራም በማዘጋጀት እንዲሁም ቤት ለቤት በመሄድ የኢፍጣር ፕሮግራም አከናውነዋል። በተጨማሪም የዲስትሪክቱ አመራር አባላትና ሠራተኞች የእርስ በርስ ትስስርና ትብብራቸውን ለማጠናከር በጋራ የአፍጥር ፕሮግራም አዘጋጅተው ያሳለፉ ሲሆን እንዲሁም፤- የባንካችን ምሥራቅ አዲስ አዲስትሪክት በቦሌ ጃዕፋርና ጡሩ ሲና መስጊዶች እና በአያት ጣፎ ዳሩል ሠላምና በሲኤሲ አላምራን መስጊዶች ለምስኪኖች በተዘጋጀ የኢፍጣር ፕሮግራሞች ላይ የዱቄት፣ ዘይት፣ ቴምርና እሽግ ውሃ ድጋፍ በማድረግ ተሳትፏል። በተጨማሪም የዲስትሪክቱ አመራሮችና ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ ድጋፍ በማፍረግ የተሳተፉ ሲሆን የምስራቋ ፈርጥ የሆነችው ከተማም ድሬዳዋ ዲሰትሪክት በሐረር ከተማ ሐረር አራተኛ ኢማሙ አሕመድ እና መስጂድ ጃሚዕ በኩል ለተደረጉ የኢፍጣር ዝግጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል። በአጠቃላይ ባንካችን ታላቁን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ ከላይ ከተጠቀሱት ቦታዎች በተጨማሪም በሌሎችም ቦታዎች ከእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቹና ሙስሊም ማኅበረሰቡ ጋር ወሩን በጋራ እያሳለፈ መሆኑን እየገለጽን፣ መልካም የረመዳን የፆም ወራት እንዲሆንላችሁ ይመኛል።
Show all...
👍 77 8🤔 3
ማርች 8 የሚከበረውን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሴት ባለተሰጥኦዎችን በማሳተፍ በባንካችን ሲካሄድ የነበረው የ “እችላለሁ” 3ኛ ዙር ሙዚቃ ውድድር የተጠናቀቀ ሲሆን ለውድድሩ ከቀረቡት የሙዚቃ ስራዎች ውስጥም አስር ስራዎች በባለሙያዎች ተገምግመው ለመጨረሻው የታዳሚዎች ምርጫ የተለዩ ሲሆን፣ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት መምህራን የሆኑት የሹምነሽ ታዬ ፣ ሜሮን ረጋሳ እንዲሁም ሰላማዊት አራጋዉ የሙዚቃ ስራዎችን በመገምገም ስራ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በቀጣይም ከሙዚቃ ዘርፍ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የሚወጡት ባለተስጥኦዎች በአድማጭ ድምፅ 30% ፣እንዲሁም በዳኞች 70% ነጥብ የሚለዩ ይሆናል፡፡ በመሆኑም በመጀመሪያ ዙር የተለዩት አስር የሙዚቃ ስራዎች ከዚህ ጋር ተያይዘው የቀረቡ በመሆኑ ከዛሬ መጋቢት 20 እስከ መጋቢት 23 ቀን 2016 ባለው ጊዜ ውስጥ ይህን የፌስቡክ ሊንክ https://www.facebook.com/share/v/wSpQRyEDry49Pf6Z/?mibextid=WC7FNe በመጠቀም በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የሚገኘውን መለያ ኮድ በመጠቀምና የመረጣችሁትን በፌስቡክ ኮመንት ሥፍራ ላይ በመፃፍ የድምፅ አሰጣጥ ተሳትፎ እንድታደርጉ እንጋብዛለን፡፡ መልካም ዕድል ለተሳታፊዎች!
Show all...
👍 77 9🔥 1