en
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 413 subscribers, ranking 5 577 in the Religion & Spirituality category and 2 192 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 413 subscribers.

According to the latest data from 13 July, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 71 over the last 30 days and by -3 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 25.53%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 9.38% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 933 views. Within the first day, a publication typically gains 1 446 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 23.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 14 July, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

15 413
Subscribers
-324 hours
+357 days
+7130 days
Posts Archive
ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት)፤ ፬ኛ ሳምንት፥ዘጥቅምት ፲፰፤

‹‹ ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይህ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በወርኃ ነሐሴ ፳/፳፻፲፣በመስከረም ፲፪ና ፲፫/፳፻፲ ዓ.ም. ጋብቻችሁን ለፈጸማችሁ የደብራችን አገልጋይና የሰ/ት/ቤታችን አባላት * ሙላት ተሾመ * ዲ.ን ዐሥራት ለይኩን * ይትባረክ ሙላቱ ከደመቀች ሽፈራው * መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ የፈጸማችሁትን ጋብቻ፤ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ፤ ቅ/ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ፡፡ ✤ ‹‹ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንዲሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እንደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡›› ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፖሊካርፐስ በላከው መልእክቱ ✤ ከተጋባችሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ዘርአያዕቆብ፡፡

በወርኀ ነሐሴና መስከረም የተመረቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ 1ኛ. ኪሩቤል ቴዎድሮስ፤ በኮምፒውተር ሳይንስ ዲግሪ፤ ከአኵሱም ዩኒቨርሲቲ 2ኛ. ኪሩቤል ጀቤሳ፤ በኮሙኒኬሽን ኢንጂነሪንግ ዲግሪ፤ ከአ.አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 3ኛ. ፈለቀች አሰፋ፤ በአካውንቲንግ ዲግሪ፤ ከአድማስ ዩኒቨርሲቲ 4ኛ. አልማዝ በቀለ፤ በሚድዋይፈሪ ዲግሪ፤ ከዳግማዊ ምኒልክ የጤና ሳይንስ ኰሌጅ 5ኛ. አክሊሉ ደስዬ፤ በማኔጅመንት ዲግሪ (በከፍተኛ ማዕረግ በሜዳልያ ተሸላሚነት)፤ ከጌጅ ኰሌጅ 6ኛ. ራሔል ተሾመ፤ በአካውንቲንግ በዲግሪ፤ 7ኛና 8ኛ) የሺሃረግና ሙሴና አስካለ ሙሴ፤ በቡዝነስ አድሚንስትሬሽን በማስተርስ፤ ከሲፒዩ ኰሌጅ /ፎቶዎቹ ተሰባስበው እጃችን እስኪገቡ በዘግየቱ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡/

✤ ብዙዎቻችን ከማናውቃቸው ነገሮች መካከል(የአቡነ አረጋዊ በሶ እምነት)፤ ና የጥቅምት 14 ክብረ በዓልን በወፍ በረር፤ ፨ የአቡነ አረጋዊ በሶ እምነት፤ በዓመት አንድ ጊዜ ጥቅምት 14 በደብራችን በሚበሩት በቅዱስ ገብረ ክርስቶስ አቡነ አረጋዊና ሙሴ ብእሴ እግዚአብሔር ክብረ በዓል ላይ በሶ ይሰጣል ይኸውም የበሶ እምነት ብዙዎችን ፈውሷል፤ በሶ የአቡነ አረጋዊ እምነት የኾነበት ምክንያጥ በታላቁ ገዳም በደብረ ዳሞ የመናንያኑ ምግብና ወደዚሁ ቦታ ለሚሄዱ ምዕመናን እንደ እምነት ተደርጎ የሚሰጥ በመኾኑ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ደብራችን መጀመሪያ ሲመሠረት ይቀድሱና ያወድሱ የነበሩት የደብረ ዳሞ ገዳም መነኰሳት ናቸው፡፡ ዘንድሮ የበሶ እምነት ያመለጣችሁ ለከርሞ ያድርሰን፡፡ ✤ የጥቅምት 14 ክብረ በዓልን በወፍ በረር ስንቃኘውዋይዜማው ማኅሌቱ ሰዐታቱና ኪዳኑ ከተከናወነ በኋላ፤ ታቦቱ ወጥቶ በዐውደ ምሕረት በቆመበት ሰዐት፤ ✣ የደብራችን ሊቃውንት፤ የደብሩን ቀለም የኾነውንና ልብን የሚመስጠውን (ብፁዓን አበዊነ አረጋዊ ሙሴ ወገብረ ክርስቶስ፤ ዘበምድር መነኑ ዘበሰማያት ዴገኑ ዘበሰማያት) የሚለውን ሲወረቡ ✣ የደብራችን የሕፃናት ክፍል የሰ/ት/ቤት አባላት ደግሞ ‹‹ዘእምደብረ ደናግል አባ ኤልያስ፤ ወትሩፈ ምግባር አረጋዊ ዘውገ ሙሴ ወገብረ ክርስቶስ›› የሚለውን ወረበዋል፡፡ ✣ የተሰጠው ትምህርት፤ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፡፡ ማቴ. 5፤ በመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ፡፡ (የቅዱሳንን ታሪክ እንዲሁም ቅዱሳኑን አሁን ካለንበት ኹኔታ አንጻር እያመሳጠሩ /የቀድሞዎቹ ቅዱሳን ከሌላ ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ ለጽድቅ ተሰደው ሲመጡ እኛ ደግሞ ዛሬ ለሥጋችን እንሰደዳለን፤ ቅዱሳን ዘር ብሔር (ቦታ ሀገር) ሳይለቻው ክርስቲያንን ወደዋል አስተምረዋል እኛ ደግሞ ሁሉ ነገራችን በዘርና በብሔር ላይ ኹኗል፤ ታዲያ ቅዱሳኑ እንዴት አያዝኑብን፤ ……… በማለት አስተምረውናል፡፡ ✤ በማታ የሰርክ ጕባኤ (የረቡዕ ልዩ የሠርክ ጕባኤ) ላይ ትምህርተ ወንጌል በመምህር ጳውሎስ መልክአ ሥላሴ ‹‹›› አሁን ካለንበት የዘመናችን በተለይም የሃገራችን ኹኔታ ጋር እያገናዘቡና እያመሳጠሩ አስተምረዋል፤ ዝማሬም በዘማሩ ቡሩክና በሲስተር ሄለን ቀርቧል፡፡ /በነገራችን ላይ የማታ የሰርክ ጕባኤ ላይ የሰዐትና መርሐ ግብር ማስተካከያ ቢደረግ ብላችሁ የሰጣችሁትን አስተያየት ግምት በማስገባት የማስተካከል ሥራ እየተሠራ ነው፤ በዚህም ምክንያ ጕባኤው 2፡05 ላይ ተጠናቋል፡፡)

የሰ/ት/ቤታችን የሕፃናት ክፍል አባላት ለጥቀምት 14 ለበዓሉ ተስማሚ የኾነውን ወረብ እያቀረቡ፡፡
የሰ/ት/ቤታችን የሕፃናት ክፍል አባላት ለጥቀምት 14 ለበዓሉ ተስማሚ የኾነውን ወረብ እያቀረቡ፡፡

ጥቅምት 14፤ ✤ ቅዱስ ገብረክርሰቶስ በዓለ እረፍቱ፤ ✤ በጋዛ ምድር ኢትዮጵያዊውን ጃንረባ ባኮስን ያጠመቀው ረድኡ ሐዋርያ ቅዱስ ፊሊጶስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ✤ አቡነ አረጋዊ ወደ ደብረ ዳሞ በዘንዶ የወጡበት፤ ✤ ቅዱስ ሙሴ እግዚአብሔር በዓለ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ✤✤ ጥቅምት 14 በአ.አ. ክብረ በዓል የሚከበርባቸውን አብያተ ክርስቲያናት እንጠቁማችሁ፡፡ ✤ በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን (የቅዱስ ገብረ ክርስቶስ አቡነ አረጋዊና ሙሴ ብእሴ እግዚአብሔር ታቦት በድርብነት ከጥንት ጀምሮ ይከብራል) ✤ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ባለውለታችን የኾነውና ለመጀመሪያ ጊዜ በሐዲስ ኪዳን የእግዚአብሔርን ቃል የተናገረን፤ የክርስትና ጥቀምት አባትና አጥማቂያችን ከ72ቱ አርድዕት አንዱ የኾነው ቅዱስ (ሐዋርያው) ፊልጶስ በሀገራችንን ውስጥ ብቸኛ በኾነውና በአ.አ ኮልፌ አጠና ተራ በሚገኘው ቤ.ክ. ደብረ ምጥማቅ ቤ.ክ በዓለ ዕረፍቱ ይከበራል፡፡ ✤ በደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤ.ክ /ዘነበ ወርቅ/ ✤ በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን (የአቡነ አረጋዊ ታቦት በድርብነት ይገኛል) ✤ በሽሮ ሜዳ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን (የአቡነ አረጋዊ ታቦት በድርብነት ይገኛል) ✤ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤ.ክ. (የአቡነ አረጋዊ ታቦት በድርብነት ይገኛል)

ዘጥቅምት ፲፩፤ ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት) (፯ኛ ዙር ዓመት፤ ፫ኛ ሳምንት፥ ዘጥቅምት ፲፩) በዓለ ቅድስት ሐና ወጲላግያ ወቅዱስ ኢያቄም ወያሬድ፡፡ ✤ ልዩ አዋጅ ዘወርኃ ጽጌ ✤  የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል ዑራኤል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን፤ የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው፤  የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ እያሳሰብን፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ እንድትጠቀሙበት ኹሉንም አስቀምጠነዋል፡፡