en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 16 129 subscribers, ranking 5 230 in the Religion & Spirituality category and 2 226 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 16 129 subscribers.

According to the latest data from 31 October, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 520 over the last 30 days and by 7 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 22.41%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 10.30% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 597 views. Within the first day, a publication typically gains 1 653 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 28.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 01 November, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

16 129
Subscribers
+724 hours
+197 days
+52030 days
Posts Archive
‹‹ ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይህ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በወርኃ ጥር ፲፰ና ፲፱/፳፻፲፩ ዓ.ም. ጋብቻችሁን ለፈጸማችሁ የሰ/ት/ቤታችን አባላት፤ #ባዩልኝ_ጌታዬነው_ከሕይወት_አየነው ጋር #ማኅሌት_የኋላው_ከፍጹም ጋር የፈጸማችሁትን ጋብቻ፤ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ፥ ያጣምራችሁ፥ ያዋሕዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ፡፡ ✤ ‹‹ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንዲሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እንደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡›› ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፖሊካርፐስ በላከው መልእክቱ ✤ ከተጋባችሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ዘርአያዕቆብ፡፡ /ከቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

ዛሬ ጥር 22 ቀን፤ #ርዕሰ_መነኰሳት_ቅዱስ_አባ_እንጦንስ_ልደቱና_ዕረፍቱ ነው፡፡ በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ብቸኞቹ 2ት የቅዱስ እንጦንስ ገዳማት፡፡ 1ኛ) #ጎንደር_ደብረ_እንጦንስ፤ በጻድቁ አፄ ዮሐንስ /ከ1659-1674/ የተመሠረተ፥ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱና ዋነኛው፡፡ ጎንደርከ300 ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ መዲና ከተማ ሆና በቆየችባቸው ዘመናት የአቡን (የጳጳስ) ቤት (መንበረ ጵጵስና) ሆኖ ያገለገለ፡፡ 2ኛ) #እንጦንስ_ኢየሱስ፤ በጣና ላይ ከሚገኙ የደሴት ገዳማት አንዱ፡፡ እንዲሁም 3ኛ) #ግብጽ_እንጦንስ_ገዳም ናቸው

ዛሬ ጥር 22 ቀን፤ #የብርሃን_መልአክ_ከሣቴ_ምሥጢር_የሆነው_ቅዱስ_ዑር/ራ/ኤል_በዓለ_ሢመቱ ነው፤ በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤ 1ኛ) በአዲስ አበባ የሚገኘውና ጥንታዊው ደብር #ደብረ_ጽጌ_ቅዱስ_ዑርኤል 2ኛ) #ግሸን_ቅዱስ_ዑርኤል 3ኛ) #ጎንደር_ደብረ_ኀይል_ቅዱስ_ዑርኤል_ወበዓታ፤ /ዛሬ ታቦተ ሕጉ ወደ ጠበል በመውረድ ይከብራል/ እንዲሁም የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል መራሔ ብርሃናት ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ናቸው፡፡

#ጥር21_አስተርእዮ_ማርያም_በዓለ_ዕረፍታ_ለማርያም_ለሶልያና #እመቤታችን_በ64_ዓመቷ_ጥር_21_በ49ዓም_ያረፈችበት_ዕለት_መታሰቢያ_ክብረ_በዓል_ነው፡፡ #ተናገራ_ዕዝራ_ተናገራ_ዳዊት_ዘመራ፤ #ዕዝራ_በመሰንቆ_ዳዊት_በበገና_እያጫወቷት፤ #ሳታውቀው_አለፈች_ያንን_መራራ_ሞት፡፡ ጌታችን ለናታችን ለቅድስት ማርያም ብዙ ቃልኪዳንን ከገባላት በኋላ፤ ቅድስት ነፍሷን ከክብርት ሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት፥ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት ደመና ጠቅሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ በአጎበር አድርገው እናትና አባቷ ወደተቀበሩበት ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲወስዷት አይሁድ አይተው፤ ልጇ ተነሳ፥ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖሩ አሁን ደግሞ እሷ ተነሳች፥ አረገች እያለ ሉያውኩን አይደለምን? ንዑ ናዓውያ ሥጋሃ ለማርያም /ኑ ሥጋዋን እናቃጥልባቸው/ ብለው ተነሱ፤ ለዚሁም ከመካከላቸውም ታውፊኒያ የተባለውን የጎበዝ አለቃ መረጡ፤ እርሱም የአልጋዋን ሸንኮር ሊያቃጥል ሲይዝ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን ዘምበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው አድርግለት ብላ አዘዘችው፤ እርሱም እጁን አድኖለታል፡፡ ከዚህ በኋላ ጌታችን ከመካከላቸው ነጥቆ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ስር አኑሯታል፡፡ ….. ሐዋርያት የቀበሯት ግን ከ6 ወር በኋላ በነሐሴ 14 ነው /ሌላውን ታሪክ በፍልሰታ ጾም ላይ ያንብቡ፤ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዲሉ፡፡››/ ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና(ለማርያም) ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ፡፡ **#ሶልያና_የእመቤታችን_የማርያም_ሌላ_ስሟ_ነው፡፡ *የእመቤታችንን ዕረፍት ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ‹‹ሞትሰ ለመዊት ይደሉ፥ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኵሉ፡፡ /ሞት ለሚሞት ሰው ሁለ የተገባ ነው፥ የማርያም ሞት ግን ሁለን ያስደንቃል፡፡›› በማለት አደንቆ ጽፏል፡፡ ***እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ የላይ ቤት (የግምጃ ቤት ማርያም) አብነትና የታች ቤት(የበዓታ) አብንትን ሁለቱንም አዘጋጅተንላችኋል፡፡ መልካም ክብረ በዓል፡፡ **ክብረ በዓሉ በሃገራችንና በዓለማችን ክፍሎች ባሉ የእመቤታችን አብያተ ክርስቲያናት የሚከብሩ ቢሆንም ግን፤ በልዩ ሁኔታ እንደ ጎንደር አዘዞ ሎዛ ማርያም ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ግን እንደ ጥምቀት በዓል፤ ከዋይዜማው ጀምሮ ወደ ጥምቀተ ተወርዶ በማደር ክብረ በዓሉ በልዩ ሁኔታ መከበሩን ልብ ይሏል፡፡ (የሎዛ ማርያምና የጥር 21 በዓል አከባበሯን ፎቶ ያላችሁ ላኩልን፡፡)

ጥር 18 ዝርወተ አጽሙ ለቅዱስ ጊዮርጊስ በተለያዩ የሃገራችንና የዓለማችን ክፍሎች ተከብሮ ውሏል፤ በተለይ ግን በጎንደር ከተማ የሚገኘው ርዕሰ አድባራት አበራ ጊዮርጊስ እንደ ጥምቀት በዓል ወደ ባሕረ ጥምቀት በዋይዜማው ወጥቶ አድሮ ነው የሚመለሰው፤ እኛ ለዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኘው የደብረ ጽባሕ ቅዱስ ጊዮርጊስ የገበያ ቦታውን ባርኮ ሲመለስ የሚያሳየውን በፎቶ አቅርበንላችኋል /በፎቶ ላይየምታይዋቸው ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ታላቁ አባት ናቸው/ ፡፡ የጎንደር አበራ ጊዮርጊስ ፎቶ ያላችሁ ላኩልን፡፡ /በነገራችን ላይ በጎንደር በጥር ወር የሚከበሩ በዓላት ወደ ጥምቀተ ባሕር በመውጣት የሚከበሩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ጥር 18 አበራ ጊዮርጊስ፤ ጥር 21 ሎዛ ማርያም፣ ጥር 22 ቅዱስ ዑራኤል (በዓታ ያለው)፤ ጥር 25 ቅዱስ መርቆሬዎስ በተለይ በገጠሩ አካባቢ፡፡ እርሱ እንደ ንብ አውራ ፈረሱ እንደ አሞራ፤ ጊዮርጊስ፥ ጊዮርጊስ፥ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያን አደራ፡፡ ሰአል ለነ ጊዮርጊስ፤ ሰማዕተ ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ ዘሐረፀከ ዱድያኖስ፤ ወወገረከ ደብረ ይድራስ፤ ዘዘረወከ በነፋስ፡፡

አዲስ ቤተ ክርስቲያን ሲሰራ (ቅዳሴ ቤት ሲከበር) ወይም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ሲመረቅ የሚባለውን #ሥርዐተ_ማኅሌት እነሆ አቅርበንላችኋል፡፡ (ቤተ ክርስቲያኑ የቅዱስ ገብርኤል ከሆነ የሚቆመው ማኅሌት ከሌሎቹ ሁሉ ስለሚለይ የማኅሌቱን ጽሑፍ ያለ ሐረግ አዘጋጅተነዋል፡፡) #የሚመረቁ_አብያተ_ክርስቲያናትን_እንጠቁማችሁ #እናንተም_ጨምሩባቸው፤ #አዲስ_አበባ_ደብረ_በረከት_ቅዱስ_ገብርኤል፤ ካራቆሬ፤ አየር ጤና አጠገብ፤ ጅማ በር (ጥር 18 ስባረ ዓጽሙ ለጊዮርጊስ፤ ጥር 19 ቅዳሴ ቤቱ ለቅዱስ ገብርኤል) #መጠቆሚያ_ማርያም፤ ጊንጪ፤ በ1942ዓ.ም. የተመሠረተች፤ /ጥር 21 ይመረቃል/፤ #ሰንበት_ትምህርት_ቤታችን_ወደዚህች_ቤተ_ክርስቲያን_ለመሄድ_የምትፈልጉ_በምረቃዋ_ዋይዜማ_ጥር_20_ጀምሮ_ጉዞ_አዘጋጅቷል_/ #ሻምቡ_ከምቦልቻ_ማርያም፤ ሆሮ ጉድሩ፥ ወለጋ፤ /ጥር 21 ይመረቃል/ #ሻምቡ_ቃዎ_ጊዮርጊስ፤ ሆሮ ጉድሩ፥ ወለጋ፤ /ሚያዝያ 21 ይመረቃል/ #ተጎራ_ማርያም፥ መርሐ ቤቴ፥ ሰሜን ሸዋ /ጥር 21 ይመረቃል/ /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ. ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት/

በባሌ ሀገረ ስብከት ሮቤ ከተማ የሚገኘው የመ/መ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ረቡዕ ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ለጊዜው ባልታወቀ መንስኤ መቃጠሉን መ/ር ያሬድ ገ/ማርያም የወረዳው ቤተ ክህነት ጸሐፊ ገለጹ፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ቃለ ምዕዳን በሰጡበት ወቅት "ልጆቼ ሁሉም ፈቃደ እገግዚአብሔር ነው፤ ቃጠሎው ከምን እንደሆነ እግዚአብሔር ይመርምር" ብለዋል፡፡ ችግሩን ለመፍታት ክርስቲያንና ቀናነት ያላቸው ሙስሊም በአንድነት ተባብረዋል፡፡ #ጸልዩ_በእንተ_ሰላመ_ቤተ_ክርስቲያን_አሐቲ_ቅድስት_ጕባኤ_እንተ_ሐዋርያት_ርትዕት_በኀበ_እግዚአብሔር፡፡ (ሐዋርያት በሰበሰቧት በእግዚአብሔር ዘንድ ሰለቀናች፤ ክብርት ስለምትኾን አንዲት ቤተ ክርስቲያን ጸልዩ፡፡) #ጸልዩ_በእንተ_ሰላም_ፍጽምት_ወፍቅር_ተአምኁ_በበይናቲክሙ_በአምኃ_ቅድሳት፡፡ (ፍጽምት ስለምትኾን ሰላምና ፍቅር ጸልዩ፤ እርስ በእርሳችሁ በተለየች ሰላምታ እጅ ተነሳሱ፡፡) #አድኅነኒ_ወባልሐኒ_እምእዴሆሙ_ለደቂቀ_ነኪር_እለ_ከንቶ_ነበበ_አፉሆሙ_ወየማኖሙኒ_የማነ_ዐመፃ፡፡ (አድነኝ አፋቸውም ምናምን ከሚናገር ቀኛቸውም የሐሰት ቀኝ ከኾነ፤ ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ፡፡) /#መዝ.፻፵፫፥፯/ ✤#በሐኪ_በሐኪ_ቤተ_ክርስቲያን_እምነ፤ #ግበሪ_ጸሎተነ_በእንቲአነ፤ #እምኀይለ_ጸላዒ_ወፀር_ዕቀቢ_ኪያነ፤ #ትንባሌኪ_የሃሉ_ምስሌነ፡፡ ✤‹‹#እግዚኦ በመዓትከ ኢትቅሰፈነ፥ ወበመቅሰፍትከ ኢትገስጸነ፡፡›› መዝ.ዳዊት

እንኳን ደስ አለን፤ በመዲናችን በአ.አ. የቤተ ክርስቲያን ቤተ መዘክሮቻችንን ቊጥር ወደ 9 ከፍ የሚያደርገውን ቤተ መዘክር (Museum) በጥንታዊቷ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ጥር 4/2011ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተመርቆ ለእይታ ክፍት ሆነ፡፡ በእለቱም ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት ተገኝተዋል፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኙ 9ኙ ቤተ መዘክሮቻችን የሚከተሉት ሲኾኑ እየሄዳችሁ ታዩ ዘንድ እንጋብዛለን፡፡ #የጠቅላይ ቤተ ክህነት መንበረ ፓትርያርክ ቤተ መዘክር(Museum) ፤ #እንጦጦ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጕኤል ወኤልያስ ቤተ መዘክር(Museum) ፤ #እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ማርያም ቤተ መዘክር(Museum) ፤ #ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ቤተ መዘክር(Museum) ፤ #መናገሻ ገተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ መዘክር(Museum) ፤ #ጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል የአቡነ ቴዎፍሎስ መታሰበያ ቤተ መዘክር(Museum) ፤ #መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ መዘክር(Museum) ፤ #ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤተ መዘክር(Museum) ፤ #እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳማ ቤተ መዘክር(Museum) ፡፡ (ሰፋ ያለ ታሪካቸውን ግን አዲስ በጀመርነው ‹‹ገዳማትና አድባራት›› መርሐ ግብር ላይ ከቤተ ክርስቲያናቸው ታሪክ ጋራ አብረን እናቀርባለን፡፡) #እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም፡፡ ይህች ገዳም ታሪኳ ከታላቁ ገዳማችን ዋልድባ (ገዳመ ዋሊ) ለ2ኛ ጊዜ መሥፋፋት (መመሥረት ጋር) የተያያዘ ታሪክ ያላት ናት፡፡ ይኸውም የሸዋ አባቶች ወደ ዋልድባ #በ485_ዓ_ም_በንጉሥ_አልአሜዳ_ዘመነ_መንግሥት_ባቀኑ_ጊዜ_ለ3_ወራት_የተሰባሰቡባት_ቦታ_ናት፡፡ እነዚህም አበው ከመኖሪያ ቀዬቸው (ቡልጋ/ምንጃር/……) ሁለት ታቦታትን (ታቦተ ኪዳነ ምሕረት ዘምሕረት አምባና፤ ታቦተ መድኀኔ ዓለም ዘአብዬ ገዳምን) ይዘው ነበር፤ ይዘዋት በመጡት ታቦተ ኪዳነ ምሕረትም ገዳመ ሐመረ ኖኅን መሥረተዋል፡፡ የመድኀኔዓለም ታቦትን ደግሞ በታላቁ ገዳም በዋልድባ አኑረዋል፡፡ ይህች #ሐመረ_ኖኅ_፤ *በ500 ዓ.ም. በአባ ሊባኖስ የአንድነት ገዳም ሆና ተስፋፍታ ተቋቋመች፡፡ *በ9ኛ መቶ ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት የአክሱም ጽዮንን ቤተ መቅደስ ለማቃጠል ስትነሳ ንጉሡ አንበሣ ውድም ታቦተ ጽዮንን በምሥጢር በማስያዝ ወደ ሸዋ መጥተው በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ገዳም ታቦተ ጽዮንን አሳድረው ወደ ዝዋይ ደሴት ሲሄዱ ለገዳሟ ንዋየ ቅድሰት ስጦታ አበርክተዋል፤ ጠበሏን ተጠምቀው ቦታዋን መርቀው ሄደዋል፡፡ *በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከንጉሥ ላሊበላ ጋር ወደ ዝቋላ አምባ ሲመጡ በዚህች ገዳም በእንግድነት አድረው በጠበሏ ተጠምቀው ቦታውን ባርከዋል፡፡ *አፄ ዘርዓ ያዕቆብም ወደዚህች ገዳም መጥተው አቀማመጧንና የጠበሏን ፈዋሽነት ተመልክተዋል፤ ‹‹ዳሯ እሳት መሐሏ ገነት ይሁን›› ብለው ብዙ ስጦታ አበርክተዋል፡፡ *አፄ ልብነ ድንግልም ወደ ገዳሟ መጥተው ተማህጽኖ አድርገው በጠበሏ ተጠምቀው ታቦተ ልደታንና ብዙ ንዋየ ቅድሳት ሰጥተው ሄደዋል፡፡ *በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት ይህች ገዳም ሐመረ ኖኅ ኪዳነምህረት ገዳም ተብላ ተሰይማለች፤ አሁን ያለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንም ታንጿል፡፡ ***ይህች ቦታ ከታላቁ ገዳም ከዋልድባ ጋር አሁንም ግንኙነቷ እንደጠነከረ ነው፤ በዋልድባ ያሉ አባቶች ለተለያየ ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ በዋነኛነት የሚያርፉባት ጥንተ ርስታቸውም ናት፡፡ ይህች ቦታ በርካት ቅዱሳን በኪደተ እግር የረገጧት በመኾኗ የብዙ መነኰሳት መጠጊያ ናት፡፡ ጠበሏም የአጋንንት ድል መንሻ፥ የሕሙማን መፈወሻ፥ የአእምሮ ማደሻ ናት፡፡ የእመቤታችንን ቃል ኪዳን ለማግኘትም በአዲስ አበባ ከሚገኙ ቦታዎች ብዙ ጊዜ ለሱባኤ ከሚመረጡ ቦታዎችም አንዷ ናት፡፡ **ወደዚህች ገዳም በየወሩ ለኪዳነ ምሕረት የሚጎርፈው ምዕመን ኈልቈ መሳፍርት ያልተገኘለትና በሃገራችን በየወሩ ምዕመናን በመሳለም ትልቁን ቊጥር ይዟል፡፡ የዓመታዊ ክብረ በዓሉንማ ምንን እንነግራችኋለን፡፡ (ከሽሮ ሜዳ ታክሲ ቦታው ድረስ ያደርስዎታል፡፡)