en
Feedback
የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

Open in Telegram

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።

Show more
2 635
Subscribers
No data24 hours
+157 days
+5530 days
Posts Archive
በሰንበት ትምህርት ቤታችን የተልዕኮ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ከ350 በላይ የ5 ኛ ዙር የተልዕኮ ት/ት ተማሪዎች የነገረ ቅዱሳን ትምህርት በመስጠት በትናንትናው ዕለት እሑድ ግንቦት 30/2018 ዓ.
+5
በሰንበት ትምህርት ቤታችን የተልዕኮ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ከ350 በላይ የ5 ኛ ዙር የተልዕኮ ት/ት ተማሪዎች የነገረ ቅዱሳን ትምህርት በመስጠት በትናንትናው ዕለት እሑድ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም ጉባኤ ተከናወነ።

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ወርሐዊ የባለትዳር አባላት ጉባኤ ——————————————— እሑድ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም ከ5:00- 7:00 ጉባኤው በወር አንድ ቀን ብቻ የሚ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን   ወርሐዊ የባለትዳር አባላት ጉባኤ ——————————————— እሑድ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም   ከ5:00- 7:00 ጉባኤው በወር አንድ ቀን ብቻ የሚከናወን በመሆኑ በእለቱ  ተገኝተው ቃለ እግዚአብሔርን ይመገቡ።             የባለትዳር ጉባኤ ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com

'' ነገረ ክርስቶስ በገድላትና በድርሳናተ'' ክፍል - 2 በመ/ር ዲ/ን ቢኒያም አድማሱ የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 29/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በ
'' ነገረ ክርስቶስ በገድላትና በድርሳናተ''                   ክፍል - 2    በመ/ር  ዲ/ን ቢኒያም አድማሱ የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር  ዛሬ ቅዳሜ  ግንቦት 29/2018 ዓ.ም ከምሽቱ  11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ  ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ። የቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን  https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com/

የሐዘን መግለጫ የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነችው የእህታችን ምዕራፍ እንዳሉ ወላጅ አባት አርፈዋል። ሥርዓተ ቀብራቸው ነገ ግንቦት 28/2018 ዓ.ም በቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤ/ክ ከቀኑ 6:00  የሚፈጸም በመሆኑ በቀብሩ ላይ መገኘት  የምትችሉ ተገኝተን እንዲሁም መኖሪያ ቤታቸው  ጎላ በላይኛው መግቢያ በር አካባቢ በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን።  የአባታችንን ነፍስ  ይማርልን ። ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያናችን እና በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት  አባታዊ መልእክት አስተላለፉ። ቅዱስነታቸው  ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን  መልእክት እንደሚከተለው  ነው፦ መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ‹‹ወረሰዩ አብድንቲሆሙ ለአግብርቲከ መብልዐ ለአዕዋፈ ሰማይ፣ ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊተ ገዳም፦ የአገልጋዮችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የቅዱሳንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት።›› (መዝሙረ ዳዊት ፸፰፥፪) በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው። የእምነት ነፃነት ተደፍሮ መቶ ዓመታት ያስቆጠረው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በተቃጠለበት፣ እንዲሁም የካራ ኩፍቴና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በተዘረፈበት በዚህ ክፉ ቀን፤ በርካታ ምእመናን በግፍ መሰዋታቸውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ ያሳዘነ ክስተት ነው። የሰላም፣ የፍቅርና የታሪክ ማህደር የሆነችው ቤተ ክርስቲያን በምድራዊ መከራ ውስጥ ያሉትን ምእመናን በምታጽናናበት በዚህ ወቅት ራሷ በፈተና ውስጥ ሆና ከመቸገሯም በላይ በአርሲ ምድር በተደጋጋሚ የሚስተዋለው በደልና ግፍ በሁላችንም ልቡና ውስጥ "እስከ መቼ?" የሚል የቁጭት እና የኀዘን ጥያቄን ፈጥሯል። በመሆኑም ይህ መከራ እያበቃ ሳይሆን እየሰፋ በመምጣቱ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና በየመዋቅሩ ያላችሁ ሓላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ በማቅረብ ከታሪክ ባለዕዳነት ትድኑ ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም አበክረን እናሳስባለን። በየአካባቢው የምትገኙ ምእመናንና መላው ኢትዮጵያውያንም በወንድማማችነት መንፈስ ተጋግዛችሁ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና በጸሎት ከቤተክርስቲያናችን ጎን እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያናችን ለሰላም፣ ለይቅርታና ለሰው ልጆች ክብር ሁል ጊዜ የምትቆም መሆኑን በመግለጽ ይህንን የኀዘን ሰዓት አምላካችን በምሕረቱ ያሳልፍልን፣ የሞቱትን ነፍሶቻቸውን በመንግሥቱ ይቀበልልን፣ የተጎዱትንም በቸርነቱ ያጽናናልን በማለት አባታዊ የኀዘን መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን። እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን።  አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ © የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ወርሐዊ የባለትዳር አባላት ጉባኤ ——————————————— እሑድ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም ከ5:00- 7:00 ጉባኤው በወር አንድ ቀን ብቻ የሚ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን   ወርሐዊ የባለትዳር አባላት ጉባኤ ——————————————— እሑድ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም   ከ5:00- 7:00 ጉባኤው በወር አንድ ቀን ብቻ የሚከናወን በመሆኑ በእለቱ  ተገኝተው ቃለ እግዚአብሔርን ይመገቡ።             የባለትዳር ጉባኤ ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com

በአርሲ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ወረዳዎች በዘጠኝ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ግድያ መፈጸሙን በመግለጽ ሀገረ ስብከቱ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ቅዱስ ሲኖዶስ ከመንግሥት ጋር በመነጋ
+1
በአርሲ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ወረዳዎች በዘጠኝ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ግድያ መፈጸሙን በመግለጽ ሀገረ ስብከቱ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ቅዱስ ሲኖዶስ ከመንግሥት ጋር በመነጋገር መፍትሄ እንዲሰጡት ጠየቀ። ©Eotc