የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
Открыть в Telegram
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Больше2 795
Подписчики
Нет данных24 часа
+77 дней
+2530 дней
Архив постов
#አቡነ_አረጋዊ እና #ቅዱስ_ሚካኤል
በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበሩ አባቶች አንዱ ጻድቁ አቡነ አረጋዊ ናቸው። ጻድቁ የተወለዱት በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው "ንጉሥ ይስሐቅ" እና "ቅድስት እድና" ይባላሉ ።
የተወለዱበት አካባቢም ሮም ነው ። ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው። ወላጆቻቸው "ዘሚካኤል" ሲሏቸው በበርሃ "ገብረ አምላክ" ተብለዋል። በኢትዮጵያ ደግሞ "አረጋዊ" ይባላሉ። አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ። በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ጳኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል። ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግሥት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል። "የት ልሒድ?" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮጵያን አሳያቸው። ተመልሰውም ለስምንት ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየኋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከስምንቱ ጋር ከቄልኬዶን ጉባዔ በኋላ በ፬፻፶፩ ዓም ወደ ኢትዮጵያ መጡ ።ከዘጠኙ ቅዳሳን ወደ ኢትዮጵያ ከሮምና ከመካከለኛው ምሥራቅ ከፈለሱት አንዱ አቡነ አረጋዊ ናቸው ።
በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ። ወደ ሃገራችን የመጡ በአራት መቶ ሰባዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል። በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጽሐፍትን እየተረጎሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል ። አቡነ አረጋዊ ለብዙ ጊዜ በዓት ፍለጋ ደክመዋል ። በመጨረሻም ደብረ ዳሞ ማርካቸዋለች ።
እያስተማሩና እየፈወሱ ደብረ ዳሞ ሲደርሱ ወደ ሰማይ ቀጥ ያለች ተራራ ሰው በምንም መንገድ ሊደርስባት ወይም ሊወጣባት የማይቻለውን ቦታ እሳቸው ተመኙዋት ። ከዚያም "አሁን ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ" እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግሩ ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነቢዩ ዳዊት ላይ አድሮ በመዝሙር ፺፣፺፩:፲፩ - ፲፮ ላይ “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና ፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል ። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። እንዳለው የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስደሳ ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ #ቅዱስ_ሚካኤል ሰይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል ፡፡ ወዲያው ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው አመስግነዋል ፡፡ ቦታውም ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሏል ፡፡ በዚያ ዕለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምድራዊ ሕብስት አልተመገቡም ፡፡ በሰንበተ ክርስታያን ከቅዳሴ በኋላ ሕብስተ ሰማያዊ እያመጡላች ይመገቡ ነበር እንጂ፡፡ ኋላ ግን ዜና ጽድቃቸውን ሰምተው ከስድስት ሺህ ያላነሱ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበውላቸዋል ፡፡
ክፍል - 2 ይቀጥላል...
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
"አልቦ መልአክ ዘከማከ መሐሪ ወመፍቀሬ ሰብእ፤ ዘይሰአል በእንተ ኃጣኦን።"
«ስለ ኃጢአተኞች የሚለምንና የሚማልድ እንደ አንተ ያለ ርኅሩኅና ሰውን ወዳጅ መልአክ የለም።»
#ሐዋርያው_ወንጌላዊ_ቅዱስ_ማቴዎስበዚችም ቀን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የአንዱ የወንጌላውያ ማቴዎስ የዕረፍቱና የምስክርነቱ መታሰቢያ ነው። በይህም እንዲህ ነው በብዙ አገሮች ውስጥ አስተምሮ ብዙዎች ሰዎችን እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ ከመለሰ በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ወደ ካህናት አገር እንዲሔድ አዘዘው። ተጒዞም ወደ ከተማው መግቢያ ደጅ በደረሰ ጊዜ አንድ ወጣት ብላቴና አገኘ ወደ ከተማው ለመግባት እንዴት እንደሚችል ጠየቀው ወጣቱ ብላቴናም እንዲህ ብሎ መለሰለት "አንተ ግን ራስህንና ጽሕምህን ካልተላጨህ በእጅህም ዘንባባ ካልያዝክ መግባት አትችልም"። ይህም ነገር ለሐዋርያ ማቴዎስ አስጨንቆት ሲያዝን አስቀድሞ ያነጋገረው ያ ወጣት ብላቴና ዳግመኛ በስሙ ጠራው። ሐዋርያውም "ወዴት ታውቀኛለህ" አለው እርሱም "እኔ ጌታህ ኢየሱስ ነኝ አሁንም እንደ ነገርኩህ አድርግ እኔም ከአንተ ጋር አለሁ ከአንተም አልርቅም" አለው። ከዚህም በኋላ ጌታችን እንዳዘዘው አድርጎ ወደ ካህናት አገር ገባ ለአማልክት ካህናት አለቃቸው ከሆነ ከአርሚስ ጋር ተገናኘ ከእርሱም ጋር ስለ አማልክቶቻቸው ተነጋገረና ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ጣዖቶቻቸውን አቃጠላቸው እንዲህም አላቸው። "ራሳቸውን ማዳን ያልቻሉ ሌላውን እንዴት ያድናሉ" በዚያንም ጊዜ ከአርሚስ ጋር ብዙዎች ሰዎች አምነው አጠመቃቸው ከሰማይም ማዕድ አውርዶ መገባቸው። የሀገሩም ንጉሥ ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ ከአርሚስ ጋር ሐዋርያውን ወደ እሳት ጨመረው ጌታችንም አዳናቸው። ከዚህም በኋላ በሚአሠቃያቸው ነገር ሲአስብ እነሆ ልጁ እንደ ሞተ ነገሩት እጅግም አዘነ። ሐዋርያ ማቴዎስም "ልጅህን እንዲያስነሡት ወደ አማልክትህ ለምን አትለምንም" አለው ንጉሡም "የሞተ ማንሣት እንዴት አማልክት ይችላሉ" ብሎ መለሰ። ቅዱስ ማቴዎስም "ብታምንስ የእኛ አምላክ ልጅህን ማሥነሣት ይችላል" አለው። ንጉሡም "ልጄ ከተነሣ እኔ አምናለሁ" አለ በዚያን ጊዜ ሐዋርያው ክብር ይገባውና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለየና የንጉሡን ልጅ ከሞት አስነሣው። ንጉሡም ክብር ይግባውና በጌታችን አመነ የአገር ሰዎች ሁሉም አመኑ የቀናች ሃይማኖትንም አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው ካህናትንም ሾመላቸው ከዚህም በኋላ ወደ ሌሎች አገሮች ሒዶ ወንጌልን አስተማረ። ከዚህም አስቀድሞ በደመና ተነጥቆ ብሔረ ብፁዓን ገብቷል ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስን ሁል ጊዜ በየበዓላቸው ወደ እነርሱ ሲመጣ አየው ከእርሱም ጋር መቶ አርባ ሽህ ሕፃናት አሉ መላእክትም ሁሉ በዙሪያው ቁመው ያመሰግኑታል። በብሔረ ብፁዓን ስለ ሚኖሩ ወገኖችም ድንቅ ስለሆነ ሥራቸው ሁሉ ከሐዋርያው በኋላ ወደርሳቸው የገባ ዘሲማስ ቀሲስ ምስክር ሆነ። ከዚህም በኋላ የሐዋርያው የተጋድሎውና የምስክርነቱ ፍጻሜ ሲቀርብ ወደ አንዲት ከተማ ገብቶ አስተማረ ብዙዎችንም አሳመነ አገረ ገዢውም ይዞ ከወህኒ ቤት ጨመረው። በዚያም አንድ እጅግ የሚያዝን እሥረኛ አይቶ ስለኀዘኑ ጠየቀው እርሱም ብዙ የሆነ የጌታው ገንዘብ ከባሕር እንደ ሠጠመበት ነገረው ሐዋርያ ማቴዎስም "ወደ ዕገሌ ባሕር ዳርቻ ሒድ ወርቅን የተመላ ከረጢትንም ታገኛለህ ያንንም ወርቅ ወስደህ ለጌታህ ስጥ" አለው። ስለዚህም ድንቅ ተአምር ብዙዎች ክብር ይግባወና በጌታችን አመኑ። መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ቅዱስ ማቴዎስንም ራሱን እንዲቆርጡ ሥጋውንም ለሰማይ ወፎች እንዲጥሉ አዘዘ። ከከተማውም አውጥተው ቈረጡት ምእመናንም በሥውር መጥተው ወስደው በመልካም ቦታ አኖሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው በቅዱስ ማቴዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያ ቀን ጀምሮ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት ላይ በኀይል መጣ፤ ሳሙኤልም ወደ አርማቴም ሄደ። 1ኛ ሳሙ ፲፮፥፲፫በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
"ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው..." ማቴ 26፥41
የስራ ማስታወቂያ
1. ጉዳይ አስፈፃሚ
ከሰኞ-ቅዳሜ/በስራሰዓት
ደሞዝ በስምምነት
የትምህርት ደረጃ 10 እና ከዛ በላይ
ጥሩ የመግባባትችሎታያለው
2.ሴልስ
10ክፍል
ደሞዝ በስምምነት
ወንድ/ሴት 2ሰው
የስራቦታ=ቴውድሮስ አደባባይ
3.ኮንስትራክሽን ሰዓት ተቆጣጣሪ
ደሞዝ=10,000
ቦታ=ተክለሃይማኖት
ለበለጠ መረጃ 0920978623/0912330902/0911091598
ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።... ማቴ ፭፥፲፩-፲፪በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
#ሦስት_ቀን_ቀረው
"...ወዘተወክፈ ጻድቅ በስመ ጻድቅ ዐስበ ጻድቅ ይነስእ...ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።" ማቴ ፲÷፶፩
ጥቅምት 14 በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የጻድቁ አባት የአቡነ አረጋዊ ዓመታዊ በዓል በደብራችን ታቦተ ህጉ ወጥቶ ይከበራል። እርሶም ተገኝተው የበረከቱ ተካፋይ በአክብሮት ተጠርተዋል።
"#የጻድቅ_መታሰቢያ_ለበረከት_ነው፤" ምሳ ፲÷፯
መረጃው ለብዙዎች እንዲደርስ ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።
እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።... ማር ፲፫፥፱በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
ለነባር ወራቢያን በሙሉ
ጉዳዩ :- መደበኛ ወራቢያን ስለመለየት
ከላይ ለመግለጽ እንደሞከረው በሰንበት ት/ቤታችን ከድሮ ጀምሮ በተለያየ ዘመን የወረብ አገልግሎት ሲሰጥ እስከአሁን ትውልድ ድረስ ደርሷል። በመሆኑም
#1. በተለያየ ዘመን በወረብ አገልግሎት ስናገለግል የቆየን ምን ያህል አባላት እንዳለን በሰ/ት/ቤታችን ቁጥሩ ስለማይታወቅ
#2. በተለያየ የወረብ አስጠኚ ወንድሞች ስለተማርን መዋሀድ ስላስቸገረን
#3. ቋሚ የሆነ የጥናት ቀን ስላልተመቻቸ
#4. በቤት ርቀት, በትምህርት, በተለያዩ ነገሮች ከአገልግሎቱ ስለራቅን ይህን እና በመሳሰሉ ምክንያቶች አሁን ላይ አገልግሎቱ ላይ ባለመሳተፈችን እንደ ሰ/ት/ቤት በሚፈለገው መጠን ፣ ጊዜው እንደሚፈቅድው መጠን ውጤት ላይ አልደረስንም። በመሆኑም አሁን ላይ እንደ መዝሙርና በዓላት ክፍል
#1. ሁላችንም ከዚህ አገልግሎት የራቅን ለቤታችን ለሰ/ት/ቤታችን መሰረት አስቀምጠን እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ እንድናልፍ ይህ የሚመለከተን አባላት በሙሉ ከዚህ በታች የተቀመጠው ሊንክ ውስጥ በመግባት join እንድታደርጉ
#2. እዚህ ግሩፕ ውስጥ ሁላችንም አንድ የምያደርገን ትምህርት እንደ አዲስ ስለምንማር ራሳችን እንድናዘጋጅ
#3. ይህን ትምህርት በአጭር ጊዜ ውስጥ ጨርሰን እንደ መዝሙር እና በዓላት ክፍል የተዘጋጀ ለሰ/ት/ቤታችን አዲስ አሻራ አዲስ ስራ ስለምንሰራ የዚህ ታሪካዊ ዘመን ተሻጋሪ ስራ እንድንሳተፍ
#4. በዚህ ግሩፕ ውስጥ ያለን አባላት ብቻ ለጊዜው የክብረ በዓላት ጥናት አጥንተን የምንሳተፈው እኛ ስለሆንን ላልሰሙ አባላት ትነግሩልን ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።
#5. በተለያየ ሁኔታም ያለን ማለትም በቤትም ርቀት, በትምህርት, በሥራ መገኘት የማንችል አባላትም በዚህ ግሩፕ ውስጥ መቀላቀል ለናንተ የተለየ የጥናት ሁኔታ ስለተመቻቸ እንድትቀላቀሉን።
#6. በተለይ የድሮ አባላት በወረብ አገልግሎት የነበራችሁ የወረብ ፍቅሩን ከናንተ በላይ ማንም የሚያውቀው የለምና ላሳደገቻችሁ ለፍኖተ ብርሃን አሁን ታስፈልጋላችሁና እንድትገኙ እናሳስባለን።
መልካም የአገልግሎት ጊዜ
መዝሙርና በዓላት ክፍል
https://t.me/finotwereb2019
Repost from ፍኖተ ወረብ ወመዝሙር
ለነባር ወራቢያን በሙሉ
ጉዳዩ :- መደበኛ ወራቢያን ስለመለየት
ከላይ ለመግለጽ እንደሞከረው በሰንበት ት/ቤታችን ከድሮ ጀምሮ በተለያየ ዘመን የወረብ አገልግሎት ሲሰጥ እስከአሁን ትውልድ ድረስ ደርሷል። በመሆኑም
#1. በተለያየ ዘመን በወረብ አገልግሎት ስናገለግል የቆየን ምን ያህል አባላት እንዳለን በሰ/ት/ቤታችን ቁጥሩ ስለማይታወቅ
#2. በተለያየ የወረብ አስጠኚ ወንድሞች ስለተማርን መዋሀድ ስላስቸገረን
#3. ቋሚ የሆነ የጥናት ቀን ስላልተመቻቸ
#4. በቤት ርቀት, በትምህርት, በተለያዩ ነገሮች ከአገልግሎቱ ስለራቅን ይህን እና በመሳሰሉ ምክንያቶች አሁን ላይ አገልግሎቱ ላይ ባለመሳተፈችን እንደ ሰ/ት/ቤት በሚፈለገው መጠን ፣ ጊዜው እንደሚፈቅድው መጠን ውጤት ላይ አልደረስንም። በመሆኑም አሁን ላይ እንደ መዝሙርና በዓላት ክፍል
#1. ሁላችንም ከዚህ አገልግሎት የራቅን ለቤታችን ለሰ/ት/ቤታችን መሰረት አስቀምጠን እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ እንድናልፍ ይህ የሚመለከተን አባላት በሙሉ ከዚህ በታች የተቀመጠው ሊንክ ውስጥ በመግባት join እንድታደርጉ
#2. እዚህ ግሩፕ ውስጥ ሁላችንም አንድ የምያደርገን ትምህርት እንደ አዲስ ስለምንማር ራሳችን እንድናዘጋጅ
#3. ይህን ትምህርት በአጭር ጊዜ ውስጥ ጨርሰን እንደ መዝሙር እና በዓላት ክፍል የተዘጋጀ ለሰ/ት/ቤታችን አዲስ አሻራ አዲስ ስራ ስለምንሰራ የዚህ ታሪካዊ ዘመን ተሻጋሪ ስራ እንድንሳተፍ
#4. በዚህ ግሩፕ ውስጥ ያለን አባላት ብቻ ለጊዜው የክብረ በዓላት ጥናት አጥንተን የምንሳተፈው እኛ ስለሆንን ላልሰሙ አባላት ትነግሩልን ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።
#5. በተለያየ ሁኔታም ያለን ማለትም በቤትም ርቀት, በትምህርት, በሥራ መገኘት የማንችል አባላትም በዚህ ግሩፕ ውስጥ መቀላቀል ለናንተ የተለየ የጥናት ሁኔታ ስለተመቻቸ እንድትቀላቀሉን።
#6. በተለይ የድሮ አባላት በወረብ አገልግሎት የነበራችሁ የወረብ ፍቅሩን ከናንተ በላይ ማንም የሚያውቀው የለምና ላሳደገቻችሁ ለፍኖተ ብርሃን አሁን ታስፈልጋላችሁና እንድትገኙ እናሳስባለን።
መልካም የአገልግሎት ጊዜ
መዝሙርና በዓላት ክፍል
https://t.me/finotwereb2019
እንኳን ለፃድቁ አባታችን ለአቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
ስማቹ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የባለትዳር ክፍል አባላት የጥቅምት አቡነ አረጋዊ ዘማሪ መሆናችሁን እናሳውቃለን።
1 ወ/ሮ ባንቺዋሉ ዋሲሁን
2 ወ/ሮ እጸገነት ቱፉ
3 ወ/ሮ አዳነች መሐሬ
4 አቶ ወርቅነህ ባህሩ
5 ወ/ቀለሟ ባደግ
6 ወ/ ሙሉበርሔ
7 ወ/ሮ እጸገነት ፍቅሪ
8 ወ/ሮ ትእግስት ተስፉዮ
9 ወ/ሮ ገነት ሙላት
10 አቶ ማሙሽ ኡርጌሳ
11 ወ/ሮ መቅደስ ቀጸላ
12 ወ/ሮ ኤደን በቀለ
13 ወ/ሮ ሰናይት ተሰማ
14 ወ/ሮ ፍቅርተ ታዬ
15 ወ/ሮ ቡርቱካን አበበ
16 አቶ ወድሙ ኤርሚሹ
17 አቶ ደረጀ አበራ
18 ወ/ሮ አበባ ተስፉዮ
19 ወ/ሮ ትእግስት አማረ
20 ወ/ሮ ሰላማዊት ይልማ
21 አቶ ሙሉቀን አሰፉ
22 አቶ ተስፉለም ጣዕመ
23 ወ/ሮ ሩት ዋሲሁን
24 ወ/ሮ ይርገድ በቀለ
25 ወ/ሮ ሽብሬ ካሳ
26 አቶ ሽፈራው ታሬኩ
27 ወ/ሮ አለምገነት ፉንቱ
28 አቶ ሙሴ መሐሬ
29 ወ/ሮ አስኳል ተ/ሀይማኖት
30 ወ/ሮ የምስራች ተስፉዮ
31 ወ/መሰረት አሰፉ
32 ወ/ሮ ፊሬወይኒ ኤቢሳ
33 ወ/ሮ ኢሌኒ ሸንተማ
34 ወ/ሮ ውቅነሽ ጌታቸው
35 ወ/ሮ ሳባ አየለ
36 ወ/እመቤት ጌታሁን
37 አቶ ወገኔ ግዛቸው
38 አቶ አለሙ ጉደታ
39. ወ/ሮ ኤደን ከበደ
40. አቶ ደረጄ ወ/ዮሐንስ
41. አቶ ተስፋዬ መንግስቱ
42. አቶ እስጢፋኖስ ብርሃኑ
43. ወ/ሮ ፋሲካ መኮንን
44. አቶ ወደርየለህ ነጋሽ
45. አቶ ወንድምዬ አዋሽ
46. ወ/ሮ መቅደላዊት ጌታቸው
47. ወ/ሮ ሉላ አፈወርቅ
48. ወ/ሮ ዮርዳኖስ አፈወርቅ
49. ወ/ሮ ገነት ሰለሞን
50. ወ/ሮ ዮዲት ገ/ሥላሴ
51. ጌታቸው ግርማ
ከላይ ስማችሁ ከተዘረዘረው ውስጥ በዕለቱ በተለያዩ ምክንያቶች ማገልገል የማትችሉ አባላት ከወዲሁ አሳውቁን፤ ሳያስፈቅዱ መቅረት አይገባም። ጥያቄና አስተያየት ካለ በስልክ ቁጥር
+251913005033
+251911147634
+251911692562
ማቅረብ ይቻላል።
የባለትዳር ክፍል ኮሚቴ
ቶማስም፦ ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን? አለው። ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል አለው። ዮሐ ፲፬፥፭-፯በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
ኑ!
ጥቅምት 14 በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የጻድቁ አባታችን የአቡነ አረጋዊ በዓለ ንግሥ ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የወንጌል ጉባኤ ላይ እንዲሳተፉና የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ በጻድቁ ስም መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
አዘጋጅ፦ የደብራችን ስብከተ ወንጌል እና የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት በጋራ።
እግዚአብሔር አምላክ ምሕረትንና እውነትን ስለ ወደደ፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም። የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በአንተ የታመነ ሰው ምስጉን ነው። መዝ ፹፫፥፲፩-፲፪በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🎤ከዚህ ቀደም በመዝሙር ክፍል ላገለገላችሁ አባላት በሙሉ!
በተለያዩ ጊዜያት በሰንበት ት/ቤታችን መዝሙር ክፍል ያገለገላችሁ ቀደምትና አሁንም ድረስ በማገልገል ላይ ያላችሁ አባላት በሙሉ የመዝሙር ክፍል አገልግሎትን ለማጠናከር ይረዳን ዘንድ የአስጠኚዎች የመዝሙር ጥናት በመደረግ ላይ ይገኛል። ስለዚህ ፍላጎቱና ጊዜው የሚያመቻችሁ አባላት በዚህ የአስጠኚዎች ጥናት ላይ እንድትሳተፉ ጥሪ እያቀረብን፤ የፊታችን ሰኞ ከ11:30 ጀምሮ መገኘት ትችላላችሁ፤ የበለጠ መረጃ የምትፈልጉ በስልክ ቁጥር +251919306262 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የመዝሙር ክፍል
