የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
Відкрити в Telegram
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Показати більше2 795
Підписники
+324 години
+47 днів
+2230 днів
Архів дописів
ሐናም ስትጸልይ እንዲህ አለች፦ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፥ቀንዴ በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤በማዳንኽ ደስ ብሎኛል። ፩ሳሙ ፪፥፩በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
+1
📢ለሁለተኛ ጊዜ የተለጠፈ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ
📜የሥራ ዘርፍ ዝርዝሮች:-
1. 💻የጽሕፈትና ጠቅላላ አገልግሎት ባለሙያ
2. 📚የቤተመጻሕፍት ባለሙያ
ዝርዝሩን በመመልከት በሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት ወይንም ከላይ በተጠቀሱት የቴልግራም አድራሻዎች በአስቸኳይ እንድታመለክቱ እናሳስባለን።
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅእንኳን ለታላቁ አባት ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዝቋላ ተራራ ባሕር ውስጥ መቶ ዓመት ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ምሕረት ለምነው ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ቃል ኪዳን ለተቀበሉበት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን! የሰማዕቱ እና የጻድቁ አባት አጭር የሕይወት ታሪክአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ደቡባዊ ግብፅ (ንሒሳ) ሲሆን፣ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ። ወላጆቻቸው ሠላሳ ዘመን ልጅ አጥተው ካለቀሱ በኋላ በመጋቢት 29 ቀን ፀንሶ በታኅሣሥ 29 ቀን ተወለዱ። ከተወለዱበት ቅጽበት ጀምሮ ተነሥተው
«ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ»ብለው አምላካቸውን ያመሰገኑ ሲሆን፤ የእናት ጡት ሳይጠቡና የዓለምን ምግብ ሳይመገቡ አድገዋል። በሦስት ዓመታቸው በሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል አማካኝነት ወደ ገዳም ተወስደው፣ በብፁዕ አባ ዘመደ ብርሃን ዘንድ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አጠናቀው ዲቁናን፣ ቅስናንና ምንኩስናን ተቀብለዋል። ከሰው ተለይተው ወደ ጫካ ሲገቡም ከራሳቸው እስከ እግራቸው ድረስ አንድ ክንድ ከስንዝር ርዝመት ያለው ፀጉር በቀለላቸው፤ ምንም ዓይነት ልብስ ሳይለብሱ በምድረ በዳ እንደ መላእክት ኖረዋል። ሰማያውያን ሁሉ ወዳጆቻቸው ሲሆኑ፣ 60 አንበሶችና 60 ነብሮች እየተከተሉ ያገለግሏቸው ነበር። የዝቋላ ተራራ ተጋድሎ እና የቃልኪዳን ርስት በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በዝቋላ ተራራ ባሕር ውስጥ ገብተው
«መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከዚህ ባሕር አልወጣም»ብለው መቶ ዓመት ሙሉ ተዘቅዝቀው ጸልዩ። ደማቸው ፈሶ ውኃውን እስከሚቀይረው፣ ሥጋቸው አልቆ አጥንቶቻቸው እንደበረዶ እስኪሆኑ ድረስ ተጋድለዋል። ሰይጣንና አጋንንት ቢፈትኗቸውም፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦላቸው
«መላ ኢትዮጵያን ምሬልሃለሁ፤ ስምህን የጠራውን፣ መታሰቢያህን ያደረገውን ሁሉ እምርልሃለሁ»የሚል ሰፊ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል። በተጨማሪም ወደ ዐረብ ሀገር ሄደው ወንጌልን በማስተማር፣ በመብረቅ የሞቱትን አራት መቶ ሺህ (400,000) ሰዎች በጸሎታቸው ከሞት አስነሥተው አጥምቀዋል። አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያ 262 ዓመት ጨምሮ በጠቅላላው 562 ዓመት በተጋድሎ ከኖሩ በኋላ ዐርፈው ሥጋቸው በመላእክት ክንፍ ተጭኖ በኢየሩሳሌም ተቀብሯል። የአባታችን የረድኤት በረከት ከእኛ ጋር ይሁን፤ በጸሎታቸው ይማረን! አሜን! 🙏

በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን!
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓዱ ኣምላክ ኣሜን፡፡
ብፁዕ ኣቡነ ሳዊሮስ
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ ኣስኪያጅ፤
ብፁዕ ኣቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና፤
ብፁዓን ኣበው ለቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት፣
የተከበራችሁ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያውና የየርጅቱ ኃላፊዎች
የተከበራችሁ የየኣህጉረ ስብከቱ ስራ ኣስኪያጆችና ተወካዮች
የኣዲስ ኣበባ ሀገረ ስብከት ኃላፊዎች፣ የየገዳማቱና ኣድባራቱ ኣስተዳዳሪዎች፣
በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኣጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የተገኛችሁ ክቡራንና ክቡራት በሙሉ!
ፍጥረቱን በትክክለኛ መርሕ የሚያስተዳድር እግዚአብሔር ኣምላክ ከኣራቱ መዓዝነ ዓለም ኣሰባስቦ በዚህ ቅዱስና ሓዋርያዊ ጉባኤ ስለ ሰበሰበን ክብርና ምስጋና ለእሱ ይሁን፤ እናንተም ወደ ቅድስት እናት ቤተ ክርስቲያን ማእከላዊ ጉባኤ እንኳን በደኅና መጣችሁ!
“ኲሉ ማዕምቅ ይምላእ፣ ወኲሉ ወግር ይተሓት ወኲሉ መብእስ ይኩን መጽያሕተ ርቱዐ፤ ወይርኣይ ኲሉ ዘነፍስ ኣድኅኖቶ ለእግዚአብሔር፡- ዓዘቅቱ ሁሉ ይሙላ፤ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሁን፤ ሸካራውም ይስተካከል፤ ሥጋዊም ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ (ሉቃ. 3፥6)
የዚህ ትምህርተ መለኮት መሠረታዊ መልእክት ትክክለኛ፣ ፍትሕንና እኩነልነትን በማኅበረ ሰብ መካከል ማረጋግጥ ነው፤
ፍትሕና እኩልነት ለሰው ልጅ ያላቸው ዋጋ፣ ከምግብ፣ ከመጠጥና ከልብስ ፍላጎት ያልተናነሰ ነው፤ የሰው ልጅ ደስታና የኅሊና ነጻነት የሚለካው ኣስተማማኝ በሆነ የፍትሕና የእኩነልነት ሃልዎት እንጂ በምግብ፣ በመጠጥና በልብስ ወይም በሃብት ብዛት አይደለም፤ ብዙ ሃብት ያላቸው ሰዎች ፍትሕንና እኩልነትን ካጡ፣ ኅሊናዊ ተሃውኮ ላይ ይወድቃሉ፤ ኑሮኣቸውም በእጅጉ ይረበሻል፤ ለሃብታቸውም ዋስትና እንደሌለው ስለሚረዱ ነገራቸው ሁሉ ይቃወሳል፣ ይናጋልም፡፡
ብፁዓን ኣበው ሊቃነ ጳጳሳት!
የተከበራችሁ እንግዶች!
ፍትሕና ርትዕ ለሰው ልጅ የተቃና ኑሮ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጡ ምርጥ ስጦታዎች ናቸው፤ ፍትሕና እኩልነት በሕግ የበላይነት ጥላ ሥር ሲውሉ ለሰው ኅሊና ፍጹም ነጻነትን ያጐናጽፋሉ፤ ሲዘነጉና ሲናቁ ግን ኑሮው የተመሰቃቀለና ተስፋ ቢስ የሆነ ማኅበረ ሰብ ይፈጠራል፤ ነገሩ ሲራዘም ደግሞ ግጭትን ይወልድና መጠፋፋትን ያስከትላል፤ ፍትሕና እኩነልነት የእግዚአብሔር ገንዘቦች እንደመሆናቸው መጠበቅና መከበር ያለባቸው በቤተ እግዚአብሔር ነው፤ “ፍትሑ ለነዳይ ወለዕጓለ ማውታ ወኣጽድቁ ግፉዐ ወምስኪነ” የሚለውን ትምህርት የምናገኘው በቤተ እግዚአብሔር ነውና፤
ይሁን እንጂ “በኣንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን” እያልን ኣንዱ ደብር የተራራ ያህል በሃብት የናጠ፣ ሌላኛው ደብር ደግሞ ሁሉን ኣጥቶ የተዘጋ ነው፤
በሰው ኃይል ኣስተዳደርም ኣንዱ ከበቂ በላይ ደመወዝ ሲያገኝ፣ ሌላው ድቃቂ ሳንቲም ኣጥቶ በችግር ይማቅቃል፤ በኣድልዎ፣ በጥቅም ትስስርና በብልሹ የሃብት ኣያያዝ የሚከሠተው ምዝበራ ሁሉ የፍትሕና የእኩልነት እጦት ውጤት ነው፤
እንደዚህ ዓይነቱ ብልሹ ኣሰራርን ካላረምን በቀር መልካም ኣስተዳደርን ማስፈንና ቤተ ክርስቲያንን ለቀጣዩ ትውልድ ማሸጋገር የማንወጣው ከባድ ዳገት ይሆንብናል፡፡
ብፁዓን ኣበው ሊቃነ ጳጳሳት
የተከበራችሁ እንግዶች!
የሰው ኃይል ኣስተዳደራችን ፈተና የበዛበት፣ ከፍ ያለው ዝቅ ይበል፤ ዝቅ ያለው ከፍ ይበል፤ የተጣመመው ቀጥ ይበል፤ ሰው ሁሉ የራሱን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ይመልከት ያለውን መለኮታዊ ኣስተምህሮ ወደ ጐን ስለ ተተወ ነው፤ በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያናችንና ልጆችዋ ካህናት እየተጐዱብን ነው፤ ለዚህም ያለ በቂ ምክንያት ከስራና ደመወዝ እየተፈናቀሉ እሮሮ የሚያሰሙ ካህናትና ሰራተኞች በርካታ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል በተፈጸመው የማፈናቀል ክሥተት ከተጐዱ ካህናት መካከልም እስካሁን ዕንባቸው ያልታበሰ ብዙ ናቸው፤ ችግሩም ሲቆም አይታይም፤ በየጊዜው ባለሥልጣን ይነሣል፤ ባለሥልጣን ይተካል፤ ችግሩ ግን ከመባባስ በቀር ምንም ዓይነት መሻሻል ኣይታይበትም፤ ለምን እንደዚህ ሆነ ብለን ብንጠይቅ፣ ችግሩ የቤተ ክርስቲያን ሳይሆን፣ እኛው ራሳችን ፍትሕንና እኩልነትን ለማስፈን ቊርጠኝነቱን ስላጣን ነው የሚል መልስ ያመዝናል፤ ከዚህ ሌላ ምንም ዓይነት ኣመክንዮ ሊቀርብለት ኣይችልም፤
ስለሆነም ይህ ጉባኤ የችግሩን ኣሳሳቢነት ግምት ውስጥ በማስገባት ፍትሕንና እኩልነትን፣ ሥርዓትንና የሕግ የበላይነትን ያረጋገጠ፣ ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን ያሰፈነ አሰራር የሚያዋልድ ኣቅጣጫ መቀየስ ይኖርበታል፤ ወጣ ገባውና ኣንዱ በይ ሌላው የበይ ተመልካች የሚያደርገውን እንደዚሁም ሐዋርያዊ ተልእኮን ያላስቀደመ ልማዳዊ ኣሰራር ማረም አለብን፤ በምትኩም በቴክኖሎጂ ሲስተም የታገዘና ሁሉንም በፍትሕ ፊት እኩል ኣድርጎ የሚያስተናግድ ኣሰራር በዚህ ዓመት ማረጋገጥ ይኖርብናል፤ ስለሆነም ይህ ጉባኤ ለዚህ ትክክለኛና ችግር ፈቺ ውሳኔ እንዲሰጥበት በኣጽንዖት እናሳስባለን፡፡
በመጨረሻም
ከኣራቱ መዓዝነ ዓለም የመጣችሁ የቤተ ክርስቲያናችን ኃላፊዎችና ተጠሪዎች የዘመኑን ፈተና ተቋቊማችሁ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝቡን በቅንነት ከማገልገላችሁም በላይ፣ ደጋ ወጥታችሁ፣ ቆላ ወርዳችሁ ያስገኛሁትን ውጤት በመያዝ በዚህ ጉባኤ መገኘታችሁን በኣድናቆት የምንመለከተውና ምስጋና የምንቸረው መሆኑን እየገለጽን እንኳን ደኅና መጣችሁ በማለት የሁለት ሺሕ ዓሥራ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተከፈተ መሆኑን እናበስራለን፡፡
እግዚአብሔር መልካም ጉባኤ ያድርግልን
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን!!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
ዘኣኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣
ጥቅምት 3 ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
የሐዘን ቤት የማጽናኛ መርሐግብር
በትላንትናው ዕለት ላረፉት ለዳዊት ብርሄኔ ቤተሰብ ዛሬ ጥቅምት 04/2019 ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ የማጽናኛ መርሐግብር ስለሚደረግ፤ የምትችሉ አባላት 43 ጂምናዚየም አካባቢ ተገኝተን በጉባኤው እንድንሳተፍ ቤተሰብንም እንድናጽናና በአክብሮት እናሳስባለን።
ትምህርት ክፍል
የሐዘን መግለጫ
የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆኑት የወንድማችን ኢ/ር ሮቤል አሰፋ እና የሙሉቀን አሰፋ አያት አርፈዋል። ሥርዓተ ቀብሩ ዛሬ ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም አየር ጤና አካባቢ በሚገኘው የረጲ መድኀኔዓለም ቤ/ክ ከቀኑ 8:00 ሰዓት የሚፈጸም በመሆኑ በቀብሩ ላይ መገኘት የምትችሉ ተገኝተን እንዲሁም በመኖሪያ ቤታቸው ወለቴ አካባቢ በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን። ነፍስ ይማርልን ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሐቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሐ (ኢዛና እና ሳይዛና) ከአባታቸው ንጉሥ ታዜር (ሠይፈ አርእድ) እና ከእናታቸው ሶፍያ (አህየዋ) የተወለዱ የብፅዓት ልጆች ናቸው። ወላጆቻቸው መካን ስለነበሩ ንግሥት ሶፍያ የካቲት 18 ቀን ሱባዔ ገብታ በጸሎትና በእንባ ፈጣሪዋን ለመነች። በሱባዔዋም መጨረሻ ረጅም ዛፍ፣ ሁለት መሰላሎች እና የወርቅ ዘንግ የያዘ ብርሃናዊ ሰው በራእይ አየች። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ተገልጾ ዛፏ ወንጌል፣ ተራራዋ ኢትዮጵያ፣ ዘንጓ ጥምቀት፣ ብርሃናዊው ሰው አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን፣ ሁለቱ መሰላሎች ደግሞ የምትወልዳቸው ልጆቿ መሆናቸውን ተረጎመላት። በዚሁ መሠረት ታኅሣሥ 29 ቀን በ312 ዓ.ም መንታ ልጆችን ወለደች። ሕፃናቱ ከተወለዱበት ቀን ጀምሮ እርስ በእርስ እየተባበሉና «የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን» እያሉ ያመሰግኑ ነበር፤ በአምስት ዓመታቸውም በብፅዓት መሠረት ወደ ቤተ መቅደስ ገቡ። በ12 ዓመታቸው አባታቸው ንጉሥ ታዜር በመሞቱ እና ልጆቹ መንትያ በመሆናቸው ማንን ማንገሥ እንዳለባቸው አሳሳቢ ሆነ። ነገር ግን ሕዝቡና ሊቀ ካህናቱ ፈቃደ እግዚአብሔርን በጸሎት ሲጠይቁ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጾ ሁለቱንም በአንድ መንበር እንዲያነግሡ አዘዘ። ሥመ መንግሥታቸውም ኢዛና እና ሳይዛና ተብሎ ነገሡ፤ ሀገሪቱንም በታላቅ ፍቅር፣ ፍትሕና ትሕትና መምራት ጀመሩ። ወጣቶቹ ነገሥታት ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ይጨነቁ ስለነበር፣ አባ ሰላማ (ፍሬምናጦስ) የትስብእትን ምስጢር ካስተማራቸው በኋላ የጥምቀትና የቁርባን ሥርዓትን ለማስፋፋት ሥልጣነ ክህነት ያስፈልግ ነበርና ወደ እስክንድርያው ፓትርያርክ ቅዱስ አትናቴዎስ ደብዳቤና ገጸ በረከት አስይዘው ላኩት። ቅዱስ አትናቴዎስም ፍሬምናጦስን «አቡነ ሰላማ» ብሎ ኤጲስ ቆጶስ አድርጎ ሾመው፤ ከመጻሕፍትና ከንዋያተ ቅዱሳት ጋርም ወደ ኢትዮጵያ ሰደደው። አቡነ ሰላማ ሲመለሱ የመጀመሪያው የጥምቀት ሥራ በነገሥታቱ ተከናወነ፤ ኢዛና «አብርሃ»፣ ሳይዛና «አጽብሐ» ተብለው ተሰየሙ። ቀጥሎም ሠራዊቱና ሕዝቡ ተጠምቀው ሥርዓተ ቁርባን ተፈጸመላቸው። ከዚህ በኋላ ጌታችን ተገልጾ ባሳያቸው ቦታ፣ ባሕሩ በተአምር ደርቆ በ24 የግሪክና የጢሮስ ጥበበኞች የአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ታነፀ፤ ይህ ታላቅ ሕንፃ ለ600 ዓመታት አገልግሎ በ10ኛው ክፍለ ዘመን በዮዲት ጉዲት ተቃጥሏል። ቅዱሳን ነገሥታቱ በየክፍለ ሀገሩ (በወሎ፣ በሸዋ፣ በከፋ፣ በሰላሌ፣ በጎጃም እና በጎንደር) እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክ 154 አብያተ ክርስቲያናትን ያነጹ ሲሆን፣ አብርሃ በ374 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን፣ አጽብሐ ደግሞ በ379 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን አርፈው ቀስተ ደመና በመቃብራቸው ላይ ተተክሏል። እግዚአብሔር አምላክም ዝክራቸውን ለዘከረና በስማቸው ለተመጸወተ ታላቅ የመንግሥተ ሰማያት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል። የቅዱሳን ረድኤታቸው፣ በረከታቸውና አማላጅነታቸው አይለየን፤አሜን!!!
በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን!
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የሐዘን መግለጫ
የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የወንድማችን ዳዊት ብርሃኑ ወንድም አርፏል። ሥርዓተ ቀብሩ ዛሬ ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም በቀጨኔ መድኀኔዓለም ቤ/ክ ከቀኑ 5:00-6:00 ሰዓት የሚፈጸም በመሆኑ በቀብሩ ላይ መገኘት የምትችሉ ተገኝተን እንዲሁም በመኖሪያ ቤታቸው 43 ቀበሌ ጂምናዚየምን አለፍ ብሎ ከረዮ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን። የወንድማችንን ነፍስ ይማርልን ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫጥቅምት ሦስት በዚህች ዕለት ከመጽሐፈ ሰዓታት ውጭ እጅግ ብዙ ድርሰቶችን የደረሰ ፈላስፋም ጻዲቅም ደራሲም መናኝ ባሕታዊም የሆነ ድርሰቶቹንም ለቅዱሳን በነፋስ ጭኖ ይልክላቸው የነበረ የቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ኩራት ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በዓለ ፅንሰቱ ነው፡፡አባታችን ጥቅምት ሦስት ቀን ፲፫፻፶፯ ዓም ተፀንሰው ሐምሌ ፯ ቀን ዕለተ ማክሰኞ ተወለዱ። አባ ጊዮርጊስ ነገረ ሃይማኖትን ጠንቅቆ የተረዳና የሚያስረዳ ስለነበር በዘመኑ የተነሡ የሃይማኖት ክርክሮች ሁሉ እርሱ ከሌለ አይሳኩም ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ በሸዋ በይፋት ራሳቸውን ቤተ እስራኤል እያሉ የሚጠሩ አይሁድ ነበሩ፡፡ ከአቡነ ዜና ማርቆስ ጀምሮ ብዙ መምህራን ወደነዚህ ሕዝቦች እየተሠማሩ ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ክርስትና ለተመለሱት ቤተ እስራኤላውያን በእመቤታችን፣ በቅዱስ ሚካኤል፣ በአባ ኖብና በሰማዕቱ በጊጋር ስም አራት አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተው ነበር፡፡ ሁለቱ የመጀመሪያዎቹ አሁንም አሉ፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም ቤተ እስራኤላውያኑ ሙሉ በሙሉ ወደ ክርስትና አልተመለሱም ነበር፡፡ ከእነዚህ አይሁድ መካከል አንዱ ከክርስቲያኖች ጋር በነገረ ሃይማኖት ለመከራከር ጥሪ አቀረበ፡፡ “ክርስቲያኖች ከረቱኝ ወደነርሱ ሃይማኖት እገባለሁ እኔ ከረታኋቸውም ወደኔ ሃይማኖት ይገባሉ” ሲል ነገሩን ጥብቅ አደረገው፡፡ ዐፄ ዳዊት ይህን ጉዳይ ሲሰማ በጣም ስለ ተናደደ ሊቃነ ካህናቱን፣ ንቡራነ እዱንና የመጻሕፍት ዐዋቂዎችን ሁሉ ከየሀገሩ እንዲሰባሰቡ አዘዘ፡፡ አይሁዳዊው በአንድ ወገን መምህራኑ በአንድ ወገን ሆነው ክርክሩን ጀመሩ፡፡ የመጀመርያው እድል የተሰጠው ለአይሁዳዊው በመሆኑ ቀጥሎ ያለውን ጥያቄ አቀረበ፡- “እናንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የምትሉት ይሄ ክርስቶስ እውነት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፣ ወደ ቢታንያ በመጣ ጊዜ አልዓዛር የተቀበረበትን ቦታ ሳያውቅ ቀርቶ ''አልዓዛርን የት ቀበራችሁት?” ብሎ እንደ ጠየቀ በወንጌላችሁ ተጽፏል፡፡ ለዚህ መልስ ስጡኝ፣ እኔንም ከመጽሐፈ ኦሪቴ ጠቅሳችሁ ጠይቁኝ?” ሲል የመከራከርያ ነጥቡን አቀረበ፡፡ በዚህ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ ታሞ አልጋ ላይ ነበር፡፡ ሊቃውንቱም “እንዲህ ያለው ነገር ያለ እርሱ አይሆንምና አባ ጊዮርጊስ ይምጣ” ሲሉ ለዐፄ ዳዊት ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አባ ጊዮርጊስም በአልጋ ላይ እያለ እንዲመጣ ተደረገ፡፡ በአልጋ ላይ ሆኖም በጉባኤው ላይ ተገኘ፡፡ ጉባኤተኞቹ የቀረበውን ጥያቄ ነገሩት፡፡ አባ ጊዮርጊስ የሰጠውን መልስ ገድሉ በሚከተለው መንገድ ይገልጥልናል “እኔ ግን በወንጌል ሳይሆን በኦሪት እከራከርሃለሁ፡፡ የምኩራብ መጻሕፍት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን የታወቁ ናቸውና፡፡ ምኩራብ ዘራች ቤተ ክርስቲያንም አጨደችው፤ ምኩራብ ፈተለችው ቤተ ክርስቲያን ለበሰችው፤ አዳምን በገነት ሳለ አዳም ሆይ ወዴት ነህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? አብርሃምንስ ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? ብሎ የጠየቀው ማነው? እስቲ መልስልኝ? ሰይጣንንስ ከወዴት መጣህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? እግዚአብሔር አብ አይደለምን?” በዚህ ጊዜ አይሁዳዊው መልስ አጥቶ ዝም አለ፡፡ ንጉሡ፣ ሊቃውንቱና መኳንንቱም እጅግ ተደሰቱ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ሌላው ያጋጠመው ክርክር ቢቱ ከተባለው ሰው ጋር ያደረገው ክርክር ነበር፡፡ ቢቱ “በምጽአት ጊዜ የሚመጣው ወልድ ብቻውን እንጂ አብና መንፈስ ቅዱስ አይመጡም” የሚል ኑፋቄ ማስተማር ጀምሮ ነበር፡፡ ቢቱ ከዚህ ኑፋቄው በተጨማሪ የጥንቆላ ሥራም ይሠራ ነበር፡፡ ቢቱ በጥንቆላ ሥራው የተነሣ በቤተ መንግሥቱ ተቀባይነት የነበረው ሰው እንደ ነበረ ገድሉ ይናገራል፡፡ ይህን መሰሉን ተግባር አጥብቆ የተዋጋው ዘርዐ ያዕቆብ እስኪመጣ ድረስ ነገሥታቱ ምንም ክርስቲያኖች ቢሆኑ በዚህ መሰሉ ስንኩል ሕፀፅ ይዋጡ ነበር፡፡ ቢቱና አባ ጊዮርጊስ ወደ ንጉሥ ዳዊት ቀርበው በጉዳዩ ላይ መነጋገር እንደሚፈልጉ ገለጡ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ጳጳሱና ሊቃውንቱ ባሉበት እንዲነጋገሩ ስለ ወሰነ ጳጳሱ እንዲመጡ አዘዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ተንኮለኛው ቢቱ ከአባ ጊዮርጊስ ጋር ከተከራከረ እንደሚረታ ስላወቀ “ንጉሡ የአባቶቻችንን ሃይማኖት ክዷልና አትምጣ” የሚል ደብዳቤ በአባ ጊዮርጊስ ስም ጽፎ ጳጳሱን ሊጠሩ በሄዱት መልእክተኞች እጅ ላከ፡፡ ወድያውም ለዐፄ ዳዊት ይህንን ነገር አሳበቀ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ፈጣን መልእክተኞች ልኮ የፊተኞቹ መልእክተኞች እንዲመለሱ አደረገና ደብዳቤው ተነበበ፡፡ የቢቱ ተንኮል ያልገባው ንጉሥ ዳዊት ይህን ደብዳቤ ሲመለከት አባ ጊዮርጊስን በደም አበላ እስኪነከር ድረስ እንዲደበደብ አድርጎ ወደ እስር ቤት አስገባው፡፡ ዐፄ ዳዊት እስኪሞትና ልጁ ቴዎድሮስ እስኪነግሥ ድረስም በዚያ ቆየ፡፡ ቢቱ ግን በመልአክ ተቀስፎ ሞተ፡፡ የአባታችን የጻድቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ረድኤት አይለየን!!
በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን!
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን!
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
ሊቁ ቅዱስ አባ ሕርያቆስ
" እግዚአብሔር አብ በሰማይ ሆኖ ምሥራቅንና ምዕራብን ሰሜንንና ደቡብን ዳርቻዎችንም ሁሉ በእውነት ተመለከተ ተነፈሰ አሻተተም እንደ አንቺ ያለ አላገኘም የአንቺን መዓዛ ወደደ ደም ግባትሽንም ወደደ የሚወደውን ልጁንም ወደ አንቺ ሰደደ።"ክርስቲያን ሆኖ እመቤታችንን የሚወድ ሰው ሁሉ ይህንን አባት ያውቀዋል። አባ ሕርያቆስ ተወልዶ ያደገው በምድረ ግብጽ ሲሆን አካባቢው ብህንሳ (ንሒሳ) ይባላል። ይህቺ ቦታ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳንን ያፈራች ናት። አባ ሕርያቆስን በዚህ ዘመን ነበረ ተብሎ ትክክለኛውን ዓ/ም ለመናገር ይከብዳል። ከቤተ ክርስቲያን ትውፊት መረዳት እንደሚቻለው ግን የነበረበት ዘመን 4ኛው ወይም 5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደ ሆነ መገመት ይቻላል። ቅዱሱ በዘመኑ የተለየ ማንነት የነበረው ሰው ነው። ገና ከልጅነቱ እመ ብርሃንን የሚወዳት በመሆኑ ቅን የዋህና ገራገር ነበረ። መቼም እመቤታችን ይወዳል ሲባል እንደ ዘመኑ በአፍ ብቻ እንዳይመስለን። ቀንና ሌሊት ለፍቅሯ የሚተጋ ማዕበለ ፍቅሯ የሚያማታው ሰው ነበር እንጂ። የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ስም ሲጠራ ምስጥ ብሎ ልቡናው ይሰወርበት ነበር ዘወትር የእርሷን ፍቅር ከማሰብ በቀር ሌላ ሥራ አልነበረውም። የልጅነት ጊዜው ሲያልፍም ድንግልንና ቸር ልጇን ያገለግል ዘንድ መነነ። ዘመኑ ዘመነ ሊቃውንት እንደ መሆኑ ሁሉም ለትምሕርት ሲተጉ እርሱ ግን ለጸሎትና ለደግነት ብቻ ነበር የሚተጋው። ከትምሕርት ወገንም የሰሞን ጉዋዞችን አንዳንድ ቅዳሴያትንና የዳዊትን መዝሙር ተምሮ ነበር። በተለይ ግን የዳዊትን መዝሙር እየጣፈጠው መላልሶ መላልሶ ያመሰግንበት ነበር። ከዳዊት መካከል ደግሞ መዝሙር 44ን ፈጽሞ ይወዳት ነበር። ይህቺ ጥቅስ የምትጀምረው
"ጐስዐ ልብየ ቃለ ሠናየ"ብላ ነው። የውስጧ ምሥጢርም ስለ ድንግል ማርያምና ስለ ክርስቶስ ነው። አባ ሕርያቆስ ይህቺን መዝሙር በቃሉ አጥንቶ? ቁሞም ተቀምጦም ተኝቶም ተነስቶም ያለ ማቁዋረጥ ይላት ነበር። እየጣፈጠችው
"ልቡናየ በጐ ነገርን አወጣ"እያለ ይዘምር ነበር። በወቅቱ ታዲያ የብህንሳ ኤዺስ ቆዾስ በማረፉ ምትክ ሲያፈላልጉ መንፈስ ቅዱስ አባ ሕርያቆስን መረጠ። ምንም አለመማሩ ቢያሰጋችቸውም 'በጸሎቱ በደግነቱ ሃገር ይጠብቃል' ብለው ሾሙት ነገር ግን ምንም በሥልጣን የበላያቸው ቢሆን ተማርን የሚሉ ሰዎች ይጠሉት ይንቁትም ነበር። እርሱ ግን እንደ ጠሉኝ ልጥላቸው እንደ ናቁኝ ልናቃቸው ሳይል በፍቅር ያገለግል ነበር። አንድ ቀን ታዲያ መንገድ ይወጣል:: በበርሃ ብቻውን እየተራመደ "ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" እያለ እየዘመረ ተመሥጦ ቢመጣበት መንገድ ሳተ። እርሱ በምስጋናው ሲደሰት እግሩ ግን ከገደል ጫፍ ደርሶ ነበር። ገደሉን ልብ አላለውም ነበርና ሳይታወቀው ወደ ገደሉ ውስጥ ተወረወረ። በዚህ ጊዜ ደንግጦ ቢመለከት እጅግ ጥልቅ በሆነ ገደል ውስጥ ራሱን አገኘው። ነገር ግን አንድም አካሉ አልተነካም። ልብሱም አልቆሸሸም። ለራሱ ተገርሞ ዙሪያ ገባውን ሲመለከት እርሱ ቁጭ ያለበት ብርሃንን የተሞላ የልብስ ዘርፍ ነበር። "እመ ብርሃን" ብሎ ሲጮህ የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነች እመቤታችን ከፊቱ ቁማ ታየችው። እመ አምላክን በገሃድ ቢያያት እንደ እንቦሳ ዘለለ። የሚገርመው ደግሞ የተቀመጠበት የድንግል ማርያም የቀሚሷ ዘርፍ ነበር። እመቤታችን አነጋገረችው ባረከችው። ፍቅሯ ቢመስጠው ከሰው ሳይገናኝ ምግብም ሳይበላ እዚያው ገደሉ ውስጥ ለ1 ዓመት ያህል በተመስጦ ቆይቷል። በሁዋላ እመ ብርሃን መጥታ ከገደሉ አውጥታ ወደ ሐገሩ መለሰችው። ከጥቂት ጊዜ በሁዋላም አንድ ፈተና ገጠመው። አንድ ቀን እመቤታችን በተወለደችበት ግንቦት 1 ቀን ቅዳሴ 'ማን ይቀድስ' ሲባል ሰዎቹ 'አባ ሕርያቆስ ይሁን' አሉ። እርሱ ግን "እኔ አይቻለኝም እናንተ ሊቃውንት ቀድሱ" አላቸው። "አይሆንም"ብለው እርሱኑ አስገቡት። ይህንን ያደረጉት ለተንኮል ነበር። ልክ ወንጌል ተነቦ ፍሬ ቅዳሴ ሲመረጥ እርሱ "እግዚእን (የጌታ ቅዳሴን) ልቀድስ" ቢል እነርሱ "የሚቀደሰው የሊቅ ቅዳሴ ነው" አሉት። ይህንን ያሉት እርሱ የሊቃውንቱን ቅዳሴ አያውቅምና በሰው ፊት እንዲዋረድ ነው። እንዲህም ብለው ባለመማሩ ተሳለቁበት። አባ ሕርያቆስ ግን እያዘነ ወደ መንበሩ ዞረ። ድንግልንም "እመቤቴ መናቄን መገፋቴን ተመልከች" አላት። ወዲያው ግን ድንግል ማርያም ወርዳ ቀጸበችው (ጠራችው)። በዘርፋፋው ቀሚሷ ላይም ረቂቅ የሆነ ቅዳሴን አሳየችው። ደጉ ሰው ደስ ብሎት
"ጐሥዐ ልብየ" ሲል 2ቱ እግሮቹ ከመሬት ከፍ አሉ። እርሱም "ወአነ አየድእ ቅዳሴሃ ለማርያም" ብሎ እስከ ኃዳፌ ነፍሱ ድረስ አደረሰው።ሕዝቡና ካህናቱ በሆነው ነገር ሲደነቁ አንዳንዶቹ "ዝም ብሎ ነው የቀባጠረ" አሉ። ቅዱሱ ግን ቅዳሴ ማርያምን በብራና ጠርዞ በሕዝቡ መካከል ድውይ ፈወሰበት። እሳት ሳያቃጥለው: ውሃ ሳይደመስሰው ቀረ። መጽሐፈ ቅዳሴው ሙትንም አስነስቷል። ከዚህች ሰዓት ጀምሮ በዘመኑ ቁጥር 1 ሊቅም ሆነ። ብዙ መጻሕፍትን ሲተረጉም አጠቃላይ ድርሰቶቹም እልፍ (10,000) ናቸው። ሊቁ እንዲህ በንጹሕ ተመላልሶ ዐርፏል። ይህቺ ቀን ለቅዱሱ የልደቱና ዕረፍቱ መታሰቢያ ናት። አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ጣዕሟን ፍቅሯን ያሳድርብን🙏🙏 የቅዱሳን ረድኤት በረከት በሁላችንም ላይ ይደር!!