cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

ይህ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ልሳን ነው።

Show more
Advertising posts
7 272
Subscribers
+724 hours
+167 days
+18730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

03:12
Video unavailableShow in Telegram
Video from Menkir
Show all...
Show all...
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሚዲያ ሰ/ት/ቤቶች ከ500 ሺህ ነድያን ጋር በበዓለ ትንሣኤ

✍️YouTube 👇

https://www.youtube.com/channel/UC83L...

✍️ FaceBook 👇

https://www.facebook.com/EOTC.GSSU

✍️Telegram 👇

https://t.me/EOTCNSSU

✍️Website👇

https://eotc-gssu.org/a/

✍️Twitter👇

https://twitter.com/tibeb_felege

“በእምነት ትንሣኤ፣ በአምልኮተ እግዚአብሔር ትንሣኤ፣ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ትንሣኤ፣ በፍቅር ትንሣኤ፣ በሰላም ትንሣኤ፣ በይቅርታ ትንሣኤ፣ በመከባበር ትንሣኤ፣ በአንድነት ትንሣኤ፣ በመተሳሰብ ትንሣኤ ወዘተ በመሳሰሉ ሃይማኖታዊና ግብረ ገባዊነት ጸንተን መኖር ከቻልን የፊተኛው ትንሣኤ ማለት እሱ ነው፡፡ “    ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ #ቃለ_በረከት_ዘብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወስድስቱ ዓመተ ምሕረት፡፡ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤ በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ፡- የትንሣኤ ሙታን በኲር በመሆን ቀድሞ የተነሣው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ! “ወይእዜኒ ክርስቶስ ቀደመ ተንሥኦ እምኲሎሙ ሰብእ ሙታን@ አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኲር ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል” (1 ቆሮ 05.!) በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት የሚከበረው የጌታችን ትንሣኤ ለሰው ልጅ ያለው መንፈሳዊ ትርጉም እጅግ የላቀ ነው፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን በሙሉ በተለይም የሰው ልጅን ሲፈጥር በፍጹም ፍቅር ነው፡፡ ለዚህም የሰው በአርአያ እግዚአብሔር መፈጠር በቂ ማስረጃ ነው፤ ሰው በበደሉ ምክንያት ለሞት ቢዳረግም የእግዚአብሔር ፍጹም ፍቅር ጨርሶ አልተለየውም፤ እግዚአብሔር አንድ ቀን ሞትን ከሰው ጫንቃ አሽቀንጥሮ እንደሚጥል በየጊዜው ይገልጽ ነበረ፤ ያም በራሱ ልዩ ጥበብ እንደሚከናወን አረጋግጦ ለሰው ልጅ ተስፋውን አሳውቆ ነበር፤ ያም ልዩ ጥበብ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ዕውቀትና ጥበብ ድንበር የለውምና ከፍጥረተ ዓለም በፊት ሳይቀር የሰው ድኅነት በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እንደሚፈጸም በእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ነገር ነበረ፤ ጊዜው ሲደርስም በህላዌና በክዋኔ ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ እግዚአብሐር ወልድ የሰውን ሰውነት ተዋሕዶ ሰውን የማዳን ስራውን አንድ ብሎ ጀመረ፡፡ ሰዎች በኃጢአትና በዲያብሎስ በደዌና በሞት ላይ ሥልጣን ያለው አዳኝ እሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ የማዳን ስራውን በመዋዕለ ሥጋዌው በስፋት አከናወነ፡፡ ልዩ ልዩ ደዌና በሽታ የሚያሠቃያቸውን ፈወሰ፤ ኃጢአተኞችን በይቅርታ ተቀበለ፤ ኃጢአታቸውንም ደመሰሰ፤ አጋንንትንም በትእዛዝ አስወጣ፤ ወደ ጥልቁም አሰመጣቸው፤ ዲያብሎስንም ድል ነሥቶ አባረረ፤ ሙታንንም አነሣ፤ በባሕር ላይ በእግሩ ተራመደ፤ ነፋሳትን ገሠጸ፤ በአምስት እንጀራ ከአምስት ሺሕ ሕዝብ በላይ መገበ፤ ውሀውንም ወደ ጠጅ ለወጠ፡፡ ሰውን ሁሉ በፍቅርና በይቅርታ ይቀበልና ያገለግል ነበር እንጂ በአንዱ ስንኳ የመጨከንና የማግለል መንፈስ አላሳየም፤ ይህ ሁሉ ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፍቅር ማሳያ ነበረ፡፡ በፍጥረት ሁሉ ላይ መለኮታዊ ሥልጣን እንዳለውም ማረጋገጫ ነበረ፤ መልእክቱም ዓለም መዳኛዋና አዳኝዋ እሱ መሆኑን አውቃ በአእምሮ እንድትከተለውና የድኅነቱ ተቋዳሽ እንድትሆን ማስቻል ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! በእግዚአብሔር አሠራር ኃጢአት ያለ ቤዛነት አይሰረይም፤ በመሆኑም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ኃጢአተኛ ሆኖ ስለተገኘ ቤዛ ሆኖ የሚያድነው ያስፈልገው ነበር፤ ቤዛ መሆን የሚችለው አካል ደግሞ ራሱ ፍጹም ንጹህ መሆን ነበረበት፡፡ ከዚህም አንጻር በእግዚአብሔር ፊት ለሱ የሚመጥን ንጹህ ኣካል ከፍጡራን ወገን አልተገኘምና እሱ ራሱ ሰው ሆኖ የሰው ቤዛ ለመሆን በሥጋ ተገለጠ፤ በዚህም መሠረት የሰው ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ በመሰቀል ንጹህ ደሙን አፈሰሰ፤ በዚህ ደም ምክንያት የሰው ኃጢአት በሥርየት ተዘጋ፤ ለዚህም ነው ቅዱስ መጽሐፍ “ያለ ደም ሥርየት ወይም ይቅርታ የለም” ብሎ የሚነግረን፡፡ ከዚህ ደም መፍሰስ በኋላ ወደ ሲኦል ወርዶ በዚያ የነበሩ የኃጢአት ግዞተኞችን በሙሉ ፈትቶ ወደ ቀደመ ስፍራቸው ወደ ገነት መለሰ፤ ከስቅለተ ክርስቶስ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ያለው የሰው ኃጢአት በሙሉ በክርስቶስ ደም ይደመሰሳል፡፡ ሆኖም ይህ ሥርየት የሚገኘው በእምነት መሆኑን ቅዱስ መጽሐፍ አበክሮ ይነግረናል፣ በክርስቶስ አምኖ በደሙ የነጻ ሁሉ ክርስቶስ በተነሣው ዓይነት ትንሣኤ ይነሣል፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! የጌታችንን ትንሣኤ ስናከብር የኛንም ትንሣኤ በማሰብ ሊሆን ይገባል፤ ትልቁ ነገርም የኛን ትንሣኤ ማሰቡ ላይ ነው፤ ምክንያቱም የክርስቶስ ትንሣኤ ለኛ ተብሎ የተደረገ በመሆኑ ነው፡፡ የሱ ትንሣኤ ለኛ ትንሣኤ በኲር ነው፤ ማሳያና ማረጋገጫም ነው፤ እግዚአብሔር በየዕለቱ የሚፈልገው የኛን ትንሣኤ ማየት ነው፤ የኛ ትንሣኤ በአንድ ቀን በቅፅበት የሚሆን አይደለም፤ ትንሣኤያችን አምነን ስንጠመቅ ተጀምሮ ከመቃብር ስንነሣ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ እግዚአብሔር ዛሬም እያንዳንዱ ሰው በትንሣኤ ሕይወት እንዲመላለስ ይጠራል፤ ምክንያቱም የኋለኛው ትንሣኤ የሚገኘው በፊተኛው ትንሣኤ እንደሆነ እግዚአብሔር በመጽሓፉ ነግሮናልና ነው፤ በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕ ነው፤ በሱ ላይ ሞት ሥልጣን የለውምና ነው፤ ለሰው ልጆች ተጠብቆልን ያለው ተስፋ ይህ ነው፡፡ ተስፋውን እውን ማድረግ የሚቻለውም በኛ ሃይማኖታዊና ተግባራዊ ተሳትፎ እንደዚሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ ደም ነው፤ የነገውን ትንሣኤ ተሳታፊ ለመሆን ዛሬ መነሣት ግድ ይላል፤ ይህም የሚቻል እንጂ የማይቻል አይደለም፡፡ በእምነት ትንሣኤ፣ በአምልኮተ እግዚአብሔር ትንሣኤ፣ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ትንሣኤ፣ በፍቅር ትንሣኤ፣ በሰላም ትንሣኤ፣ በይቅርታ ትንሣኤ፣ በመከባበር ትንሣኤ፣ በአንድነት ትንሣኤ፣ በመተሳሰብ ትንሣኤ ወዘተ በመሳሰሉ ሃይማኖታዊና ግብረ ገባዊነት ጸንተን መኖር ከቻልን የፊተኛው ትንሣኤ ማለት እሱ ነው፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር እያንዳንዳችን ይህንን ትንሣኤ እውን አድርገን ስንኖርና ስንመላለስ ማየት ይፈልጋል፡፡ በአንጻሩም ክሕደትን፣ ከሕገ ተፈጥሮ ያፈነገጠ ጸያፍ ተግባርን፣ ጥላቻን፣ ጦርነትን፣ መለያየትን፣ ራስን ብቻ መውደድን፣ መጨካከንን፣ ግብረ ኃጢአትን፣ ፈሪሐ እግዚአብሔር ገንዘብ አለማድረግን፣ ፈጣሪን አለማመንን የተጸየፈ ምእመንን ማየት ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ኃጣውእ አፅራረ ትንሣኤ ናቸውና ነው፤ ኃጣውእ በምድርም በሰማይም የሰው ጠላቶች ናቸው፤ በምድር ለሥጋዊና መንፈሳዊ በሽታ ይዳርጉናል፡፡ በተለይም በእግዚአብሔር ፊት እጅግ አስጸያፊ የሆነው የነውረ ኃጢአት ርኲሰትና በጋብቻ ያልታሰረ ሩካቤ ሥጋ ትውልድን እንደ ቅጠል እያረገፈው እንደሆነ፣ ምንም ዓይነት ፈውስ ላልተገኘለት የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ ዋነኛ መተላፊያም ይህ ነውረ ኃጢአት እንደሆነ ተደጋግሞ ተነግሮአል፡፡ ይሁንና አሁንም ጥንቃቄ በጎደለው ድርጊት ስሕተቱ በመቀጠሉ በጦርነት ከሚያልቀው ሕዝብ ባልተናነሰ በዚህ ገዳይ በሽታ ብዙ ወገን እያለቀ ነውና እባካችሁ ሕዝበ እግዚአብሔር አንድ ለአንድ በመተሣሰርና በተቀደሰ የጋብቻ ሕይወት በመወሰን ትንሣኤያችንን እናብስር፡፡
Show all...
በመጨረሻም በዓለ ትንሣኤ የእግዚብሔር ፍቅር መገለጫና የተስፋችን ማሳያ መሆኑን በመገንዘብ ለእግዚአብሔር ክብርና ለሰው ልጆች ደኅንነት በአንድነት በመቆም ለተራቡት፣ ለተጠሙት፣ ለታረዙት፣ ለታመሙትና ለታሰሩትም ሁሉ ካለን ከፍለን በመስጠት ከኛ ጋራ በመንፈስና በሞራል በዓለ ትንሣኤውን እንዲያሳልፉ እናደርግ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን። በድጋሚ በዓሉን የሰላም የዕርቅ የይቅርታ የትንሣኤ ኅሊና ወልቡና ያድርግልን፤   እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን። አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሚያዝያ 27 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
Show all...
የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ በትናንትናው ዕለት ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚገኙ አሳውቀን ነበር። በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን እየገለጽን፣ በሂደቱ ጉዳዩን በመረዳት አፋጣኝ ምላሽ የሰጡንን የመንግሥት የጸጥታ አካላት እናመሰግናለን። በተጨማሪም በትዕግሥት ስትከታተሉና በጸሎት ስታስቡ ለነበራችሁ አባቶች፣ ምእመናን እና የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እያመሰገንን፣ በዓሉ የሰላምና የበረከት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ማኅበረ ቅዱሳን!
Show all...
ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድን ጨምሮ ሁለት የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ታሠሩ ! ሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) በቅርቡ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተመደቡት ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12:00 በፌዴራል ፖሊስ ለጥያቄ ይፈለጋሉ በሚል ከቤታቸው ተወስደው መታሠራቸውን ቤተሰቦቻቸው ለሚዲያችን ገልጸዋል። በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ ኦርትዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ዘግቧል። ምንጭ: ተዋሕዶ ሚዲያ
Show all...
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸው ታውቋል። የሁለቱ አገልጋዮች መኖሪያ ቤት መፈተሹም ተገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌዴራል ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚገኙ ሲሆን የተያዙበት ምክንያት አልታወቀም። ዝርዝር እንደደረሰን እናቀርባለን።
Show all...
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ቤቶች አንድነት አስተባባሪነት በከተማዋ በሚገኙ ሁሉም አጥቢያዎች ሥር በሚገኙ ሰ/ት/ቤቶች አማካኝነት ለትንሣኤ በዓል ከ500,000 (ከአምስት መቶ ሺህ) በላይ ነዳያንን የማስፈሰክ መርሐግብር እንዲሁም በሕመም ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን የመድኃኒት መግዣ ድጋፍ ይደረጋል። #እርስዎም_በአቅራቢያዎት_በሚገኝ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የአቅምዎን_አስተዋጽኦ_ይለግሱ_ዘንድ_በልዑል_እግዚአብሔር_ስም_እንማጸናለን!!! ♦ከአዲስ አበባ በርቀት ላሉ እንዲሁም በማዕከል ለብዙኃን ሰንበት ት/ቤት መርዳት ለሚፈልግ ከታች የሒሳብ ቁጥራቸው በተቀመጠ ለዚሁ በተዋቀረው የኮሚቴ አባላት ስም በተከፈተው አካውንት ገቢ ማድረግ  ይቻላል። አሐዱ ባንክ  0044214310101 አቢሲኒያ ባንክ 176437219 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 100060669296 ለሁሉም የሒሳብ ቁጥር ስም ጥላዬ እሸቱ ፣ ቤተልሔም ካሳዬ እና ዘነበ ክፍሉ በሚለው ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። https://www.wegenfund.com/causes/tinsae-ke-nedayan-gar ለበለጠ መረጃ 📞 0911653462                       📞0911674308 #እኔ_ከወገኖቼ_ጎን_እቆማለሁ! #እርስዎስ??? የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
Show all...