ከሥድስት ቀናት ቀደም ብሎ በፌስቡክ የማውቃት አንዲት እህት ከታች የተጫነውን ቪዲዮ ላከችልኝ። የምትመለከቷቸው አባት ሙዘሚል ያሲን ይባላሉ። አዲስ አበባ ሳሪስ አዲስ ሰፈር የሚገኘው የሒክማ መስጅድ እርግብ ናቸው። የዒሻን ሶላት ሰግደው ከጨረሱ በኋላ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ መንገድ ላይ ሁሌም የመካ እና የመዲና ናፍቆት ውስጣቸውን ይንጠዋል። የተባረከውን ቅዱስ ምድር ለመመልከት ለዓመታት የጓጓው ዓይናቸው ዛሬም ከሀበሻ ምድር ላይ ሆኖ በርቀት ያማትራል።
የተዘየነው ፣ የተዘየነው
መካ መዲናን ምን ነው ባየነው
የተዘየነው ፣ የዘገየ ነው
መካ መዲናን ምን ነው ባየነው
እያሉ በናፍቆት አለንጋ ይገረፋሉ። ሁሌም እንዲህ ሲያቀነቅኑ የተመለከተች አንዲት ክርስቲያን ወገናችን «ፈጣሪ ዕድል ሰጥቶኝ የሚመኙት አገር ብወስዳቸው ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር» ማለቷን ቪዲዮውን የላከችልኝ እህት ነግራኛለች።
የነብዩ ሙሐመድን የትውልድ ቀዬ እና ክቡር አካላቸው ያረፈበትን የመዲና መንደር ለማዬት በናፍቆት የተንገበገቡትን አባት ህልማቸው እውን እንዲሆን ስለምሻ ዑምራ እንዲያደርጉ በጋራ እንድንረባረብ ጥሪ አቀርብላችኋለሁ። ለጉዞ ፣ በመካ እና መዲና ለሚኖራቸው ቆይታ እና ለእጃቸው የሚሆን 200,000 ብር ለመሰብሰብ ዕቅድ አለኝ። በዚህ በጎ ተግባር መሳተፍ እና ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ ሁሉ ኮሜንት ማስቀመጫ ሳጥኑ ላይ ፍጋፍ የማድረግ ፍላጎታችሁን በማሳወቅ በግል ልታነጋግሩኝ ትችላላችሁ።
☎ በአገራችን ሰማይ ላይ ያንዣበበው አስፈሪ ድባብ ተገፎ በሰላምና በፍቅር የምንኖርበትን ሁኔታ አላህ ይፍጠርልን - አሚን
http://t.me/abuafnanmoh
Show more ...
Mohammed Ahmed Official
የዩቲዩብ 👉 youtube.com/@gharuhira
በግል ጥያቄ እና አስተያየት ካላቹህ 👉 @afhasmen